በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ እምድብር ከተማ ላይ የፋሲካ ማግስት ማታ የደቡብ ክልል ልዩ ሀይሎች ከከተማው ወጣቶች ጋር ግጭት ውስጥ ገቡ።
በፋሲካ ማግስት አምሽተው ወደ ቤታቸው በመግባት ላይ ከነበሩ ወጣቶች ከወልቂጤ—ሆሳዕና መንገድ የመልሶ ግንባታ በማካሄድ ላይ የሚገኘውን የCGGC ካምፓኒ ንብረት ለመጠበቅ ከተመደቡ የደቡብ ክልል ልዩ የፖሊስ ሀይሎች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ፖሊሶቹ ወጣቶቹን መደብደብ ሲጀምሩ ወጣቶቹ ባሰሙ የይድረሱልኝ ጩኸት የከተማው ሰው በብዛት በመውጣት ለማረጋጋት ሲሞክር ፖሊሶቹ ተኩስ በመክፈት እስከ 12 ጥይት የተኮሱ ቢሆንም በተኩሱ የተጎዳም ሆነ የሞተ ሰው የለም።
ፖሊስ ለምን ይህን እርምጃ እንደወሰደ ሲጠየቅ “በጥበቃ ላይ በነበርንበት ወጠቶቹ መጥተው ድንጋይ ወረወሩብን” በማለን ምክንያታቸውን ሲገልጹ ወጣቶቹ በበኩላቸው ይህ ሆን ብሎ የተቀነባበረና የአካባቢው ወጣቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከመንገዱ ጋር ተያያዥዥ የሆኑና ሌሎች ልማታዊ መብቶችን በመጠየቃችን የወረዳው አመራሮች በማቄማቸው እና ይህን የመብት ጥያቄ በማጠልሸን የጥያቄዎቻችንን መልክ ማስለወጥ በመፈለጋቸው የተሸረበ ሴራ ነው በማለት ሲገልፁ በአካባቢውም የነበሩ የአይን እማኞች አንድ ማንነቱ ያለኙት ወጣት ከአንድ ሹፌር ጋር ተጣልቶ ለሱ የወረወረው ድንጋይ ወደ ፖሊሶቹ አልፎ ድንጋዩ ሳይገባ እዳልቀረ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ።በማያያዝም በወቅቱ ድለኘንጋይ ወርዋሪው ሮጦ ሲያመልጥ በወቅቱ በመንገዱ ሲያልፉ የነበሩ ልጆችን ይዘው ሲደበድቡ ድንጋይ ተወረወረበት የተባለው ሹፌር ወደ ፖሊሶች በመምጣት ወርዋሪው ጓደኛው እንደሆነና ድንጋዩንም የወረወረው እየተቀላለዱ እንደነበበር ሲገልፅላቸው እንደሰሙ አክለው ገልፀዋል።
በአሁን ሰዓት 4 የከተማው ወጣቶች በዕለቱ ተይዘው ወልቂጤ ከተማ እሚገኘው አበሽጌ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ የተወሰዱ ሲሆን በወቅቱ ግርግሩ ሲፈጠር በቦታው ያልነበሩ ወጣቶችን ፖሊስ ለመያዝ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መረጃው ቀድሞ የደረሳቸው ወጣቶች ከተማዋን ትተው በመውጣት ለስደት ተዳርገዋል።
በወረዳዋ እጅግ ዘርፈ ብዙ አስተዳደራዊ ችግሮች እንዳሉ የወረዳዋ ነዋሪዎች በተደጋጋሚ ሲገልፁ ይደመጣሉ።ከነዚህም ውስጥ በተለያየ ጊዜ በሚሾሙ ባለስልጣናት የተመዘበረው ከግብአት ገቢ መሆን ያለበት ከ3.4 ሚሊየን ብር በላይ በመመዝበሩ ወረዳዋ ባለ ዕዳ በመሆኗ የመንግስት ሰራተኞች ከሌላው ወረዳ በተለየ ከ10—20 ቀናት ዘግይተው ደሞዝ እንደ ሚወስዱና ይህን ተከትሎ እጅግ ብዙ ሰራተኞች እንደሚፈልሱ ይታወቃል።