(ዘ-ሐበሻ) ከደቂቃዎች በኋላ የጃኪ ጎሲ የዋሽንግተን ዲሲ ኮንሰርት ከመጀምሩ አስቀድሞ ከዘ-ሐበሻ ጋር ቃል የተመላለሱት የጃኪ ጎሲ የህግ አማካሪ የሆኑት አቶ መንግስቱ አስፋው የፍርድ ሂደቱ የጃኪ የሰሜን አሜሪካ ኮንሰርቶች ከመደረጋቸው በፊት ቢጠናቀቅ እንኳ የሌሎች ከተማዎችን ኮንሰርቶች ምንም የሚያሰጋ ነገር እንደለሌለና በተሳካ ሁኔታ እንደሚደረጉ አስታወቁ። የሕግ አማካሪው “ለጃኪ ክስ መከላከያዎችን ስናሰባስብ ከዚህ ቀደም ሸዋ ኢንተርቴይመንት በቴዲ አፍሮ፣ በሄኖክ አበበና በጆኒ ራጋ ላይ ክስ መመስረቱን ማስረጃውን አግኝተናል” ካሉ በኋላ በተለይም ሄኖክ አበበና ጆኒ ራጋ በዋሽንግተን ዲሲ በሸዋ የተነሳ የደረሰባቸውን ሸዋ የጃኪን ኮንሰርትም ለማሰናከል 11ኛው ሰዓት ላይ ክስ መመስረቱን በማስታከክ አብራርተዋል።
ሸዋ ኢንተርቴይመንት በፍርድ ቤት የጃኪን ስም በመጥፎ ነገር እንዳያነሳ ተነግሮት እያለ በዘ-ሐበሻ ላይ ወጥቶ የተናገረው በሕግ ሊያስጠይቅ እንደሚችል የጠቆሙት አቶ መንግስቱ የጃኪ ኮንሰርትን ለማሰናከል ባደረገው ጥፋት እስከ 400 ሺህ ዶላር በሚጠጋ የካሳ ክፍያ በሕግ ጠይቀነው ጉዳዩ በፍርድ ቤት ተይዟል ብለዋል። ሸዋ ኢንተርቴይመንትም በተመሳሳይ የ$500 ሺህ ዶላር የካሳ ክፍያ ክስ መመስረቱን ለዘ-ሐበሻ መግለጹ ይታወሳል። አቶ መንግስቱ በጃኪ ጎሲና ኢቫንጋዲ ፕሮዳክሽንን ወክለው ለዘ-ሐበሻ የሰጡትን ቃለምልልስ ይከታተሉት።