ከሊሊ ሞገስ
በዚህ ጉዳይ ላይ ሴቶችን ለይተን ተጠያቂ ማድረጋችን የድርጊት ተቀባይ በመሆናቸውና ውጤት የአስተናጋጅነት እጣ ፈንታው በእነሱ በኩል እንዲያመዝን ተፈጥሮ ያደላችበት ፍርጃ ስላለ ነው፡፡ ምክንያቱም በመጀመሪያው የግንኙነት ወቅት የአካል መጉደል የሚከናወነው በእነሱ አካል ላይ ስለሆነ ማለት ነው፡፡ በዚህ የተነሳ ለድርጊቱ ሴቶች ከወንዶች የተሻለ ትውስታና የጠለቀ ስሜት ስለሚኖራቸውም ነው፡፡
ድንግልና እና ክብረንፅህና
ድንግልና፡- የወንዶችም ሆነ የሴቶችን የአካል መቆጠብ ለመግለፅ የምንጠቀምበት ቃል ሲሆን ይሄም የሚያገለግለው ከግብረ ስጋ ግንኙነት መቆጠብን ይመሰክራል፡፡ ይህ የመቆጠብና የመጠበቅ ሒደትም ለሰውነቴ ክብር መስጠት ነውና የሰውነትን ንፅህና ለመግለፅ ስንጠቀምበት ክብረ ንፅህና (የንፅህና ክብር) በማለት ይብራራል፡፡
ድንግልና በምን ይገለፃል?
በእርግጥ ለሁለቱም ፆታ መታቀብን ተከትሎ ቢያገለግልም በወንዶች ላይ መታቀቡና መጽናቱን ተከትሎ የሚታይ አካላዊ ለውጥ የለም፡፡ በሴቶች በኩል ግን የተራክቦ አካላት ከሆኑት መሀል በብልት አካባቢ ይህን የድንግልና መገለጫ ምልክት ይሆን ዘንድ ተፈጥሮ አስቀምጦት ይገኛል፡፡
በምን መልኩ?
ድንግልና በሴቶች ብልት በራፍ ላይ የተቀመጠ አነስተኛ መጠን ያለው በደም ስሮች የተሞላ ስስና ሴንሴቲቭ /ስሱ/ የሆነ የሰውነት ክፍል ነው፡፡ ይህ ስስ የሰውነት አካል ለሽንትና ለወር አበባ መፍሰሻ በሚያገለግል መልኩ በትንሿ ጣት ልክ ክፍተት ያለው ክብ ቀዳዳ ነው፡፡
የድንግልና አይነት
የድንግልና አይነት በተለያዩ ሴቶች ላይ በአራት (4) ሁኔታ ይገኛል፡፡
1ኛ/ ሙሉ የብልት አካልን በራፍ እንደ መጋረጃ የዘጋና ለወር አበባና ለሽንት ማለፊያ በትንሿ ጣት ልክ ቀዳዳ በክብነት ያለው ሆኖ ይገኛል፡፡
2ኛ/ ብዙ ጊዜ ባይሆንም በአንዳንድ ሴቶች ላይ እንደሚታየው የወንፊት መልክ በያዘ የተበሳሳ በርካታ ቀዳዳዎች ሙሉ ለሙሉ የብልቱ በራፍ የተጋረደ ሆኖ የሚገኝበት ሁኔታ ነው፡፡
3ኛ/ በተፈጥሮ ምንም አይነት የሰውነት ክፍል በብልቱ በራፍ ላይ ሳይጋረድ ወይም የብልቱ በራፍ ከሆነው ቀዳዳ በላይ በሆነ አካል ግርዶሽ ተሸፍኖ የሚገኝበት አጋጣሚም አለ፡፡
እነዚህ በተፈጥሮ የሚሆኑ ሲሆኑ በግንኙነት ጊዜ በሚፈጠረው ፍትጊያና በወንዱ አካል (ብልት) የሚወገዱ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ
በ4ኛ/ ደረጃ የሚጠቀሰው ድንግልናው በተፈጥሮ በጠነከረ ቆዳና በቀላሉ በወንዱ አካል (ብልት) ሊወገድ የማይችል አይነት ነው፡፡ ይህ አይነቱ ድንግልና ብዙ ጊዜ በህክምና ተቋም በመሄድ በቀዶ ህክምና ከሴቷ ብልት በራፍ የሚወገድ ለተራክቦ አካሏ የሚስተካከልበት ሁኔታ ነው፡፡
ከሞላ ጎደል የሴት ልጆች ድንግልና በዚሁ መልኩ በተፈጥሮ የሚሰጣቸው ልዩ ፀጋ ነው፡፡
ይህ ፀጋ ደግሞ አንዴ በመወለድ የሚገኝ የአንድ ጊዜ ዕድል ነውና በህይወታቸው ውስጥ ሴቶች የማይረሱት አሻራን ያነጥቡ ዘንድ ሰፊ ዕድል ያረገዘ ነው፡፡ ይህ አካልና የክብር መግለጫ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚደረግ የግብረስጋ ግንኙነት ሊጠፋ ይችላል፡፡ እንዲሁም በአላስፈላጊ እንቅስቃሴም፣ በፈረስና ሳይክል ግልቢያ፣ ከባድ ዕቃ በማንሳትና በጀርባ በመሸከም በሂደት በመስፋትም ሆነ በመተርተር ሊጠፋ ይችላል፡፡
ግብረስጋ ግንኙነት ምንድነው?
የግብረስጋ ግንኙነት ማለት ወንድና ሴት የሆኑ ፆታዎች በተራክቦ አካላት የሚፈፅሙት የአካል መገናኘት ግብረ ስጋ ግንኙነት ሲባል ሂደቱ ግን የተለያዩ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ስሜቶችን ይዞ ይገኛል፡፡ ይህ ቢሆንም አላማው ግን አንድም ስሜት (ስጋዊ ፍላጎትን) ለማርካትና ምላሽ ለመስጠት ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ የግብረ ስጋ ግንኙነት ትርጉም ዘር ለመተካት የሚያደርግ ሂደት በመሆን ይገለፃል፡፡ ከዚህ አኳያ ሴቶች ወንዶች አካላዊ በሆነ ንክኪ ስሜታቸውን ምላሽ ለመስጠትም ሆነ ዘር ለመተካት በሚደረግ ግንኙነት ይህን አካል ያጡታል፡፡ ይህ ደግሞ ፈቅደውና ተገደው የሚሆንበት አጋጣሚ እጅጉን ሰፊ ነው፡፡ ፈቅደውም ሆነ ተገደው ክብረ ንፅህናቸውን በማጣትም ሆነ በተለያየ መልኩ ካጡት በኋላ ቢሆንም ለመጀመሪያ ጊዜ በሚባለው የግብረ ስጋ ግንኙነት ሴቶች ምን ስሜት ይሰማቸዋል? የሚለው አብይ ጉዳያችን ነው፡፡
ለምን?
የትውልድ መሸጋገሪያዎች ሴቶች እናቶች ናቸው፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ሴቶች የህብረተሰቡ ግማሽ አካል ናቸው፡፡ እውነቱ ይሄ ከሆነ የሴቶች ጤናማነት ያለው አስተሳሰብ ጤናማ ትውልድን በመቅረጽ ጥሩ ዜጋን ለመተካት ይረዳልና ያለፈውን ለማረም፣ ለሚመጣው ትውልድም ከሚፈጥረው ስሜት አኳያ ተሞክሮን በማኖር መማማሪያ ለማትረፍ ከሚል በመነሳት ነው ይህን ሀሳብ የያዘ ደብዳቤ በየቦታው ለሴት እህቶቻችን በመስጠት የሰጡንን የስሜት ነፀብራቅ ለማቅረብ የወሰነው፡፡
ፍቅር እና ሴክስ ምንድናቸው?
ፍቅርና ሴክስ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ያህል ግድ ናቸው የሚባልበት በአራት ነጥብ የተዘጋ ገለፃ የለም፡፡ ሁለትም አንድም ናቸው፡፡ ሁለትነታቸው በአተረጓጎም የሚለያዩና የተራራቁ ሲሆኑ፣ አንድነታቸው ግን ከመፈቃቀድ በኋላ አንዳቸው ለአንዳቸው መደራጀትና መጠናከር ጠንካራ አስተዋፅኦ መስጠታቸው ነው፡፡ ፍቅር ኖሮ ሴክስ ሲታከልበት ይበልጥ መግባባት ይቻላል፡፡ ፍቅር ባይኖርም በሴክስ መግባባት ሲቻል ያ መግባባት አንዱ የፍቅር ግብአት በመሆን ፍቅርን ለመፍጠር ይቻላል፡፡ በዋናነት ግን አሳማኝ በሆኑ ምክንያቶች ሲፈተሽ ፍቅር ላቅ ብሎ ይገኛል፡፡ ፍቅር መስዋዕትነት አንዱ ባህሪው ነውና በሴክስ ብቃት ባይደገፍም እንኳ ብቻውን ሊፀና ይችላል፡፡ ይህ ሁኔታ በአንፃሩ ፍቅር ሳይኖርም አካላዊ ምላሽ በመስጠት መንፈሳዊ እርካታ ባይገኝበትም ዘር ለመተካት በሚል በስጋዊ ምላሽ… እየተተረጎመ ሲኖር ይታያል፡፡ እስቲ የአንዷን አስተያየት እናንብብ፡፡
በመጀመሪያው ሴክሴ ፈሪ ሆኜ ቀርቻለሁ!
ይህን ያለችን ሴት የ38 ዓመት ስትሆን 3 ልጆች አሏት፡፡ በተሟላ ትዳር ውስጥ ናት፡፡ የምትወደው ባልም አላት፡፡ እንዲህ ነበር ስሜቷን ያሰፈረችው፡፡
‹‹…የ18 ዓመት ልጅ እያለሁ… በሰፈራችን ውስጥ ያለ ሸበላ ወጣት ጋር ፍቅር ጀመርን፡፡ ሁለታችንም ተማሪዎች ስለነበርን ከአለማችን በፊትና