ከምኒልክ ሳልሳዊ
በኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ስልጣን እርከን ላይ የተቀመጠ እና በሙስና አልተዘፈቀም የተባለ ቢኖር ደፍሮ ይህ ነው የሚል የለም። ከራሳቸው ስም ጀምሮ እስከ ዘመድ አዝማዶቻቸው ወዳጅ ጓደኞቻቸውን ሳይቀር በዘረፋ ውስጥ በማመሳጠር ያሰማሩት የወያኔ ባለስልጣናት ተቆጥረው አያልቁም። ከትንሽ የቀበሌ ካድሬ ጀምሮ ልከክልህ እከክልኝ ብላ እንብላ መውደቂያህን አሳምር ወዘተ እየተባለ የህዝብ ሃብቶች የሃገር ውስጥ እና የውጪ ባንኮችን አጨናንቀዋል።
የወያኔ ባለስልጣናት የሆኑና ከቤተሰቦቻቸው ከዘመድ ወዳጆቻቸው ጀርባ ሆነው ከፍተኛ የዘረፋ ስራ ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ የሚተገብሩ በአደባባይ ግን እንደ ንጹሃን ምንም እንዳሌለባቸው መታየት የሚፈልጉ ያሻቸውን ነገር በስልክ ቲዛዝ አሊያም በተላላኪ ደህነንቶች የሚያስፈጽሙ እንደ ደብረጺሆን ገ/ሚ ሳሞራ የኑስ አባይ ወልዱ በረከት ስምኦን ሃይለማርያም ደሳለኝ እና የተወሰኑ 3 % የሚሆኑ የሕወሓት አመራሮች ሃገሪቷን እየዘረፉ ይገኛሉ።
ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እና የሕወሓት አመራሮች በዘረፋ ስራ ላይ መሰማራታቸው ሳያንስ ከተለያዩ የዘረፋ ቡድኖች ጋር የተሳሰረ ግንኙነት /ኔትወርክ/ በምስራቅ አፍሪካ ዘርግተዋል ። ከአውሮፓ እና ከኢሽያ የሚነሱ የማፊያ ቡድኖች እና እጽ አዘዋዋሪዎች እና ህገወጥ ነጋዴዎች ጋር በመመሳጠር ሃገሪቷን የህገወጦች መተላለፊያ ከማድረጋቸውም በላይ ኮንትሮባንድን በህግ ሽፋን እየተገበሩ ሃገሪቷ ማግኘት ያለባትን እንዳታገኝ ለግል ጥቅማቸው በመሯሯጥ ዘረፋውን አጧጡፈውታል።
የደህኝነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ ከፍተኛ ጄኔራል መኮንኖች እንዲሁም በመሃል አገር የከተሙ የሕወሓት ሹሞች በአጭር ጊዜ ውስጥ በዘረፋ ብቻ ቢሊየነር ለመሆን የበቁ እና በቤተሰቦቻቸው እንዲሁም በተለያዩ የፈጠራ ስሞች እና ሰነዶች የትልልቅ ፋብሪካዎች እና የከባድ ኮንስትራክሽን ካምፓኒዎች ባለቤቶች ከመሆናቸውም በላይ ካለምንም ግብር እና ቀረጥ እንዲሁም ጨረታን አሸናፊ በመምሰል ለራስ ጥቅም በማዋል የውጭ ምንዛሬ በስልክ ትእዛዝ ብቻ በውጪ አገር አካውንታቸው እንዲገባ ባንኮችን በማዘዝ (ባንክ ኦፍ ማሌዥያ ለዚህ ጉዳይ ተጠያቂ ነው) ሃገሪቷን እየበዘበዟት ነው።
በተለያዩ የቤተሰቦቻቸው ስም ዘረፋውን ከሚፈጽሙ ቢሊየነር ባለስልጣናት ውስጥ አባዱላ ገመዳ ፤ አርገበ እቁባይ ፡ግርማ ብሩ እና ካሱ ኢላላ ይገኙበታል። በቅርቡም ይህንን የቢሊየነሮች ቡድን የተቀላቀለው የደህንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ በቤተሰቦቹ አክሲዮን ስም አዲስ የከፈተውን የኮንስትራክሽን ካምፓኒ ሊያስመርቅ በዝግጅት ላይ ሲሆን አገር ውስጥ ከሚሰሩት የከባድ ኮንስትራክሽን ካምፓኒዎች 77% የወያኔ ባለስልጣናት መሆናቸው ይታወቃል።
አቶ ጌታቸው እና የጦር መኮንኖቹ አዲስ በአዋጅ በተሰጣቸው ስልታን መከታ በማድረግ የተለያዩ ባለሃብቶችን በቡድን ባደራጁት ዘራፊዎች በማዘረፍ በማስፈራራት እና የመንግስትን በጀት ያለ አግባብ በመጠቀም በሙስና እና በዘረፋ ተዘፍቀዋል። ይህንን የደህነንቶች የዘረፋ ተግባር በተመለከተ አዲስ አበባ ያሉ እና በሚሊዮን ብሮች በግዳጅ የተነጠቁ ባለሃብቶች ታሪክ ለምስክርነት ያቆያቸዋል።