ለሰላም እና አንድነት ከቆሙ ምእመናን የተካለፈ ወቅታዊ ማብራሪያ፦
4/17/2014
በሥላሴ ስም አንድ አምላክ አሜን።
ከእንግዲስ ይሁን ሰላም።
ቤተክርስቲያናችን ሚኒያፖሊስ ደብረሰላም መድኃኔዓለም በአሁኑ ወቅት ወሳኝ ወደሆነ ምእራፍ ላይ ተቃርባለች። ይህም በፍርድ ቤት በተሰጠ ት እዛዝ ሜይ 11/2014 ዓ.ም በሚደረገው የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ የሚወሰን ይሆናል። ይህ በዚህ እንዳለ ባለፍው ሳምንት በሆሳዕና እለት የተከሰተውን አሳዛኝ ድርጊት በመጥቀስ የተዘጋጀውን አጠር ያለ ሐተታ እነሆ፦
እሁድ ኤፕሪል 13 ቀን 2014 ዓ.ም በዕለተ ሆሳዕና ከጌታ ዋና ዋና በዓላት አንዱ በሆነው አውደ ዓመት እለት አባ ኃይለሚካኤል ሙላት፣ቀሲስ ስንታየሁ ወልደየስ፣ቀሲስ አሃዱ አስረስና ዲያቆን ሄኖክ ያሬድ ቅዳሴ አንቀድስም አገልግሎት አንሰጥም ብለው የተፈራረሙበትን ደብዳቤ ለቅዳሴ ለታደመው ምዕመን እንዲነበብ በማድረግ ከቤተክርስቲያን ወጥተው ሄደዋል።
በዚህ ታላቅ የምስጋና እለት ሰው ብቻ ሳይሆን ድንጋዮች እንኳን ሳይቀሩ ያመሰግኑኛል ብሎ ጌታ ራሱ በቃሉ በተናገረበት ክብረ በዓል ቅዳሴ አንቀድስም አገልግሎት አንሰጥም በማለት የፈጸሙት አስነዋሪና ፈጽሞ ክርስቲያናዊ ያልሆነ ድርጊት የደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤትክርስቲያን አባላትን እጅጉን አሳዝኗል። ለበርካታ ዓመታት ሲያገለግሉበት የነበረውን ታላቅ ደብር ክርስትና ሲያነሱበት፣ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲፈትቱበት፣ ቅዱስ ጋብቻ ሲፈጽሙበት፣ ዝማሬ ሲያቀርቡበትና ሌላም በርካታ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ሲያከናውኑበት የኖሩትን ቅዱስ ስፍራ ትተው በእለተ ሰንበት በበዓለ ሆሳዕና አሕዛብ በሚዳሩበት አስረሽ ምችው በሚካሔድበት ጥሻ ውስጥ መገኘታቸው ከኅሊና በላይ የሆነ የበደል ሥራ ነው።
በቤተክርስቲያናችን ውስጥ የተፈጠረውን አለመግባባት በውይይትና በሕዝብ ውሳኔ ለመፍታት ባለመቻሉ እና አንዳድ የአስተዳደር ቦርዱ አባላት መጀመሪያ በወሰዱት የጠበቃ መያዝና ሕገ-ወጥ ርምጃ ምክንያት ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት በማምራቱ ፍርድቤቱ ችግሩን የመፍታት የመጨርሻ ስልጣንና ኃላፊነት ላለበት ለጠቅላላ ጉባዔ መርቶታል።
በዚህም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሠረት በፔቲሺን የቀረቡትን አጀንዳዎች ጠቅላላ ጉባዔው ድምጽ እንዲሰጥባቸው፤ እስከዚያው ድረስም የአባላቱን ሰላምና ደህንነት ከማስከበር አኳያ ቤተክርስቲያኑ በነበረበት ሁኔታ እንዲቀጥል ማለትም የፓትርያርክም ሆነ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ስም እንዳይጠራ፣
ከውጪ አባላት ያልሆኑ ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች እንዳይመጡ እና የፍርድ ቤቱንምት እዛዝ ለማስከበር የጸጥታ አስከባሪዎች /ፖሊስ/ እንዲመደብ በማለት የወሰነውን ፍትሐዊ ብይን በመቃወም ከላይ የተጠቀሱት ካህናትና ጥቂት ተከታዮቻቸው እነርሱ የፈለጉትን ማድረግ ካልቻሉ አገልግሎት መስጠት
እንደማይችሉ በመግለጽ በጽሑፍ አሳውቀዋል። ይህንንም የአናገለግልም መግለጫ ምእመናኑ በፈቃዳቸው ስራቸውን እንደለቀቁ በመቁጠር ተቀብሎ አገልግሎቱ የቤተክርስቲያኑን መተዳደሪያ ደንብ እና ሲሰራበት የኖረውን አካሔድ ተቀብለው ለማገልገል ፈቃደኛ በሆኑ ካህናትና ዲያቆናት እንዲቀጥል ፈቅዶ የበአለ ሆሳዕናው አገልግሎት ምንም ሳይጓደል ተከናውኗል። በዚህ አጋጣሚም ከሁሉ የሚበልጠው እግዚአብሔርን ማመስገን ነው በማለት ኃላፊነት በመውሰድ አገልግሎቱ እንዳይታጎል መስዋዕትነት የከፈሉትን አገልጋዮች እናከብራለን እናመሰግናለን።
ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ደግሞ በፍርድ ቤት በጠበቃቸው በኩል ያቀረቡት ይግባኝ ውድቅ ክሆነና ሕዝቡም ድርጊታቸውን እንደማይቀበል በተግባር ከገለጸ በኋላ፤ ተከታዮቻቸውም በጣት የሚቆጠሩ ስሜታዊና ያልበሰሉ ሰዎች ብቻ እንደሆኑ ካዩ በኋላ ‘የፖለቲከኞች ቤት ነው’ እያሉ በማንቋሸሽ ትተውት የሄዱትን ቤተክርስቲያንና አማኝ እንደገና እናገለግላለን ብለው መመለሳቸውን ፈጽሞ የማንቀበለው ነው። ‘ጳጳሳት’ በድብቅ አስመጥተው የእግዚአብሔርን ማደሪያ ቤት ያሳማ ማጎሪያ ያህያ ማሰሪያ ያድርጉት አሮጌውን ፎቅ ለቃችሁ ውጡና የራሳችሁን ጎጆ ቀልሱ’ እያሉ ሲያሰድቡና እነርሱም በዚህ አባባል ሲሳለቁ የነበሩ ስለሆኑ ከእነኝህ ከማያምኑ ሰዎች ጋር ምንም ዓይነት ሕብረት ከዚህ በኋላ የለንም።
በሰፊው እንደሚነገረውና አንዳንድ ተከታዮቻቸውም በግልጽ እንደሚናገሩት የእነኝህ ሰዎች ዋና አላማ የቤተክርስቲያኑን ገንዘብ መካፈል ነው። ቤተክርስቲያኑ ከታክስ ነፃ ሆኖ የተቋቋመና በጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ የሚተዳደር በመሆኑ ማንኛውም አባል የጠቅላላ ጉባዔውን ውሳኔ በመቀበልና በማክበር የሚኖርበት አሰራር ብቸኛ መንገድ ነው ያለው። በቤተክርስቲያኑ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ከጠቅላላ ጉባኤው ¾ ኛው እንኳን የቤተክርስቲያኑ አገልግሎት እንዲያበቃና /ዲዞልቭ / እንዲሆን ቢወስን ያለው ገንዘብና ንብረት ሁሉ ገቢ የሚሆነው ወደ ስቴቱ ጄኔራል ፈንድ ነው። የቤተክርስቲያን ገንዘብ የንግድ /ቢዝነስ/ ስላልሆነ እንደሼር ሆልደር/ባለ አክሲዎኖች/ አባላቱ የሚካፈሉት አይደለም! ደግሞስ ለቤተክርስቲያን አንድ ጊዜ የተሰጠን ገንዘብ መልሱልኝ እንዴት ይባላል? ይህ ሃሳብ ከክርስትና ፈጽመው የመውጣታቸውና ቤተክርስቲያንን የመከፋፈልና የህዝብን አንድነት የመናድ አላማ ያላው ኃይል ተልእኮ ፈጻሚ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው።
ስለዚህ የደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አባላት በሙሉ ሜይ 11 2014 ዓ.ም በሚደረገው የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመገኘት የቤተክርስቲያናችንን ሕልውና እንድናስከብርና ለዚህም ዓላማ የቆሙ አዳዲስ የቦርድ/ሰበካ ጉባኤ/ አባላትን እንድንመርጥ እናሳስባለን። በተጨማሪም ሁላችንም የጠቅላላ ጉባዔውን ውሳኔ በመቀበል ለእውነት፣ለአንድነትና ለሰላም መቆም ይገባናል። የካህናቱን ውሳኔና የጳጳሳቱን የስድብ ቃላት ለማስርጃነት ያህል ቀጥሎ ይመልክቱ፤ ያድምጡ። በፍርድ ቤቱ የተሰየሙት ማስትር ዳኛ የሰጡትንም ትዕዛዝ ይመልከቱ።
listen to the sermon by aba Markos at a conference held on April 5, 2014 organized solely by a pro woyane group. በተለይ በክፍል አንድ ላይ ከ12:30 minutes ጀምሮ ያለውን የእግዚአብሔርን ማደሪያ የሆነውን ቤተክርስቲያን ሲሳደቡና ሲያጥላሉ ያድምጡ፦ (ቪድዮው ዳውንሎድ ለማድረግ ሰፊ ሰዓት ስለሚወስድ ወደ ከሰዓት በኋላ ይለቀቃል)
‘አሮጌውን ፎቅ ትታችሁ የራሳችሁን መስርቱ፣ በሉ ያው አህያ እሰሩበት ብላችሁ መሔድ ነው በማለት ከፋፋይነታቸውን/ካድሬነታቸው በይፋ ከመናገራቸው በተጨማሪ ኢትዮጵያ ቢሆን ኖሮማ እናሳየው ነበር በማለት ሲቆጩ ይደመጣሉ። ቀጥለውም አህያ እሰሩበት አሳማ
አርቡበት በማለት ፍጹም ከአንድ አባት የማይጠበቅ የወያኔ ካድሬነታቸውን ከመግለጽ ባሻገር እንደወያኔ በጠመንጃ አሳየው ነበር በሚል አገላለጽ ሲያፌዙ ይሰማሉ።