Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ድምጻዊ ጎሳዬ ቀለሙ (ጃኪ ጎሲ) ከተሾመ አሰግድ ለሰረቀው ዘፈን ይቅርታ ይጠይቅ ይሆን? ወይስ ማን አለብኝነት ያልፈዋል?

$
0
0


ይታየው ከሚኒያፖሊስ

ከዓመት በፊት በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 38  ነዋሪነቱ ሚኒሶታ የሆነው ስመ ጥሩው ድምጻዊ ተሾመ አሠግድ “በጠራራ ጸሐይ ተዘረፍኩ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደኝ” ሲል ለዘ-ሐበሻ ጋዜጣ በሰጠው መግለጫ ላይ አስታውቆ ነበር። ካለፈቃዱ ጎሳዬ ቀለሙ (ጃኪ ጎሲ) የተባለው ድምጻዊ የተሾመን “የኔ አካል” ወስዶ መሥራቱን አምርሮ መቃወሙንም አንብበን ነበር። “አንድ ዘፋኝ የአንዱን ወስዶ ለሕዝብ ሲያቀርብ ባለቤቱን ማስፈቀድ ይኖርበታል” ያለው ተሾመ “ጎሲ ከ20 ዓመት በፊት የተጫወትኩትን፦ “የኔ አካል የኔው ነሽ፤ ምን አወርስሻለሁ፤ አንጀቴና ልቤን ያው ትቼልሻለሁ”” ዘፈኔን ካለፈቃድ በክሊፕ ጭምር ማውጣቱ ክፉኛ በድሎኛል” ካለ በኋላ “ድምጻዊው ጎሳዬ ቀለሙ የኔን ብቻ ሳይሆን ዘፈኑን የደረሱልኝን ገጣሚው ይልማ ገብረአብን እና የዜማ ደራሲውን አበበ መለሰን ሁሉ ተዳፍሯል። ይህንን ዘፈን በፈረንጆች በ1987 ዓ.ም አካባቢ ከነራሄል ዮሐንስ ጋር በጋራ ባወጣሁት አልበም ውስጥ ሳካትተው ግጥሙን እና ዜማውን የሰጡኝ እነርሱ ናቸው። በሙዚቃ ክሊፑ ላይ የነዚህ ስም አልተጠቀሰም። ይልቁንም የሌላ ሰው ስም በመጻፍ የኛን ሥራ የራሱ በማስመሰል አቅርቦ ሥራዬን ዘርፏል” ሲል ቅሬታውን አሰምቶ እንደነበር አንበበናል።
jacki gossee
“ወደ ሕግ ጋር መሄዴ የማይቀር ነው። ጉዳዩን ፍርድ ቤት አድርሼ እሞግተዋለሁ” ያለው ድምጻዊ ተሾመ አሰግድ “የኔ አካል” የተሰኘውን ሥራዬን ካለፈቃዴ ተነጥቂያለሁና ከዚያ በፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደኝ፤ በጠራራ ጸሐይ ነው የተዘረፍኩት።” በማለት የኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰረቁ ዘፈኖች ሲወጡ ከኦርጂናሉ ዘፋኝ በይሁንታ መገኘቱን እና አለመገኘቱን ማረጋገጥ ይኖርበታል ሲል ጥሪውን አቅርቦ ነበር። “ድምጻዊ ጎሳዬ ቀለሞ (ጃኪ ጎሲ) የተሾመ አሰግድን ዘፈን መሥራቱን አምኖ በቪድዮ ክሊፑ ላይ ምስጋና አቅርቧል” በሚል የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ለተሾመ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

ተሾመም “ይሄ ገሎ ማዳን ነው። ነጮጭ ሲናገሩ መጀመሪያ አቁስለውና ከዛ ለቁስሉ ማበሻ ጨርቅ ስጠው ይላሉ። ጎሳዬም ያደረገው ያ ነው። ዘፈኑን ካለፈቃዴ ወስዶ፤ ክሊፑም ከመልዕክቱ ጋር የማይገናኝ አድርጎ ሰርቶ በመጨረሻ ተሾመ አሰግድን አመሰግናለሁ ብሎ ቢጽፍ ምን ዋጋ አለው? ከገደለኝ በኋላ ማርኩህ ቢለኝ ምን ዋጋ አለው?” በማለት አምርሮ ሲናገር መስማታችን ይታወሳል።

በኢትዮጵያ ስመ-ጥር ከሆኑ ድምጻዊያን መካከል የሆነውና ብዙዎች “ኢትዮጵያዊው ስቲቭ ዎንደር” የሚሉት ተሾመ አሰግድ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በመስከረም ወር 1945 ተወልዶ በተወለደ በ5 ወሬ ዓይነ ስውር መሆኑን በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 2 ላይ በሰጠው ቃለ ምልልስ መናገሩ ይታወሳል። የመጨረሻ ካሴቱን ካወጣ 17 ዓመት ያለፈው ይህ ድምጻዊ እስካሁን ስንት ካሴቶችን ሰርተሃል በሚል ጥያቄ አቅርበንለት “ጥቂት ካሴቶችን አውጥቻለው:: ትዝታና ባቲ በሚባለው የሙዚቃ ቅኝት በፊሊፕስ አሳታሚነት በ1960ዎቹ አንድ ሸክላ አውጥቼ ነበር:: ከዛ በተረፈ ያልተሳካለት አንድ ካሴት ሰርቼ ነበር:: ከዛ ወዲህ ግን ጅቡቲ ለ5 አመታት ከቆየው በሗላ ከሮሀ ባንድ ጋር በመሆን ‘የኩባያ ወተት”ን ሰራሁኝ:: ይበልጥ ከሕዝብ ጋር ያስተዋወቀኝም ይሄ ሥራ ነው:: በሌላ በኩል ከነራሄል ዮሐንስ; አሰፉ ደባልቄ እና ኬኔዲ መንገሻ ጋር አንድ ካሴት; እንዲሁም ከማርታ አሻጋሪ; በዛወርቅ አስፋው እና ኤልያስ ተባባል ጋር በመሆን አንድ ኮሌክሽን ሰርቼ ነበር:: በራሴ በኩል 2ኛውን ሙሉ ካሴቴን “ደርባባዬ’ን አውጥቼ ነበር:: ብዙም በሕዝብ ዘንድ አልገባም:: ግን አልፎ አልፎ ሰዎች ያውቁታል::” ሲል መልሷል። 

ተሾመ ጎሳዬ ሰረቀኝ ባለው ዘፈን ዙሪያ ይህን ቢናገርም ጆሲ ሾ ላይ የቀረበው ጃኪ ጎሲ በማን አለብኝነት እንደውም ተሾመ ስለዚህ ዘፈን አያገባውም ሲል መናገሩ ይታወሳል። ጎሳዬ ቀለሙ ይህን ያለው ለደራሲው እንደገና ስለከፈልኩት ተሾመ ይህ ዘፈን የኔ ነው ብሎ መከራከር አይችልም ሲል በቲቪ መድረክ መናገሩ ይታወሳል። ይህን ያለው ሃገር ቤት ሆኖ ነበር። ዛሬ ተሾመ አሰግድ በሚኖርበት ሰሜን አሜሪካ ጎሳዬ ቀለሙ መጥቷል። ተሾመ ፈቃድ ይፈልጋል። ሆኖም ግን ጃኪ በማን አለብኝነት “ድምጻዊው የለፋበትን ሥራ አያገባውም” ሲል ተናግሯል። ጃኪ እነ ምነው ሸዋ ላይ እንዳሳየው በግትርነቱ ይቀጥል ይሆን ወይስ ተሾመ እንዳለው ወደ ሕግ በመሄድ ጃኪን በስርቆት ይከሰው ይሆን? አብረን የምናየው ይሆናል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>