በአማራ ክልል ከአምስት ሺህ በላይ ዜጎች ሜዳ ላይ
ወድቀዋል ሰማንያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል
በጀት ስለሌለን ምንም ያደረግነው የለም
አቶ አማረ በሪሁን የወረዳ የብአዴን ኃላፊ
በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ በመቄት ወረዳ ቀበሌ 0 40 ልዩ ቦታው አሳሳ በተባለ ቦታ መጋቢት 20 ቀን 2006 ዓ. ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ የተነሳው እሳት አደጋ ለሰላሳ ድስት ሰዓት ማለትም ለአንድ ቀን ተኩል በመንደድ በአካባቢው ያሉ ሰማንያ ቤቶችን ከነ ሙሉ ንብረታቸው ሲያወድም አቶ ጫኔ አካሉ የተባለ አርሶ አደር ሲሞት ሌሎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች የቆሰሉ መሆናቸውን ከአካባቢው ባገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ ለማወቅ በአካባቢው ለሚገኙ አርሶ አደሮች ጥያቄ ያቀረብን ሲሆን ሲመልሱም እኛ የአደጋውን መንስኤ ምን እንደሆነ አላወቅንም ነገር ግን ማንም ሳይደርስልን የአርባ ሁለት አባወራ ከነቤተሰባቸው ሙሉ በሙሉ ንብረታችን ወድሞ አሁን ያለምንም መጠለያ ሜዳ ላይ ወድቀናል እባካችሁ ምግብ እንኳን የሚያቀምሰን ድርጅት ከተገኘ ድምፃችንን አሰሙልን ብለዋል በአካባቢው ያሉ የወረዳና የቀበሌ መስተዳድር አካላትን ለጊዜው ማግነት ያልቻልን ሲሆን ለነዋሪዎቹ ግን በመንግስት በኩል የተደረገ ድጋፍ አለ ወይ ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄ ሲመልሱ የወረዳው አስተዳደር አካላት መጥተው ፎቶ አንስተውን ቪዲዮ ቀርፀውን ሄደዋል እስኪ ፍረዱን እኛ ማደሪያ እጥተን የሚቀመስ ቸግሮን ፎቶና ቪዲዮ ምን ይሰራልናል ብለው ይጠየቃሉ ፡ ፡ አሁን ቤታቸው የወደመባቸው አርሶ አደሮች ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ በመውደሙ እንዲሁ ሜዳ ላይ ወድቀው ይገኛሉ፡ ፡ በቀጣይም አስተዳደርቹን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ባይሳካም የወረዳው ብአዴን ፅ/ ቤት ኃላፊ የሆኑትን አቶ አማረ በሪሁን በተንቀሳቃሽ ስልካቸው አግኝተን ስለጉዳዩ ማብራሪያ ጠይቀናቸው ነበር ሲመልሱም ‹‹ ልክ ነው አደጋው ተከስቷል ተጎጂዎቹም ችግር ላይ እንዳሉ አውቀናል ነግር ግን እርዳታ ለመስጠት ባጀት ስለሌለን ምንም ያደረግንላቸው ነገር የለም ወደ በላይ አመለክተናል ምላሹን እየተጠባበቅን ነው ብለዋል ፡፡