Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ወደ እስራኤል ለመሄድ ቪዛ የጠየቁ ጉዟቸውን እንዲያራዝሙ ኢምባሲው አስታወቀ

$
0
0

Israel Flag
ለጉብኝትና ለሥራ ወደ እስራኤል የሚጓዙ ኢትዮጵያዊን አዲስ አበባ ከሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ የቪዛ አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸውን ለሰንደቅ ጋዜጣ ገለፁ።

አዲስ አበባ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ለሰንደቅ እንደገለፀው፤ ወደ እስራኤል ለጉብኝት የሚጓዙ ኢትዮጵያዊያን ላልተወሰነ ጊዜ ጉዟቸውን እንዲያራዝሙ አሳስቧል። የቪዛ አገልግሎት የሚያገኙት የቡሩንዲ እና የሩዋንዳ ዜጎችንም ጉዟቸውን እንደሚያስተጓጉል ለማወቅ ተችሏል።
ኤምባሲው አያይዞ እንደገለጸው፤ በእስራኤል መንግስት እና በእስራኤል ዲፕሎማቶች መካከል የደሞዝና የጥቅማጥቅም ጭማሪ አስመልክቶ የተነሳው ውዝግብ እልባት እስከሚያገኝ የዲፕሎማሲና የቪዛ አገልግሎት እንደማይሰጥ አስታውቋል።

የእስራኤል ዲፕሎማቶች ከማርች 5 ቀን 2014 ጀምሮ የመቱትን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ በዓለም የሚገኙ የእስራኤል ኤምባሲዎች፣ ከእስራኤል መንግስት ባለስልጣናት፣ ተቋማት፣ ግብረ ሰናይ ደርጅቶች፣ አርቲስቶች እና ከሌሎቹም ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አቋርጠዋል።

አዲስ አበባ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ቃል አቀባይ የሆኑት ሊዮ ቪኖቨስኪ ስለተፈጠረው አለመግባባት አነጋግረናቸው በሰጡን ምላሽ ፣ “ለእስራኤል በተለያዩ የስራ መስኮች እየሰራን እንገኛለን። ስለዚህም በዓለም ዓቀፍ ተቀባይነት ባለው ደረጃ ደሞዛችን መስተካከል አለበት። በሌሎች ሀገሮች የዲፕሎማሲ ስራዎች የብሔራዊ ጥቅም ማስከበሪያ ማገሮች ተደርገው ነው የሚወሰዱት፣ ለእኛም በዚህ ደረጃ ሊስተካከልልን ይገባል። ዲፕሎማት በመሆናችን በድርድር እናምናለን። በሌላ ወገን ግን ለመነጋገር ፍቃደኛ ካልሆኑ ውጤቱ ግልፅ ይመስለኛል። ስለዚህም ሚኒስትር ላፒድ እና የስራ ባልደረቦቻቸው መንቃት አለባቸው። ምክንያቱም እኛ የወሰድነው እርምጃ፣ የማንቂያ ጥሪ ነው” ብለዋል።

በእስራኤል ውስጥ እና ውጪ የሚገኙ 1200 ዲፕሎማቶች ለድርድር መንግስታቸውን የጋበዙ ቢሆንም የእስራኤል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያቤት ድርድሩን አስመልክቶ የሰጠው መግለጫ የለም።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>