Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

[የመልካም አስተዳደር እጦት በወሎ] የዘረፈ፣ እግር የቆረጠ፣ ሕዝብን በጥይት እየገደለ ያለ ስልጣን ላይ ሆኖ ይንደላቀቃል

$
0
0

(የሰሜን ወሎ ሕዝብ በገበያ ላይ - ፎቶ ፋይል)

(የሰሜን ወሎ ሕዝብ በገበያ ላይ – ፎቶ ፋይል)


ለዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ አዘጋጆች
ክቡር ሰላምታየ ይድረሳችሁ

ከዚህ በመቀጠል የዘወትር የፕሮግራምችሁ ተከታታይ ስሆን ይህን የመልካም አስተዳደር ችግር አየር ላይ እንድታውሉልኝ እየጠየኩ እን ሁልግዜው ለሁሉም የምታቀርቡትን አስተያየት ሙያችሁ በሚፈቅደው መሠረት እንደምታቀርቡልኝ ወይም አየር ላይ እንደምታውሉልኝ በመተማመን ነው፡፡
በሰሜን ወሎና ዞን በሀብሩ ወረዳና በመርሳ ከተማ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ አካባባቢ በየግዜው የሚስተዋሉት የመልካም አስተዳደርና የሙስና ችግሮች ነዋሪውን የከተማና የገጠር ህዝብ እግር ተወርች ሰቅለው ይዘውታል፡፡ ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር ከመንግስት ደቀመዛሙርት መሰል ሚዲያዎች የምንተነፍስበት ወይም ሃሳባችንን የምንገልፅበት አማራጭ አለመኖሩ ነው፡፡ ይህም የናንተ የዘገባ አድማስ ሁሉንም አካባቢዎች የሚሸፍን አለመሆኑ ይመስለኛል ፡፡

ከዚህ በተረፈ ጉዳዩ አዲስና ልዩ ባይሆንም ድግግሞሽና አንደኛው ከሌለኛው ሲነፃፀር በጣም የከፋ እየሆነ በመምጣቱ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት አቤቱታው በምድር ላይ ያሉት ቱባ ባለስልጣኖች ጆሮ ነፊውን በየእምነቱ በፈጣሪው መፀለይ እና አቤት ለማለት ተገዷል እናም የናንተ የአቀራረብ ብስለት ታክሎበት መልዕክቱን ለአየር ታውሉልኛላችሁ ብዩ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡
መቸም የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ሲነሳ ተነግሮ አያልቅም ነገር ግን ቀደም የተፈፀመው በደል ላያንሰው አዳዲስና ከፀሐይ ጋር አብረው ብቅ የሚሉት የትም የለሉ ቢሆንም የቅርቡን ለመግለፅ ያህል
1. በመርሣ ከተማ አስተዳደር ነዋሪ የሆኑ 35 /ሰላሳ አምስት/ መንጃ ፈቃድ ያላቸው ነዋሪዎች በአማራ ክልል በቅርቡ እንዳያወጡ በመከልከላቸውና

ሙስና የበዛበት አሰራር ስላለ ወደ ተሻለውና አገሪቱን በበላይነት ወደ ሚመራው ክልል 1 ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ በመሄድ መንጃ ፈቃድ አውጥተው አሁን በከተማው የትግራይ ክልል መንጃ ፈቃድ አማራ ክልል ላይ አይሰራም በማለት ታግደዋል ፡፡ ክልሉ በማንና በምን እንደሚመራ ካለመታወቁም በላይ የወያኔን መሪነት ብአዴን መካዱ ይሆን ወይስ በአንድ አገር ሁለት ዓይነት ህግ መኖሩ ነው መልስ ያጣ ጉዳይ ሆኗል፡፡

2. በዚሁ በመርሣ ከተማ ዙሪያዋን በሚገኙ ወደ ከተማ የተከለሉ ቀበሌዎች ነዋሪ የሆኑ አራሽ ገበሬ ለፍቶና ጥሮ ለአመታት ጥሪቱን በሚያስጨርስ ሁኔታ የሰራውን ቤት ለምሳሌ አቧሬ አካባቢ የአቶ ሙመድ ሰይድ ቤት 8X9 የሆነ ቤት አገልግሎት በማይሰጥ መልኩ አፍርሰው ወደ ሌሎች መሰል ግለሰቦች ሲገቡ ነዋሪው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ባለስልጣኖቹን በመፈታተኑ እንዲባረሩ አድርጓቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በ25/6/2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 /አራት ሰዓት ተኩል / አካባቢ በዚሁ ከተማ ልዩ ቦታው መልካጨፌ ከተባለው አካባቢ የ8 /ስምንት/ ሰው አርሶ አደር ቤት አፍርሰው ወደቀጣዩ ሲሸጋገሩ ጉዳዩ ያበሳጨው ነዋሪ ህዝብ ከአንድ መቶ በላይ የሚቆጠር ፖሊስ ፣ሚሊሻ አመራር በመሆን ህዝቡ በአመፅ በመነሳት ከሃምሳ በላይ ጥይት ተተኩሶ ሁለት ግለሰብ አርሶ አደሮች የህዝብ ተወካይ ነን በሚሉ ታጣቂዎች ተመትተው ቆስለው ህክምና ላይ ሲገኙ የጣፋው ጠፍቶ ቀሪውን በትግል ማዳን ችሏል ይሁንና መብቱን መገፋቱ ሳያንሰው ብሎም በቤት ውስጥ የነበሩ መንታ የወለደች ሴት ሜዳላይ እንድትወድቅ ተደርጓል ድርጊቱን ለምን ተከላከላችሁ ተብለው ሁከት ፈጣሪ በመባል ማረሚያ ቤት ገብተው ይገኛሉ ፡፡ ቀሪዎቹ ነዋሪዎች የተተኮሰውን ጥይት ዋጋ እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል፡፡ ይህ የህዝብ ወገናዊነት ወይስ ምን ይሉታል ?

3. የህዝብን ሀብትና ንብረት ስልጣናቸውን ተጠቅመው የከበሩ የወረዳ አመራሮች ከመጠየቅ ይልቅ ወደ ፓርላማ እንዲገቡ ለከፍተኛ ትምህረት ተቋም ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ መሬት በሽልማት የሚሰጥበት ለህገ-መንግስቱ መሬት መሸጥ መለወጥ ላሳር የተባለበትን ለካቢኔ በሽልማት የሚሰጥበትን ሁኔታ ሲኖር ከዚህ እንደሚቀጥለው ይሆናል

ለአብነት ያክል፡-
• የቁጥር 27 ቀበሌን የገበሬውን መሬት የሸጡ ወይም እንዲሸጥ በቃለ ጉባዔ የያዙ የከፍተኛ ትምህርት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሲበረታቱ የቀበሌው አስተዳዳሪ ግን በ9/ዘጠኝ/ አይነት ክስ ተከሶ ማረሚያ ቤት ይገኛል

• በተጨማሪ11/አስራ አንድ ቤት /ያቃጠለ የአንድ ሰው እግር የቆረጠ ይባስ ብሎ በዚሁ ድርጊቱ ሳይበቃው ከሌላ የካቢኔ ጓደኛው ጋር በመሆን በሽጉጥ ከስደት ተመላሽ የሆነን ግለሰብ በሴት ምክንያት ጠግቦ አደሮች እጁ ላይ ተመትቶ በሆስፒታል በመረዳት ላይ ሲገኝ ይህ ሳያንስ ቤተሰቦቹ ተለቅመው እንዲታሰሩ ተደርጎ ሲቀጡ ጉዳዩን የፈፀሙት ባለስልጣኖች እድሜ ለስልጣን ብለው ሌላውን ባለተራ የጥይት ማረፊያቸውን ይጠብቃሉ።

4. የወረዳው አመራር /የሀብሩ ወረዳ ማለቴ/ ነው ከክልል በመጣ የኦዲት ባለሙያ በተረጋገጠው መሠረት አንድ አመራር ከ44 – 75 ሽህ ብር ከ365 ቀን በላይ በውሎ አበልና መሰል የወጭ ዘዴ ተጠቅሞ ከህግ ውጭ ማድረጋቸው ስለተረጋገጠ የክልሉ ኦዲተር ሪፖርት ቀርቦ እያለ እስካሁን ድረስ በህግ ፊት ሁሉም ሰው እኩል ነው የሚባለውን በነሱ ላይ ስለማይሰራ በፍታብሄርም ሆነ በወንጀል እንዳይጠይቁ ጠያቂና ተጠያቂ ጠፍቶ የአገር ሀብት ባክኖ ቀርቷል፡፡ አቤት የሚባልበት ቦታ ጠፍቷል ፡፡

5. ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ጉዳዮች ማለትም የገጠር ወረዳውና የከተማ አስተዳደሩ የሚፈፅማቸውን አላግባብ የሆኑ አሰራሮች መከታተልና መቆጣጠር የተፈፀመውንም ሆነ ችግሮች እንዳይፈፀሙ መከላከል ሲገባቸው ይባስ ብለው የወረዳው ፍ/ቤት ሰብሳቢ ዳኛ ከዳኝነት ነፃ የሆነው እንኳ ሳይቀር የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ ካቢኔ ተብየው እነዚህ አመራሮችና ሙሰኞች በህግ እንዳይጠየቁ ምርመራ ሲጀመር ከዞን ጀምሮ ምርመራ እንዲቋረጥ እየተደረገ የዳኝነት ነፃነት በሚጋፋ መልኩ በህግ ፊት ሁሉም ሰው እኩል ነው ተብሎ በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 25 ላይ በግልፅነት ተቀምጦ እያለ ለአመራር /ተሿሚ / ህጉ የማይሰራበት ለሌች ዜጎች ግን ተተንትኖና ተዘርዝሮ የሚሰራበት ወረዳ በመሆኑ ህግ አልባነት ወይስ ህግ የተላበሰ አሰራር ይህን ሁሉም መልሶ አጥቶበታል።

በአጠቃላይ በከተማችንና በወረዳችን ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር የሰዎች ሰብዓዊ መብት አለመከበር ድብደባ ዛቻና ማስፈራራት በመጠቀም ስልጣናቸውን ለማራዘም ከላይ ታች የሚባዝኑ ስለሆነ ለሀገርም ሆነ ለህዝብ የማይጠቅም በመሆኑ ይህነን አስነዋሪ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የማይመጥንና የማይገልጽ ነውር ተግባር በህዝቡ ስምና በራሴ ስም ለአየር ይበቃ ዘንድ መልካም ትብብራችሁን ከአክብሮት ጋር እንደማትነፍጉኝ በመተማመን አቀርባለሁ፡፡
የዘወትር አንባቢያችሁ ይነበብ ታምሩ
ከመርሳ ከተማ

ጉለቶቹን ለማጣራት ካስፈለገ ስልክ የከተማ አስተዳደሩ
ከንቲባ ስልክ 0921522287
የገጠር ወረዳ አስትዳደር ስልክ 0333330007(49)
የገጠር ፖሊስ ስልክ 03333300022(21) ክፋታቸው ካልበረታ ማገኘት ይቻላል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>