ከኡመልኸይር ቡሎ
ካዪላ ዊህለር የተወለደችው ሁለት እግርና አንድ እጅ ሳይኖራት ነው:: ሐኪሟም ዋናን እንደ አንድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንድትጠቀም ይመክራት ነበር። በእዚህ መሠረት ባደረገችው ጥረት ዊህለር ግን በ16ዓመቷ በዋና የዓለምን ሪከርድ ለመስበር ችላለች፡፡
ሲ ኤን ኤን እንደዘገበው ታዳጊዋ በብራዚል ሜክሲኮና ኔዘርላንድ ውድድሯን ያደረገች ሲሆን፤ በ2016 ፓራኦሎምፒክ ለመወዳደር እቅድ ይዛለች። በ2013 በተካሄደው50 ሜትር የሴቶች ሻምፒዮን ተወዳድራ አዲስ ሪኮርድ አስመዝግባለች፡፡
«ነገሩን ሁሉ ለመግለፅ አስቸጋሪ ነው። ስሟ ሲጠራና ዩናይትድ ስቴትን መወከሏን ሳውቅ በጣም ተገረምኩ፣ ማመን አቃተኝ፣ ከደስታ ብዛት የምይዝ የምጨብጠውን አጣሁ። ይች እኮ የእኔ ድንቅ ልጅናት አልኩኝ» ይላሉ እናቷጆሲ ዊህለር፡፡
«ሁሌም ምንም ማድረግ የማትችይው ነገር የለም እያልን እንነግራታለን። ነገር ግን ነገሮችን ላንቺ ማድረግ እንዲመቹ ማመቻቸት ይጠበቅብናል ስለምንላት እርሱዋም በጥረቷ ቀጠለች» ሲሉ አክለዋል።
ዊህለር በማትዋኝባቸው ጊዜያት ቤዝቦል እና ቦውሊንግ በመጫወት ጊዜዋን ታሳልፋለች በትምህርቷም ከፍተኛ ውጤት የምታስመዘግብ የደረጃ ተማሪ ስትሆን፤ በኮምዩኒቲ ኮሌጆች አድቫንስድ ኮርሶችን ትወስዳለች፡፡ ንቁ ተሳተፎም ታደደርጋለች፡፡
በእዚህ ዓመት ባስመዘገበችው ከፍተኛ የአትሌቲክስና የአካዳሚክ ውጤት «ስኩላ ስቲክ» የተባለ የክብር ስያሜ አግኝታለች፡፡
በርግጥ ዊህለር በ2012ም ፓራኦ ሎምፒክ ለመወዳደር ተመርጣ ነበር። ነገር ግን እንዳጋጣሚ ሆኖ አብሯት የሚወዳደር ሰው ባለመኖሩ ሳትወዳደር ቀርታለች። ምክንያቱ ደግሞ በፓራኦሎምፒክ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች የሚመደቡት እንደ አካል ጉዳታቸው ደረጃ በመሆኑ በእርሷ የጉዳት ደረጃ የሚወዳደር ሰው ባለመኖሩ ነው፡፡
« አምና በፓራኦሎምፒክ አልተወ ዳደርኩም ነበር። ምክንያቱም በእኔ ምድብ የምትወዳደር ሌላ ሴት ተወዳዳሪ አልነ በረችም። የእኔ ምድብ ኤስ ዋን ሲሆን፤ በእዚህ ምድብ የሚካተቱ ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው» ትላለች ዊህለር።
«ሃገሬን በመወከል መወዳደር እፈል ጋለሁ። አዲስ ሪኮርድ ማስመዝገብና ሜዳሊያ ማግኘት በጣም የሚያስደስትና የሚያስገርም ነገር ቢሆንም እኔ ግን ከውድድሩ ባሻገር አርዓያ በመሆን እዚያ ቦታ መገኘት እፈልጋለሁ» ብላለች።
↧
ሁለት እግርና አንድ እጅ አልባዋ የዋና ሻምፒዮን
↧