Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በጎንደር አድማ መርታችኋል የተባሉ 6 ታክሲ ሹፌሮች በእስር ቤት እየተንገላቱ ነው

$
0
0

የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)

የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)


ክሱን ከፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ለማገናኘት የሞከረው ፖሊስ አልተሳካለትም
ምንሊክ ሳልሳዊ :- በጎንደር ከተማ የታክሲ ሹፌሮች የስራ ማቆም አድማ ላይ ተቃውሞ አሰምታችኋል አድማውን መርታችኋል በሚል ሰበብ የታሰሩ 6 ሰዎች እንዳሉ ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል:: ከአንድ ወር በፊት የጎንደር ከተማ የታክሲ ሹፌሮች አዲሱን የትራፊክ የቅጣት ደንብ በመቃወም የስራ ማቆም አድማ መምታታቸውን ተከትሎ አድማውን አስተባብረዋል በሚል ሰበብ ተፈጥሮ ከየመንገዱ ከስራቸው እና ከየቤታቸው ታፍነው የተወሰዱ የታክሲ ሹፌሮች በእስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ መሆኑን ለወሕኒ ቤት ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል::

ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤት ቀርበው የዋስትና መብታቸው ሳይከበር ወደ እስር ቤት የተመለሱት የታክሲ ሹፌሮች ከሰማያዊ ፓርቲ የመጣ ትእዛዝ ነው የስራ ማቆም አድማ ያደረጋችሁት በሚል ጉዳዩን ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በሃሰት ለማገናኘት በፖሊሶች በሃይል ለማሳመን ጥረት ቢደረግም እንዳልተሳካ ምንጮቹ ገልጸው እስካሁን ምንም አይነት መረጃም ሆነ ማስረጃ መርማሪዎች በማጣታቸው በስራ ማቆም አድማ ላይ የተሳተፉ የታክሲ ሹፌሮችን በታሰሩት ላይ እንዲመሰክሩ በጥቅም እያግባቧቸው መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል::

በአድማው ወቅት የታክሲ ባለንብረቶችም የታሪፍ ማስተካከያ አለመደረጉን በመቃወም የታክሲ ሹፌሮቹን ተቀላቅለው የነበር ሲሆን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባለስልጣናት ሾፌሮቹና ባለንብረቶቹ ወኪል ልከው እንዲነጋገሩ በጊኤው የጠየቁ ቢሆንም ሹፌሮቹ “የክልሉ መንግስት ወከሎችን በተደጋጋሚ የማሰር ልምድ ስላለው ወኪል አንልክም” ብለው እንደነበር ይታወሳል::


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>