Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

[የለንደኗ ጽዮን ማርያም ቤ/ክ ጉዳይ] –ትግላችን ከሕወአትና ከግብረ-ዐበሮቹ ጋር ነው!

$
0
0

New Picture (15)
ፍርድ የእግዚአብሔር ነው! ወገን ተባበረን!
መጋቢት ፪ ፦ ፪ሺህ ፮ ዓም ከኮማንደር አሰፋ ሰይፉ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ።
ጻ! መንፈስ ርኩስ!!!
አሜን!!!
የቤተ ክርስቲያናችን ችግር ከጀመረ ረጅም ጊዜ ነው። አበው “ቁጭ ብለን የሰቀልነውን ቆመን ማውረድ አቃተን!” እንዳሉት ኾኖ ተካርሮ ለመዘጋት ከበቃች መጋቢት ፩ አንድ ዓመቱ ነው። ብዙዎቻችሁ ችግራችንን ችግራችሁ አድርጋችሁ ስትከታተሉ ስለነበር ሃተታ አላበዛባችሁም።
ባጭሩ፦ የመተዳደሪያ ደንባችን እንዲሻሻል ይወሰናል፦ከካህናትና ከምእመናን
አርቃቂዎች ይመረጣሉ፦በኅብረት ሥራቸውን ያኪያሂዳሉ
የልዩነታቸው መነሻ፦
መሠረቱ- የምእመናን ወኪሎች ቤተክርስቲያኗ ሕጋዊ ሰውነት እንዲኖራት
ያስፈልጋል ይላሉ።እስከዛሬ የተዳደርንበት ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ
ሃብትና ንብረትዋን በሚገባ አያስከብርላትምና። ይህም ማለት ባለዐደራዎቹን
በድምጽ ብልጫ ሕንፃ ቤ.ክርስቲያኗን ሳይቀር ለሌላ ሊያሳልፉ ያስችላቸዋል (አኹን በተጨበረበረ ሕጋዊነት፦ ምልአት እንኳን ሳይኖራቸው እንዳደረጉት) “ሊሚትድ ካምፓኒ ባይ ጋራንቲ” የሚባለው ግን ያለ ጠቅላላው ጉባኤ
ስምምነት በሃብቷና በንብረትዋ እንዳሻ ማዘዝ አይቻልም። ሲባል የካህናት ወገኖች ቀንዳቸው ቆመ። አለቃው ግን- ተስማምተው፦
- የሰበካ ጉባኤው ሊ. መንበር መነኩሴ እንዲኾን ፦
- አለቃውም፦- ደሞዝ ለመጨመር ፦
– ጉርሻ ለመስጠት
- የየንዑስ ኮሚቴዎች ሊ. መንበር እንዲኾን
ረቂቁ ውስጥ እንዲካተትላቸው ሲጠይቁ፦

ምእመናን አርቃቂዎች
ሊ. መንበሩ መነኩሴ ይኹን ማለቱ ቃለ- ዓዋዲውን “ከካህናት ውስጥ ይመረጣል” ስለሚል ያፈርሰውዋል። ያገሪቱንም ሕግ ይጻረራል፦ እንዲሁም የዴሞክራሲን መንፈስ፦ የተመዘገብንበትም የግብረሠናይ ድርጅት መመሪያ ስለሚንድ ልንስማማ አንችልም።
- ደሞዝ መጨመሩም የጠቅላላ የሰበካ አመራሩ ሥልጣን ስለኾነ፡
- ጉርሻ የተለመደ ስላልኾነና፡ ካስፈለገ ጉባኤው ሊወስነው ስለሚገባ
- የአለቃው የየንኡስ ኮሚቲዎችም ሊ. መ. መኾን፦ የየኮሚቴዎችን ሥልጣንና መብት ስለሚጋፋና ሥራ ስለሚበደል ፦
- አለቃው፦ በሊ.መንበርነት ሰበካ ጉባኤው ላይ የኹሉንም ከአባላቱ ጋር ኾነው ስለሚያዩት በገለልተኛ ዳኝነት ጉዳዩን ሊመረመሩት ይችላሉ። አለዚያ ግን ማንኛውንም በንኡስ ኮሚቴዎች የሚቀርበውን ኹሉ በፈለጉት መርተው ሰበካ ጉባኤው ስብሰባ ላይ ዳኛ በመኾን ፈንታ ጠበቃ በመኾን ሥራ ይበደላል፤፡ ስለዚህ
ንኡስ ኮሚቴዎችን ማጨናነቅና ሥራን መበደል ስለሚኾን
አንስማማም፦ በመባላቸው ካህናት ዐውደ-ምሕረቱ ላይ አሳዛኝና
አሳፋሪ ስብከታቸውን ቀጠሉ። ለአብነት አንድ ላቅርብ፦ “እኛ
ካህናት የምንለውን የማይቀበል በመንግሥተ-ሰማያት ቦታ የለውም።”

ይህ አባባል የቫቲካኖቹ የቅ. ጳውሎስን ርዕሰ አድባራት ሲሠሩና ገንዘብ ሲያጥራቸው ማይምኑን አማኝ፡”የሞተብህን ዘመድ እያሰብህ(ሽ) ገንዘብ ብትሰጠን የሞተብህ ዘመድ ከሲኦልም ቢኾን መንገሥተ-ሰማያት በቀጥታ ይገባል።” እንዳሉት አይደለም??!የኛዎቹ ግን ይባስ ብለው ወደራስ አዞሩት!!! አንዳንድ የታሪክ ጸሐፊዎች ስለዚህ ጉዳይ ሲጽፉ “ለማርቲን ሉተር የመጨረሻዋ ገለባ ይኽች ነበረች።”* ይላሉ። ጠንቁም ካቶሊክ ቤ.ክርስቲያንን አፍርሶ ፕሮቴስታንትን ወለደ። እኛ ጋ ምን በመፈለግ ነው??
የምእመናን አርቃቂዎች ጥያቄ አንድ ብቻ ነበር ነውም። ይኸውም ያረቀቅነውን የተማስማንበትንና ያልተማማንበትን ይዘን ወደ ሰየመን አካል (ጠ. ጉባኤ.) አቅርበን ጉባኤው ይወስን ቢሉ አሻፈረኝ ከማለት አልፈው – “የግል ኩባንያ ሊያደርጓት ነው..ለግላቸው ሊበደሩባት ነው… ምሥጢራት እንዲደፈሩ ሊያደርጉ ነው… ቀኖናን ያፋልሳሉ — ቃለ-ዓዋዲን ያፈርሳሉ ወዘተ” የወሬ ዘመቻ ባርቃቂ ጓደኞቻቸው፡ በቤ/ክርስቲያ ነባርና ቅን አገልጋዮች ላይ ከፈቱባቸው።

ይህ የወሬ ዘመቻ ያሳዘናቸው ሽማግሌዎች በገዛ ራሳቸው ተነሳሽነት ሊያደራድሩ ቢፈልጉ መለሷቸው። ምእመናን በዚህ ተስፋ ሳይቆርጡ ኹለት ጊዜ የተለያዩ ሽማግሌዎች የቀድሞው አለቃ “እኔን ካልደገፋችሁ በማለት አሳዝነውና አሳፍረው መርጠው ላኩ። የነእርሱም ልፋት ከመጀመሪያው አልተለየም። አሉባልታው ግን ነፈሰ።
እኔም፦ ‘እንዴት እንዲህ ይኾናል?’ በማለት ነበር ከምእመናን ዐርቃቂዎች አንዱን ስጠይቅ፦ በ ’እንዴት ጠረጠሩን’ ድምጸት የካህናቱ መግለጫ ባለፈው ሳምንት ነበር የኛ የሚቀጥለው ስለኾነ ሰምተው ይፍረዱ’ አለኝና ሄድሁ። ቀኖናውንና ቃለ-ዓዋዲውን ከካህናት በበለጠ አጥንተው፦ የፈረሰው በካህናት እንጂ በነርሱ አለመኾኑ ገልጸው “ እስቲ ቀኖና ፈረሰ ፦ ቃለ-ዓዋዲ ፈረሰ የምትሉትን በአንቀጽ ጠቅሳችሁ አቅርቡ ቢባል። ከየት??
ምእመናን አርቃቂዎች ለምእመኑ አንዲት የቀኖና አንቀጽ እንዳላፈረሱ፤- እንዲሁም ቃለ-ዓውዲውን ለሥራቸው እንደተመሩበት አስረዱ፤- ካህናት ግን ያወረዱባቸውን ሕዝቡን በሀሰት ሊያሳስቱ የሞከሩባቸውን በማስረጃ ሊያቀርቡ እንደማይችሉ ሲያረጋግጡባቸው፦
“ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ከአጥር ወጪ ታሳድራለች።” እንዲሉ ‘መነኩሴ ናቸው፦ አደራ ያከብራሉ፦ ቤተክርስቲያናንን አክብረው ያስከብራሉ፦ እኛንም ያስተምራሉ፦ ብንጣላም ያስታርቁናል። ባህልን ጠብቀው ያስጠብቁናል፦’ ብሎ የመረጣቸውን ምእመን በአሳፋሪና በአሳዛኝ ኹናቴ ከድተው አገራችንንም ሃይማኖታችንንም ለታዛቢ ጣሏቸው።

እኔንና መሰል አዛውንትን የሚያሳዝነን ቅዱስ መጽሕፍና እምነታችን እጅግ ያልዘለቀላቸውን ወገኖቻችንን ስላሳሳቱብን ነው። ለሥልጣንና ሹመት ብሎም ለጥቅም መፈጽም ላይ ያሉትን ወንጀል፦ “ለሃይማኖቴ ነው ብሞትም ግድ የለኝ|!” ሲሉ በውኑ ለሃይማኖት መሞትን የሚፈልጉ ከኾነ፦ ከአንድ አምስት ስድስት ዓመት በፊት ሲኖዶስ ውስጥ ብዙ ካህናት በአክራሪ እስላሞች እንደሚገደሉ አቤቱታ ሲያቀርቡ፦ ሟቹ የሲኖዶስ ሊ.መንበር፦ እንደ መቼውም ልባቸው ሥራቸው ላይ ስላልነበረ ፡” ማሕበረ-ቅዱሳን ይላኩ፡” ቢሉ አንድ ልባቸው የተነካ የቤተክርስቲያኗ ልጅ በንዴት ተነስተው፦” አላሁ አክበር!” እያለ እጸድቃለሁ ብሎ ወደሚገድለው ማሕበረ-ቅዱሳን ይሂዱ ማለት ምንድር ነው?” ያሉትን በማስታወስ በዕውኑ ለሃይማኖታቸው ስማእትነትን ማግኘት ከፈለጉ የኛ የቀድሞው አለቃና ግብረ-ዐበር ካህናት ወዳሉበት ሠፈር ለምን አይሄዱም?” እዚህ ወጣቱንና ያልዘለቀውን ከማሳሳት? ማተባችሁን በጥሱ ያላችሁ አለ? ከኛ ወገንስ ማተቡን የበጠሰ አለ?
ሊ. ጳጳስ አባ እንጦስ እንዳሉት፤ ‘ቤትክርስቲያን መዝጋት መንፈሳዊ አይደለም።’ በኢመንፈሳዊነት አቢይ ጾም በተያዘበት ዕለት፡ ዘጓት!! ይህም ያለንበእትንም አገር የተመዘገብንበትንም ሕግ ይጥሳል። በማግሥቱ አንድ-ኹለት ካህናት ይዘው ወደ ኤምባሲ ዘለቁ። በሦሰትኛው ቀን ወደ ሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሊ.ጳጳስ ቢሄዱ፦ “ አንተ… ቀድሞውንስ እኛ እዚህ እያለን ኤምባሴ ምን ወሰደህ?” ተብለው ከተዘለፉ በኋላ በኹለቱ የገዥዎች ወኪሎች፦ በኤምባሲውና በጳጳሱ መካከል መመላለሱ ጦፈ።
እነሆ! ስደተኛ ነኝ፦ የአ.አበባውን ሲኖዶስ ለ.መንበር ስም በጸሎት አላነሳም፦ አቡነ እንጦስ የተባሉት የወያኔ ካድሬ እኔ ካልሞትሁ የማርያምን ቤ/ክን በር አይረግጧትም! ብለው የደነፉት ጠቅልለው ከገዥዎቹ ጉያ ገቡ። ገዥዎቹም፦ ምናቸው ሞኝ?! ‘እንዲህ ብለኸን/አርገኸን አልነበረም ሳይሉ እጃቸው እስቲገባላቸው ድረስ ያሽሞነሙኗቸዋል። ከቅ.ማርያም ወደ እነ ጳጳሱ የሄዱትን ኹሉ አግደዋል፤፡ በኋላም በዚህ ዓይነት ያባረሯቸውን ካህናት ጫማቸው ላይ ወድቀው ማሩኝ አሉ። በኛ ላይ ወገን ለማብዛት።
አዲስ አበባንም አዘወትሩ። ቶሎ ቶሎ እየተመላለሱ በሄዱ ቁጥር ደግሞ ሻንጣዎቻቸው እየተወጠሩ ነው። ‘በምን?’ ውስጥ የማንገባው ሳናውቀው ቀርተን ሳይኾን በትዝብት ማለፍን መርጠን ነው። አኹን ይህችን ጽሑፍ እንዳቀርብ ያስገደደኝ፦ በጥቅምትና ኅዳር በውጣው “ ዜና ቤተክርስቲያን ዘ ኢትዮጵያ ” ላይ የሰጡትን ቃለ-ምልልስ አይቼ ነው።
ለመመለስ ይህን ያህል ጊዜ የፈጀብኝ፦ለጽሑፌ ርዕስ ተቸግሬ ነው። እንኳንስ የመነኩሴ ቆብ የደፋውን ማንንም ‘ ዋሾ ‘ ማለት ይከብዳል። የባህል ተፅዕኖም ቀላል አይደለም። መተዉ ደሞ ሊላውን የማሳሳት ተባባሪ መኾን ነው። በዚህ ውስጥ እያለሁ መጀመሪያ የመጣልኝ ርዕስ

“ከእውነት ጋር የሚያስተዋውቅልን/ የሚያስታርቅልን ያለህ!” ነበር፦
“ከታማኝነትስ?”
የሚለው ደግሞ ይጠዘጥዘኝ ጀመር።
እያመነታሁ ሳለሁ ‘በፍኖተ ዴሞክራሲ’ የኢሓፓ ሬዲዮን ላይ በአንድ ወቅት
(ለኔ ጥሩ የዜና ምንጭ ያለው ኾኖ አግኝቼዋለሁ።

“ ለምን ይዋሻል? – እስከ መቼስ ይዋሻል?”

የሚለው ትዝ አለኝ። ይህን ወደ መምረጡ ላይ ሳለሁ በቅርቡ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ደግሞ፦

“ የምዋሸው ዕውነቴን ለመቆጠብ ብዬ ነው።”

የሚል ርዕስ አየሁ። አይጣጣ ! ምን እዳ ገባሁ? እያልሁ መጽሐፍ ቅዱሴን ለመግለጥ ሳስብ፦ ‘ በደረጃ ሂድ እንጂ! ‘ የሚል ስሜት አደረብኝ። ስለዚህ ስለ ‘ ውሸት ‘ ምድራውያን ዐዋቂዎች ምን ብለው ይኾን? በማለት ማገለባበጥ ጀመርሁ። እዚያም ላይ ወደ እምነት ተመሳሳዮቻን ሄድ ብዬ መቃኘትን ሳስብ፦ የሩሲያን ደራስያንን መረጥሁ። በዚያው ባነበብሁት ቋንቋ፦
london
Simply put by Leo Tolestoy,

“ Anything is better than lies & deceits.” ብሎአል

The writer of “ The Brothers Karamazov “ Fyrdor Dostoyevsky

“ Above all, don’t lie to yourself. The man who lies to himself and listens to his own lies comes to a point that he cannot distinguish the truth within him, or around him and so loses all respect for himself and for others and having no repsect he ceases to lose love.” (አጽንዖቱ የኔ)
ይህን የቀድሞው አለቃ በየሄዱበት ስብሰባም ኾነ ቀብር ወይም ድግስ ቀምሰውታል። (ለተመልካች እስከሚከብድ ድረስ) እኔም አልጠቅስም!

ታዲያ ምእመናን ወገኖቼ፦ የዶስቶየቪስኪው ምክር ቅዱስ ጳውሎስ በመጀመሪያው የቆሮንቶስ መልእክቱ ም. ፲፫ ላይ ልብ በሚሠብር ዓይነት ያሠፈረልንን አያስታውሳችሁም? በትንሹ እነሆ፦ አጭር ናትና ምዕራፏን ዝለቋት።አደራ !! አኹን ግን ከ ቁ ፩-፫ ያሉትን ላስነብባችሁ፤፡
“በሰዎችና በመላእክት ቋንቋ ብናገር ፍቅር ግን ከሊለኝ እንደሚጮህ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ኾኛለሁ።ትንቢት ቢኖረኝ፦ምስጢርንም ኹሉና ዕውቀትን ኹሉ ባውቅ፦ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ኹሉ ቢኖረኝ፦ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ኹሉ ባካፍል ፦ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ፦ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።”
ታዲያ በኛ ላይ የሚመጻደቁትና ልጆቻችንን ያሳቱብን ካህናት ምን ለማግኘት ነው? ከአካባቢያቸው ውርደትን፦ ንቀትን.. ለምን? በገዥዎች ለመሾም!?!?

ለሦስት ከፍለውን፦ አንዱ ወገን በሀዘን እቤቱ ሲቀር ፦ ሌሎቻችን በዚህ አገር መራር ብርድ በአቢይ ጾም ከገረገራው ስንጸልይ የኛ ካህን መላከ ብርሃን ብርሃኑ ወደዚያኛው ወገን በመሄድ “ እባክችሁ አብረን እንጸልይ። ተለያይተን የምንጸልየው አያርግም።” ብለው ቢማጸኑ ከነሱ መዘምራን አንድ-ኹለቱ “እኛ ከአሕዛብ ጋር አንጸልይም!” ሲሉ፦ ጥቂቶች ተጨመሩላቸው። እውን እነዚህ ልጆች የ”አሕዛብን” ስንኳንስ ትርጉሙን ቃሉን ዐውቀውት ነው?
ወንድም እህቶቼ ሆይ፦ ያስረዘምሁባችሁ ግንዛቤያችሁ የተሟላ እንዲኾን ነውና ይቅርታ። እንደምንም ብላችህ የመጨረሻዋን ገጽ ተመልከቱልኝ አደራ!

ጌታ በወንጌሉ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ኹሉ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባህር መስጠም ይሻለው ነበር።” ማለቱ ተዘንግቶ ነው? ተንቆ!!
እዚህ ላይ ታናናሾቹ ሲል የእድሜ ጨቅላዎችን ብቻ አለመኾኑንእንደማይዘነጉት ተስፋ አለኝ።
በዜና ቤተክርስቲያን ላይ ለወጣው (የልብ-ወለድ) መግለጫ በብዛት ከላይ በተገለጸው የተሸፈነ ይመስለኛል፡፤ በተለይም ለችግሩ መነሻ የነበረውና አኹንም ድረስ ከቤተክርስቲያኗ ልጆች ጋር በጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ ከመነጋገር ብሎም ከመነጻጸር በየቦታው… የሚነዛው …ነው። አማርኛችን ሰፊ ሲኾን ለኹናቴው መግለጫ በሚኾኑት ለመጠቀም ትውፊትና ባህል ስለሚከለክሉ ልለፈው። የዜና ቤ/ክንን ለማጠቃለል፦ ከታሪክ መዝገብ
“ እባብ ሆነ ውቤ ሰውነቱን ትቶ
ሊነክ(ግ)ስ ነው አሉ ካቡን ተጠግቶ።”
የተባለውን “ያብዬን ለእምዬ!” ስለኾነ እዚያው ተቻቻሉበት። ከአቡኖች ብሎም ከሲኖዶስ የተጠጋው ማንነው? ያውም “ የፓትሪአርኩን ስም አልጠራም!” ካለ በኋላ!

አኹን በግለ ሰቦች ላይ በድፍንም ኾነ በነጠላ ሊያጎድፉ ስለሞከሩት ልመለስ።ከዜና ቤተ ክርስቲያን ሳልወጣ፦

“ ማንም ሳይወክላቸው ቤ/ክንን(ባልተጠቀሰ ቃለ-ዓዋዲ ተደግፈው)ኃላፊነቱ በተወሰነ የግል ኩባንያ ኹለት ግለሰቦች ባለንብረትነት በግል ስማቸውና በግል ባለ ንብረትነት በመኖሪያ ቤታቸው አድራሻቸው
በማስመዝገብ ቤ.ክንን በንግድ ተቋምነት ለመቆጣጠር እንዲያመች በሕገ ወጥ መንገድ በስውር አስመዝግበው፡ ተገኝተዋል።” ብለዋል። እግዜር ይቅር ይበልዎ።ድሮ የመስኮቡ ክሩሾቭ ሲናገሩ የሰማሁትን አስታወሱኝ። የቃል-በቃል ጥቅስ ሳይኾን መልእክቱ ‘ውሸትህ እንዲታመን ከፈለግህ እውነት ቀላቅልበት’ ነው። እዚች እጠቅስኋት ውስጥ እውነቱ ኹለት ጽኑ ስደተኞች ኢትዮጵያውያንና ለቤተክርስቲያንዋ በገንዘብም በጉልበትም የለፉ የተባለውን መፈጸማቸው ነው። ሌላው እውነት በግል ስማቸውና አድራሻቸው ማድረጋቸው ነው። ያደረጉበትም ምክንያት የቀድሞው አለቃ ለሌላ አሳልፈው ሊሰጡ ቢሞክሩ ባለቤት እንዳለው በማስመዝገብ በድብቅ ስም እንዳይዘዋወር ነው። ይህም ሠርቷል። የቀድሞው አለቃ ይህን ሊያውቁ የቻሉት የተፈራውን እኩይ ተግባር ሊፈጽሙ ሄደው ‘ ይህማ ባለቤት አለው!’ በመባላቸው አይደለም? እንግዲያውስ በባለቤትነት መመዝገባቸው እንዳለ ኾኖ ርሳቸውም በአለቃነቴ እንዳለሁ ነኝ እያሉ እያስቸገሩ ሳሉ፦ ታዲያ እነዚህ በባለቤትነት የተመዘገቡትን ግለ-ሰቦች በሕገ-ወጥነት ባለቤትነቱን ከወሰዱ ለምን አልከሰሱም? አለመክሰሳቸው ትልቅ የእምነት ጉድለትን አያሳይም? ሕጋዊ ተግባር መፈጸማቸውን ካወቁ ለምን ለአሉባልታ አበቁት? በሃሰት ለመወንጀል? ሊላው ሃተታ ኹሉ ክሩሾቭ እንዳሉት ነው።
-“ …ካህናት በሥርዐተ ጥምቀት ላይ በጸሎት እንዳሉ መስቀል በመቀማት…” እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ! የማን መስቀል ተቀማ? ግቢውን በፖሊስችና በውድ ዋጋ (በኤምባሲ) በቀጠሯቸው በግል ጠባቂዎች ሞልተውት ነበር፦ ታዲያ እውነት ከነበረ የቢተክርስቲያኗ ንብረት ሲቀማ ለምን አላስመለሱም? ይህም
በሕግ የሚያስጠይቅ ነው።
የአንዳንድ ሰው ለልበ-ወለድ ነገር ያለው ስጦታ ይደንቃል።

“ …በሕገ-ወጥ መንገድ የመረጧቸውን ግለ-ሰቦች ስም ለባንክ በማስተላለፍ የቤተ ክርስቲያኑን የባንክ ሂሳብ በግለ ሰብ አድራሻ በማዞር …” እንዴ እስካሁን ድረስ እንዳሉት የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ሲዘረፍ እያወቁ ሕግ ባለበት አገር ዝም ካሉ ተጠያቂው ርስዎ መኽንዎን በራስዎ መሠከሩ። በችሎታ ማጣት ነው ይባል? ኃላፊነትን አለማክበር? ወይስ በግድ-የለሽነት?
- በተሰለጠነበት የልብ-ወለድ ዝባዝንኬ በኋላ “…ቤተ ክን ውስጥ በጫማቸው ዘልቀው በመግባት…” ፈሪሃ እግዚአብሔርን ፈጽማችሁ ከልባችሁ አውጥታችሁታል ማለት ነው? ይህ ኹሉ አገር ውስጥ ይህንን …የሚያነብቡትን የእምነት ወገኖቻችንን ለማሳዘን? ምን አጠፉ? እነርሱማ ሃዘን ምን ገድዶአቸው? በሽ-በሽ አይደለም እንዴ? ብሎም በኛ ለማስፈረድ? እንደተጫማ እንደ ኹል ጊዜም የሚገባ በእግዚአብሒር እጅ የተያዘና የአገሪቱም የጤና ተቅዋምተገቢውን ድጋፍ የሚያደርግለት አንድ ወንድማችን መኾኑን እያወቁ? አገር ውስጥ ያለውን ሕዝበ ክርስቲያንን ማሳሳት ይገባል? የውጪው አነሰና ነው?
እኛን ስደተኞችን ለማስጠላት? ይህ ወንድማችን ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ ጽኑ አገልጋይ መኾኑን የማያውቅ የለም።

ዜና ቤ/ክን አንድ ወገን ሰምቶ ሳያጣራ በዚህ ወገን ያለነውን ክብር በመንካትና ሌላውንም ሕዝብ በኛ ላይ በማሳሳቱ ይህን መልስ ለማስተካከያ ካላተመው በጸሐፊውና ባታሚው እንዲሁም በባለቤቱ ላይ ሕጋዊ ርምጃ የመውሰድ መብታችን የተጠበቀ መኾኑን እናስታውቃለን
“የጋዜጣው መለክት” ብሎ ውሸት ተቀብሎ ውሸትን ያባዛው በውሸትም አንባቢያን ወገኖቻችንን ያሳሳተው ሳይውል ሳያድር የሚገባውን ነገር መፈጸሙ ይጠቅመዋል። ይህ፦”ጌታዋን የተማመነች..” ሂደት ውሎ አድሮ ያስከፍላል።

ግለ-ሰቦችን በሚነካ ጉዳይ!

በገዜጣው ለወጣው የግለ-ሰቦችን ለማጠቃለል፦

“ ከካህናቱም መካከል እነ ቄስ ብርሃኑ ብሥራት የመሰሉት…” ተብሎ
የተጻፈው መላከ ብርሃን ብርሃኑ ናቸው? ሳይመነኩሱ የመነኩሴ
ባህርይ ያላቸው፦ የተማሩ፦የተከበሩና የተወደዱ፦ ጽኑ አገልጋይ
ጥሩ መምህር፦አርአያነታቸው የሚፈለግ፡ ናቸው ከሚኖሩበት ከለንደን
ከምስጋናና ፍቅር በስተቀር ስንኳን የጸያፍ ነቀፌታ ቅሬታ እንኳን ሰማሁ
ያለኝ አላጋጠመኝም። እስቲ ዘርዘር አድርጌ ግልጋሎታቸውን ለንባቢያን
ላቅርብ፦

ሀ- በአሜሪካ-
-ሜሪላንድ – ቦልቲሞር፦ ደብረ-ብርሃን ቅ. ሥላሴን መሥራች
-ላስቬጋስ – የኃመረ ኖኅ ኪዳነ-ምሕረት ወሚካኤል አቋቋሚ
ለ- በአውሮፓ፦
– ስዊድን፦ ደብረ-ሰላም ቅድስት ማርያም መሥራች
– ስዊትዘርላንድ፦በርን የደብረ-አሚን ተክለሃይማኖት “
– ሆላንድ፦ ዴንሃግ፦ የዉሉደ-ብርሃን የወጣቶች የሰንበት ት/ቤት መሥራች

ስለርሳቸው የሚሰማው ፍቅር፦ ውዳሴና አክብሮት ነው። ይበልጥ ደግሞ
ቀድሰው ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ፈትተው አቀብለው በመጨረሻ
በእጃቸው በሚያሳልሙበት ጊዜ ትንፋሻቸው ‘ቁርጥ-ቁርጥ’ እያለ፡ ወደ ሴቶች
ወተት ማውጫ ይወርዳል ተብሎ ተነግሮባቸው አይታወቅም።

ታዲያ እኒህን በስም ሳይመነኩሱ በግብር የመነኮሱትን በብቁ
ችሎታና በመልካም ግልጋሎታቸው ከቀድሞው አለቃ ቢያንስ
ከአራት ዓመታት በፊት
የ ‘ መልአከ ብርሃን ‘ ማእረግ የተሰጣቸውን በርስዎ የተነፈጋቸው በምን ሥልጣን ነው? ወይስ ማእረጉ የተሰጣቸው በብቸኛነት በአሜሪካ፦በዌስት ኢንዲስና በደቡባዊ አፍሪካ ለቤተ ክርስቲያናችን ከአርባ ሺህ
ልጆች በላይ ልጆች ባፈሩላት የምራባዊው ዓለም ሊቀ ጳጳስ በነበሩት መሾማቸው? ወይስ እኚህ የተቀደሱና የተባረኩ እውነተኛ የኢትዮጵያና የቤተክርስቲያኗ ልጅ ቆራጥ ልጅ በቀውጢው ጊዜ ልጅነታቸውን እንደ ብዙሐን ተብረክርከው ያልካዱ በስደተኝነት ለብዙሐን አርአያ መኾናቸው ተብረክራኪዎችን አስቀንቶ የርሳቸውን ሹመት ላለመቀበል የተደረገ ሴራ ነው? ጌታዬ ይግባኝ በሌለብት ቃሉ “ማንንም አባት አትበሉ!” ባይል እኒህን ሊ.ጳጳስ አቡነ ይስሐቅን ‘አባት!’ ብላቸው ክብር ይሰማኝ ነስበር። መሬት ይቅለላቸው።
ይህም ቢኾን፦ በቆሙበት አለመርጋት ነው። በአራተኛው ፓትሪአርክ የሚመራው የውጪው ሲኖዶስ የሾማቸውን እንቀበላለን ተብሎ የለ? አሳዛኝና አሳፋሪ! ይህ ኹሉ ልፋት ምድራዊ ጌቶቻችሁን ለማስደሰት? ታዲያ ጌታችን

’ለኹለት ጌታ…” ያለው ተፈጸመባችሁ አይደለም? ማንን ለማስደሰት?
ትርፉ ትዝብት ነው።
ወገኖቼ
“የገብርኤልን መገበሪያ የሰረቀ ሲለፈልፍ ያድራል!” ሲባል ሰምታችሁ የለ!?

“ይሁን እንጂ በለንደን ያለውየኢትዮጵያ ኤምባሲ በታቻለው መጠን እየረዳን ስለሆነ…”
ብለው አፍረጠረጡት፦ ይህ ተሰውሮን ሳይኾን… ሕገ-መንግሥታቸው
“መንግሥት በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ አይገባም።” ያለውን በማፍረጥረጥ ማስረጃ መስጠታቸውን ነው የወደድነው።

የኤምባሲው ርዳታ ምን ምንን እንደሚያጠቃልል በክፍል ኹለት እገልጻለሁ

እነዚህ በደርግ የጦር ሹማምንትነት የሚብጠለጠሉት የቀድሞው አለቃ “ከሸፈቱ ይቅርታ፦ እውነተኛ አቅዋማቸው ከተገለጸ በኋላ፦” የመጡ አይደሉም።ኹሉም፦ ማለት ይቻላል፦ከርሳቸው በፊት በተለያዩ የቤተክስቲያኗ ኮሚቴዎች ውስጥ ያገለገሉ ናቸው።ቤተክርስቲያኗም ከዕዳ ነጻ እስክትደርስም ኾነ በኋላ በተፈለጉበት ተግባራት ተሠማርተው አገልግለዋል አኹንም ያገለግላሉ። አንዳንዶቹማ መነኩሴ አገኘን ብለው እንደግል መኪና ነጅነት ድረስ ያገለገሉበት ወቅት ነበር። ዋጋቸው መወረፍ ኾነ እንጂ- በቀድሞው አለቃ በኩል!
ደግሞ ፖለቲከኞች – ፖለቲከኞች የሚባለው ባገር ላይ የተጫኑትን ተቃዋሚዎች ለማለት ነው እንጂ ሊላ ምክንያት ምንም የለ። ይህም ገዥዎቹ የሚቃወማቸውን ኹሉ “አሸባሪ!” እንዲሉ የገዥዎቹ ደጋፊነታቸውን ለማረጋገጥ የገዥዎቹን ተቃዋሚ ስደተኞችን “ፖለቲከኛ!” በማለት ለመቅረብ መኾኑን የሚያረጋግጥ ነው።
አንዱ ‘ፖለቲከኛ – ፖለቲከኛ’ ሲባል የመለሰው ለጥቅስ የሚገባ ነው። “እኔ እኮ ክርስቲያን የኾንኩት እንኳን ፖለቲከኛ ልባል ፖለቲካ የሚባል ነገር ሳልሰማ ነው።” አለ። የቀድሞውም አለቃ ፖሊስ ጠርተውና በዐውደ-ምህረቱ ላይ ከነጫማው እጁን ይዘው መጥተው ፖለቲከኛ የተባለው ወንድማችን ሲናገር፦ “ዚስ ዚስ ፖሊቲካ! “ ቢሉት ፖሊሱ ገርሞትና ታዝቦ “ እዚህ አገር ማንም ባመነበት የመናገር መብት አለው። ፀጥታ ያደፈረሰበት ኹናቴ የለም።” ብሎ እጁን አስለቅቆ እንደ ወጣ ተነግሮኛል። እዚህ ላይ በሰበባ-ሰበቡ ፖሊሶች ሲጠሩና ዐውደ ምሕረቱም ላይ ሲያንጓጓቸው ሳይጫሙ ኖሯል? ይህ ማነብነብ ከወጣትነት ትምሕርቴ አንድ ነገር አስታወሰኝ። “ብዙ ሲዋሹ ለአንዳንዱ ዕውነት ይመስላል”
የሚባለውን። ማንን ለማሳመንና ከማንስ ወገን ለመኾን የተደረገ ስልትና ጥረት እንደኾነ “ዶሮ ጭራ የምታወጣው ነው።”
በተረቀቀው ውስጥ አርቃቂዎቹ ‘ለፖለቲካ መነገገሪያ ትኾናለች’ የሚል እንኳን ተነባቢ ዐረፍተ-ነገር በአንድምታ የሚደረስበት ዐረፍተ-ነገር ቀርቶ መንፈሱ አለ??
ወደ ትውስታዬ ስመለስ ዝነኛው ሼክስፒር በጻፈው ጁሊየስ ሲዘር ላይ
“ ከንቱ ስባሄን አልወድድም!” ይላል ጁሊየስ ሲዘር፦ ጸሐፊውም
“እንዲህም በማለቱ ሲዘር ራሱን በከፍተኛ ደረጃ በከንቱ አወደሰ!” ይለዋል።(ከንቱ ስባሄ ለራሱ አደረገ ሲል ነው) የቀድሞውም አለቃ ፖለቲከኛነታቸውን በዚህ መልክ ያለማቋረጥ ያነበንቡታል።
አኹንም ወገኖቼ ሕወአትንና ግብረ-ዐበሮቻቸውን ለማስደሰት በተናገሩ ቁጥር የደርግ ከፍተኛ መኮንኖችንና በተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት ውስጥ ተሳታፊዎችን በመወረፍ ጌቶቻቸውን ሲያስደስቱ፦ሼክስፒር እንዳለው የራሳቸውን ፖለቲከኛነት በነጋሪት ያስተዋውቃሉ። ለማያውቃቸው!!!

ይባስ ብለው “ ንጉሡን ያወረዱ፦ ፓትሪአርኩን ያስገደሉ” ማለታቸው ተወርቶአል። እዚህ ላይ፤
“አንተ ግብዝ፦ ሌባ ጣትህን በሰው ላይ ስትቀስር ሦስቱ ጣቶችህ ወዳንተ ማመልከታቸውን አትርሳ” ያለውን ማስታስወስ ይጠቅማል። በ ፷፮ ዓም ወሬው ኹሉ ስለ ሶሺያሊዝም በነበረበት ጊዜና ሕዝቡም ስለሶሻሊዝም የሚያውቀው ፀር-ሃይማኖትነቱን ስለነበር ቆዝሞና አጉሞተሞቶ ነበር። ይሄን ጊዜ ያኹኑ ሊ.ጳጳስ መልከጼዴቅ፦ ሊ/ሥልጣናት ሃብተማርያም ለቤተክርስቲያናችን እሁድ እሁድ ጠዋት የሬዲዮ ፕሮግራም አስፈቅደውላት ስለነበር በዚች ፕሮግራም አንድ ጎረምሳ “ቀሲስ” ‘የሶሺያሊዝምና የወንጌል ትምሕርት አንድ ናቸው። ኹለቱም ኹለት ያለው አንዱን ለሌለው ይስጥ ይላሉ’ ብሎ ሕቡን ያስተኛ በማን ፈቃድ ነበር? ካለስ በኋላ ከቤ/ክን ሃላፊዎች “ወንጌልንና ሶሻሊዝምን በአንድ ዓይነት አታቀርብም!” ብሎ እንኳን ቅጣት ግሳጼስ አድርሶበታል? ሲኾንስ ጠንካራ ማስተባበያ መስጠት አይገባትም ነበር?? አኹን ታዲያ ‘የእምዬን ለአብዬ’ መስጠቱ ሕወ አትንና ግብረ-ዐበሮቹን በማስደሰት ለመሾም ነው?? ይበልጥ ደግሞ የስደተኛን ንብረት በማስረከብ!!! ማን ይኾን በነገ ሊያዝዝ የሚችል?

በጉዳያችን ገብተው ስለነበሩ ወይም ስለገቡ ሊ.ጳጳሳትና ስለ ሲኖዶስ በክፍል ኹለት እገልጻለሁ፡
አንዳንድ የቤት ክርስቲያኗ ልጆች፦በብዙ ልፋት አርቃቂዎች የሠሩትን ለባለ ጉዳዮች እንዲያቀርቡ ኾኖ፤- ካህናት የረቂቁን መግለጫ ተራቸውን ጨርሰው፦ የምእመናንም ወኪሎች ተወጥተውት በስምምነቱ መሠረት የጠቅላላ የምእመናኑ ተራ ላይ ካህናት “እኛ በቀረበው ላይ መናገር አለብን።” ሲሉ ምእመናን በውስጣቸው ታምቆ የነበረው ፈንድቶ “የኛ ተራ ነው!” ባሉ ጊዜ ኹኔታው ለቁጥጥር የማያመች ነበር። ከዚህ ቀደምም እንደገለጽሁት፦ በዚህ ጊዜ የቀድሞው አለቃ ከዓውደ ምሕረቱ መድረክ ወደ ምእመኑ ሲመጡ ሳይ፦ በነበረብት ኹኔታ ቢወርዱ የሚከተለውን በመፍራት ለመከላከል ስሄድ፦ አንድ በጣም ትሁት፦ ሰላምተኛና ታዛዤ የነበረ ወጣት፡ ፊቱን አጨማድዶ “ርስዎ ደግሞ ምን ሊያደርጉ መጡ?” ያለኝ አይረሳኝም። እንዲሁም ከህቶቻችን “ኮማንደር -ኮማንደር- አይሂዱ! አይሂዱ!” ከሚሉት ውስጥ አንዷ ልብሴን በመጎተት የተማጸነችኝን አስታውሳለሁ። ይህን ያነሳሁበት፦ የቀድሞውን አለቃ ከአፋፉ ላይ ሳገኛቸው “ይህን ኹሉ ያቀነባበሩ ርስዎ ነዎት!” በማለት ወደ ተረበሸው ሕዝብ በጃቸው አመለከቱ። ለካስ ‘ እባክዎ አይሂዱ!’ እያሉ የሚከላከሉኝ በቀድሞው አለቃ እኔን የነገሩ አንቀሳቃሽና የኋላ መሪ አድርገው ያሳድሙብኝ ስለነበር ነው።
ይህ ክብር ለኔ በምንም ምን አይገባኝም። “ከብት ያልዋለበት ኩበት ለቀማ !” ነው። ከዚህ ቀደም በዚቹ ቤ/ክን የተነሳ ስሜ ተጥርቶ ስለነበር አኹንም ለማያያዝ ነው፤፡ ከእውነት የራቀ ኾነባቸው እንጂ።የመጣሁት ከቦካ በኋላ ነው እውነቱን አግኝቼ ለማግባባት ልሞክርም ነውይኸውም ካህናት ‘በተነገረው ላይ መልስ አለን!” ሲሉና ምእመናን በአጽንኦት ሲቃወሙ አበራርጄ ካህናት የጠይቁት እንዲፈቀድላቸው ማድረጌ በቂ ማስረጃ ነበር። የቀድሞው አለቃ ግን ሰውን አሳሳሱት!! በተለይ መዘምራንና አንዳንድ እህቶችን። ይቅር ይበላቸው! ይበለን።

ይህን ክፍል ሳጠናቅቅ በልዩ ማሳሰቢያ ነው፦
 በመጀመሪያ የመጨረሻውን ስብሰባ የመራኸው ለእኩል ሰዓት
ቆሜ ስለሥርዐት! ስለ ስምምነት! ስለ ኅሊና፦ ስለእግዚአብሔር
ብዬ ስማጸን ፍጆታ የከለከልኸኝ ካህን አንዲት ግሩም እህታችንን
ለመጨረሻ ጊዜ ለመሸኘት ደቡብ ለንደን መካነ መቃብር
ስንጠብቅና አስከሬኑን የያዘ መኪና ሲቃረብ ከመኪና ልወርድ
ስከፍት ጉልበቴ ላይ ተደፍትህረጅም ለመሰለኝ ጊዜ የቆየኸው፦
ከኹለታችንም አንድ ትንፋሽ ሳይወጣ የተለያየነውን በተለያዩ ስሜቶች አስተውሳለሁ። ዋናው የኢትዮጵያዊነት መሠረተ ጨዋነት እንዳለህ ነው። ለዚህም አመሰግንሀለሁ።
የሚበልጠው ግን መሠረተ ክርስቲያንነትህ ስለኾነ
ኹለተኛው፡ አንድ በጣም ሰላምተኛና ጨዋ የቅዳሴ ጠበልም ታመጣልኝ የነበርህ ከአሥር ቀናት በፊት መውጫው ላይ ተገኛኝተን “ለምን ርስዎ ደግሞ መጡ?” ብለህ በጠቆረ ፊት ለምን አነጋገርኸኝ ስልህ የመለስክልኝን የመቆርቆር መልስ በምስጋና ተቀብያለሁ። ግን..
ሦስተኛ፡ አንዲት ወጣት መዘምር ችግራችንን በፍጥነት ለመፍታት
“ ከቅዳሴዎቹም አጭሩን፦ ትምሕርቱም ከተነበበው ወንጌል ባጭሩ፦ከሓውርያት አባቶቻችን የወረስነውንከቅዳሴ በኋላ ምእመናን አምጥተው ኹሉም የሚቋደሰውውን ከግሪክኛ “አጋጴ!” (ፍቅር) የተባለውን ካህናት ምእመናንን ትተው በመኮምኮም ብዙ ጊዜ የሚያጠፉትን ሲኾን አቆይተው አልያም ፈጠን ብለው ችግራችንን እንፍታው በማለቴ አንዳንድ ነገር ልታስምሪኝ መጥተሽ “ ኮማንደር-ኮማንደር የሚባሉት ርስዎነዎት? ያልሽኝና ትንሽ የተነጋገርነው
-እንዲሁም አሕዛብ ያላችሁን ሊሎችም የጋራ ችግራችን ግልጽ ያልኾነላችሁ እባካችሁ ሐሙስ የካቲት ፲፩ ቀን (20/03) እምሽቱ ፲፪ ሰዓት (6ፒ ኤም) ኢትዮጵያውያን ተራድኦ ማሕበር ተገናኝተን በአገርና በአንዲት ቤ/ክን ልጅነት እንወያይ። እናንተም የእኛን ዐቅዋምና ምክንያት ትረዱልናላችሁ፦ እኛም የናንትን ከዚያ በኋላ በየዐቅዋማችን በወንማችነት/እህትማማችነት/አባትና – እናት ልጅነት የሰደት ኑሮአችንን እንቀጥላለን። የምን ጠብ፦ የምን ኩርፊያ? ማንን ለማስደሰትና ለመጥቀም?!!?

ተንኮልና፦ ክፋት የተመላባቸው የጠላት መሣሪያዎች እንዳንገናኝ የማይሞክሩት የለም። እናንተ ግን በነፃ አገር በነፃነት የምትኖሩ እንደመኾናችሁ በዐእምሮአችሁ ለኅሊናችሁና ለሃይማኖታአችሁ ታዘዙና ወስኑ።እኔና የእኛን ዐቅዋም ሊያስረዱ የሚችሉ በሰዓቱ ተገኝተን እንጠብቃችኋለን።
አድራሻው 3A, Lithos Rd. (off Finchley Rd) Stations Fichley Rd & Finchley Rd & Busses 13, 82, 113, 187, 268
ፈቃዳችሁ ቢኾን በስልክ ቁትር 0207 794 4265 እንደምትገኙ ብታስታውቁን ይጠቅምውናል።

እሁድ የካቲት ፳፫ ቀን ጠ.ጉ. ተጠርቶ ካስተላለፋቸው ውሳኔዎች ውስጥ
- ጉዳያችን ባስቸኳይ ፍ/ቤት እንዲቀርብና
- ጉዳያችንን አለ አግባብ ሲያሽ ያከረመብንን ያገሪቱን የግብረ ሠናያት ድርጅት (ቻሪቲ ኮሚሽንን) በጥምር ተከሳሽነት እንዲቀርብ ተውስኖአል።

ይህ ማለት ወጪው የትዬ ኤለሌ መኾኑን አጥተነው አይደለም። ተስድደን ካለንበትም መጥተው ትግራይን እንገነጥላለን ባዮችና ግብረ-ዐበሮቻቸው በገንዘባችን የገዛነውን አናስነጥቅም በማለት ነው፤፡ ያገራችን አይበቃም!!?? ሊተባበረን ሊረዳን አብሮን ሊቆም ለሚፈልግ ወገን በ

NatWest Bank, Account name Save St. Mary of London—Sort Code: 60-19-26, Account no. 29112052
ለምትተባበሩን ኹሉ ልባዊ ምስጋናችንን እያስቀደምን ሂደታንን ለማሳወቅ ይመች ዘንድ ማድረጋችሁን በ commanderassefa@yahoo.co.uk
ብትገልጹልኝ አስታውቃችኋለu።

በክፍል ፪ ፦
— በጉዳያችን በገቡት ሊቃነ ጳጳሳት ኮራንባቸው
ወይስ?
— እንደሚሉት የሲኖዶስ ልዑካን ነበሩ ወይስ?
— ሲኖዶስ ዐውቆም ኾነ ሳያውቅ / ፈልጎም ኾነ
ተገድዶ ‘…እንዳያንሠራራ አድርገን
አሽመድምደነዋል..’ ብሎ ከሚፎክርበት ጋር የሚ..?
—ያገራችን ገዥዎች ባለንባት አገር መንግሥት ላይ
ተጽዕኖ እያረጉ ነው ወይስ?
የሚሉትን ዓበይት ጉዳዮች ስለምዳስስ እነምትከታተሉን ተስፋዬ ጽኑ ነው

ወስብሀት ለእግዚአብሔር!


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>