ቃሊቲን ጨምሮ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች በሃሰተኛ ሕወሓት ሠራሽ ክሶች ወደ ዘብጥያ ሲወረወሩ ይህን ሃሰተኛ ክስ በማስፈጸም ታማኝነታቸውን ሲያሳዩ የከረሙት አቶ ብርሃን ሃይሉ ከስልጣናቸው መነሳት አሁንም ለሆዳቸው አድረው ከመንግስት ጎን በመቆም የሕወሓትን የበላይነት ለማንገሥ እየሰሩ ላሉት ባልሰልጣናት ትምህርት ይሆናቸዋል የሚሉ አስተያየቶች እየተሠነዘሩ ነው።
በአሁኑ ወቅት በመላው ኢትዮጵያ በአንካሳ ሕግ እስር ቤት ለሚማቅቁት ወገኖች አናካሳውን ሕግ በማስፈጸም ረገድ ተጠያቂ እንደሆኑ በህዝብ ዘንድ የሚመሰከርባቸው አቶ ብርሃን ሃይሉ ከዚህ ቀደምም በፈረሰው ማስታወቂያ ሚ/ር በሚኒስትርነት ማዕረግ በመሥራት የሕወሓት መንግስት የነደፈውን የመናገር መብትንመንፈግን ሲያስፈጽሙ ቆይተዋል።
ሚንስትሩ እ.አ.አ በ2005 ዓ.ም. በማስታወቂያ ሚንስትርነት ሲሰሩ ነበር። ሆኖም ማስታወቂያ ሚንስትር እንዲፈርስ ሲደረግ፤ በቀጥታ ሌላ ሹመት በማግኘት የፍትህ ሚንስትር ሆነው ኢህአዴግን በታማኝነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
ከሰሞኑ የባልስልጣናት በሙስና መታሰር፤ የአቶ ብርሃን መባረር ኢሕአዴግ ውስጥ ያለውን ሽኩቻ ያሳየ ነው የሚሉት አስተያየት ሰጪዎ አብዛኛው የኢሕ አዴግ ባልስልጣናት በሙስና ተጨማልቀው እያለ እነዚህ አሁን የታሰሩትን፤ ሁሉም የኢሕ አዴግ አመራሮች የአምራርነት ብቃት የሌላቸው መሆኑ እየታወቀ ጊዜ ጠብቆና ባልስልጣናቱ ለምን? ማለት ሲጀምሩ እንደብርሃን ኃይሉ ከስልጣን ማሰናበት የተለመደ የወያኔ የፖለቲካ አካሄድ ነው ሲሉ ሃሳባቸውን ይሰነዝራሉ።
አቶ ብርሃን ኃይሉ ሥልጣን ላይ በነበሩ ጊዜ ስለ እስክንድር ነጋ ጠረጴዛ እየመቱ የተናገሩትን ለግንዛቤ እንደሚከተለው ቪድዮውን አቅርበነዋል።