የህብር ሬዲዮ የካቲት 30 ቀን 2006 ፕሮግራም
እንኳን ለዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን አደረሳችሁ
<...የአምስት ሺህ ሜትር ሩጫ ላይ ተሳትፈው ተቃውሞ ያቀረቡት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሴቶች ከታፈኑ በሁዋላ የተወሰዱት የካ ፖሊስ መምሪያ ነው። እዚህ ይሄው ይፈቷቸዋል ብለን የፓርቲው አመራሮች ጣቢያ በር ላይ ነን እስካሁን አልፈቷቸውም ...>>አቶ ወረታው ዋሴ የሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ጉዳይ ሀላፊ በአደባባይ ተቃውሟቸውን ያሰሙትን የፓርቲው አባላትን አስመልክቶ ከሰጡት ቃለ ምልልስ (ሙሉውን ያዳምጡ)
<<...እነዚህ የጣይቱ ልጆች መሆናቸውን ያስመሰከሩ በይፋ ተቃውሟቸውን ያስመሰከሩ ጀግኖች ናቸው። እኛ እዚህ ሆነን ምን እያደረግን ነው...?>>
አቶ ጌታነህ ካሳሁን የሰማያዊ ፓርቲ የሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ኮሚቴ ሰብሳቢ ለህብር ከሰጡት አስተያየት (ሙሉውን ያዳምጡት)
<...እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የአገሩ ድንበር ለሱዳን ተላልፎ እንዳይሰጥ መቃወም አለበት።ከድርጅት በላይ ለአገሩ ጉዳይ ቅድሚያ በመስጠት ሸንጎው ከድንበር ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ጋር በመሆን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚሰጠውን የኢትዮጵያውያን የጋራ የተቃውሞ ፊርማ መፈረም ይገባል...>
ዶ/ር ታዬ ዘገዬ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ የወቅቱ ሊቀመንበር ለሱዳን ድንበር እንዳይሰጥ ስለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለህብር ከሰጡት ቃለ ምልልስ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንና በመከራና በመብት ረገጣ ውስጥ ያሉ የኢትዮጵያውያን ሴቶች ህይወት(ልዩ ዘገባ)
የአሜሪካ መንግስት በ2013 የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝን አስመልክቶ ያወጣው ሪፖርት ሲቃኝ
ኢትዮጵያ በዚህ አገዛዝ እየደማች እየተመዘበረች ነው። ይሄ ውድቀት ነው…>> ዶ/ር አክሎግ ቢራራ ከህብር ጋር ካደረጉት ቆይታ (ሁለተኛ ክፍል ቃለ መጠይቅ)
የህብር ሬዲዮ አራተኛ ዓመት በዓል ልዩ ሪፖርት
ሌሎችም ዝግጅቶች
ዜናዎቻችን
- የኢትዮጵያው አገዛዝ ሮኬትን ጨምሮ ከኤርትራ በየመን በኩል ሊገባ ነበር ያለውን መሳሪያ ያዝኩ አለ
- የግብጽ የቀድሞ ጄኔራል ከህዳሴ ግድብ ካልተጠቀምን አባይ ግርጌ መሞት አለብን አሉ
- ለሩጫ ወጥተው ተቃውሟቸውን ስላሰሙ የታፈኑት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የካ ፖሊስ መምሪያ በእስር ላይ ናቸው
- ከኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት ያመለጡት ኢትዮጵያዊው የቀዶ ጥገና ባለሙያ በቬጋስ የበርካቶችን ሕይወት እየታደጉ ነው
- አብርሃ ደስታ ሕወሓት ለአለማየሁ አቶምሳ ሐዘን ለሶስት ቀን ባንዲራ ዝቅ ስላደረገ የኦሮሞን ሕዝብ ለማክበር አድርጎ ማቅረቡን አጣጣለ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ