(ዘ-ሐበሻ) ባለፈው ቅዳሜ ሕይወቷ በአሰቃቂ ሁኔታ ያለፈው ኢትዮጵያዊቷ ሜላት ማሞ ዛሬ በዳላስ ከተማ የቀብር ሥነ-ሥርዓቷ ተፈጸመ። በወጣቷ ቀብር ላይ ከ500 ሰው በላይ መገኘቱንም የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከስፍራው አስታውቀዋል።
ዘ-ሐበሻ በሁለት ዜናዎች እንደገለጸችው ከባቡር ጋር የምትነዳው መኪና ተጋጭቶ ሕይወቷ ያለፈው ሜላት ማሞ በዳላስ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ፍትሃት ከተደረገላት በኋላ በበሪ’ስላንድ የመቃብር ቦታ (Restland Cemetary) አስከሬኗ አርፏል።
በስፍራው የነበረው ሕዝብ በከፍተኛ ሃዘን ተውጦ ሃዘኑን ሲገልጽ እንደነበር የገለጹት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች በተለይም በቅርቡ በሳዑዲ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ጥቃትና ግድያ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመውጣት ለወገኖቿ ያላትን ፍቅር መግለጿን በማስታወስ ሃዘናቸውን በጥልቀት ሲገልጹ እንደነበር ጠቅሰዋል።
ወጣቷ ሜላት ማሞ የ4 ዓመት ወንድ ልጅ እናት እንደሆነችም ተያይዞ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ዛሬ የቀብር ስነስርዓቷ ሲፈጸም የሚያሳየውን ፎቶዎች ከዳላስ የዘ-ሐበሻ ተባባሪዎች ልከውልናል – እነሆ።
ስለሜላት ከዚህ ቀደም የዘገብናቸውን 2 ዘገባዎች ተጨማሪ መረጃዎች ይሰጧችኋል፤ ሊንኮቹን እነሆ
1ኛ. በዳላስ የምትነዳው መኪና ከባቡር ጋር ተጋጭቶ ሕይወቷ ያለፈው ኢትዮጵያዊት ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ይፈጸማል
2ኛ. በዳላስ የምትነዳው መኪና ከባቡር ጋር ተጋጭቶ ሕይወቷ ያለፈው ወጣት ኢትዮጵያዊት ናት ተባለ