(ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ከአዲስ አበባ እንደዘገበው) በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቦረና ዞን ቡሌሆራ/ ሀገረ ማርያም/ ከተማ የምትገኘው ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን እንዲፈርስ መታዘዙ በአካባቢው ቁጣ መቀስቀሱን ታወቀ፡፡ የአካባቢው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጹት “የከተማው ከንቲባ ሀላፊነት በጎደለው እና በማን አለብኝነት ቤተክርስቲያኑን አፍርሰው ቦታውን ለባለሀብት ለመሸጥ መወሰናቸው ለሀይማኖቱም ለህዝቡም ያላቸውን ንቀት ያሳዩበት ነው፡፡” ሲሉ አውግዘዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች አሁን የወሰዱትን አቋም ሲገልጹ የከተማው ከንቲባ በድፍረት ቤተክርስቲያኑን አፍርሰን እንጨትና ቆርቆቆውን እንድናነሳ አዘዋል ፡፡
“እኛ የእግዚያብሄርን ቤት አናፈርስም ፡፡ እሳቸው ከፈለጉበት በሚረፈልጉት ኃይል ሊያስፈርሱ ይችላሉ ፡፡ ለወረዳው አስተዳደር አመልክተን የወረዳው አስተዳዳሪ በስፍራው ተገኝተውተ ተመልክተውታል ፡፡ ቤተክርስቲያኑ እንዳይፈርስ የሚያስችለው ውሳኔ ይሰጣሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉ ተናግረተዋል ፡፡
አስተያየት ሰጪዎቹ በመጨረሻ በሰጡት አስተያየት በዚሁ ከተማ የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አለ፡፡ ይህ ቤተ ክርስቲያን ካለፈው መንግስት ጀምሮ በከተማው ማስተርፕላን መሰረት ፍቃድና ካርታ አለው ይሁን እንጂ እኚህ የከተማው ከንቲባ ቦታውንና ከቦታው ላይ ያለውን ባህርዛፍ አላስረክብም ብለው ችግር ፈጥረውብን እስካሁን ችግሩ ባልተታበት
ሁኔታ እንደገና አሁን ደግሞ ፊታቸውን ወደ ቅድስት አርሴማ ማዘወራቸው ገርሞናል ብለዋል ከተማውን ከንቲባ አቶ ቡሌ ገመዳ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡበት በተንቀሳቃሽ ስልካቸው እና በጽ/ቤታቸው ስልክ ለማግኘት ያደረግነው መከራ ለጊዜው አልተሳካም ፡፡
↧
ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን እንዲፈርስ መታዘዙ በአካባቢው ቁጣን ቀሰቀሰ
↧