ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)
መጀመርያ በዚህ የአመቱ ምርጥ ብየ በምጠቅሰው ጥቅስ ልጀምር፦”የመሬት ላራሹ” ጩኸት ውጤቱ “መሬት ለነጋሹ” ሆኗል፤ ለገበሬው የታሰበውን መሬት ወያኔ ወሰደው። የዱሮ ንጉሣዊ ገዢዎቿ ቤተ ሰቦች ስለነበሩ በቊጥራቸው ማነስ ምክንያት እነሱን በማር ግብር ለማጥገብና በሰላም ለመኖር ቀላል ነበረ። የዛሬዎቹ ገዢዎች ብሔረ ሰቦች ስለሆኑ እነሱን ሁሉ በሚሊዮን ዶላር ማጥገብ መራቆትን አስከትሏል።” ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ (‘ዕርቅና ሰላም፤ የሕይወት ቅመም’ የካቲት 2006 ዓ.ም)
ወየኔዎች ወደ ሥልጣን ከመጡ በሗላ የአገሪቱን ሃብት ባገኙት አቅም እና ዘዴ ሁሉ በማራቆት ብቻ የተወሰኑ ሳይሆኑ የትግራይ ሕብረተሰብ በታሪክ ላይ የሚኖሮው ግንዛቤ የተጣመመ እንዲሆን አድረገውታል። በርከት ያሉ እንሰሳዎች በተለያዩ ምክንያቶች ሆን ብለው አጥቂዎቻቸውን ወይንም መሰሎቻቸውን ያታልላሉ። እንሰሳዎቹ በማታለል ዘዴ የሚኖሩበት ምክንያት የተለያዩ ምክንያቶች አሉዋቸው። ለምግብ፤ ወይንም እራሳቸው ከጥቃት ለመከላከል ሊሆን ይችላል።ይሁን እንጂ በተፈጥሮ እራሳቸውን እና ሌሎችን ሆን ብለው ለማታተለል/ለመዋሸት “የተሰሩ ፍጡሮች” ሰዎች ብቻ እንደሆኑ ያነበብኳቸው አንዳንድ የስነ ልቦና መጻሕፍቶች ይገልጻሉ።