Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Health: ባለቤቴሽን ከሌላ ሴት ጋር አልጋ ላይ ብታገኚው ወዲያው ፍቺን ከማሰብሽ በፊት ይህን አንብቢ

$
0
0

ባለቤቴን ከሌላ ሴት ጋር አልጋ ላይ የያዝኩት ዕለትን የመሰለ መጥፎ ቀን በህይወቴ አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ እንደዚህ አይነት ነገር ያደርጋል ብዬ አስቤ አላውቅም፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ከባለቤቴ ጋር ስንነጋገር ‹‹ውዴ እወድሻለሁ፤ ነገር ግን ልጅቷንም እወዳታለሁ›› አለኝ፡፡ ይህን ሲለኝ እምባዬን መቆጣጠር አቃተኝ፡፡ እየቆየሁ ስሄድ ለባለቤቴ ወደ ሌላ ሴት መሄድ ጥፋቱ የእኔ እንደሆነ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ባለቤቴን በትክክል ላስደስተው ብችል ኖሮ እንዲህ አይነት ውሳኔ ላይ ላይደርስ ይችል ይሆን?
ሳራ

love and Divorce
የኢሳያስ ከበደ ምላሽ፦ ብዙ ሚስቶች ባሎቻቸው ወደ ሌላ ሴት በሄዱ ቁጥር ጥፋተኛ የሚያደርጉት ራሳቸውን ነው፡፡ ‹‹እኔ በአልጋ ላይ ጨዋታ ባለቤቴን ባስደሰተው ኖሮ ከሌላ ሴት ጋር አይተኛም ነበር›› ብለው ያምናሉ፡፡ ይህ አስተሳሰብ የሚስቶች ብቻ ሳይሆን የባሎችም ነው፡፡ ባሎችም ሚስታቸው ከሌላ ወንድ ጋር መዳራቷን ሲያውቁ ‹‹ሚስቴን ላስደስታት አልቻልኩም ማለት ነው›› ብለው ነው የሚያስቡት፣ እውነቱ ግን ይሄ አይደለም፡፡

ከትዳር ውጪ ዝሙት ሲፈፅም ባል ወይም ሚስት ራሳቸውን ጥፋተኛ አድርገው ማሰባቸው ተገቢ አይደለም፡፡ ጥፋቱ ዝሙትን የፈፀመው ሰው እንጂ የሌላው ወገን አይደለም፡፡ ባልና ሚስት በመካከላቸው የዚህ አይነት ችግር ሲከሰት በፍጥነት ለመለያየት ከመወሰንና ከማኩረፍ ይልቅ በረጋ መንፈስ ለመነጋገር መሞከሩ ተገቢ ነው፡፡ ሳራ ባለቤቷን በግልፅነት ልታነጋግረው ሞክራለች፡፡ ባለቤቷም ስለ ሁኔታው ያለውን አቋም ሲያሳውቃት ትቆጣለች ወይም ትናደዳለች ብሎ ሳይሆን ስሜቱን ነው፡፡ ባለቤቷ ሁለተኛ የዚህ አይነት ድርጊት አልፈፅምም ብሎ በድብቅ ማድረጉን ቢቀጥልስ? ከፍተኛው የህሊና ጉዳት በሳራ ላይ የሚደርሰው የዚያን ጊዜ ነው፡፡

ሳራ በሰከነ መንፈስ ባለቤቷን በድጋሚ እንዲህ ብላ ልታናግረው ይገባል፡፡ ‹‹በትዳር ሕይወታችን ላንተ ያለኝ ፍቅር አሁንም አለ፡፡ በጋብቻችን ዕለት የገባህልኝን ቃል አሁንም አስታውሰዋለሁ፡፡ ነገር ግን አሁን እኔን ብቻ ሳይሆን ልጅቷንም እንደምትወዳት ገልፀህልኛል፡፡ እኔ ሚስትህ ነኝ፡፡ እኔንና እሷን በእኩል ደረጃ ልትወደን የቻልክበት ምክንያት አልገባኝም፡፡ በጋብቻችን ዕለት በተባባልነው ቃል መሰረት ቃላችንን ልንጠብቅ ይገባል፡፡ ይህ ካልሆነ ደግሞ በሰላም ልንለያይ ይገባል››
‹‹በትዳር ህይወታችን ላንተ ጥሩ ሚስት ለመሆን የዘወትር ምኞቴ ነው፡፡ ካንተ ሌላ ገላዬን ለማንም አሳልፌ ገልጬ አላውቅም፡፡ አንተ ግን ከሌላ ሴት ጋር ተኝተሃል፡፡ በዚህ ሁኔታ ግን ለመቀጠል ይቸግረኛል፡፡ ከእሷ ጋር መቀጠል ከፈለግህ ልትፈታኝ ትችላለህ፡፡ በግድ ባል ሆነህ እንድትቆይ ማስገደድ አልችልም፡፡ ይሄ ትዳር ሊሆን አይችልም››

የሳራ ባለቤት ይህንን ካዳመጠ በኋላ በፍፁም ደስተኛ ሊሆን አይችልም፡፡ በሚስቱ ላይ የፈፀመው በደል ቁልጭ ብሎ ነው የሚታየው፡፡ የሚስቱ ንግግር ለባሏ ያላትን ፍቅርና አለኝታነት የሚያሳይ በመሆኑ እግሯ ላይ ወድቆ ይቅርታ ለመጠየቅ አያመነታም፡፡ ከሚስቱ ሌላ የለመዳት ሴት ሚስቱ ልትሆን እንደማትችል የሚረዳው ወዲያውኑ ነው፡፡ የሚስቱ ይቅር ባይነትና ትህትና ባለቤቷን በእጇ ለማስገባትና ለመመለስ ትልቅ አስተዋፅኦ ነው ያለው፡፡

ሳራና ባለቤቷ አሁን በጥሩ የትዳር ህይወት ውስጥ ነው ያሉት፡፡ የሳራ ትዕግስትና ርህራሄ ባለቤቷ ራሱን እንዲመረምርና ይቅርታ እንዲጠይቃት አስችሏል፡፡ ሳራ ባለቤቷን አልጋ ላይ እንደያዘችው ለፖሊስ ደውላስ ቢሆን? ዛሬ ፍቅር የሞላበት ትዳር ይፈርስ ነበር፡፡S


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>