Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ድሬዎች ለሰማያዊ ፓርቲ፡ “ኢሕአዴግ ክፉ መንግስት ነው፤ አብረናችሁ እንታገላለን”

$
0
0

*‹‹ወደ ድሬዳዋ መጥታችሁ ስላነጋገራችሁን ደስ ብሎናል›› የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች፤

ዘገባ በጌታቸው ሽፈራው

ድሬዳዋ፡- ሰማያዊ ፓርቲ (ሰማያዊ) በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችና በፓርቲው የትግል አቅጣጫ ዙሪያ ከድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ጋር የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም በከተማዋ ተገኝቶ ባደረገው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተወያየ፡፡

በስብሰባው ላይ ፓርቲው እስካሁን ያደረጋቸውን ህዝባዊ ትግሎችና ያስገኛቸውን ዋና ዋና ውጤቶች በድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ጌታነህ ባልቻ በኩል ለነዋሪዎች ገለጻ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም በፓርቲው ሀገራዊ አላማና የፖለቲካ ፕሮግራም ዙሪያ ለከተማዋ ነዋሪዎቹ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
Birhanu Tekeleyared, engreer yilikal and Engeener Getaneh Balcha
‹‹ወደ ድሬዳዋ ከተማ መጥታችሁ ስላነጋገራችሁን ደስ ብሎናል›› ያሉት የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ‹‹ምርጫ ሲደርስ ብቻ ወደ እኛ የመምጣቱን የቆየ ልምድ ሰብራችሁ ከአሁኑ ራሳችሁን ስላስተዋወቃችሁንና የትግል አጋራችሁ እንድንሆን ስለፈቀዳችሁ እናመሰግናለን›› ብለዋል፡፡ በስብሰባው ላይ የተገኙ አንድ አስተያየት ሰጭ በድሬዳዋ ከተማ ስላለው ወቅታዊና የፖለቲካ ሁኔታ አንስተው፣ በኢህአዴግ አገዛዝ የድሬዳዋ ነዋሪዎች እየደረሰባቸው ያለውን በደል አጋልጠዋል፡፡

‹‹ኢህአዴግ የማይገባበት ነገር የለም፤ ወዳጅ መስሎ በመሐላችን እየገባ ያጣላናል፡፡ ኢህአዴግ ክፉ መንግስት ነው፡፡ እንኳን መጣችሁልን እንጂ አብረናችሁ እንታገላለን፤ ለነጻነታችን ለመታገል ሞትን አንፈራም›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በድሬዳዋው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ከህዝቡ በርካታ ጥያቄና አስተያየቶች የተሰነዘሩ ሲሆን በፓርቲው ከፍተኛ አመራሮችም ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡ የድሬዳዋ ነዋሪዎች መሬትን፣ ብሄር ብሄረሰብን፣ ሰንደቅ አላማን፣ የታሰሩ ጋዜጠኞችንና ፖለቲከኞችን፣ ምርጫ-2007ን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የውህደት አጀንዳን እና ሌሎች በርካታ አንኳር ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡

የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በተለይ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት በተመለከተ ‹‹በኢትዮጵያ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዳሉ እንገነዘባለን፡፡ ነገር ግን ፓርቲያችን በግለሰብ ነጻነትና መብት ያምናል፡፡ ምክንያቱም የግለሰብ መብት ከተከበረ የቡድን መብትም አብሮ እንደሚከበር እናውቃለን፡፡ እስኪ ለአብነት የግለሰብ መብት ተከብሮ የቡድን መብት የማይከበርበት ሁኔታ ካለ እናንሳ…የለም፡፡ ስለዚህ ትኩረታችን በግለሰብ መብት መከበር ከሆነ የቡድን የሚባሉ መብቶችም አብረው መከበራቸው እሙን ነው›› በማለት አስረድተዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ‹ሞደሬት ሊብራሊዝም› አይዶሎጅን እንደሚያራምድ የተናገሩት ሊቀመንበሩ፣ የመሬትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ከዚህ መነሻነት የተቃኙ እንደሚሆኑ ጠቅሰዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ‹‹ሰማያዊ አብሮ በመስራትና በትብብር ያምናል፡፡ ነገር ግን ሁሌም ምርጫ ሲደርስ እንደሚደረገው በሩጫ ወደ ውህደት ለመግባት አንፈልግም፡፡ ካለፉት የሌሎች ተሞክሮዎች ብዙ ተምረናል፡፡›› ብለዋል፡፡

semayawi party Drie Dawa
ሰማያዊ ፓርቲ ድሬዳዋ በነበረው ቆይታ በዚያው የከፈተውን ቢሮና የአካባቢውን መዋቅር የማስተዋወቅና የማጠናከር ስራም ሰርቷል፡፡ ፓርቲው በሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ ስራ መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>