(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንን ወደ ስዊዘርላንድ አቅጣጫ አስቀይሮ የዓለም መነጋገሪያ የሆነው ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራን በመደገፍ፤ የስዊዘርላንድ መንግስት አብራሪው የጠየቀውን የጥገኝነት ጥያቄ እንዲቀበለው ለመጠየቅ በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ። አርብ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 2014 በበርን ከ12 ሰዓት ከ30 ጀምሮ ይደረጋል በተባለው በዚሁ ሰልፍ ላይ “የሃይለመድህን ድምጽ የኔም ድምድ ነው” በሚል መርህ እንደሚደረግ የሰልፉ አስተባባሪዎች ለዘ-ሐበሻ በላኩት በራሪ ወረቀት ላይ አስታውቀዋል። በዚህ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንዲገኙም ጥሪ ቀርቧል።
ሃይለመድህን አውሮፕላኑን ወደ ስዊዘርላንድ ጠልፎ ካሳረፈው በኋላ ይህን ዜና የዘገቡ የውጭ ሚዲያዎች በአብዛኛው በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት አብረው ዘግበዋል። የአውሮፕላን ጠለፋውንም ከዚሁ የሰብአዊ መብት አለመከበር ጋር አያይዘው ብዙ መዘገባቸው ይታወሳል።
↧
ረዳት ፓይለቱ ኃይለመድህን አበራን በመደገፍ በስዊዘርላንድ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠራ
↧