Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

አንድነት እና መኢአድ በመጪው እሁድ በባህርዳር በተጠሩት ሰልፍ የተነሳ ከወዲሁ ወጣቶች እየታፈሱ ነው

$
0
0

abugida “አንድነትና መኢአድ የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ ብአዴንን አሳስቦታል “ስራ አጥ” ያላቸውን ወጣቶችን ዛሬ ሲያሳፍስ ውሏል” ሲል ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዘገበ። እንደ ጋዜጣው ዘገባ “የባጃጅ አሽከርካሪዎችም ሰልፉን እንዳይቀሰቅሱና እንዳይሳተፉ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸዋል”

ፍኖተ ነፃነት ዜናውን ከምንጮቼ አረጋግጫለሁ እንዳለው አንድነት ፓርቲ ከመኢአድ ጋር በመሆን የጠራውና በመጪው ዕሁድ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም ብአዴንን በመቃውሞ በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ብአዴንን እንዳሳሰበውና በባህር ዳር ከተማ “ስራ አጥ” ያላቸውን ወጣቶችን ዛሬ ሲያፍስ ውሏል።

የአማራ ክልልን እየመሩ አማራውን በፀያፍ ቃላት የተሳደቡትን አቶ አለምነው መኮንን ለፍርድ እንዲቀርቡ፤ ከስልጣንም እንዲወርዱ ለመጠየቅ በተጠራው በዚህ የባህርዳሩ ሰልፍ የተነሳ አፈሳው ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ሕዝቡን ለማስፈራራት ነው። እንደፍኖተ ዘገባ አፈሳው በመንገድ ላይ ንግድ የተሰማሩና ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ዜጎችንንም የጨመረ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

ጋዜጣው በተጨማሪም ከዚሁ ጎን ለጎን የብአዴን ካድሬዎች የባህር ዳር ከተማ የባጃጅ አሽከርካሪዎችንም በመሰብሰብ ሰልፉን እንዳይቀሰቅሱና በተቃውሞ ሰልፉ ላይም እንዳይሳተፉ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋቸዋል ሲል የዘገበ ሲሆን የባህር ዳር የባጃጅ አሽከርካሪዎች አንድነት ፓርቲ በሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ በባህርዳር ባደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በራሳቸው ተነሳሽነት ቅስቀሳ ሲያሰርጉ እንደነበር ይታወሳል በማለት ዘገባውን አጠናቋል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>