የህብር ሬዲዮ የካቲት 2 ቀን 2006 ፕሮግራም
<<... ገዢው ፓርቲ እንደ ትላንቱ የተቃዋሚ መሪዎችን አስሮ ወደፊት ያራምደኛል ማለቱን ሕዝቡ የሚቀበለው አይመስለኝም። አቶ አስራት ጣሴን እስር ቤት ሄጄ አግኝቻቸዋለሁ። መንፈሳቸው ጠንካራ ነው።ከተናገሩት ...ይህን መሰሉን የተበላሸ አካሄድ ሕዝቡ በቃ ሊለው ይገባል...>>አቶ ዳንኤል ተፈራ የአንድነት የድርጅት ጉዳይ አላፊ ከቃሊቲ መልስ ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
* በሳውዲ የሶስት ሹህ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ዕጣና የመምህራኑ የስራ ማቆም አድማ ቀጠሮ (ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በስፍራው የታዘበው ሙሉ ዘገባ)
የካቲት 12 የጣሊያን ፋሺስት በአዲስ አበባ ጭፍጨፋ ያካሄደበት ቀን ታስቦ ሲውል እንደ ቬጋስ ሁሉ በዓለም ላይ በሰላሳ ከተሞች ይከበራል (አቶ ኪዳኔ አለማየሁ የዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ የኢትዮጵያ ጉዳይ ዋና ዳይሬክተር )
ሌሎችም ዝግጅቶች
ዜናዎቻችን
ኢትዮጵያ በቅርቡ የመፈራረስ አደጋ ከተጋረጠባቸው የአፍሪካ አገሮች ተርታ መሆኗ ተገለጸ
በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አስራት ጣሴ ከቃሊቲ እስራቸውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከምከፍለው መስዋዕትነት ትንሹ ነው አሉ
ጠበቃቸው ነገ ይግባኝ ይጠይቃሉ
* በትግራይ የአረና ስራ አስፈጻሚ ተይዘው እየተደበደቡ መሆናቸው ተገለጸ
* አብርሃ ደስታ ከመቀሌ ህወሃት የደርግን ስርዓት እየደገመ መሆኑን አስታወቀ
* ሰሞኑን በኬኒያ ታስረው ደብዛቸው ጠፋ የተባሉትን የኦሮሞ ተወላጆች ጉዳይ እንዳሳሰበው አንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ገለጸ
* በአባይ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር ዳግም አልወያይም ያለችው ግብጽ ነገ ልኡካኖቿ አዲስ አበባ ይገባሉ
* በሳውዲ የሶስት ሺህ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ዕጣ አሳሳቢ ሆኗል
* መምህራኑ የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል
* ኦባማ ኬር በግራ ዘመም መገናኛ ብዙሃን እንደሚባለው አዳዲስ ስራዎችን ገዳይ አለመሆኑ ተገለጸ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ