የባህር-ዳር ከተማ አስተዳደር መምህራን “የምህራን መብት ይከበር” በሚል ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ፅህፈት እንዳስታወቀው በሰልፉ ላይ መምህራኑ ‹‹እኛ የመምህራን ሰላማችንና መብታችን ለማስከበር ከለውጡ ሐይሉ ጎን ቁመን ያለሰለሰ ትግል እናደርጋለን›› ብለዋል፡፡ ሰልፈኞቹ ጨምረውም ‹‹የመምራት ብቃት የሌላቸው ፤ መብታችን የጣሱ በከተማ አስተዳድሩ ያሉ አመራሮች በህግ ይጠየቁልን” ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
↧