Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Sport: የዛሬ ምሽቱ የገንዘቤ ዲባባ እና የአበባ አረጋዊ ፍጥጫ በስቶክሆልም

$
0
0

ከቦጋለ አበበ
genzebe d
ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው የወቅቱ የመካከለኛ ርቀት ኮከብ አትሌቶች መካከል ገንዘቤ ዲባባና አበባ አረጋዊ ግንባር ቀደሞቹ ናቸው። አበባ አረጋዊ ካለፈው የለንደን ኦሊምፒክ በኋላ ዜግነቷን ቀይራ ለስዊድን መሮጥ ብትጀምርም የኢትዮጵያ ፍሬ መሆኗ አይካድም።

ሁለቱ አትሌቶች በአንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር ለአገራቸው በአንድ ላይ በመሮጥ የተለያዩ ድሎችን ቢያስመዘግቡም አሁን ግን የሚሮጡት የተለያየ ሰንደቅ ዓላማ ለማውለብለብ ነው። ቀድሞ የነበራቸው አንድነትና ትብብርም አሁን ላይ አይሰራም።

አበባ ባለፈው የውድድር ዓመት በርቀቱ ጎልታ የወጣችበትን ድል አስመዝግባለች። በተለይም የዳይመንድ ሊግ ውድድሮችን ጠራርጋ ከማሸነፏ በላይ የሞስኮው የዓለም ሻምፒዮና ላይ የርቀቱ ሻምፒዮን መሆኗ ከገንዘቤ በበለጠ ትኩረት እንዲሰጣት አድርጓል።

ገንዘቤ ደግሞ የዘንድሮው የውድድር ዓመት ገና ከመጀመሪያው ያማረ ሆኖላታል። ይህም ባለፈው ቅዳሜ በቤት ውስጥ ሻምፒዮና የዓለምን ክብረወሰን በማሻሻል ማሸነፏ እንደ ምክንያት የሚወሰድ ነው።

አበባ የወቅቱ የአንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር ሻምፒዮን ነች። ገንዘቤ ደግሞ የርቀቱ የቤት ውስጥ ባለ ክብረወሰን መሆኗን ከቀናት በፊት አሳይታለች። እነዚህ ሁለት እንቁዎች በአንድ የውድድር መድረክ ተፎካክረው የትኛዋ ምርጥ አትሌት እንደሆነች ለማየት የስፖርት ቤተሰቡ ጉጉት ነው። የሁለቱ አትሌቶች ፍልሚያም ጊዜ ሳይፈጅ ዛሬ ምሽት የምናይበት አጋጣሚ ተፈጥሯል።

አበባ በዛሬው ምሽት ውድድሯ የቀድሞ የአገሯን ልጅና የውድድር ባልደረባዋን ገንዘቤን በስዊድን ስቶክሆልም ታስተናግዳለች። የቤት ውስጥ የዓለምን ክብረወሰን 3፡55፡17 በሆነ ሰዓት የጨበጠችው ገንዘቤም ያለፈው ዓመት መጥፎ ትዝታዋን ለመካስ የዓለም ሻምፒዮን ጓደኛዋን ትገጥማለች።
aregawi abeba
የሁለቱ አትሌቶች ፍጥጫ በዛሬው ምሽት የሚከናወኑ ሌሎች ውድድሮችን አደብዝዘዋል ማለት ይቻላል። ምናልባትም እነዚህ አትሌቶች ከአስራ ስድስት ዓመት ወዲህ በርቀቱ ያልተመዘገበ ፈጣን ሰዓት ሊያስመዘግቡ እንደሚችሉ የስፖርቱ ተንታኞች እየተነበዩ ይገኛሉ።

አበባ በደጋፊዎቿና በአገሯ ላይ እንደመሮጧ መጠን የአሸናፊነት ግምት ቢሰጣትም ገንዘቤ ባለፈው ቅዳሜ የዓለም ክብረወሰን ያሻሻለ ብቃት ማሳየቷን ተከትሎ የዛሬ ምሽቱን ውድድር ማን እንደሚያሸንፍ መገመት አዳጋች ሆኗል።

ለዘገባው የመረጃ ምንጭ የሆነን የዓለምአቀፉ አትሌቲክስ ማህበራት ፌዴሬሽን ድረ -ገፅ ውድድሩን አስመልክቶ ከትናንት በስቲያ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አበባ አረጋዊን አግኝቶ የተለመደውን «ምን አስበሻል?» የሚል ጥያቄ አንስቶላታል።
«ባለፈው የውድድር ዓመት ጥሩ ጊዜ አሳልፌያለሁ፤ አሁንም ጥሩ ልምምድ አድርጌያለሁ፤ የቀድሞው ብቃቴ አብሮኝ ነው፤ ከቻልኩኝ የዓለምን ክብረወሰን ለማሻሻል ሮጣለሁ» በማለት አበባ አረጋዊ መልሳለች።

አበባ የገንዘቤ ወቅታዊ ብቃት እቅዷን ሊያፋልስባት ይችል እንደሆን ተጠይቃም «ገንዘቤ ጥሩ ልምምድ አድርጋለች፤ በመልካም አቋም ላይም ትገኛለች፤ እኔም እንደዚያው፤ ስለዚህ አሸንፋታለሁ» በማለት አስተያየቷን ሰጥታለች።

አበባ አረጋዊ ባለፈው ዓመት በስቶክሆልም በሦስት ሺ ሜትር የዓለምን ክብረወሰን ለማስመዝገብ ሦስት ሰከንድ ያህል ተጠግታ ሳይሳካላት ቀርቷል። ይህ የሦስት ሺ ሜትር ክብረወሰን በመሰረት ደፋር የተያዘ መሆኑ ይታወሳል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>