Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በሳንሆዜ፤ ከተማ እና አጎራባች ከተሞች፤ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ በህብረት የወያኔን ሴራ እናምክን!!

$
0
0

በሳንሆዜ፤ ከተማ እና አጎራባች ከተሞች፤ ለምትኖሩ
ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤
በህብረት የወያኔን ሴራ እናምክን!!

UDJ - Ethiopia ሐገራችን ኢትዮጵያ የአንጸባራቂ ታሪክ ባለቤት፤ ለአፍሪካና እንዲሁም በአለም ዙሪያ ለሚኖሩ ጥቁር ህዝቦች በሙሉ እንደ አጥቢያ ኮከብ የምትታይ መሆኑዋ በወዳጅም በጠላትም የተመሰከረ ሃቅ ነው። ታሪካዊ ጠላቶች፤ የሀገራችንን ሉአላዊነት፤ የህዝባችንን በራስ መተማመን፤ ሀገር ወዳድነት፤ የራሱ የሆነ ባህል፤ ወግ እና እምነት ጠብቆ መቆየት እንቅልፍ
ነስቷቸው፤ ሲቻላቸው ከመሃከላችን፤ ለጠላት ያደሩ ከሃዲ ባንዳዎችን በመመልመል፤ ሳይቻል ደግሞ በቀጥታ በመዝመት እኛነታችንን ለማክሰም፤ የነበራቸው ህልም፤ በጀግኖች አባቶቻችን እና ጀግኖች እናቶቻችን ቆራጥ ተጋድሎ የወራሪው ሃይል ህልም መክኖ ቀርቶዋል።

እንዳለመታደል ታዲያ በህዝባችን ጫንቃ ላይ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት የስልጣን መንበር ላይ የተፈናጠጠው ጎጠኛውና አምባገነኑ የወያኔው ቡድን ከህዝባችን ፍላጎት በተቃራኒው በመቆም፤ የታሪካዊ ጠላቶቻችን ባለሙዋልና ጉዳይ አስፈጻሚ በመሆን፤ የሺ አመታት ታሪክ ባለቤት የሆነችውን ሃገራችንን፤ ህዝቦችዋን እና በውስጡዋ ያዘለችውን
አኩሪ ባህል፤ በመናቅ፤ በመካድ፤ ብሎም በዘርና በጎሳ በመከፋፈል፤ በጎጥና በቁዋንቁዋ በመነጣጠል፤ በመንደር እና በወንዝ በመለያየት፤ የሃይማኖት ልዩነትን ወዳልተፈለገ ጥግ በመግፋት፤ የጋራ የሆኑ ታሪካዊ እሴቶቻችንን፤ እንደ ህዝብ የሚያስተሳስር ሰንደቅ አላማችንን ሳይቀር በመለወጥ፤ ህልውናችንን ከመፈታተን አልፎ፤ ወደ ማጥፋት ግስጋሴ ላይ እንደሆነ የታወቀ ነው። በዚህ ጠባብና ጎጠኛ ቡድን የአገዛዝ ዘመን፤ ታሪካዊ ሃገራችን ወደብ አልባ፤ ትውልድ አልባ፤ እምነት አልባ፤ ጀግና አልባ፤ ብሎም በአጎራባች ሃገሮች ቸርነት ላይ ተስፋዋን የጣለች፤ መጻግኡ ሆናላች ብንል የተጋነነ አይደለም። ጀግኖች ኣባቶቻችን ኣጥንታቸውን ከስክሰው፤ ከባሩድ እና ከጥይት ጋር ተጠራምሰው፤ በመርዝ ጭስ ተጨርሰው፤ እነሱ አልፈው ያቆዩትን ሰነደቅ አላማ፤ ይሄ ዘረኛ ቡድን በበርሃ ስኩዋርና በሶ ሲሸከምበት፤ ከተማ ከገባ በሁዋላም ጨርቅ ነው እያለ ሲራቀቅ እና ሲመጻደቅ የነበረ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

united we stand በወያኔ አገዛዝ ጋዜጠኞች አሸባረ በመባል ዘብጥያ ወርደዋል፤ የሃይማኖት አባቶች ሞት እና ሰደት እጣ ፈንታቸው ሆኖል፤ ገዳማት ተደፍረዋል፤ዜጎቸ በራሳቸው ሃገር ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው ሃብት እና ንብረት የማፍራት መብታቸውን ተነፍገዋል፡ አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ እናቶቸ እና እህቶቸ የሚያመክን መድሃኒት በመስጠት የአማራው ቁጥር እንዲቀንስ ተደርጉዋል። እስር ቤቶች በተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በተለይም በኦሮመኛ ተናጋረ ወገኖቻችን ተጨናንቋል፤ የኑሮ ውድነቱ እማይቀመስ ሆኖል፤ በምርጫ የተሸነፋው ወያኔ በጠራራ ጸሃይ ያልታጠቁ ህጻናትን በአደስ አበባ እና በሌሎች ክተሞች በግፍ ፈጅቷል። የእስልምና ጉዳይ አፈላላጊ ወገኖችን በአሸባረነት ከሱዋል፤ በመሃከለኛው ምስራቅ ወጣት ሴት እህቶቻችን ለዘመናዊ ባርነት በመዳረግ በታረካችን ታይቶ እማይታውቅ ውርደት እና የሰነልቦና ጠባሳ ጥሎብናል። በጋምቤላ ዜጎችን በማፈናቀል እና የውጪ ጉቦ ሰጭዎች ለም ቦታ እንዲየዙ አድረጎል፤ በኦጋዴን ግድያው አስገድዶ መድፈሩ እና የሰብአዊ መብት ጥሰቱ እንደቀጠለ ነው፤ አልፎ ተርፎም የሃገራችን ድንበር ለሱዳን በእጅ መንሻነት ተስጥቷል።

በጣሊያን ወረራ ዘመን ድልድይና ህንጻ በመሰራቱ ወራረው ጦር ይግዛን ያላለውን እና ነጻነቱን ያስቀዳመውን ህዝባችን ዛሬ የወያኔ ደናቁርት ካድሬዎች በህዝብ ጠኔ የትላልቅ ህንጻ ባለቤት እና ባለዘመናዊ ተሽከርካሪ ባለቤት መሆናችው ያደባባይ ሚስጥር ሆኖ ሳለ፤ ላለፉት ሃያሶስት ያገዛዝ አመታት የህዝባችን ኑሮ ከድጡ ወደማጡ ማምራቱ እየታዎቀ ’ልማታዊ’’ የሚል ጭምብል ለብሰው ለማደናገር መሞከር ከጀመሩ ሰንበትበት ብሎል በየሄዱበት ቢከሽፍም። ዛሬ ታድያ በዚህ ብምንኖርበት በሳን ሆዜ ከተማ ውህዳን የወያኔ ጀሌዎች የወያኔን ጭምብል ለብሰው “ልማታዊ” የልመና አኩፋዳቸውን አዘጋጅተው ለፌብሯዋሪ 8፣ በ770 ሞንታጊዩ ኤክስፕሬስ ዌይ ሳን ሆዜ ካሊፎርኒያ (770 Montague Expressway San Jose CA 95134) በህዝባችን እንባ ሊሳከሩ እና በሃዘኑ ሊሳለቁበት ተዘጋጅተዋል።

እኒኚህ ከሃዲዎች የወያኔን ሹማምንትም ጋብዘዋል። ከሃዲዎችን ማጋለጥ እና ቅስማቸውን መስበር ኢትዮጲያዊ ግዴታችን በመሆኑ ሁላችንም ኢትዮጲያውያን አንድ ላይ በመሆን በሌሎች ከተሞች እንደተደረገው ሳን ሆዜ ለባንዳዎች አይሆንም ልንላቸው ይገባል። እላይ በተጠቀሰው አድራሻ ክ3፡00PM በመገናኘት ድምጹን ማሰማት ላልቻለው ህዝባችን ድምጽ እንሆነው ዘንድ ጥሪ ቀርቧል።

ከአባይ በፊት ሰብዓዊ መብትን መገደብ ይገደብ !!!!
ሁሉም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ይፈቱ!!!!
ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!!!
የሳንሆዜ ሀገር ወዳዶች ግብረሃይል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles