Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

መንግስት ትኩረት ይስጠን በሚል ለቅሬታ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ቢሮ ደጃፍ የወጡ የሳዑዲ ተመላሾች በፖሊስ ተበተኑ

$
0
0

በቪዲዮው ላይ የምታይዋቸው የሳዑዲ ተመላሾች በአዲስ አበባ ጎዳና ላይ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር መፍትሄ ፍለጋ ሲሄዱ ነው።

(ዘ-ሐበሻ) “መንግስት እየለመነብን ነው፤ ለምኖብንም ምንም ያቀመሰን ነገር የለም፤ እኛ ግን በጊዜያዊ ማረፊያ ውስጥ ተቀምጠን በችግር እየተቆላን ነው” ያሉ በስንት ኢትዮጵያውያን እምባና ሰላማዊ ሰልፍ ከሳዑዲ አረቢያ የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ቅሬታቸውን ለማሰማት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቢሄዱም በፖሊስ “ሁለተኛ እዚህ ድርሽ እንዳትሉ” በሚል እንደተባረሩ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ ዘግበዋል።

ከሳዑዲ የተመለሱ ኢትዮጵያውያን - ፎቶ ፋይል

ከሳዑዲ የተመለሱ ኢትዮጵያውያን – ፎቶ ፋይል


“በሳዑዲ አረቢያ የተስቃየነው ስቃይ ሳያንስ በሃገራችንንም መንግስት በኛ ስም ገንዘብ እየለመነብን ሕይወታችንን ሊለውጥ አልቻለም፤ በኛ ስም የተለመነው ገንዘብ ሁሉ ተመዝብሮ የስራዓቱ ኃላፊዎች ውስኪ እየተራጩበት ነው” በሚል ቅሬታቸውን የሚያሰሙት ኢትዮጵያውያኑ፤ “በተሰጠን ጊዜያዊ ማረፊያ ከውሃና ካልበሰለ ምግብ ውጭ የሚሰጠን ነገር የለም” ሲሉ መንግስት ትኩረት ይስጠን በማለት ሕገመንግስታዊ መብታቸውን በመጠቀም ከ400 የሚበልጡት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቢሄዱም ፖሊሶቹ አስፈራርተው እንደበተኗቸው ለዘጋቢያችን ተናግረዋል።

“የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የሳዑዲው ዜና በተጋጋለበት ወቅት ለፖለቲካ መጠቀሚያነት እኛን አውሎናል። በየጊዜው ለሳዑዲ ተመላሾች እርዳታ አደረግኩ በሚል ፎቶ በመነሳት፤ ቪድዮ በመቅረጽ የፖለቲካ ስብዕናውን ለመገንባት ከተጠቀመብን በኋላ ዞር ብሏል። ዛሬም እርሱ ቢሮ ድምጻችንን ለማሰማት ብንሄድ የጠበቀን የሚሰማን መንግስት ሳይሆን እንግልት እና ዱላ ነው” በሚል ወቀሳ ያቀረቡት እነዚሁ የሳዑዲ ተመላሾች በሃገራችንም በሳዑዲም ስቃይ እየደረሰብን “ለምን ከዚያ ተመለስን?” እስከማለት ደርሰናል ብለዋል።

በቦሌ አካባቢ የሰፈሩት እነዚሁ ኢትዮጵያውያኑ በከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውን በተደጋጋሚ እየገለጹ ሰሚ አልባ ሆነዋል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>