Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ሰይፉ ፋንታሁን እና ሚካኤል መሐመድ በዱባይ ታስረው ተፈቱ

$
0
0

Seifu Fantahun

አርቲስት ሚካኤል መሐመድ

አርቲስት ሚካኤል መሐመድ

(ዘ-ሐበሻ) በራድዮ ፕሮግራሞቹ እና በኢቢኤስ ቲቪ ላይ በሚያቀርበው “ሾው” የሚታወቀው ሰይፉ ፋንታሁን እና በባለታክሲው ፊልም ላይ ምርጥ ትወናውን ያሳየው አርቲስት ሚካኤል መሐመድ በዱባይ ታስረው መፈታታቸውን ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገለጹ።

ለሁለቱ አርቲስቶች ቅርበት ያላቸው የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳስታወቁት ባለፈው እሁድ በአል ታዋር ዱባይ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ሰይፉ ፋንታሁን እና ሚካኤል መሐመድ የታሰሩት ቪዛችሁ የተሳሳተ ነው በሚል ምክንያት ነው። ጉዳዩ እስኪጣራ በሚል ሁለቱ አርቲስቶች ለ24 ሰዓታት መታሰራቸውን ያስታወቁት ምንጮቹ ሁለቱም አርቲስቶች በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ሥራቸውን እየሰሩ እንደሚገኙ ታውቋል።

ወደ ዱባይ በተደጋጋሚ የሚሄደው ሰይፉ ፋንታሁን እስካሁን ድረስ እንዲህ ያለ ችግር አጋጥሞት እንደማያውቅ ያስታወቁት እነዚሁ የመረጃ ምንጮች በተሳሳተ ቪዛ ታስሮ መፈታቱ እንዳስገረማቸው ጠቁመዋል።

በዚህ መረጃ ዙሪያ ሰይፉ ፋንታሁንን እና አርቲስት ሚካኤል መሐመድን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ለግንዛቤዎ
በ2011 ዓ.ም በዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ ላይ የታተመውን የሰይፉ ፋንታሁንን ቃለ ምልልስ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>