ከግርማ ብርሃኑ
እርጅናን መዋጋት
በቀን ለ30 ደቂቃ ያህል በሳምንት ለ3 ወይም 4 ቀናት የእግር ጉዞ ማድረግ ብቻ እርጅናን ለመዋጋት በቂ መሆኑን ያውቃሉ? በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው በሰውነታችን የሚገኝን የጉልኮስ መጠን ማቃጠል መቻል ከምንም ነገር በላቀ እርጅናን መከላከል እንደሚያስችል ያረጋገጠ ሲሆን በተለይ ቀኑን ሙሉ ቢሮ ተቀምጠው የሚውሉ ሰው ከሆኑ የእግር ጉዞ ማድረጉ ሌሎች የበሽታ አይነቶችን ከመከላከል አንፃር ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
በአንዳንድ የጃፓን ከተማ ታላላቅ ድርጅቶች ውስጥ የቡድን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ባህል እየሆነ መጥቷል። በእነዚህ ድርጅቶች በ20 ደቂቃው ደወል የሚደወል ሲሆን በዚህ ጊዜ ማንኛውም ሠራተኛ ስራውን አቁሞ ሰውነቱን ማፍታታትና ማሳሳብ ይገባዋል። ይህን ካደረጉ በኋላ ግን ምንም እንዳልተፈቀረ ወደ ስራቸው ይመለሳሉ። የጃፓን ስ/አስኪያጆች ሠራተኞቻቸውን ውጤታማ ለማድረግ ይህን ሲያቅዱ እግረ መንገዳቸውንም የሠራተኞቻቸውን እርጅና እየተዋጉ መሆኑን ልብ ይበሉ።
ጭንቀትን መዋጋት
ጭንቀት የዕለት ተዕለት ተግባርዎ ነው? መልካም። እንግዲያውስ ዛሬውኑ ከጭንቀትዎ ሊፈወሱ ይገባል። በእርግጥ የሰው ልጅ ከጭንቀት ሊርቅ አይችል ይሆናል ነገር ግን ጭንቀት በትክክለኛው ጊዜና ቦታ መሆን ይገባዋል። የፒንሴልቫኒያ ዩኒቨርሲቲ ሳይኮሎጂስቶች በዚህ ችግር ተጠቅተው ያገኟቸውን ሰዎች አንድ ምክር ይለግሳሉ። ይኸውም በጭንቀት የተጠቁት ሰዎች በየቀኑ ለ20 ደቂቃ ያህል ‹‹የጭንቀት ክፍለ ጊዜ› እንዲመድቡና ይህንንም በተመሳሳይ ሰአትና በተመሳሳይ ቦታ እንዲተገብሩት ነበር የመከሩት። በእነዚህ 20 ደቂቃዎች ልጨነቅባቸው ይገባኛል ጥቆማዎች ያሏቸውን ጉዳዮች አሰባስበው መጨነቅ የሚገባዎትም በእነዚህ 20 ደቂቃዎች ውስጥ
ብቻ ሲሆን ከዛ ውጭ ካሉት ጊዜያት በምንም ምክንያት ለመጨነቅ ዝግጁ መሆን/መፍቀድ/ አይኖርብዎትም። ይህን ልማድ ማዳበር ‹psychosomatic› ከሚባሉ ስነ-ልቦናዊ ችግሮች ለመዳን ብሎም ቀስ በቀስ ጭንቀትዎን በቀላሉ መቆጣጠር የሚችሉባቸውን መንገዶች መረዳት ያስችልዎታል። ይሞክሩት።
የልብዎ ጉዳይ
አተኛኘትዎ ምን ይመስላል? በሆድዎ አልያም በግራ ጐንዎ የሚተኙ ከሆነ ልብዎ የሰውነትዎን ክብደት እንዲሸከም እያደረጉት ሲሆን ይህም ልብዎ ደም በመርጨት ረገድ በምታደርገው ጥረት ላይ አሉታዊ ችግር ይፈጥራል። እንግዲህ ያስቡት የዕድሜዎትን 1/3 ያህሉን ጊዜ የሚያሳልፉት ተኝተው ሲሆን በዚህ ሁሉ ጊዜ ልብዎ እንድትጨነቅ መፍቅድ አይኖርብዎትም። እንግዲያውስ በጀርባዎ ወይም በቀኝ ጐንዎ የመተኛት ልማድ ያዳብሩ።
በሲጋራ አመጣሽ ካንሠር
አለመሞት
የሚያጨሱ ከሆነ ማጨስ ቢያቆሙ መልካም ነው። አይሆንልኝም፣ ካሉም በሲጋራ ከሚመጣ ካንሠር ለመዳን የካሮት ጁስ ይጠጡ። እንደ ጀርመን የህክምና ባለሙያዎች ገለፃ በካሮት ውስጥ የሚገኘው ‹Carotene›የተሰኘ ንጥረ ነገር ካንሠርን በመከላከልም ሆነ አልፎ አልፎም በማዳን ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል።
እንደየህክምና ባለሙያዎቹ ገለፃ 60 ሲጋራ በቀን የሚያጨስ ሰው 4 ብርጭቆ የካሮት ጁስ ቢጠጣ ለካንሠር የመጋለጥ እድሉ የማያጨሱ ሰዎች ያህል የቀነሰ እንደሚሆን ይናገራሉ። በእርግጥ የካሮት ጁስ ለመጠጣት የግድ አጫሽ መሆን አይገባዎትም። ለጤንነትዎ ቢጠጡት ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም።
አይንዎን ይጠብቁ
የአይናችን አፈጣጠር ቅርበት ባለው ነገር ላይ ለረጅም ሰዓታት ማተኮርን አይፈቅድም። ምናልባት በስራዎ ጠባይ ረጅም ሰዓታትን የኮምፒውተር መስኮት ላይ አተኩረው መዋልን የሚጠይቅዎ ከሆነ ወይም ረጅም ሰዓት ቴሌቪዥን መመልከት የሚያዘወትሩ ከሆነ በየመሀሉ ቴሌቪዥኑን /ኮምፒውተሩን መመልከት ያቁሙና አይንዎትን ያፍታቱ። ለምሳሌ አይንዎትን በትልቅ ክብ ቅርፅ እንዲያይ ማሽከርከር። ወደ ግራና ወደ ቀኝ እንዲሁም ወደ ላይና ወደታች መመልከት ይመልከቱ። ወይም በመስኮትዎ አሻግረው ራቅ ያለ አካባቢን በአይኖችዎ ለመቃኘት ሙከራ ያድርጉ። በዚህም መንገድ አይኖችዎን በቀላሉ ከጉዳት መታደግ ይቻልዎታል። ይህ ሁኔታም ከአይኖችዎ በተጨማሪ አዕምሮዎ ዘና እንዲል ምክንያት ይሆናል።
ውፍረትን ይከላከሉ
የፓኪስታን ሴቶች ውፍረትን ለመከላከል የሚጠቀሙበት አስገራሚ መንገድ አለ። ይህን መንገድ ሲሰሙ በውጤቱ ላይ ጥርጣሬ ሊያድርብዎ ቢችልም ይሞክሩት። አስገራሚ ለውጥ ያያሉ።
የፓኪስታን ሴቶች እንደላስቲክ (የብር ላስቲክ) ያለ ነገር በእጃቸው ላይ ያደረጋሉ። ይህ በእጅ ላይ የሚደረግ ላስቲክ ዘላቂነት ያለው ጫና በነርቭ ስርዓታችን ላይ ስለሚያስከትል ሰውነታችን ክብደትን ለመከላከል አስተዋፅኦ ያላቸውን ኬሚካሎች ማመንጨት ይጀምራል። ላስቲኩን አንዱን ከክንድዎ ዝቅ ብሎ ሌላውን ከእጅዎ መታጠፊያ በታች ያድርጉት። ይህ ዘላቂነት ባለው ሁኔታ መደረግ ሲኖርበት በጣም ጠብቆ የደም ዝውውርን የሚገታ ወይም በጣም ላልቶ ቦታውን የሚለቅ እንዳይሆንም ጥንቃቄ ያድርጉ።
↧
Health: ጤናማ ሆኖ ለመቆየት 6ቱ ምርጥ ጥቆማዎች
↧