Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

[የሳዑዲ ጉዳይ] ዛሬም ያልታወቀውን እያየን ትተን ፣ የታወቀውን አስከሬን ሸኘን…ነብዩ ሲራክ

$
0
0

ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ

“ከሞቱ አሟሟቱ “

እኔና ወዳጆቸ ከወር ላላነሰ ጊዜ እንከታተለው የነበረ የአንዲት እህት አስከሬንን ዛሬ ተሸኘ …ምሽት ላይ የከሬኑን መሸኘት አረጋግጨ እና በስራ የደከመ አዕምሮየን ላሳርፍ ስውተረተር አንድ መልዕክት ቢጤ በኤሌክትሮኒክስ መልዕክት መላኪያ የአስከሬኑን መሸኘት መረጃ አስተላለፍኩ … ጉዳዩ እንድከታተል አደራ ጨምረው ለተመጸኑኝን ቤተሰቦች የላኩት መልዕክት የጉዳዩን ማለቅ የሚየሳወቅ ወደ ሃገረ አሜሪካ የላኩት መልዕክት ምላሽ ከምስጋና ጋር ሳይዘገይ ደረሰኝ ። ከደረሰኝ የምስጋና ምላሽ ውስጥ ስለ ማላውቃት ሟች ማንነት የሚገለልጽ መረጃ ሰፍሮበታል። የሚያሳዝን …
ዛሬ የተሸኘው አስከሬን የሁለት ወንድና ሴት ለአቅመ አዳምና ሔዋን የደረሱ ልጆች እናት መሆኑን እንግዳ የሆነኝ መረጃ አሳዝኖ ቅስሜን ቢሰብረው ከሰሞኑ ያየኋቸውን ማንነታቸው የማይታወቁት ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ሩቅ ወስዶ መለሰኝ ። እናም ዛሬ መናገር ያልፈለግኩት እናገረው ዘንድ ..ተገደድኩ ! መረጃየን ወደ ኋላ አሁን ወደ ደረሰኝ መልዕክት ላቅና …

(ፎቶ ፋይል)

(ፎቶ ፋይል)


ከሟች ቤተሰቦች የደረሰኝ መልክት አንድ ክፍል” ሟች ልጆችዋ እናታችን የታለች?” እያሉ ዘመድ አዝማዱን ሌት ተቀን አፋጠው የእናታቸውን መዋደቂያ ይጠይቁ እንደ ነበር እና የሟች ልጆች ጥያቄ መላ ቤተሰቡን ለወራት በጭንቀት የምይዙ የሚጨብጡት አጥተው እንደ ነበር በመጠቆም ምንም እንኳን ሃዘኑ የከበደ ቢሆንም የልጆችና የሚወዷት የናፈቋት ቤተሰቦችዋ ጥያቄ ዛሬ አስከሬኑ ሲሸኝ መልስ ማግኘቱን መልዕክቱ ይገልጻል።
በአስከፊው ሞት “አተርፍ ባይ አጉዳይ ” እህታቸውን የተነጠቁት ወላጆች ፣ልጆችና ቤተሰብ የእናት እህታቸውን ሞት መርዶ መራራ የሟችን መዳረሻ ሳያውቁ ለወራት መባዘናቸው እንደ ትልቅ ነገር መቆጠሩ እውነት ነው ። ለቀሪው ቤተሰብና ለዘመዱ” እንኳ አረብ ሃገር ሄዳ ቀረች !” ቢባል ተቀባይነት ሊኖረው ይችላል ። ነፍስ ላወቁ ልጆችን ግን በዚህ ዘመን “እናታችሁ ሞታለች! ” ብሎ ማርዳት ብቻ በቂ አይደለም ። ይህን ለመረዳት ነገሮችን አዟዙሮ ማየት ፣ ጭንቀት ፣ ሰቀቀን ጸጸቱን ባለ ጉዳዩን እንደራስ አድርጎ ማየት ብቻ በቂ ነው ። ውስብስቡን የአረብ ሃገር ስደት በቦታው ሆኖ ለተመለከተ “ማንቴስ ” ተብላ በወላጆቻቸው የሚታወቁ ዜጎች ኑሮን ለማሸነፍ ፣ ኑሮን ለመቀየር ፣ ለማደግ ሌላ ስም ተቀብተው ከልታማውን ህይወት ተቀላቅለዋልና መዳረሻቸውን ማወቅ ከሁሉም የከባደ ነው ። አሁን አሁን በተለይ ዜጎች ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ሲታወቅ የሟችን ስም አረጋግጦ ፣ የአስከሬኑን ማንነት ከብዙው ባለቤት ካልቀረበለት ኢትዮጵያዊ መካከል ለይቶ ማወቅ በራሱ እድለኛ መሆን ያስፈልጋል።

እነሆ ነገ በአስከፊው ሞት የተበጠቁት ቤተሰቦች የእናት እህታቸውን ክቡር አስከሬን ይረከባሉ። በከራረመ ሃዘን ተኮራምተው ፣ ውዳቸውን በክብር ሊሸኙት መቻላቸው ከፍ ያለ ደስታና ወሰን የሌለው እርካታ እንዳለው ከምስጋና ጋር የደረሰኝ መልዕክት ይገልጻል። የእኒህ ወገኖች የእኒያ ታዳጊዎች ጥያቄ ዛሬ መልስ አግኝቷል! ይህ እንዲሳካ እኔ መልዕከት በማስተላለፍ ብሳተፍም የትልቁን ምስጋና ባለቤቶች ሌሎች ናቸው! ትልቁን ስራ ለከወናችሁ በቤተሰቡ ስም የእኔም ምስጋና ይድረሳችሁ! የሟችን ነብስ አብዝቶ ይማር !
ይብላኝላቸው ማንነታቸው ሳይታወቅ ለሚሸኙት ሙታን የዚህች እህት ጉዳይ በሰመረ መንገድ ተከውኗል። ይህችን ማስታወሸሰ እንድጽፍ ስሜቴን ወደ ሸነቆጥ ክፍል ላምራ … መሰንበቻውን የዚህችን እህት ሽኝት ጉዳይ በቅርብ ስከታተል የታዘብኩት እውነት በተለያዩ ሆስፒታሎች ቁጥራቸው አነስተኛ የማይባል ማንነታቸው የማይታወቅ ዜጎች አስከሬን ለበርካታ ሳምንታት በማቀዝቀዣ ውስጥ እንደሚገኝ መረጃ መሰባሰቤ ነበር ። የእኒህ ዜጎች ማንነት አለመታወቅና ጠያቂ ማጣት በእርግጥም እንደ ሰው ያሳስባል ፣ ያማል! ዘመዳቸው የተገኘ አይሆኑ ሁነው የወገናቸውን መዳረሻ ያገኛሉ ፣ የፈለጉ ወደ ሃገራቸው ይሰዳሉ ፣ ያልቻሉት እርማቸውን አውጥተው እዚሁ እንዲቀበር ይፈቅዳሉ ። ባለቤት ያልተገኘላቸው ሟቹች ያለ ቤተሰብ፣ ወገን እና ዘመድ አዝማድ አልተፈጠሩም እና ማንነታቸው ሳይታወቅ ወደ አፈር የሚሸኙበት የመጨረሻ ግብአት የእኔ ጉዳይ ብለው ሲያስቡት ያሳዝናል ።
እኒህ ምንዱባን ወደ ማይቀረው አለም መሄዳቸው ያለና የማንመክተው የተፈጥሮ ህግ መሆኑ እንዳለ ሆኖ አበው ” ከሞቱ አሟሟቱ !” እንዲሉ ማንነታቸው እና አሟሟታቸው አቅም በፈቀደ መጠን በተለያየ መንገድ እየተጣራ በወጉ አፈር እንዲቀምሱ ማድረግ ቢቻል መልካም ነው ቢያንስ ለቀሪ ቤተሰብ ለማርዳት ማንነታቸው ያልታወቀ አስከሬኖችን በማጣራቱ ረገድ የመንግስት ተወካዮቻችን አንድ ሊሉት ይገባል ። ” ነግ በኔ ” ነውና በዚህ ጉዳይ ሌላው ቢቀር ለህሊናችን ስንል የሁላችንም ትብብር ታክሎበት አንድ መላ ሊበጅለት ይገባል !
አዎ ዛሬም ያልታወቀውን እያየን ትተን ፣ የታወቀውን አስከሬን ሸኘን …

የሟችን ነፍስ ይማር ፣ የቤተሰብን ሃዘን እሱ ያቅልል!
ነቢዩ ሲራክ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>