የሚሊዮኖች ድምጽ – ለነገዉ የአዳማ ሰልፍ ቅስቀሳው ቀጥሏል – (ፎቶዎች ይመልከቱ)
የስብሰባ ጥሪ- የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የጋራ ግብረሃይል የፊታችን ጁን 15, 2014 ህዝባዊ ውይይት አዘጋጅቷል
የዛሬው የሚሊዮኖች ድምጽ በአዳማ እና ደብረ ማርቆስ የተቃውሞ ሰልፍ (LIVE UPDATE)
6:00 ሰዓት / 5:00 PM ደብረ ጽዮን ከአዲስ አበባ፣ አዳማ ጋር የቴሌኮሚኒኬሽን መስመር ዘግቶነው የዋለዉ።ኔትዎርኩ እንደተለቀቀ፣ አሊያም የሰልፉ አስተባባሪዎች የነበረዉን ሁኔታ የሚያሳዩ ፎቶዎችና ቪዲዮዎችን ይዘው አዲስ አበባ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ሲመለሱ ይፋ ይሆናል። ከጠዋቱ 5:45 ሰዓት / 4:45 PM የአዳማዉ ሰልፍም በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል። ፎቶዎችና ቪዲዮች እንደደረሱን እንለቃለን። በመኢአድ ጽ/ቤት ተደራዳሪዎች ፊርማቸውን እያሰፈሩ ነው። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የፊርማ ስነ-ስርዓቱ ይጠናቀቃል። ቀደም ብለን ለመጥቀስ እንደሞከርነው፣ አቶ አበባዉ መሃሪ የመኢአድ ሊቀመንበር ንግግር እያደረጉ፣ ድንገት ከዉጭ የድንጋይ እሩምታ በጽ/ቤቱ ላይ ዘነበ። ዱርዬዎች ለመረበሽ ሞክረዋል። በዚሁ ሂደትም በስብሰባዉ የነበሩት የአንድነት የፋይናንስ ክፍል ሃላፊ አዮ ጸጋዬ አላምረው በድንጋይ ተፈንክተዋል። መኢአድና አንድነት በዝግጅቱ ወቅት ፖሊስ ጥበቃ እንዲያደርግ ጠይቀው የነበረ ቢሆን፣ ፖሊሲ በስፋራው አልተገኘም። ሕግና ስርዓት የሚያስጠበቀ ፖሊሲ ሳይሆን የተላኩት ድርዬዎች ነበሩ። ምናልባትም ፖሊሶቹ እራሳቸው የፖሊስ ልብሳቸውን አዉልቀው መጥተዉም ልሆን ይችላል። ተጨማሪ የደብረ ማርቆስ ፎቶ ! ቪዲዮዎች እንደደረሱን ይፋ እናደርጋለን።
ከጠዋቱ 5:30 ሰዓት / 4:30 PM የደብረ ማርቆሱ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል። አንዲት ጠጠር አልተወረወርችም። በንብረትም ሆነ በሰው ላይ ጉዳይ አልደረሰም። ብአደኖች «ሰልፉ ሕገ ወጥ ነው። ይረበሻል»ሲሉ ነበር። ነገር ግን ከሰላሳ ሺህ በላይ የሚሆን ህዝብ ድምጹን በሰላም አሰምቶ፣ በሰልም ተበትኗል። አቶ አበባዉ መሐሪ ንግግር ሊያደርጉ ባለበት ወቅት፣ ከዉጭ ድንጋይ በመወርወር ለመረበሽ ሙከራ ተደርጓል። የአቶ አበባዉ ንግግር ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ ነበር። የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላ ፣ አቶ ጸጋዬ አላምረው በአገዛዙ ከተላኩ ዱርዬዎች በተወረወር ድንጋይ ፈንክቷቸዋል። አቶ አበባው ንግግራቸው ቀጥለዋል። አቶ አበባዉ «መዋድ ብቻ በቂ አይደለም። ለሌላው አርዓያ በመሆን ትግሉን በጥንካሬ መመራት አለብን» ብለዋል።
ከጠዋቱ 5:15 ሰዓት / 4:15PM በአዳራሹ የተጠሩ እንግዶ፣ የፖለቲክ ድርጅት መሪዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች ስፋራቸዉን ይዘዋል። በመኢአድ ጽ/ቤት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉ የአንድነት ሊቀመንበር ንግግር አድርገው ጨርሰዋል። የፓርቲዎች የተናጥል ጉዞ የአምባገነኖችን እድሜ ያራዘመ ነው ሲሉ እንጂነር ግዛቸው አብሮ መስራት ድላን እንደሚያፋጥን ተናግረዋል። «ሁሉም ለአንዱ፣ አንዱ ለሁሉም መታገል አለበት» ኢንጂነር ግዛቸው አንዱዋለም አራጌ መኢአድና አንድነት እንዲዋሃዱ ብጥረት ያደርግ እንደነበረ የገለጹት ኢንጂነር ግዛቸው አንዱዋለም በዛሬው ቀን በሚሆነው ነገር በጣም ይደሰታል ብለዋል። አቶ አበባዉ መሐሪ ንግግር ሊያደርጉ ነው። ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት / 4:00 PM የደብረ ማርቆሱ ሰልፍ እየተጠናቀቀ ነው። በአዳማም እንደዚሁ። በኔትዎርክ ችግር አዳማ ስላለው ሰልፍ ዝርዝር ዘገባ ማግኘት አልተቻለም። በመኢአድ ጽ/ቤት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉ የአንድነት ሊቀመንበር ንግግር እያደረጉ ነው። የፓርቲዎች የተናጥል ጉዞ የአምባገነኖችን እድሜ ያራዘመ ነው ሲሉ እንጂነር ግዛቸው አብሮ መስራት ድላን እንደሚያፋጥን ተናግረዋል። ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት / 4:00 PM በመኢአድ ጽ/ቤት አዳራሽ የቅድመ ዉህደት ስምምነት ፕሮግራም ሊጀመር ነው። የመኢአድና የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊዎች ስለ ፕሮግራሙ፣ አጠር ያለ ዘገባ አቅርበዋል። በቅድሚያ ከምርጫ 97 ወቅት በግፍ ለተገደሊ የሕሊና ጸሎይ ይደረጋል። ከዚያ የአንድነት ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዝቸው ሽፈራው ንግግር ካደረጉ በኋላ፣ የመኢአድ ሊቀምንበር አቶ አበባዉ ይቀጥላሉ። ከዚያም አደራዳሪዎች የቅድመ ዉህደቱን ሰንድ ይፈርሙና የድርጅቶቹ መሪዎች ፊርማቸውን ያኖራሉ። በመጨረሻ ከጋዜጠኞች የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ይመልሳሉ። በአዳራሹ የተጠሩ እንግዶ፣ የፖለቲክ ድርጅት መሪዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች ስፋራቸዉን ይዘዋል። ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት / 3:30 PM ናዝሬት/አዳማ ሰልፉ በድምቀት እየተካሄደ ነው። በርካታዎች ሰልፉን እየተቀላቀሉ ነው። ትልቅ የኔትዎርክ ችግር ግን አለ። በደብረ ማርቆስ በርካታዎች ሰልፉን እየተቀላቀሉ ነው። ብአዴን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በ እሁድ ቀን ሜካፕ ክላስ እንዲሰጣቸው መመሪያ በመስጠቱ ተማሪዎች ትምህርት አለ ተብለው ነበር። ካድሬዎች በየሰፈሩ እየሄዱ እውቅና ያገኘዉን ሰልፍ፣ ሰልፉ ሕገ ወጥ ነው፣ ረብሻ ይነሳል» እያሉ ሲያስፈራሩ ነበር። ነገር ግን እስከአሁን ድረስ ሰልፍ በሰለማ እየተደረገ ነው።፡ከተጠበቀዉ በላይ በርካታ ሕዝብ ተግኝቷል። ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት / 3:00 PM የአዳማው የተቃውሞ ሰልፍ መነሻውን ፖስታ ቤት አደባባይ አድርጎ በበቀለ ሞላ መንገድ አልፎ ወደ ቀይ መስቀል አቅንቶ በአስተዳደር ጽ/ቤት ዞሮ ሰልፉ በተጀመረበት ፖስታ ቤት አደባባይ ሰልፉ ይጠናቀቃል፡፡ አዳማ ያለውን ሰልፍ ለመዘገበ፣ የስልክ መስመር ከአዲስ አበባ አዳማ ማግኘት አልተቻለም። ኔትዎርክ እንጅሩ !!!!!! ዜናዎች እንዳገኝን እናሳወቃለን።፡ በደብረ ማርቆስ መፈክሮች እየተሰሙ ነው። ሰልፉ ደምቋል። የሕሊና እስረኞች በስም እየተጠሩ፣ በአስቸኳይ እንድፈቱ እየተጠየቀ ነው።፡«መብትን መጠየቅ ሽብርተኝነት አይደለም» እያሉ እነ አንድዋለም ጀግኖች እንጆ ሽብርተኞች እንዳልሆነ በመናገር ለሕሊና እስረኞች ያለዉን አጋርነት ሰልፈኛዉ እየተናገረ ነው። ከጠዋቱ 3:45 ሰዓት / 2፡45 PM በደብረ ማርቆስ ከሚታዩ መፈክሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡ «ሙስና የስርዓቱ መገለጫ ነው» «ዜጎችን ማፈናቀልና ማዋረድ ይቁም» «የኦሮሞ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው አፈና በአስቸኳይ ይቁም» «ልማትና ነጻነት አይነጣጠሉም» «የኑሮ ዉድነት የኢሕአዴግ ፖሊሲ ዉጤት ነው» «የኦሮሞ ተወላጆችን የገደሉ በአስቸኳይ ለፍርድ ይቅረቡ»
ከጠዋቱ 3:20 ሰዓት / 2፡30 PM ጁን 8 ዲሲ ሰዓት በደብረ ማርቆስም በአዳማም ሰልፉ ተጀምሯል። መፈክሮች እየተሰሙ ነው።«መብቱን መጠየቅ ሽብርተኝነት አይደለም !»፣ «ዉሸት ሰልችቶናል !» የደብረማርቆሱ የተቃውሞ ሰልፍ መነሻውን ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አደባባይ አድርጎ፣ በአብማ ወደ መስቀል አደባባይ ያመራል። ለደብረማርቆስ ሰላማዊ ሰልፍ ከተዘጋጁት መፈክሮች አንዱ ይህን ይላል
ከጠዋቱ 2:20 ሰዓት / 1፡20 PM ጁን 8 ዲሲ ሰዓት ነጻነት ! ነጻነት ! ነጻነት ! ቢሊሱማ ! ቢሊሱማ ቢሊሱም ! በድብረ ማርቆስና በአዳማ ሰልፉ ከአንድ ሁለት ሰዓት በኋላ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። በዛሬዉ ቀን በመኢአድ ቢሮም ትልቅ ክስተት ይኖራል። አንጋፎቹ የአንድነት እና የመኢአድ ድርጅቶች ለመዋሃድ የቅድመ ዉህደት ፊርማ ይፈርማሉ። ያሏቸውን ጥቂት ልዩነቶች በዉይይትና በምክክር ፈተው፣ ወደ ዚህ ደረጃ መድረሳቸው በጣም ትልቅ ድል ነው።
ከጠዋቱ 1 ሰዓት / 12፡00 PM ጁን 8 ዲሲ ሰዓት በቁጫ ወረዳ ሰልፍ ዛሬ ለማድረግ ዝግጅቶች ተደረጎ ነበር። ግን በዚያ ያሉ ካድሬዎችና ሃላፊዎች ህዝቡ ድምጹን የማሰማት መብቱ እንዳያከበር፣ እንቅፋት ፈጥረዋል። ከአዲስ አበባ የቅስቀሳ መኪና ና የተለያዩ የቅስቀሳ እቃዎችን ይዘው የሄዱ የአንድነት አባላት በወታደር ተከበው ከወረዳው ትላንት ማታ እንዲወጡ ተደርገዋል። ዳዊት ሰለሞን እንደዘገበው የዛሬዉን ሰልፍ በኃይል ካጨናገፉ በኋላ ሕዝብ በጣም መናገዱን የተረዱ የአካባቢው ባለስልጣናት ሰልፉ ለሚቀጥለው ሳምንት እንዲደረግ ጠይቀዋል። የአንድነት ፓርቲ በቁጫ ጉዳይ ላይ የሚያሳለፈዉን ዉሳኔ ከጥቂት ቀናት በኋላ እንሰማለን። አንድ ነገር ግን እርግጥ የሆነው የቂጫ ወረዳ ሕዝብ ሕገ መንግስቱ የሚፈቅደለትን ድምጹን የማሰማት መብት ይጠቀማል። ዳዊት ሰለሞን ቁጫን በተመለክለተና የአዳማዉን እና የደብረ ማርቆስን ሰልፍ በተመለለተ የሚከትለውን ከሰባት ሰዓታት በፊት ጽፏል። «በብዙ ትግል የአዳማና ደብረማርቆስ አደባባዩች ነገ ተቃውሞ ይስተጋባባቸዋል የተለጠፉ ፖስተሮችን ከመቅደድ አንስቶ በቅስቀሳ ስራ የተሰማሩ አባላትን በማሰር በሁለቱ ከተሞች እንዲደረጉ የታቀዱ ‹‹ሰላማዊ››ሰልፎችን ለማክሸፍ የሰሩ ሃይሎች በስተመጨረሻ ህይወታቸውን ጭምር ለመስጠት በማይሳሱ ሰላማዊ ታጋዩች ጥንካሬ ድል በመመታታቸው ወደ ጎሬያቸው ለመግባት ተገደዋል፡፡ አሁን ከተሞቹ ለነገው ሰልፍ ዝግጅታቸውን በማጠናቀቃቸው የሚጠበቀው የሰዓቱ መድረስ ብቻ ነው፡፡በቅስቀሳ ስራ ተሰማርተው የነበሩ አባት በነገው ሰልፍ የሚያዙ መፈክሮችን በማዘጋጀት ስራ ተጠምደዋል፡፡ህዝቡም የታፈነ ድምጹን በአንድነት በኩል ለማሰማት እየተዘጋጀ ነው፡፡በቁጫ አንድነት በተመሳሳይ ቀን ሊያደርገው የነበረ ሰልፍ ለቀጣይ ሳምንት እንዲተላለፍ የአካባቢው አስተዳደር መጠየቁ ተሰምቷል።» ከጠዋቱ 12 ሰዓት ሰኔ አንድ 2006 / 11፡00 PM ጁና 7 ዲሲ ሰዓት አሁን በደብረ ማርቆስና በአዳማ ነግቷል። ከጥቂት ሰዓት በኋላ ሰልፉ ይጀመራል። ላለፉት ሁለት ሶስት ቀናቶች በሁለቱ ከተሞች የነበረው ቅስቀሳ በጣም አስገራሚ ነበር። የአንድነት አስተባበሪዎችና ቀስቃሾች ከሕዝቡ ብዙ ማበረታታን ድጋፍ ሲሰሙ ነው ቀናቶቹን ያሳለፉት። በጣም የሚያስደስተው ደግሞ አብዛኛዉን የቅስቀሳና የዝግጅት ሥራ የሰሩት በአዳማ እና በደብረ ማርቆስ ያሉት የአንድነት አባላት ናቸው። የአንድነት ፓርቲ ድርጅት ጉዳይ ትልቅ ሥራ ነው የሰራዉ። ዜጎችን በክልላቸው እንዲህ አይነት ሥራ ሲሰሩ ማየት በጣም ያስደስታል።
እንደ ዘበት ያለፉት ነፍሶች – (እውነተኛ የወንጀል ታሪክ)
እነዚህ ሁለት የወንጀል ታሪኮች የተፈፀሙበት ጊዜ ጥቂት ዓመታት ወደኋላ ይርቃል፡፡ ሁለቱም ወንጀሎች የተለያዩና የሚያገናኛቸው ነገር የሌለ ቢሆንም ማጠቃለያቸው ግን ሞት መሆኑ ያመሳስላቸዋል፡፡ በተለይ በተለይ የህይወት ህልፈቱ ሳይታሰብ እንደዘበት መፈጠሩ ‹የተቆረጠለት ቀን› የሚባለውን አይነት አሟሟት ያስታውሳል፡፡ ሁለት ነፍሶች በተለያየ ዓመት በተለያየ ሁኔታ በተለያዩ ቀናትና በተለያየ ምክንያት እንደዘበት አልፈዋል፡፡ ሳይታቀድና ሳይታሰብ ህይወታቸውን የተቀሙት ሰዎች መቃብር ውሎባቸው- ገዳዮቹም አስር ቤት አሽጓቸው ተረሳስተዋል፡፡
አንድ
ቀልድ የጠራው ሞት
ጥር ወር 1996 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 15 ነዋሪ ‹አንዳች እንከን የማይወጣለት ፍቅር ያላቸው ናቸው› ይላል፡፡ ለዓመታት በመቀራረብና በመተሳሰብ የዘለቁት ጓደኛሞች ፍቅራቸው ለብዙሃን ምሳሌ ሆኖም ኖሯል፡፡ በመካከላቸው ያለው የእምነት ልዩነት፤ የህይወት ፍልስፍና አለመገናኘት፤ የቤተሰብ ሁኔታ አንድ አለመሆንና ሌሎችም የጋራ ያልሆኑ መለያዎቻቸው ቢበዙም ከዚህ ሁሉ በላይ ገዝፎ የወጣ የጓደኝነት ፍቅራቸው ሁሉን አስረስቷቸው አንድ አድርጓቸዋል፡፡ እንደብዙዎቹ እምነት የጓደኝነት ሙሉ ትርጉም ስፍራ ይዞ የሚታየውና ጎልቶ የሚንፀባረቀው በእነዚህ ሰዎች ነው፡፡
ሁለቱ ወዳጆች አብረው የሚበሉ አብረው የሚጠጡ መሆናቸው ብቻ አይደለም ‹ጓደኛ› የሚለውን ስያሜ ያሰጣቸው፡፡ ሁለቱም ከመብላትና ከመጠጣት በላይ የህይወታቸውን ክፍተት የሚሞሉበትን ፍቅር መሰጣጣት የቻሉ ነበሩ፡፡ አንዱ ሲቸግረው ሌላው እየረዳው፤ አንዱ ሲጨንቀው ሌላው እያዋየው፤ አንዱ ደስ ሲለው ከሌላው እየተካፈለው ስሜታቸውን እየተጋሩት ኖረዋል፡፡ መወለድ ቋንቋ ነው እስከሚባል ድረስ ሁለቱ ወዳጆች አምሳልነታቸውን አንድ አድርገው ዘልቀዋል፡፡ ዓመታትን የተሻገሩትና የወዳጅነታቸውን ዘመን ትሩፋት የተቋደሱት በመካከላቸው ባለው ፍቅርና መቻቻል ነው፡፡ ለዚህም ይሆናል አንዱ ሌላውን ሲያስተዋውቅ ‹ጓደኛዬ ነው› የሚለው ቃል ብቻውን የሚወክልለት የማይመስለውም፡፡ ‹እንደወንድሜ የማየው ጓደኛዬ ነው› በሚል ቃል የወዳጅነታቸውን ልክ ሞቅ አድርጎ መግለፅን ነው የሚያዘወትሩት፡፡
ብዙዎች የእነዚህን ወዳጅነትና ፍቅር ይቀኑበት ነበርና የአብሮነታቸው ‹ሳይንስ› ለማወቅ ይጥሩ ነበር፡፡ ከሁለቱም ጋር የቅርብ እውቂያ የነበረው ወጣት እንደገለፀው ጓደኛሞቹን አንድ ያደረጋቸው ነገር ሁለቱም ቀልድና ጨዋታ መውደዳቸው ነው፡፡ ‹‹መጫወትና መቀለድ ይወዳሉ፡፡ እንደ ህፃን ልጅ ይላፋሉ፡፡ ይደባደባሉ፡፡ ሰዎች እስከሚገርማቸው ድረስ አይለያዩም፡፡ እንደውም አንዱ ሌላውን ካጣው ‹ሳላይህ ስውል ትናፍቀኛለህ› የሚባባሉ ወጣቶች ናቸው፡፡ ይህ ቅርርባቸው አንዱ ሌላውን እንደራሱ አድርጎ እስኪያውቀው ድረስ ልብ ለልብ ያጣመራቸውን ሁኔታ ፈጥሮም ነበር፡፡
አልፎ አልፎ ቢጋጩም ፀባያቸው ብዙም አይከርርም ነው የሚሉት የሚያውቋቸው፡፡ አንድ ሰው ‹‹ሁለቱም ለሳቅና ለጨዋታ ቅርብ የመሆናቸውን ያህል ለኩርፊያም ያንኑ ያህል ናቸው፡፡ ነገር ግን ኩርፊያቸው ራሱ የቀልድ ስለሆነ የሚያመር የለም፡፡ ለምን አኮረፍከኝ ብሎ መጠያየቅም የለም፡፡ ራሳቸው ማንም ሳይመጣ ይቀራረቡና መኮራረፋቸውን እንኳን ይረሱታል፡፡ ኩርፊያ ሲባል ታዲያ ከሰዓታት ያልዘለለው ዓይነት እንጂ ቀናት የሚፈጀው አይደለም›› ብለዋል፡፡
ጥር 23 ቀን 1996 ዓ.ም
ቀን ላይ ሁለቱም ከየዋሉበት መጥተው ተገናኙ፡፡ የዋሉበትም እዚያው ቀበሌ 15 ክልል ‹‹ኬር ኢትዮጵያ እርዳታ ድርጅት›› አካባቢ ነው፡፡ በተለመደው ፍቅርና ሰው ባወቀው የወዳጅነት ውሏቸው ነው ዛሬም የቀጠሉት፡፡ የሚያወቋቸው ሰዎች በሁለቱም ላይ ያነበቡት የተለየ ገፅታ የለም፡፡ የተለመደው ሳቅ- የተለመደው ጨዋታ- የተለመደው ልፊያ- የተለመደው መጎነታተል ዛሬም አለ፡፡ ያያቸው ማንነታቸውን እንኳ ከማወቁ በፊት የአብሮነታቸውን ፍቅር ከፊታቸው የሚቀዳባቸው ሁለቱ ጓደኛሞች ዛሬን እስከ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ያሳለፉት ከዚህ ባልተለየ ሁኔታ ነው፡፡ በመጨረሻ ላይ ግን አንድ ቃል ከሁለቱ ፍቅር መሀል ጥለቅ አለች፡፡ ‹‹ሸፋፋ›› የምትል ቃል፡፡
ተናጋሪው የዘወትሩ ንግግሩን ውጤት የጠበቀ ከፈገግታና ከሳቅ ጋር የሚመላለስ ምላሽ ውስጥ ነው፡፡ አንደኛው እግሩ በመጠኑ ዘወር ያለ መሆኑን አይቶ ነው ሌላውን ሸፋፋ ብሎ የሰደበው፡፡ በእርግጥ ከዚህ ቀደም ይህንን ቃል ተጠቅሞበት አያውቅም ነበር፡፡ ተሰዳቢው ‹ሸፋፋ› የሚለውን የቀልድ ስድብ ሲያደምጥ ውስጡ አንዳች ቁጣ የተተራመሰ መሰለው፡፡ ዘወትር እንደሚያደርጉት ያለ መተራረብ ነውና ተናጋሪው ከአፉ ለወጣው ቃል ቀልብ የሰጠው አልመሰለም፡፡ ከዚህ ቃል በኋላ የዕለቱ የፍቅር ውሏቸው ተቋጨና ተለያዩ፡፡ ተናጋሪው በውስጡ ነገን እየናፈቀና አብረው የሚውሉበትን ሰዓት እያሰበ ወደ ቤቱ ሲገባ ‹ሸፋፋ› የተባለው ደግሞ ከራሱ ጋር እያወራና ብስጭቱ ያመጣበትን ግልፍተኝነት ለማረጋጋት እየሞከረ ሄደ፡፡ ጥቂት ሰዓታት አለፉ፡፡
ተናጋሪው ሰውዬ ከቤቱ ወጣ፡፡ ሚስቱና ልጁን ሰላም ብሎ ወደ ጎረቤት ነበር አወጣጡ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ቴሌቪዥን ለማየት ነው፡፡ ቤቱ ቴሌቪዥን የሌለ በመሆኑ ጎረቤት ወዳለው ጓደኛው ነበር የሄደው፡፡ እዚያ እየተጫወተና በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ሙዚቃ እየኮመኮመ ቆየ፡፡ ቀኑ ማመሻሸት ጀምሮ ነበርና ልቡ ወደ ቤቱ በመሄድና እዚያው በመቆየት መካከል ሲወላውል ስሙ ሲጠራ የሰማ መሰለው፡፡ የልጁ ድምፅ ነው፡፡ ‹አባዬ ና ትፈለጋለህ› ሲል ሰማው፡፡
ይህን የ10 ዓመት ህፃን የላከው የአባቱ ጓደኛ የሆነው ያ ‹ሸፋፋ› ተብሎ የተተረበ ሰው ነው፡፡ በልቡ ያሰበውን እኩይ ተግባር አንግቦ ወደዚህ ወዳጁ ቤት ሲመጣ በዚያ እሳት የለበሰ ስሜቱ ውስጥ እንዳለ ሆኖ የፈለገውን ማግኘት አልቻለም፡፡ የሰውየው ሚስት ‹ባልሽ የት ሄደ?› ተብላ ስትጠየቅ ነገሩ ስላላማራት ቤት አለመኖሩን ትናገራለች፡፡ ምንም የማያውቀው የ10 ዓመት ህፃን ደግሞ ብቅ ብሎ ‹አለ- ጎረቤት ቴሌቪዥን ሊያይ ሄዶ ነው› በማለቱ ነው ጥራው ተብሎ የጠራው፡፡
የሚፈልገው ሰው ማን እንደሆነ ለማወቅ ብቅ ያለው ወጣት ጓደኛው መሆኑን ሲያውቅ ፈገግ ብሎ ተናገረው፡፡ ‹‹ምነው በሰላም ነው? አብረን ውለን ትፈልገኛለህ?› ብሎ ነበር የጠየቀውና ወደ ቆመበት የተጠጋው፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሚስትና ህፃን ልጅ ቆመው ይመለከታሉ፡፡ ወደ ጠሪው ሲቃረብ ያ ‹ጥሩልኝ› ያለ ወጣት በጥፊ ተቀበለው፡፡ ራሱን ለመከላከል ሙከራ በሚያደርግበት ወቅት ደግሞ ያላሰበውን ጩቤውን ከጎኑ አውጥቶ አንገቱ ላይ ሽጦበት ሮጦ ሄደ፡፡ ልጁና ሚስት በሁኔው ተደናግጠው ሲጮሁ የተወጋው ሰው ጥቂት ለመንገታገት ሞክሮ ባለመቻሉ በቁሙ ተዘረረ፡፡ ጎረቤቶች ጩኸት ሰምተው ሲወጡ ከተጎጂው አንገት ስር የሚወርደው ደም አካባቢውን አበላሽቶት ነበር፡፡ ወደ ሕክምና ሊወስዱት ሲያነሱት ግን ህይወቱ አልፋለች፡፡
ማንም ባላሰበውና ባልገመተው ሁኔታ ገዳይ ‹ሸፋፋ አለኝ› በሚል ምክንያት ቤቱ ገብቶ ጩቤ ታጥቆ ለግድያ መውጣቱ ብዙዎችን አስገርሟል፡፡ ቀናቸውን በመተራረብና በመሳሳቅ የሚያሳልፉ ሁለት ጓደኛሞች በግድያ የቆየ የወዳጅነት ፋይላቸውን ሲዘጉ መስተዋሉም ለብዙዎች እንቆቅልሽ ነበር፡፡
ተጠርጣሪው ከሸሸበት በህዝቡ ትብብር ተይዞ ሲጠየቅ ‹በፈለገው ነገር ቢቀልድ ምንም አይመስለኝም፡፡ ነገር ግን በተፈጥሮዬ እንዴት ይቀልዳል?› ነበር ያለው፡፡ ሁሌም የለመዱት መተራረብና መሰዳደብ ላልታሰበ ግምት ሊያደርሳቸው እንደሚችል የጠረጠረ የለም፡፡ ሟችም ሀገር አማን ብሎ የተቀመጠ- እንኳን በጓደኛ በሌላ ሰው እጠቃለሁ ብሎ የማያስብ እንዲሁም እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ለገዳዩ የነበረው ፍቅር ያልቀነሰ ምስኪን ነው፡፡ በአንዲት ቃል ህይወት ጠፋ፡፡ የጓደኛው ሞት ያሳዘነው የሚመስለው ገዳይ ‹‹ሳላስበው ሰይጣን አሳስቶኝ ያደረኩት ነገር ነው›› አለ፡፡ የሁለቱ ፍቅር በመቃብርና በእስር መደምደሙ ግን ግድ ሆነ፡፡ እናትና ልጅም እያዩት አባወራቸውን ቀበሩ፡፡
ሁለት
የ‹ዱብ ዕዳ› ምሽት
ነሐሴ ወር
1998 ዓ.ም
መሽቷል፡፡ አፋር ኬክ ቤት አካባቢ ከፒያሳ ወደ ሰይጣን ቤት በሚስደው ቁልቁለት መንገድ ላይ የክረምቱ ዝናብ መውጫ መግቢያ አሳጥቶት የዋለው አዲስ አበቤ በየካፌዎቹና በየሬስቶራንቱ ተጠልሎ ጋብ ሲልለት ነው ወደ አስፓልቶቹ ወጣ ያለው፡፡ በአንፃሩ ሌሎች በየቤታቸው ተቀምጠው የነበሩ ወደ ካፍቴሪያዎች ‹ሞቅ ላለ ሻይ› ጎራ ብለዋል፡፡ ጭር ያለው የክረምት ቀን ምሽቱ አካባቢ ደመቅ ያለ ይመስላል፡፡
ስዩም የ27 ዓመት ወጣት ነው፡፡ የዚያን ዕለት ከእናቱ ጋር ነው የዋለው፡፡ ወደ አመሻሹ ላይ ሲወጣ እቁብ ክፈል ተብሎ የተሰጠውን አንድ ሺ ብር ይዞ ነበር፡፡ ብቻውን ወደ አፋር ኬክ ቤት ጎራ ያለው ሻይ ለመጠጣት ብሎ ነበር፡፡
የስዩም ሰፈር እዚያው አካባቢ ነው፡፡ ቴዎድሮስ አደባባይ አስከሬን አበባ የሚሸጥበት በተለምዶ አበባ ሰፈር ተብሎ የሚጠራው አካባቢ በአካባቢው ልጆች ጋር የሚቀራረብ ቢሆንም ብዙዎች ግን የግሩፕ ፀብ የሚወዱ በመሆናቸው ብዙም ሊጠጋቸው አይፈልግም፡፡ የዚህ ወጣት ስራ መማር መስራት ህይወቱን በአግባቡ መምራት ብቻ ነው፡፡
ሻዩን ጠጥቶ ሲወጣ ከ3 የሚበልጡ ወጣቶች ቆመዋል፡፡ አያውቃቸውም፡፡ እነርሱ ግን የሚያውቁት መሰለው፡፡ አስተያየታቸው አላማረውም፡፡ ከምሽቱ 2 ሰዓት ሆኗል፡፡ አንደኛው ‹ና ወደዚህ› አለው፡፡ ስዩም አካባቢውን ቃኘት አደረገ፡፡ ብዙ ሰው የለም፡፡ ፈራ፡፡ የጠሩት በሰላም እንዳልሆነ ገብቶታል፡፡ ነገር ግን አማራጭ አልነበረውምና ተጠጋቸው፡፡ አጠገባቸው ከደረሰበት ደቂቃ ጀምሮ መጨረሻ እስከሆነው ነገር ድረስ ያዩ ሰዎች ነገሩን ለፖሊስ ተርከውታል፡፡
‹‹ተጠጋቸው፡፡ በዚህ መሀል ወዲያው በላይ የተባለው አንደኛው ጠጋ አለና በያዘው ጫፉ ላይ ብረት ያለው ዱላ አናቱን መታው፡፡ ስዩም ወደቀ፡፡ በወደቀበት ቦታ ጥለውት ይሄዳሉ ሲባል ከየት እንደመጡ ያልታወቁ 11 ወጣቶች ድንገት ደረሱና በወደቀበት ቀጠቀጡት፡፡ ጌቱ የተባለ አንድ ወጣት የስዩም መቀጥቀጥ አልበቃ ብሎት ድንጋይ አምጥቶ ጭንቅላቱን መታው፡፡ ስዩም ጣር ላይ ነበር፡፡ ድንገት ብድግ ብሎ ከዚያ ውርጅብኝ ለማምለጥ ሮጠ፡፡ ብዙ ርቀት ግን አልተጓዘም፡፡ ተደናቀፈና ቦይ ውስጥ ወደቀ፡፡ በዚው ቀረ፡፡ ይህን ያዩና ሲሮጥ የተከታተሉት ደብዳቢዎቹ አልተዉትም፡፡ እዚያው የየድርሻቸውን ደብድበውት ጥለውት ሄዱ፡፡ በዚያን ጊዜ የአካባቢው ሰዎች ለማገላገል ያደረጉት ሙከራ የለም፡፡ የቡድን ፀብ በጣም ይፈራ ስለነበር ነገሩን በዝምታ ከመከታተል ውጪ ምርጫ ያለው አልነበረም፡፡ በቅፅበት ውስጥ የተከናወነው ድብደባ ደግሞ ፖሊስ ለመጥራት አመቺ አልነበረም፡፡ ያም ሆነ ይህ ትቦ ውስጥ የወደቀውን ተደብዳቢ ለማንሳት ወደ ስፍራው የሄዱት የአካባቢው ሰዎች ወጣቱ በዘግናኝ ሁኔታ መሞቱን አወቁ፡፡ በጨለማ ድብደባው ወቅት ሌዘር ጃኬቱን፣ ያጠለቀውን የወርቅ ሀብልና ኪሱ ውስጥ የተገኘውን 1 ሺ ብር የወሰዱት ደብዳቢዎች ተሰውረዋል፡፡
ጥቂት ቀናት ከፈጀ ምርመራና ክትትል በኋላ የተያዙት 11 ተጠርጣሪዎች ግድያውን አንዱ በአንዱ ላይ ሲያላክኩ ቆዩ፡፡ በተለይም የገደልኩት እኔ አይደለሁም ለማለት ከፍተኛውን የድብደባ ደረጃ ወደ ሌላ ለማዞር ጥረት ተደርጎም ነበር፡፡
የግድያው መነሻ የተባለው ነገር ነው ለሁሉም አስገራሚ የነበረው፡፡ ሁሉም ተጠርጣሪዎች ስዩምን አያውቁትም፡፡ ከሁሉም ውስጥ አንዱ ‹ና› ብሎ የጠራው ብቻ ስዩም ‹የአበባ ሰፈር› ልጅ እንደሆነ ያውቃል፡፡ ስዩም ተማሪ ይሁን አስተማሪ ሰራተኛ ይሁን ስራ አጥ የሚያውቅ የለም፡፡ ነገር ግን አንድ እውነት አለ፡፡ ስዩም የአበባ ሰፈር ልጅ ነው፡፡ በአበባ ሰፈር ነዋሪዎችና በእነዚህ ወጣቶች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ፀብ አምርቶ አሁን ሁለቱም ሰፈሮች ለጥቃት ተዘጋጅተው የተቀመጡ ናቸው፡፡ ይህን ደግሞ አንድም ወጣት ቢሆን ‹ሰፈሩን ላለማስደፈር› እንዲነሳ አድርጎታል፡፡ ይህም የቡድን ፀብን አስፋፍቷል፡፡
ስዩም አንዳች በማያውቀውና በማይጠረጥረው መንገድ ህይወቱ ሲጠፋ ለሰሚ ግራ የሚያጋባ ነበር፡፡ የቡድን ፀብ ተሳታፊ ሳይሆን አበባ ሰፈር የሚኖር ሰው በመሆኑ ብቻ የፀበኞች ጥማት ማስታገሻ መሆኑ ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡
ለዚህ እንደዘበት ያለፈ ህይወት ብዙዎች ‹ቀኑ ከዚህ አትለፍ ቢለው ነው› በማለት ሃሳባቸውን ሊሰጡ ቢሞክሩም ይህን መሰል ክስተቶች ማመዛዘንና ማሰብ በተሳናቸው ሰዎች ወደሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶች እንደሚመራ ፖሊስ ተናግሯል፡፡
የቡድን ፀብ የአዲስ አበባ ከተማ ዋነኛ ችግር በነበረበት በዚያን ዓመት በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የሚፈፀሙ ወንጀሎች ተበራክተው- ብዙዎችም ከህይወት ህልፈት እስከ ንብረት ውድመት ደርሶባቸው መኖራቸው ፖሊስ ችግሩን ለመከላከል ጠንካራ አሰሳ እንዲያደርግ አድርጎታል፡፡ የዚያም ውጤት ነው እነዚን ከ11 ያላነሱ የቡድን ፀብ ተዋንያን ለዚህ አንድ ነፍስ መጥፋት ዋና እና ተባባሪ ወንጀለኛ አድርጎ እንዲከስሳቸውና ወደ ዘብጥያ እንዲያወርዳቸው ምክንያት የሆነው፡፡
“አባ” ግርማ! እንኳን ለግንቦት ፳ አደረሰዎ! ይኽቺ ጎንበስ-ጎንበስ ዕቃ ለማንሳት ነው!
ወንድሙ መኰንን – ከብሪታኒያ
ሚያዝያ ፴ ቀን ፪ሺ፭ ዓ. ም
7 June 2014
ወያኔ አሁን ደኅና ልማታዊ መነኵሴ አገኘች! ጎሽ! የለንደኑ ኤምባሲዋ፣ አዲሱን ወዶ-ገባ ለግንቦት ፳ አሰልጥና አስመረቀች! በድንኳን ባደረገቸው ድግስ ላይ በግልጽ ለዕይታ አበቃች። ማብቃቷንም በራሷ የሚዲያ መረብና (http://www.ethioembassy.org.uk/news_archive/Ginbot-20_celebrated_in_London.pdf) እና በዓይጋ ድረ-ገጿ በተነች። “አባ” ግርማ፣ የለንደኗን ርዕሰ አድባራት ደብረጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ሕንጻና ንብረቷን፣ እጅ መንሻ አድርገው በማቅረባቸው፣ አሁን የወያኔ ባለውለታ አሽከርነታቸውን አረጋገጠዋል። እንዲያ ነው እንጂ! ማጥ ውስጥ ከወደቁ አይቀሩ በቅጡ መንከባለል ይሻላል። ለወያኔ አድረዋል ስንል፣ “ስም አጥፊዎች” ተባልን። አሁን ደጋፊዎቻቸው ምን ይበሉ? በየሳምንቱ፣ የጥበቃ ዘበኞችን ቀጥራ ስታስጠብቃቸው የነበረችው በከንቱ አልነበረም። በነዚህ ፈርንጆችና ሶማሌ እንግዶች መሀል የሚታዩት ሁሉቱ ከሀዲ ግርማዎች ናቸው – ግርማ ከበደና፣ ግርማ ቡፋ ይባላሉ! ተዋወቋቸው!
እዚያም ሂደሽ በላሽ! እዚህም መጥተሽ በላሽ!
ሰው ታዘበሽ እንጂ ሆድሽን አልሞላሽ!
የሆድ አደሮች ሕሊና ግርም ነው የሚለኝ። ምንም ባወጣው-ባወርደው፣ ልደርስበት አልቻልኩም። ሕሊናቸው የሚመራው፣ በአዕምሮአቸው ሳይሆን በሆዳቸው መሆን አለበት ልበል? እኚህ ሰው፣ ከዚህ በፊት፣ ጸረ-ወያኔ ነኝ ብለው በመቅረባቸው፣ ወያኔ ገዳሞቻችንና ቤቴክርስቲያኖቻችን ላይ የምታደርገውን ግፍና በደል ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በመቃወማቸው፣ የሕዝቡን አመኔታና ከበሬታ አገኙ። በሔዱበት ሁሉ የክብር ቦታ ተሰጣቸው። ሬስቶራንት ከሔዱ፣ አንዲት ሳንቲም ሳይክፍሉ የሚመገቡ ተወዳጅ “አባት” ተበለው ነበር። እስቲ እግዚአብሔር ያሳያችሁ፣ እንደዚያ የወደዳቸውንና ያከበራቸውን ሕዝብ፣ ለጠላቱ አሳልፈው ለኩርማን እንጀራ ሲሸጡት ምን ይባላል? ሕሊና ቢኖራቸው፣ እንዲህ በየወያኔ ድግሱ እየዞሩ መብላት ቀርቶ በሰላም ተኝተውም የሚያድሩ አይመስሉኝም ነበር። “እሳቸው እልኸኛ ናቸው እንጂ፣ ከወያኔ ጋር አይሰለፉም” ከሚሉት ምዕምናን መሀል አንዱ ነበርኩ! ወይኔ ሰውዬው! አሁንም ተሸወድኩ። ሰውን በሰውነቱ ስለማምን ነው በየጊዜው ጉድ የምሆነው! ሰው ግፍ ሠርቶ በሰላም ይተኛል? ምን ዓይነቶቹ ጉዶች ናቸው፣ ሆድ-አደሮች? እስካሁን ያየኋቸው ሆዳ-አደሮች፣ ክርስቶስን ከሸጠው ይሁዳ ጀምሮ፣ ሰሎሞን ተካልኝንም በሉ፣ “አባ መላ” የሚባለውን ገበየሁ ባልቻ፣ አሁን ደግሞ የለንደኑ ግርማ ከበደ (ዕውነተኛ ስማቸው “ግሩም”) 1800 ዙረው የክሕደት አክሮባት ሲሠሩ፣ አለማፈራቸው፣ ሊዋጥልኝ ያልቻለ ጉድ ነው። ምናልባት የቁጥር እንጂ የሥነ-አዕምሮ ባለሙያ ባለመሆኔ አልገብቶኝ እንደሆን! እራሴን በነሱ ቦታ አስቀምጬ ስገመግመው ሁሌ ይሰቀጥጠኛል! ስለነሱ አፈርኩ!
የታወቁት የፖሊቲካ ግልሙትና (ይቅርታ ለእንግሊዚኛው “political prostitution” ለሚለው ቃል በ”ሸ” የሚጀምር አማርኛ ቃል ቢኖርም፣ መጠቀም ስለከበደኝ ነው) ተዋኒ ፍጡሮች፣ አስገራሚ አክሮባት/መገለባጥ ግብራቸው ነው። መቼም በተለምዶ “ትያትር”/ድራማ የሚባለውን ተውኔት ሲተውኑ ከጳጳሱ በላይ ካቶሊክ ሁነው ነው ቁጭ የሚሉት። “ወይ-ያኔ! ወይ-ያኔ! አንተን አንተን አያርገኝ የዚያን ቀን መጥኔ” ሲለን ስንቶቻችን ነን ከመቀመጫችን ተንስተን “ሰሎሞን! ሰሎሞን!” ብለን ላንቃችን እስኪነቃ የጮኽነው? አሁን ያን ሰሞን፣ አባ መላ የተባለው ጉድ “ወያኔን ክጄ ከተቃዋሚው ጎራ ተቀላቅዬአለሁ” ሲለን ስንቶቻችን ነን የክብር ቦታ የሰጠነው? አዪዪዪዪዪ! ተመልሶ ገባ!
እስቲ ግሩም ጸረ-ወያኔ ሁነው የከየኗትን ተውኔት ላስታውሳችሁ! የዘመኑ ቪዲዮና ሞኝ የያዘውን አይለቅም አይደል!
“ገዳማትን መንካት ማለት ኢትዮጵያን መንካት ነው! ወያኔ ገዳሞቻችንን አትንካ” ብለው ላንቃቸው እስኪነቃ እንዳልጮኹ ተገልብጠው የወያኔን 23ተኛ የጨለማን ዘመን አክባሪ ሁነው ተገኙ! እንኳን ለዚህ አበቃዎት “አባ” ተባዩ ጉድ!
የወያኔ የታማኝነት ባጅ ያገኙበትን ሌላ አጭር ግን በጣም አስገርሚ ተውኔት እስቲ እናስታውስ! አሁን እኚህ ናቸው መነኵሴ!
http://www.youtube.com/watch?v=otlM6x8mzWk
ወዶ-ገባ ልብሱ ዳባ ይባላል። አሁን ወያኔ እንደፈለገችው ልታሽከረክራቸው ትችላላች። ግን የግሩም አወዳደቅ ከባድ እንደሚሆን አትጠራጥሩ። እህታችን፣ ገጣሚ አበባ አመዴ እንዲህ ብላ ነበር፡
እላይ ቤት እታች ቤት፣ ስትይ አገኝ አገኝ
ጅብ አህያ ለምዷል፣ እኔ አንቺን አያርገኝ።
እኚህ ሰው “ሕዝብ ምን ያውቃል። እንደነዱት የሚነዳ ከብት ነው” ብለው ሕዝብ ሲንቁ በጆሮዬ ሰምቼአቸውለሁ። የቀበሮ ባሕታዊው፣ ወያኔ ሲወድቅ አብረው እንደሚንኮታኮቱ አትጠራጠሩ! እኚህ እግዚአብሔርም ላይ፣ ሕዝብም ላይ ግፍ የሠሩ የበሉበትን ወጪት ሰባሪ ግለሰብ ለብዙ ሥቃይ ዳርገውናል። ከዚህ በኋላ፣ እኚህን ሰው፣ ወያኔ እንደ ሰብዓዊ ፍጡር ሳይሆኑ እንደ ከግዑዝ አካል ዕቃ ተጠቅማ ትተፋቸዋለች። ለመሆኑ፣ ይኸ አክሮባት ሠርቶ ወያኔ ሥር ጎንበስ-ጎንበስ ማለት የቱን ዕቃ ለማንሳት ይሆን? ለመሾም-ለመሸለም? ይቅርብዎት “አባ!” የወያኔ ሹመት ምን ማለት እንደሆነ ሟቹ ጣዖታቸው መልስ ነግሮን አሸልቧል! “የወያኔ ሹመት የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው! ሽልብ ሲያደርግ ዱብ!”
ለምንኵስና ሕዝባችን ያለውን ክብር በማወቅ፣ “መነኵሴ ነኝ” ብለው የቀረቡን ግሩም፣ በሶልዲ ሸጡን! ትላንትና “ወያኔ! የዋልድባን ገዳማት አትንካ፣ የአሰቦትን ገዳም አትንካ፣ የዝቋላን ገዳም አትንካ” ብለው “ያዙኝ ልቀቁኝ” ሲሉ የነበሩት የቀበሮ ባኅታዊ፣ የለንደኗን ደብር ሳይቀር ለዕጅ መንሻ፣ ሕዝቡን ቀንሰው፣ አቅረበዋት በትነውን ከወያኔ ሰይጣኖች ጋር ግንቦት ፳ ለማክበር ድግሷ ላይ በኩራት ተገኙ! እነሆ ሕጻኑ፣ ሴቱ፣ ወንዱ ሽማግሌውና ወጣቱ፣ ውጭ ጸሐይና ውርጩ እየተፈራረቀበት፣ ይንከራተታል። እሳቸው ግን እነሆ በግልጽ ከወያኔ ጋር አዲስ ፍቅር ጀምረዋል። አዲስ ፍቅር ያመናቅር! ይመቻችሁ! ከርታታው የቤተክርስቲያኗ ምዕምን ግን ከወያኔ ጋር ትንቅንቅ ከጀምረ ሁለት ዓመት ሊያስቆጥር ምንም አልቀረውም። ሕገ-ወጡ የወያኔ ጳጳስ፣ እንጦንስም በጉልበታቸው፣ ያለምንም ሀፍረት፣ በወያኔ ቅጥረኛ ዘበኞች ታጅበው የቤተክርስቲያናችንን ቁልፍ ከግሩም ተረክበው፣ በሯን ገፍትረው ከፍተው ገብተዋል። አልፈው ተርፈውም፣ አንድ ከሕዝቡ ጋር የሚንከራተቱትን ካህን ሕዝቡን እንዳያገለግሉ ለመገዘት ዳድቶአቸዋል። ጻዲቅ ቢሆኑ እንኳን ባማረባቸው። እንደ የወያኔዎች ባለሟሎች “ሕግ እንዳንተላልፍ” ተመክረን፣ በትዕግስት አንጡራ ገንዛባችንን አንጠፍጥፈን፣ የገዛናትን ቤተክርስቲያናችን ለስኳተርስ ትተንላቸው ምዕምናኑ ውጪ ቁመን እግዛብሔርን በማምለክ ላይ እንገኛለን። አልሆነላቸውም እንጂ ከዚያም ሊያባርሩን ዳድቶአቸው ነበር። ልብ እንቅርት ይመኛሉ ነው የሚባለው? ቢሆንም የለንደን ኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ትግል፣ አልተቋረጠም። ቀጥለንበታል! ወያኔና የቀበሮ ባሕታውያን እንዳዋረዱን፣ እግዚአብሔር በሕግ ፊት ያዋርዳችዋል።
በዓለም ተበትናችሁ የምትኖሩ፣ ወገኖቻችን፣ በያላችሁበት በጸሎት አትርሱን። ፍርድ ቤት ስንደርስ ለሚያፈልገን ሁሉ ከጎናችን ቁሙልን! የወያኔን ዓላማ ለንደን ላይ ድባቅ መምታት ማለት ሌላ ቦታ እንዳይሞክር አከርካሪውን መስበር ማለት ነው! ከዚህ በፊት ወያኔ እንዴት አድርጎ የቀበሮ ባህታውያንን አሰልጥኖ እንዳሰረገብን በሰፊው ጽፌአለሁ። ዞር ዞር እያላችሁ፣ አካባቢአችሁን እዩ! የቀበሮ ባሕታውያንን ከመሀከላችሁ ከተሰገሰጉ በዓይነ-ቁራኛ ተከታተሉአቸው። ለሥልጣንና ለገንዘብ ሲንገበገቡ ትነቁባቸዋላችሁ! ለንደንን ያያችሁ ተቀጡ! ሀሳዊ መነኵሴ ጎንበስ-ጎንበስ ካለ ነገሩ ‘ዕቃ ለማንሳት” ነውና ጠንቀቅ በሉ። ዕውነተኛ አባቶችን በፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁና፣ አይጭነቃችሁ!
እግዚአብሔር የግሩምን መጨረሻ ያሳየን! አሜን!
Sport: የውጭ ተጫቾች በኢትዮጵያ- ተጠቀምን ወይስ ተጠቀሙብን? –ከገነነ መኩሪያ (ሊብሮ)
አላን ኮል የተባለ ጃማይካዊ በ1969 ዓ.ም ለአየር መንገድ ሲጫወት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጀው ውድድር የተጫወተ የመጀመሪያው የውጭ ተጨዋች ነው፡፡አላን መልኩ ቀይ ሆኖ ቁመቱ ረጅም ሲሆን በኳስ ቴክኒክ ችሎታው የተደነቀ ኳስን እንደፈለገ የሚያደርግ ነበር፡፡ከምድር ጦር ጋር በተደረገ ጨዋታ ሪጎሬ እግሩን አቆላልፎ ሲመታ ተመልካቹ በጣም ተደንቆ ነበር፡፡አላን ኮል የታዋቂው የሬጌ አቀንቃኝ የቦብ ማርሊ ፕሮሞተር ነበር፡፡ከቦብ ጋር አብሮ አደግ ሲሆን ቦብ በ1971 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ያስመጣውም እርሱ ነበር፡፡ በእርግጥ በአዲስ አበባ ስታዲየም ለማቅረብ ያሰቡት ዝግጅት ባይሳካም(ይሄ ነገር እንዴት እንደከሸፈና ቦብ ሻሸመኔ መጥቶ የተከሰተውን ነገር ማወቅ ትፈልጋላችሁ?ልጻፍላችሁ?)አላን አሁን በእንግሊዝ ሀገር ይገኛል ፡፡በተጫዋችነት ዘመኑ ለአርጀንቲና ብራዚል ክለቦች ተጫውቷል ፡፡ናውቲካ፤ አጀኖቲካና ሳንቶስን የመሳሰሉ ክለቦች አዳርሷል፡፡አየርመንገድ አላንን ከውጭ አስመጥቶት እንደ ፕሮፌሽናል ተጫዋች ኮንትራት ተፈራርሞ ሰይሆን በሌላ ጉዳይ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለመጣ እንዲጫትላቸው ጠይቀውት ነው፡፡ ወደ ሀገሩ ለእረፍት ሲሄድ ትራንስፖርት በነጻ ነው፡፡ከአላን በኋላ የውጭ ተጨዋቾች መምጣት የጀመሩት ከ18 አመት በኋላ ነበር ፡፡በ1987 ዓ.ም ከኬንያ አንድ ናይጀሪያዊ አጥቂ ጊዮርጊስ አስመጣ፡፡አመት ቆይቶ ሄደ ፡፡ከዚያ በኋላ ለተወሰነ አመታት የመጣ ሰው አልነበረም፡፡ ካለፉት 12 አመታት ግን እየተበራከቱ ከበረኛ እስከ አጥቂ በመጉረፍ ላይ ይገኛሉ…………በእኔ እይታና ምደባ ከውጭ የሚመጡ ተጫዋቾች በአምስት ይከፈላሉ፡፡በተለይ ከናይጀሪያ፤ጋና፤ካሜሩን የመጡ ፡፡ለምሳሌ ከናይጀሪያ የሚመጡትን ስናይ
1ኛ ደረጃ፡- አውሮፓ በተለይ ትላልቅ ሊጎች እንግሊዝ፤ስፔይን ጣሊያን የሚጫወቱ
2ተኛ ደረጃ-፡ ምስራቅ አውሮፓ እንደ ሩማንያ፤ቡልጋሪያ የሚጫወቱ
3ተኛ ደረጃ-፡ በኤሽያ የሚጫወቱ
4ተኛ ደረጃ-፡በአፍሪካ ሰሜን አካባቢ ቱኒዝያ፤ግብጽ፤ሞሮኮ የሚጫወቱ
5ኛ ደረጃ-፡ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ናቸው፡፡እዚህ የሚጫወቱት ምራጭና አራቱ ጋር እድል ያላገኙ ሰሜን አፍሪካ ሞክረው ሳይሳካላቸው የሚመጡ ናቸው፡፡ስድስተኛ ደረጃ ስለሌለ የመጨረሻቸው እዚህ ነው፡፡በሀገራቸው ምናልባት ቀበሌ ካለ ከዚያ ወይም በዚያ አቻ ከሆነ ቦታ ወይም ሰፈር ከሚባለው ሜዳ የመጡ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡እዚህ የሚመጡት የናይጀሪያ ፤የካሜሩን ተጫዋቾች አንድም ቀን ለሀገራቸው ብሄራዊ ቡድን ያልተጫወቱ ፡፡መጫወት ብቻ ሳይሆን ለምርጫ የመጠራት እድል የማያገኙ ናቸው፡፡ፊፋ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን እነዚህን ተጫዋቾች የሀገራቸው ብሄራዊ ቡድን ሲጫወት የኢትዮጵያን ክለቦች ቶሎ እንዲለቋቸው አያስገድድም (ስለማይጠሩ)ክለባቸውም ለብሄራዊ ስለማይሄዱ የተጫዋች እጥረት ይገጥመኛል የሚል ሀሳብ የለበትም፡፡እስካሁን በብዛት ተጫዋች በግንባር ቀደም ያስመጣው ጊዮርጊስ ነው፡፡ካሜሩን ፤ኬንያ፤ሩዋንዳ፤ናይጀሪያ፤ታንዛንያ፤ኡጋንዳ፤ጋና……ጊዮርጊስ ከ1987 ጀምሮ ሲያስመጣ አስካሁን በውጭ ተጨዋች በመጠቀም 19 አመት ሆኗቸዋል፡፡ በእነዚህ አመታት ጊዮርጊስ ምን ተጠቀመ? ጊዮርጊስ እነዚህ የውጭ ተጫዋቾች ከማምጣቱ በፊት በርካታ ዋንጫዎች አግኝቷል፡፡እነርሱም ከመጡ በኋላ ሻምፒዮና ሆኗል፡፡ስለዚህ በእነርሱ የተለየ ነገር አላገኘም፡፡ጊዮርጊስ በኢንተርናሽናል ውድድር እነርሱ ከመምጣታቸው በፊት ደካማ ነው፡፡የውጭ ተጫዋቾች ይሄን ይቀርፋሉ እንዳይባል በፊትም የነበረውን ውጤት ነው አሁንም ያስመዘገበው፡፡በዚህ 12 አመታት በርካታ የውጭ ተጫዋቾች ወደ ክለቡ መጥተው የምስራቅ አፍሪካ(ሴካፋ)ዋንጫን እንኳን አላገኙም ፡፡ታዲያ የውጭ ተጫዋቾች በጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ ምን የተለየ ነገር አሳዩ? በኢንተርናሽናል ለውጥ ከሌለው ለሀገር ውስጥ ዋንጫ ድሮም በኢትዮጵያውን ተጫዋቾች ውጤት ያመጣል፡፡ለውጥ ለሌላው ነገር ቢሳተፉ ዶላር ይወስዳሉ በተጨማሪም የአንድ ሀበሻ የመጫዋቻ ቦታ ይይዛሉ………….. መብራት ሀይል በሚያሳድጋቸው ተጫዋቾች ጥሩ ቡድን በተደጋጋሚ ሰርቷል፡፡ማሳደጉ የተጀመረው በ1958 ጀምሮ ነው(ከፍቃደ ሙለታ-እስከነ መስኡድ ድረስ)ከዚያን ጀምሮ በብዛት ከታችኛው ቡድን ያወጣል፡፡ በ1993 ዓ.ም ደብል ዊነር ሲሆን በአብዛኛው ባሳደጋቸው ተጨዋቾች ነው፡፡
ካለፉት አራት አመታት ወዲህ ግን ከውጭ በግዢ በሚያስመጣቸው ተጫዋች እየተጠቀመ ነው፡፡ በቡድን ብቃት፤ በተጫዋች ጥራትና በውጤት ያሁኑ ቡድን ከበፊቱ ያነሰ ብቻ ሳይሆን የወረደ ነው፡፡ከጨዋታም ከውጤትም የለበትም፡፡በማሳደግ ጥሩ ተጫዋች እያገኙና ይሄን በቡድኑ ባህል የሆነውን አሰራር አፍርሶ ምንም ለውጥ ወዳላሳዩ የውጭ ተጫዋቾች መሄድ ለምን አስፈለገ?
1 ከገንዘብ አንጻር
2በብዛት ከማሳደግ አንጻር
የተሻለው የበፊቱ ነው፡፡በተለይ በ2004 ከበረኛ ጀምሮ እስከ አጥቂ በውጭ ተጫዋች ተደራጅቶ ነበር ፡፡አስታውሳለሁ ደጋፊው የናይጀሪያን ባንድራ ይዞ እስከማውለብለብ ደርሶ ነበር፡፡ቡድኑ የኢትዮጵያ መብራት ሳይሆን የናይጀሪያ መብራት ሀይል ይመስል ነበር፡እነዚህ ከውጭ ብዛት ተጫዋች የሚያስመጡ ለወደፊቱ ደጋፊ ከናይጀሪያ ካሜሩን ሊያስመጡ ይችላሉ የሚል ድምዳሜ ላይ እንድደርስ እየገፋፉኝ ነው፡፡
በሀገራችን እስካሁን የተጫወቱና በመጫውት ላይ ያሉ በሁሉም ክለቦች ሲታዩ ያን ያህል ወሳን ተጫዋቾች አይደለሙ(እንደ ናይጀሪያዊነታቸው)ለምሳሌ በረጅም አመት ቆይታቸው ኮከብ ተጨዋች የተባለ አጥቂ ወይም አማካይ ሰምቼ አላውቅም ፡፡እሺ!! ይሄ እንኳን መራጮቹ ለሀገራቸው አድልተው ነው ሊባል ይችላል፡፡ ኮከብ ግብ አግቢ ግን በምርጫ አይደለም ብቃት ነው፡፡ያገባው ጎል ነው የሚወስነው፡፡አንድ ጊዜ ኮከብ ግብ አግቢ ተብሎ ውድድሩን የጨረሰ የውጭ ተጨዋች አላየሁም፡፡መጨረስ ብቻ ሳይሆን ፉክክር ውስጥ ገብቶ ኮከብ ባይሆንም እስከመጨረሻው የዘለቀ ተጫዋች አይታይም፡፡
እነዚህ የውጭ ተጨዋቾች አዲስአበባ ብቻ ሳይሆን ክልል ድረስ እየሄዱ ነው፡፡በሀገራችን እግር ኳስ ላይ ምንም ጠቀሜታ ከሌላቸው ምን ያደርጉልናል፡፡ እነርሱን በክለባችን አካተንም ሆነ ሳናካትት በክለብ በኢንተናሽናል ውድር ወጤት ከሌለ የነርሱ መኖር ምን ጠቀሜታ አለው?፡፡ብርቃችን ነው እንዴ? ከአንድ አመት በፊት ድሬዳዋ ከነማ ሶሰት ያህል የውጭ ተጫዋች ነበሩ፡፡ ድሬዳዋ አሸዋ ሜዳ ባፈራቸው ድንቅ ተጫዋቾች ከራሱ አልፎ ለአዲስ አበባ ክለቦች በርካታ ተጨዋች አፍርቷል፡፡እነአሰግድ ፤ቡሉ፤አሸናፊ፤ኬኔዲ፤ሙቅቢል፤ጌቱ…..አስደናቂ ነገር በመስራት ተመልካቹን በማስደሰት የግል ደጋፊ የነበራቸውና እነርሱን ብቻ ለማየት ወደ የሚመጡ ብዙ ነበሩ፡፡ድሬዎች ያንን ትተው ከናይጀሪያ ተጫዋች አሰመጡ፡፡ ቡድኑም ያኔ(የዛሬ ሁለት አመት) ድሬዳዋ ከነማ ሳይሆን ናይጀሪያ ከነማ ሊያስብለው ምን ቀረ? ድሬዳዋን አነሳሁ እንጅ አዳማ ከነማም ገብተዋል፡፡ የሚገርመው ከከነማ አልፈው ክፍለ ከተማ ድረስ ሄደዋል፡፡ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አንድ የውጭ ተጫዋች አስፈርሞ ነበር፡፡ከነማዎች በስራቸው ብዙ ቀበሌ አለ ፡፡ከነማ አላማው በየቀበሌው ያሉ ተጫዋቾችን አወዳድሮ ጥሩ የተባሉትን ወደ ዋናው ቡድን ማሳደግ ነው፡፡ነገር ግን ይሄ ቀርቶ ከነማዎች ከውጭ ሲያስመጡ ከቆሙለት አላማና ከአሰራሩም ወጡ ማለት ነው፡፡ወደ ዋናው ቡድን እንገባለን ያሉ የቀበሌ ተስፈኞች ከነማ ፊቱን ወደ ናይጀሪያ ሲያዞር ከታች ያሰፈሰፉት የስራ ዘርፋቸውን ለመቀየር ይገደዳሉ፡፡በተለይ አሁን ከመቸውም ጊዜ የውጭ ተጨዋቾች በብዛት ወደ ሀገራችን በመጉረፍ ክለብ እያጠያየቁ በመሆናቸው አጥለቅልቀውንየኛን ወጣቶች ቦታ እንዳያሳጡን ያሰጋል፡፡……….ባለፈው ግዜ ፌዴሬሽን በጠራው ውይይት የተነሳው አንዱ ጉዳይ የበረኞቻችን ብቃት ማነስ ነው ችግር ተብሎ የቀረበው፡፡ በክለቦች አብዛኛው የመሰለፍ እድል የሚያገኙት ከውጭ የመጡት በመሆኑ የኛዎቹ በረኞች የመሰለፍ እድሉን ስለማያገኘ ብቃታቸው ወርዷል ተባለ፡፡ እንደውም ክለቦች ከውጭ በረኛ እንዳያስመጡ የሚል መመሪያ ለማወጣት እየተዘጋጁ እንዳለ አውቃለሁ፡፡በርግጥ ይሄ ሲታይ እውነት ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን የኛዎቹ ቦታቸው በውጭ በረኞች በመያዙ አልነበረም ብሄራዊ ቡድን ችግር የተፈጠረው፡፡ እነዚህ የውጭ በረኞች በብዛት የመጡት ከስምንት አመት ወዲህ ነው፡፡ከዚያ በፊትም ቡድናችን ላይ በብዛት ግብ እየተቆጠረ የነበረና ችግር አለ ሲባል ነበር፡፡አሁንም በበረኞቻችም ላይ ያለው ችግር ከአጨዋወት ጋር የሚያያዝ እንጅ የውጭ በረኞች ቦታ ስለያዙ አይደለም፡፡እንደ አጠቃላይ ሲታይ የውጭ በረኛ አሰለፍንም አላሰለፍም ምንም ለውጥ አላመጣንም ፡፡
አሁን መነጋገር ያለብን የውጭ ተጫዋች በሀገራቸን እግር ኳስ ምን ለውጥ አመጣ የሚለው ነው…….በመንግስት በጀት የሚንቀሳቀሱ ክለቦች አላማቸው ስፖርቱን መደገፍና ቅድሚያ መስጥ ያለበት ለሀገሩ ዜጋ ነው፡፡ መንግስት ለሀገሬው ሰው ነው የፈቀደው፡፡በሀገራችን ገንዘብ የውጭ ሰው ቀጥረን የስራ አድል ለእነርሱ መስጠቱ ምን ይባላል፡፡ክለቦቻችን በኢንተርናሽናል ውጤት ቢኖራቸው የሀገርን ስም ስለሚያስጠራ ከውጭ አምጥቶ ማጫወቱ አይከፋም፡፡ ምንም ለውጥ ለሌለው ለምን ከውጭ እናስመጣለን? ያውም በዶላር ለምከፍል (አንዳንዶቹ በእኛ ብር ቢከፈላቸውም ብዙዎቹ በዶላር ነው)አሁኑኑ ይሄ ነገር በውይይት አንድ እልባት ማግኘት አለበት፡፡ደግሞም እኮ ዝውውሩ የአንድ ወገን ነው፡፡እኛ ሀገር በተለያየ ጊዜ ከ30 አስከ 40 የሚሆኑ ናይጀሪያውያን መጥተዋል፡፡ ነገር ግን አንድም ኢትዮጵያዊ ናይጀሪያ ክለብ የመጫወት ቀርቶ የሙከራ እድልም አላገኘም፡፡እኛ በእርግጥም ስለማንመጥን ወይም ለእግር ኳስ አስፈላጊ በሚባሉት ነገር ከናይጀሪያውያን ስለማንሻል ከእኛ አልወሰዱም ፡፡ሆኖም እኛም ስናመጣ እዚህ ካሉት የተሻሉ ሊሆኑ ይገባል፡፡ግን እስካሁን ወሳኝ አይደሉም፡፡እናም አሁን ቆም ብለን እናስብና እንወስን፡፡ስላልጠቀሙን ገንዘብና ከእኛ ልጆች የተወሰደውን የመሰለፍ ቦታ እናስመልስ፡፡ካለበለዚያ በየክለቡ በርካታ የውጭ ተጫዋች ይሰለፍና የኢትዮጵያ ፕሪመር ሊግ ሳይሆን‹‹የአፍሪካ ፕሪመር ሊግ››ወደሚያስብል ስያሜ ሊወስድ ይችላል፡
Health: ለራስ ምታት ህመም ፍቱን የሆኑ 4 የምግብና የመጠጥ ዓይነቶች
የውጪ ሀገራትን ያህል ባይሆንም በርካቶች ለትንሹም ለትልቁም ህመም ክኒን ወደ አፋቸው ወርወር ማድረግን ከለመዱ ቆይተዋል፡፡ መድሃኒቶች በአግባቡ ሲወሰዱ የመርዳት አቅማቸው ከፍተኛ የመሆኑን ያህል ከበሽታ አምጪዎች ጋር ሲላመዱ ደግሞ ጣጣቸው ብዙ ነው፡፡ የጎንዮሽ ጉዳቶችንም ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ ለህመሞቻችን ሁሉ ሁልጊዜ ክኒኖችን እንድንወስድም አይመከርም፡፡ ቀለል ያሉትን በአካባቢያዊ፣ አመጋገብ እና አጠቃላይ ጤናማ አኗኗር ብቻ ማስታገስ እና ማዳን እንደምንችል ባለሞያዎቹ ይጠቁማሉ፡፡ ለዛሬ ትኩረት ያደረግነው አንዴ ወይም ሌላ ጊዜ አብዛኞቻችን ገጥሞን በሚያውቀው ራስ ምታት ላይ ነው፡፡ መደበኛው ቀላል ራስ ምታት ወይም ጠንካራው ማይግሬይን ሊሆን ይችላል፡፡ ለዚህ ቀላል መፍትሄ አድርገው ሰዎች የሚወስዱት የራስ ምታት ክኒን ውጠው እንዲሻላቸው መጠበቅ ነው፡፡ ነገር ግን ከክኒኖች በተሻለ ያለጎንዮሽ ጉዳት በምግብና መጠጦች ራስምታቱን በፍጥነት ማስታገስና ማስቀረት እንደሚቻል በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ ባለሞያዎች እየገለፁ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ለመደበኛው ራስምታትና ማይግሬይን ፍቱን የተባሉት ምግቦችና መጠጦች የትኞቹ ይሆኑ?
ራስ ምታት የሚደጋግማት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዋ ማህሌት ግርማ ራስ ምታት ሲጀምራት ሰው ማት ራሱ ያስጠላታል፡፡ የለመደችውን ክኒን ካልዋጠች ፍፁም እረፍት አታገኝም፡፡ ክኒኑ ግን ሁልጊዜ በቅርብ ላይገኝ፣ የተፈገለውን ፈጣን ፈውስም ላይሰጣት ይችላል፡፡ ‹‹አንዳንዴ እናቴ ቡና ታፈላልኝና አንድ ስኒ ስወስድበት ቀለል ይላል፡፡ ምናልባትም ከክኒኑ ቡናው ፍቱን ሳይሆን አይቀርም›› ትላለች ማህሌት፡፡ የማህሌትን ሀሳብ አሁን አሁን የሚደረጉ ጥናቶችም ሳይንሳዊ ድጋፍ እየሰጡት ይገኛሉ፡፡ ቡና ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ተፈጥሯዊ ምግብና መጠጦች ከራስ ምታት ክኒኖች በተሻለ ለቀላሉ ራስ ምታትም ሆነ ከበድ ላለው ማይግሬይን ጥሩ የጎንዮሽ ጉዳት የሌላቸው መፍትሄዎች መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ምስጋና የመጣላቸው ቡና እና የተለያዩ ፍራፍሬዎች በውስጣቸው የያዟቸው ንጥረ ነገሮች ለዚህ አብቅተዋቸዋል፡፡
1ኛ. ቡና
ቡና በሳይንሱ ከፍተኛ ጥናትና ምርምር ከሚካሄድባቸው አነቃቂ መጠጦች አንዱ ነው፡፡ ለአንዳንዶች ቡና ፍቱን የራስ ምታት መድሃኒት ሲሆን ማይግሬይን ላለባቸው አንዳንድ ሰዎች ላይ በብዛት ሲወሰድ ማይግሬይኑን የሚቀሰቅስበት አጋጣሚ አለ፡፡ ሳይንሱ ሁሉንም የቡና ምስጢር ፈትቶ ባይጨርስም እስካሁን ባሉት ትናቶች መሰረት ግን ቡናን ፍቱን የራስ ምታት መድሃኒት አድርጎ መውሰድ ይቻላል፡፡ መጠኑን በልክ ማድረግ አብሮ ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ለከባዱ የራስ ምታት ማይግሬይን የሚታዘዙ ክኒኖች ውስጥ የቡና ዋና ንጥረ ነገር ካፌይን ይገኛል፡፡ ስለሆነም ቡና ለራስ ምታት በመፍትሄነት መቅረቡ አስደናቂ ነገር አይሆንም፡፡ ይሁንና መጠኑ በበዛ ቁጥር ራስ ምታትን ከማስታገስ ይልቅ ጭራሽ ሊቀሰቅሰው ይችላል፡፡ ማህሌት ‹‹ብዙ ጊዜ ይህን ሞክሬ ተሳክቶልኛል፡፡ ቡና መድሃኒቴ ነው›› ትላለች፡፡ ሳይንሱም ለዚህ ድጋፉን እየሰጠ ይገኛል፡፡ እጅግም ወፍራም ያልሆነ አንድ ወይም ሁለት ስኒ ቡና ከሁለት ክኒን የተሻለ ተፈጥሯዊ መድሃኒት ሆኖ ተገኝቷል፡፡
2ኛ. ሃብሃብ
ሃብሃብ ወይም በእንግሊዝኛው ወተርሜለን በውስጡ እጅግ ብዙ ፈሳሽ እና ማዕድናትን የያዘ ከፍራፍሬዎችም በትልቅነቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በተለይ ከአዲስ አበባ ወደ ናዝሬትና ሐዋሳ መስመር ሲሄዱ በመንገድ ዳር ተሸክመው ሲሸጡት እንመለከታለን፡፡ ሞክረውት እንደሆነ ባላውቅም በጉዞው ወቅት ለሚኖረው ሙቀት እና የውሃ ጥም ሁነኛ መፍትሄ ሆኖ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጥቅሙም ባሻገር ለራስ ምታት ፍቱን መድሃኒት መሆኑ በባለሙያዎች ተጠንቶ ተቀምጧል፡፡ የሪደርስ ዳይጀስት መጽሔት በቅርቡ ባሰፈረው ጽሑፍ ሃብሃብ ለራስምታት ፍቱን ያስባለው ከፍተኛ የውሃ እና ማዕድናት በተለይም ከፍተኛ የማግኒዚየም ማዕድን መጠኑ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ለራስምታት ከሚያጋልጡ ምክንያቶች አንዱ ድርቀት ወይም በሰውነት ውስጥ በቂ ፈሳሽ ያለመኖሩ ነው፡፡ ይህ ፍራፍሬ ደግሞ ይህን ችግር በደንብ ይፈታል፡፡ ከራስ ምታት ክኒን ይልቅ በቅርብ ሃብሃብ ከተገኘ በደቂቃዎች ውስጥ ከራስምታቱ እረፍትን ይሰጣል ብለው ባለሞያዎቹ ይናገራሉ፡፡
3ኛ. ዝንጅብል
ዝንጅብል ላይ የሚደረጉ ምርምሮች ገና በቅርቡ የተጀመሩ ቢሆንም በውስጡ የደም ቧንቧዎችን መቆጣት እና ህመም የሚቀንሱ መድሃኒቶች ውስጥ ካሉ ኬሚካሎች ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ተመራማሪዎች ማግኘት ችለዋል፡፡ በተለይ በከባድ የራስ ምታት ወቅት የደም ቧንቧዎችን መቆጣት በማስከተል ራስምታቱ እንዲቀሰቀስ የማድረግ ተግባር ያላቸውን ፕሮስታግላንዲን የሚሰኙ ንጥረ ቅመሞች መጠን በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ራስ መታቱን እንደሚያስታግስ የሪደርስ ዳይጀስት መጽሔት ይገልጣል፡፡ ራስ ምታቱን ሙሉ በሙሉ ባያቆመው እንኳ ከራስ ምታት ጋር የሚመጡ ደስ የማይሉ እንደ ማቅለሽለሽ አይነት ስሜቶችን በቶሎ ይቀንሳል፡፡ ለዚህ ሳይሆን አይቀርም ኢትዮጵያውያን ያለጥናቶቹ ውጤትም ቀድመው ለሆድ ህመም እና ማቅለሽለሽ ዝንጅብል አኝክበት ሲሉ የኖሩት!
4ኛ. ስፒናች
ትኩስ ስፒናች ጎመን ቅጠል በውስጡ የያዛቸው ቅመሞች ራስ ምታትን በማስታገስ ብቻ ሳይሆን የደም ግፊት መጠንን በመቀነስም በቀደመው ጊዜ ጥቅም እንደነበራቸው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ አትክልትና ፍራፍሬ በርካሽ ለሚገኝባቸው እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት ይህ ጥሩ ዜና ይመስላል፡፡ በውጪው ዓለም ስፒናችን አብስሎ ወይም በትኩሱ ከቲማቲም ጋር ከትፎ በመብላት ብቻ ሳይሆን ጨምቆ ከመጠጣትም ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ደግሞ ይህ ፍቱን አትክልት ለራስ ምታትም ፈጣን መፍትሄ ይሰጣል ብለዋል፡፡ ቢፈልጉ ጨምቀው ከሻይ ጋር አለዚም ባዶውን ወይም ትኩሱን ቅጠል ሰላጣ እንደሚያዘጋጁት አዘጋጅተው ቢመገቡት ከራስ መታቱ ፋታ እንዲያገኙ እንደሚረዳዎት የተደረጉ የመጀመሪያ ደረጃ ጥናቶች አመልክተዋል፡፡
ነገር ግን…
ለራስ ምታት ፍቱን ተብለው በጥናት ስር ያሉ በርካታ ተፈጥሯዊ ምግቦችና ፈሳሾች የሚገኙ ሲሆን በአንፃራዊነት ጥሩ ውጤት ካስገኙት መካከል ጥቂቶቹን አነሳሳን እንጂ ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፡ በዋነኛነት ባለሞያዎች የሚመክሩት ራስ ምታቱን ከማስታገስ ባለፈ ዋናውን የራስ ምታት ምንጭ ፈልጎ መፍትሄ መስጠቱ ላይ ነው፡፡ እንደ ድርቀት፣ ውጥረት፣ ከፍተኛ ድካም መሰል ከስራ እና ማህበራዊ ምክንያቶች መነሻነት የሚመጣውን ራስ ምታት ከክኒን ይልቅ በተፈጥሮ መፍትሄዎች ማስታገስ ቢመከርም ከሰውነት የውስጥ በሽታዎች ምክንያት የሚነሳን ራስ ምታት ግን ምንጩን ካልታከሙት ማስታገስ ይከብዳል፡፡ አልፎ አልፎ ለሚከሰት ራስ ምታት ያነሳሳናቸው አይነት የቤት ውስጥ ቀላል መፍትሄዎች ጥሩ ናቸው፡፡ ተደጋጋሚ ራስ ምታት ግን የባለሞያ እርዳታን ይሻልና ቸል አይበሉት ይላሉ ባለሞያዎቹ፡፡ ራስ ምታት ይደጋግመኛል ስትል ሃሳቧን በመግቢያችን ያጫወተችኝ ማህሌት ከዚህ ምክር ሳትመደብ ትቀራለች ሰላም!
ከዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ላይ የተወሰደ
መኢአድ እና አንድነት የውህደት ስምምነት ፊርማቸውን ፈጽመዋል።
በወያኔ ሰኔ አንድ ቀን 1997 የተጨፈጨፉት ወገኖቻችን በስምምነት ውቅት ታስበው ውለዋል።
የአንድነት የሂሳብ ክፍል ሰራተኛን ሲፈነክቱ አንድ የመኢአድ አመራር ጥርሱን በድንጋይ አውልቀውታል።
በዛሬው እለት ከጠዋቱ አራት ሰአት ጀምሮ አዲስ አበባ በሚገኘው የመኢአድ ጽ/ቤት ውስጥ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች ዲፕሎማቶች ጋዜጠኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ እና የአንድነት ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ (አንድነት) የውህደት ፊርማቸውን በደመቀ ስነስር ስት መፈራረማቸውን በስፍራው የተገኙ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
ውህደቱን ለማደናቀፍ የተወጠነው ሴራ በሁለት መልኩ ቢሆንም አንደኛው የቀድሞ መኢአድ አባላትን በማደራጀት አስርጎ ለማስገባት የተድረገው ሙከራ የመግቢያ ካርድ ባለመያዛቸው እንዲሁም ከድርጅት የተባረሩ መሆናችው ተነግሯቸው በሰላም የተሸኙ ሲሆን ሁለተኛ ብድን የመጀመርያዎቹን አለመሳካት ትክትሎ የተላከ የካድሬዎች ቡድን በር በመገንጠል ለመግባት ሲሞክር አንደኛው ሲያዝ ሌላው የቡድኑ አባላት ከቦታው ሮጠው ማምለጣቸውታውቋል፡፤
በአከባቢው የተመደቡ ፖሊሶች እንዲይዙት ቢጠየቁም ሄዳችሁ የክስ ፋይል ክፈቱና እንይዝላቹሃልን የሚል መልስ ቢሰጡም ማንነቱ እና አድራሽው የማይታወቅ ሰው እንዴት ይከሰሳል ወንጀል ሲሰራ እጅ ከፍንጅ መያዝ ሲገባቸው በንዝህላልነት እና በአደርባይነት መንፈሳቸው ከፍትህ ጋር አብረው ተቀብረዋል።
የአንድነት የሂሳብ ክፍል ሰራተኛን ሲፈነክቱ አንድ የመኢአድ አመራር ጥርሱን በድንጋይ አውልቀውታል።
በዛሬው እለት ከጠዋቱ አራት ሰአት ጀምሮ አዲስ አበባ በሚገኘው የመኢአድ ጽ/ቤት ውስጥ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች ዲፕሎማቶች ጋዜጠኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ እና የአንድነት ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ (አንድነት) የውህደት ፊርማቸውን በደመቀ ስነስር ስት መፈራረማቸውን በስፍራው የተገኙ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
ውህደቱን ለማደናቀፍ የተወጠነው ሴራ በሁለት መልኩ ቢሆንም አንደኛው የቀድሞ መኢአድ አባላትን በማደራጀት አስርጎ ለማስገባት የተድረገው ሙከራ የመግቢያ ካርድ ባለመያዛቸው እንዲሁም ከድርጅት የተባረሩ መሆናችው ተነግሯቸው በሰላም የተሸኙ ሲሆን ሁለተኛ ብድን የመጀመርያዎቹን አለመሳካት ትክትሎ የተላከ የካድሬዎች ቡድን በር በመገንጠል ለመግባት ሲሞክር አንደኛው ሲያዝ ሌላው የቡድኑ አባላት ከቦታው ሮጠው ማምለጣቸውታውቋል፡፤
በአከባቢው የተመደቡ ፖሊሶች እንዲይዙት ቢጠየቁም ሄዳችሁ የክስ ፋይል ክፈቱና እንይዝላቹሃልን የሚል መልስ ቢሰጡም ማንነቱ እና አድራሽው የማይታወቅ ሰው እንዴት ይከሰሳል ወንጀል ሲሰራ እጅ ከፍንጅ መያዝ ሲገባቸው በንዝህላልነት እና በአደርባይነት መንፈሳቸው ከፍትህ ጋር አብረው ተቀብረዋል።
በወቅቱ ብጥብጥ ለመፍጠር ሞክረው አልሳካ ያላችው ካድሬዎች ቢያመልጡም ከተያዘው አንደናው ኪስ ውስጥ የኢሕ አዲግ አባልነት ክፍያ ደረሰኝ እንዲሁም መታወቂያ የተገኘበት ሲሆን ለረብሻው የተላኩት ሶስቱን የትግርይ ብሄር ተወላጆች ሲሆኑ ፎቶግራፋቸው የተያዘ ሲሆን ድንጋይ በመወርውር አከባቢውን በጥብጠውታል። በፎቶግራፋቸው ይምታይውቸው አቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ መኪና ተደግፎ የቆምውና አመራሮቹን በድንጋይ የፈነከተው እንዲሁም መኢኣድ ግቢ ውስጥ የተያዘው ካድሬ ምስሎቻቸውን ይመልከቱ።
ውህደቱ ለማደናቀፍ ቢሞከርም ወያኔ ሳይሳካለን በሰላም መፈረሙ ታውቋል።
ሥለምን ወያኔን ከሥር መንቀል ያስፈልጋል? ሰማዕታት ሲታሰቡ (ከሥርጉተ ሥላሴ)
ሰማዕታት ሲታሰቡ።
ከሥርጉተ ሥላሴ 08.06.2014 (ሲወዘርላንድ – ዙሪክ)
ሰማዕታት ሲታሰቡ፤ ከቅርንጫፉ እ! ውጋት ነው። ከወገቡ እ! መጋኛ ነው። ከቋንጃው እ! ቁርጠት ነው። ከእጁ እ! ካንሰር ነው። ወያኔ ከሥረ መሰረቱ ነው መነቀል ያለበት። ስለምን የኢትዮጵያን ሉዕላዊ ህልውና አደጋ ላይ የጠላ ትውልድን ያሚያጠቃ ማነፌስቶ ስላለው። የወያኔ ማኒፌስቶ አንድን ዘር ብቻ መሰረት አድርጎ የተነሳ የጎጥ ማንፌስቶ ነው። ስለሆነም ነው ህልውናውን ለማቆዬት መሰል ተለጣፊ የጎጥ ድርጅቶችን ፈብርኮ የኢትዮጵያን ችግር ወስብስብ፣ ትብትብና ዳጥ ያደረገው።
በጎጥ ተመርቶ ለድል የበቃ፣ የህዝብን ጥቅም በእኩልነት ያስጠበቀ አንድም ሀገር ለናሙና ማቅረብ ፈጽሞ አይቻልም። የለም እንጂ – ቢኖርም እንኳን ለኢትዮጵያ እንደ ተፍጥሯዋ የራሷ አምክንዮዊ መንገድ ሊኖራት ይገባል። ልዕልት ኢትዮጵያ በኩረጃ ንድፍ ልትመራ የምትችል ሀገር አይደለችም። አሁን ኢትዮጵያ ሀገራችን ለዛውም በአንሳው ጎሳ ስብስብ ነው እዬተጎረደች ያለችው። የአንድ ጎጥ ድርጅት ማዕከሉ ጎጡ ብቻ ነው። ከዚህ የሚያልፍ ራዕይና አመለካከት የለውም። ሊኖረውም ፈጽሞ አይችልም። በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ሀገራዊ ሃብታት በሙሉ ይጠቀጠቃሉ – ይደፈጣጣሉ። ሃብታት ሲባል የሃብት ሃብት የሆነውን የሰለጠነውን የሰውን ልጅን ጨምሮ።
የሰውን ልጅ እኩልነት ማዕከል ያላደረገ አስተዳደር ደግሞ ትንፋሹ ጥፋት ነው። ጥፋቱ ምትክ የማይገኝለትን የህዝብና የሀገር ፍልሰት ምድረ – በዳነት ነው። ኢትዮጵያ ሀገራችን እንደ ቤተ ሙካራ ጥንቸል ሁሉ ተሞክሮባታል። የዐፄ ሥርዐት ለዘመናት፤ የሶሻሊስት ሥርዐት ለ17 ዐመታት፤ ቋንቋን መሰረት ባደረገ ፌድራዚም የጎጥ አስተዳደር ደግሞ ለ23 ዓመታት። ሁሎችም ግን የህዝብን መከፋት ያደመጡ ባለመሆናቸው ሁልጊዜም ከስሜን እስከ ደቡብ፣ ከደቡብ እስከ ምስራቅ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ያለውን የህዝብ ችግር መፍታት አልቻሉም። ትናንትም እንባ ዛሬም እንባ …. ኑራቸው ሆኗል። የእንባና የደም መኖር። ቀረ የሚባል አንዳችም የሙከራ ጣቢያ፤ ሆነ ሥልት የለም። የቀረው ነገር „ሀገር አለኝ“ ማለት አፋፍ ላይ ያለበት ሁኔታ ብቻ ነው። በዘመነ ወያኔ – ስለትናንት የሚናገሩ ማናቸውም ሃብታት ተቀጥቅጠዋል፤ በፋስ ተፈልጠዋል፤ በገጆሞ ተከታትፈዋል። አፈሩም – ተፈጥሮውም – አዬሩም አልቀረለት። የትኛውም መሥሪያ ቤት ለመግባት የመጀመሪያው መጠይቅ ብሄረሰብህ ከዬት ነው? ዜግነትን ዘቅዝቆ ያንጠለጠለ – ደም የሚያዘንብ የመገለ ዘመን። የሁሉም ነገር ልኬታ መስፈሪያ ወቄቱ ጎሳ …. ጠቀራ! እንዲያውም በተገላቢጦሽ ኢትዮጵያዊነትን ለማወጅ ወንጀል የሆነበት የተኮደኮደ ዘመን፤ ኩፍትርትር የነቀዘ የጨቀጨቅ ወቅት፤ እጅግ የተማረረና ያለቀሰ ዘመን። ህም!
ከእንግዲህ በኋላ ለሁሉ መዳህኒት የሆነ የአቅም ጥሪት መሰብሰብ ግድ ይላል። የአቅም ምንጩንም ሚስጥር ለማግኘት ተግቶ መባተል። ይህ የአቅም ጥሪት አነሳው ብዙኃኑን ወይንም ብዙኃኑ አናሳውን ሊጨቁኑ ወይንም ሊድጡ የማይችሉበት ወጥ ሥርዓት መፍጠር ነው – ሥርዬቱ። የትርጉም ሥራ ለኢትዮጵያ ጠፍ ፍልስፍና ይመስለኛል። አቅብቅበው የሚጠብቁ ባዕዳን ስሜቶች አሉ። ቅስማቸው የሚሰበረው ከራሳችን – ከውስጣችን መነሳት ስንችል ብቻ ይሆናል። ኢትዮጵያዊነት እኮ ከሰማዩ ፈጣሪ በስተቀር የትኛውም ፕ/ ሆነ ሳይንቲስት አንቦልቡሎ ወይንም ጠፍጥፎ ሊሠራው ከቶ የሚችል አይደለም። አንዷን ነገር ነጥለን አውጥተን የማን ነሽ? ማን ፈጠረሽ? መቼ ተገኘሽ? ብለን ብንመረምራት? ሃብትነቷ የሁላችንም መሆኑን በድፍረት አንገቷን ቀና አድርጋ በልበ ሙለነት ትነግረናለች።
ይህንን እርቀን – ከማንርቀው፤ ገፍተን – ከማንገፋው ወይ ካለባበሳችን፤ ወይ ከአመጋገባችን፤ ወይ ከጋብቻ ሥርዓታችን ብቻ አንዷን ዘለላ አንሱና ጠረጴዛ ላይ አስቀምጧት፤ እናንተም በክብር ወንበራችሁን ይዛችሁ ተቀመጡ። ተወያዩ! ጣዕሙ – ጠረኑ የሚውደው ባለቤትነቱ የእኔም – ያንችም – የእርሶዎም መሆኑን ነው። ሰውሰራሽን መጸሐፍ ማንበብ ይቻላል። መተርጎምም ይቻላል። በብዙ ጥልቅ ቅመም የተቀመረን – የነጠረ አንቱ የማንነት ተፈጥሮን ግን በእውነቱ አይቻልም። ይህንን ነው ወያኔ የተዳፈረው። ይህን ነው ደቁሶ አቃጥሎ አመድ ለማድረግ እዬታገለ ያለው። ይቻለዋልን? ወደ ራሳችን ተመልሰን ራሳችን እንጠይቅ። መልሱ አቅማችን ይለካል። መልሱ ትውልድን ታሪክን ሀገርን ይታደጋል ወይ ያከስላል። እራስን ማሸነፍ ድፍረትን ይጠይቃል። ራስን ሃቅ ማንተራስም ወኔን ይሻል። ራስን መሆን መቻልም ክህሎት ነው። እንደ እራስ ለመኖር መቁረጥም ቁሞ ያስኬዳል። አንገትን ቀና አድርጎ እኩል አፍሪካዊነትን ያጎናጽፋል፤ ልብን አደላድሎ ዓለምአቀፋዊነት ይሸልማል።
ስለሆነም ይህን መንገድ ለማግኘት በጎጥ ተደራጅቶ ፈጽሞ የማይታሰብ ነው። ወይንም በዕምነት ተደራጅቶም የማይታሰብ ነው። አንዲት ጠባብ ክፍል ውስጥ ዘግቶ መኖርን እሰቡት። ይህ ለኑሮ አፍ ያለው መቃብር ነው – እፍን። የታሪኳ፤ የባህሏ፤ የቀለሟ፤ የሥልጣኔዋ፤ የተፈጥሮ ሃብታቷ፤ የእምነት ውርርሷ፤ የመልካዕ – ምድራዊ አቀማመጧ፤ የህዝቦቿ ሥነ-ልቦናዊ አመለካከት – ውበቷ፤ ከጎረቤት ሀገሮች ጋር የነበራት የባህል – የወግ – የልማድ የመልካም ጉርብትና ውርርሷ፤ የተፈጥሮዋ ጥልቅነት ተመርምሮ መነሻውም መድረሻውም፤ ጎጠኝነትን አላይህም አለስማህም የሚል የእንቢተኝነት መንፈስ መፍጠር ያስፈልጋል። እኩልነትን ያደመጠ፤ ማስተዋልን የሰነቀ፤ ሰብዕዊነትን ማዕከል ያደረገ፤ ነፃነትን የኳለ ኢትዮጵያዊ ንድፍ – ነድፎ ተግባራዊ ማደረግ ሲቻል ያን ጊዜ የተበተነ ሃሳብ፣ የተጎዳ መንፈስ፣ የቆሰለ አካል፣ የጎሳቀለ ህሊና ፈውሱ ይገኝለታል። በእያንዳንዱ ዜጋ ያለውን የታሰረ ፍላጎት ሊፈታ የሚችለው በበዚህ መንፈስ ስንሰባሰብ ብቻ ይሆናል። የኮሰሰ ወይንም የኮሰመነ ስሜትንም ወደ እራስ አስጠግቶ ሃብት ማድረግ የሚቻለው ያሰረንን ትብትብ እራሳችን በራሳችን ይፍታህ ስንለው ብቻ ነው። በዚህ ዙሪያ እኮ ብዙ አንደበቶች ታስረው ነው የሚታዩት ….
ከሞት በላይ ምን የከፋ ነገር አለ?! በተለይ ለአንዲት እናት ሀገር፣ ሆነ ለወለደች እናት ልጇን ከማጣት የበለጠ ምን መራራ አሳንጋላ ነገር አለ?! እጅግ ከመከራዎች ሁሉ ጎምዛዛው የልጅን መከራ ቆሞ ማስተናገድ ነው፤ በወያኔ መርዝ ይህንን እንኳን በእኩልነት ለማስተናገድ ተፈጥሮን የጋጠ ገጠመኝ ነው ያለው። ስለምን? መከራን መጋራትን ሸሽተናዋል። እንዲያውም በአንዱ መካራ ሌላው ያላጋጣል፤ በሌላው ጥቃት አንዱ ይስለቃል። ይህ ዛሬን ያሳድራልን? ይህ ነገን በብሩህ ተስፋ ያጫልን? እእ! እርግጥ ነው ለዚህ ተፈጥሮን የዘለለ ሰብእናን የጨፈለቀ የግዴለሽነት የመንፈስ ሆነ ዬበረሃማናት ባዕዳዊ ስሜት ወያኔ ጸንፆ ኮትኩቶ ያሳደገው ነው። ይበል እያለም ግርማ ሞገስ እልብሶ አሽሞንሙኖ የዳረው የኳለው መርዝ መሆኑ ይረደኛል። ግን ነገር ግን ይህ ለእኛ መዳኛችን ሳይሆን መጥፊያችን ነው። ይህን አሸንፈን ጥሰን የወጣን ዕለት ትንሳኤ ነው። በስተቀር ግን ከዚህ የባሰና የከፋ የተጋጋጠ እንዲሁም የደማ – በበቀል እርር ኩምትር ያለ ጥንዙል ነገ ከፊት ለፊታችን ያፋጠናል። እጅግ የምናፍቃችሁ ወገኖቼ የሀገሬ ልጆች – እኛም በዚህ ዙሪያ ወስጥ ወይንም ውጪ መሆናችነን ከራሳችን በላይ ሌላ የፖሊስ መርማሪ የለምና እንፈትሽ ….
ወያኔ ሌባ ነው። በዙ ነገራችን ቀምቶናል። ከሥር እንዲነቀል የሚያስፈልግበትም መሰረታዊ እውነት ከዚህ ይመነጫል ወያኔ እኛን ዘርፎናል። ሀገራችንንም አዋርዷል። ልዑላዊነቷን አስደፍሯል። ሽጧታል። ለነገም ተክፍሎ የማያልቅ የዕዳ ባለቤት አድርጓታል። በማወዕለ ንዋይ ብቻ ሳይሆን በመንፈስም። የቤት ሥራችን የገዘፈና የገረዘዘም ነው። የዘረፈንን እኛነት ማስመሰለስ ደግሞ ከእያንዳንዱ በግል ከሁላችንም በጋራ የሚጠበቅ ግዴታ ነው። ለወያኔ ፓሊሲ አለመጠቃታችን ማወቅ የሚቻለው ፈተናውን ስናልፍ ብቻ ነው። ፈተናውን ለማለፍ እራስን ከጋለ ምጣድ ላይ አስቀምጦ እዬተገላበጡ መኮረጅ ነው፤ በትልቅ ብርት ድስት ውሃ አፍልተን ስሜታችን ጨምረን እንፈትሸው። ይመቻል? ይደላል? የሰርግ ሽርሽር ነውን? – በባሩድ በዬጊዜው የሚቃጠሉትን፤ በቤንዚን እዬነደዱ የሚያልቁትን፤ በስደት ሆነ በሀገር ውስጥ በሳንጃ የሚሸነሸኑትን፤ ከቀያቸው በግፍ የሚፈናቀሉትን ወገኖች የእኔ ነው አይደለም ብልን እራሳችን አፋጠን በምናገኘው ምላሽ ነገ እራሱን አምጦ ይወልዳል።
የትም ቦታ የሚቃጠለው ቤት፤ የትም ቦታ የሚፈሰው ደም፤ የትም ቦታ ለባዕድ ተቆርሶ የሚሰጠው መሬት፤ የትም ቦታ የሚገፋው ወገን የሥጋ ቁራጭ ነው። የደም ዘር ነው። ልንገፋው፣ አልሰማነም አላዬንም ብለን ልንሸሸው የምንችለው አይደለም። የትውልዱ አደራ እያነባ ይጠብቃል – እኛኑ፤ ግን መልሱን ፈርተነዋል። መድፈር ተስኖናል። ስለምን እኛ ያለነው በግል ጎጇችን እንጂ በአዳራሳችን ውስጥ አይደለምና።
የእንግዲህ ትግላችን በቅጣቱ ሰለባነት የሚጠዘጥዘን ስሜት አሻግረን ወያኔ ላይ በመጣል ብቻ ሳይሆን፤ ወያኔ በእኛ ላይ አቅም የሌለው መሆኑን በአይኑ እንዲይ ወስነና ቆርጠን ተግባር ላይ መገኘት ስንችል ብቻ ነው። ይህም ከተቀበርንበት አሸዋ ወጥተን ቁልጭ ባለ ግልጽ ፍላጎት መስመራችን ፈለግን ማግኘት ስንችል ብቻ ይሆናል – መፍትሄው። የእትዮጵያ ህዝብም ባልታዬው የጎሳ አስተዳደር አሳሩን ከፍሏል። በማያውቀው ዕይታ ፍዳውን ከፍሏል። ባልኖረበት ማንነቱ በመጤ ማንነት እንዲጫረስ እንዲፋጅ ተዶልቶበታል፤ ጨዋው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁለንትነውን ባከሰላው የጎሳ አስተዳደር መስመር ያለውን ጉዞ ሁሉ በቃኝ ማለት ይኖርበታል። ይበቃዋል። ከዚህ በላይ ምን የፈተና ጊዜ አለ? እሳቱ እኮ ሁሉንም አዳረሰ። ይህ ሁሉ ጦስ የጎጥ ማኒፌስቶ የአመጣው መርዝ ነው። ሌላ የጎጥ ዘመን ናፍቆተኞችንም ፍላጎታቸውን የሚያመክንበት መንሹ ያለው በእጁ ነው። ከዚህ ሌላ እራሳቸውን ሰውረው በብሄረሰብ ወይንም በእምነት ተቆርቋሪነት ሰም የደም ነጋዴዎችንም መርምሮና ፈልፍሎ ለመለዬት ማንዘርዘሪያም የሚስፈልግበት እጅግ ፈታኝ የጠቆረ ወቅት ላይ እንገኛለን። ከማን ጋር ነኝ? የእኔ ነውን? እንዳቀርበኩት አቅረቦኛልን? ቅንነቴን አክብሮታልን? ግልጽነቴን አድምጦታልን …. ንጹሑን ውስጤንስ ጨፍሮበታል ወይንስ ቦታ መድቦለታል? …. በሁሉም አቅጣጫ በጥንቃቄ ከቋሳ በጸዳ ሁኔታ መመርመር የተጋባ ይመስለኛል። ዝንቅ ህይውት ለማህበራዊ ኑሮ ሸጋ ነው፤ ቀለማምም ነው። ኑሮ ያመርበታል – ጌጣማ። ለፖለቲካ አብሮነት ግን ….. እህህህ!
እንደ እኔ እንደ ሥርጉተ ዕይታ – በጎጥ የሚያስብ ሰው ሰብዕዊነትን ለመተርጎም አቅም ያንሰዋል። በጎጥ የሚየስብ ሰው ርህርህናን ለመተርጎም አቅሙ የሟሟ ነው፤ በጎጥ የሚያመልክ ሰው አህጉራዊ ዕይታዎችን ለማስተናገድ ሽባ ነው። በጎጥ የሚይ ሰው ዓለም ዓቀፋዊነትን ለመቀበል ደረጃው አይፈቅድለትም። በጎጥ የሚተነፍስ ሰው ዘመኑ ከሸለማቸው ሥልጣኔ ጋር ለመኖር ዳፍንት ይዞታል። ሌላው ቀርቶ በጎጥ የሚየስብ ሰው ከጎረቤቱ ቀርቶ ከትዳር አጋሩና ከልጆቹ ጋር ተስማምቶ ለመኖር ሚያስችለው ተፈጥሮው ተፍቆበታል። በጎጥ ማሰብ ስለ ሰው ልጅ ኃላፊነት በማይሰማው የህልም አለም ግን ጉድጓድ ውስጥ መኖር ማለት ነው – እንደ እኔ። ይህ የእክሌ – ተከሌ በሽታ አይደለም። ተሸፍነን ከመጋረጃው በስተጀርባ የምናሽሞነሙነው ሰብዕናን አጋድሞ የሚያርድ የአብዛኞቻችን ገመናችን ነው። ዬቅርባችን ብቻ ነው ዓይናችን የሚፈቅደው። የአብዛኞቻን ችግር ይህ ነው። ከዚህ ጋር መፈታት መቻል ነው ስለ ነገ ራዕይ አለን ማለት የሚያስችለው ፍሬ ነገር። ቀን ደግሞ አድመኛ ነው። ትንሽ ነገር ብቅ ባደረገ ቁጥር ፈትለክ እያልን የአደባባይ ሲሳይ እንሆናለን። ተከድኖ የሚቀር ነገር የለም – አይኖርምም።
አውነት ለመናገር አብዛኞቹ ወጣቶች እኮ በጣም በልጠውናል። እጅግ ከእኛ በጣም ሩቅ ተጉዞው ነው ብሩሁን ቀን የሚያስቡት። ያስቸገርነው እኛ ቀደም ብለን የተፈጠረነው ነን። ይህም በመሆኑ እነሱ ያልበሉትን እዳ እንዲከፍሉ መደረጋቸው አልበቃ ብሎ የሚከፍሉትን መስዋእትንትም ዋጋ እያሳጣነው ነው። ያረመጠመጣል። እንደ እኔ ነገ በጎሳ በጎጥ ቲወሪ ፈጽሞ መታለም የለበትም ባይ ነኝ። ቲወሪው የሀገር ሉዕላዊነት፤ የህዝብን ክብርና ታሪክ የሚደረምስ አሲድ ነው። በጎሳ የተደራጀ አካል ጥላቻው በቀልን ያረገዘ ደም የጠማው ነው። በቀሉ ደግሞ አይደለም ነገን ዛሬን ክው አድርጎ የሚያድርቅ እጅግ ኋለቀር ኢሰብዕዊ መንገድ ነው። መማር – መሰልጠን – ማወቅ ማለት ከዚህ ኋላቀር አስተሳሰብ ጋር መፋታት ካልተቻለበት መማሩ ሥጦ ወይንም ውሃ ሲሄድበት የከረመ አለት ነው – ለእኔ።። መማር መብለጥ ነው፤ መቅደም ነው። መማር ለመልካም ነገሮች ሁሉ አብነትነት ነው። መማር ዓለምን አልፎ ፕላኔቶችን መመርምር ማለት ነው። መማር መሰልጠን ነው። ተፈጥሮን መተርጎም ማለት ነው። የሰው ልጅ ውበትን አድንቆ በውስጡ መኖር እንጂ የዚህ ተጻራሪ ሆኖ በአንድ እግር ተንጠልጥሎ መቆም መማር አይደለም። የጉም ሽንት ዓይነት ልበለው …. እራሱን መተርጎም የተሳነውም – ወይንም እራስን ለመተርጎም አስተርጎሚ ተበዳሪ እሳቤ - እንደ ሥርጉተ ማህይምነት በስንት እጁ ጣዕሙ -
እርግጥ ነው ወያኔ ከሥሩ እስኪነቀል ድረስ ተጓዳኝ የትግሉ ዘርፎች ይዘለሉ ማለት አይደለም። ወያኔ ያበቀላቸው እሾኾች ሁሉ በተገኘው አጋጣሚ መነቀል አለባቻው። የተሟላና የተደራጀ የህሊና ሥራም መሰራት አለበት። በግንባር ያሉ ፈተናዎችን ከእግር እግሩ እዬተከተሉ እዬተነተኑ እርቃኑን ማስቀርት – ማደረቅ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ዘላቂ ፍላጎትን ለማሟላት እራስን አሸንፎ በታቀደ፤ ህዝብን መሰረት ባደረገ፤ ነገ ከመምጣቱ በፊት ለምልሞ እንደሚጣ በሚያደረግ በተጠና መርኃ ግብር በቋሚነትና በተከታታይነት ሥራ ላይ መገኘት ያስፈልጋል።
ከውና – አንድ ነገር ወያኔ በለኮሰ ቁጥር ከዋናው ፍላጎት በመውጣት፤ ወይንም በደራሽ ችግሮች ላይ አትኩሮ ዋናውን ፍላጎት የሚሻውን ትኩረት ሆነ አቅም መንፈግ የተገባ አይደለም። ለአንድ መንገድ የተለያዩ ስልቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ግን ተቀናጅተው አንዱ የዘለለውን ወይንም ያላዬውን ሌላው ክፍቶቹን እዬሞላ እዬተደጋገፉ እኛኑ ሊውጠን ካሰፈሰፈው የጠላት ሁለገብ ሴራ እራስን ማዳን ዬቅድሚያ ትንፋሻችን ብቻ ሳይሆን መንፈሳችን ሊያርፍበት ዬሚገባው ዓይናማ አመክንዮ ሊሆን ይገባል እላለሁ። ለይደር የሚቀጠር ምንም ነገር የለም። አዳሩም ሞት ውሎም ሞት፤ አዳሩም ጥቃት ውሎም ጥቃት። አዳሩም ወርደት ውሎም ውርደት። ስለሆነም ሰቅስቆ ከሥሩ አረምን ማስወገድ፤ ማሳን አለስልሶ ቡቃዮዎችን ማስበል …. ከሁሉ በላይ የነፃነት ትግል ሰብዕዊነትን ይጠይቃል። ሰማዕታት ሲታሰቡም እራስን ከእሥር መፍታት በአጽህኖት አብዝቶ ይጠይቃል። በስተቀር የትውፊት ተደሞ ይታዘበናል። ። ልብ ያለው ሽብ። የኔዎች እኔ እንዲህ ታይቶኛል። ከክብሮቼ ጋር ውስጤን እንዲህ አውጥቼ ከመግለጽ በላይ ገነት የለም። አመሰግናችኋለሁ – በፍቅር። ኑሩልኝ።
እራሳችን የምናዳምጥበት አቅም አምላካችን ይስጠን። አሜን!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
Hiber Radio: በባህር ዳር ታጣቂው በተማሪዎች ላይ የግድያና የማቁሰል አደጋ አደረሰ * 62 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የመን ባህር ዳርቻ ሰጠሙ
የህብር ሬዲዮ ሰኔ 1 ቀን 2006 ፕሮግራም
<<...ኢትዮጵያ በመንታ መንገድ ላይ ትገኛለች ... የገዢውን ተንኮል ለማክሸፍ ተቃዋሚው ሀይል ህዝቡ ብዙ ስራ መስራት አለበት ...>> ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
የሰኔ አንድ 97 ሰማዕታት ሲታወሱ(ልዩ ዝግጅት)
ብራዚል እና የዓለም ዋንጫ ዋዜማ
በቬጋስ ሁለት ኩላሊቷን ላጣችው ኢትዮጵያዊት ኩላሊቷን በውጭ አገር ለማስቀረት ሃምሳ ሺህ ብር ተዋጣ (ለወገን ደራሽ ወገን ነው ልዩ ዝግጅት)
ውይይት
ዜናዎቻችን
62 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የመን ባህር ዳርቻ ሰጠሙ
130 ሊቢያ ላይ ሲታሰሩ 77 ከግብጽ ተባረሩ
አንድነትና መኢአድ የቅድመ ውህደት ፊርማቸውን አኖሩ
ውህደቱን ላማደናቀፍ ጽ/ቤቱን በድንጋይ ሲደበድቡ ከነበሩት የአገዛዙ ሰዎች አንዱ ማንነቱ ተጋለጠ
በባህር ዳር አንድ ታጣቂ በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ተኩስ ከፍቶ የግድያና የማቁሰል አደጋ አደረሰ
ደብረ ማርቆስ ላይ ለሰልፍ የወጣው ተቃዋሚ <<ነጻነት ነጻነት ቢሊሱማ ቢሊሱማ !>> ማለቱ ተገለጸ
አንድነት በአዳማና በደብረ ማርቆስ የጠራው ሰልፍ የተሳካ እንደነበር ተገለጸ
ሰማያዊ ፓርቲ የሰኔ አንድ ሰማዕታትን በ/ጽቤቱ ዘከረ
አሜሪካ ናይሮቢ የሚገኝ ኤምባሲዋን ከአልሸባብ ጥቃት ለመጠበቅ ልዩ ኮማንዶ ላከች
አዲስ አበባ፣ጅቡቲና ናይሮቢ የአልሸባብ ጥቃት ያሰጋቸዋል ተብሏል
ሌሎችም ዜናዎች አሉ
በአንድነት እና በመኢአድ መካከል የተደረገው ውህደት በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ (የሰሜን አሜሪካ የአንድነት የድጋፍ ማህበራት)
በአገራችን የሰፈነዉን አምባገነንነት በመቃወምና በአገራችን ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን፣ ላለፉት አያሌ አመታት ትእግስት አስጨራሽ ትግል ቢደረግም በተለያዩ ምክንያቶች የተፈለገው ዉጤት ሳይገኝ ቀርቷል፡፡
በየሰሜን አሜሪካ የአንድነት የድጋፍ ማህበራት የተሰጠውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
አባይን እነማን መቼ ይገድቡት?
የአንድነትና መኢአድ ስምምነት፣ ሊበረታታ የሚገባው መልካም ተግባር!
ሰኔ 2፣ 2006 (June 9, 2014)
የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ(ሸንጎ)፣ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ)ና አንድነት ለዴሚክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በትላንትናው ዕለት ለውህደት የሚያበቃ የመጀመሪያ ስምምነት በመፈራረማቸው የተሰማውን ታላቅ ደስታና አድናቆት ይገልጣል። ሙሉውን መግለጫን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
“ነጻነትነታችን እንደ ዕርዳታ እህል ከምዕራባውያን የሚለገሰን አይደለም!”
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የፖለቲካ መሪዎች ያስተላለፈው ግልጽ መልዕክት
የተወደዳችሁ በኢትዮጵያ የምትገኙ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤
በቅድሚያ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የአክብሮት ሰላምታ በማቅረብ በትግሉ መስክ የምትከፍሉትን መስዋዕትነት የሚያደንቅ መሆኑን ይገልጻል፡፡ በተለይ በአሁኑ ጊዜ የፖለቲካ ምህዳሩ እጅግ ጠብቦ የለም የሚባልበት ደረጃ በደረሰበት ወቅት በምታገኙት ስንጥቅ ሁሉ እየተጠቀማችሁ ለህዝባችሁ የብርሃን ጭላንጭል ስለምትፈነጥቁ አኢጋን ሥራችሁን ያደንቃል፤ ያከብራል፡፡ እኛ በሥራችሁ ስኬት የምንመኘው ለቆማችሁለት የፖለቲካ ዓላማ ብቻ ሳይሆን ከህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ራሳቸውን ነጻ ለማውጣት አቅቷቸው መፈናፈኛ ላጡትም የመወሰን ኃይል እንደምትሰጧቸው በማመን ነው፡፡
አገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ የበርካታዎች ጥያቄ “ህወሃት/ኢህአዴግን በምን ዓይነት የተሻለ አስተዳደር እንዴት መለወጥ ይቻላል የሚለው ነው?” ይህ ጥያቄ “እኛ ኢትዮጵያውያን የዘርና የጎሣ ትንንሽ አጥሮቻንን አፍርሰን ሁሉን አቀፍ ትግል ለማድረግ ተዘጋጅተናል ወይ?” ብለን ራሳችንን መልሰን አንድንጠይቅ የሚያደርገን ነው፡፡ እንዲሁም ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ በመስጠት ሁሉም ነጻ ሳይወጣ ራሳችንን ነጻ ለማውጣት እንችላለን ወይ? ብለንም እንድንጠይቅ የሚያስገድደን ነው፡፡ …
ሽንፈት ላይ እያተኮሩና የጠላትን ኃይለኛነት እየሰበኩ ድል አይገኝም፡፡ ልዩነትን እያራመዱ ኅብረትና አንድነት ተግባራዊ መሆን አይችልም፡፡ ለአገራዊ ዕርቅ እንሰራለን እያሉ በፓርቲ መካከል ከዚያም በታች በግለሰብ ደረጃ መተራረቅ ካልተቻለ ብሔራዊ ዕርቅ ከቀን ቅዠት አያልፍም፡፡ እያንዳንዳችሁ የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ፣ መኢአድ፣ አንድነት፣ ሰማያዊ፣ ኦህኮ፣ አረና፣ እና ሌሎች እጅግ በርካታ ፓርቲዎች የተቋቋማችሁትና ዓላማ ያደረጋችሁት ኢህአዴግን እየተቃወማችሁ ለመኖር እንዳልሆነ የፓርቲ ፕሮግራማችሁ ይመሰክራል፡፡ ወይም ዓላማችሁ የራሳችሁን የፓርቲ ምርጫ የማድረግና ፕሬዚዳንት (ሊቀመንበር)፣ ምክትል፣ ሥራ አስፈጻሚ፣ … በመምረጥ አዙሪት ውስጥ ራሳችሁን ላለማሽከርከር እንደሆነ ከማንም በላይ ራሳችሁ ታውቁታላችሁ፡፡ ከዚህ አንጻር በጥንቃቄና በብዙ ጥናት የተቀመጠው የፓርቲያችሁ ፕሮግራምና ዓላማ ለአገራችን አንዳች ለውጥ ሳያመጣ እንደዚሁ እንዳማረበት ቢቀመጥ ለሕዝብ የሚያመጣው ትርፍ ምንድርነው? እናንተንስ ለመቃወም ብቻ የምትሰሩ አያደርጋችሁምን? … (ሙሉውን መልዕክት ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
የሕዳሴ አብዮት አተገባበር! (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ )
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተከታታይ ባቀረብኳቸው ጽሑፎች ገዥው-ግንባር የመረጠው ስሁት መንገድ፣ ኢትዮጵያችንን ለሳልሳዊው አብዮት እያዘጋጃት መሆኑን ማውሳቴ ይታወሳል፡፡ ይህ የለወጥ መስመርም “የሕዳሴ አብዮት” የሚል ስያሜ ኖሮት፣ ሁሉን አሳታፊ ፖለቲካዊና ማሕበራዊ ንቅናቄ በመፍጠር አገሪቱን በዳግም
ውልደት ለማንፃት ብቸኛ አመራጭ የመሆኑ ጉዳይ በስነ-አመክንዮ ተሰናስሎ ቀርቦበት ነበር፡፡ በዚህ ተጠየቅ ደግሞ አብዮቱን ከዳር ለማድረስ ሊተገበሩ የሚችሉ (በሰላማዊ ትግል ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ) ስልቶች እና በመጀመሪያው የንቅናቄው ምዕራፍ ሥርዓቱ ለመመለስ ሊገደድባቸው የሚገቡ ጥያቄዎችን እንዳስሳለን፡፡
ለምን እንሞታለን?
የዓለም ታሪክ አምባ-ገነኖች እብደታቸውን እንዲተገብሩ የሚያስችላቸው የታጠቀው ኃይል (ጦር ሠራዊት፣ ደህንነት እና ፖሊስ) ስለመሆኑ አያሌ ማሳያዎችን ዘርዝሮ ያስረግጣል፡፡ የኢትዮጵያችን የቅርብ ጊዜ ታሪክንም ብንመለከት፣ የአፄ ኃይለስላሴ ጨቋኝ አስተዳደርን ግማሽ ክፍለ ዘመን አፋፍ ድረስ ተሸክመው የተጓዙት እነዚህ ኃይሎች መሆናቸው ጉዳዩን አምነን እንድንቀበል ያስገድደናል፡፡ የኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም በላኤ-ሰብ ዘመን በታሪክነት ተመዝግቦ ለመታወስ የቻለውም ይህንኑ ክፍል አጥብቆ በመያዙ መሆኑ የትላንት ክስተት ነው፡፡ ባለፉት ሁለት አስርታት ያስተናገድነው የኢህአዴግ ብልጣ ብልጥ አምባ-ገነን አስተዳደርም ከከፋፍለህ-ግዛ ስልቱ በተጨማሪ ዋና መሰረቱ ጠብ-መንጃ አንጋቹ አካል ለመሆኑ ይህ ትውልድ የአይን እማኝ ነው፡፡ አዲሱ የሕዳሴ አብዮታችንም በዚህ ኃይል ላይ ትኩረት ያደርግ ዘንድ የተገደደበት መግፍኤ ይኸው ነው፡፡
ከግፉአኑ (ከጭቁኖቹ) አብራክ የወጣው ጦር ሠራዊት ‹‹ተኩስ!?›› ተብሎ በታዘዘ ቁጥር ስለምን አምሳያው የመከራ ተቸንካሪ ላይ ሁሌ ጥይት እንደሚያዘንብ እጅግ ግራ አጋቢ ነው፡፡ እውን የህፃናትን ግንባር የሚበረቅሰው፣ እህት-ወንድሙን አነጣጥሮ የሚጥለው ሥርዓቱን ተቀብሎት፣ ትዕዛዙንም አምኖበት ነው ወይ? በጉልበትም ሆነ በሥነ-ምግባር ከሚልቃቸው ግለሰቦች የሚተላለፍለትን መመሪያ እየተገበረ ሰጥ-ለጥ ብሎ የሚገዛው የግል ጥቅም አመዝኖበት? ወይስ ለአለቆቹ የዘፈቀደ ተግባር ሎሌ ሆኖ? …የደህንነት መ/ቤቱ አባላትስ እንዲህ ታች ወርደውና አጎንብሰው የፓርቲ አገልጋይ የመሆናቸው ምስጢር ምን ይሆን? ከገዥው-ግንባር የተለየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸውን ድርጅቶች ቢሮ፣ አመራሩን እና ጋዜጠኞችን በመሰለል መጠመዳቸው የ‹‹እንጀራ›› ጉዳይ ብቻ ሆኖባቸው ነውን? ንፁሀንን በጠራራ ፀሀይ ሳይቀር አፍነው ለስቅየት አሳልፈው እንዲሰጡ የተገደዱበት መነሾስ ምንድር ነው? …የፖሊስ ሠራዊትስ የሥርዓቱ የማጥቂያ መሳሪያ በመሆን እንዲህ ማዕረጉን አቅልሎ ለሀፍረት የተዳረገበት ጉዳይ በማን እርግማን ይሆን? …እኮ ለምንድር ነው የእነርሱንም ጭምር ነፃነትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያውጅ ጥያቄ ባነሳን ቁጥር ደማችንን ደመ-ከልብ የሚያደርጉት?
እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ሰፊ ጥናት የሚጠይቅ መሆኑ ሳይዘነጋ፣ የንቃተ ህሊና ማነስ እና ነፍሰ-ገዳይን አወዳሹ ነባር ባሕላችን ከገፊ- ምክንያቶቹ መካከል ስለመጠቀሳቸው ለመናገር ግን የምሁራን ትንተና የሚያስፈልገው አይመስለኝም፡፡ ከዚህ አኳያም ሕዳሴን መሰረት የሚያደርገው አብዮታችን ከትኩረት ማዕከሉ ቀዳሚ አድርጎ መጠነ ሰፊ ቅስቀሳና የንቃት ሥራ በመስራት፣ ባለፉት ዘመናት የጭቆናው አስፈፃሚ ሆኖ በታሪክ ጥቁር መዝገብ የሰፈረውን ታጣቂ ኃይል፣ ወደ ተባባሪነት (ሕዝባዊነት) መለወጥ እንደሚኖርበት ተረድቶ መፍትሔ ካላበጀለት በታሪክ ፊት ከሥሉስ ውድቀቱ የሚታደገው አይኖርም፡፡ በአናቱም አብዮቱ ክብሩን ሊመልስለት እንጂ፣ ነቅንቆ ሊበትነው የተነሳሳ እንዳልሆነ ታጣቂ ኃይሉን ማሳመን የእኛ ዓብይ ተግባር ነው፡፡ እነርሱ አንድም በኑሮ ውድነት፣ ሁለትም ነገን በመስጋት ስር እንዲያድሩ ተቀይደው ነጻነታቸውና መብታቸው የተገፈፈ የመሆኑን እውነታ አስረግጦ ነግሮ ከሕዝብ ጎን በመቆም ሚናቸውን ይወጡ ዘንድ ማግባባት አብዮታዊ ግዴታ ለመሆኑ ነጋሪ አያሻም፡፡ ከለውጡ በኋላም ሠራዊቱ ከአገር አለኝታነቱ በዘለለ፣ ከአድሎአዊነትና ከእርስ በርስ (ከዘውጋዊ) ጥላቻ በፀዳ ፍትሓዊ አስተዳደር ተጠቃሚ የመሆኑን ጉዳይ ማሳመኑ በቀውጢው ሰዓት ወሳኝ ድጋፍ ለማግኘት ጠቃሚ ነው፡፡ የጥቂት ጀነራሎች የሙስና ወንጀልም፣ አቻ ባልደረቦቻቸውንም ሆነ መላ ሠራዊቱን የሚወክል አለመሆኑን ከዘለፋ በራቁ ጨዋ ቃላት መወትወት ጉልህ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ይህን ታላቅ ተልዕኮ ለማሳካት በተለይም የአዛዦቹም ሆነ የተራው ወታደር ቤተሰብ፣ ጎረቤት፣ ጓደኞች፣ ዘመድ-ወዳጅ ወገኖች ቀዳሚውን ኃላፊነት መሸከም ይጠበቅባቸዋል ብዬ አስባለሁ፡፡
የትግሉ ስልቶች…
‹‹የከፋ ጭቆና ቢኖርም ሥርዓቱን የተሸከሙት ብዙ ሰዎች ለረጅም ጊዜ ትብብር ከነፈጉት ጨቋኙ አገዛዝ ተዳክሞ በመጨረሻ መውደቁ አይቀርም›› የሚለው ጄን ሻርፕ፤ የትብብር መንፈግ ፅንሰ-ሀሳብን የሰላማዊ ተቃውሞው ዋነኛው የትግል ማዕከል አድርጎ ያቀርበዋል፡፡ ለዚህ ስልት መተግበር ሀሳብን የማሰራጫ መንገዶች ያስፈልጋሉ፡፡ በይፋ የማይታወቁ የትግሉ መሪዎች/ቡድኖች፣ ሐሳቡ ጨቋኞቹን ለመጣል በሚካሄደው መሬት አንቀጥቅ አብዮት ላይ እንዴት ከፍተኛ ሚና ሊኖረው እንደሚችል፣ ለማሕበረሰቡ ማስገንዘብ ይገባቸዋል፡፡ ይህን ማሕበረሰባዊ ጠንካራ መረዳት ለመፍጠርም፣ በራሪ ጽሑፎችን፣ ማሕበራዊ ድረ-ገፆችን፣ ሕብረ-ዜማዎችን፣ አጫጭር አነቃቂ ፊልሞችንና የሞባይል ስልክ መልዕክት መለዋወጫ ዘዴዎችን ጨምሮ የተለያዩ የምስልና የድምፅ ሚዲያዎችን ማመቻቸት (መዘርጋት) ይጠበቅባቸዋል፡፡ እነዚህ ከግብፅ እስከ ዩክሬን ተሞክረው የተሳኩ አማራጮችን በኢትዮጵያችንም ለመተግበር፣ በሚገባ መደራጀትና በኃላፊነት መስራት በእጅጉ አስፈላጊና ግዴታ የመሆኑ ጉዳይ አያከራክርም፡፡ እንዲሁም ከሕዝበ-ሙስሊሙ የ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› የተፈተነ እንቅስቃሴ ስኬታማ ተሞክሮዎችን ማጎልበትና ወደ ፖለቲካዊው ተቃውሞ መቀላቀል እንደሚቻል መዘንጋት የለበትም፡፡ የአደባባይ ተቃውሞ የሚፈቅደውን ሕገ-መንግስታዊ መብት በምልአት አንጠፍጥፎ መጠቀም ለሰላማዊ ትግሉ ዋነኛ መሰረት እንደሆነ አምኖ መቀበልም ሌላው መረሳት የሌለበት ጭብጥ ነው፡፡ እነዚህን ኩነቶች ለመተግበር የማይነጣጠሉትን እንቅስቃሴዎችም በሶስት በመክፈል በደምሳሳው እንመለከታቸዋለን፡፡
የአደባባይ እምቢተኛነት…
ዛሬ ላይ ስለመታገያ መንገዶቹ ብዙ ነጥቦችን ዘርዝሮ ማቅረቡ ላያስፈልግ እንደሚችል ይሰማኛል፡፡ ምክንያቱም በአገዛዝ ውስጥ የሚመረጡ የትግል ስልቶች በይፋ ከመቅረብ ይልቅ፣ በተቃውሞው አደረጃጀት ጥልቅ ዝግጅት እንደየአውዱ እየተመረጡ ቢተገበሩ የተሻለ ውጤታማ እንደሚሆኑ አምናለሁና፡፡ ሆኖም በዚህ መነሻነት ጥቂት ነጥቦችን ብቻ አንስቼ አልፋለሁ፡፡ በእነ ጄን ሻርፕ እና መሰል የትግሉ መምህራን ተደጋግሞ የሚጠቀሰው ‹‹የአደባባይ መቀመጥ›› የሚባለው ለሰላማዊው አመፅ ግንባር ቀደም ተደርጎ ይጠቀሳል፡፡ ለረዘሙ ቀናት/ሳምንታት አደባባዮችን ሞልቶ፣ ተጨባጭ ፖለቲካዊ ማሻሻያም ሆነ መሰረታዊ የሥልጣን ሽግግር እስኪደረግ ድረስ የመተካካት ስልት በተከተለ እና ግላዊ የዕለት ተዕለት የኑሮ መመሰቃቀሎችን ባገናዘበ (በእጅጉ ጉዳቶቹን በሚቀንስ) መልኩ በፈረቃ ፕሮግራም የሚደረግ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በትእምርትነትም የእስልምናን፣ የክርስትናን እና የአይሁድ እምነት ምልክቶችን ለመሰባሰቢነት በመጠቀም፣ በዋና ዋና ግልፅ ሕዝባዊ የመሰባሰቢያ ስፍራዎች ላይ የሰላም ድንኳኖችን መዘርጋት፣ የመማፀኛ ፊርማ ማሰባሰብ፣ በሕንፃዎች አናትና በግድግዳዎች ላይ ለውጥ የሚጠይቁ መፈክሮችንና ምስሎችን መለጠፍ፣ የመኪና ጥሩንባንና ሌሎች ከፍተኛ ድምፅ ሰጪ መሳሪያዎችን ያለማቋረጥ ማስጮኽ፣ የቤት ውስጥ መቀመጥ፣ የሥራ፣ የትምህርትና የረሃብ አድማዎችን መምታት፣ በማሕበራዊ ጉዳዮች ላይ ማደም፣ በየእምነት ተቋማቱ በጋራ ፀሎት ማድረግ… በዚሁ ስር የሚካተቱ ተግባራት ናቸው፡፡
በርግጥ ይህ ሁሉ ሲሆን የአገዛዙ መሪዎች ሕዝባዊ አብዮቱን በታጠቀው ኃይል ለመቀልበስ ሙከራ ማድረጋቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ይሁንና በዚህን ጊዜ ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር እሰጥ-ገባ ውስጥ ባለመግባት፣ ምንም አይነት አፀፌታዊ ግብረ-መልስ ባለመስጠት፣ በተንኳሽ የቁጣ ቃላት በመጎነታተል ለማበሳጨት ባለመሞከር፣ ተቀጣጣይና ስለት ነገሮችን ከአካባቢው በማራቅ ወይም በፍፁም ባለመያዝ… የተቀኙ ስልቶችን መከተል የሕዳሴ አብዮታችን መገለጫ ነውና፤ በዚሁ መንገድ መፅናት ግዴታ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ይህ አካሄድ በአንዳንድ አገራት እንደተስተዋለው አጋጣሚውን በመጠቀም አብዮቱን ለመጥለፍም ሆነ ሰርገው በመግባት ወደ ደም-አፋሳሽ ነውጥ ለመግፋት የሚሞክሩትን ለመከላከል ያስችላል፡፡
ሌላኛው ጭብጥ፣ የትግሉን ግብ በግልፅ ቋንቋ ካስቀመጡ በኋላ፣ የተለያዩ ሀገራትና ተቋማት ለሥርዓቱ የሚሰጡትን ድጋፍ እንዲያቋርጡ መወትወት ነው፡፡ ቀጥታዊዎቹን ሰብአዊ ዕርዳታዎች ሳይጨምር ኢህአዴግ በቀዳሚነት የባጀት ድጋፎቹን ከነዚህ ሀገራትና ተቋማት እንዳያገኝ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጫና የሚካሄድበትን ስልት መቅረፅ በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ አፈናውን ለማራዘም በርትተው በሚሰሩት የሥርዓቱ ፊት-አውራሪዎች ላይ፤ የጉዞ ማዕቀቦችን ጨምሮ ሌሎች ወደ ድርድሩ ማዕቀፍ እንዲመጡ የሚያስገድዱ ግላዊ ጫናዎች እንዲጠናከሩባቸው መጣር፣ ተጨማሪ የትግሉ መንገድ መሆን ይኖርበታል፡፡
አብዛኛዎቹ የአለማችን ጨካኝ አገዛዞችን ለታሪካዊ ሽንፈት የዳረገው ሌላው የመታገያ ስልት፣ አፋኝ ሕጎቻቸውን በግልጭ መጣስ መሆኑ በቀዳሚነት የሚወሳ ነው፡፡ በእርግጥ ይህን መሰል የአደባባይ የኢ-ፍትሓዊ ሕጎች ጥሰት ብዙ ዜጐችን ለእስር ይዳርጋል፡፡ ሆኖም የሰላማዊ አብዮት ውጤት መገለጫ፣ የዜጐች እስርን የመዳፈር ብርታት እንደሆነ ከመታወቁ አኳያ፣ ይህኛው አካሄድ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡ በእኛም ምድር እስርን የሚዳፈሩ ብርቱና ቆራጥ ጎበዛዝት በተበራከቱ ቁጥር፣ የተቃውሞ አድራጊዎች መጠን በሂደት እየጨመረ እንደሚመጣና ግንባሩም ስጋት አድሮበት ከአፈና እርምጃዎቹ መቆጠቡ ስለማይቀር፣ ለምንፈልገው ሥርዓታዊ ሽግግር አስገዳጅ ፈቃደኝነት ውስጥ ልንከተው እንደሚቻለን ማመን ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ይሁንና ውጥረቱ እየበረታ በሄደ ቁጥር ሥርዓቱ ተቃውሞውን ለማክሸፍ በብዛት ወደ እስር መላኩ አይቀሬ ቢሆንም ‹ስለኔ አታልቅሱ› እንዲል መጽሐፉ፣ በእርምጃው ሳይደናገጡ በአቋም በመፅናት ከአደባባዩ ሳያፈገፍጉ፣ ታሳሪዎቹን በጀግንነት እያወደሱ፣ ለእስር የሚዳርጉ ሕጎችን በመጣስ ጀግኖቹን መቀላቀልና ማጎሪያዎቹን አለቅጥ ማጨናነቅ አገዛዙን ለማሽመድመድ ጠቃሚነቱ በተግባር የተሞከረ ስልት መሆኑን ማስታወስ ያሻል፡፡ ነፃነቱን በነፃ ያገኘ ከቶም ቢሆን የለምና! በሰላም ጊዜ እንጂ በእንዲህ አይነቱ የንቅናቄ ወቅት እስር ቤት ቅንጣት ታህል የሚያስፍራ አለመሆኑን በልበ-ሕሊና ማሳደሩ ጠቃሚ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
ኢኮኖሚያዊ ትብብር መንፈግ
ስለትብብር መንፈስ መንፈግ ጉዳይ አስቀድመን ልናነሳው የሚገባን ኢኮኖሚ ተኮር የሆነውን የትግል ስልት ነው፡፡ ይህ ሥርዓት ለጭቆናው መሰረት ካደረጋቸው መካከል፣ በዝባዥ የምጣኔ-ሀብት ተቋማትን ማቋቋሙ አንዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እናም የኢኮኖሚ ትብብር መንፈግን ቀዳሚው የትግል አማራጫችን ብናደርገው የሕዳሴውን አብዮት ግቦች በአጭር ጊዜ ለማሳካት የማስቻሉ ዕድል የሰፋ ይሆናል፡፡ ለዚህም በዋናነት ልናተኩርባቸው የሚገቡ ሁለት ጉዳዮች አሉ፡፡ አንደኛው በማዕከላዊ መንግስቱ በቀጥታ እንደሚመሩና እንደሚደገፉ ከሚነገርላቸው ድርጅቶች፣ ምርቶችን ባለመግዛትና የምርት ሂደቱንም ከውስጥ በማጨናገፍ፣ እንዲዳከሙ ማድረግን የሚመለከት ነው፡፡ ረዥሙ ትግል ከባድ ዋጋ እንደሚጠይቀን ከተማመንን፣ ለህልውናችን የቀን ተቀን ኑሮ እጅግ ወሳኝ የሆኑትን የምርት ውጤቶች ከመንግስታዊ ተቋማቱ አለመግዛት፣ ሥርዓቱን ለማሽመድመድ ውጤታማ መሆኑ አይቀርም፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ፣ በእነዚህ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሠራተኞችንና መሀከለኛ የአመራሩን አባላት፣ የምርት ሂደቱን እንዲያስተጓጉሉ በማግባባት፣ ተቋማቱን በዝግመታዊ ሂደት አቅማቸውን ማድቀቅ አንዱ የትብብር መንፈግ አማራጭ ነው፡፡ ይህ መንገድ ከዛሬው ነባራዊ ሁኔታችን አንፃር የማይቻል ቢመስልም፤ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ‹‹በርግጥ! እንችላለን!!›› እንዲል፤ እኛም የነቃንለትን ሃሳብ ለመፈፀም የማንፈነቅለው ድንጋይ እንደማይኖር በተግባር ማሳየት ይጠበቅብናል፡፡ ደግሞም በቀላሉ በማይደበዝዝ መነቃቃት ካልታደስን መጪው ጊዜ አደገኛ ይሆን ዘንድ እንደመፍቀድ ይቆጥራልና፤ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ መንግስታዊ የንግድ ተቋማት ውስጥ ያሉትን ሠራተኞች በአንድ የግንኙነት መስመር በማስተሳሰር ሁኔታዎች ግድ ባሉ ቀን በተመሳሳይ ጊዜ በማንቀሳቀስ፣ ሥርዓቱን ክፉኛ ማዳካሙ ተግዳሮት የበዛ አለመሆኑ አከራካሪ አይመስለኝም፡፡ የኢኮኖሚ ትብብር መንፈግን የግድ የሚያደርገው ሌላው ጉዳይ፣ ግብር (ታክስ) ያለመክፈል ሕዝባዊ እምቢተኝነትንም ስለሚያጠቃልል ነው፡፡ የጭቆናው አገዛዝ ተጠናክሮ የቆመው በታክስ ሥርዓቱ ላይ መሆኑንም ሆነ ለሥልጣን ዕድሜ ማራዘሚያው መጥቀሙን በቅጡ መገንዘብ ከቻልን ታክስ ባለመክፈል፣ የቆመበትን መሰረት መቦርቦር የሚቻልበት ዕድል መኖሩን ማስታወስ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
ሁለተኛው ደግሞ የኢትዮጵያችን ነባራዊ ሀቅ፣ አብዮቶቹ ከተተገበረባቸው ሀገራት አንድ ለየት የሚል ገፅ ያለው ከመሆኑ ጋር የሚነሳ ነው፡፡ ይኸውም የገዢው ግንባር አባላት ተከፋፍለው በሀገሪቷ ኢኮኖሚ የአንበሳውን ድርሻ መያዛቸው ነው፡፡ ከማዕድን ቁፋሮ እስከ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ፤ ከፋይናንሺያል ተቋማት እስከ አልኮል ምርቶች ድረስ የተቆጣጠሩበትን መንገድ ማዳከም፤ ሕዝባዊ ጉዳት ሳይከተል ቀጥታ የሥርዓቱን የመጨቆኛ ምንጭ ማድረቁን ቀላል ያደርገዋል፡፡ በርግጥ አገዛዙ ከእነዚህ የፓርቲዎቹ ተቋማት ምንም አይነት አገልግሎት ላለመጠቀም የሚደረገውን አድማ በመመዝመዝ፣ ሂደቱን በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ላይ ያነጣጠረና ብሔሩን ሆን ተብሎ ለመጉዳት ታስቦ እንደተደረገ አስመስሎ የሚነዛውን መርዛም ፕሮፓጋንዳ ከወዲሁ ለማጨናገፍ፣ ከድርጅቶቹ ምርቶቹን ያለመግዛት ውሳኔ፣ ከማንኛውም ብሔር ጋር እንደማይገናኝ ማመን እና መተማመንን መፍጠር ቀዳሚው ተግባር መሆኑ ይኖርበታል፡፡ በ‹‹ኤፈርት›› የበለፀገች ትግራይ፣ በ‹‹ዲንሾ›› ያደገች ኦሮሚያ፣ አልያም በ‹‹ጥረት›› የተጠቀመ የአማራ ክልል አለመኖሩን፣ መጀመሪያውኑ ከልብ ተገንዝበን ከተንቀሳቀስን፣ ፓርቲ ተኮር ድርጅቶቹን ማግለል አስቸጋሪ አይሆንብንም፡፡ የተቃውሞ እንቅስቃሴው ቀጣይ ቅቡል መሪዎችም ይህን ጭብጥ ሕዝቡ ዘንድ በሚገባ ማስረፅ አንዱ ኃላፊነታቸው መሆኑን ሊዘነጉት አይገባም፡፡
የገዥው ፓርቲ አባላት…
ሶስተኛው ልንዘጋጅበት የሚገባው ጉዳይ፣ በመጀመሪያው የአብዮቱ እርከን ለዘብተኞቹን የግንባሩ አባላት በእንቅስቃሴው እንዲሳተፉ ማመቻቸት ነው፡፡ በተለይም ከድህረ-97ቱ የምርጫ ፖለቲካ ድቀት እና ይህን ተከትሎ በመጣው የተቃውሞ ስብስብ መዳከም የተነሳ፣ ‹ፓርቲውን በአዝጋሚው መንገድም ቢሆን እየገሩ መሄድ ይቻላል› በሚል የተቀላቀሉ እንዳሉ ይታወቃልና፤ እነዚህን ወንድሞችና እህቶች በሂደቱ ውስጥ ለማሳተፍ፣ የአብዮቱን መሪ ህልም እንዲያምኑበት ማድረጉ የግድ ነው፡፡ እነርሱን እያካተትን በተጓዝን መጠን፣ ሌሎቹም የፓርቲው አባላት ትግሉን በመቀላቀል፣ የራሳቸውን ጥያቄዎች አንግበው ሥርዓቱ ወደመነጋገር እንዲመጣ ያስችሉታል ብዬ አምናለሁ፡፡ የታቀደ አብዮት ስኬቶችን ስንመረምር እነዚህን መሰል ክስተቶችንም የለውጡ አካል ማድረጉን መረዳታችን አይቀርም፡፡ በነገራችን ላይ በመታደሳችን ዘመን ለቀደሙ ወንጀሎችም ሆነ ሀገራዊ ውድመቶች ሂሳብ ማወራረድን ታሳቢ ማድረግ ፍፁም አብዮቱን መጎተት ከመሆኑም በላይ፣ የታሪካችንን አስቀያሚ ገፅ በመድገም ቁልቁል መዝቀጥ እንደሆነ መተማመን ይኖርብናል፡፡ ግባችን ኢትዮጵያን እያደሱ ወደፊት ማራመድ እስከሆነ ዘንዳ፣ የተሻለ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን የመፍጠሪያው መንገድ ላይ ብቻ ማተኮር ብቸኛው መፍትሄ ነው፡፡ ያለፈው ዘመን ሰማዕታትን እየዘከርን፣ ለአጥፊዎቹ ምህረት እያደረግን በይቅርባይነትና በመቻቻል ላይ የምታብበውን ኢትዮጵያን መመስረት የሕዳሴው አብዮት ግብ ሊሆን ይገባል፡፡
የንቅናቄው ፊት መሪዎች
ይህን የለውጥ መንፈስ በፊት መሪነት ማስተባበር የሚችሉ ጠንካራ የሲቪክ ተቋማት በሀገሪቱ ያለመኖራቸው ጉዳይ፣ ለሂደቱ መፍጠን የግድ ሌላ አማራጭ እንድንፈልግ ያስገድደናል፡፡ በርግጥ አንዳንድ ወገኖች ለእንዲህ አይነቱ ጊዜ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መጠቀምን ይመክራሉ፡፡ ይህ ግን አደገኛና ያልተጠበቀ ክስረት ሊያስከትል የሚችል ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ድርጅቶቹ የየራሳቸው የተለያየ ዓላማ አንግበው የሚታገሉ በመሆኑ ከተሳታፊነት አልፈው በመሪነት መምጣታቸው፣ ሁነቱን ከሁሉን አሳታፊነት ወደ ቡድንነት፤ ከዲሞክራሲያዊ ሽግግር ወደ ሥልጣን ነጠቃነት (መፈንቅለ መንግስት) የመቀየር አደገኛ ክስተት ውስጥ ሊያስገባው ይችላል፡፡ ይህ አካሄድ በሌሎች ሀገራት ለከሸፉ አብዮቶች በማሳያነት መጠቀሱንም ታሳቢ በማድረግ፣ ለእኛ ችግር መፍትሔውን አዲስ (ከዚህ ቀደም ያልተሞከረ) አማራጭን ከራሳችን ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር መፈለግ ላይ ማተኮሩ ይበጃል፡፡ በግሌም ይህንን ታላቅ ሀገራዊ ግዴታ ለመሸከም የተሻሉ ናቸው ብዬ የማስበው ዩንቨርስቲዎቻችንን ነው፡፡ በመላ ሀገሪቱ በተመሳሳይ ወቅት መጀመር የሚኖርበትን የሕዳሴ አብዮት፣ ሁሉም መንግስታዊ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙበትን ከተሞች ጨምሮ አጎራባች አካባቢዎችን ለማስተባበር ኃላፊነት የሚወስዱበት መንገድን ማማቻቸቱ የሚሳካበትን ስልት ከወዲሁ መቀየስ የሚቻል ይመስለኛል፡፡
ርግጥ ነው በዛሬው እውነታ ላይ ሆነን በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የገዢው ፓርቲ የፖለቲካ መናኸሪያ የመሆናቸውን ነገር ግምት ውስጥ አስገብተን ስናምሰለስለው፣ ሁነቶቹ አልጋ በአልጋ ሊሆኑ እንደማይችሉ ከማንም የተሰወረ አይሆንም፡፡ ግና፣ በየተቋማቱ የየትኛውም ፓርቲ አባል ያልሆኑ ለውጥ አራማጅ መምህራንና ተማሪዎች በራስ ተነሳሽነት በመሰባሰብ የማስተባበሩን ኃላፊነት ተረክበው ከፊት መስመር እንዲሰለፉ የማንቃትና ማብቃት ሥራ ቢሰራ፣ አንድም እዚህ ግባ የሚባል ተግዳሮት ባለመኖሩ ሂደቱን ለማፋጠን ይጠቅማል፤ ሁለትም ከንቅናቄው ስፋት አኳያ ለከበደ መስዋዕትነት የመዳረጉ አጋጣሚ እጅግ የጠበበ በመሆኑ ግንባር ቀደም ተሰላፊ ደፋሮችን ማግኘት አዳጋች አያደርገውም፡፡ ይህ ዕቅድ የሚሳካ ከሆነ ደግሞ ዩኒቨርስቲዎቹ በዕኩል ውክልና የጋራ ማዕከል (አዲስ አበባ ለዚህ አመቺ ሊሆን ይችላል) አቋቁመው አብዮቱን በሀገርና ሕዝብ ጥቅም አስተሳስረው መምራት እንደሚኖርባቸው እንደማይዘነጉት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
የአብዮቱ የመጀመሪያ ጥያቄዎች
ሕዝባዊ ንቅናቄው በሚገባ ተጠናክሮ ከቀጠለ በኋላ መንግስት እጁን ተጠምዝዞ እንዲተገብራቸው መነሳት ያለባቸው ቀዳሚ ጥያቄዎች (ለለውጡ መደላድል የሚሆኑት) የሚከተሉት ቢሆኑ መልካም ነው፡- በመላ ሀገሪቱ ባሉ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ የፖለቲካ፣ የሕሊና እና የሀይማኖት እስረኞችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት፤ በውጪ ሀገር ያሉ ተቃዋሚ ድርጅቶች፣ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች እና የመብት ተሟጋቾች ያለልዩነት ወደ ሀገር ቤት ገብተው በነፃ እንዲንቀሳቀሱ መፍቀድ፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የወጡ አፋኝ ሕጎችን መሰረዝ፤ በሀገሪቱ የመንግስት ምሥረታ ላይ የአፈና መዋቅር ሆኖ የሚያገለግለውን ምርጫ ቦርድ አፍርሶ አብዛሃ ኢትዮጵያዊን ሊያሳምን በሚችል ገፅ እንደገና ማዋቀር፤ ለዴሞክራሲ ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ ተቋማትን ነፃ ማድረግ፤ የብዙሃን (የመንግስት) ሚዲያን እውነተኛ የሕዝብ ልሳን የሚሆኑበትን አሰራር መዘርጋት፤ መከላከያ ሰራዊቱ፣ የደህንነት ሰራተኛው እና የፖሊስ አባላት በነቢብ ሳይሆን በገቢር ተጠሪነታቸውን ለሕገ-መንግስቱ ማድረግ… ሲሆን፤ እነዚህ ሁኔታዎች ከተሟሉ በኋላ በ2007 ዓ.ም. የሚካሄደውን ምርጫ ለተጨማሪ አንድ አመት በማራዘም፤ ለሁሉም ተወዳዳሪዎች (ለነባሮቹም ሆነ አዲስ ለሚደራጁት) መድረኩን ክፍት አድርጐ የሕዳሴውን አብዮት ለውጥ መተግበር ይቻላል ብዬ አምናለሁ፡፡ እዚህ ጋ መዘንጋት የሌለበት ዋነኛው ጉዳይ አብዮቱ በራሱ በገዥው-ፓርቲ ውስጥ ያሉ በፖለቲካ ቀኖናዊነት ያልተጠለፉና ሀገራዊ ለውጥ ፈላጊ የአመራር አባላት ‹የኢህአዴግ መንግስት ወይም ሞት!› የሚሉ ግትር ጓዶቻቸውን አግልለው፣ ይህንን ኃላፊነት እንዲወስዱ ጫና ማድረግ ላይ የሚያተኩር እንጂ፤ በደፈናው ግንባሩን በጠላትነት ፈርጆ የሚያሳድድ አለመሆኑን ግንዛቤ መውስድ ያስፈልጋል፡፡ የሕዳሴው አብዮታችን የ‹ጊሎትን› ማሽን የማይታጠቅና ልጆቹንም የማይበላ፤ በአጥፍቶ መጥፋት ጨዋታ ሕግ የማይመራ መሆኑን ማስረገጥ ቀዳሚው ተግባር ይሆናል፡፡ ጎን ለጎንም የለውጡን (የጥያቄዎቹን) መፈፀም የሚከታተል ከንቅናቄው አስተባባሪዎች፣ ከንግዱ ማሕበረሰብ፣ ከኃይማኖት ተቋማት፣ ከሲቪክ ማሕበራት፣ ከልሂቃኑ እና ከሀገር ሽማግሌዎች መካከል በተወጣጡ ግለሰቦች የጋራ ምክር ቤት አዋቅሮ ቁጥጥር ማድረግ የሚቻልበትን አሰራር መቀየሱ ሌላኛው ጠቃሚ ክዋኔ ነው፡፡ ይህ መንገድ በድህረ-ኢህአዴጓ ኢትዮጵያችን ፖለቲካዊና ማሕበራዊ ምስቅልቅሎሽ ቦታ እንዳይኖራቸው የመታደግ አቅምንም ለመገንባት ማስቻሉ መዘንጋት የለበትም፡፡
የተባረከችዋ ቀን መቼ ትሆን?
ይህን መሰል የለውጥ ጥያቄ ማቅረቡ ሥርዓቱ ከሃያ ሶስት ዓመት በላይ ከመቆየቱ አኳያ የተቻኮለ እንደማይሆን አምናለሁና፤ ከላይ ከተጠቀሱት ዋና ዋና አብዮታዊ ጉዳዮች አንፃር፤ እንዲሁም በአንድ ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ ‹‹ልጄ ፋኖ ተሰማራ እንድትል አልፈልግም›› እንዳለው ሁሉ፤ ህወሓት የታሪካችን የመጨረሻው ‹‹ነፃ አውጪ›› ድርጅት ይሆን ዘንድ የሚታወጅበት ዕለትን ከወዲሁ መወሰኑ ላይ ከተስማማን፣ የ2007ቱ ወርሃ መስከረም በሁለት ጉዳዮች ቢመረጥ የተሻለ ይመስለኛል፡፡ የመጀመሪያው በቀጣዩ ዓመት የሚደረገውን አምስተኛ ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫን የማራዘሙ አስፈላጊነት ከሕዝባዊ ጥያቄው መካከል ግንባር-ቀደም በመሆኑ ለአገዛዙ በቂ የጥሞና ጊዜ መስጠት የማስቻሉ ጠቀሜታ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የአዲስ ዓመት ጅማሮ ከመሆኑ አኳያ ባሕላዊም ሆነ ስነ-ልቦናዊ መነቃቃት የመፍጠር አቅሙ የራሱ በጎ አበርክቶ ይኖረዋል ተብሎ ስለሚታሰብ ነው፡፡
ከሞላ ጎደል ለሶስት ሳምንታት ያህል የተነጋገርንባቸው እነዚህ ታላላቅ አጀንዳዎች እውን ይሆኑ ዘንድ ቀጠሮውን በልቦናችን ይዘን፣ ራስን በውስጥ ዝግጅት ማሰናዳቱ ለነገ የማይተው የቤት ስራችን መሆኑንም ጨምሮ መረዳት ያሻል፤ በዚህም የሕዳሴያችን ንቅናቄ እንደ ቀዳሚዎቹ ሁለት አብዮቶች አዲስ መዘዝ፣ ሳይሆን አዲስ ተስፋ እንዲያመጣ እናስችላለን ብዬ አስባለሁ፡፡ በመጨረሻም ያቺ ትንሳኤ አብሳሪ ዕለት በኢትዮጵያችን ምድር ከቶም ቢሆን አቻ የላትምና፣ በአያሌ ናፍቆት ስለመጠበቋ ዛሬ ላይ እንዲህ መመስከሩ ከምኞት የተሻገረ መሆኑን አስረግጬ ብናገር ማጋነን አይሆንም፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
“እኛና አብዮቱ” በሚል ርእስ በተፃፈው መፅሓፍ ላይ የቀረበ የግል አስተያየት
የመፅሃፉ ደራሲ፤ ሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ
አስተያየትና ማስተካከያ ሃሳብ አቅራቢ፤ ላቀው አለሙ (ዶ/ር)
አጠቃላይ አስተያየት፣
ሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ መፅሃፍ ማሳተማቸውን እንደሰማሁ መፅሃፋቸውን አግኝቼ ለማንበብ በጉጉት እጠባበቅ ነበር። ዘግይቶም ቢሆን በአንድ ወዳጄ አማካኝነት መፅሃፉ እጄ ገብቶ አነበብኩት። ደራሲው በዚያ የአብዮት ዘመን ስለተከናወኑ ተግባሮች አጠር ባለና በጥሩ አቀራረብ ፅፈዋል። በሂደቱ ውስጥ ላለፍነውም ሆነ ለአዲሱ ትውልድ ጠቃሚ መረ
ጃዎችን መፅሃፉ አካቶ ይዞዋል። የሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ አስተዋፅኦ የሚደነቅ እና እርሳቸውም ላደረጉት ጥረት ሊመሰገኑ ይገባል።
አነሳሴ በሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ መፅሓፍ ላይ ሁለንተናዊ ግምገማና ትችት ለማቅረብ አይደለም። መፅሃፉን ካነበብኩ በሁዋላ በአዕምሮዬ ውስጥ ሲጉላሉ ለነበሩ ጥቂት ጉዳዬች አጭር አስተያየት እና ማስተካከያ ለማቅረብ ነው። በቅድሚያ በወቅቱ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች በተለይም መኢሶንና ኢህአፓ ስለኢትዮጵያ ህብረተሰብ ከነበራቸው የተለያየ ግምገማ በመነሳት ያከናወኑዋቸው ተግባሮቶች እና በዚያም ሳቢያ ስለደረሱ ጥፋቶች ከመፅሓፉ ያገኘሁትን ግንዛቤ አሰፍራለሁ። በሁለተኛ ደረጃ ታላቅ ወንድሜ ሻምበል አለማየሁ ሃይሌን በተመለከተ ደራሲው ከፃፉት ሃሳቦች አንዳንዶቹ የተሳሳቱ በመሆናቸው እውነተኛውን ነገር ካለኝ መረጃ በመነሳት ላብራራ እሞክራለው ።
በቅድመ አብዮት ኢትዮጵያ ጠንካራ የኢኮኖሚ መሰረት አልነበራም። በድርጅታዊ አቅም እና በልምድ የዳበሩ የፖለቲካ ድርጅቶችም በህብረተሰቡ መካከል አልነበሩም። የንጉሳዊ አገዛዙ እያቆጠቆጠ ከነበረው ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ወደሁዋላ ቀርቶ ስለነበር የህብረተሰቡን የለውጥ ፍላጎት እና ጥያቄዎች ለማስተናገድ አቅም አልነበረውም። ስለሆነም ሀገር አቀፍ ህዝባዊ ብሶት ወደ ብሄራዊ የአመፅ እንቅስቃሴ ወይም አብዮት ተሸጋገረ። በአብዮታዊ እንቅስቃሴው ውስጥ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ የነበሩ ቢሆንም የተሻለ የድርጅት አቅም የነበረው የወታደሩ ክፍል የህዝቡን ብሶት እየተከተለ ፀረ መንግስት እርምጃዎችን መውሰድ ጀመረ። በሂደትም ንጉሳዊ ስርአቱን አስወግዶ ስልጣኑን ተቆጣጠረ ። ይህ የወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታ የፈጠረውና የህብረተሰቡ ግፊት የታከለበት አስገዳጅ ክስተት እንደነበር ከመፅሃፉ ይዘት መረዳት ይቻላል።
ንጉሳዊ ስርአቱ እንደተወገደ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች በህብረተሰቡ መካከል እንቅስቃሴ ማካሄድ ጀመሩ። ሆኖም በመካከላቸው በነበረው የአላማና የአካሄድ ልዩነቶች እንዲሁም ስልጣን በያዘው ወታደራዊ ደርግ ላይ በያዙት አቋም እርስ በርስ በመጠላለፍ ተግባር እና የፖለቲካ ሽኩቻ ውስጥ ገቡ። በዚህም ተግባራቸው የትውልድ ጥፋትና ክስተት እንዲደርስ አድርገዋል። ለጋ እድሜ የነበራቸው እነዚህ የፖለቲካ ድርግቶች ከሌሎች ሃገሮች የቃረሙትን ንድፈ ሃሳብ በድፍኑ በማንበልበል ከእገሪቱ እውነታና ከህዝቡ የግንዛቤ ደረጃ በመራቅና በስሜት እየተገፉ የስልጣን ፍላጎት ላይ ብቻ በማተኮራቸው በወቅቱ ለደረሱት ጥፋቶች የበኩላቸውን አስተዋፆ አድርገዋል።
ወታደራዊ ደርግ በጊዜው ህዝቡ ላነሳቸው መሰረታዊ የኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ተገቢና ስር ነቀል እርምጃዎችን ወስዷል። የኢኮኖሚ ማሻሻያዎቹ (reforms) ላአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ጠቀሜታ የነበራቸውና ለተከታታይ እድገትም ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ ነበሩ። ይሁን እንጂ ለሁለንተናዊና ቀጣይነት ላለው የኢኮኖሚና ማህበራዊ እድገት ወሳኝ የሆነው የፖለቲካ ጥያቄ ተገቢውን መፍትሄ ሳያገኝ በመቆየቱ ችግሮች ይበልጥ ተወሳሰቡ፤ ያልተፈለገ ጥፋትም በሃገሪቷ ላይ ደረሰ። ተራማጅ ነኝ ይል የነበረው የምሁሩ ክፍል ብስለት ማጣትና ለስልጣን መስገብገብ እንዲሁም ለደርግ ከነበራቸው ንቀት የተነሳ ለፖቲካዊ ችግሮች መወሳሰብ አስተዋፆ ማድረጋቸውን የሻ/ል ፍቅሬን መፅሃፍ በጥንቃቄ ላነበበ ሁሉ በግልፅ ይታያል። ከነዚህም በተጨማሪ የቅርብና የሩቅ ሃገሮች ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነትና ግፊት ሌላው የችግሩ ምንጭ እንደነበር የግል ግንዛቤና አስተያየት አለኝ።
የደርግ አባላት በተለይም ሊ/መንበር መንግስቱ ኃ/ማሪያም ብልሃት በጎደለው የኢትዮጵያዊነትና የሃገር ፍቅር ስሜት በመገፋፋት የፖለቲካውን ውስብስብ ችግሮች በሃይል ብቻ ለመፍታት በመሞከራቸው በትውልዱ ላይ ከፍተኛ መከራና ጥፋት እንዲደርስ አድርገዋል። አልፎ ተርፎም ሃገራችን ዛሬ ለምትገኝበት የችግር ማጥ ዳርገዋት ሄደዋል።
ሻምበል ፍቅረስላሴ ከላይ ያነሳኋቸውንና ሌሎች የወቅቱን አበይት ክስተቶች በመፅሃፋቸው ውስጥ ለመዳሰስ ሞክረዋል። አያሌ ቁምነገሮችና ጠቃሚ መርጃዎች በመፅሃፉ ውስጥ ተካተው ስለቀረቡ ጠቀሜታቸው የጎላ ነው ብዬ አምናለው። ሻምበል ፍቅረስላሴ በቅርበት የሚያውቋቸው ሌሎች ቀሪ ጉዳዬች ቢኖሩም በመፅሃፉ ውስጥ የቀረቡ ማብራሪያዎች በአብዛኛው ሚዛናዊ ናቸው ብዬ እገምታለው።
ሻምበል አለማየሁ ኃይሌን በተመለከተ፣
ሻምበል አለማየሁ ከኦሮሞና ከከፋ ብሄረሰቦች እንደሚወለዱ ሻምበል ፍቅረስላሴ በመፅሓፋቸው ጠቅሰዋል። ይህ ፈፅሞ ትክክል ያልሆነ መረጃ ነው። ምንም እንኳ የወላጆቻችን የትውልድ ሃረግ ከኦሮሞ፤ ከጉራጌና ከአማራ ብሄረሰቦች የሚመዘዝ ቢሆንም የወላጆቻችንና የእኛ ስብዕና በአብዛኛው ኦሮሞነትን መነሻ አድርጎ በኢትዮጵአዊነት ስነልቦና የተገነባ ነው። ስለዚህ ሻምበል አለማየሁ ብሄረሰቡ ኦሮሞ እንጂ ከከፋ ብሄረሰብ ጋር በቀጥታ የሚያገኛኘው ነገር የለም። ይሁን እንጂ እንደአብዛኛው ኢትይጵያዊ በጋብቻ የተነሳ በከፊል ከከፋ፤ ከሲዳማና ከሃዲያ ብሄረሰቦች የሚወለዱ የሩቅ ዘመዶች እንዳሉን መካድ አይቻልም።
ሻምበል ፍቅረስላሴ በደርግ ውስጥ በእነ አለማየሁ ወገንና በሊ/መንበር መንግስቱ ደጋፊዎች መካከል ስለነበረው ቅራኔና በመጨረሻም ስለተወሰደው እርምጃ (የመንግስት ግልበጣ) ባብራሩት የመፅሃፋቸው ክፍል ውስጥ፣ ሻምበል አለማየሁ የኢህአፓ አባል እንደነበር፤ የታገለውም ኢህአፓን ስልጣን ላይ ለማውጣት እንደነበር ፅፈዋል (ገፅ 310)። እውነቱ ግን በፍፁም ከዚህ የተለየ እንደነበር እኔ በቅርብ የማውቀው ጉዳይ ነው። በመጀመሪያ ነገር አለማየሁ የኢህአፓ አባል አልነበረም። ይህንኑ ሃቅም የኢህአፓ አንዱ መሪ የነበሩት አቶ ክፍሉ ታደሰ በመፅሃፋቸው ውስጥ ገልፀዋል (ያ ትውልድ)። የአለማየሁ እምነትና ፍላጎት ደርግ ለኢትዮጵያ ህዝብ በይፋ ቃል ገብቶ ስልጣንን በጊዚያዊነት የያዘ ኃይል እንደመሆኑ፤ የአብዮቱ ወገን የሆኑና ኃላፊነት የሚሰማቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ተባብረውና የጋራ ግንባር ፈጥረው በህዝብ ይሁንታ ስልጣኑን እንዲረከቡ ይፈልግ ነበር። የደርግ አባላትን በተመለከተ ምርጫ በማድረግ ወደ ፈለጉት ድርጅት ውስጥ ተጠቃለው ትግሉን መቀጠል ይችላሉ ወይም ሌሎች የግል ምርጫዎችን መውሰድ ይችላሉ ብሎ ያምን ነበር። ደርግ በመንግስትነት ሚናው ለሁሉም ፓርቲዎች መድረኩን በእኩልት ማመቻቸት አለበት እንጂ አንዱን ድርጅት አገልግሎ፣ ሌላውን ማቅረብ የለበትም የሚል አቋም ነበረው። ለአብዮቱ የቆሙትን ኃይሎች ሁሉ በእኩል አይን በማየት፤ በማዕከልነት ማስተባበርና እኩል ድጋፍ መስጠት የደርግ ኃላፊነት መሆን አለበት ይል ነበር።
ለዚህም ሲባል እያንዳንዱ የፖለቲካ ድርጅት በተለይም መኢሶንና ኢህአፓ አቋማቸውን አስተካክለው የአብዮቱን አላማ፤ የሀገሪቱን ጥቅምና የህዝቡን ፍላጎት እንዲከተሉ አለማየሁ በግሉ ይወተውታቸው እንደነበር በቅርብ አውቃለሁ። የመኢሶን መሪዎችን “እኛን ብቻ ማለትን መተው አለባችሁ።” ኢህአፓዎችን ደግሞ “የግለሰቦችን ግድያና ንብረት ማውደምን አቁሙ።” በማለት ሁለቱን ወገኖች በግልፅ እየወቀሰ እንዲቀራረቡ ጥረት ያደርግ ነበር፡፡ መኢሶንና ኢህአፓ እንዲሁም ሌሎች ህቡዕ የፖለቲካ ድርጅቶች በማሌ እርዮተ አለም ዙርያ ተሰባስበው በመሰረታዊ የፖለቲካና ሃገራዊ አጀንዳዎች ላይ ተግባብተው በጋራ ግንባር ስር እንዲሰባሰቡና እንዲሰሩ አለማየሁ ብርቱ ፍላጎት ነበረው፡ መኢሶንና ኢህአፓ በብቸኝነት ስልጣን ላይ ለመውጣት ሲሉ እርስ በርስ ለመጠላለፍ ያደርጉ የነበረውን እሩጫና በሴራ የታጀበ የትግል ሥልታቸውን አለማየሁ ፈፅሞ አይደግፍም ነበር። የእርስ በርስ ሽኩቻና የመጠላለፍ አካሄድ በአገሪቷ ላይ የግለሰብ አባገነንነትን ያስከትላል፣ በዘላቂነት ደግሞ አገራችንንና ህዝቡን ይጎዳል ብሎ ያምን ነበር። ከዚህ ውጪ አለማየሁ በግሉ የስልጣን ፍላጎት ወይም ኢህአፓን በብቸኝነት ለስልጣን ለማብቃት አቅዶ አልተቀሳቀሰም። የእርሱ ጥረት እያሰጋ በመምጣት ላይ የነበረውን የግለሰብ አባገነንነት ወይም ብቸኛ የስልጣን ማዕከልነት ለማስወገድ ብሄራዊ እርቅና የፖለቲካ ትብብር ተፈጥሮ ለኢትዮጵያና ለህዝቡ ጥቅም በጋራ የሚሰራበት ሁኔታ መፍጠር ነበር። ዳሩ ምን ያደርጋል የፖለቲካ ድርጅቶች ያነገቡት ድብቅ ፍላጎትና ይህንኑ ለማሳካት የቀየሱት የሴራ መንገድ ሻምበል አለማየሁን እና ሌሎች አያሌ ሀቀኛ ምርጥ የኢትዮጵያ ልጆችን ላልተጠበቀ መስዋዕትነት ዳርጓል፡፡
ሻምበል አለማየሁ አላማውን ለደርግ ከማቅረቡ አስቀድሞ እርሱና ጓደኞቹ ስለ ህቡዕ የፖለቲካ ፓርቲዎች አቋምና አሰራር ጥናትና ግምገማ አድርገዋል፡፡ ሻምበል ፍቅረስላሴ ቢያንስ የዝያን ታሪካዊ ፅሁፍ ይዘትና ዓላማ ለምን በመጽሓፋቸው ውስጥ ለመጥቀስ እንዳልፈለጉ አስገርሞኛል፡፡ ጥናታዊ ፅሁፉ በደርግ አባላት መካከል ለተፈጠረው የሐሳብ መለያየትና ደርግ በአዲስ መልክ ተዋቅሮ የስልጣን ክፍፍል እንዲደረግ የረዳ በ45 ገፅ የተጠናከረ መሰረታዊ ሰነድ ነበር፡፡ ሻምበል ፍቅረስላሴ እንደፃፉት (ገፅ 305)፣ ሰነዱ በኢሕአፓ ተዘጋጅቶ ለነአለማየሁ የተሰጠ ሳይሆን ለዚሁ ተብሎ በተቋቋሙ ኮሚቴዎች የተጠና እና ረቂቁ በአለማየሁ ተስተካክሎ በደርግ ስብሰባ ላይ ለወይይት እንዲቀርብ የተደረገ ነበር፡፡ በተቋቋሙት የጥናት ኮሚቴዎች ውስጥ በህቡዕ የሚሰሩ የፖለቲካ ድርጅቶች አባላት በአባልነት ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል::
እስከማቀው ድረስ ወንድሜ ሻምበል አለማየሁ በባህሪው ግልፅ፣ ነገሮችን በቀና መንገድ የሚመለከት፣ ለግል ጥቅም የማይጓጓ፤ ወዳጆቹን ከልብ የሚወድና የሚያምን፣ ላገሩ ከፍተኛ ፍቅር የነበረው ወጣት መኰንን ነበር፡፡ የነገሮችን አመጣጥ ፈጥኖና አስቀድሞ የመረዳት ችሎታ የነበረው ቢሆንም የፖለቲካ ብልጠት፣ አሻጥር እና ሴራ ግን በፍፁም አያውቅም፡፡ አለማየሁ ሁሉ ነገሩ ፊት ለፊትና በቀጥታ ነበር፡፡ በኔ ግምት ይህ የግልፅነት እና የየዋህነት ባህሪው እንዲሁም በወቅቱ በደርግ ውስጥ ለጊዜው ታይቶ የነበረው የዲሞክራሲ ጭላንጭል አለማየሁን እምነት ስላሳደረበት በፍርሃትና በአድር ባይነት ከመጓዝ ለአመነበት ዓላማ መስዋእትነትን ከፍሎ ማለፉን እንዲመርጥ አድርጎታል፡፡ ይህንን ሁኔታ እኔና ወንድሞቼ እንዲሁም ሌሎች የአለማየሁ የቅርብ ወዳጆች እስከዛሬ በታላቅ ቁጭት የምናስታውሰው ጉዳይ ነው።
ጥር 26 ቀን 1969 የደርግ አባላት ስብሰባ ላይ እያሉ መፈንቅለ መንግስት ተደርጎ አለማየሁንና ሌሎችን ለሞት ያበቃው እርምጃ ታስቦበትና በከፍተኛ ሚስጥር በጥንቃቄ እንደተዘጋጀ የሚታወቅ ነው፡፡ ለዚህ ዝግጅት መጀመር ፋና ወጊ የነበሩት ሻምበል ፍረስላሴ ወግደረስ እንደነበሩ፣ የሰውና የጽሁፍ ማስረጃዎች አሉ። የደርግ አባል የነበረው ወታደር እሸቱ አለሙ የፃፈው መፅሓፍ የሚጠቀስ ነው። እነ አለማየሁ በበኩላቸው ከሊቀመንበር መንግስቱ ሊደርስባቸው የሚችለው አደጋ እውን ከመሆኑ በፊት ቀድመው እርምጃ ለመውሰድ ሻምበል ፍቅረስላሴ እንደፃፉት (ገፅ 316)፣ በእርግጥ ዝግጅት ነበራቸው። በዚህ መሰረት ሊቀመንበር መንግስቱ ጥር 28 ቀን 1969 በቁጥጥር ስር ውለው፣ አድርሰዋል ለተባሉት ጥፋቶች ሁሉ በህግ እንዲጠየቁ ቀደም ሲል ወስነው ነበር፡፡ ይህ የተወሰነው በብርጋዴር ጄኔራል ተፈሪ በንቲ ሰብሳቢነት የተወሰኑ የደርግ አባላት በተገኙበት ስብሰባ ሲሆን፣ ሻምበል ፍቅረስላሴም የዚህ ስብሰባ ተሳታፊና የውሳኔው ተካፋይ ነበሩ፡፡ ታድያ ጥር 28 ቀን ሊታሰሩ የነበሩት ሊቀመንበር መንግስቱ እንዴት ጥቂት ቀናት አስቀድሞ ጥር 26 ቀን 1969 መፈንቅለ መንግስት ለማካሄድ እድሉን አገኙ? እርሶን በቀጥታ የሚመለከተው የዘማቾች በጀት ጉዳይ ከመደበኛ የቅዳሜ ስብሰባ በፊት ሀሙስ እለት በአስቸኳይ አጀንዳ ተይዞ ለውይይት እንዲቀርብ አለማየሁ በዋና ፀሀፊነቱ እንዴት አምኖ ሊቀበል ቻለ? ማንስ አነጋግሮ አሳመነው? ይህ ጉዳይ በቀጥታ እርሶን የሚመለከት ስለሆነ እባክዎትን ሻምበል ፍቅረስላሴ ሃቁን አፍረጥርጠው ይንገሩን፡፡ ከንግዲህ በኋላ ያለው ነገር ሁሉ ፋይዳው ለትውልድና ለታሪክ ስለሆነ የተደበቁ እውነታዎች በሙሉ ይፋ መሆን አለባቸው የሚል ብርቱ እምነት አለኝ፡፡
ሻምበል አለማየሁ ከፖለቲካ ልዩነት ባሻገር በሊቀመንበር መንግስቱ ላይ የግል ጥላቻና ቂም አልነበረውም፡፡ በህይወታቸውም ላይ ጥፋት ለማድረስ አላማና ሃሳብም አልነበረውም፡፡ ሊቀመንበር መንግስቱ ሊያጠፉት እንዳሰቡ ካወቀ በኋላ እንኳን “መንግስቱን እንምታው” እያሉ ለሚጎተጉቱት ወገኖች እንኳን “ይህ ትክክል አይደለም፣ እኔ በነፍስ ማጥፋት አላምንም፣ ጥፋት ካለ ታይቶ በህግ መጠየቅ አለበት እንጂ ለምን ይገደላል?” እያለ ይመልስላቸው ነበር፡፡ ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆነና “ለምሳ ሲያስቡን ለቁርስ አደረግናቸው” ተብሎ በአደባባይ የተፎከረው በሃቅ ላይ ያልተመሰረተ የሴረኝነት እና የጭካኔ መግለጫ ከመሆን ውጪ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡
ሻምበል አለማየሁ ሊቀመንበር መንግስቱ ላይ የነበረው ቅሬታ ስልጣን በብቸኝነት ጠቅልሎ ለመያዝ የነበራቸው ከፍተኛ ፍላጎትና ጭካኔ የተሞላው ተግባራቸው ብቻ ነበር፡፡ እንደዚያም ሆኖ ሊቀመንበሩ በነበራቸው የማስተባበር ችሎታ ዘወትር አድናቆቱን ይገልፅ እንደ ነበር አውቃለሁ፡፡
በመጨረሻ ሻምበል ፍቅረስላሴ ሻምበል አለማየሁ ታታሪና ጎበዝ ሰራተኛ እንደነበር አያሌ ስራዎችን በብቃት በማከናወን ደርግ ስርአትን ተከትሎ እንዲሰራ ከፍተኛ ጥረትና አስተዋፅኦ ማድረጉን በመፅሐፋቸው ውስጥ ጠቃቅሰዋል፡፡ በቅንነት ላቀረቡት የምስክርነት ቃልም በበኩሌ ላመሰግን እፈልጋለሁ፡፡
መልካም ጊዜ ለሁላችን !
ላቀው አለሙ (ዶ/ር)
Email ፡ lakewalemu@Yahoo.com
Mobile፡ 202 492 0674
የሻምበል አለማየሁን የግል የህይወት ታሪክ በዝርዝር ለማጀጋጀት ስለታሰበ በተለያየ መልኩ ለመተባበር የምትፈልጉ ሁሉ በአድራሻዬ ልታገኙኝ ትችላላችሁ፡፡
በዕውነት ፕሮፌሰር መሥፍን እንደሚሉት ፣የትግራይ ሕዝብ በወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ አይደለም?
(ተክሌ የሻው፣የግል አስተያዬት) ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም”የወያኔ ጥላቻ ፍሬ» በሚል ርዕስ የጻፉትና በተለያዩ ድረ-ገጾች የወጣው ነው። ፕሮፌሰሩ በዚህ ፍሑፋቸው፣ የትግራይ ሕዝብ በዘመነ ወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ አይደለም፤ ተጠቃሚዎቹ “ጥቂቶች ናቸው» ብለው የደመደሙት ሀሳብ ዕውነት አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ክህደት በመሆኑ፣ ትግሬዎች በዘመነ የወያኔ አገዛዝ እንዴት ተጠቃሚዎች እንደሆኑ ተጨባች ነቃሾችን በማቅረብ የፕሮፌሰር መሥፍንን ሀሳብ መሞገት [ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]
በሰበታ ባለቤቱን ዓይኗን ረግጦ በሰንጢ ሆዷን የቀደደው ግለሰብ ተያዘ
ባለቤቱን በተለያዩ የሰውነት ክፍሏ ላይ በአሠቃቂ ሁኔታ በስለት ወግቶ የመግደል ሙከራ ያደረገው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋሉን የሰበታ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ማስታወቁን የኢትዮጵያ ፖሊስ ሚድያ አታወቀ፡፡
(zehabesha.com)
በሰበታ የክፍለ ከተማ ሁለት ፖሊስ ጣቢያ የወንጀልና የትራፊክ አደጋ መርማሪ ም/ሣጅን ስለሺ በቀለ እንደገለፁት ተጠርጣሪው ተበዳይን ወ/ሮ ጫልቱ ጎበናን ግንቦት 13 ቀን 2006 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ በሰበታ ከተማ 05 ቀበሌ ልዩ ቦታው ዲማ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ‹‹ብር እንድትሰጪኝ እፈልጋለሁ›› በሚል እና በመጠጥ ኃይል ተገፋፍቶ እንቢተኝነቷን ሰበብ በማድረግ በተኛችበት አንገቷን ከአነቃት በኋላ ስትፈራገጥ ቀኝ አይኗን ረግጧት በያዘው ሰንጢ ሆዷን ከላይ እስከ ታች በመቅደድ እንዲሁም በክንዷ እና ትከሻዋ ላይ በተመሣሣይ ሁኔታ በመውጋት ትንፋሿ አለመኖሩን አረጋግጦ ከጣላት በኋላ እጁን ለፖሊስ ሰጥቷል፡፡
እንደ ም/ሣጅን ስለሺ ገለፃ ተበዳይዋ ጉዳቱ እንደደረሰባት ቤተሰቦቿ ወዲያውኑ ሆስፒታል የወሰዷት ሲሆን ከብዙ የህክምና ጥረት በኋላ ሕይወቷ ሊተርፍ ችሏል፡፡ ተከሳሹ በአሁን ሰዓት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራው እየተጣራበት መሆኑንም ም/ሣጅን ስለሺ አያይዘው ገልፀዋል፡፡
ም/ሳጅን ስለሺ በመጨረሻ በአስተላለፉት መልዕክት ተከሳሽ ከተበዳይ ጋር በትዳር አለም የቆዩት ለሁለት ወር ብቻ ነበር ስለዚህ በመሃላቸው መጠናናትና መተዋወቅ የለም በዚህም ለእንዲህ ዓይነቱ አደጋ ተጋልጠዋል ሲሉ መርማሪው መግለጻቸውን የፖሊስ ሚዲያ መረጃ ያመለክታል።
Sport: ስለ ዓለም ዋንጫ አንዳንድ ነጥቦች ….
ከአድማስ ራድዮ የተገኘ
• የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ የተደረገው በጁላይ 13 ፣ 1930 ኡራጓይ ውስጥ ሲሆን በመጀመሪያው ጨዋታ ፈረንሳይ ሜክሲኮን 4-1 አሸነፈች ..
• የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ አገሮች 13 ነበሩ፣ አሜሪካ አንዷ ነበረች።
• የዓለም ዋንጫን በብዛት በማሸነፍ የደቡብ አሜሪካና የአውሮፓ አገሮች ይመራሉ፣ ደቡብ አሜሪካውያን 9 ጊዜ፣ አውሮፓውያን 10 ጊዜ እስካሁን አሸንፈዋል። ከነዚህ ውጭ ዋንጫ የወሰደ አህጉር እስካሁን የለም።
• የዓለም ዋንጫን ብራዚል 5 ጊዜ፣ ጣሊያን 4 ጊዜ፣ ም ዕራብ ጀርመን 3 ጊዜ፣ ኡሯጓይ 2 ጊዜ፣ አርጀንቲና 2 ጊዜ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና ስፔን አንዳንድ ጊዜ ወስደዋል።
• በራስ አገር መጫወት ጥቅም አለው ፣ በዓለም ዋንጫ ታሪክ እስከዛሬ ከነበሩት 19 የዓለም ዋንጫ ውድድሮች 6ቱ የተወሰዱት በአዘጋጅ አገር ነው።
• ቦራ ሚሊቲኖቪች የተባሉ አሰልጣኝ ከ1986 እስከ 2002 ድረስ በዓለም ዋንጫ ላይ በአሰልጣኝነት ተገኝተዋል፣ ግን ለተለያዩ አገራት ቡድኖች ነው፣ ለሜክሲኮ፣ ለኮስታሪካ፣ ለአሜሪካ ፣ ለናይጄሪያ እና ለቻይና …
• እስከዛሬ ድረስ 6 አገሮች በተሳተፉበት የዓለም ዋንጫ ሳይሸነፉ ግን ከግማሽ ፍጻሜ ሳይደርሱ ጨርሰዋል፣ እነሱም ስኮትላንድ በ1974፣ ብራዚል በ1978፣ እንግሊዝ በ1982፣ ካሜሩን በ1982፣ ቤልጂየም በ1998፣ ኒውዚላንድ በ2010 ናቸው። አይሸነፉ እንጂ በማሸነፍ ወይም እኩል በመውጣት ነው የጨረሱት።
• ሁለት የዓለም ዋንጫዎችን በተለያየ የጨዋታ ዓይነት የተሳተፈ አንድ ተጫዋች አለ፣ ቪቭ ሪቻርድስ ይባላል፣ ለአንቲጓ የ ዓለም ዋንጫ እግር ኳስ ላይ ሲሳተፍ፣ ለዌስት ኢንዲስ ደግሞ በአለም ዋንጫ የክሪኬት ውድድር ላይ ተሳትፏል። አውስትራሊያዊቷ ኤሊስ ፔሪ ደግሞ ለአገሯ በ2009 በክሪኬት ለዓለም ዋንጫ፣ በ2011 ደግሞ ለሴቶች የ እግር ኳስ የዓለም ዋንጫ ተሳትፋለች።
• እስካሁን በዓለም ዋንጫ ከተሳተፉት ውስጥ በ ዕድሜ አንጋፋው ካሜሩናዊው ሮጀር ሚላ ነው፣ ሚላ በ1994 ከራሺያ ጋር ሲጋጠሙ ዕድሜው 42 ዓመት ከ 39 ቀን ነበር። በአንጻሩ በጣም ወጣቱ ተጫዋች ደግሞ የሰሜን አየርላንዱ ኖርማን ዋይትሳይድ ሲሆን በ1982 ከዩጎዝላቪያ ጋር ሲጋጠሙ ዕድሜው 17 ዓመት ከ41 ቀን ነበር።
• በዓለም ዋንጫ ማሊያ አውልቆ መለዋወጥ የተከለከለው በ1986 በፊፋ ነው፣ ፊፋ ተጫዋቾች ራቁታቸውን እንዲሆኑ አልፈልም ብሎ ነው ያስቆመው።
• እስካሁን በተደረጉት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች በብዛት ተመልካች የተገኘው በ1950 ዓ.ም ኡሯጓይ ከብራዚል ሲጋጠሙ በማራካና ስቴዲየም የተገኘው ብዛት ነበር። 199ሺ 854 ሰው ትኬት ቆርጦ በስቴዲየሙና በአካባቢው ተገኝቶ ነበር።
• በዓለም ዋንጫ ከተሳተፉ ተጫዋቾች ውስጥ በጣም የተለመደና የብዙዎች መጠሪያ የነበረ ስም ጎንዛሌዝ ሲሆን፣ በአብዛኛው የዋንጫ ጨዋታ የማሸነፊያ ጎል 1-0 ነው።
• ብራዚል በሁሉም የዓለም ዋንጫዎች ተሳትፋለች፣ በሁሉም የዓለም ዋንጫዎች ለግማሽ ወይም ለሩብ ፍጻሜ በማለፍም ብቸኛዋ አገር ነች።
• አዘጋጅ አገር ሆና ገና በመጀመሪያው ማጣሪያ በመሰናበት ደቡብ አፍሪካ ብቸኛዋ አገር ነች።
• ከአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዓለም ዋንጫ ያለፈች አገር ግብጽ ስትሆን እሱም በ1934 በሁለተኛው የዓለም ዋንጫ ነበር።
• በዓለም ዋንጫ ውድድር በብዙ ጎል በማሸነፍ ሃንጋሪ ትመራለች፣ በ1982 ኤልሳልቫዶርን 10-1፣ በ1954 ደቡብ ኮሪያን 9-0 አሸንፋለች።
• በ ዕድሜ አናሳ ሆኖ የዓለም ዋንጫ ላይ ግብ በማግባት ፔሌ ይመራል፣ ፔሌ በ1958 ዌልስ ላይ ሲያገባ ዕድሜዋ 17 ዓመት ከ239 ቀን ነበር።
• በአንድ የዓለም ዋንጫ ግጥሚያ ላይ 4 ጎል በማግባት የሚመራው የፖላንዱ ኽርነስት ዊልሞውስኪ ሲሆን፣ ያገባውም ብራዚል ላይ በ1938 ዓ.ም ነው፣ ምን ዋጋ አለው፣ ጨዋታው 6-5 በብራዚል አሸናፊነት ተጠናቀቀ።
በዓለም ዋንጫ የመጀመሪያዎቹ
__________________
• በዓለም ዋንጫ ታሪክ በቀይ ካርድ ከሜዳ በመውጣት የመጀመሪያው ተጫዋች የፔሩ ተጫዋች ሲሆን፣ ተጋጣሚው ሮማንያ በጁላይ 14/1930 ነበር።
• በዓለም ዋንጫ የመጀመሪያውን ሪጎሬ በመምታት ጎል ያገባው የሜክሲኮው ማኑ ኤል ሮኪታ ሮሳስ ነው። ያም ጁላይ 19/1930 አርጀንቲና ላይ ነው።
• በዓለም ዋንጫ ታሪክ የመጀመሪያው በአንድ ጨዋት 3 ጎል በማግባት ሃት ትሪክ የሰራው ተጫዋች የአሜሪካው በርት ፓትኑድ ሲሆን፣ ጎሎቹን ያገባውም ፓራጓይ ላይ ፣ በ1930ው የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ላይ ነበር።
• በዓለም ዋንጫ የመጀመሪያዋን ጎል ያገባው የፈረንሳዩ ሊቺን ላውረንት ሲሆን፣ ጎሏም የገባችው በ19ኛ ደቂቃ ላይ በመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ወቅት ነው።
• በዓለም ዋንጫ ታሪክ የመጀመሪያው በጉዳት ከሜዳ በመውጣት የተቀየረው የፈረንሳዩ ግብ ጠባቂ አሌክስ ዘፖት ነው፣ ያም በመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታ ወቅት ነው።
• የዓለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ በቲቪ በቀጥታ የተላለፈው በ1958 ዓ.ም ነበር።
የዘ-ሐበሻ 6ኛ ዓመት የፊታችን እሁድ ጁን 15 በሚኒሶታ ይከበራል
(ዘ-ሐበሻ) ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ እና ዘ-ሐበሻ ድረገድ የፊታችን እሁድ በሚኒሶታ 6ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ያከብራል። በዚህ የ6ኛ ዓመት በዓል ላይ በሚኒሶታ በመልካም ሥራቸው ከሚታወቁ የማህበረሰቡ አባላት ውስጥ አንዱ “የዓመቱ ምርጥ ሰው” በሚል እንደሚሸለም የዝግጅቱ አስተባባሪዎች አስታውቀዋል።
ታዋቂው አክቲቪስት እና አርቲስት ታማኝ በየነ በዚህ በዓል ላይ በክብር እንግድነት እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን ለዘ-ሐበሻ ድረገጽና ጋዜጣ ማጠናከሪያ የሚውል የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት እንደሚኖርም ታውቋል።
በሚኒሶታ ሴንትፖል ከተማ ኬሊ ኢን በተባለው ሆቴል ከቀኑ 3 ሰዓት ጀምሮ በሚከበረው በዚህ በዓል ላይ ከታማኝ በየነ በተጨማሪ በሚኒሶታ የሚገኙ ምሁራን የሚሳተፉባቸው ፕሮግራሞች መዘጋጀታቸውም ታውቋል።
ዘ-ሐበሻ በሚኒሶታ ግዛት ውስጥ የተመሰረተች ነፃ የመገናኛ ብዙሃን እንደመሆኗ መጠን በዓሉን በተመሰረተችበት ከተማ ለማክበር መመረጡን ያስታወቁት አስተባባሪዎቹ ወደፊት በሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀት እቅድ እንዳለ አስታውቀዋል።
በዚህ በዓል ላይ በሌላ ስቴት የሚኖሩና ሊገኙ የማይችሉ ድጋፋቸውን በፔይፓል በኩል መክፈል የሚችሉ ሲሆን በቼክ ለመላክም አድራሻው እንደሚከተለው ቀርቧል።
ዝግጅቱን ለማገዝና እንዴት ዘ-ሐበሻን ማገዝ እንደምትችሉ ለመጠየቅ የበዓሉን ዋና አስተባባሪ አቶ አልዩ ተበጀን በስልክ ቁጥር 612-986-0557 ያነጋግሩ።
ለዘ-ሐበሻ በቼክ እገዛችሁን ለመላክ
Zehabesha LCC
6938 Portland Ave S
Richfiled
MN 55423
መጠቀም ትችላላችሁ።
ዘ-ሐበሻን በፔይፓል በኩል ማገዝ ለምትፈልጉ የሚከተለውን ሊንክ ላይ ይክፈሉ
እውነት ያሸንፋል!