Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አንባ ገነኖች የስልጣን ጥም አባዜ (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና )

$
0
0

በገዛኸኝ አበበ (ኖርዌይ ሌና)

Gezahegnወይዛሬ በአለማችን ላይ መንግስታቶች ሊመሩት እና ሊያስተዳድሩት በላው ሕዝብ ላይ  የሰብሃዊ መብት ረገጣ እስራት እና ግድያ በሕዝባቸው ላይ እንደሚያደርሱ ይታወቃል በተለይም የአፍሪካ መሪዎች እና መንግስታቶች በአንባ ገነንት እና የሕዝባቸውን ሰብሃዊ መብት በመርገጥ ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ አገራችን ኢትዮጵያ አንዶ ናት :: በአሁኑ ሰአት በሀገራችን ኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ አይን ያወጣ የሰበሃዊ መብት ጥሰት በዜጎች ላይ እየፈጸመ እንዳለ ይታወቃል ይህም የወያኔ የዜጎችን የሰብሃዊ መብት መርገጥ እና ሕዝብና እያስፈራሩ ረግጦ መግዛት ከምንም ነገረ የመነጨ ሳይሆን ሕዝቡ ስለ ዜግነት መብቱ እንዳያስብ በታጠቀ ኃይል እያስፈራሩ የሥልጣን እድሜን ለማራዘም ወያኔዎች ያዋጣናል ብለው የመረጡት መንገድ ሲሆን  ዜጎችን መረበሽ፣ መዝረፍ፣ ማሰር እና መግደልን ተያይዘውት ይገኛሉ::

ዜጎችን ማሰቃየት፣ ማሰር እና መግደል የአንባ ገነን መንግስታቶች መገለጫና መታወቂያ ሲሆን        አንባ ገነን መንግስታቶች  በሰለም እና በመረጋጋት ሊመሩት እና ሊያስተዳድሩት የበላይ ሆነው የተሾሙለት ሕዝብ ሰበሃዊ መብት በመርገጥ  ግፍና በደል እንደሚፈጽሙባቸው በገሀድ የታወቀ ሲሆን እነዚህ አምባ ገነን መሪዎች ለምንድ ነው ግን ሕዝባቸውን የሚያሰቃዩት፣ የሚያስሩት እና  የሚገደሉት ብለን ማሰባችን እና መጠየቃችን አይቀርም በየትኛውም አለም እንደምናየው አንባ ገነኖች ያለምንም ተቀናቃኝ በስልጣን ዙፋናቸው ላይ ለመቀመጥ ከመሻት የተነሳ  ዜጎቻቸውን  ያሰቃያሉ፣ ያስራሉ፣ይገድላሉ

በተለይም እኛ ኢትዮጵያኖች በሀገራችን መንግስት በየጊዜው በግፍ ስለሚያሰቃዩት፣ ስለሚታሰሩት እና  ስለሚገደሉት ወገኖቻችን ሁል ጊዜ እንዳለቀስን እና እንደጮህን እንገኛለን::

ምክንያቱም ወያኔ /ኢህአዲግ  ወደ ስልጣን  ከመጣበትና የኢትዮጵያንም ሕዝብ  በሀይል መምራት  ከጀመረበት ጊዜ አንስቱ እስከ አሁን ድረስ ከሁለት አስርት ከአመታት በላይ መሆኑ ነው አንድም ቀን በሰላም እና በተረጋጋ ሁኔታ የኖረበት እና የኢትዮጵያ ሕዝብንም በሰላም የመራበት ጊዜ የለም ብል ማጋነን አይሁንብኝም::ይኼው የወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ ሁልጊዜ እንደፈራ ሕዝቡንም እንዳስፈራራ ሁል ጊዜ እንደተረበሸ ሕዝቡንም እንደረበሸ የሚኖር ሲሆን ይህም የወያኔ  ባህሪና መገለጫዎች ናቸው:: ከዚህም የተነሳ ሀገራችን ኢትዮጵያ በወያኔ ኢህአዲግ መንግስት መገዛት ከጀመረችበት ጊዜ  አንስቶ ወያኔ ያሰረው እና የገደለው ሀገሩንም ጥሎ እንዲሰደድ ያደረገው ሕዝብ ቁጥሩ እጅግ ብዙ ሲሆን የዜጎችንም ሰላም በመረበሽ እና በሀገራቸው ተረጋግተው እንዳይቀመጡ በማድረግ ላይ ይገኛል::

ከዚህ በታች  የአንባ ገነኖችን ማንነት መገለጫ የሆኑትን ነገሩች  በአጭሩ የተወሰኑ ነጥቦችን በማንሳት ለመዳሰስ እሞክራለው

    1,አምባገነኖች ያለ ሕዝብ ፍላጎት ለብዙ አመታት በስልጣን ላይ የመቆየት ማንነት ይታይባቸዋል            (የስልጣን ሱሠኞች) ናቸው ::
 

ብዙዎን ጊዜ እንደ  አፍሪካ እና አረብ ሀገራት ያሉ አምባ ገነን  የሀገር መሪዎች ወደ ስልጣን ሲመጡ የሕዝብን ህውቅና አግኝተው ወይም በሕዝብ ድምጽ በምርጫ ተመርጠው ሳይሆን አንድም በመፈንቅለ መንግስት አንድም በጦርነት በሀይል ስልጣንን መቆጣጠር ወይም በዘር ውርስ የስልጣን እርክብክቦሽ አማካይነት መሆኑ ይታወቃል:: ስለሆነም  ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ  ስልጣናቸው ወይም መንግስታቸው በሀገራቸው ዜጎች እውቅና ሲሰጠው አይታይም :: ከዚህም የተነሳ ከሕዝባቸው ጋር አይጥ እና ድመት በመሆን ተፈራርተው ሕዝባቸውን  ሲያስፈራሩና ሲረብሹ ይኖራሉ ::  እንደነዚህ ያሉ ሀገራቶች  በማን አለብኝነት ያለምም ተቀናቃኝ ለብዙ አመታት የስልጣንን ወንበር ተቆጣጥረው ስልጣንንም መከታ በማድረግ የሕዝብን መብት በመርገጥም  ሲኖሩ ይታያሉ:: እነዚህ አንባ ገነን መንግስታቶች በሕዝባቸው ላይ አመኔታ የላቸውም ሕዝቡም በእነሱ ላይ አመኔታ የለውም ስለዚህ ሁል ጊዜ በዜጎቻቸው እንደተረገሙ እነሱም ሁል ጊዜ ዜጎቻቸውን እንደረገሙ ይኖራሉ::እየወለ እየደር ግን የአንባ ገነኖች መጨረሻቸው በሕዝብ ቁጣ ተርፍረክርኮ መውደቅ ነው::

በግብጽ በቱኒዚያ በየመን እና በሌሎችም ሀገሮች እንዳየነው አንባገነኖች ለብዙ አመታት ስልጣንን በማውረስ እና በመረካከብ ሕዝብን በመጨፍለቅ ሲገዙ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው ለምሳሌ በግብጽ ጀማል ሙባረክ የሚቀጥለው የግብጽ መሪነትን ከአባቱ ለመውረስ እና ለመረከብ በመዘጋጀት እያለ ነበር ድነገት ባልጠበቁት ሰአት የቱኒዚያው ሱናሜ የተነሳው እና ያለሙትን አላማ ሳይተገብሩ በአንባ ገነኖች መገዛት በሰለቸው ሕዝብ ቁጣ እንደ ሰም ቀልጠው የቀሩት:: እነዚህን ሀገሮች እንደ ምሳሌ አነሳው እንጂ እንደነ ምሮኮ እና ኮንጎ የመሳሰሉ አብዛኞች ሀገሮች ስልጣንን በሀይል ወይም በውርስ በማውረስ እና በመረካከብ  ያለ ሕዝብ ፍላጎትና ህውቅና  ለዘመናት በማን አለብኝነት ስልጣንን በግላቻው በመቆጣጠር የሕዝቦችን ሰብሃዊ መብት ሲጨፈልቁ የሚኖሩ ሀገሮችን መጥቀስ ይቻላል::አንባ ገነኖች  እነሱን ከሚመስላቸው ውጭ  ለሌላ የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅትም ሆነ ሀገርን ለመምራት አቅምም ሆነ ብቃቱ ላላቸው ሰዎች በማንኛውም መንገድ ቢሆን ስልጣንን ለመልቀቅ ፍቃደኞች ሲሆኑ አይታዩም::

ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ስንመጣ ይህንኑ ነው የምናየው በአሁኑ ሰአት ሀገራችንን ኢትዮጵያን እየመራው ነው የሚለው የወያኔ  መንግስት ስልጣንን በዘር ሲወራረሱ እንደነበሩ  እንደ አንዳንድ አረብ  እና አፍሪካ ሀገራት አንባ ገነን መሪዎች በዘር አይወራረሱ እንጂ  ከሕዝብ ፍቃድ እና ፍላጎት ውጭ ለዘመናት የስልጣን ወንበሩን በማን አለብኝነት በሀይል ተቆጣጥሮ የዜጎችን ሰብሃዊ መብት እየረገጠ ያለ መንግስት መሆኑ ይታወቃል::አሁን ባለው አካሄድ እና አንዳንድ የወያኔ ባለስልጣኖች አንዳንድ ጊዜ አፋቸው እያመለጣቸው እንደሚናገሩት እነዚህ የስልጣን ሱሠኞች የሆኑት የወያኔ ባለስልጣኖች በፈቃዳቸው ስልጣንን ይለቃሉ ተብሎ የማይታሰብ ቢሆንም ድንገት ግን የሕዝብ ቁጣ ገንፍሎ ወያኔ የሚባል የአንባ ገነን የማፊያ ቡድን ዳግመኛ እንዳያንሰራራ በግብጽ ፣ በቱኒዚያ እና በሌሎችም ሀገሮች እንደ ሆነው ሁሉ የአንባ ገነኑን የወያኔን መንግስት  ስርአት ወደ መቃብር ያስገበዋል የሚል ከፍተኛ የሆነ እምነት አለኝ::

የሰሜን አፍሪቃ እና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ዜጎች ለአስርት ዓመታት በአምባገነን አገዛዝ ተገዝተዋል። እኛ ደግሞ ለአስርት ዓመታት አምባገነን ብቻ ሳይሆን ዘረኛም ጭምር በሆነ የስልጣን ጥም አባዜ በተጠናወጠወ አገዛዝ እየተገዛን ነው። እኛ እየደረሰብን ያለውን ዓይነት አዋራጅ ዘረኝነት እነሱ ላይ አልደረሰባቸውም። አምባነንነት እነሱን አስመርሮ በገዚዎቻቸው ላይ በአንድነት እንዲነሱ አድርጓቸዋል። እኛ ዘንድ ደግሞ አምባገነንነትና ዘረኝነት ተዳብለውብናልና ከእነሱ በላይ አምርረን በህብረት የስልጣን ሡስ በተጠናወጣቸው አንባገነኖች ላይ እንነሳለን።

2,አምባገነኖች በራስ የመተማመን (self confidence)ስለሌላቸው ለሁሉም ሃይል መጠቀም ይወዳሉ።

አንባ ገነን መንግስታቶች ሕዝብን በአግባቡ መምራት ሕዝብ የሚጠይቀውን ማንኛውንም አይነት ጥያቄ ለመመለስ ፍቃደኛ አይደሉም:: አንባ ገነን መንግስታቱች በነገሱበት ሀገር የመብት የነፃነት የፍትህ ጥያቄ መጠየቅ በፍጹም የማይታሰብ ሲሆን ዛሬ ስንቶች ናቸው መብታቸውን  ስለጠየቁ  ብቻ በአንባገነኖች ጥይት በየሀገሩ እንደ ቅጠል እየረገፉ ያሉት::

እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ነገር የኛዎቹ አንባ ገነኖች የወያኔዎች መጀመሪያውኑ ወደ ስልጣን ሲመጡ እና  ለዘመናት ከሁለት አስርት አመታት በላይ በስልጣን ላይ  ሲቀመጡ በሕዝብ ፍላጎት እና ነጻ ምርጫ ሳይሆን ሌሎች አንባ ገነን መንግስታቶች እንደሚያደርጉት ሁሉ ሕዝብን እያስፈራሩ እና ሃይልን በመጠቀም የሕዝብን ናጻነትና መብትን በማፈን እንደሆነ ይታወቃል::   በመሆኑም የስልጣንን ወንበር ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ መንግስታቸው የሕዝብ ተቀባይነት የለውም:: ስለሆነም   ፈጽመው ተረጋግተው መኖር በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ሲገኙ  ሁልጊዜ መንግስታቸው በስጋት ውስጥ ነው የሚኖረው::

አንባ ገነኑ የወያኔ መንግስት በራሱ የማይተማመንና በስጋት ውስጥ የሚኖር መንግስት  እንደሆነ በቅርቡ  የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሒዩማን ራይትስ ዎች የወያኔን መንግስት አሳፋሪ ድርጊት በመኮነን ያወጣው ሪፖርት አመላካች ነው::እንደ  የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ሪፖርት  ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንንና ሌሎች ባለሙያዎችን በማነጋገር አዘጋጀሁት ባለውና ባለፈው  ሳምንት ይፋ ባደረገው  የኢትዮጵያ መንግሥትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ እንዳለ እና  ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ወይም አገር ውስጥ እንዳይንቀሳቀስ ከታገደ የፖለቲካ ድርጅት ጋር በማንኛውም መንገድ ቅርበት ያላቸው ኢትዮጵያውያኖች በወያኔ መንግስት እንደሚሰለሉ እና እነዚህ ሰዎች የሚያደርጉት የስልክ ንግግር በተለይ ደግሞ ከውጭ አገር የተደወለ ከሆነ ያለ ግለሰቦቹ ፈቃድ ወይም ዕውቅና ተጠልፎ እንደሚቀዳ ሒዩማን ራይትስ ዎች በሪፖርት ላይ ይፋ አድርጎል  ለዚህም የስለላ ተግባሩን ለመፈጸመ  የሚያገለግሉ መሣሪያዎችን ከተለያዩ አገሮች እንዳገኘ፣ሪፖርቱ ጨምሮ ይፋ አድርጓል::

የወያኔ መንግስት በራስ መተማመን የጎደለው እና በፍርሃት የተሞላ መግስት መሆኑን በአደባባይ ያስመሰከረ አንባ ገነን መንግስት ነው ::መሪዎቹ በጭራሽ በራስ መተማመን ብሎ ነገር ስላልፈጠረባቸው መተማመኛቸው ጠብመንጃ፤በጦሩ ጉያ ተሸጉጠው ሃገርና ሕዝብን ለእልቂት ለረሃብ ለመከራ የሚያበቁበትን ቆመውም ተቀምጠው ተኝተውም ማውጠንጠን ነው፡፡ ይህንንም ስል እንዴው ዝም ብዬ ከመሬት ተነስቼ እንዳለ ይታወቅልኝ:: እኔ እስከማቀው ድረስ የወያኔ መንግስት ስልጣኑን ሀ ብሎ የኢትዮጵያን ሕዝብ ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቱ እስከ አሁን ድረስ ከ22 አመት በላይ መሆኑ ነው አንድም ቀን በሰላም እና በተረጋጋ ሁኔታ የኖረበት እና የኢትዮጵያ ሕዝብንም በሰላም የመራበት ጊዜ የለም ብል የተሳሳትኩኝ አይመስለኝም:: ከዚህ ስጋታቸውም የተነሳ የኢትዮጵያን ሕዝብ አፍነው ይዘውታል::

ዜጓች ሕገ መንግስታዊ  መብታቸውን ተጠቅመው  የሚደርስባቸው ጭቆናና የሰበሃዊ መብት ጥሰት   በነጻነት መቃወም አልቻሉም :: አንባ ገነኑ ወያኔ ይኼን ያክል ዘመን በስልጣን ላይ ሲቆይ ስልጣኑን መከታ በማድረግ  ስንቶችን ሲገርፍ፣ ሲያስር ፣ ሲያሰቃይ እና ሲገድል እንደኖረ በአደባባይ የተገለጠ ሀቅ ነው::ሕዝብም ስለመብቱ እና ነጻነቱ የጠየቀ ከሆነ ይታሰራል ፣ይገረፋል ይገደላል::

ኢትዮጵያን በዘር ፣ በቋንቋ እና በሃይማኖት ከፋፍሎ የህዝቡን አንድነት ለማጥፋት የሚጥረውን አገዛዝ መቃወም ደግሞ “አሸባሪ’’ የሚል ታርጋ አስለጥፎ ዘብጥያ ያስወረውራል።  ዛሬ የኛዎቹ እነ እስክንድር ነጋ ፣ርዕዮት አለሙ እና ሌሎችም ወጣት ወገኖቻችን በሽበርተኝነት ስም ተወንጅለው በአንባ ገነኖች እስር ቤት ውስጥ ተጥለው እየተሰቃዩ ያሉት የወያኔ መንግስት እንደሚለው ሽብርተኛ  ሳይሆኑ  የነጻነት እና የፍትህ ታጋይ ጀግኖች እንደሆኑ በድፍረት መናገር እችላለው::
በወያኔ አንባ ገነናዊ እኩየ ስራዓት የህግ የበላይነት የለም፤ ዲሞክራሲ ተደፍጥጡዋል፤ የደህንነት ዋስትና የለም፤ ነፃ ፕሬስ ተረት ሆኗል፣ የብዙሃን ፓርቲ ያልምንም እፍረት ተገፍትሮል። የሲቪክና ሙያ ማህበራት የማሽመድመዱ ተግባር ተከናውኗል።ይለቁንም ዘረኞች ግፈኞች፣ ወንጀልኞች፣ አምባገነኖች፣ ሙሰኞች እንዳሻቸው ዛሬም እየፈነጩ፤  በተቃራኒው ደግሞ ለፍትህ ለእኩልነትና፣ለነጻነት ሲሉ ለህሊናቸው፣ የሚታገሉ የሚዋረዱበት፣ የሚሰደዱበትና የሚታስሩበት አገር መሆኑ በጣም ያንገበግባል፣ ያስቆጫል።
ነገርግን አንባ ገነኖች የስልጣን ሃይላቸውን በመጠቀም ማሰር፣ መግደል ሕዝብን ማሰቃየት ከያዛቸው የስልጣን ጥም አባዜ የተነሳ በስልጣን ላይ ረጅም ጌዜ ለመቆየት የሚጠቀሙበት መንገድ ሲሆን ይህም በራስ መተማመን እንደሌላቸው ያሳያል ::ነገር ግን እዚህ ላይ ማወቅ ያለብን ነገር ይህ አይነት አካሄድ አንባ ገነን መንግስታቶችን የትም ሊያደርሳቸው እንደማይችል ሲሆን አንባ ገነኖችም ይህን ሊገነዘቡትና ሊያውቁት ይገባል ባይ ነኝ ::በርግጥ የታፈኑ ብሶት ገንፍሎ የነጻነት ደማቅ ፀሐይ የምናይበት ጊዜ እንደሚመጣ ቅንጣት ያክል አልጠራጠርም። የሰሜን አፍሪቃ እና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ዜጎች በያገራቸው ፍትህ በመጓደሉ ተማረዋል። እኛ አገር ደግሞ ፍትህ ራስዋ ተዋርዳለች። ፍርድ ቤቶች ማጥቂያዎች ሆነዋል። አገራችን እስር ቤት ሆናለች። አብዮት ከቀሰቀሱት ጎረቤቶቻችን በባሰ እኛ ተበድለናልና  ከእነሱ በባሰ አምርረን ልንነሳና አንባ ገነኖችን ዳግም እንዳይነሱ ልንቀብራቸው ያስፈልጋል።
     3,አምባገነኖች ከሀገር እና ከሕዝብ ጥቅም ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም ያስቀድማሉ (ሙሰኞች ናቸው)

የአንባ ገነኖች ሌላው የባህሪያቸው ዋንኛ መታወቂያቸው ሙሰኝነት ሲሆን ይህንንም ተከትሎ  አገራችንን ኢትዮጵያን ጨምሮ አፍሪካ  አንባ ገነኖች በስፋት የነገሱባት  ሙሰኝነት እና ሙሰኞች የተንሰራፉበት አህጉር በመሆን ትታወቃለች :: በአፍሪካ ሀገራት የሚነሱ መሪዎች ወደ ስልጣን ከመጡ እና ስልጣን ከያዙ በኋላ ስለ ሀገር እና ስለ ሕዝባቸው ግድ የለሾች ሲሆኑ ስለ ሀገር እና ስለ ሕዝባቸው ግድ የማይላቸው ሆዳሞችና የራሳቸውን ጥቅም ብቻ የሚያሳድዱ ገንዘብ ወዳዱች ናቸው::በሀገራችን ኢትዮጵያ በስልጣና ላይ ያለው አምባ ገነኑ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖች  ከላይ እስከታች በተዘረጋው የወያኔ ስርአት ውስጥ ከቁንጮ ባለስልጣናት እስከታችኛው አገልጋይ ድረስ በሙስናና በሌብነት ያልተዘፈቀ የስርአቱ አገልጋይ ቢፈለግ አይገኝም ብል ማጋነን አይመስለኝም:: በአሁኑ ሰአት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አዲስ አበባን ነዋሪ ጨምሮ ሕዝቡ በከፍተኛ የኖሮ ችግር ውስጥ እንዳለ ይታወቃል:: ካለውም ታላቅ የኑሮ ውድነትና፣ የስራ ማጣትና ያለው ብልሹ የመንግስት ፖለቲካዊ አስተዳደር ተደምሮበት ሕዝቡ ሀገሮን ጥሎ ወደ ተለያየ ሀገር እየተሰደደ በተለይም ወጣቶች ወንዶችና ሴቶች እህቶቻችን ሀገራቸውን ጥለው ሲወጡ በየድንበሩ እየሙቱና ወደ ተለያየ ሀረብ ሀገራትም ሄደው ለተለያየ መከራ ስቃይ እና ችግር ሲደርስባቸው እና ዜጓቻችን ሲገደሉ ምንም ግድ የማይሰጣቸው ነገር ግን   እኔ ከሞትኩኝ ሰርዶ አይብቀል እንደሚባለው የወያኔ  አንባ ገነን መሪዎች ሙሰኞች ከኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረፉትን  በመቶ ሚሊየኖች የሚቆጠር ዶላር ከኢትዮጵያ ህዝብ በማሸሽ በውጪ አገር ባንኮች በማካበት ላይ እንደሚገኙ ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ 11 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የአገሪቱ ገንዘብ በውጭ ባንኮች መቀመጡን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል ።

በወር ስድስት ሺህ ብር ደሞዝተኛ እንደነበሩ በባለቤታቸው የተነገረላቸው አንባ ገነን የነበሩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር ሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ ሁላችንም እንደምናስታውሰው ከጥቂት ዓመታት በፊት የትንሳኤ ሬድዮ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሀብት የዘረፉ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖችን፥ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ የዘረፉትን ሀብት መጠንና ገንዘቡን ያስቀመጡበትን አገር ጭምር ይፋ አድርጎ እንደነበር አስታውሳለው።  ይሄ ሬድዮ ጣቢያ አቶ መለስ ዜናዊ በማሌዥያ በባንክ ፬፪ (አርባ ሁለት) ሚሊዮን ዶላር እንዳስቀመጡ ገልጾ ነበር።ይታያችው እንግዲህ  በተከታዩቻቸውና የአቶ መለስ አፍቃሪ በሆኑ ሰዎች እስከ አሁን ድረስ ሰውየው ስለ ሀገራቸውና ስለ ሕዝባቸው ፍቅር የነበራቸው፣ ባለራእይ መሪ እንደነበሩ ሲወደሱ እና ሲዘመርላቸው መስማት የሰለቸን ጉዳይ ነው:: እውነታው ግን የሚያሳየው ሌላ ነው ተከታዩቻቸውና የአቶ መለስ አፍቃሪ እንደሚሉት ሳይሆን አንባ ገነኖች አንድም ቀን የሀገር እና የሕዝባቸው ፍቅር ኖሯቸው አያውቅም እኝው አንባ ገነን የቀድሞ መሪ ሕዝባቸውን ሲያዋርዱና ሲያንቋሽሹ ለሀገራቸውም ቅንጣት ያከል ፍቅር እንደሌላቸው የሚያሳይ ስራ ይሰሩ የነበሩ እና ጀግኖች አባቶቻችን የታወደቁለትን ባንዲራ እንኳን ሳይቀር ጠቅላይ ሚኒስትር ተብዬ የነበሩት አንዴ ሲዘቀዝቁት አንዴ ጨርቅ ነው ሲሉት እንደነበር እናስታውሳለን::

በአሁኑ ሰአት የወያኔ መንግስት ሙስናን ለማጥፋት እየታገለ እንዳለ በተለያዩ መድረኮችና ሚድያዎች ከመግለፅ ኣልፎ። ራሱ የፀረ ሙስና ኮምሽን ብሎ ባደራጀውና  በሚጠራው ተቋም ሙሰኞች ባላቸው ግለሰቦች  ላይ ክስ በበመመስረት ወደ ፍርድ ሲያቀርባቸውና እስርቤት ውስጥ ሲያጉራቸው ይስተዋላል ነገር ግን ይህ የወያኔ መሰሪ ተንኮል ሆነ ብሎ ለህዝብና ለኣለም ማህበረሰብ ወያኔ እራሱን የብርሃን መላእክት አድርጎ በማቅረብ ለማታለል ተብሎ እየተሰራበት ያለ ተንኮል ነው::

ወያኔ እራሱን ፀረ-ሙስና ድርጅት ለመምሰል ለህዝብና ለኣለም ማህበረሰብ ለማታለል እየተሰራበት ያለ ድብቅ ተንኮል     ነገር ግን ለስርኣቱ ተገዢ ሆነህ እስካገለገልክ ድረስ በአስተሳሰብ የተለየ እስካልሆንክ ሰው ብትገድል እንኳ በእርቅ ነፃ መውጣት ትችላለህ፡፡ስልጣንህን ተገን በማድረግ የህዝብ ንብረትና ገንዘብ ለመስርቅ ሙሉ ዋስትና እንደሚሰጥህ፣ የፈለከውን ያክል ገንዘብ ብትዘርፍ ዘመነኛ ተብለህ ልትሸለማለህ ትችል እንደሆነ እንጂ ሙሰኛ አያሰኝህም፡፡ ነገር ግን ከእነሱ ትንሽ ለየት ያለ የፖለቲካ ልዩነት ያላቸው እና ለበላይ ኣለቆቻቸው  ያላጎበደዱና ያልተስማሙ ግን ሙስናን ተገን በማድረግ በቁጥጥር ውስጥ እንደሚውሉ ይታወቃል:: ይህም  የወያኔ  ስርአት ምን ያህል አንባ ገነን መሆኑንና ስርኣቱ የስልጣን ጥም አባዜ በተጠናወጣቸው የስልጣን ሙሰኞች  የተሞላ ኣስመሳይ ፀረ ህዝብ ኣሰራር መሆኑንን ያመለክታል::

ሙስና የአንባ ገነን መንግስታቶች መገለጫ ሲሆን የሰሜን አፍሪቃ እና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት የነበሩት አንባ ገነን ሹሞች በሙስና ያካበቱት ሃብት በቢሊዮን ዶላሮች እንደሚገመትና ሕዝቡንም ለአመጽ ያነሳሳው ይኸው የአምባ ገነኖች ከልክ ያለፈ ሙሰኝነትና ሌብነት እንደሆነ ይታወቃል። የእኛ የመጨረሻይቱ ድሃ አገር አንባ ገነን የወያኔ ሹሞችም በሙስና ያካበቱት ሃብት እንደዚያው ነው። እርግጥ ነው በከተሞቻችን ህንፃዎች በርክተዋል ሆኖም ግን የሙሰኞቹ እንጂ የለፍቶ አዳሪዎቹ አይደሉም። ስለዚህ በአሁኑ ሰአት እያደጉት ያሉት አንባ ገነኖች እና ሙሰኞች እንጂ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንዳይደለች መታወቅ አለበት የሀገሬ ምስኪንና ደሃ ሕዝብማ በየቦታው በረሃብ እያለቀ ነው የሚገኘው:: በሃብት መበላለጥ የተቆጩት እና በሙስና መብዛት በአንባ ገነንና በስልጣን ሱሰኞች መሪዎቻቸው የተናደዱ የአህጉራችን  የሰሜን አፍሪቃ ዜጎች በገዢዎቻቸው ላይ ተነስተዋል እኛ ደግሞ  ከእነሱ በላይ ተጎድተናልና ከእነሱ በላይ አምርረን ልንነሳ ሙሰኛውን፣ የሀገርና የሕዝብ ፍቅር የሌለው አንባ ገነኑ የወያኔ መንግስት ልንፋለመው ይገባል እያልኩኝ ጹሁፊን ላጠቃላል ፈጣሪ ቸረ ወሬ ያሰማን ።

የአንባ ገነኖች መጨረሻቸው ውርደት ነው !!! ድል ለሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን !!

gezapower@gmail.com


የጃኪ ጎሲ የሰሜን አሜሪካ የሙዚቃ ኮንሰርቶች የሕግ ጥያቄዎች አሉበት፤ ይሳካ ይሆን? አላሙዲ ከጃኪ ጀርባ አለ?

$
0
0

የምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት ባለቤት ሸዋ ኢተና የጃኪ ጎሲን የሙዚቃ ኮንሰርት በሰሜን አሜሪካ ለማየት ለሚጠባበቁ ወገኖች ጥሪ አቀረበ። ከዚህ ቀደም የስራ ፈቃድ አውጥተንለት ወደ ሰሜን አሜሪካ እንዲመጣ ጉዳዩን ጨርሰን ኮንሰርት እስከመሰረዝ ደርሰናል፤ በዚህም ኪሳራ ደርሶብናል በሚል የሚከሰው የሸዋ ኢንተርቴይመንት በተለይም በቅርቡ ዋሽንግተን ዲሲን ጨምሮ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ድምጻዊው ኮንሰርት ያቀርባል ብለው ሰዎች ገንዘባቸውን እንዳያፈሱ ጥሪውን አቅርቧል። “ጃኪ ባለን ስምምነት መሰረት [ከሌላ ሰው ጋር] (ምንም ዓይነት ኮንሰርት) መስራት አይችልም” የሚለው ሸዋ “በጃኪ ላይ ስለሚወሰደው እርምጃ ሕዝቡ እንዳያዝን” ይላል። የሸዋ ባለቤት ከኢትዮቲብ ድረ ገጽ ጋር ካደረገው ቃለ ምልልስ እናስቀንጭብዎ እና አወዛጋቢው ጃኪ በድጋሚ በማወቅም ይሁን በማያውቀው መንገድ ከሌሎች ጋር ስለመላተሙ የሚዘግበውን ጽሁፍ ከታች አቅርበናል። ከዚህ ቀደም ጃኪ ለዘ-ሐበሻ ‘ከምነው ሸዋ ጋር ምንም ስምምነት ኖሮኝ አያውቅም” ሲል መናገሩ አይዘነጋም።

የድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ያሜሪካ ዝግጅት ለ 2ኛ ጊዜ ውዝግብ አስነሳ

ይህ በጃኪ ኮንሰርት ዙሪያ ተክደናል የሚሉ ወገኖች ያሰራጩት መረጃ ነው።

ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ በጥቂት ነጠላ ዜማዎቹ ከፍተኛ ዝናን ያገኘ ወጣት ድምፃዊ ነው። ጃኪ ጎሲ የኢትዮጵያን ባህላዊ የአዘፋፈን ስልቶች ከዘመናዊው ሙዚቃ ጋር የሚያዋህዱ ማራኪ ስራዎቹ በህዝብ ዘንድ እጅግ ፈጣን እውቅናን አጎናጽፈውታል። ይህ ወጣት ድምፃዊ በኢትዮጵያ የሙዚቃ አለም ገና ከጅምሩ የደረሰበት ደረጃ ወደፊት ብዙ ሊሰራና ከፍተኛ ዝናን ሊጨብጥ እንደሚችል አመላካች ነው።

ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ከምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ውዝግብ ውስጥ ገብቶ እንደነበር ይታወቃል። ጃኪ ጎሲ በ2012 በፈረንጆቹ አቆጣጠር በሰሜን አሜሪካ ሃገራት ሊያደርጋቸው የነበሩ የሙዚቃ ኮንሰርቶች በዚህ ውዝግብ ምክንያት በመሰረዛቸው ብዙ አድናቂዎቹን እንዳሳዘነ ይታወሳል።

jacki gosseeበጃኪ ጎሲ ዙሪያ ከዚህ በፊት የተፈጠረው ውዝግብ ብዙ ኢትዮጵያውያን አድናቂዎቹን ማስከፋቱ የሚያሳዝን ክስተት ሆኖ ሳለ፤ ዘንድሮም በዚሁ አርቲስት ዙሪያ በሌሎች የኢንተርቴንመንት ስራን በሚሰሩ ሁለት ድርጅቶች መካከል በድጋሚ የተፈጠረው የሚያስገርም ውዝግብ የበለጠ ህዝብን የሚያሳዝን፣ የድምፃዊውንም ስምና ዝናን የሚያጎድፍ፣ እንዲሁም በዙሪያው አብሮ ለመስራት ሽር ጉድ የሚሉትን ፕሮሞተሮች ስምና ስብእናን ከጥርጣሬ ውስጥ የሚከት በመሆኑ፤ በጉዳዩ ዙሪያ ላሉ አካላትና ለአንባቢያን ግንዛቤ ማስጨበጥ አስፈላጊ ነው።

ነገሩ እንዲህ ነው፤ ኢቫንጋዲ ፕሮደክሽንና ማሂ ፕሮደክሽን በሰሜን አሜሪካ አትላንታ ከተማ የሚገኙ ሁለት የኢንተርቴንመንት ስራን የሚሰሩ ድርጅቶች ሲሆኑ፤ የሺ ማርት ደግሞ በዚሁ በአትላንታ የሚገኝ የሃበሻ ሱቅ ነው። ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ በሰሜን አሜሪካ ኮንሰርቶች ለማዘጋጀት ከየሺ ማርት እና ከኢቫንጋዲ ፕሮደክሽን ጋር በመሆን በጋራ ስምምነት ያደረጉ ሲሆን፤ ይህንኑ ለማስፈጸምላለፉት ሁለትአመታት ወደ ሰሜን አሜሪካ ለመግባት የሚያስችለውን ፕሮሰስ ለመጨረስ ሙከራ በማድረግ ላይ ቆይቷል። ሆኖም በኢቫንጋዲ ፕሮደክሽን አማካኝነት እየተሞከረ የነበረው የፕሮሰስ ሂደት ሳይሳካ በመቅረቱ ምክንያት፤ኢቫንጋዲ ፕሮደክሽን ከሌላ አካል እርዳታ አስፈልጎት ነበር።

በዚህም መሰረት ኢቫንጋዲ ፕሮደክሽን እዚሁ አትላንታ የሚገኘውን ማሂ ፕሮደክሽን የአርቲስት ጃኪ ጎሲን የቪዛ ፕሮሰስ እንዲያስጨርስለት በመጠየቅ፤ ስምምነት አድርጎ ነበር። ስምምነቱን ባጭሩ ለመግለጽ ያክል፤ ማሂ ፕሮደክሽን የድምፃዊ ጃኪ ጎሲን የቪዛ ፕሮሰስ ካስጨረሰ ድምፃዊው በሰሜን አሜሪካ ከሚያደርጋቸው ኮንሰርቶች ውስጥፕሮደክሽኑ በሚመርጠው አንድ ቦታ ላይ ድምፃዊ ጃኪን ሊያሰራ፤ ኢቫንጋዲ ፕሮደክሽንም ቃሉን አክብሮ ይህንኑ ሊያስፈጽም ነበር።

እንደ ማሂ ፕሮደክሽን መረጃ ከሆነ በዚህ ስምምነት መሰረት ማሂ ፕሮደክሽን የድምፃዊ ጃኪ ጎሲን የቪዛ ፕሮሰስ አስጨርሶ ድምፃዊው ወደ ሰሜን አሜሪካ የሚያስገባውን ቪዛ በእጁ እንዲገባ አድርጓል። ነገር ግን ኢቫንጋዲ ፕሮደክሽን የገባውን ቃል አክብሮ መፈጸም ሲገባው፤ ማሂ ፕሮደክሽን ያደረገውን ውለታ እንደማያውቅና የድምፃዊ ጃኪ ጎሲ የቪዛ ጉዳይ ያለቀው በሼክ ማሃሙድ አል አሙዲን በኩል እንደሆነ በመናገር ላይ ይገኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ማሂ ፕሮደክሽን በተፈጠረው ሁኔታ ስለተበሳጨ ጉዳዩን ወደ ፍርድቤት ለመውሰድ በዝግጅት ላይ እንደሆነ ይናገራል።

(ከዚህ ቀደም የተሰረዘው የጃኪ ኮንሰርት ፍላየር)

(ከዚህ ቀደም የተሰረዘው የጃኪ ኮንሰርት ፍላየር)

እዚህ ላይ በጣም የሚገርመው ጉዳይ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ በኢቫንጋዲ ፕሮደክሽንና በማሂ ፕሮደክሽን መካከል ስምምነቱ ሲደረግና የቪዛ ጉዳዩ ያለቀው በማሂ ፕሮደክሽን በኩል መሆኑን እያወቀ ችላ በማለቱ ምክንያት ለሁለተኛ ጊዜ ውዝግብ ውስጥ መግባቱ ነው። ጥፋተኛው ማንም ሆነ ማን፤ የዚህ ፅሁፍ ዋናው አላማ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲን ጨምሮ ሶስቱም አካላት ውዝግቡ የሚያስከትለውን መዘዝ ከወዲሁ ተገንዝበው በቶሎ መፍትሄ እንዲያበጁለት በአፅንዖት ለማስገንዘብ ነው።

በመጨረሻም ፅሁፋችንን ላነበቡና ሃሳባችንን ለተጋሩ ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋናችንን እያቀረብን፤ የምንሰናበተው ይህንን ጎጂና ደስ የማይል ውዝግብ በተመለከተ፤ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡትን መልስ ጨምሮ፤ ሰፋያለ መረጃ በቅርቡ ይዘን እንደምንቀርብ ቃል በመግባት ነው::
——————————–

አንባቢያንስ ምን ትላላችሁ? ይህ ተወዳጅ ድምጻዊ እንደዚህ ያሉ ውዝግቦች ውስጥ መግባት ነበረበት ወይ? አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ካወጣው 4 ዘፈን አኳያ ይህ ሁሉ ነገር ይገባዋል ወይ? በሌሎች ወገኖች እንደሚከሰሰው አላሙዲ ጋር ስሙ መያያዙ በልጁ የወደፊት ሥራ ላይ የሚፈጥረው ነገር ይኖራል? አስተያየታችሁን ጻፉት።

ነገ በደሴ ለሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ እየተደረገ ያለውን ቅስቀሳ የሚያሳይ ፎቶ ዜና

$
0
0

የአንድነት ፓርቲ “የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪ ቃል 2ኛውን ዙር ሕዝባዊ ንቅናቄ በደሴ ከተማ ነገ እሁድ ኤፕሪል 6 ቀን 2014 ዓ.ም በሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ያደርጋል። የደሴ ነዋሪዎች አደባባይ ወጥቶ ብሶቱን እንዲያሰማ አንድነት ጥሪ ያቀረበ ሲሆን የፓርቲው መሪዎች ሳይቀሩ ሕዝብ በተሰበሰበት በመገኘት በራሪ ወረቀቶችን በመበተን፣ በሞንታርቦ እና በሌሎችም መንገዶችም በመቀስቀስ ላይ ይገኛሉ። ነገ እሁድ በደሴ የሚደረገውን ሰልፍ በማስመልከት እየተደረገ ያለውን ቅስቀሳ የሚያሳየውን ፎቶዎች ይመልከቱ።
udj dessie 2

udj dessie 3

udj dessie 4

udj dessie 5

udj dessie 6

udj dessie 7

udj dessie 8

udj dessie 9

udj dessie

ህወሓት በአፅቢ (እንዳስላሴ) ረብሻ ለመቀስቀስ እየሞከረ ነው፤ ነገ እሁድ አረና ለጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳውን ቀጥሏል

$
0
0

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

Arena-Tigray-logoየዓረና አባላት ለነገ እሁድ መጋቢት 28 በአፅቢ (እንዳስላሴ) ከተማ ለሚደረግ ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛሉ። በዓድዋ ቅስቀሳ ስናደርግ “እንዳትነኳቸው፣ በሰላም ይቀስቅሱ!” ብሎ መመርያ የሰጠ በመቐለ ከተማ የሚገኝ የህወሓት ከፍተኛ አመራር ዛሬ በአፅቢ ከተማ በምናደርገው ቅስቀሳ ረብሻ እንዲነሳ መመርያ መስጠቱ ከአንድ ሰዓት በፊት ሰማሁ። አላመንኩም ነበረ። ለማረጋገጥ ወደ አፅቢ ደወልኩ።

የዓረና አባላት ቅስቀሳ ሲያደርጉ ገብረማርያም የተባለ የወረዳው የሚልሻ አዛዥ ወጣቶችን አሰባስቦ የሚታደለውን ወረቀት መቅደድና መሳደብ መጀመራቸው ተነገረኝ። በራሪ ወረቀቱ መቅደድና መሳደብ የጀመረው የወረዳው ዋና አስተዳድሪ ሲሆን እሱን ተከትለው የሚረብሹ የተደረጁ ወጣቶችም ነበሩ። አሁን ህዝቡ ጣልቃ ገብቶ የሚረብሹ ወጣቶችን አስፈራርቷል። ዋና አስተዳዳሪውን በህዝብ ተሰድቧል። አሁን ሁኔታው ተረጋግተዋል። አቅጣጫው ግን በተደራጀ መልኩ የሚከናወን የዓዲግራትን ዓይነት ይመስላል። በአፅቢ ወንበርታ በጣም ብዙ የዓረና አባላትና ደጋፊዎች አሉ። ከወራት በፊት ህወሓትን ተቃውመው ዓመፅ አስነስተው እንደነበር ይታወሳል። አሁን ወደ አፅቢ እየሄድኩ ነው።

የተጋላቢጦሽ! ተቃዋሚ ፓርቲ ሰላምና ፀጥታ እንዲከበር ጥረት ሲያደርግ ገዥው ፓርቲ (መንግስት) ደግሞ ረብሻ ለመቀስቀስ ጥረት ያደርጋል፤ ስልጣኑ ተጠቅሞ የህዝብን ሰላም የሚበጠብጡ ወጣቶች በክፍያ ያደራጃል፣ ሰለማዊ ሰው እንዲደበድቡ ያበረታታል። ዓመፅ መቀስቀስ ለምዷቸው ይሆን?! ዓረና ግን ሰለማዊ ፓርቲ ነው። ለህዝብ ነፃነት ስንል እንደበደባለን፤ ለሰላም ስንል መስዋእት እንሆናለን። ምክንያቱም የሰላም መንገድ ሰለማዊ መሆን መሆኑ እንረዳለን። ትግሉ ስንጀምር ብዙ መስዋእትነት እንደሚያስከፍለን እናውቃለን። የአፅቢ ህዝብ እንደሚተባበረንም እርግጠኞች ነን።

በደሴ ፖሊስና የደህንነት ነን የሚሉ ግለሰቦች የሰላማዊ ሰልፉን ቅስቀሳ ለማደናቀፍ ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ ቀረ

$
0
0

April 5, 2014 8:00 am

የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ባልደረቦች ክስተቱን በፎቶግራፍ አንስተዋል

የአንድነት ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተውን የቅስቀሳ ቡድን ተግባር ለማደናቀፍ ፖሊሶችና ደህንነት ነን የሚሉ ግለሰቦች በስውር ቪዲዮ በመቅረፅ እና ስለሙስሊሙ የመብት ጥያቄ የሚስተጋቡ መፈክሮችን ለማስቆም ሙከራ አድርገዋል፡፡ በተለይም የከተማዋ የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊ ቅስቀሳው በተደረገባቸው ስፍራዎች በመገኘት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን ለማስፈራራትና ከቅስቀሳ ቡድኑ አባል ላይ የቅስቀሳ ቁሳቁስ ለመንጠቅ ሲሞከር በዝምታ ተመልክተዋል፡፡ ይህ ሁሉ የማደናቀፍ ሙከራ ቢደረግም ቅስቀሳው ተጠናክሮ ቀጥሏል፤  የደሴ ህዝብ ከአንድነት ፓርቲ ጎን በመሆን ቅስቀሳውን አጧጡፎታል፡፡

101

1015
1017

 

 

ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ! (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

$
0
0

መጠላለፍ ወደየትኛው ገደል እየመራን ነው?

Pro Mesfinየአዲስ አበባን መኪናዎች በተለይም በጫት የሚሽከረከሩት ታክሲዎችን በማንኛውም መስቀልኛ መንገድ ላይ ለአምስት ደቂቃ ቆሞ የተመለከተ ሰው በቀላሉ እንደሚረዳው “እኔ ካላለፍሁ ማንም አያልፍም!” በሚል መመሪያ መኪናዎቹ ተቆላልፈው እንዲቆሙ ማድረግ ነው፤ እንደሚመስለኝ የአባቶቻችንን ዕዳ እየከፈልን ነው፤ ዱሮ በደጉ ዘመን ሁለት ኢትዮጵያውያን መስቀልኛ መንገድ ላይ ሲገናኙ አንተ-እለፍ አንተ-እለፍ እየተባባሉ የሰማዕታቱንና የቅዱሳኑን ስም እየጠሩ ይገባበዙ ነበር! ይህ ባህል በጠንካራ የሥልጣኔ ላጲስ ተደምስሶ ጠፍቶ በምትኩ እኔ ካላለፍሁ ማንም አያልፍም መንገዱን ሁሉ መቆላለፍ አዲስ የመጠላለፍ ባህል እየተተከለ ነው፤ የመጠላለፍ ባህል የሚታየው በባቡር መንገዶች ላይ ብቻ አይደለም፤ በብዙ ነገር መጠላለፍ ባህል እየሆነ ነው! የዚህ ዝንባሌ መጨረሻው አሸናፊ የሌለበት ሙሉ ጥፋት ነው።

በመንገዶች ላይ ጥቂት በጫት የሚነዱ መኪናዎች በመቶ የሚቆጠሩ መኪናዎች እንዳይንቀሳቀሱ ለማድረግ ይችላሉ፤ ሲያደርጉም በየቀኑ እየታየ ነው፤ በማኅበረሰባዊና በፖሊቲካ ግንኙነትም አንድ ሰው የሚዘራው መርዝ የጊዜው ሁኔታ በሚፈቅድለት ፍጥነት የማኅበረሰቡን አባላት ያዳርሳል፤ እንቆቅልሹ እንደሚለው ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ! ማለት መርዝ፣ እሳት፣ ተላላፊ በሽታ በሕዝቡ ላይ ማሰራጨት ከአምስትና ከአሥር ዓመታት በኋላ ውጤቱ ምን እንደሚሆን መገመት አያቅትም።

ድብብቆሽ አይጠቅምም፤ሁለት ነገሮችን በግልጽ ማውጣት አለብን፤አንደኛ በአሜሪካና በአውሮፓ መሽጎ ፍርሃቱንና ሽቁጥቁጥነቱን ለመሸሸግ መርዙን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚረጨው ለምንድን ነው? አገዛዙ ይህንን የሚያደርግበት ምክንያት ግልጽ ነው፤ ከፋፍሎ የመግዛት ዘዴ ነው፤ ከአገዛዙ ጋር በሚደረግ ትግል ከታች ሆነው ከሥልጣን ውጭ የሆኑ ዜጎች በሥልጣን ላይ ከተቀመጡት ጋር እየተቆራቆዙና እየተጋጩ ናቸው፤ ይህንን እኔ የላይና-የታች ግጭት (vertical conflict) የምለው ነው፤ ከወያኔ/ኢሕአዴግ ጋር የሚደረገው ትግል ይህ ነው፤ ይህንን ለማክሸፍ ወያኔ/ኢሕአዴግ ትግሉን ከላይና-ታች አውጥቶ ወደጎን-ለጎን ግጭት (horizontal conflict) ሊለውጠው ይፈልጋል፤ ከወያኔ/ኢሕአዴግም ውጭ በጎሠኛነትና በሃይማኖት አክራሪነት የደነዘዙ ሰዎችም ትግሉን ጎን-ለጎን ሊያደርጉት እየሞከሩ ናቸው።

የፖሊቲካ ትግልን የሚመሩ ሰዎች በጎሠኛነትና በሃይማኖት አክራሪነት ስሜት እየተሳቡ ትግሉን የላይና-የታችነቱን ጠብቀው በተደራቢነት የጎን-ለጎን ትግሉን ይጨምሩበታል፤ ይህ ሲሆን ሀሳብ፣ ጉልበትና ሀብት ይከፋፈላል፤ ይበታተናል፤ ወደዓላማ ለመድረስም ያስቸግራል፤ ወያኔ ወደመጨረሻው ላይ ኢሕአዴግ ብሎ የሰየመውን ቀፎ አስቲፈጥር ድረስ በስሙ ውስጥ ኢትዮጵያን የሚያነሣ ነገር አልነበረውም፤ ወያኔን ለድል ያበቃው የማታለያ ስሙ እንደሆነ በበኩሌ አልጠራጠርም፤ ከሃያ ሁለት ዓመታት የጎሣ ሥርዓት በኋላ ኢትዮጵያ ቆስላለች እንጂ አልሞተችም፤ የአሐዝ ማስረጃ ለማቅረብ ባልችልም በብዙ ጎሣዎች መሀከል ጋብቻ እንደዱሮው እየቀጠለ ነው፤ ይህንን የቆየ የዝምድና ሰንሰለት ለመበጠስ የሚጥሩም አሉ።

ኒው ዮርክ ተቀምጦ ትኩስ ውሻ (ሆት ዶግ!) እየበላ ለእስላም ኦሮሞዎች የመገዳደያ መመሪያ የሚሰጥ ሰው የመንፈስ ጤንነቱን እጠራጠራለሁ፤ ይህንን የኒው ዮርክ ቀረርቶ ተከትሎ ሌላ የመጠላለፍ አዋጅ ሰማን፤ ቴዎድሮስ ካሣሁን ለአጼ ምኒልክ ስለዘፈነ ከበዴሌ ቢራ ፋብሪካ ጋር ለማስታወቂያ የገባው ውል ሥራ ላይ ከዋለ የበዴሌን ቢራ አንጠጣም ተባለና ማስታወቂያው ተሰረዘ ይመስለኛል፤ ማን እንዳሸነፈ ወደፊት ጊዜ ይነግረናል፤ አሁን ደግሞ ሌላ ማዘዣ ሰማሁ፤ “የስ” በሚለው ውሀ ጠርሙስ ላይ እንስራ የተሸከመችው ኮረዳ መስቀል አድርጋ ነበር፤ ልጅቱ ከነመስቀልዋ የምትታይበትን ውሀ እስላሞች አንገዛም ስላሉ ነጋዴዎቹ መስቀሉን አወለቁባት! ይህንን ማዘዣ ላወጣው አክራሪ እስላም ወረባቦ ቅዳሜ ገበያ ሄዶ እንዲጎበኝ አሳስበዋለሁ፤ ዛሬ ተለውጦ እንደሆነ አላውቅም እንጂ እኔ ብዙ ጊዜ ተመላልሼ እንዳየሁት የወረባቦ ኮረዶች ሁሉ ትልልቅ መስቀል በአንገታቸው ላይ ይታይ ነበር፤ መስቀል የእምነት መግለጫ ይሆናል፤ አያጠራጥርም፤ ግን መስቀል ጌጥም ይሆናል! መስቀል የናዚ ምልክትም ሆኖ ነበር! ለማናቸውም የዚህ ዓይነቱን መጠላለፊያ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚገምዱ ሰዎች ዓላማቸው ማንንም ለመጥቀም ሳይሆን ፍቅርንና ሰላምን ለማደፍረስ ነው፤ የኢየሱስ ክርስቶስ መሠረታዊ ትምህርት ክፉን በክፉ አትመልሱ ነውና ለተበጠሰው መስቀል አጸፋውን ለመመለስ ማሰብ አይገባም።

ከኒው ዮርክ የተሰማው ቀረርቶም ሆነ የመስቀል ማስወለቁ ጉዳይ የተከሰተበትን ጊዜ ልብ ልንለው ይገባል፤ እስላሞች ስለነጻነት የሚያደርጉት ንቅናቄ በጣም እየጋለ በመሄድ ላይ እያለ ክርስቲያኖችም የዜግነት ግዳጃቸው አድርገውት ድጋፋቸውን በሚሰጡበት ጊዜ ነበር፤ ይህ መሆኑ ጥርጣሬን ይጋብዛል፤ የገጠመውን የእስላሞችና የክርስቲያኖች ሰልፍ በማደፍረስ ወይም በመክፈል የሚጠቀም ማን ነው? የሚጎዳውስ ማን ነው? ሁሉም የትግል አጋፋሪዎች ለዚህ ጉዳይ የሚያስፈልገውን ክብደት ቢሰጡት ትግሉ በጎን-ለጎን እንዳይሄድና እንዳይዳከም ይረዳል፤ ከዚያም በላይ አክራሪነት የሚባለውና የሚያስከትለውም ሽብርተኛነት የሚመጣው እንዲህ እያለ ነው፤ እግዚአብሔር ከዚያ ያውጣን!

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
መጋቢት 2006

(ምንጭ: Mesfin Woldemariam Blog)

Entertainment: ቅዳሜን ከአንጋፋው ድምጻዊ መሐመድ ወርዲ ጋር

$
0
0

Mohamed Wordi
(አፈንዲ ሙተቂ)

አቦ የምን መጨነቅ ነው? የምን መጨናነቅ! የምን መተጋተግ! ተነሱ እስቲ አንዴ ከመሐመድ ወርዲ ጋር ዓለማችንን እንቅጭ! ተነሱ እስቲ ከዚህ ጭቅጭቅና ጭንቅንቅ የበዛበት ዓለም ወደ ፍቅር ሐድራ እንሰደድ! ቅዳሜያችንን ከመሐመድ ወርዲ ጋር ቅዳሜ እናስመስል! በ“ገመር ቦባ” ድብርቱን እናባርር! በ“ቲስዓተ ዐሸር ሰና” የህይወት ምርጫንችን እናሳምር! በ“ሱድፋ” እድላችንን እንሞክር! በ“ፉአዲ ሐኒን” ውበታችንን እንለካው! በ“አነ ማ በንሳክ” ቃልኪዳናችንን እናድስ!

በየፌርማታውና በካፍቴሪያው ተደብተህ የተጎለትከው ሆይ! እስቲ ለዛሬዋ ቀን ተከተለኝ፡፡ በሓሳባችን ወደ ውቢቷ “ኻርቱም” በርረን በሐሴት አውድማ ላይ ውበት ሲመላለስ አብረን እናያለን፡፡ የምስራቅ አፍሪቃ ህዝቦች የጋራ ጌጥ የሆነው ሙሐመድ ወርዲ ቅዳሜአችንን ቅዳሜ ሊያስመስለው ተዘጋጅቷል፡፡
——–
በቅድሚያ የቱን ልጋብዝህ/ልጋብዝሽ? ከ“አነ ዐርፈክ ያ ፉአዲ” ብጀምርልህ ይከፋሃል? እንዴት ሆኖ ነው የሚከፋህ ጃል?.. እንዲያውም ዜማውን በደመ-ነፍስህ ጭምር ስለምታውቀው በቅድሚያ እርሱን ብጋብዝህ ነው ቅዳሜያችን የሚያምርልን፡፡…. ምክንያቱም ዜማውን የኛ ውድ የሆነው ጥላሁን ገሠሠ ሲያዜመው ሰምተህዋልና ነው፡፡ ጥላሁን እንዲህ ብሎ ሲዘፍን ሰምተኸው አልነበር?

አንቺ ከቶ ግድ የለሽም
ስለፍቅር አይገባሽም
ሁሉን ነገር እረስተሽው
ችላ ብለሽ ስለተውሽው
ቻልኩት ፍቅር ለብቻዬ
አዎን! እርሱን ነው የምልህ ወዳጄ! ሙሐመድ ወርዲ በዚሁ ዜማ ምን ብሎ ነበር መሰለህ?

“አነ ዐርፋክ ያ ፉአዲ
ጠል ዐዛበክ ዋ ሱሃዲ
ዋ ሽጃያ አነ ዐዛቢ”

ነበር ያለው፡፡ ታዲያ ሙሐመድ ወርዲ የዘፈነውን ጋሽ ጥላሁን እንዲሁ በጋጠወጥነት ወደ አማርኛ የመለሰው እንዳይመስልህ! የወርዲ ቡራኬ አለበት፡፡ በቀዳማዊ ኃይለሥላሤ ዘመን የካርቱም መንገድ ለኛ የውሃ መንገድ ነበረ፡፡ ለሱዳኖችም ከዋዲ ሃልፋ ይልቅ ሸገር ትቀርባቸው ነበር፡፡ እናም በዚህ ምልልስ መሀል የኛዎቹ አንጋፋዎች (ጥላሁን ገሠሠ፣ ምኒልክ ወስናቸው፣ አለማየሁ እሸቴ፣ ዓሊ ሸቦ፣ ዓሊ ቢራ ወዘተ..) እና የሱዳኖቹ ገዲም አርቲስቶች (አሕመድ አል-ሙስጠፋ፣ ሰይድ ኸሊፋ፣ ሙሐመድ ወርዲ፣ አብዱልከሪም አል-ካብሊ፣ አብዱል ዓዚዝ አል-ሙባረክ ወዘተ…) የአንድ ቤተሰብ ልጆች ሆነው ነበር፡፡ ሱዳኖቹ ያዜሙትን የኛዎቹ ወደ አማርኛ፣ ኦሮምኛና ሶማሊኛ እየመለሱ ይጫወቱታል፡፡ የኛንም ዘፈን ሱዳኖች በቋንቋቸው እየተረጎሙ ይዘፍኑታል፡፡ አንዳንዴ ዕድል ሲገጥማቸው ሁለቱም አንዱን ዜማ በአንድ መድረክ ላይ በየቋንቋቸው ይጫወቱታል፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት ነው እንግዲህ የሙሐመድ ወርዲ “አነ ዐርፈክ ያ ፉአዲ” ወደ አማርኛ የተመለሰው፡፡ አገኘኸኝ አይደል? እንዲያ ነው ነገሩ ወዳጄ! እነ ጋሽ ጥላሁን እንደ አሁኖቹ ዘፋኞች (አንዳንዶቹን ማለቴ ነው) የሱዳንና የፈረንጅ ዜማን ወደ አማርኛ እየገለበጡ “የራሴ ድርሰት ነው” ብለው ሊያሞኙን አይከጅሉም፡፡ ዋናው አርቲስት ባለበት ጭምር እየዘፈኑ ያሳዩትና “እንዴት ነው! አበላሽቼብህ ይሆን?” በማለት ምክርና እገዛ ይጠይቁታል፡፡ ሱዳናዊው አርቲስትም በሰማው ነገር ላይ የራሱን አስተያየት ይሰጣል፡፡ የኛዎቹም ከሱዳናዊያኑ አርቲስቶች የሚሰጣቸውን አስተያየት ተንተርሰው እጅግ የተሻለ ስራ ይሰሩና ህዝቡን እንካችሁ ይሉታል፡፡ ለዚያም ነበር ስራው የሚዋጣላቸውና ዘመን ተሻጋሪ የሚሆንላቸው፡፡
*****

አዎን ወዳጄ! ኑሮ አይሞላም፡፡ ላይሞላ ነገር ሁልጊዜ “ተዐብ ዘምዛሚ” መሆን አንችልም፡፡ ሁል ጊዜ መነጫነጭ ይገድለናል፡፡ “ራሃ” እና “ፌሽታ” በአቅማችን ማድረግ አለብን! በዛሬዋ ቀን ጭንቀትን ድራሽ አባቱ እናጥፋው፡፡ እናም የወርዲ ግብዣዬን ልቀጥልልህ!

በርካታ የሀገራችን የሙዚቃ ወዳጆች ከመሐመድ ወርዲ ዜማዎች መካከል ለ“ገመር ቦባ” እና ለ“ቲስዐተ ዐሸር ሰና” (ብዙዎች የሚያውቁት “ሰበርታ” በሚለው ስም ነው) ልዩ ፍቅር አላቸው፡፡ እኔ ግን ብዙ ልጠራልህ እችላለሁ፡፡ በተለይም “ሱድፋ”፣ “ቃሲ ቀልበክ”፣ “አልሀወል አወል”፣ “አነ ማ በንሳክ”፣ “አዚብኒ ወተፈነን”፣ “አንናስ አል-ጊያፋ”፣ “ሐረምተ አድ-ዱንያ”፣ “ያ ኑረል ዐይን”፣ “ሸተል ዘማ”፣ “አል-ሙርሳል” የመሳሰሉትን በአንደኛ ደረጃ አሰልፋቸዋለሁ፡፡ ታዲያ ከዚህ ቀጥዬ የትኛውን ልጋብዝህ?… “ሱድፋ”ን ልመርጥልህ ወድጄ ነበር፡፡ ሆኖም ቪዲዮውን ከበይነ መረብ (ኢንተርኔት) ላገኘው አልቻልኩም፡፡ ስለዚህ በቅርበት ያገኘሁትንና ሙሐመድ ወርዲ የዛሬ 18 ዓመት ገደማ በኛ ስታዲየም የተጫወተውን “ዐዚብኒ ወተፈነን”ን ልጨምርልህ፡፡ እግረ መንገድህን የኛ ህዝብ ወርዲን ምን ያህል እንደሚወደው ታይበታለህ፡፡

ዐዚብኒ ወዚድ ዐዘባ ዩምኪን ገልቢ ይክሳዚይክ
ዜይመን ሳኒ ገልበክ ዩምኪን ገልቢ ይክሳዚክ፡፡
አዚብኒ ወተፈነን ፊ አልዋን ዐዛቢ
ማ ቲምሳሕ ዲሙዒ ማ ቲርሐም ሸባቢ፡፡
ኸሊኒ ፊሹጁኒ ዩምኪን ገልቢ ይክሳዚይክ
ዜይ መንሳኒ ገልበክ ዩምኪን ገልቢ ይክሳዚይክ፡፡
ቪዲዮውን በሚከተለው ሊንክ ላይ ተመልከተው….

በመሀሉ የዛሬዋ ቅዳሜ ምርጫችን ስላደረግነው ሙሐመድ ወርዲ ታሪከ-ህይወት ጥቂት ሐተታ ካስፈለገህ እነሆ ልበልህ ወዳጄ!

ሙሉ ስሙ ሙሐመድ ዑስማን ሳሊሕ ወርዲ ነው፡፡ እርሱ ግን “ሙሐመድ ወርዲ” ወይንም በአጭሩ በቤተሰቡ ስም “ወርዲ” ተብሎ ነው የሚታወቀው፡፡ የተወለደው እ.ኤ.አ. በ1932 ዋዲ ሀልፋ በተሰኘው ሰሜናዊው የሱዳን ክፍለ ሀገር፣ “ሱወርዳ” በተባለች ትንሽዬ የገጠር መንደር ውስጥ ነው፡፡ እናቱ የኑቢያ ተወላጅ ስትሆን አባቱ ዐረብ ነው፡፡ ወርዲ የሙት ልጅ ነው፡፡ ሁለቱንም ወላጆቹን በልጅነቱ ነው ያጣው፡፡ በመሆኑም በዘመዶቹ ጥበቃ ስር ሆኖ ነው ያደገው፡፡ ትምህርቱን በዋዲ ሀልፋ እና በካርቱም ተከታትሏል፡፡ የተወለደበትን ሀገር እስከ 1956 በመምህርነት ሙያ ካገለገለ በኋላ በወቅቱ ይሞካክራቸው የነበሩት ዘፈኖች በኦምዱርማን ሬድዮ ጣቢያ ተቀርጸው በመተላለፋቸው በህዝብ ልብ ውስጥ ገባ፡፡ ያገኘው የሞራል ድጋፍ ማነሳሻ ስለሆነው መምህርነቱን ትቶ የአርቲስትነቱን ጎራ ተቀላቀለ፡፡ ከዚያም ሱዳኖች ከሚያፈቅሯቸው ቁንጮ ዘፋኞቻቸው አንዱ ለመሆን በቃ፡፡

ወርዲ በህይወቱ የተረጋጋ ኑሮ አልኖረም፡፡ በሱዳን የተለዋወጡት መንግሥታት በተቃዋሚነት እየፈረጁት አንገላተውታል፡፡ በመሆኑም ለሀያ ዓመታት ያህል በካይሮና በለንደን ነው የኖረው፡፡ በ2002 ግን ወደ ሀገሩ በክብር ተመልሷል፡፡ ወርዲ በሙዚቃው ዕድገት ላደረገው አስተዋጽኦ ከካርቱም ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተሸልሟል፡፡ ከልዩ ልዩ የአውሮጳ፣ አፍሪቃና እስያ ሀገራትም ሽልማቶችን ተቀብሏል፡፡ ሱዳኖች እ.ኤ.አ. በ2000 ባደረጉት ምርጫ “አል-ገመር ቦባ” የተሰኘው ዘፈኑ የክፍለ ዘመኑ ምርጥ “ነጠላ ዜማ” ተብሎ ተመርጧል፡፡ መሐመድ ወርዲ በመጨረሻዎቹ ዓመታት በደረሰበት የጤና መታወክ ሁለት ኩላሊቶቹ ከጥቅም ውጪ ሆነው ነበር፡፡ ይኸው የኩላሊት ህመም ፋታ ነስቶት በየካቲት ወር 2012 ከዚህች ዓለም አሰናብቶታል፡፡

መሐመድ ወርዲ ከብዙ በጥቂቱ እንዲያ ነበር፡፡ አሁን በርሱ ዘፈኖች “ራሓ” ማድረጋችንን እንቀጥል፡፡

—-
ታሕሳስ 6/2013

ምን ይደረጋል? እናት አገር ትኑር!

$
0
0

ከጌታቸው ሽፈራው

የመመረቂያ ጽሁፌን ለመጨረስ ደፋ ቀና እያልኩ ባለሁበት ወቅት ነው አንድ የማላውቀው ስልክ የተደወለልኝ፡፡ ይህ ስልክ አባል ባለመሆኔ ስራ እንደማላገኝ ተስፋ ወደመቁረጥ በተቃረብኩበት ወቅት ለስራ እንደምፈለግ አበሰረኝ፡፡ ስልኩ ከኢመድኤ (INSA) መሆኑ ተነግሮኛል፡፡ ይህን መስሪያ ቤት ስም ፈጽሞ ሰምቼው አላውቅም፡፡ ለጓደኞቼ ሳወራቸው ከእኔ በፊት አብዛኛዎቹ ተደውሎላቸው እንደነበር አጫወቱኝ፡፡ የህወሓት፣ የብአዴን፣ የኦህዴድ፣ የደኢህዴን ልጆች እርስ በእርሳቸው እንደተጠቋቆሙም ወሬ ደረሰኝ፡፡ በስተመጨረሻ እኔም መጠራቴ ነው፡፡ ሌላኛው ግራ የሚያጋባው ወሬ ግን መስሪያ ቤቱ የስለላ ተቋም እንደሆነ መስማቴ ነው፡፡ ሁለት ሆድ ሆንኩ፡፡ የኋላ ኋላ አይቶ መውጣቱ እንደሚሻል ወሰንኩ፡፡ አንድ በጣም የሚቀርበኝ ጓደኛዬ ስለተቋሙ ካጫወተኝ በኋላ እንዲቀጥሩኝ አባል መሆኔን (ሸውጄ) እንድነግራቸው አግባባኝ፡፡ አልፈለኩም፡፡
ethiopia first
ለጥያቄ የተቀጠርንበት ቀን ደረሰ፡፡ ለፈተና ቀረብን፡፡ ጥያቄዎቹ ከጠበቅናቸው በላይ ናቸው፡፡ ከጠበቁት በላይ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት በርካታ ጥያቄዎች ቀርበውልኛል፡፡ ከዚህ መርህ ያፈነግጣሉ የተባሉ ጓደኞቻችን ሳያልፉ ቀርተዋል፡፡ ፈተናውን አልፈን ለስልጠና በገባንበት ወቅት ደግሞ ሌላ ተስፋ ሰጭ ጉዳይ ተከሰተ፡፡ በነጻነት መከራከር ቻልን፡፡ በአንድ ትምህርት ዘርፍ (ፖለቲካል ሳይንስ) ለቅጥር ያለፍነው 12 ወጣቶች ሌሎቹን እንድናስተባብር በየ ውይይት ክበቡ ተሰባጠርን፡፡ ኢንሳን ብቻ ሳይሆን ፖለቲካውን የሚርቁትን ይቀይራሉ ተብለንም ‹‹12ቱ ሐዋሪያት›› የሚል ስም ወጣልን፡፡ በኋላ አንዷ የውጭ አገር እድል አግኝታ ስትወጣ ‹‹ይሁዳዋ!›› ብለን ተሳልቀንባታል፡፡ ይሁዳ ያወቀው ይህኔ ነው፡፡ ነገር ሳይበላሽና ሳይቆስሉ ቦታ መያዝን የመሰለ ነገር የለም፡፡

ስልጠናውን ጨርሰን ለአንድ አመት ያህል በነጻነት ሰራን፡፡ የማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆን ይቻላል፡፡ ነገር ግን ይህ አቋም ስራ ላይ ማንጸባረቅ አይፈቀድም ተባልን፡፡ ይህ ለእኛ ትልቅ ነገር ነበር፡፡ አሁን አሁን ሳስበው ግን ለኢንሳዎች ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ማለት ኢዴፓ ብቻ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ምክንያቱም አንዱ ‹‹አለቃ›› ስለጉዳዩ ተናግሮ ሳይጨርስ ‹‹ይህን ስል ግን የኢዴፓን አቋም እዚህ (ስራ) ላይ ማንጸባረቅ ይቻላል ማለት አይደለም፡፡›› ሲል አስታውላለሁ፡፡

ብቻ ያ ጊዜ ለመስሪያ ቤቱ መልካም አመለካከት የነበረን ጊዜ ነው፡፡ ጅራትና ምንድን ነበር ወደኋላ የሚመጣው? በእርግጥ ከዚህ በፊት ኢንሳ ጠለፋና ሌሎቹንም ነገሮች እንደሚሰራ መስማት ጀመረናል፡፡ ስለ ጉዳዩ እርግጠኛ ባንሆንም የት ነው የምትሰራው ተብሎ ‹‹ኢንሳ!›› ለማለት የሚያኮራ አልነበረም፡፡ ብዙዎቹ ጓደኞቻችን ‹‹ሰላይ!›› እንመስላቸው ነበር፡፡ የእኛ አገር ችግር ይህ ነው፡፡ ስለላን ገዥዎች አበላሸተውታል፡፡ ህዝቡም ሆነ ሰላይን መልሶ መሰለል የሚባል ነገር አያውቅም፡፡ ዝም ብሎ መራቅ፡፡ ዝም ብሎ ማማት ብቻ ነው፡፡

አሁን ጅራትና ጉድ ጭራሹን እየፈጠጡ መጡ፡፡ የፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆን አትችሉም ተባለ፡፡ መጀመሪያ የነበረን ተስፋ ሁሉ እንደገና ተስፋ አጣ፡፡ ይህ በሆነበት ወቅት ነው፣ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ እንደ አንዳች ክፉ ነገር የሚጠሉትና የሚጠየፉት አቶ መለስ ሰንደቅ አላማውን ከላይ ወደታች ገለበጡት፡፡ እኔም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ‹‹ሰውዬው ለምን ሰንደቅ አላማውን ገለበጡት?›› የሚል ጥያቄ አነሳሁ፡፡ ከቀናት በኋላ ይህን ሰንደቅ አላማው ላይ የጻፍኩትን ትንሽዬ ነገር ተከትሎ 12 አስቂኝ ከስሶች ቀረቡብኝ፡፡ አብዛኛዎቹ ህገ መንግስቱን ካለመቀበል፣ የፖለቲካ ቡድኖች (እነማን እንደሆኑ እነሱው ይወቁት) አባል ሆነሃል እና ጽንፈኝነት ጋር የተለነቀጡ ናቸው፡፡ በዝርዝር የአሰብ ወደብን የኢትጵያ ነው ብለሃል፣ ኢትዮጵያ የውጭ ብድር አለባት ብለሃል፣ የጋዳፊን ፎቶ ግራፍ አጋርተሃል (ሸር አደርገሃል)፣ ከጉራፈርዳ ስለተባረሩት አርሶ አደሮች ጽፈሃል፣ ኢህአዴግን ግንባራም ብለሃል……የሚሉት ይገኙበታል፡፡

በእነዚህ ክሶች መሰረትም ለ2 ወራት ያህል ከስራ ታገድኩ፡፡ በዚህ ወቅትም ለክሶቼ መልስ እንድሰጥ ታዝዣለሁ፡፡ እናም ክሱ እንዲነሳልኝ የክሶቹን ፍሬ ቢስነት ጠቅሼ ተከራከርኩ፡፡ አይ እኔ ሞኙ! ህግ በሌለበት፡፡ በዚህ ክርክር የዲስሊን ኮሚቴ አባል ናቸው የተባሉ የህወሓት አባላት ልክ እንደ ከሳሽ ‹‹እንዴት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ታንቋሽሻለህ›› የሚል ክስ አቅርበው ተከራክረውኛል፡፡ የብአዴን አባላት ደግሞ እነሱን ተከትለው አስተጋብተዋል፡፡ ያም ሆነ ይህ ‹‹በከፍተኛ ወንጀል›› ተባረርኩ፡፡ በዚህ ወቅት አንድ የብአዴን ካድሬ ያለኝ መቼም ሊረሳኝ አይችልም፡፡ የቅርብ አለቃዬ ስለነበር ስለ ነበረኝ ስነምግባር፣ ስለ ስራ አፈጻጸም፣ ክስ የተባሉት የማያስከስሱኝ መሆኑን ገልጬ መባረሬ አግባብ አለመሆኑን አሳወቁት፡፡ እሱም ‹‹ዋናው ታማኝ መሆን ነው፡፡›› ብሎኝ አረፈው፡፡ ኢህአዴግ ብትሆን አትባረርም ነበር ለማለት ነው፡፡ የሚገርመው ይህ ካድሬ ፌስ ቡክ ላይ እራሱን ፈላስፋ አድርጎ ስለነጻነትና ፍትህ ሲዛላብድ የሚውል መሆኑ ነው፡፡

ከተባረርኩ ከሳምንት በኋላ መሰናዘሪያን ተቀላቀልኩ፡፡ ከወራት በኋላ (ጥቅምት 20) ደግሞ አቶ መለስ የማይወዱት ሰንደቅ አላማ በዓል ተከበረ ተባለ፡፡ በእውኑ ግን ተከብረው የዋሉት ሟቹ ሰውዬ ናቸው፡፡ ጥቅምት 21 መሰናዘሪያ በፊት ገጽ አንድ ጽሁፍ (የእኔው ነው) ይዛ ወጣች፡፡ መለስ የገለበጡትን ሰንደቅ አላማ አንግባ ‹‹እውን ኢህአዴግ ሰንደቅ አላማውን ያከብረዋልን?›› የሚል ነው፡፡ መሰናዘሪያ በሳምንቱ አልተመለሰችም፡፡ አታሚው ኢህአዴጎችን ሰንደቅ አላማው ላይ የተጻፈው ጽሁፍ ስላስቆጣቸው እንዳያትም እንደነገሩት አስታወቀን፡፡ በቃ ዳግም ተባረርኩ ማለት ነው፡፡ አሁን ሌላ ስራ መፈለግ ይጠበቅብኛል፡፡ የኢንሳን ልምድ ሳሳይ ደግሞ በርካቶች ይበረግጋሉ፡፡ በግል ሚዲያው ብጽፍም በቋሚነት ለማሰራት አቅም አልነበራቸውም፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ከገዥው ፓርቲም በላይ ለሚዲያውም ሆነ ለሰራተኛው በዝባዥና ገዳዮች ሆነው አግቻቸዋለሁ፡፡
እንዲህ እንዲህ ስል ለሁለት አመት ያህል ቋሚ ስራ መፈለግ ነበረብኝ፡፡ አራት አመት ያህል ደግሞ ከቤተሰብ ጋር ተቆራርጫለሁ፡፡ 18 አመት ያህል አስተምራኝ፣ ስራ ይዠያለሁ ያልኳትን እናቴን እንዴት ተባርሬያለሁ ልበላት? በፖለቲካ አቋሜ ተባረርኩ ብላት ደግሞ ከዚህ ሁሉ የባሰ ይሆናል፡፡ እናም ዝም ብዬ ስራ ፍለጋ መኳተኑን ያዝኩት፡፡ መነኩሴዋን እናቴን አይኗን ሳላያት አራት አመት ሞላ፡፡ ዛሬ ነገ እሄዳለሁ ስል ቀኑ ነጎደ፡፡ ከዛሬ ነገ አግይቼ አይኗን አያታለሁ ያልኳት እናቴም እንደሳሳኋት፣ እሷም እንደሳሳች ለወዲያው ላንገናኝ ተለያየን፡፡ እናቴ አለፈች፡፡ ያለ አግባብ የተፈናቀልኩበትን ስራ ልይዝ፣ ከያዥኩ ከጥቂት ጊዜም በኋላ ‹‹ልረጋጋ!›› ላይ ታች ስል ለረዥም ጊዜ የተለየኋት እናቴ አመለጠችኝ፡፡

በእርግጥ እናቴ ወርቅን በባሌስትራ ከሚቀይሩት ወገን አይደለችም፡፡ መሬት አልሸጠችም፡፡ ህዝብን በጠባብ ማንነት አልከፋፈለችም፡፡ አገር አላስገነጠለችም፡፡ ሰንደቁን አላዋረደችም፣ አልዘቀዘቀችም፡፡ የህዝብ መብት አላፈነችም፡፡ የህዝብ ገንዘብ ወደ ውጭ አላሸሸችም፡፡ ንጹሃንን አልገደለችም፣ አላሰረችም፡፡ አላፈናቀለችም፡፡ እናቴ ንጹህ ነች፡፡ የእሷ ነፍስ የገነት ነፍስ ነች፡፡ ሌሎች ግን የሞት ሞታቸውን ሞተዋል፡፡ ትውልድም አጥንታቸውን እንደረገመ ይኖራል፡፡

እኔም እላለሁ፡፡ ሞት ማለት የሞት ሞት ሲሆን ነው፡፡ ይህን እናቴ አልሞተችውም፡፡ ምስኪኗ ወላጅ እናቴ የክብር ሞቷን ስትሞት አሁን ለእኔ የቀረኝ አንዲት እናት ብቻ ናት፡፡ እናት አገር ኢትዮጵያ! አገር ብትኖር ወላጅ እናቴ ተቀብራበታለች፡፡ እኔም አልቅሸበታለሁ፡፡ አዎ! ወላጅ እናት ባትሞት እጅጉን መልካም ነበር፡፡ ከሞተች ግን ምን ይደረጋል? ብቻ እናት አገር አትሙት!

እናቴ ሆይ! አምባገነኖቹ ፊቴ ላይ የደቀኑብኝን አቀበት ለመውጣት ስጥር አንቺ አምልጠሽኛል፡፡ አሁን ብችል እናት አገርን ለማዳን ከሌሎቹ ጋር ሆኜ ጠጠር ለመጣል፣ ጥረቴ ለዚህ ባይበቃ እንኳ የራሴን መብት ለማስከበር፣ ይህንን ደግሞ ባልችል ሆድ አደር ላለመሆን አቀበቱ ላይ ነኝ፡፡ ሞት አይቀርምና አንድ ቀን እንደምሞት አውቀዋለሁ፡፡ የሞት ሞት መሞት ግን አልፈልግም፡፡ ደግሞም ከአንቺ ጋር ያለያየኝን አቀበቱን ወጥቼ ሜዳው ሳልደርስ ባልከተልሽ ደስ ይለኛል፡፡ በዚህ አንቺም እንደማትቀየሚኝ አውቃለሁ፡፡ እስከዚያው ግን አምላክ ነፍስሽን በገነት ያኑራት!


አቡነ ዘካሪያስ በሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ተቃውሞ ገጠማቸው (ቪዲዮ ይዘናል)

$
0
0

አቡነ ዘካሪያስ በሚኒሶታ ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ከፍተኛ ተቃውሞ ደረሰባቸው። በቪድዮ ተደግፎ በደረሰን መረጃ መሠረት ምዕመናኑ “ጎጃም ላይ የተሰረቀው ገንዘብ ሚኒሶታ ላይም አይደገምም” በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አሰምተውባቸው አንዳችም ንግግር ሳያደርጉ ከደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ እንዲወጡ መደረጋቸው ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም ሲያስተምሩ “በኢትዮጵያው ሲኖዶስ ስር ካልገባችሁ ኢትዮጵያ መቀበር የለም”፣ የሚሶታውን መድሃኔዓለም ቤ/ክ “በረት” ሲሉ ገልጸውታል በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ የደረሰባቸው አቡነ ዘካሪያስ ከአቡነ ማርቆስ ጋር በመሆን ቤተክርሲያኑ በመንታ መንገድ ላይ ባለበት ሰዓት የመጡት ለመከፋፈል ነው በሚል ለሰላም እና ለአንድነት የቆሙ ምዕመናን ይከሳሉ። የአቡነ ዘካሪያስን የአቡነ ማርቆስን የሚኒሶታ ደብረሰላም ቤ/ክ የተቃውሞ ውሎ የሚያሳይ ቪድዮ ይመልከቱ፤ ከታች ደግሞ ለሰላም እና ለአንድነት የቆሙ ም ዕመናን ያቀረቡትን ወቅታዊ ጽሁፍ ይመልከቱ አቡነ ዘካሪያስ የጎጃምን ሃገረ ስብከት በሚመሩበት ወቅት ስላጎደሉት ገንዘብ በቪኦኤ ሲጠየቁ “ገንዘቡ ጎሎብኛል፤ ለምኜ እከፍላለሁ” ማለታቸውን ብዙዎች ያስታውሱታል።

አቡነ ዘካሪያስን አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፤ እንዳገኘናቸው ይዘን ለመቅረብ እንሞክራለን።

በእግዚአብሔር ስም አሜን። 4/5/2014

ለሰላምና ለአንድነት የቆሙ ምእመናን
አንድነትን፣እርቅንና ሰላምን ከራሳችሁ ጀምሩ!

በኢተዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ እንደዚህ ዘመን ትልቁ ትንሽ የሆነበት ኃይማኖቱን በእለት ጥቅምና ሹመት ለውጦ ሁሉም ከትልቅ እስከትንሽ ለሆዱ ያደረበት ጊዜ የለም። የቀደሙት አባቶቻችን የቤትከርስቲያንን መብትና ሉአላዊነት ከማስከበር አልፈው ለአገራቸውም አርበኛና ሰማዕታት በመሆን
በታሪ የላቀች ሉዐላዊት ሃገርንና ርትዕት ኃይማኖትን አቆይተውልናል። ራቅ ያለውን ታሪክ ትተን የቅርቡን የጣሊያን ፋሺስት ወረራ ዘመን እንኳን ብናስታውስ ብዙ ካህናት አባቶች ከጀግኖት አርበኞች ኢትዮጵያውያን ጋር ሆነው ለአገራቸውና ለኃይማኖታቸው ሰማእትነትን ተቀብለዋል። ታላቁ ጻድቅና
አርበኛ ሰማእት ቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ የሰሩት እጅግ አስደናቂ ታሪክ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው።

መንጋውን እንዲጠብቅ በወንጌል የታዘዘ እረኛ ሕይወቱን እስከ ሞት ድረስ ለበጎቹ አሳልፎ ይሰጣልና ኅዝቧም ምድሪቷም አይገዙልህ ብለው ጠላትን በማውገዝ በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ የማይረሳ አኩሪ ተጋድሎን በደም ቀለም ጽፈውልን አልፈዋል። ዛሬስ? ንዑዳን ክቡራን የተባሉ አባቶች ለስማቸውና ለክብራቸው የሚገባ ሥራ እየሰሩ ይሆን?

በአደባባይ ቤተክርስቲያን በአላውያንና በመናፍቃን ሹማምንት ስትሰደብ፣ገዳማቶቿ ሲደፈሩና ሲቃጠሉ፣ ካህናትና ምእመናን ሲታረዱ፣ ጥንታዊትና ታሪካዊት የሆነች ሃገርን ያቆየች ቤተክርስቲያን እንደወፍ ዘራሽ የትም ከበቀሉ ድርጅቶች ጋር ትቆጠሪያለሽ እንደ አዲስ ተመዝግበሽ ፈቃድ አውጥተሽ ብቻ ነው
መንቀሳቀስ የምትችይው ስትባል፣ ቤተክርስቲያን የነፍጠኛ ዋሻ ናት እያሉ በገሃድ አላውያኑ ሲሳደቡ፣ መለኪያው ኦርቶዶክስ የነበረውን ሰብረነዋል እየተባለ ሲፎከር የዛሬዎቹ አባቶች ጳጳሳት ምን እየሰሩ ነበር? ይሆን? እውነቱን እውነት ሐሰቱን ሐሰት ማለት ለምእመናን ብቻ የተጻፈ የወንጌል ቃል ነው እንዴ?

ሰሞኑን በዚህ በሜኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በጥቂት አማጽያን ግለሰቦች የቤተክርስቲያናችንን ሰላምና አንድነት ለማደፍረስ ተጠንሶ እየተካሔደ ባለው ስርዓት አልበኝነት አንዳንድ ከኢትዮጵያ የመጡና እዚሁ የከረሙ ‘ጳጳሳት’ ቢመከሩና ቢዘከሩ እምቢ ብለው በእሳት ላይ ቤንዚን ለማርከፍከፍ መጥተዋል። የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች እንዲሉ ለ3 አመታት ያህል ሲለፋበትና ከፍተኛ ውጣ ውረድ ሲደረግበትቆይቶ ወደ ፍጻሜ ደርሶ የነበረውን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲይያን የሰላምና የእርቅ ሂደት በኢትዮጵያ ሥልጣን ላይ ካለው ኃይል ጋር በመሆን ካፈረሱ በኋላ አሁን ደግሞ የቤተክርስቲያን አንድነትና ሰላም ፈላጊ መስለው ምእመናንን ለመከፋፈልና የቤተክርስቲያንን ችግር ከድጡ ወደማጡ ለማውረድ የሾማቸውን ኃይል ተልዕኮ ለመፈጸም እየዳከሩ እገኛሉ።

በቤተክርስቲያን አባቶች ዙሪያ ያለው ልዩነት በግልጽ በፖለቲካ ጣልቃገብነት የተፈጠረ መሆኑን ሁላችንም ጠንቅቀን እናውቃለን። ይሁን እንጂ የችግሩን መንስዔ በመሸፋፈን ምእመናን እውቀት አንሷቸው የቤተክርስቲያን ስርአት የተበላሸ ይመስል የራሳቸውን ጥፋትና ችግር የችግሩ መንስ ኤ የሆነውን ኃይል
በሚቃወሙ ምእመናን ላይ በመላከክ ለማጭበርበር ሲሞክሩ ይታያሉ። ወያኔ ያበላሸውን ቀኖና ቤተክርስቲያን ወደጎን በመተው፤ ለሥልጣንና ለጥቅም አድረው ዋናውን ችግር ለመፍታት ከመንበርከክ ይልቅ እናንተም እንደእኛ ለሆዳችሁ እደሩ፣ ባንዳ ሁኑ እያሉ የማይገባ ነገር ሲናግሩና ሲሰሩ ማየት እጅጉን ያሳዝናል።

በመሰረቱ አባቶች እንደ አባቶች ሊከበሩና ሊታዩ የሚችሉት እንደ አባት ሆነው የሃገርና የቤተክርስቲያን ጠላት ከሆነው ኃይል ራሳቸውን ሲያገሉ አልያም ያልፍርሃት ክፉ ስራውን ሲቃወሙ ነው። ቄሱም ዝም መጽሐፉ ዝም ከሆነ ግን ቄሱም ቄስ አይደለም መጽሐፉም መጽሐፍ አየደለም!!!

በፖለቲካኖች ታቅዶ ቤተክርስቲያናችንን ለመንጠቅ እየተካሔደ ያለውን ታላቅ ሴራ ለማክሸፍ እየተደረገ ባለው ትንቅንቅ ላይሁላችሁም በመገኘት ምንደኞችን እንድናሳፍር ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪቃል በደሴ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል

$
0
0
Millions of voices for freedom – UD

የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪቃል በደሴ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተና አመራሮችና የዞን አመራሮች በሰልፉ ለተሳተፈው የደሴ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ #Dese #UDJ “እድሜ ለአንድነት አስተነፈሰን” የደሴ ነዋሪ.

የደሴው ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ እየተካሔደ ቢሆንም የአዲስ አበባው ዋና ጽ/ቤት ከፍተኛ በሆነ የፖሊስ ሀይል ተከቧል፡፡

ተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከሚስተጋቡ መፈክሮች ውስጥ
- መሬት ለህዝብ ይመለስ
- ጭቆና በቃን
- ድል የህዝብ ነው
- በግፍ የታሰሩ ይፈቱ

- አንድነት ኃይል ነው
- የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ

1025

19034

1024

 

11 100

10250312_615933295158275_1305539042701871448_n

በአማራ ክልል ከአምስት ሺህ በላይ ዜጎች ሜዳ ላይ ወድቀዋል ሰማንያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል በጀት ስለሌለን ምንም ያደረግነው የለም

$
0
0

 

በአማራ ክልል ከአምስት ሺህ በላይ ዜጎች ሜዳ ላይ
ወድቀዋል ሰማንያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል
በጀት ስለሌለን ምንም ያደረግነው የለም
አቶ አማረ በሪሁን የወረዳ የብአዴን ኃላፊ
በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ በመቄት ወረዳ ቀበሌ 0 40 ልዩ ቦታው አሳሳ በተባለ ቦታ መጋቢት 20 ቀን 2006 ዓ. ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ የተነሳው እሳት አደጋ ለሰላሳ ድስት ሰዓት ማለትም ለአንድ ቀን ተኩል በመንደድ በአካባቢው ያሉ ሰማንያ ቤቶችን ከነ ሙሉ ንብረታቸው ሲያወድም አቶ ጫኔ አካሉ የተባለ አርሶ አደር ሲሞት ሌሎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች የቆሰሉ መሆናቸውን ከአካባቢው ባገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ ለማወቅ በአካባቢው ለሚገኙ አርሶ አደሮች ጥያቄ ያቀረብን ሲሆን ሲመልሱም እኛ የአደጋውን መንስኤ ምን እንደሆነ አላወቅንም ነገር ግን ማንም ሳይደርስልን የአርባ ሁለት አባወራ ከነቤተሰባቸው ሙሉ በሙሉ ንብረታችን ወድሞ አሁን ያለምንም መጠለያ ሜዳ ላይ ወድቀናል እባካችሁ ምግብ እንኳን የሚያቀምሰን ድርጅት ከተገኘ ድምፃችንን አሰሙልን ብለዋል በአካባቢው ያሉ የወረዳና የቀበሌ መስተዳድር አካላትን ለጊዜው ማግነት ያልቻልን ሲሆን ለነዋሪዎቹ ግን በመንግስት በኩል የተደረገ ድጋፍ አለ ወይ ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄ ሲመልሱ የወረዳው አስተዳደር አካላት መጥተው ፎቶ አንስተውን ቪዲዮ ቀርፀውን ሄደዋል እስኪ ፍረዱን እኛ ማደሪያ እጥተን የሚቀመስ ቸግሮን ፎቶና ቪዲዮ ምን ይሰራልናል ብለው ይጠየቃሉ ፡ ፡ አሁን ቤታቸው የወደመባቸው አርሶ አደሮች ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ በመውደሙ እንዲሁ ሜዳ ላይ ወድቀው ይገኛሉ፡ ፡ በቀጣይም አስተዳደርቹን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ባይሳካም የወረዳው ብአዴን ፅ/ ቤት ኃላፊ የሆኑትን አቶ አማረ በሪሁን በተንቀሳቃሽ ስልካቸው አግኝተን ስለጉዳዩ ማብራሪያ ጠይቀናቸው ነበር ሲመልሱም ‹‹ ልክ ነው አደጋው ተከስቷል ተጎጂዎቹም ችግር ላይ እንዳሉ አውቀናል ነግር ግን እርዳታ ለመስጠት ባጀት ስለሌለን ምንም ያደረግንላቸው ነገር የለም ወደ በላይ አመለክተናል ምላሹን እየተጠባበቅን ነው ብለዋል ፡፡

jano

 

 

በስምምነት ላይ የተመሰረት ባህላዊ ውህደት Vs ህገ-መንግስታዊ ቀናዒነት ( ገለታው ዘለቄ )

$
0
0

ገለታው ዘለቄ

መግቢያ

በዚህ ጽሁፍ ሥር ለውይይት ይሆን ዘንድ የምናነሳው ኣሳብ   constitutional patriotism   ወይም ህገ መንግስታዊ ቀናዒነት ወይም ኣርበኝነት የሚባለው ጽንሰ ሃሳብ ባለፈው በተከታታይ ካቀረብኳት የ  Conventional Cultural Unity  ወይም በስምምነት ላይ የተመሰረት ባህላዊ ውህደት ካልኩት ኣሳብ ጋር እንዴት እንደሚለያይና  በኢትዮጵያ ሁኔታ ከሁለቱ ኣሳቦች የትኛው ተገቢና ችግር ፈቺ ሊሆን እንደሚችል  ኣሳብ ለማፍራት ነው።

በቅድሚያ ኣንድን ፖለቲካዊ የሆነ ፍልስፍና ወይም ቲየሪ በኣንድ ሃገር ፖለቲካ ውስጥ መሰረታዊ የመጫወቻ ወለል ኣድርገን ከማንጠፋችን በፊት ቲየሪው ወይም ኣሳቡ በጣም መጠናትና ግልጽ መሆን ኣለበት። ግልጽነት ሳይኖረውና ሳንረዳው በስሜት ከተከተልነው ሁዋላ ላይ ጉምን እንደ መጨበጥ ይሆንና እናርፋለን። ለዚህ ምሳሌ ኣምጣ ብትሉኝ የኢትዮጵያን የኣሁን ዘመን ፖለቲካ መጥቀስ እችላለሁ። ባለፈው ኣርባና ኣምሳ ኣመት ገደማ የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦችን ነጻ እናወጣለን በሚል ብዙ መፈክር ተሰምቱዋል። መዝሙሮችም ተዘምረዋል ግጥሞችም ተገጥመዋል። ታዲያ ቆይቶ ኣጥብቆ ጠያቂ ትውልድ ሲመጣ ብሄር ብሄረሰብ ደግሞ ህዝቦች የሚባሉት የት የት ነው ያሉት? የሚል ጥያቄ ሲያመጣ ሞተንለታል ከሚሉት ሰዎች ደጅ መልሱ ጠፋ። እነዚህ የዋሆች የሞቱላቸው የፖለቲካው እግሮች (radicals) ባለም ላይ የሉም እስከ መባል ደርሶ እንዲሁ በዚህ ኣይነት ግልጽ ባልሆነ የፖለቲካ ኣስተሳሰብ ውስጥ ገብተዋል። ከዚያ ደግሞ ኣብዮታዊ ዴሞክራሲ የሚባል ነገር ኣመጡና ኣብዮታዊ ዴሞክራሲ ማለት ምን ማለት ነው? እስቲ በይኑት(define ኣድርጉት) ቢባል የሚበይነው ጠፋ። ካድሬዎቹም መሪዎቹም ግልጽ ባልሆነ የፖለቲካ ርእዮት ውስጥ ይገኛሉ። እንዲህ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች የኣንድን ሃገር የፖለቲካ መሰረት ሲጥሉ ኣደጋው ሰፊ በመሆኑ መጀመሪያ ኣብጠርጥሮ ማወቅ ተገቢ ነው። ለዚህ ነው  የconstitutional patriotismን  ቲየሪ በሚገባ ማየት ኣለብን ያልኩት።  እንግዲህ ዝቅ ሲል  constitutional patriotismን   እና   Conventional Cultural Unityን   እያወዳደርን ኣይተን ከኢትዮጵያ ተፈጥሮና ተጨባጭ ችግሮች ኣንጻር የትኛው ተመራጭ ሊሆን እንደሚችል ለማየት እንሞክር። መልካም ንባብ።

 4

 

 

1.  constitutional patriotism  ንድፈ ሃሳብ ታሪካዊ ኣመጣጥና የፍልስፍና መሰረቶቹ

ጀርመን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ በምስራቁ ክፍል ያለውን ግዛትዋን በቀድሞዋ ሶቪየት ዩኒየን በመነጠቋና ቀጥሎም ቀዝቃዛውን የዓለም ጦርነት ተከትሎ በመጣው የዚህ ዓለም ኣተያይ ለጽንፍ ልዩነቶች ዳረጓት። ይህንኑ ቀዝቃዛውን የዓለም ጦርነት ተከትሎ ምእራቡ ክፍል የምእራቡን ዓለም ኣመለካከት ሲያስተናግድ ምስራቁ ክፍል ኣጥባቂ የኮሚኒስት ደጋፊ በመሆን በወቅቱ  ተፎካካሪ ለነበሩት ሶቪየት ዩኒየንና ምእራባውያን  ሁለቱ ጀርመኖች ለሁለቱ ጎራዎችደጋፊ በመሆናቸው ተለያይተው ለየብቻ ጎጆ ወጥተው መኖር ጀመሩ።

ሁለቱ ጀርመኖች ቋንቋቸው ኣንድ ይሁን እንጂ ይከተሉት የነበረው የዚህ ዓለም ኣተያይ ሁለት የተለያዩ ሰዎች እስኪያደርጋቸው ድረስ ልዩነታቸው ሰፋ። ምስራቁ ክፍል የኮሚኒዝምን የህይወት ፍሬዎች እያፈራ ቆየ። በኣንጻሩ ምእራቡ የካፒታሊስቱን ፍሬ እያፈራ ቆየ። ሁለቱ ወንድማማቾች ይከተሉት የነበረው የዚህ ዓለም የፖለቲካ ትምህርት በህይወታቸው የተለያየ ፍሬ እንዲያፈሩ ስላደረጋቸው የማንነት ልዩነቶችን ኣመጡ።

የማርቲን ሉተር ሃይማኖታዊ ሰው መነሻ የነበረችው ምስራቅ ጀርመን ሃይማኖትን ኣራክሳ የነበረ ሲሆን ሌላው ቀሮቶ ኣሁን ከተዋሃዱ በሁዋላ በ2012 OSW (Center for Eastern studies) ባደረገው ጥናት ካላት ህዝብ ከሃያ ስድስት በመቶ በታች የሚሆነው ህዝቡዋ ወደ ቤተክርስቲያን የሚሄድባት ኣገር ሆና ስትገኝ በኣንጻሩ ምእራብ ጀርመናዊያን በግልባጩ ሰባ ሶስት በመቶ የሚሆነው ህዝቡዋ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይሄዳል።ይህ የሚያሳየው በሃይማኖት ዝንባሌያቸው ምን ያህል ተራርቀው እንደነበር ነው። በኣጠቃላይ በዴሞክራሲ ኣረዳድ፣ በማሀራዊ ሃብት ክፍፍል፣ ወዘተ የተራራቀ መረዳትን ከመያዛቸው የተነሳ ያፈሩት ስብእና ነው የተለያየ ማንነትን ያመጣው።

እንግዲህ ሁዋላ ላይ በኣለም ላይ የኮሚኒዝም ስርዓት መንኮታኮት ሲጀምር ምስራቅ ጀርመንም በእጁዋ ያለውን የኮሚኒዝም ፍሬ ለማየት የጽሞና ጊዜ ኣገኘች። ለምስራቅ ጀርመን የለውጥ እንቅስቃሴ ያደረገው የውስጡ የህዝቡ በኮሚኒዝም ፍሬ ያለመርካት ዋናው ጉዳይ ሲሆን የሶቪየት ዩኒየኑ መሪ ሚካዔል ጎርቫቾቭ ሁዋላ ላይ ያመጡት የክፍትነት(openness) ኣሳብና ሶቪየትን እንደገና የማዋቀር ዓላማ እና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ለውጦች እንደ ውጪያዊ ተጽእኖ የሚታይ ነው።

የምስራቅ ጀርመን ህዝብ በወቅቱ በነበረው ኣስተዳደር ኣዝኖ ውስጥ ውስጡን ለለውጥ ራሱን ማዘጋጀት ጀመረ። ሁዋላ ላይ በፕሮቴስታንቶች ቤተክርስቲያን ውስጥ ኣገራችን ውስጥ ምን እየሆነ ነው? የሚል ውይይት ከፍተው መወያየት ጀመሩ። የጽሞና ጊዜ ኣምጥተው ያለፉበትን የህይወት ልምድ መገምገም ጀመሩ። በርግጥ ባፈሩት ፍሬ ኣልተደሰቱም ነበርና በቤተክርስቲያን ውስጥ የጀመሩት ተቃውሞ እየሰፋ ሄዶ እልፎች ተቀላቀሉት። በየሳምንቱ ሰኞ ሰኞ ኣንድ ኣመት የዘለቀ ተቃውሞ ተሰማ። “እኛ ነን ህዝብ ማለት” (We are the people) እያሉ መዘመር ሲጀምሩ በጣም መሰረታዊ የዴሞክራሲ ወይም የህዝቦች ልእልና ጥያቄ ያነሱ መሆኑ ታወቀ። የኣንድ ፓርቲ የበላይነትን በመንቀፍ የህዝቦችን የበላይነት ጥያቄ ይዘው ታገሉ። ይህ የሚያሳየው ምስራቅ ጀርመናዊያን ዴሞክራሲን መጠማታቸውን ብቻ ሳይሆን የማንነት ለውጥ ለማምጣት መዘጋጀታቸውንም ነበር።

የለውጡ ግፊት እየበረታ መጣና 1990 የሁለቱ ጀርመኖች ውህደት ኣሳብ መጣ። የህዝቡ ንቅናቄ ያስደነገጣቸው የምስራቅ ጀርመን መሪዎች ማሻሻያ ለማድረግ ደፍ ደፍ ሲሉ ውህደቱ ቀደመና ያሻሻሉትን ህገ መንግስት ወዲያ ጥለው ሁለቱ ጀርመኖች ለውህደት በቁ። ሁለቱም ወንድማማች ህዝቦች ያለያያቸውን የበርሊን ግንብ ኣፍርሰው ይገናኙ እንጂ ባለፈው ግማሽ ምእተ ዓመት የሚጠጋ ጊዜ ያፈሩት የህይወት ፍሬ የተለያዩ ኣድርጉዋቸው እንደነበረ ይበልጥ ሳይገነዘቡ ኣልቀሩም። ለማናቸውም ውህደቱ ተሳካና የተባበረችውን ጀርመን ወጥ በሆነ የፖለቲካ ስርዓት ለመምራት ፖለቲከኞቹ ሲነሱ የብሄራዊ ማንነት ጥያቄ ተነሳ። ምንም እንኳን ኣንድ ቋንቋ ብንናገርም የተለያየን ሆነናልና ብሄራዊ ማንነታችን እንዴት ሊሆን ነው?ሁለቱም ጀርመኖች የባህላዊው ብሄራዊ ማንነት(Traditional national identity)  ኣልተመቻቸውምና እንዴት ነው ብሄራዊ ማንነታችንን የምንገንባው? የሚሉት ጥያቄዎች በወቅቱ ለነበሩ የጀርመን ፖለቲከኞች መከራከሪያና ዋና የመወያያ ጉዳይ ሆኖ ነበር። በዚህ ጊዜ ነው እንግዲህ ሃበርማስ የተባለ ጀርመናዊ የሶሲዮሎጂ ፈላስፋ የህገ መንግስታዊ ቀናዒነትን ንድፈ ሃሳብ ይዞ ብቅ ያለው።

እንደ ሃበርማስ እነዚህ የተለያየ ማንነትን ያዳበሩ ህዝቦች ሊያገናኝ የሚችል፣ በቅድመ ማንነታቸው ወይም (traditional national identity ) ላይ ምቾት ያልተሰማቸው ህዝቦች ዘንድ ሌላ ድህረ ብሄራዊ ማንነት(post national identity) ሊመጣ የሚችለው ጀርመኖች ለህገ መንግስታቸው ቀናዒ ሲሆኑ ነው። ሑላችን ለህገ መንግስቱ ተገዢ ስንሆንና ለሊብራል ዴሞክራሲ ህገመንግስት እሴቶችና ኖርሞች ታማኝ ስንሆን የሰው መብት ስናከብር ስናስከብር በተቋማት ላይ መታመን ሲኖረን ያ የብሄራዊ ማንነታችን መገለጫ ይሆናል ማለት ነው የሚል ቁም ነገር ኣመጣ።። በመሆኑም  ህገ መንግስታዊ ቀናዒነት (constitutionl patriotism) የብሄራዊ ማንነታችንን ጥያቄ የሚፈታው ነው ብሎ ፖለቲከኞችን መጫን ጀመረ።

በወቅቱ የማንነት ጉዳይ ትልቅ ጥያቄ ሆኖባቸው ለነበሩት የጀርመን ፖለቲከኞችና በባህላዊው ማንነት ምቾት ያልተሰማቸው ጀርመኖች ኣዲስ ሊፈጥሩት ላሰቡት ማንነት ይህ የሃበርማስ ኣሳብ በርግጥም ልብ ኣሳራፊ ሆኖ በዚያን ጊዜ ተገኘ።

ለሁለቱ ጀርመኖች የመገናኛ መስመር ህገ መንግስቱ ሆኖ ሊብራል በሆነ ዴሞክራሲ ውስጥ ብሄራዊ ማንነታቸውን እንዲጥሉ ሃበርማስ መምከሩ በርግጥ ጥበብ የተሞላና ወቅታዊም ነበር ማለት ይቻላል።

ይህ የሃበርማስ ኣሳብ የጀርመንን ፖለቲከኞች ስሜት ያረጋ በመሆኑ እንደዚሁ የተለያየ ማንነትን ይዘው ብሄራዊ ማንነት ለመገንባት የተነሱ ኣገሮችም ለውስጥ ችግሮቻቸው መፍትሄ  ይሰጣል ብለው ሞክረውታል። ቦስኒያ ለዚህ ተጠቃሽ ናት::  ቦስኒያ ውስጥ በተለይ በሙስሊሙ ህብረተሰብ ዘንድ ይህ የሃበርማስ ኣሳብ በጣም የተቀነቀነ ነበር። የኣውሮፓ ህብረትም ይህንን የሃበርማስን ኣሳብ እንደተጠቀመበት ይታያል።

ሃበርማስ ለህገ መንግስቱ ቀናተኛነት ሲል ለፍትህ ፣ ለዴሞክራሲ፣ ለእኩልነት፣ ለሶሻል ዌልፌር መቆም እንደማለት ሲሆን እነዚህ ማንነቶች በርግጥ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ናቸው። ኣንዳንድ ምሁራን እንደሚሉት የሃበርማስ ኣሳብ ኣንድን የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመፍጠር የተነሳ ስለሆነ ኣገራዊ የሆነ ሰፋ ያለ ሶሊዳሪቲን ለማምጣት በጣም ይቀጥናል ይላሉ። በርግጥም ኣገር የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ፣ ፖለቲካዊ ይዘት ብቻ እንዳለው ኣድርጎ ማየቱና ብሄራዊ ማንነትን ከስቴት ጋር ብቻ ማጣበቁ ቀጣይነት ያለው ማህበረሰብ(sustainable community) ለመመስረት ኣይሳሳም ወይ የሚል ትችትም ሊቀርብበት ችሉዋል ። ያም ሆኖ ግን በወቅቱ የጀርመኖች ልዩነት ፖለቲካ የወለደው በመሆኑ የሃበርማስም ኣቀራረብ ፖለቲካዊ እንዲሆን ተጽእኖ ኣድርጎበት ነውና ኣሳቡ የሞራልና የሲቪሊቲ ጉዳዮችን ኣንስቶ የሚገጥሙትን የኮሙኒከሽን ችግሮች በትእግስት በማየት ተቻችሎ ለመኖር ጥሩ ምክር ነበር ማለት ይቻላል።

ከሁሉ በላይ ግን ሁለቱ ጀርመኖች ወደ ውህደት እየመጡ የነበሩት የማንነት መራራ  ጥያቄ ይዘው ኣልነበረም። ለሁለቱ ህዝቦች ውህደት ትልቅ ኣስተዋጾ ያደረገው የምስራቅ ጀርመን ህዝብ የማንነት ለውጥ ለማደርግ ፍላጎትና ጥማት በማሳየቱ ወይም እጅ በመስጠቱ ነው። ምእራብ ጀርመን ከነበራት ፖለቲካዊ ማንነት ንቅንቅ ሳትል ምስራቅ ናት ለውጥ እያመጣች ወደ ምእራቡ ኣሰተሳሰብ መቀላቀል ያማራት። በመሆኑም የሃበርማስ ኣሳብ የፖለቲከኞቹን ጥያቄ ወዲያ  ያርግብ እንጂ ውህደቱን ያሳለጠው ግን  ኣብዛኛው የምስራቁ ህዝብ የማንነት ለውጥ በማምጣቱ ነው።  ለዚህ ዋቢ የሚሆነን ጉዳይ ሁለቱ ሃገራት ወደ ውህደት ከመጡ በሁዋላ የጋራ ህገ መንግስት ሲያረቁ የምስራቁን ሀገ መንግስት ወዲያ ጥለው ከጥቂት ማሻሻያዎች ውጭ ምእራብ ጀርመን ትጠቀምበት የነበረውን ህገ መንግስት ነው እንዲቀጥል ያደረጉት። ይህ ማለት እነዚህ ህዝቦች ለመዋሃድ መሃከለኛ የሆነ የሁለቱን  ቅይጥ ሀገ መንግስት ኣላስፈለጋቸውም ነበር ማለት ነው።

ከፍ ሲል እንዳልኩት ምስራቅ ጀርመን የማንነት ለውጥ ለማድረግ በመወሰኑዋ ስትጠላው የነበረውን ያንኑ የምእራቡን ኣመለካከት እንደገና የህይወቱዋ መሪ ለማድረግ መወሰኑዋ ነው የውህደቱ መሰረት።። መሬት ላይ ያለው ሃቅ ይህ ከሆነ የሃበርማስ ሃሳብ በውስጠ ተዋዋቂ ምስራቅ ጀርመን የጀመረችውን ወደ ምእራቡ ኣስተሳሰብ የመዋሃድ (assimilation) እንቅስቃሴ ገፍታበት ሁለቱም ህዝቦች ቀድሞ ምእራብ ጀርመን እያሳደገችው የመጣችውን ፖለቲካዊ ማንነት የጋራ ድህረ ብሄራዊ ማንነት መገለጫ እንዲያደርጉት የሚገፋፋ ነው ማለት ይቻላል።

የሆነ ሆኖ ግን የሃበርማስ ኣሳብ ከፍ ሲል እንዳልኩት በፖለቲካው ለሂቅ ዘንድ ተቀባይነት በማግኘቱ ከስሜት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ጉዳዮችን በማብረድ ለጀርመኖች ውህደት ትልቅ ኣፋጣኝ ሚና ተጫውቱዋል።

   2.   የሃበርማስ ኣሳብ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ማንነት ጥያቄ መፍትሄ ሊያመጣ ይችላል ወይ?

መልካም። በመሰረቱ ሃበርማስ ያመጣው ይህ ኣሳብ በኣንዳንዶች ዘንድ ኣዲስ ተደርጎ ኣይወሰድም።ቀድሞውንም ቢሆን  ኣገሮች ህገ መንግስት ኣውጥተው ሲተዳደሩ እንደ ሃበርማስ  Constitutional patriootism  ብለው ኣይሰይሙት እንጂ ዞሮ ዞሮ በውስጠ ተዋዋቂ ያው ለህገ መንግስቱ ተገዢ በመሆን ህዝቦች በኣንድ የፖለቲካ ጥላ ስር ታምነው እንዲኖሩ ነው የሚፈልጉት። በመሆኑም ኣሳቡ በመጀመሪያ ደረጃ ኣዲስ ኣሳብ ሆኖም የቀረበ ኣይደለም። እንዴውም ሊብራል ዴሞክራሲ የሚባለው ኣመለካከት ይውጠዋል። ይህ ማለት የ Constitutional patriootism  ተግባራዊ ገጽታው ያው ዞሮ ዞሮ ሊብራል ዴሞክራሲ ነው የሚሆነውና ምንም ኣዲስ ነገር ኣልመጣም እየተባለ ይተቻል። ቲየርው ይዞ የመጣው ጉዳይ የሞራል፣ የምክር፣ ስሜትን የመቀስቀስ ኣይነት ነው። ሌላው የሃበርማስን ኣሳብ ስናይ በርግጥ ህገ መንግስታዊ ቀናዓኢነት የሚመጣው በህገ መንግስቱ ላይ በመታመን፣ ተቋማትን በማፍቀር ከሆነ ማፍቀርና መደገፍ ከሂደትነታቸው በላይ ውጤትነታቸው ነው ጎልት የሚታየው።  ዜጎች ለሀገ መንግስቱ ኣርበኞች እንዴት ሊሆኑ ይችላሉ? ኣርበኛ ለመሆን ውጤት ሊጠብቁ ኣይችሉም ወይ? የፖለቲካ ተቋማቱን ፍሬ እያዩ ነው እያደር የሚያፈቅሩዋቸው።ሌላው ደግሞ የሃበርማስ ኣሳብ ጠበብ ያለ የፖለቲካ ማህበረሰብ በመፍጠር ብሄራዊ ማንነትን የመገንባት ኣሳብ የያዘ በመሆኑ ቁርጠኛ የፖለቲካ መሪዎች ከጠፉና ተቋማት መርከስ ከጀመሩ ዜጎች ኣርበኛ ስለማይሆኑ ኣገር ሊፈርስ፣ ብሄራዊ ማንነት ሊደመሰስ ነው ማለት ነው። በርግጥ የሃበርማስ ቲየሪ ቀጭን(thin) ቲየሪ ነው የሚሉትም ለዚህ ነው።

ወደ ዋናው ኣሳባችን ስንመጣ የሃበርማስን  ኣስተያየትወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት በመጀመሪያ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የማንነት ጥያቄ መረዳት ያስፈልጋል። ጀርመኖች ያነሱት የማንነት ጥያቄ ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ሲሆን የኢትዮጵያው ግን የተለየ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የማንነት ጉዳይ የመጣው የባህላዊ ቡድንን ማንነት ለብሶ የመጣ ሲሆን ቡድኖች በራሳቸው ኣባላት ራስን ማስተዳደር ይችላሉ የሚል ኣይነት ኣስተዳደርንና ኣስተዳደራዊ ችሎታን ከባህላዊ ማንነት ጋር ኣደባልቆ ብቅ ያለ የማንነት ጥያቄ ነው ያለው። ከዚህ የምንረዳው ሃቅ የኢትዮጵያ የማንነት ፖለቲካ ጥያቄዎች ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ኣደባልቆ የመጣ በመሆኑ ችግሩን ሊፈታ የሚችለው ሶሲዮ ፖለቲካል ቲየሪ ነው። ማንነቶችን ማደባለቅና ለብሄራዊ ማንነት የጠራ መልክ ማጣት የኢትዮጵያ ዋና ችግር ነው። እንዲህ ከሆነ ታዲያ የሃበርማስ ኣሳብ የሚጨነቀው ቨርቲካል ለሆነውና ፖለቲካዊ ለሆነው ማንነት ብቻ በመሆኑ የኢትዮጵያን ሶሺዮ ፖለቲካል ችግር ሊፈታው በጣም ይቀጥናል። ላሉብን ማህበራዊና ፖላቲካዊ ችግሮች የግድ የሶሺዮ ፖለቲክስ ንድፈ ሃሳብ ነው የሚያስፈልገንንና የሃበርማስ ኣሳብ በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠረው የማንነት ጥያቄ መፍትሄ ሊሰጥ ኣይችልም።

ካናዳን እንደምሳሌ ማንሳት እንችላለን። ካናዳን ብናይ የኮቤኮችን የቡድን ማንነት ጥያቄ የሃበርማስን ቲየሪ በመጠቀም በሊብራል ዴሞክራሲ ህገ መንግስት ሊፈታ ኣልቻለም ወይም ኮቤክ በዚህ ልባቸው ኣርፎ ኣልታየም። ከፍ ሲል እንዳልነው የኮቤኮች ጥያቄ ፖለቲካዊ ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ጉዳዮችን ይዞ ስለመጣ ሃበርማስ እንደሚለው በሊብራል ህገ መንግስት የሚፈታ ኣልሆነም።

በሃገራችን ኢትዮጵያ በተለይ በ1960ዎቹ የተነሳው የቡድን ነጻነት ጉዳይ ሲነሳ ድንገት የተደባለቀው የቡድን ማንነትና የፖለቲካ ማንነት እንዲሁም መልኩ የደበዘዘው ብሄራዊ ማንነት ጠርቶ ሳይሄድ እስካሁን ቀርቱዋል። ከቀዝቃዛው ጦርነት በሁዋላ የጽንፈኝነት ፖለቲካ የከሰመ ቢሆንም ኢትዮጵያ ግን የራሱዋን ኣለም ሰርታ ኣሁንም በቀዝቃዛው ጦርነት ውስጥ ትገኛለች። እጅግ በሰፋና ጽንፈኛ በሆነ የፖለቲካ ኣስተሳሰብ ውስጥ ያለን በመሆኑ ዴሞክራሲ ሌላው ኣለም ላይ እያደገ ሲሄድ እኛ ጋር ቁልቁል ሲያድግ ይታያል።

የሃበርማስ ኣሳብ ኣንዱ ለኢትዮጵያ የማይሆንበት መንገድ ፖለቲካዊ ብቻ በመሆኑ ሲሆን ከሁሉ በላይ ኣንድ ቤት ሲሰራ ዋልታና ማገር ያስፈልጋል። ዋልታውንና ማገሩን እንደ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ልንመስለው እንችላለንና የጠነከረች መሰረት ያላትን ኢትዮጵያን ለመገንባት የሃበርማስ  ኣሳብ  ኣቅም ያጥረዋል። በመሆኑም እኛው ራሳችን ኣገር በቀል የሆነ ኣንድ ሶሺዮ ፖለቲካል ቲየሪ ልናመጣ ያስፈልገናል ከሚል ነው  የ CCU (Conventional cultural unity)   ኣሳብ የመጣው።

3.  CCU (Conventional cultural unity ) እንዴት ኢትዮጵያን መልሶ ለማዋቀር ሊረዳ ይችላል?

ኣሳቡ በዋናነት መሰረት ያደረገው የኢትዮጵያን ቡድኖች ቸርነት፣ ኣብሮ የመብላት፣ ኣብሮ የመኖር የማካፈል፣ ተፈጥሮ ነው። ከዚህ የተነሳ እነዚህ ቡድኖች ኣንድ ኣገር ሲመሰርቱ በቀጠነ ሁኔታ የፖለቲካ ማህበረሰብ ብቻ መሆን ሳይሆን የሚፈልጉት ለኣዲሱ ቤታቸው ነፍስ ሳይቀርላችው ያላቸውን ሁሉ ለኢትዮጵያዊነት የሚሰውበት ኣሳብ ነው። ባህል ስንል የምግብ ኣሰራር፣ ኣለባበስ፣ የበዓላት ኣከባበር ወዘተ ወግና ልማዶች ሲሆኑ እነዚህን ሁሉ ለማካፈልና ለኢትዮጵያዊነት ሰውቶ የጋራ ቤት ለመስራት ኢትዮጵያዊያን የቸርነት የጋራ ባህል ኣላቸውና ማህበራዊ ቲየሪው ይህንን ተፈጥሮ ያገናዘበ ነው።

በዚህ ኣገባብ ባህላዊ ውህደት ስንል ባህላዊ ቡድን የሚይዘውን ሁሉ ያቀፈ ነው። ይህ ማለት ቋቋ፣ ባህል፣ መልክዓምድር ወይም የተፈጥሮ ሃብትን ሁሉ የያዘ ነው። ቡድኖች ኢትዮጵያዊ መሆን (Being Ethiopian) ለምንለው ይህንን ሁሉ ሲሰው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በዜግነት መብታቸው እየተዘረዘረ በተግባር ይደርሳቸዋል ማለት ነው። ይህ ማህበራዊ ማንነት የፖለቲካ ማንነት ወለል ስለሚፈጥር በዚህ የጋራ ማንነት ስር የሚቆመውና በዚህ ጥላ ስር የሚጠለለው ፖለቲካ እንደ ማገር እየሆነ የጋራውን ቤት ይሰራል ማለት ነው።

ከዚህ በፊት እንዳልኩት ይህ ማለት ቡድኖች ባህላቸውን ያላቸውን ሁሉ ለኢትዮጵያዊነት ሰውት ማለት ከዚያ በሁዋላ ይጠፋሉ ማለት ኣይደለም። የቡድኖች ቋንቋና ባህል ጉዳይ ንብረትነቱ የኢትዮጵያዊያን ሁሉ ሆኖ ይሰዋ እንጂ በዚያ ቡድን ውስጥ እየገቡ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ያን ቋንቋና ባህል ወደላይ ጠብቀው እያሳደጉት ይኖራሉ። በጣም ተግባራዊ ምሳሌ ለማምጣት ኣንድ ኣባቱና እናቱ ኣማራ የሆኑ ሰው እሱ ኮንሶ ውስጥ ሄዶ ቋንቋውን ለምዶ ባህሉን ባህሉ ኣድርጎ ከኖረ ወይም ፈቃደኛ ከሆነ ኮንሶ ብሎ ራሱን ከባህል ኣንጻር የሚገልጽበት ኣውድ(context) ሲፈጠር በዚህ ራሱን ሊገልጽ ይችላል።  በዚህ ኣሳብ መሰረት ማንነት የሚቀየር የሚለወጥ በመሆኑ ኢትዮጵያዊያን በሰፊው የሃገራቸው ባህል ወስጥ የመሳተፍ የዚያን ቡድን ጥበብ የመደሰት መብት ኣላቸው። የቡድኖች ቤት ሁሉ ለኢትዮጵያዊያን ክፍት ይሆናል ማለት ነው። የተፈጥሮ ሃብትም ሆነ ሌሎች የቡድን ጥበቦች ሁሉ በእንደዚህ ኣይነት ማህበራዊ ስምምነት ስር መጀመሪያ ሊወድቅ ይገባዋል። ኢትዮጵያዊያንም ይህን ማህበራዊ የሆነ ኪዳን ከምንም በላይ ሊያስቀድሙ ይገባቸዋል። በዚህ ኣሳብ መሰረት የግዛትም ጉዳይ ኣንዱ ሲሆን ቡድኖች ኣገጣጥመው የሰሩዋትን የኢትዮጵያን ግዛት(territory) በሚመለከት ኣንዱ የቡድኖች መጣበቅ(attachment) መገለጫ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ግዛታቸው ከህልውናቸው ጋር በጥብቅ እንዲያያዝ ስለሚያደርግ ብሄራዊ ስሜትን ያጎለብታል።ከፍ ሲል እንዳልነው ይህ የቡድኖች ኪዳን ከሁሉ በላይ የሚውል ይሆንና ከዚያ ቀጥሎ በዚህ ማንነት ስር የሚገነባው የፖለቲካ ማንነት የራሱን ህገ መንግስት ኣውጥቶ በዚያ ይተዳደራል ኣገሪቱን ወደ በጎ ለውጦች ይመራል። የኢትዮጵያዊያን ብሄራዊ ማንነትም የነዚህ የሁለቱ ድምር ውጤት ይሆንና በማህበራዊም በፖለቲካዊም ጎኑ የተሙዋላ ብሄራዊ ማንነት እንገነባለን። የኢትዮጵያዊያን ብሄራዊ ማንነት በግዛት፣ በባህል ውህደት፣በዜግነት የሚገለጽ የዳበረ ማንነት እናፈራለን ማለት ነው። ወደዚህ ኪዳን ደፍረን መግባት፣ ሁሉንተናችንን በመተማመን ለኢትዮጵያዊነት መሰዋት ከቡድኖች ሁሉ የሚጠበቅ ጀብዱ ሲሆን ይህ ትውልድ ይህን ኣደረገ ማለት ኢትዮጵያ ኣሁን ተፈጠረች ተብሎ ሊወሰድ ግን ኣይችልም። ይህ ስራ ኢትዮጵያን መልሶ የማዋቀር ስራ እንጂ ኢትዮጵያ ለዘመናት የኖረች  ጥንታዊት ኣገራችን መሆኑዋ ኣያጠራጥርም።

4.ኪዳን ስንል ምን ማለታችን ነው? ምንን ምን ይይዛል?

በዚህ ጽንሰ ሃሳብ መሰረት ኪዳን የሚለው ጉዳይ ቡድኖች ለትውልድ የሚያስተላልፉት የስምምነት ሰነድ ነው። የተጻፈ ሰነድ ለትውልድ ማስተላልፍ መጀመሩ ለኢትዮጵያ የወደፊት ህይወት መልካም ነው። በመሆኑም ኪዳኑ የሚይዛቸው ጉዳዮች እጅግ የላቁ የቡድኖችን ስምምነት ሲሆን ይህ ስምምነት ዘመን የማይሽረው ይሆናል። የስምምነት ነጥቦቹን ቡድኖች በብሄራዊ እርቅ ሂደት ውስጥ ሲገቡ የሚያነሱዋቸው ሲሆን የማትከፋፈል ኢትዮጵያን ለትውድ ለማሳለፍ፣ የቡድኖች የባህል ውህድት ስምምነት፣ የህዝቦች የበላይነት ጉዳይ የኢትዮጵያን ፋውዴሽን ጉዳይና   ሌሎች እጅግ ከፍ ያሉ ኣሳቦች ሊሆኑ ይችላሉ።እንግዲህ ኢትዮጵያ በዚህ ኣሳብ መሰረት ሁለት ሰነድ የሚኖራት ሲሆን ኣንዱ ይህ ኪዳን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ፍትህ ፣ እኩልነት፣  የመሳሰሉትን የሚያሳልጥ የእለት ተእለት ህይወቱዋን የምትመራበት ህገ መንግስት ይኖራታል።

 

 

 

 

በዚህ ኣዲስ ኣወቃቀር መሰረት ሁለት ኣይነት ኣስተዳደር የሚኖራት ሲሆን ኣንደኛው ባህላዊ ኣስተዳደር ነው። ይህ ባህላዊ ኣስተዳደር የሚመሰረተው ከየቡድኑ ኣንድ ኣንድ ባህላዊ ተወካዮች ተመርጠው ይመጡና የኪዳኑን ኣርበኞች ቤት ይመሰርታሉ። እነዚህ ኣርበኞች እንደስምምነታቸው በየ ኣመቱ በእጣ እየመረጡ ንጉስ የሚሾሙ ሲሆን ይህ ንጉስ በዚያ በመጣበት ባህላዊ ቡድን ባህል መሰረት ይነግሳል። እንዲህ እያለ ሁሉም ቡድኖች በተራ እየነገሱ ይኖራሉ ማለት ነው። ይህ ኣካል ፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ ኣይገባም። ሃላፊነቱ የሽምግልና ስራዎችን መስራት፣ የተለያዩ የባህል ፌስቲቫሎችን ማዘጋጀትና መምራት፣ የኬር ቴከር ሃላፊነትን መውሰድና የፖለቲካ ችግር ሲፈጠር ኣገር ኣረጋግቶ መንግስትን መመስረት የመሳሰሉት ውሱን ስራዎችን የሚሰራ ነው። በባህላዊ ጉዳዮች ውስጥ ኣክቲቭ ሊሆን ይችላል።

ሌላው መዋቅር መንግስት ሲሆን በፓርላመንታሪም ይሁን ፕሬዚዳንታዊ ዘዴ የሚመሰረተው መንግስት ህግ ኣውጪው ኣስፈጻሚውና ተርጓሚው ነጻና እርስ በርስ ቼክ እና ባላንስ ያለበትን ስርዓት መስርቶ ይኖራል። ይህ የኢትዮጵያ ቅርጽ ሁለት መንኳን የሚያሳይ ሲሆን በኣንድ በኩል ማህበራዊውን ጉዳይ በሌላ በኩል ፖላቲካውን መልኳን ያሳያል። የነዚህ ድምር ውጤት በዜግነታችን የሚገለጸው ኢትዮጵያዊነት የወንዶችና የሴቶች ኢትዮጵያዊያን ብሄራዊ ማንነት መገለጫ ይሆናል ማለት ነው።

5. ያለፈ ትውስት (Past memories) በኣዲሱ ኪዳን እንዴት ይታያል?

ምእራብ ጀርመንና ምስራቅ ጀርመን ልዩነት ሲያምራቸው ታሪክን ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል ጀምረው ነበር። ኣንዱ የጀርመኖችን ፖለቲካ ያራራቀውም ይሄው ነበር። በተለይ በናዚ ወቅት የተፈጸመውን የሆልኮስት ዘር ማጥፋት ወንጀል በተመለከተ ሁለቱ ጀርመኖች በተለያየ መረዳት መተርጎም ከመጀመራቸው ኣልፎ በርሊንና ቦን ሁለት ሙዚየሞች ቆመው የተለያየ ነገር ማስተማር ጀምረው ነበር። ያለፈውን ታሪክ ለማስታወስ የፈለጉበት ሞቲቭና ታሪኩን ወደ ትውልድ ለማሳለፍ የሞከሩበት ዘዴ ይለያይ ነበር።

ባለፈው ጊዜ ዶክተር መራራ ጉዲና ጥሩ ነገር ተናግረዋል። ታሪክን ለፖለቲካ ፍጆታ ኣናውለው ብለዋል። በርግጥ ጀርመን  ከታየው በላይ የኢትዮጵያን ኣጠቃላይ የታሪክ መሰረት የሚያምስ ሁኔታ ተፈጥሩዋል። ይህ የሆነው የማንነት ፖለቲካን ለማራገብ ታሪክ መሳሪያ ሆኖ በመቅረቡ ነው።

በርግጥ ኣንድ ሃገር ሲቆም ያለፈን ትውስታ ወዴትም ኣንጥለውም። ነገር ግን ትውስታችንን የምናይበትን መንገድ ማስተካከል ኣስፈላጊ ነው።

በ   CCU  ኣመለካከት በኢትዮጵያ ስቴት በመመስረቱ ሂደትና ከመሰረተች በሁዋላ የተፈጸሙ በጎም ሆኑ መጥፎ ታሪኮች ሁሉ የኢትዮጵያ ትውስታዎች (Past memories) ናቸው።  ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ትውስ የሚላት ታሪክ ነው። በጎ በጎውን መርጠን የመታሰቢያ ቀን ኣቁመን የጋራ ታሪካችን እያልን እየሞቅን መጥፎውን ነቅሰን ኣውጥተን ለኣንድ ቡድን ኣናላክክም። ሁሉም የኢትዮጵያ ታሪክ ነው። የሚያሳዝነው ያሳዝነናል፣ የሚያስደስተው ያስደስተናል።

ባለፉት ጊዚያት በግልም ይሁን ቡድንን እየለየ የተፈጸመ በደል ሁሉ የኢትዮጵያ ትውስታ(past memories) እንጂ ያ በደል የተፈጸመበት ቡደን  ቋንቋ ተናጋሪና ኣባል ብቻ ኣይደለም።

ሌላው ታሪክን በሚመለከት የዓለም ህዝብ ኢትዮጵያን እንዴት እነደሚያያትም መታወቅ ኣለበት። ከኣጠቃላዩ የዓለም ህዝብ ወደ 54.9 በመቶ የሚሆነው የክርስትናና የእስልምና ሃይማኖተኛ ሲሆን ኢትዮጵያን የሚያያት በረጅም ጊዜ ታሪኳ ነው። ክርስቲያኑ በሃዋርያት ስራ ላይ የተገለጸውን ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ ዋቢ በማድረግ ክርስትናን የተቀበለች ከዓለም ቀደምት ኣገር ናት ብሎ ያከብራታል። በብሉይም ስሙዋ የተጠቀሰ ተስፋ ያላት ኣገር ኣድርጎ ስለሚያምን ተስፋዋን ይጠብቃል።። ሙስሊሙ ህበረተሰብ ደግሞ ለመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች መጠጊያ ለመሆን የበቃች ኣገር ብለው ስለሚያምኑ እንደዚሁ በሙስሊሙ ህዝብም ዘንድ ታዋቂ ናት።። ይሄ ከፍተኛ ተጽእኖ ያለው ታሪክ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆነው የዓለም ህዝብ እንዲህ እንደሚያያት መገንዘብ ጠቃሚ ነው። ሌላው ያሉን ቁሳዊ ባህሎች እንደ ላሊበላ፣ ኣክሱም በደቡብና ኦሮሚያ የሚገኙ ሃውልቶች ሁሉ የኢትዮጵያን እድሜ ይናገራሉ። እነዚህ ታሪኮች ሁሉ የጥንታዊቱን ኢትዮጵያን ትውስታ እየሰጡን እንኖራለን።በኣጠቃላይ በዚህ ጽንሰ ሃሳብ መሰረት ያለፈውን ታሪክ እንደ ወል ታሪክ የሚያይ ይሆንና የሚከተሉትን ጉዳዮች በጥብቅ ይመረምራል።ይህም ታሪኩ ታሪክ ሆኖ መቅረት ብቻ ሳይሆን ኣሁን ድረስ ይጎተታል ወይ? በተለይ መጥፎ የምንለው ታሪክ ኣሁንም ካለ ይህን ታሪካዊ ዳራ ያልውን ችግር በሪስቶሬቲቭ ጀስቲስ እና በብሄራዊ እርቅ ይፈታል ።

በኣጠቃላይ ያለፈውን ታሪክ የምናስታውሰው የወል ታሪክ ኣድርገን ሲሆን ይህንን የወል ታሪካችንን እንደ የወልነቱ ስናየው ትውስታችንን በጥሩ ሚዛን ላይ ያስቀምጠዋል።

ከዛሬ መቶ ኣመት በፊት የነበረውን ታሪካችንን ስንተነትን ኢትዮጵያን ለብቻዋ ንጥል ኣድርገን ሳይሆን ከኣለም የሰው ልጆች ታሪክ ጋር እያገናዘብን መፍረድ ኣለብን።ሌላው ኣሁን ያለንበት ከባቢስ ምን ይመስላል? በምን ኣይነት የፖለቲካና ማህበራዊ ከባቢውስጥ ሆነን ነው ታሪክን የምንተነትነው? ብለንም መጠየቅ ኣንዱ ለፍርድ በተሻለ የሞራል ደረጃ ላይ የሚያስቀምጠን ነው። ሌላው ማየት ያለብን የትውስታችን ፍላጎት ምንድነው? በታሪክ መረዳታችን ምን ልናደርግበት ነው? ብለን መጠየቅም መልካም ነው። በርግጥ ያለፉ ታሪኮችን ኣንስተን በቀልን ልናቅድ ነው? ወይስ የተሻለ ኣሰራር ለማምጣት መልካም እልህ ውስጥ ሊከተን ነው? ብለን መጠየቅ ኣለብን የሚል ምክር ይህ የባህላዊ ውህደት ኣስብ ኣዝሎኣል።

       ማጠቃለያ

ይህንን ወረቅት ስጽፍ ድፍረት ያበዛሁ እንደሆነ ገብቶኛል። ዋናው ጉዳይ መፍትሄ ስለናፈቀኝና በርግጥም የኢትዮጵያን ማህበራዊ ፖለቲካ ችግር ሊያቀል ይችላል ከሚል ነው። ኣንዳንዶቹ ያነሳሁዋቸው ነጥቦች ውሳኔ ሁሉ ይመስላሉ። ንጉስ ይኑር፣ በየኣመቱ ይሾም…. ስል ኣንባቢ የሚያስበውን እያሰብኩ ነው የጻፍኩት። ለማናቸውም ሁላችን እየተወያየን ከዚህ ብሄራዊ ማንነታችንን ካደበዘዘ ጨለምተኛ የፖለቲካ መዋቅር ፈጥነን መውጣት ኣለብን። በዚህ ጽሁፍ ላይ ኣስተያይት ካለ ጻፉልኝ። የህገ መንግስታዊ ኣርበኝነት ወይም ቀናዒነትና በስምምነት ላይ የተመሰረት ባህላዊ ውህደት ጽንሰ ሃሳብ ልዩነቶችን በሰንጠረዥ እንደሚከተለው ኣቅርቤ ጽሁፌን ላጠቃል። በዋናነት ግን ባለፈው እንደጻፍኳት ብጣቂ ኣርቲክል የቱንም ያህል መልካም ስርዓት ብናመጣ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ከሌለ ኣይጠቅመንምና ይህንን ጉዳይ ችላ እንዳንል ዛሬም ኣሳስባለሁ።

የሁለቱ ጽንሰ ሃሳቦች ልዩነቶች

Constitutional patriotism Conventional Cultural Unity
1 ፓለቲካዊ ንድፈ ሃሳብ ነው የሶሲዮ ፖለቲካል ቲየሪ ነው
2 ቀጥታ ግንኙነትን (Vertical) ብቻ የሚያይ ነው ቀጥታና ተዋረዳዊ (Vertical & horizonatal) ግንኙነቶችን ይዳስሳል
3 ለህገ መንግስት ታማኝ በመሆን ፖለቲካዊ ብሄራዊ ማንነት ለመገንባት የቀረበ ነው ባህላዊና ፖለቲካዊ ኣስተዳደሮችን በመዘርጋት ሁለንተናዊ የሆነ ብሄራዊ ማንነትን ለማዳበር የቀረበ ነው።
4 ዩኒቨርሳል የሆነ የሰባዊ መብትን መሰረት ያደረገ ነው ዩኒቨርሳል የሆነ የሰባዊ መብትን መሰረት ያደረገ ነው
5 ህገ መንግስት ከፍተኛው ሰነድ ነው ሁለት ሰነዶች የሚኖሩ ሲሆን የኪዳኑ ሰነድና ህገ መንግስት ተብለው ቀርበዋል።

እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ

ገለታው ዘለቀ geletawzeleke@gmail.com

የ2007 ዓ. ም አገርአቀፍ ምርጫና የሸንጎ አቋም

$
0
0

መጋቢት 27፣ 2006 (April 5, 2014)

shengoየኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) የሰብዓዊ መብት፣ የሕዝብ ሉዓላዊነት፣ የሕግ የበላይነት፣ የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት…ወዘተ እንዲረጋገጡ፤ የዜጎች እኩልነት እውን
እንዲሆንና በማንኛውም የሃገሪቱ ክፍል በነፃ ተንቀሳቅሰው ሃብትና ጥሪት የማፍራት መብት እንዲኖራቸው ዋስትናም እንዲያገኙ የሚያደርግ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት፣ አንድነቷና ሉዓላዊነቷ በተጠበቀ ኢትዮጵያ ውስጥ መመሥረት ያስፈልጋል ብለው የሚያምኑና ለዚህም  የሚታገሉ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪል ማህበራትና ግለሰቦች በኅብረት የፈጠሩት  ድርጅት ነው።  ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ  

እስክንድር –ይናገር!

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 06.04.2014 (ሲወዘርላንድ – ዙሪክ)

Eskinder-Nega

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ

ይመስክር – ይናገር
ያ —– አርበኛ ፍቅር
የእናቱን ነገር።
የአቅም – አንደበት፤
የመሆንም – ችሎት።

እስክንድር ይናገር
የአዬር አልቦሽ ኑሮ ——- ይዘርዝር
——————— ይመንዝር።
ትርጉሙ – ለእናቱ
ቅኔውም -  ለአዳራው፣
የማግዶ – ውሎው።
ያስቀደመ – እማን
የድጓውም – ዳን
ዓይነታ – የኪዳን።
ሩ———ቁ፤ ——- አሳቢ
አስቀድሞ – አላሚ
ማግስትን – አቅላሚ
ትንቢትን – ተላሚ።

እስክንድር ይናገር
የእናቱን ነገር።

ተሰራ በእስክንድር
የነፃነት – ቀመር፤
በተግባሩ – ንጥር።
ተበጀ – በእስክንድር
መንፈሳዊ – መስመር
የብራና – ህብር።

የቃና —– አባቱ
ረ ለባቱ።

ዝማሬ ማህሌት
ቀኑ ቀናያለት።

ሚስጥር ተ —— ዚያ፤ ማዶ
ቀራንዮን —— ወዶ፤
እራሱን – ዬሰጠ
ትዳሩን – ዬሰጠ
ናፍቆቱን – ዬሰጠ
ኑሮውን – ዬሰጠ
ምቾቱን – ዬሰጠ
እንግልት – መረጠ
ነገነን ——– ያማጠ።

እስክንድር ይናገር
የእናቱን ነገር።

አለሁልሽ ያለ
ያላወላወለ ————
ብዕር ወለወለ
ለሃቅም አደረ
አብነት —- ሰመረ።
የጽናት አድባሩ
የተቋሙ —-  ድሉ
የወርቅ እሸት ጓሉ
እሱን አሉ አሉ!

ብቃቱ – መካሪ
ኮንፓሱ – መ
ራዕይ – አሳማሪ!

                                  ሥጦታ ለአባ ትርጉም – ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ።

 

 

 

 

የጠበቆች ማህበር በአርቲስት ግሩም ኤርሚያስ ላይ የወንጀል ክስ መመስረታቸው ተሰማ

$
0
0

girum ermias

በአዲስ አበባ ታትሞ የሚወጣው ማራኪ መጽሔት እንደዘገበው በቅርቡ በሰይፉ ፋንታሁን የኢቢኤስ ሾው ላይ ቀርቦ በአዲስ ፊልሙ ላይ አደንዛዥ ዕፅ ተጠቅሞ መስራቱን ለማህበረሰቡ ያሳየው አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ የጠበቆች ህብረት በጋራ የወንጀል ክስ አቅርበውበታል።

ጠበቃ ማቲያስ ግርማ ለማራኪ መፅሄት እንዳስረዱት በክሱ ላይ ሰይፉ ፋንታሁንና አለማየሁ ታደሰ ደጋፊ ሀሳብ በመስጠታቸው ክስ ይመሰረትባቸዋል ብለዋል። አርቲስቱ ምንም እንኳ ለፊልም ግብዓት “መስለው ሳይሆን ሆነው” ለመስራት ያደረጉት ተግባር ቢሆንም ህብረተሰቡን ከወንጀል ለመጠበቅ ሲባል ክስ እንደተመሰረተባቸው የጠበቆች ተወካዩ አስረድተዋል።

አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ በፊልሙ ላይ

አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ በፊልሙ ላይ

“ይህንን የበለጠ ማጣራት የነበረባቸው ፖሊስና አቃቤ ህግ ቢሆኑም ፣ በግልፅ በሀገሪቱ የአየር ክልል የተላለፈውን መረጃ ዝም ማለታቸው እንዳሳዘናቸውም ገልፀዋል። በሀገሪቱ የወንጀል ህግ ስርዓት በተለይ ግሩም በክሱ ጥፋተኛ ከተባለ እስከ ሰባት አመት እንዲሁም የ50ሺ ብር ቅጣት ይጠብቀዋል።

በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ 1996/97 አንቀፅ 525 ንዑስ አንቀፅ/ሀ መሰረት እስከ ” አደንዛዥ ዕፅን እራሱ ወይም ሌላ ሰው ሊጠቀምበት በማሰብ የገዛ፣የተጠቀመ፣ እንዲጠቀም ያደረገ፣,,,” ከ7 ዓመት እስከ 50ሺ ብር ቅጣት ይጠብቀዋል። እነ ሰይፉ ደግሞ “ወንጀልን ባለማወቅ” ክስ ተመስርቶባቸዋል።

መጽሔቱ ዘገባውን ሲያጠናቅቅ ለግሩም በቅርብ መጥሪያ ይደርሰዋል ተብሎ ይጠበቃል ብሏል።


Hiber Radio: የኖርዌይ አምባሳደር ማዕከላዊ በመሄድ ከደቡብ ሱዳን ታፍነው የተወሰዱትን የቀድሞ የጋምቤላ ፕ/ት ለማየት ጥያቄ ማቅረባቸው ተገለጸ

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ መጋቢት 28 ቀን 2006 ፕሮግራም
<…አቶ ኦኬሎ አኳይ ከጁባ ታፍኖ ማዕከላዊ ነው።…አኪልዳማ አይነት ድራማ ሊሰራበት ይችላል።የወያኔ እሱን መያዝ በጋምቤላ ተፈጽሞ ለዓለም አቀፉ ፍ/ቤት ማስረጃው የቀረበውን የዘር ጭፍጨፋ ወደሁዋላ አያስቀርም። ማስረጃው ወጥቷል … >

አቶ ኦባንግ ሜቶ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተጠይቀው ለህብር ከሰጡት (ሙሉውን ያዳምጡ)

<… አሁን ያሉት ሰዎች የደገሱልን የእርስ በእርስ እልቂት ነበር። የኢትዮጵያ ህዝብ ጨዋ ሕዝብ በመሆኑ ያንን የደገሱለትን እልቂት አክሽፎታል።…አሁንም እነዚህ ሰዎች ያዋረዱትን የአገራችንን ባንዲራ በጋራ ሙስሊምም ሆነ ሙስሊም ያልሆነው በጋራ ለመብቱ መቆም ባንዲራዋን ነጻ ማውጣት አለበት …> ሐጂ ነጂብ መሐመድ የፈርስ ሒጅራ ፕሬዝዳንት በቬጋስ በኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ ላይ ካደረጉት ንግግር መሐከል ቀሪውን ያዳምጡት

የሩዋንዳ ጭፍጨፋ ሃያኛ ዓመትን የተመለከተ ወቅታዊ ዘገባ

የህወሃት መሪዎች ሱዳንን ከህልውናቸው ጋር በማያያዛቸው ስለ ሱዳን ህልውና ለአሜሪካ ዲፒሎማቶች የተናገሩበትን የዊክሊክስ ያጋለጣቸውን የምስጢ ር መልዕክቶች (ልዩ ዘገባ )

 

ሌሎችም ዝግጅቶች

ዜናዎቻችን

የኖርዌይ አምባሳደር ማዕከላዊ በመሄድ ከደቡብ ሱዳን ታፍነው የተወሰዱትን የቀድሞ የጋምቤላ ፕ/ት ለማየት ጥያቄ ማቅረባቸው ተገለጸ

አሜሪካ ለግብጽ የምትሰጠው ዕርዳታ በተዘዋዋሪ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እየዋለነው ሲሉ ብቸኛው የተቃዋሚ የፓርላማ አባል ወቀሳ አቀረቡ

ታንዛኒያ 43 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አሳልፋ ሰጠች

የአረና አመራሮችና አባላት ዛሬም ትግራይ ውስጥ ተደበደቡ

የታሰሩም አሉ

አንድነት በጠራው የዛሬው የደሴ የተቃውሞ ሰልፍ ከ60 ሺህ በላይ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ ቁጣውን ገለጸ

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ለሁለተኛ ጊዜ ታሰረ

የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ለማስፈታት እንዳልተሳካለት ገልጾ ለሱ ደህንነት ሲባል ሁኔታው እንዳይጋጋል ጠየቀ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በፓሪስ የማራቶንን ሪኮርድ ሰበረ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

 

ያልዘሩትን ማጨድ ከቶ አይቻልም! (ግንቦት7)

$
0
0

April 5, 2014

G7የወያኔ መንግስት የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች አጋጭቶ በመካከላቸው ጥርጣሬና መፈራራት አንግሶና የታሪክ ጠባሳዎችን እንደ አዲስ በመጓጐጥ እያደማ ከፋፍሎ ለመግዛት ካለመታከት ያደረጋቸው ሙከራዎች ገና ፍሬ ባያፈሩም ቁጥቋጦዎቹ መብቀል ጀምረዋል። እዚህም እዚያም በካድሬዎች የውስጥ ለውስጥ ተልእኮ የሚለኮሱ እሳቶች መብለጭለጭ ጀምረዋል። ሌላው ቀርቶ በአንድ ብሄረሰብ መሃል ሳይቀር በከባቢ ልዩነቶች ብቻ መናቆሮችና መጋደሎች እያስተዋልን ነው። ሰሞኑን በጉጂና በቦረና ኦሮሞዎች መካከል የወያኔ ሎሌዎች በሚያበረታቱት አተካሮ የብዙ ወገኖቻችን ህይወት ጠፍቷል። ሰዎች ከኑሮአቸው ተፈናቅለዋል። ወያኔ እንደኳስ ጨዋታ ተመልካች ዳር ሆኖ ይመለከታል፣ ያጨብጭባል።

ሰሞኑን ባህርዳር ከተማ ውስጥ በተካሄደ የስፖርት ውድድር ላይ አሳፋሪ ክስተት ነበር። ለሰሚው የሚቀፍ ብልግና የተቀላቀለበት ስድብና ቁርቋሶ አይተናል። ከበስተጀርባ ሆነው ይህንን ለፍቅር ብቻ ሊውል የሚገባ የስፖርት ዝግጅት መርዝ ረጭተውበታል። ከዚህ ላቅ ያሉ የተንኮል ድግሶችም ተደግሰው ህዝብ ውስጥ በወያኔ ከተነዙ የመርዝ ቢልቃቶች ውስጥ ስራ ላይ ሳይውሉ ቀርተዋል።

ይህ በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ዘር የሚዘራው ወያኔ ያልተከፋፈለ ህዝብ አይገዛልኝም በሚል ፍልስፍና እንደሆነ በተደጋጋሚ እያየን ነው። ሶማሌ ክልል ውስጥ በተቋቋሙ ልዩ ፖሊስ በሚል ስያሜ በሚጠሩ የመንግስት ሃይሎች ጥቃት ቁጥሩ እጅግ በርካታ የሆነ የኦሮሞ ማህበረሰብ ከኖረበት መሬት ተጠራርጎ እንዲወጣ ተደርጓል። ብዙዎቹ ተገድለዋል። ብዙ ደም መቃበት ተፈጥሯል። በየክልሉ ምስኪን የአማራ ገበሬዎችን መሬት ንብረት በመንጠቅ አከባቢውን ለቀው እንዲሄዱ አድርገዋል። መሄጃ የለንም ያሉትንም ቀጥቅጠው እንደገደሏቸው ሰሞኑን ከጅባትና ሜጫ አካባቢ ያሉ መረጃዎችን አይተናል።

እነዚህ በየቦታው የሚብለጨለጩ እሳቶች በዚህ ከቀጠሉ ሁላችንም ወደ ሚያቃጥልና የሚለበልብ የሰደድ እሳት ማደጉ አይቀርም። የወያኔ ባለሟሎች ካለምንም ይሉኝታና ማሰላሰል ይህንን እሳት እያራገቡ ይገኛሉ።

ይህንን አደገኛ አዝማሚያ በንጭጩ ማስወገድ የሚችለው ራሱ ህዝቡና የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ የነጻነት ሃይሎች ድምጽና ህብረት እንጂ የወያኔ መንግስት አይደለም። ስለዚህ ህዝቡ በተለይም ወጣቶች ከዚህ ወጥመድ ሰብረው እንዲወጡ ግንቦት 7 የነጻነት፣ የፍትህና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አጥብቆ ያሳስባል። ተመሳሳይ ተንኮሎችንም ማጋለጡን ይቀጥላል። የብሄርሰብ ልሂቃንም ይህንን መርዝ እንዲቋቋሙ፣ ይልቁንም ወያኔ እንዳይመቸው ይበልጥ መቀራረብና ፈተናውን በጋራ እንድንቋቋም ጥሪያችን በድጋሜ እናቀርባለን።

ያልተዘራ አይታጨድም። ወያኔ የዘራልን መርዝ የሚያፈራው መርዝን እንጂ ሌላ አይደለም። ልዩነቶቻችን እንደዘመኑ በሰለጠነ ዲሞክራሲያዊ መንገድ እንጂ በተያዘው መንገድ ማስወገድ አይቻልም።

ዞሮ ዞሮ በዚህ ሳይጣናዊ የወያኔ መሰሪ ሴራ ለምትፈስ ለእያንዳንዶ የደም ጠብታ ተጠያቂው የወያኔ ጉጅሌ መሆኑን አጥብቀን እናሳስባለን። በመሆኑም ለመከፋፈል ከመመቻቸት ይልቅ አንድነታችን በማጥበቅ የነጻነት ሃይሎችን በመቀላቀል ራሳችን እና የሀገራችንን ህልውና ከዚህ ከወያኔ የመከፋፈል መርዝ እንታደግ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ግልጽደብዳቤ፤- ይድረስ ለአባ ኃይለ ሚካኤል የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም በሚኔሶታ አስተዳዳሪ፣

$
0
0

ጉዳዩ፡ከዚህ፡ቀደም፡የሰማሁት፡በአስተዳደርዎ፡ጉድለት፡ምእመኑን፡በመከፋፈል፡በማውገዝም፡ያካሄዱ ት፡የነበረውን፡ውዝግብ፡በተንቀሳቃሽ፡ምሥል፡በማዬቴ፡የተሰማኝን፡ኀዘን፡ለማስታዎቅም፡ጭምር፡ነው።የተቀ ባው፡ጌታችን፡መድኃኒታችን፡” ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

 

debereselam-medhanialem

ማኅበረ ቅዱሳን በፓርቲ ፖለቲካ የማይጠረጠርባቸው ምክንያቶች (የግል ምልከታ)

$
0
0

(ኤፍሬም እሸቴ)

     ይህ ጽሑፍ የእኔን የግል ምልከታና አስተያየት ብቻ የሚመለከት እንጂ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ስሙ የተጠቀሰውን ማኅበርም ሆነ ከእርሱ ጋር የአገልግሎት ግንኙነት ያላቸውን ተቋማት የማይመለከት መሆኑን አበክሬ በመግለጽ ልጀምር።

አንድ ብሒል አለ። ውሸትን ደጋግመው ቢናገሩት እንደ እውነት የሚቀበለው ሰው መፍጠር ይቻላል። ስለዚህም ሐሰተኞች ሐሰታቸውን ሳያሰልሱ በተናገሩት መጠን፦ አንደኛ ራሳቸውንም በሐሰታቸው እውነትነት ያሳምናሉ፤ ብሎም ሌሎችን ማሳመን ይችላሉ። ደጋግሞ የመናገር ጥቅሙ ይኼው ነው።

mahbere qdusanአንዳንድ እውነት የያዙ ሰዎች ደግሞ “እውነት እስከያዝን ድረስ ደጋግሞ መናገር ለምን ይገባል?” ብለው ያቀርባሉ። እውነት አላቸው። ፀሐይ ሲወጣ ጨለማ መሸሹ፣ ሻማ ሲለኮስ ብርሃን መፈንጠቁ ላይቀር “ጨለማን ማውገዝ ምን ጥቅም አለው?” ይላሉ። ይህም እውነት ነው። “ጨለማን ደጋግሞ ከማውገዝ አንድ ሻማ ማብራት” እንደተባለው። ነገር ግን ሐሰት ተደጋግማ በመነገሯ ተከታይ መፍጠር እስከቻለች ድረስ እውነትን ደጋግሞ በመናገር የሚመጣ ምን ችግር አለ? ሻማውንም እየለኮሱ እውነቱንም ደጋግሞ መናገሩስ? ስለዚህ በእውነት ተደጋግሞ መነገር፣ በሻማ መለኮስም አምናለኹ። ደጊመ ቃል እንዲሉ የኢትዮጵያ ሊቃውንት።

እንኳን አገር ቤት ያለው አንባቢ ይቅርና እኛ ከአገራችን በብዙ ሺህ ማይሎች ርቀን የምንገኘው ሳንቀር በየዕለቱ የምንኮመኩመው አዲሱ ትኩስ ዜና የማኅበረ ቅዱሳን እና “የተጠመደለት ወጥመድ” ጉዳይ ነው። በማኅበራዊ ድረ ገጾች እና በጡመራ መድረኮች፣ እንዲህ በሕትመት ውጤቶች በሰፊው ሽፋን ያገኘ ጉዳይ ሆኗል። ብዙ ኢትዮጵያውያን (እምነት ሳይለይ) ይህንን ጣልቃ ገብነት በጽኑዕ እየተቃወሙት እያወገዙት ነው። “ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ የሚባል ከሆነ እኔም አክራሪነትን እወደዋለኹ” የሚሉ ሐሳቦች በብዛት ተጽፈው ተመልክቻለኹ።

“የአክራሪነቱ ነገር”፣ ነፍሳቸውን ይማረውና አቶ መለስ በፓርላማ ተናግረውት በነበረ ጊዜ፣ እኔን ጨምሮ ብዙ ፀሐፍት አስተያየታቸውን የሰጡበት ከመሆኑ አንጻር ወደዚያ መመለስ አይገባ ይሆናል። ማኅበሩ ከፓርቲ ፖለቲካ ጋር ግንኙነት እንዳለው በመንግሥት ሰዎች እና በደጋፊዎቻቸው የሚነሣውን ሐሳብ በተመለከተ ግን የግል አስተያየቴን ላሰፍር እወዳለኹ።

ማኅበሩ ፖለቲካ ውስጥ አለበት? ለመሆኑ ፖለቲካ ውስጥ መግባት/ አለመግባት ምንድነው? ማንኛውም ሰው የተባለ ፍጡር ፖለቲካዊ አመለካከት አለው። ፖለቲካ አልወድም የሚሉ ሰዎች ራሳቸው እንኳን ፖለቲካዊ አቋም አላቸው። ልዩነቱ እያወቁ ማወቅ እና ሳያውቁ መኖር ናቸው። የተለያዩ ሐሳቦች እስካሉ ድረስ፣ አስተዳደሮች፣ ገዢዎችና ተገዢዎች እስካለን ድረስ ፖለቲካዊ አመለካከቶች መኖራቸው ግድ ይመስለኛል። “ፖለቲካ እና ኮረንቲ በሩቅ” የሚለው ሰው ራሱ በኮረንቲ ከመጠቀም፣ ሕይወቱ በፖለቲካ ተጽዕኖ ሥር መውደቁ እስካለ ድረስ ፖለቲካ የማይነካው ኢትዮጵያዊ አይኖርም።

ይኼ በፖለቲካ ምሁራን ሳይሆን እኔን በመሳሰሉ ለፖለቲካው ዕውቀት ተርታ በሆንን ሰዎች ቋንቋ “ፖለቲካ ውስጥ መግባት ወይም አለመግባት” የምንለው የፓርቲ ፖለቲካ ውስጥ መግባት ማለታችን እንደሆነ ይሰማኛል። ፖለቲከኞች የምንላቸው እንደዚያ ያሉ ሰዎችን ነውና። ማኅበረ ቅዱሳን “ፖለቲካ ውስጥ ገባ/ አልገባም” የሚለውንም የምፈታው በዚሁ አንድምታውና አገባቡ ብቻ ነው።

ማኅበሩ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ አባላት አሉት። አባላቱ ሰዎች እንደመሆናቸው ፖለቲካዊ አመለካከት አላቸው። ማኅበሩን በአባልነት ለመቀላቀል የሚያበቃቸው ግን ይህ ፖለቲካዊ አመለካከታቸው አይደለም። የአባላቱ የዓላማ አንድነትና መሠረቱ ማኅበሩ የሚያራምደው ቤተ ክርስቲያናዊ አቋም ብቻ ነው። በሃይማኖትና በአገልግሎት ዓላማ አንድ ናቸው እንጂ በፖለቲካ ርዕዮት የተሰባሰቡ አይደሉም። ሲጀመርስ ስለ ፖለቲካ አመለካከታቸው የት ተጠያይቀው? የት ተገማግመው? የት ተለካክተው? በየትኛው ጊዜ?

ስለዚህም ማኅበሩ አንድ ሃይማኖታዊ አቋም ያራምዳል እንጂ “አንድ ፖለቲካዊ አቋም” የሚባል የለውም። ሊኖረውም አይችልም። ለምን? ምክንያቱም “ፖለቲካዊ አቋምን ለማራመድ” መጀመሪያ ፖለቲካዊ አቋም መያዝ ያስፈልገዋል። ያንን ለማድረግ ደግሞ አባላቱን በሙሉ በዚህ ፖለቲካዊ አቋም ማሳመን ያስፈልጋል፤ ያንን ማድረግ ደግሞ አስቸጋሪ ብቻ ሳይሆን ማኅበሩ የያዘውን ሃይማኖታዊ አቋም የሚጻረርና ማንም ሳይነካው እንዲፈርስ የሚያደርገው ድማሚት ነው።

እዚህ ላይ መነሣት ያለበት ቁምነገር፤ የማኅበሩ አባላት በሃይማኖታዊም ሆነ በፖለቲካዊ አስተሳሰባቸው ራሳቸውን የቻሉ (ማለትም ማመዛዘን የሚችሉ) ክርስቲያኖች እንጂ የአንድ ቡድን ጀሌዎች አለመሆናቸውን ነው። ራሱን የቻለ አስተሳሰብ ያለው ማንኛውም ሰው፣ አባል የሚሆንበትን ድርጅት ያያል፤ ይመዝናል፣ ያስባል። እንደማይጠቅመውና እንደማይስማማበት ከተረዳ ይተወዋል። ጀሌ ግን የተነገረውን ተቀብሎ እንደ በቀቀን ያስተጋባል፤ ሳያውቅ አባል ይሆናል፤ በጥቂት ጥቅም ይደለላል፣ የሚኖርለትም-የሚሞትለትም ቋሚ መርሕ አይኖረውም።

ማኅበረ ቅዱሳንን እና አባላቱን በአገራችን ላለፉት 40 ዓመታት በጠነነው የፖለቲካ ድርጅት ጀሌነት መገምገም ትክክል የማይሆነው ለዚህ ነው። አባላቱ አገልጋዮች እንጂ ካድሬዎች አይደሉም። አመራር ላይ የሚቀመጡት ሰዎች በተራቸው ለማገልገል እንጂ ከሌላው አባል የተለየ መርሕ ለማራመድ አይችሉም። እናራምድ ቢሉም አባላቱ ጀሌዎች ስላልሆኑ ሊከተሏቸው የሚችሉበት ምንም መንገድ አይኖርም። የአባላቱ አንድነት በሃይማኖት እና በሃይማኖት ብቻ ነው። በበሰለ ሚዛን የሚለካቸው ቢኖር ኖሮ በዘር፣ በቋንቋ፣ በፖለቲካ አቋም፣ በትምህርት ደረጃ፣ በዕውቀት፣ በዕድሜ ወዘተ ወዘተ የተለያዩ እንጂ እንደ ሜዳ አህያ አንድ ወጥ እና ልሙጥ አለመሆናቸውን ይገነዘባል።

ስለዚህ አንድ አባል በግልጽ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ ገብቶ የዜግነት ድርሻውን መወጣት ቢፈልግ ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቃል። በማኅበሩ ውስጥ ያለውን የአመራር ኃላፊነት ማስረከብ ይኖርበታል። በዚህ ደረጃ በይፋ ከአመራርነታቸው በሰላም ተሰናብተው ወደፈቀዱት ይፋዊ የፖለቲካ መስመር መጓዝ የቻሉ ሊኖሩ እንደሚችሉ እገምታለሁ። ማኅበሩንም የፖለቲካ ድርጅታቸውንም መምራት የሚችሉበት መንገድ አይኖርም። እነርሱ ፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለማቸውን በማኅበሩ ላይ ለመጫን ቢፈልጉም እንኳን “የፍላጎት መላተም” (“conflict of interests”) ስለሚኖር ሊሳካላቸው አይችልም። የማኅበሩ አባላት በፖለቲካ መሳተፍ የዜግነት መብታቸው ሲሆን በማኅበሩ አገልግሎት መሳተፍ ደግሞ ሃይማኖታዊ የትሩፋት ሥራ እንደመሆኑ ማቻቻል የአባሉ ፈንታ ነው።

ማኅበሩ በፖለቲካ ውስጥ ገብቷል የሚለው (በተለይ በቤተ ክህነቱ ዙሪያ ያሉ ሰዎች) ከ1980ዎቹ ጀምሮ ሲያዜሙት የነበረ የሰለቸ ዜማ ነው። የሚነቅፉት ግን ማኅበሩ “ኢሕአዴግን አይደግፍም” ብለው ስላሰቡ እንጂ “ተቃዋሚ ነው ብለው ስላመኑ” ብቻ አይደለም። ለነገሩ እነዚህ መንግሥትን በዱላነት ለመጠቀም የሚፈልጉ፣ በመንፈሳዊም በዓለማዊም ሚዛን ቢመዘኑ ውኃ የማያነሱ ደመናዎች “ፖለቲካ” የሚሉት አጎብዳጅነትን ነው። መንግሥት እነሱን ይጠቀማል። እነሱም በአቅማቸው በመንግሥት ይጠቀማሉ።

ታዲያ ማኅበሩ የትኛውንም የፖለቲካ ድርጅት እንደማይደግፍ ነገሩን ሥራዬ ብሎ ለሚከታተል ለማንኛውም ሰው ግልጽ ሆኖ ሳለ በዚህ ጉዳይ መወንጀሉ ለምን አስፈለገ? ክርስቶስ አምላካችን ራሱ “ግብር አትክፈሉ ይላል? ለቄሳር አትገዙ ብሏል፤ ንጉሣችን ሳይሆን ንጉሥ ነኝ ብሏል” የሚል ፖለቲካዊ ክስ እንደቀረበበት ሃይማኖትን ብለው የሃይማኖት አገልግሎት ላይ የተሠማሩ ሰዎች በየዘመኑ የሚከሰሱበት ጉዳይ መሆኑን ማስተዋል ያስፈልገናል።

ቅዱስ ሉቃስ “ይህ ሕዝባችንን ሲያጣምም ለቄሣርም ግብር እንዳይሰጥ ሲከለክል ደግሞም፦ እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ ሲል አገኘነው ብለው ይከሱት ጀመር” ሲል እንደጻፈው (ሉቃስ 23፥2)። በሌላው ዓለም ያለውን እንኳን ትተን በአገራችን ያለውን ብናስታውስ፣ ነገር ሰሪዎች በየዘመኑ የነበሩ ቅዱሳን አባቶቻችንን ከነገሥታቱ ጋር በማጋጨት በአደባባይ እስከመገረፍ ያደረሱበት ጊዜ፣ በግዞት በእስር እንዲማቅቁ ያደረጉበት ወቅት እንዳለ ታሪክ ያስተምረናል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን እና የደብረ ሊባኖስ እጬጌ ጻድቁ አባ ፊሊጶስን ለአብነት ብናንሣ አባ ጊዮርጊስ እንደተጋዘ፣ አባ ፊሊጶስ በአደባባይ ራቁቱን እንደተገረፈ እናነባለን።

ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት ላይ ያለ ማኅበር ትናንት እንደፈላ እንደ ክረምት አግቢ ሊታይ አይችልም። መንግሥት ይኼ ሁሉ ሐቲት አይጠፋውም። ማኅበሩ ተቃዋሚም ደጋፊም እንዳይደለ መግለጹ እስካሁን ጉንጭ አልፋ ከመሆን አልዘለለም። መደገፍ የማይችል አካል፣ ባይቃወምም እንኳን ገለልተኛ መሆኑ ለአደጋ ያጋልጠናል በሚል “ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው” የዶሮ ፍልስፍና የተቃኘ ነው።

ከዚህም ባሻገር አባላቱ ከአንድ ዘርና ቋንቋ፣ ባህልና ፖለቲካዊ አቋም የመጡ አለመሆናቸው፤ ይልቁንም ሕብረ ብሔረሰባዊና ኢትዮጵያዊ መሆናቸው እንቅልፍ የሚነሣቸው አካላት መኖራቸው ግልጽ ነው። “አዳሜ በየቅርጫትህ ግባ” ሲባል አንድ ቅርጫት ውስጥ የማይጨመሩ፣ ከሌላውም ቅርጫት ካለው ጋር ዝምድናና ፍቅር ያላቸው፤ ከቅርጫታቸው ውጪ የሚያስቡ ሰዎች ያሉበት ማኅበር መሆኑ የሚያስፈራቸው አሉ።

በውጪ አገር ባሉ የተለያዩ የመንግሥት ተቃዋሚ ቡድኖች ዘንድ ማኅበረ ቅዱሳን ሲጠረጠር እንደኖረ እነርሱም በፈንታቸው “ማኅበረ ቅዱሳን የኢሕአዴግ ደጋፊ መሆን አለበት” ሲሉ ኖረዋል። ለምን እንዲህ አላችሁ ሲባሉ ምክንያቱም “ይህንን የሚያህል ትልቅ ተቋም እንዴት ነጻና ፍፁም ሃይማኖታዊ ብቻ ሊሆን ይችላል? ጠርጥር ጠርጥር” የሚል ጥርጣሬ ያቀርባሉ።

ማኅበሩ አብሯቸው ጀብ ጀብ ላለማለቱ ምክንያቱ ዓላማውና ተፈጥሮው መሆኑን ለመቀበል የአገር ውስጡም የዳያስጶራውም ቡድን፣ እነዚያም እነዚያም ይኸው እንደተቸገሩ አሉ። እነዚያ “የዚያ ደጋፊ ነው” እንዳሉት፣ እነዚያም “የዚያ ደጋፊ ነው” እንዳሉት። ማኅበሩ ደግሞ “አነ ዘክርስቶስ፣ አነ ዘቤተ ክርስቲያን፤ እኔ የክርስቶስ ነኝ፣ እኔ የቤተ ክርስቲያን ነኝ” እንዳለ አለ። መጨረሻውን ደግሞ ዕድሜ ይስጠን እንጂ፣ እናየዋለን።

ይቆየን – ያቆየን

 ይህ ጽሑፍ አዲስ አበባ ለሚታተመው የአዲስ ጉዳይ መጽሔት የተጻፈና በዚያም ላይ ለሕትመት የበቃ ነው።

 

 

 

ሌሎችም ከደሴ አስተዳዳሪዎች ይማሩ ! ግርማ ካሳ

$
0
0

11ባህር ዳር እንደተደረገው፣  ትላንት መጋቢት 28 ቀን፣  በደሴ ከተማ ፣  ከስድሳ ሺሆች በላይ የተገኙበት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል።  የሰልፉን ሁኔታ የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን ስንመለከት አልፎ አልፎ፣  ሰማያዊ የለበሱ የፖሊስ አባላትን ተመልክተናል። በፖሊስና በሰልፈኞች መካከል ግብግቦች አልተፈጠሩም። የተወረወረ ጠጠር የለም። የተሰበረ ንብረት የለም። የተጎዳ፣ የቆሰለ ወይንም የሞተ ዜጋ የለም። ሰልፉ በሰላም ተጀምሮ ነው በሰላም ያለቀው። እንዲህ አይነት ሰልፍ ደስ ያሰኛል።

 

ለዚህም በዋናናት የደሴን ሕዝብ ላመሰግን እወዳለሁ። ኢትዮጵያዊ ጨዋነቱን እና ሰላማዊነቱን ነው በድጋሚ ያስመሰከረው። ፈርቶና አንገቱን ደፍቶ መቀመጥ ይችል ነበር። ነገር ግን ፍርሃትን አዉልቆ፣ ከአንገቱ ቀና ብሎ፣ የግፍ ቀንበርን ተቃወመ።  በአደባባይ ድምጹን በማሰማት ጀግንነቱን አሳየ። እኔም፣ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ፣ ሌሎች ኢትዮጵያዉያንን በመቀላቀል፣  በደሴ ሕዝብ መኩራቴን መግለጽ እወዳለሁ።

 

በሁለተኛ ደረጃ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላት እና ደጋፊዎችን እንዳመሰግን ይፈቀድልኝ። ሕዝብ የሚያደራጀው ድርጅት ከሌለ ለመንቀሳቀስ፣ አይቻልም ባይባልም፣ ከባድ ነው የሚሆንበት። የአንድነት ፓርቲ በዚህ ረገድ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ነው።

 

የአንድነት ፓርቲ ከአገዛዙ ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚ ነን ከሚሉትም በርካታ ቀስቶች ሲወረወሩበት እንደነበረ የሚታወቅ ነው። ዉጭ ተቀምጠው ብዙ የሚያወሩ ፣ ብዙ ብለዋል። ነገር ግን አንድነቶች፣ ዋጋ እየከፈሉ፣ ቲዮሪ እየደረደሩ ማውራት ሳይሆን፣ ትግል ማለት ምን ማለት እንደሆነ በተግባር እያስመሰከሩ ናቸው። ከደሴና አካባቢው ሕዝብ ጋር ሆነው፣ እያነቁትና እየቀሰቀሱት፣ ሕዝቡ ደፍሮ ድምጹን እንዲያሰማ ማድረግ መቻላቸው ትልቅ ነገር ነው። ከዚህ የበለጠስ ምን አለ ? ለዉጥ ሊያመጣ የሚችለው እኮ ሕዝቡ ብቻ ነው !

በሶስተኝነት፣ አዎን፣ የደሴን አስተዳደር ላመሰግን እወዳለሁ። አንዳንዶች «መስራት ያለባቸውን ስለሰሩ ለምን ይመሰገናሉ ?» ሊሉ ይችላሉ። ልክ ነው፣  ሕግን አክብረዉ፣ ዜጎች ሰለማዊ ሰልፍ እንዲያደርጉ መፍቀድ ስራቸው ነው። ነገር ግን እንደ አዲስ አበባ ፣ ባሌ/ሮቢ ፣ መቀሌ……ካሉ፣ ሕገ-መንግስቱን ንቀዉ የዜጎችን መብት በመጋፋት ሰላማዊ ሰልፎ እንዳይደረጉ ከሚያግዱ አስተዳደሮች ጋር፣ የደሴ አስተዳደር ሲነጻጸር በጣም የተሻለ ሆኖ ነው የተገኘው። በጎን ሕግን እንዲያፈርሱ የሚደረግባቸውን ጫና ተቋቁመው፣ ሕግን ማክበሩን መምረጣቸው ያስመሰግናቸዋል።

 

በቅርቡ እንደተከታተልነው፣ አንድነት ፓርቲ በአዲስ አበባ ሰልፍ እንደሚያደርግ ባሳወቀ ጊዜ ፣ አስተዳደሩ ሕግ ወጥ ደብዳቤዎችን በመጻፍ ለሰልፉ እውቅና አልሰጥም ብሎ እንደነበረ ይታወቃል። ከዘጠኝ ወራት በፊት፣ የሚሊዮኖችም ድምጽ ለነጻነት፣ ክፍል አንድ፣ እንቅስቃሴ ወቅት፣ አሁንም የአንድነት ፓርቲ በመቀሌ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ቅስቀሳዎች አድርጎ፣ ሰልፉ  ነገ ሊደረግ ዛሬ፣  «መቀሌን እንኳን አንድነት ቅንጅትም አልደፈራትም» በሚል፣ የአንድነት መራር አባላትን በማሰርና የቅስቀሳ መኪናዎችን በማገት፣ የመቀሌ የሕወሃት አስተዳዳሪዎች ሰልፉ እንዲጨናገፍ ማድረጋቸው በወቅቱ ተዘግቧል። በባሌ/ሮቢ በተመሳሳይ ሁኔታ፣ የቅስቀሳ ዘመቻ ተደርጎ፣ የሰልፉ ቀን በጠዋቱ፣  ሰልፍ ከተደረገ ከፍተኛ ደም መፋሰስ ይኖራል የሚል ዛቻ በመሰጠቱ፣ ለሕዝብ ደህንነት ሲባል ሰልፍ እንዳይቀጥል የተደረገበት ሁኔታም ነበር። ታዲያ ደሴዎች አስር እጥፍ አይሻሉም ?

እንግዲህ ሌሎች የአገራችን ባለስልጣናት፣ ከደሴ አስተዳደር ይማሩ እላለሁ። «ፖሊሶች ፣ ዜጎችን የሚደበድቡና የሚያወኩ፣ የጥቂት የአገዛዙ ባለስልጣናት አገልጋዮች የሆኑ፣ ሕዝብን የሚያስጨንቁ፣ ዛቻና ማስፈራሪያ የሚሰነዝሩ፣ በሕገ መንግስቱ የተደነገጉ ሕጎችን የሚሸረሽሩ ሳይሆን፣ በደሴ ሰልፍ እንዳየነው፣  ከሕዝብ ጋር እየሄዱ፣  ሕግና ስርዓትን እያስጠበቁ፣  ሕዝብ የሚያገልግሉና ለሕግ የሚገዙ ይሁኑ» እላለሁ።

 

ለአገራችን የሚያዋጣዉ ሁላችንም በሕግ ፊት እኩል ስንሆን ነው። ባለስልጣናት ሕግን ካከበሩ አገር ሰላም ይሆናል። በደሴ እንዳየነው ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች በሰላም ተጀመሮ በሰላም ይጠናቀቃል። እንግዲህ ሁላችንም ለሕግ ተገዥዎች ሆነን አገራችን በፍቅር እንገባ።

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live