Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

(ሰበር ዜና) ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ከሀገር እንዳይወጣ በኢሚግሬሽን ታገተ

$
0
0

Yilkal Getnet
ሰማያዊ ፓርቲ እንዳስታወቀው በአሜሪካን ሀገር ስቴት ዲፓርትመንት የተዘጋጀለትን ወጣት የአፍሪካ መሪ የሚል ሽልማት ለመውሰድ ዛሬ ሌሊት ወደ አሜሪካ ያቀና የነበረው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በቦሌ አየር መንገድ ከተገኘ በኋላ ከሀገር መውጣት አትችልም በሚል ታግቶ ይገኛል፡፡ በረራው 4 ሰአት ላይ የነበረ ሲሆን እስካሁን እስከሌሊቱ 8 ሰኣት ድረስ ታግቶ ይገኛል፡፡

ዝርዝር መረጃዎች እንደደረሱን እናቀርባለን።


የዋሸው ማን ነው? –ለመምህር ግርማ ከቤተክርስቲያን የተጻፉላቸው 14 ደብዳቤዎችና ምስክር ወረቀቶች እጃችን ገቡ

$
0
0

girma wendimu
“ለምንድ ነው የምትገፉኝ?” – መምህር ግርማ

(ዘ-ሐበሻ) ዘ-ሐበሻ የመምህር ግርማ ወንድሙን ጉዳይ ተከታትላ በመዘግብ ላይ ትገኛለች። አንባቢዎቻችን እውነታውን እስኪጨብጡ ድረስ ዘገባዎችን ማቅረቧ የሚቀጥል ይሆናል። በትናንትናው የዜና እወጃችን ቤተክርቲያን በአቡነ ገሪማ አማካኝነት የተጻፈን ደብዳቤ በመጥቀስ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን “መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ” በሚል ስያሜ የተበተነው ደብዳቤ ሕገ ወጥ በመሆኑ የሚመለከተው ሁሉ ይህን ግንዛቤ እንዲወስድ አሳሰበች፡፡” በሚል የተጻፈውን ደብዳቤዎች አቅርበን ነበር።

ቤተክርስቲያን መምህር ግርማን በፎርጂድ ደብዳቤ ማሰራጨት የሚወነጅል ደብዳቤ ቢወጣም ዘ-ሐበሻ ለመምህር ግርማ ከቤተክርስቲያን የተጻፉ 14 ደብዳቤዎችና የምስክር ወረቀቶች ደርሰዋታል። ይህም ፎርጂድ ደብዳቤ ጽፈዋል በሚል የወነጀላቸውን አካል ወይም መምህር ግርማ ህጋዊ ደብዳቤ ተሰጥቶኛል ብለው ያሰራጩትን ደብዳቤ ለተመለከተ ማን ነው የዋሸው ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ሊሆን ይችላል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ። ያንብቡ ና የዋሸው ማን ነው ለሚለው ምላሽ ይስጡ።

“አንድ ሙዚቀኛ የሙዚቃ ትምህርት ቤት አንድ ሰርተፊኬት ብቻ ካለው ተቀባይነትና የታዋቂነት ክብር ይሰጠዋል፤ የሥራ መስኩም ይወደዳል፣ ይፈቀራል። ማንም የሚቃወመውም የለም፤ በሁሉም ዘርፍ ተፈላጊ ተወዳጅ ተሸላሚ ነው። በክፉ መንፈስ ከተጠቁት ጋር ለምውለው ለእኔ ግን የተገላቢጦሽ ነው። በሺህ የሚቆጠሩ የጥሪ አገልግሎትና የምስጋና ሰርተፊኬት አለኝ። ዛሬ ይህ ሁሉ ውሸት ሆኖ የመንደር አስማተኛ፤ የሱዳን ጠንቋይና የማይታወቅ አጭበራባሪ መለያ ስሜ ሆነ፤ ግን ለምን? ከጥቁር ፀጉር እስከ ነጭ ሽበት ያገለገልኩባት ቤተክርስቲያን ትምህርትና ፈውስ የሚፈልገው ሕዝብ ሲበዛ የፈውሱ ሂደት ከሃገር ውስጥና ከውጭ ዓለም ነጮችን ጨምሮ ሲከናወን የቤተክርስቲያን የወር ባጀት እና የዓመት ገቢ በእጥፍ ሲያድግ ለአባቶች እና በየአገረ ስበከቱ ላሉ አባቶች ሕዝቡ የፈውስና የትምህርት ፍላጎት ጥያቄ ሲበዛ ለምንድ ነው አስማተኛና ጠንቋይ የተባልኩት? ከነ ሙሉ መረጃው በሚቀጥለው… “አጥርቶም አየ… ከሩቅም ሳይቀር ሁሉን ተመለከተ” (ማር.23) መቆሚያና ማብቂያ የለውም ፈተና… ግን ለምን? ለምንድን ነው የምትገፉኝ?”

- መልአከ መንከራት ግርማ ወንድሙ

ደብዳቤዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአንድነት የወላይታ ዞን ምክር ቤት ስብሰባን የመለስን ቲቨርት የለበሱ የመንግስት ካድሬዎች በኃይል አደናቀፉት

$
0
0

daniel tefera

የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ እና ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሺበሺ ደህንነታቸው አደጋ ላይ ነው፡፡

የሟቹን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊ ምስል ያለበት ቲሸርት የለበሱ ከ 10 የሚልቁ የመንግስት ካድሬዎች በወላይታ ሶዶ እየተደረገ የነበረውን አንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን ምክርቤት ስብሰባን በሀይል ማደናቀፋቸውን ከስፍራው ለፍኖተ ነጻነት የደረሰው ዘገባ አመለከተ፡፡
ካድሬዎቹ የስብሰባ አዳራሹን በሃይል በመስበር ከተሰብሳቢዎቹ ላይ የተለያዩ ሰነዶችን የቀሙ ሲሆን ብብደባ በመፈፀም ላይ ናቸው፡፡ በስብሰባ አዳራሹ ውስጥ የነበሩት የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ እና ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሺበሺ ደህንነታቸው አደጋላይ መሆኑን ለፍኖተ ነፃነት ተናግረዋል፡፡

የኢሕአዴግ መንግስት የማኅበረ ቅዱሳንን አመራርና አባላት በአክራሪነት የሚከስ ዶክመንተሪ ሊያዘጋጅ ነው ተባለ

$
0
0

ዶክመንተሪው የ2007 ሀገራዊ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት አካል እንደኾነ ተጠቁሟል

‹‹ማስረጃ አቅርቡና እንነጋገርበት›› ለሚለው የማኅበሩ ጥያቄ ምላሽ አልተሰጠም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሲኖዶሱን ይኹንታ አግኝቶ በመላው አገሪቱ የሚንቀሳቀሰውን የማኅበረ ቅዱሳንን አመራርና አባላት በአክራሪነት የሚከስ ነው የተባለ ዶክመንተሪ ፊልም ለማዘጋጀት መታቀዱ ተጠቆመ፡፡
mahbere-kidusan-300x168
የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አንዳንድ ሓላፊዎች አቀብለውታል በተባለ መረጃ እንደሚታገዝና በመንግሥት አካል እንደሚሰናዳ የተገለጸው የዶክመንተሪ ዝግጅቱ በማኅበሩ ኻያ አመራሮች እና አባላት ላይ እንዳነጣጠረ ተገልጧል፡፡ መንግሥት በምርጫ – 97 ውጤትና በተከታይ ኹኔታዎቹ ላይ ባካሔደው ግምገማ፣ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው የሚባሉ ግለሰቦች በተለይ በገጠር ቀበሌዎች ለተቃዋሚዎች ተሰሚነት ማግኘት በምክንያትነት መጥቀሱ በዜና ጥቆማው የተመለከተ ሲኾን ‹‹የአክራሪነትና የጽንፈኛ ፖሊቲከኞች ምሽግ ነው›› በሚል የሚያቀርበው ክሥም ከዚኹ የሚነሣና ለመጪው የ2007 ሀገራዊ ምርጫ የሚደረግ ቅድመ ዝግጅትም አካል እንደኾነ ተነግሯል፡፡

በቅድመ ዝግጅቱ የሚወሰዱ ርምጃዎች የማኅበሩን አቅሞችና እንቅስቃሴዎች በመቆጣጠር በተለይም የማኅበሩ መሠረቶች ናቸው የሚባሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያትን ‹‹በሴኩላሪዝም መርሖዎች የመግባቢያ ሰነድ›› ጠርንፎ ‹የአገልግሎት ቅኝቱን የማስተካከል› ዓላማ እንዳላቸው የገለጸው የዜና ምንጩ፣ ይህም ካልተሳካ በተከታታይ አስተዳደራዊ ርምጃዎችና የተቃውሞ ቅስቀሳዎች ማኅበሩን በማወከብ ተቋሙን ለዘለቄታው የማፍረስ ውጤት ሊኖረውም እንደሚችል አመልክቷል፡፡’

ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት አብያተ ክርስቲያናት የተጠሩ ናቸው የተባሉ አስተዳዳሪዎችና ሠራተኞች የሚሳተፉበት እንደኾነ የተገለጸና ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በማኅበሩ አገልግሎት ላይ ቁጥጥሩን እንዲያጠብቅ የሚጠይቅ ስብሰባ በዛሬው ዕለት በቤተ ክህነቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚካሔድ የተዘገበ ሲኾን ዓላማውም ‹‹በአክራሪዎችና ጽንፈኛ ፖሊቲከኞች ምሽግነት፣ የቤተ ክህነቱን አሠራር ባለማክበርና ከቤተ ክህነቱ በላይ ገዝፎ በመውጣት›› ማኅበሩ የሚከሰስባቸውን ኹኔታዎች በማጠናከር ለታቀዱት ርምጃዎች የሚያመቻች ነው ተብሏል፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ላይ በማተኮር የተማረው ትውልድ ሃይማኖቱን የሚወድ፣ ግብረ ገብነት ያለው፣ ሀገሩንና ቤተ ክርስቲያኑን በዕውቀቱ፣ በሞያውና በገንዘቡ የሚያገለግል ብቁ ዜጋ ይኾን ዘንድ በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደርያ ደንብ መሠረት በመሥራት ላይ እንዳለ የሚገልጹ የማኅበሩ አባላትና ደጋፊዎቹ፣ ማኅበሩ ለቀረቡበት ክሦች የሚመች አደረጃጀት ይኹን ባሕርይ እንደሌለው በመግለጽ ተጠሪ ከኾነለት ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጋራ በአሠራር ሒደት የሚፈጠር ክፍተትን በማጦዝ የሚሰነዘሩ ውንጀላዎች ተቀባይነት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡ የተጠቀሱት ክሦች ላቀረቡት አካላት ‹‹የሚነገረውና የሚጻፈው እኛን የሚገልጸን ስላልኾነ ማስረጃ አቅርቡና እንነጋገርበት›› የሚል ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ለሠለጠነ ውይይት ፍላጎት እንደሌላቸው አባላቱ አስረድተዋል፤ በምትኩ ‹‹ርምጃ እንወስዳለን›› በማለት በተለያዩ መድረኮች ማኅበሩን ማሳጣትና መክሠሥ እንደሚመርጡም ለፋክት መጽሔት አስታውቀዋል፡፡

ታቅዷል የተባለው የዶኩመንተሪ ዝግጅት እውነት ከኾነም ማኅበሩን ብቻ ሳይኾን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የማዳከም አጠቃላይ ዘመቻ አድርገው እንደሚቆጥሩትና በቀላሉ እንደማይመለከቱት አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፡ ፋክት መጽሔት ቅጽ ፪ ቁጥር ፴፰፤ መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም.)

ወላይታ ሶዶ ነፃነት አልባዋ የማፊያ ካድሬዎች ከተማ!!!

$
0
0

ከወላይታ ዞን የአንድነት ፓርቲ አመራሮች የእስርና እንግልት ማብራሪያ

 

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራና ድርጅት ጉዳይ ም/ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ በደቡብ ቀጠና በወላይታ ዞንና በሲዳማ ዞን አዋሳ ከተማ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር የፓርቲውን የትግል ስትራቴጅክ ዕቅዶች ላይ ማብራሪያ፣ ደንብና ፕሮግራም ለመስጠት እንዲሁም የስራ ጉብኝት ለማድረግ በ 12/07/06 ወደ ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ተገኝተው ነበር፡፡ በ13/07/06 ደግሞ ከሶዶ ከተማ ስራ አስፈፃሚና ከወረዳ አመራር አባላት ጋር የፓርቲያችንን ደንብ፣ ፕሮግራምና ቀጣይ የስራ አቅጣጫ አስመልክቶ የተሰናዳው ውይይት ላይ ለመታደም ከ32 በላይ አመራሮችም ተገኝተው ነበር፡፡

ቅዳሜ በ 13/07/06 ዓ.ም ከአባላት ጋር ባለው ዕቅድ መሰረት የፓርቲያችንን ህጋዊ ሰነዶችን ለወረዳና ለዞን አመራሮች ለመስጠት፣ ቀጣዩን ሀገራቀፍ ምርጫ አስመልክቶ መረጃ ለመለዋወጥ ምርጫችን የነበረው የፓርቲያችን አባል የሆነውና ወጣ ብሎ ፀጥታ የሰፈነበት ግቢ ነበር፡፡ ይህንን ለማድረግ ህገ መንግስታዊ መብት ነበረን፡፡ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የፖለቲካ ደንብና ፕሮግራማቸውን ለዞንና ለወረዳ አመራሮች ለማስጨበጥ ፈቃድ እንደማያስፈልግ ጠንቅቀን እናውቅም ነበር፡፡

በተለይም ሃለማሪያም ደሳለኝ በሞግዚትነት ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ወላይታ ሶዶ ነፃነት አልባ ከተማ እንደሆነች ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ ወላይታ በካድሬ ተወጥራለች፡፡ ዝርዝሩን በቀጣይ እንደምናቀርብ ቃል እየገባን ለአሁን በእኛ ላይ የደረሰውን በቅንጭቡ እንደሚከተለው ለኢትዮጵያ ህዝብና ለታሪክ እናቀርባለን፡፡

1. 32 የሚሆኑ አንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን አመራሮች የተሰባሰቡት ከላይ በገለፅነው አላማና ህገ መንግስታዊ መብታችንን ተጠቅመን ቢሆንም ለውይይት ቅድመ ዝግጅት ስናደርግና ውይይቱን ለመጀመር ስንዘጋጅ መታወቂያ የሌላቸው ከ 8-10 የሚሆኑ ጡንቻቸው የፈረጠመ ግለሰቦች እንደ ኮማንዶ ለውይይት የተገናኝበትን የአባላችንን ጊቢ ሰብረው በመግባት የያዝናቸውን የፓርቲ ሰነዶች፣ ሳምሰንግ ጋላክሲ ስልኮችና ያገኙትን ሁሉ ዘርፈው ሂደዋል፤ አመራሮችን ደብድበዋል፡፡

2. እነዚሁ ደብዳቢዎች ታርጋ ቁጥር በሌላቸው ሞተሮች በመታጀብ ፖሊስ ይዘው በመምጣት ፕሮግራማችንን ለማደናቀፍ በሃይልና በጉልበት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስደውናል፡፡
3. ፖሊስ ጣቢያውም እኛን የደበደቡንንና ንብረታችንን የቀሙንን ሲቢል ለባሽ ካድሬዎች በመልቀቅ የአንድነት ፓርቲ 20 አመራሮችን የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ሻለቃ ላሊሼ ኦሌ ቢሯቸው አስገብተው ችግሩን እንደሚቀርፍ አመራር ካነጋገሩንና ቃላችንን ከተቀበሉ በኋላ ሞባይሎቻችንን በመንጠቅ እንድንታሰር አድርገዋል፡፡
4. የእስሩ ሰዓት ከቀኑ 5፡00 ጀምሮ ነው፡፡ እንድ ቀፋፊና አስቀያሚ ማጎሪያ ውስጥ ካስቀመጡን በኋላ ከምሽቱ 2፡00 ላይ ህገወጥ ስብሰባ አድርጋችኋል በማለት ቃል ስጡ የሚል ምዝገባና ህገ ወጥ ስብሰባ እንዳደረግን እንድንመሰክር ለማስገደድ ቢሞክሩም እኛ መብታችንን እንደተጠቀምን እንጂ እነሱ እንደተረጎሙት ህገ ወጥ ስብሰባ እንዳላደረግን ሀቁን ስንነግራቸው እንዲሁም ሀሰትን ከመቀበል መታሰር እንደሚቻል የአንድነት አባላት ቁርጠኛ እንደሆንን ሲያውቁ ግራ ተጋብተው የበላይ አካል እስከሚያረጋግጥላቸው ጠብቀው ከእኩለ ለሊት በኋላ (ከምሽቱ 6፡30) በኋላ በእስር ላይ የቆዩ ከ20 በላይ ከፍተኛ አመራሮች እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ ይሄ የሆነው ለመፍታት ታስቦ ሳይሆን ከወረዳ የመጡ አባላት ማደሪያ ቦታ እንዲያጡና ለአደጋ እንዲጋለጡ በማሰብ ነው፡፡

5. ስንታሰር ከተዘረፉ ሞባይሎች ውጭ በፖሊስ ጣቢያ አዛዡ ተይዞ የነበረው የታሳሪዎች ሞባይል ባልታወቀ ነገር ተነክሮ ከአገልግሎት ውጭ ተደርጓል፡፡ ሞባይላችን የተነከረውና ከጥቅም ውጭ የተደረገው በኬሚካል ይሁን በሌላ ነገር አልተረጋገጠም፡፡ የማንኛችንም ሞባይል ግን ከጥቅም ውጭ ሁኗል፡፡ ይሄ የሆነው የፖሊስ አዛዡ አቶ ላሊሼ ቢሮ የታሰረ ሞባይላችን ነው፡፡

ነገ ምን እንደሚገጥመን ማወቅ አይቻልም፡፡ ያረጋገጥነው ነገር ቢኖር ወላይታ ሶዶ ነፃነቷን የተነፈገች፣ በታርጋ አልባ ሞተሮች የምትታመስና ምንም ዋስትናና ህግ የሌለባት ከተማ መሆኗን ነው፡፡ ስለዚህ ነፃነት አልባዋ ወላይታ ነፃ መውጣት አለባት!!!

የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን አመራር አባላት ከምሽቱ 9፡00 ሠዓት

 

ሶዶ ከተማ

UDJ

ከቶ ዬት ይሆን ዬፍላጎታችን ሴሉ ያለው (ከሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 23.03.2014 ( ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

blue partyበእኔ ውስጥ እኔ ነኝ ያለሁት። እማስበውም አምጽፈወም በነፃ ዕይታ መንፈሴን ቃልቲ ወይንም ቂልንጦ ሳልክ ውስጤ የሚለኝን በድፍረትና በልቡ ሙሉነት ነው። ስለዚህ እኔ „እኔን“ ስገልጽ ተሸማቅቄ ወይንም ምን ይሉኝ ብዬ ወይንም አዩኝ አላዩኝ ብዬ ተሸፋፍኜ አይደለም። በዬትኛውም ዘመንና ጊዜ እኔ „እኔን“ ተውሶት ወይንም ተበድሮት አያውቅም። በጣም ብዙ ሰዎች በተለያዬ አጋጣሚ ከልጅነት እስከ እውቀት ሥርጉተን ያውቋታል። ጊዜና ሁኔታ ሲፈቅድም ቆመው ይመሰክራሉ። ባነብም ባዳምጥም እምኖረው ግን እራሴን ሆኜ ነው – በጣም በእርግጠኝነት። ተዳብሎ የሚኖር ፍላጎት ሆነ ጭሰኛ ወይንም ሞፈር ዘመት ስሜቴ ያዘለ ወይንም የሙጥኝ ብሎ ጥገኝነት የጠዬቀ ፍላጎት ኖሮኝ አያውቅም። ለዚህም በሙሉ መንፈስ እራሴን ሆኜ እንድኖር መንፈሴን በማያቋርጥ የራስ መተማማን መስኖ አልምተው ያሳደጉኝን ወላጆቼንና እጅግ የሚናፍቀኝን ማህበረሰቤን አመሰግናለሁ።

 

ስለዚህም እኔ ለምሰጠው አስተያዬት እኔን የወከለ ስለሆነ ጊዜ ወስዳደችሁ ለምታነቡት ወገኖቼ እንዲሁም፤ አሉታዊ ሆነ አዎንታዊ አስተያዬት ለምትሰነዝሩት ወገኖቼ እኩል አክብሮት አለኝ። እማርበታለሁም። አመሰግናችኋላሁ። አለፍ ብላችሁ መሄድ ካሰኛችሁም ሥርጉተ ጠጥታው ያደገችው ፈተና ሆነ ተመክሮ ሁሉንም ለማስተናገድ ስለመቻሏ መለኪያዋ ስለሚሆን አዝናንታ እንደምታስተናግደው ተሰፋ አላት – እራሷ።

 

ትናንት ነበር ያነበብኩት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ፓርቲያቸውን ወክለው ወደ አሜሪካ የተዘጋጁበት ጉዞ እንደ ታገዱ ከዘሃበሻ። ከዚህ የባሰ ፈተና ብጠብቅም አዘንኩኝ። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/13729

እጅግ ያሳዘነኝ ደግሞ ከአንባብያን የተጻፉት አስተያዬቶች ናቸው። ለመጻፍም ያነሳሳኝ ይሄው ነው። አንዱ ወያኔ ያዘጋጀው ነው አትመኑት የሰማያዊ ሊቀመንበር እንደ ልደቱ ነው ይላል። ሁለተኛው ደግሞ ወርዶ ታች ሰፈር ይቆጥራል። ወያኔ ከወሰደው የእገዳ እርምጃ ሁለቱም አሉታዊ ሆነ አዎንታዊ አስተያዬቶች አሳዘኑኝ። ሰው እንዴት እራሱን ማሸነፍ ይሳነዋል። እኛ እንዲህ መንደር ካሰኘን፤ ስለምን ወያኔን እንነቅሳለን። ለሁላችንም መዳኛችን ኢትዮጵያዊነታችን ነው። ማናቸውም ሰው ሲያጠፋም ሆነ በጉ ሲሰራ መመዘን ያለበትም በዜግነቱ መሆን አለበት እንጂ ጎጡ?!  ክብርና ግርማ፤ ፍቅርና ትህትና፤ ናፍቆትና መሆን ያሉት ከሚስጥሩ እንብርት ከኢትዮጵያዊነት ላይ ነው። የትናንት ጀግኖቻችን ናሙናነት ወተታቸው የታለበው፤ የሞቱት የተሰዉት ለሚስጥርነታቸው ነው …. ጠበል ቢጤ በዬጓዳው ሳያስፈልግ አይቀርም …. እኔ እማውቀው የሰማያዊ ሊቀመንበር ኢ/ ይልቃል ጌትነት ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን ነው። ከዚህ ባለፈ መንፈሳችን ተቋማቱ ላይ እናሳርፍ፤ ፍቅራችንም እምነታችንም ከጋራው አመራር ላይ …. ከፓርቲው ንጥር መርህ፤ ይህ ከሆነ በስበብ አስባቡ በሚፈጠሩ ስንጥሮች አንታወክም ….

 

ሌላው ያነበብኩት አስተያዬት ብቃትን ማዬት የሚናፍቀን እንዳለን ሁሉ፤ ዓይንህ ላፈር የምንል መኖራችን ፍላጎታችን ጋር ምን ያህል እዬተላለፍን እንደመንባዝን ሰፊ ስዕል ነበር። ሰማያዊ ሲመሰረት ጀምሮ እኔ ከልብ ሆኜ እከታተለዋለሁ። አሁን ባላቤት ያላቸው ይመስለኛል ውጪ ሀገር። የሎቢ ተግባር የሚሰራላቸው። ቀደም ባለው ጊዜ ባልነበራቸው ሰዓት የሚያቅዷቸው፤ ሃላፊነት ወስደው የሚወስዷቸው ፈጣንና ደፋር እርምጃዎችና ውጤቶቻቸው፤ ፈተናዎቻቸውና ፈተናውን ተከትለው የሚያሰዮዋቸው ጥንካሬ ሁሉ ይደንቁኝ ስለነበረ ከረንት ላይ አንብቤ አስተያዬት ከሥር በጣም በትጋት እጽፍበትም ነበር።

 

ጉልህ ድፍረታቸውን ያዬሁበት የመጀመሪያው እርምጃቸው የሙሶሎኒን ግፍ ሊዘከር አይገባውም በሚል መንግሥት ነኝ የሚለው አካል ተቀምጦ እነሱ ነበሩ ቀዳሚውን የመከራውን ገፈት ፉት ያሏት፤ ከዛም በኋላ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ግልጽ ያለ አቋም መወሰዳቸው ብቻ ሳይሆን ተግባር ላይ መገኘታቸው አበረታች ነው – ለእኔ። በዛ ላዩ ታች እሳት በሚጋረፍ ቃጠሏማ ወጀብ ሆነው ዕለታዊ ቋያውን ተቀብለው በቅንነትና በሃቀኝነት እዬተንገረገቡ መገኘታቸው ወያኔ ሊያሰኛቸው ከቻለ እውርነት ነው። ሰማያዊ እንደ ተቋም ጠንካራ ራዕይና ጠንካራ ፍላጎት ይዞ በድፍረት እዬተንቀሳቀሳ ያለ ቀንበጥ ፓርቲ ነው – ለእኔ። ነገ ምን ይሆናል? ሥርጉተ ጠንቋይ አትቀልብም።

 

አሁን ባለው ሁኔታ ግን መሰረት የያዘ የተግባር ትልማና ክንውን እያዬሁ ነው። አንጋፋ የሚባሉት አብሶ ለህሊና መሰናዶ ቁብ ሲሰጡት አይታዩም። እነሱ ግን ህሊናን ከማሰናዳት ጀምሮ ያለው መንፈስ ጠንካራ ነው። አጋዥ ተቋማትን ወይንም ክንፎችን አጠናክሮ ማውጣት ብቻ ሳይሆን እንደዬባህሪያቸው „የእንቢታን“ተግባር መሸለማቸው በራሱ የብርታት መለኪያ ነው። አጋጣሚዎች ሳይበክኑ አቅምን ከሥር በመገንባት እረገድ ጅምሩም ፍሬ አዘል ነው። በአጭር ጊዜ ዘለግ ያለ ተግባርና ተመክሮውም ጠቋሚ ተስፋ አለው። ይህ ውጤታማ የግልና የቲም ተግባር ተናጠላዊ ፍርጃ የሚያሰጥም አይደለም። አመራሩ መደማመጥ፤ መከባበር መተማመን አስከቻለ ድረስ አውዱ ሰላም ነው፤ በሰላም መስመር ደግሞ ትርፍ አለ ….

 

ከኢንጂነር ይልቃል ጌትነት አንድ ሥንኝ ልዋስና „የድርሻ ልውውጡ“ ሰርቷል የሚያሰኘው ቁምነገር ያለውም ከዚህ ላይ ነው። ወጣት ለመኖር የሚጓጓ ቢሆንም ከፍላጎቱ በታች ባለው እንጂ በላይ ባላው ነገር አይደለም። እውነት ለመናገር ወጣቶች ለግል ኑሯቸው ስስታሞች አይደሉም። እንዲያውም የወያኔ መሰሪነት ዶክተሪን ለግል መኖር ነበር። ግን ተፈጥሯቸው አልፈቀደላቸወውምና በዬአጋጣሚውም የምናዬው የወያኔ ፍላጎት አብሶ ኢትዮጵያን በሚመለከት ተዘቅዝቆ ሲንጠለጠል ነው። ስለሆነም በዚህ ጠቀራማ ዘመን ብሄርና ብሄረሰብ እዬተባሉ ያደጉ የትናንት ለጋዎች በንጹህ መንፈስ ስለ አንድ ህዝብና አንድ ሀገር ፊት ለፊት ወጥተው፤ በባንዳነት ሀገርን በመበተን ላይ ያለውን ወያኔ እዬተፋለሙ መገኘታቸው ሊያስመሰግናቸውና እግዚአብሄር ይስጣችሁ ሊያሰኛቸው ይገባል። ይህንን በማደረጋቸውም  በዚህ ዙሪያ ቅሬታ ያላችሁ ወገኖች ድምጻችሁን አትስጡን ሲሉም አዳምጫቸዋለሁ። በጣም ደፋር እርምጃ ነው። ስለምን ትግላቸው ትውልድና ታሪክን፤ ሀገርን ከማዳን ላይ በጽኑ የተገነባ ስለሆነ ነው እንጂ በነፍስ ወከፍ የነበራቸው ቦታ ሆነ ኑሮ በቂ ነበር …. ማለት ይቻላል።

 

ግን አኛ አልታደለንም፤ የሚሻል፣ የሚበልጥ፣ የተወጣላት ነገር የማዬት። እንዲያውም የነጻነት ትግሉ ቤተሰቦች ሆነን አሁን በተገኘው እውቅናና ወያኔ በወሰደው የጉዞ እገዳ እርምጃ መስጥረን ደስ ሚለን የምንኖርም እንኖራለን። የእኛ ጀግናችን አደባባይ ወጥቶ እልፎችን አሰልፎ ወደ ፊት ሲገሰግስና ትርፍን ሲዝቅ ሳይሆን፤ ይልቁንም  በጠላት እጅ ገብቶ ሲታሰር፤ ሲታፍን በጠራራ ጸሃይ በባሩድ ሲነድ፤ ወይ እንደ የኔሰው ገብሬ በቤንዚን እራሱን አርከፍክፎ አቃጥሎ አምድ ሲሆን፤ ወይን ሀገር ጥሎ ተሰዶ ፊት ለፊት መጋፈጡን ሸሽቶ ለዕለት ኑሮው ሲያድር ብቻ ነው። በቃ ያልተሰረ ታታሪ፣ ያልተፈነ ባተሌ ስለነገ የሚፈለገውን ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት እወስዳለሁ ብሎ ለሚገፋጥ  ከወያኔ በበለጠ እኛው ስናሸው ሲሰኘንም ወያኔ በማለት ወስደን ከጠላት ጋር ስንለጥፈው  – አለመታዳል።

 

ከዚህ በተጨማሪ እኔ በግሌ „ሰማያዊ ጊዜ ገና ነው ተገጥሜ ለመሰፋት እኔ ለጋ ነኝ። መሬት ረግጬ እራሴን ችዬ ለመንቀሳቀስ ጊዜ እሻለሁ፤ ወይንም እራሴን ችዬ እድሌን እሞክራለሁ“ ማለቱን እራሱ ልናከብርለት ይገባል። ከእንጨትም፣ ከተራራም፣ ከቀንም፣ ከቤትም፣ ከሰውም፣ ከመሬም ዕድል አለ። እንታገልለታለን የምንለው ነፃነት እኮ ይህው ነው። ልንጫነው በፍጹም አይገባም። በተገኘው አጋጣሚም ካላፍላጎቱ በተጽዕኖ አቅጣጫውን ልናስተው አይገባም።  በመንገዱ ላይ ጋሬጣ ልንሆንበት አይገባም፤ እንደ ገራራ የማይገራ ኢጎም አድረገን ልናዬው አይገባም፤ ጉዙውን ሆነ ፍላጎቱን በፖዘቲብ ልናይለት ይገባል። ካለፉት ስህተቶች ተምሮ፣ በአገኘው ተመክሮ ተነስቶ ለትውልዱ አዲስ መንፈስ ምቹ የሚሆን ሽግሽግ ማደረጉ ራሱ ለእኔ በግሌ በጣም በጎ ነው። በራስ መንገድ፤ በራስ መርህ፤ በራስ ቴስት መንፈስን ለመምራት መወስንና መቁረጥ አንድ ጥበብ ነው። ወቅትንና ጊዜን፤ ፍላጎትንና ተስፋን ማድመጥ መቻል የአቅም ሥነ – ሥርዓት ነው።

 

በአንፃሩ ተናጠላዊ ትግሉ ጎድቶናል፤ ፍላጎታችን አጓቷል፤ ራዕያችን አርቋዋል፤ ተስፋችን አጫጭቷል፤ ለጠላት ኢላማ የቅርብ ተጠቂ አድርጎናል፤ ጉልበታችን – ተመክሯችን – መክሊታችን ብናስተጋብረው የበለጠ ህዝብ በማሰለፍ አቅምና ችሎታ ይኖረናል፤ በአንድ ላይ ሆነን አብረን እንሰራለን፤ ተዋህደን ወይ ተቀናጅተን የሚሉም ከተገኙ ወሸኔ ነው።  የእነሱንም ነፃነት  ልናከብርላቸው ልናዳምጣች ይገባል። የሚመቻቸውን የሚያውቁት እነሱ መሬት ላይ ያሉት እንጂ እኛ አይደለንም።

 

በተረፈ ዬፓርቲዎች ፉክክር ለእኔ በጎ ነው። ለሚደግፉት ፓርቲ የበለጠውን ጊዜ መስጠት ወይንም ፕሮሞት የሚያደርጓቸውም ኃይሎች የሚወስዱት እርምጃ በጎ ነው። ችግሩ ያለው ነፃነት ለራሳችን የምንፈልገውን ያህል ከሌላው ላይ ሲደርስ ወይንም ለሌላው ለመስጠት ንፉጎች መሆናችን ነው። እንደ እኔ አንዱ በአቅደው ላይ ነፃነቱን ጠብቆለት ሌላው በመሳተፍ በማገዝ፤ ሌላው በአቀደው ላይ ሌለኛው ኃላፊነቱን ወስዶ በመጋራት ፍላጎታችን ዕውን ማደረግ ይገባል እንጂ አንዱ በሌላው ላይ በመንፈስ በማማጽ፤ ወይንም ልብን በማሸፈት በጠላት ላይ የሚገኝ ድል ምንም የለም። አብሶ ይህን ቆርጠን ከምንቀጥለው የወያኔ ተለጣፊ የምንለውን ስያሜ ነገር በእጅጉ ልንቆጠብበት ይገባል። የተያዘ የተረዘዘውን ሁሉ እንዲህ እያደረግን ለምለምን ማደረቅ ምን ሊባል እንደሚችል ሂዱበት ….

 

ይከወን። ግን እኛ የእውነት ወያኔ እንዲወድቅ እንፈልጋለን? የትም ሳንሄድ ወደ ጎረቤትም እስኪ እራሳችን እንፈትሸው? ምኑ ይሆን የሚያስደስተን? ምኑ ይሆን የሚያስከፋን? ከቶ የት ላይ ይሆን የፍላጎታችን ሴል ያለው? ለነበረን ጊዜ ከልብ አመሰግናለሁ – የኔዎቹ – ክብረቶቼ ቸር ሰንብቱልኝ።

 

ፍላጎቴን ሳውቅ ቀን እኔ በእኔ ውሰጥ አለመሽሎኩን አረጋግጣለሁ።

ፈተናን ከመፈጠሩ በፊት አሸንፎ የተፈጠረ ኢትዮጵያዊነት።

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

የስፖርት ጋዜጠኞች የተያያዙት ማዝናናት ወይስ ማዘናጋት?

$
0
0
 በግሬስ አባተ
cbአሁን ባለንበት ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሁሉም ነገር በሚባል ሁኔታ ጮክ ተብለው የሚወሩት ሁለቱ ነገሮች ናቸው፡፡ አንደኛው የአውሮፓ እግር ኳስ ሲሆን ሁለተኛው ፆታዊ ግንኙነትን የተመለከቱ ርዕሶች ናቸው፡፡  በዚህ ፅሁፍ ለመዳሰስ  የፈለኩት በአውሮፓ እግር ኳስ  ዙሪያ የመገናኛ ብዙሃንን ያልተገደበ አስተዋዋቂነት ወይም ቲፎዞነት ወይም የማራገብ  ሁኔታ መመልከት፤ እንዲሁም የዚህ ማራገብ አስፈላጊነቱ ለምን እንደሆነ መግለፅ  ይሆናል፡፡
ለመነሻ ያህል በአዲስ አበባ ካሉት የራዲዮ ፕሮግራሞች እንኳን ብንጀምር ምን ያህል ሰአት ለአውሮፓ እግር ኳስ እንደሚሰጡ መታዘብ ይቻላል፡፡ ከሌሎች የራዲዮ ፕሮግራሞች አንፃር አብዛኛውን የአየር ሰአት ተሰጥቶት የሚለፈፈው የእስፖርት ፕሮግራም ነው፡፡  በአዲስ አበባ ካሉት ኤፍ ኤም ራዲዮኖች፤ በእንግሊዝኛ ከሚተላለፈው አፍሮ ኤፍ ኤም  በተስተቀር አብዛኛው ለእግር ኳስ የሚሰጡት የአየር ሰአት ከፍ ያለ ነው፡፡  እንዲሁ ለእግር ኳስ አልኩ እንጂ ይህም ለሃገር ውስጥ ከሚሰጠው የአየር ሰአት ጋር ሲነፃፀር ሰማይና መሬት መሆኑን ዘወትር የምንታዘበው ነው፡፡ ያንበሳው ድርሻ  ለማንችስተርና ለአርሰናል፤ለባርሳና ማድሪድ ወ.ዘ.ተ ይሰጣል፡፡ እዚህ ላይ የአገር ውስጡን ስፖርት እንዲሁ ለቅንነት ያህል ገለፅኩት እንጂ ከማንችስተር እና አርሰናል አንፃር  የአየር ሰአት ያገኛል ለማለት እንኳ አያስደፍርም፡፡
ለምሳሌ ያህል የራዲዮኖቹን አነሳው እንጂ በጋዜጣ የሚታተሙትን እድሜ ጠገቦቹን ኢትዮ ስፖርት፣ ወርልድ ስፖርት፣ዘ-ገነርስ… እማ  95% የሚሆነው የጋዜጣቸው ሽፋን ለአውሮፓ እግር ኳስ እንደሚሰጡ ግልፅ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ማለትም በህትመትና በራዲዮ ካሉት በተጨማሪ  ብቸኛው ኢቲቪ(ለነገሩ አሁን ኦሮሚያ ቲቪም የአውሮፓን እግር ኳስን በማስተላለፍ ከኢቲቪ ጋር እኩል እየተጋ ይገኛል፡፡) በነፃ በማስተላለፍ ጠመቃውን እያሳለጡት ይገኛሉ፡፡ አንድ አይነት አካሄድ የሚስተዋልበት ይህ የአውሮፓ እግር ኳስ የጠመቃ አካሄድ ጥርጣሬን ካጫረብኝ ሰንበትበት ብሏል፡፡  እንዳልኩት ሱፐር እስፖርት በክፍያ ኢቲቪና ኦሮሚያ ቲቪ በነፃ በድምፅ እና ምስል የሚያስተላልፉት ሲሆን በራዲዮን በኩል እነ መሰለ መንግስቱ ከሱፐር ስፖርቶቹ ጋዜጠኞች በላይ ሰፊ የአየር ሰአት ወስደው በቀጥታ ያስተላልፋሉ፡፡ ሸገር ኤፍ ኤም ላይም እንዲሁ በየሳምንቱ የሚተላለፍ ፕሮግራም እንዳለ ይታወቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የየጨዋታዎቹን ውጤት ተከትሎ ትንታኔ የሚሰጡ ጋዜጠኖች ቁጥራቸው የትየሌሌ ነው፡፡ ለዚህ ይመስላል የአውራምባ ታይምሱ አቤል አለማየሁ በአንድ መፅሃፉ ‹‹አንተ ብቻ የስፖርት ጋዜጠና ሁን›› ሲል የጊዜውን ሁኔታ የገለፀው፡፡
በየቀኑ የሚሰጡትን የእግር ኳስ የትንታኔ ሰአቶች እንኳን ትተን በሳምንት የሚሰጠውን የቀጥታ ስርጭት ብንመለከት ጉዳዩ ምን ያህል እየተሰራበት እንደሆነ እንረዳለን፡፡ ለምሳሌ ‹‹እግር ኳስን በራዲዮ ተመልከቱ›› የሚለውን የመሰለን ፕሮግራም ለአብነት ብንወስድ በየሳምንቱ ለአንድ ጨዋታ  በትንሹ 90 ደቂቃ የቀጥታ ጨዋታው + ከጨዋታው በፊት 30 ደቂቃ + 30 ከጨዋታው በሁዋላ ያለውን ብንወስድ በድምሩ በሳምንት 2:30 ይወስዳል፡፡ ይህ በወር ሲመታ፣ በአመት ሲመታ ምን ያህል ሊሆን እንደሚችል አስቡት፡፡ ከዚህ በተጨማሪ   ከውጤትና ከጨዋታ በፊትና በኋላ ያሉትን ትንታኔዎች የወሰድን እንደሆነ ከአፍሮ ኤፍ ኤም ውጪ በቀን እያንዳንዱ ራዲዮን በትንሹ 2:00 የአየር ሰአት ለአውሮፓ እግር ኳስ ይሰጣል፡፡ ይህን በሳምንት እንዲሁም በወር ሲመታ አስቡት ምን ያህል እንደሆነ!
የእኔ መከራከሪያ ለምን ስፖርት ተወራ አይደለም፡፡  ጉዳዬ ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት ላይ መነሳትም አይደለም፡፡ እርግጥ ነው መናገር መብታቸው ነው፡፡ ስለ ዋይኒ ሩኒ፣ሜሲ፣ሮናልዶ  እድሜ እና ክብደት እንዲሁም ቁመት መናገር ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት ነው ከተባለ መቼስ ምን ይደረጋል፡፡ ጥያቄዬ ስለምን ይህን ያህል የአየር ሰአት ተሰጥቶት ሊወራ ቻለ ነው? ይህንን የሚያግዝ በተጨባጭ ኢትዮጵያ ውስጥ ምን አለ ነው? መቼም አድማጭም ተመልካችም ያለው የአውሮፓ እግር ኳስን ነው፤ የሚል ቀልድ አዘል አስተያየት  አይቀርብም አይባልም፡፡ ይህ ቁጥር ነጋ ጠባ እያሻቀበ እንዲሄድና ወጣቱ ስለ ራሱ የወደፊት ሁኔታ ከመጨነቅ ይልቅ ስለ ማንችስተርና አርሰናል እንዲጨነቅ ነጋ ጠባ የሚለፈለፍለት ስለምን ይሆን? መቼም ከዚህ ጀርባ አንድ ድብቅ ሴራ እንዳለ ግልፅ ነው፡፡
ለዚህም ማጠናከሪያ የሚሆነን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአለም ወንጫ ማጣሪያ ላይ የተከሰተው  ድርጊት  ነው፡፡ ይህም የኢትዮጵያ ቡድን ሁለት ቢጫ ካርድ ያየ ተጫዋች አላግባብ አሰልፏል ተብሎ 3 ነጥብ እንደተቀነሰበት ሰምተናል፡፡ እዚህ ላይ  መነሳት ያለበት የስፖርት ጋዜጠኞች ድርሻ ነው፡፡ የኛ የስፖርት ጋዜጠኞች ምን ይሰራሉ? የነ ሩኒን ፣ የነቫምፐርሲን፣ የነሮናልዶን ወ.ዘ.ተ ከእግር ጫማቸው እስከ እራስ ፀጉራቸው ሲለፈልፉልን ስለምን ስለአገራቸው እግር ኳስ ቢያንስ በ90 ደቂቃ ውስጥ የተመዘዘውን ቢጫ ካርድ መዝግበው  መያዝ  አቃታቸው? የአርሰናሉ ኮሶሎኒ በሁለት ቢጫ ካርድ ምክንያት በሚቀጥለው ጨዋታ አይሰለፍም፣ ሜሲ እዚህ አገር ተወልዶ እንትን በምትባል መንደር አድጎ ቁመቱ ይህን ያህል ክብደቱ ይህን ያህል የሚሉን የስፖርት ጋዜጠኞች ስለምን የኛን ቡድን የ 90 ደቂቃ ቢጫ እንኳ መቁጠር አቃጣቸው ብለን ስንጠይቅ ሴራው ፍንትው ብሎ ይታየናል፡፡ በማስታወቂያ በኩል ያለውን ብንመከት ድርጅቶች ስፖንሰር የሚያደርጉት የእስፖርት ፕሮግራሞችን 90% ያለፈ መሆኑን ሌሎች ፕሮግራሞች ባንፃሩ የማስታወቂያ ድርቅ ሲመታቸው እንመለለከታለን፡፡ ምነው ይህን ያህል እዚህ አገር ሳናውቀው ኳስ ተዘርቶ ኳስ መታጨድ ተጀመረ እንዴ?
ምንአልባት በደምብ አልገለፅኩት ይሆናል አንጂ አሁን ያለው ሁኔታ እጅግ አስከፊ ወደ ሆነ አዘቅት ውስጥ የሚከተን ይሆናል፡፡ አንድ ታዳጊ አገር ያውም ከድህነትና ከችጋር ያልተላቀቀች አገር ውስጥ የተማሩና ገና የመጀመሪያ ደረጃ ትምርታቸውን ያልጨረሱ አፍላ ወጣቶች ሳይቀሩ በአውሮፓ እግር ኳስ ተጠምደው ነጋ ጠባ የሚያሳስባቸው የክለቦቹ መሸነፍና ማሸነፍ ሲሆን ወዴት እየሄድን እንደሆነ እና ሴራው ግቡን እየመታ መሆኑን እንረዳለን፡፡ በየመስሪያ ቤቱ ስለ አውሮፓ እግር ኳስ  ሲከራከሩ ከፍ ሲልም  ሲደባደቡ መመልከት ብዙም የሚያስደንቅ አይደለም፡፡ ተማሪዎችም በእረፍት ግዜያቸው ሰብሰብ ብለው ሲያወሩ የሚሰሙት   ስለ እግር ኳስ ከሆነ አመታት ተቆጠሩ፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች ሳይቀሩ የመጀመሪያው ወሬያቸው ስለተሰጣቸው የቤት ስራ ሳይሆን ስለ ማታው ጨዋታ ከሆነ ቆየ፡፡ ገና 10 እና 11 አመት ያልሆናቸው ልጆች ስለምን  ስለ አርሰናል እና ማንችስተር ነጥብ መጣል እንዲሁም ስለ ተጫዋቾች ጉዳት እንዲጨነቁ ተፈረደባቸው?
 ገና ከወዲሁ ትውልዱን በአንድ አይነት አካሄድ የመቅረፅ ሴራ… ከፍ ያለውንም እንዲዝናና ሳይሆን መሬት ላይ ያለውን  እውነት እንዳያይ ማዘናጋት የስፖርት ጋዜጠኖች ድርሻ ከሆነ ቆየ፡፡  ጋዜጠኞቹም ገንዘብ እስካገኙ ድረስ  የትውልዱ እጣ ፋንታ ግድ የሚሰጣቸው እንዳልሆነ አሳይተውናል እያሳዩንም ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ እነሆ ማን ነው ይችን አገር የሚረከባት? መቼም 4-4-2 አሰላለፍ  በስነ-ምግባርና በእውቀት የታነፀ ትውልድ ለመቅረፅ ቀርቶ ቤተሰብን ለመምራት እንኳ አያገለግልምና የትውልዱ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው፡፡ ምን ብናረግ ትውልዱን ከዚህ አይነት አፍዝዝ አደንዝዝ ሴራ ማውጣት እንችላለን? የሚለው የሁሉም የአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ  ድርሻ በመሆኑ፤ ለዚህ ሴራ መክሸፍ የበኩላችንን በማድረግ ትውልዱን ልናድነው ይገባል፡፡
ግሬስ አባተ

እሽሩሩ ማሞ –በ አሥራቴ ወርቁ


በአዲስ አበባ አንድ አንበሳ አውቶቡስ 15 ሜትር ጥልቀት ካለው ድልድይ ገባ፤ 8 ሰዎች ሞቱ

$
0
0
ዘነበወርቅ ድልድልይ የገባው አውቶቡስ ሲወጣ

ዘነበወርቅ ድልድልይ የገባው አውቶቡስ ሲወጣ

(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ከተማ ከካራ ቆሬ ወደ ለገሃር ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ ዘነበወርቅ አለርት ሆስፒታል ፊትለፊት ረዥም ድልድይ ውስጥ ገባ፤ በዚህ አሰቃቂ አደጋ ስምንት ሰዎች መሞታቸው ይፋ ሆነ።

አውቶቡሱ ቁጥራቸው እስካሁን በውል ያልታወቁ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ሲያስታውቅ የአውቶቡሱ ቁጥር 66 እንደሆነ ታውቋል።

ካራ ቆሬ ወደ ለገሃር ሲጓዝ ዘነበወርቅ አለርት ሆስፒታል ፊት ለፊት ባለው ረዥም ድልድይ ውስጥ በገባው አውቶቡስ የተነሳ በአደጋው እስካሁን አንድ እግረኛን ጨምሮ አራት ወንድ እና አራት ሴት ተሳፋሪዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ሲገለጽ 46 የሚሆኑት ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ዘ-ሐበሻ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል። የአውቶቡሱ ሹፌር እና ትኬት ቆራጭ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በሕይወት ተርፈዋል።

የአውቶቡሱ አደጋው መንስኤ ላይ መሆኑ ሲታወቅ በአውቶቡሱ ድልድይ ውስጥ መግባት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ዘ-ሐበሻ ጨምሮ የደረሳት ዜና ያስረዳል።

ለዜጎች ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ አፈናና እሰራት ምላሽ አይሆንም! ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤትየወጣ የአቋም መግለጫ

$
0
0

መጋቢት 14/2006 ዓም አዲስ አበባ

የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት መጋቢት 14 ቀን 2006 ዓ.ም ባካሄደው ሁለተኛ ዓመት አራተኛ መደበኛ ስብሰባው የካቲት 30 ቀን 2006 ዓም የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ሩጫ ላይ በተገኙ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት አባላት ላይ ፖሊስና ፍርድ ቤት በመተባበር የፈጸሙትን ሕገ መንግስት የጣሰ ተግባር፣ እንዲሁም ከአሜሪካ መንግስት በደረሳቸው ግብዣ መጋቢት 12 ቀን 2006 ዓም ምሽት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ቦሌ አውሮፕላን ማረፈያ በተገኙት የፓርቲያችን ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ላይ ራሳቸውን ከህግ በላይ ያደረጉ የደህንነት ኋይሎች የፈጸሙትን አሳፋሪና ሕገ ወጥ ተግባር በመመርመር የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡፡

  1. የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ሩጫ ላይ የተገኙ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት አባላት በሩጫው ከተሳተፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች የሚለዩት የነጻነትን ቀን ሊያከብሩ በተገኙበት ቦታ ስለ ነጻነት፣ስለ ፍትህ፣ስለዴሞክራሲ፣ስለ ሰብአዊ መብት ወዘተ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በማሰማታቸው ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 29/2 «ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሀሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው» ተብሎ የተደነገገውን ከምንም ያልቆጠረውና ሕጉን ሳይሆን ጠመንጃውን ተማምኖ፣ የሙያውን ሥነ ምግባር ሳይሆን የአለቆቹን ትዕዛዝ አክብሮ እንደሚሰራ በተግባሩ ያረጋገጠው ፖሊስ እነዚህን የሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣቶች አፍሶ ሲያስር አንዳችም ህጋዊ ምክንያት አልነበረውም፣ የፖሊስ ሕገ ወጥ ተግባር በዚህ ሳያቆም የታሰሩ የትግል አጋሮቻቸው የሚገኙበትን ቦታና ሁኔታ ለማወቅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሄዱ የፓርቲው አመራር አባላትንም አሰረ፡፡ ዋስትና ለማስከልከል አይደለም ለክስ የሚያበቃ ምንም ምክንያት ሳይኖረው ለፍ/ቤት ምርመራየን አልጨረስኩም የግዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ በማለት አባላቱ ለአስር ቀናት በጣቢያ እስር እንዲጉላሉ በማድረግ ሕግን ለማስከበር ሳይሆን የፖለቲከኞችን ፍላጎት ለማስፈጸም የቆመ መሆኑን በተግባር አረጋግጠ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ይህንን ሕገ መንግሥቱን በግልጽ የጣሰ የፖሊስ ተግባር በጽኑ እያወገዘ፣ፖሊስ የግለሰቦች ሥልጣን ጠባቂ ሳይሆን ሕግ አስከባሪ መሆኑን በተግባር እንዲያሳይ ይጠይቃል፡፡
  2. የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 19/4 «የያዛቸው የፖሊስ መኮንን ወይም ህግ አስከባሪ በጊዜው ገደብ ፍርድ ቤት በማቅረብ የተያዙበትን ምክንያት ካላስረዳ ፍርድ ቤቱ የአካል ነጻነታቸውን እንዲያስከብርላቸው የመጠየቅ ሊጣስ የማይችል መብት አላቸው፡፡» ተብሎ የተደነገገውንእንዲያቀርቡ አዟል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምር ፍርድ ቤቱ ለህግ የበላይነት የሚሰራና  በመተላለፍ ታሳሪዎቹን የዋስትና መብት ከልክሎ ለሁለት ግዜ ለፖሊስ የግዜ ቀጠሮ የፈቀደው ፍርድ ቤት፣ የእኔ ሥልጣን አይደለም መደበኛ ፍርድ ቤት አቅርቡዋቸው በማለት ካሰናበት በኋላ የምርመራ መዝገቡ ለክስ አይበቃም ተብሎ በአቃቤ ሕግ ውድቅ የተደረገበት ፖሊስ መልሶ እዛው ፍርድ ቤት ሲያቀርባቸው እያንዳንዳቸው 1300 ብርና የሰው ዋስ በጣምራ ለፍትህ መከበር የቆመ አለመሆኑን በተግባር ያረጋገጠበትን ይህን ተግባር እያወገዘ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 79/2 «በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግሥት አካል፣ከማንኛውም ባለሥልጣን ሆነ ከማንኛውም ሌላ ተጽዕኖ ነጻ ነው» እንዲሁም በአንቀጽ 79/3 ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በሙሉ ነጻነት ያከናውናሉ፣ከሕግ በስተቀር በሌላ ሁኔታ አይመሩም »ተብሎ የተደነገገው በተግባር እንዲገለጽ አጥብቆ ይጠይቃል፡፡
  3. የፓርቲያችን ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ወደ አሜሪካ የሚያደርሳቸውን አስፈላጊ የጉዞ ሰነድ አሟልተው ሻንጣቸው አውሮፕላን ላይ ካስጫኑ በኋላ ፓስፖርታቸው በደህንንት ኋይሎች ተቀዶ ጉዞአቸው እንዲስተጓጎል ተደርጓል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ይህን ሕገ ወጥ ብቻ ሳይሆን እጅግ አሳፋሪ የሆነና የደህንነት ክፍሉን ብቻ ሳይሆን የአየር መንገዱንም ስም የሚያጎድፍ ተግባር በጽኑ እያወገዘ ድርጊቱን በፈጸሙት ማን አለብኝ ባዮች ላይ ከሕግ በላይ ሊሆኑ እንደማይችሉ የሚያሳይ ሕጋዊ ርምጃ አንዲወሰድ እንጠይቃለን፡፡ 4–መንግሥት ለዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብት ጥያቄ እስራት አፈናና ማስፈራራት ምላሽ እንደማይሆን ከታሪክ በመማር ለዜጎች የመብት ጥያቄ ትክክለኛውን ምላሽ እንዲሰጥና ትግሉ ሰላማዊ፣ ዓላማው ሕዝባዊ ግቡ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እውን ማድረግ ከሆነው ሰማያዊ ፓርቲ ላይ የጥፋት እጁን እንዲያነሳ አጥበቀን እንጠይቃለን ፡፡

ለማኝዋ ስትሞት አራት ሚሊየን ዶላር ተገኘባት

$
0
0

ክንፉ አሰፋ

አንዲት የተጎሳቆለች ወይዘሮ በሪያድ ጎዳናዎች ላይ ምጽዋት ትጠይቃለች። አላፊ አግዳሚው እቺን ወይዘሮ አይቶ አያልፋትም። ሰደቃ እየወረወረላት ያልፋል። በተለይ በበዓል ወራት ገቢዋ በእጥፍ ይጨምራል።

milw1አይሻ ትባላለች። ነዋሪነትዋ ሪያድ ሳውዲ አረቢያ ነው። ላለፉት 50 አመታት በልመና ስራ ስትተዳደር ቆይታ በተወለደች በ100 አመትዋ በያዝነው ሳምንት እሁድ እለት ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች። አማሟቷም ድነገት ነበር ይላል አረብ ኒውስ።

ጉድና ጅራት ከወደኋላ ነው እንዲሉ የአይሻ ህልፈት አለምን ያስደመመ ጉድ ይዞ መጣ። ለሃምሳ አመታት በልመና የተሰማራችው ወይዘሮ ሚሊየነር ኖራለች። የወርቅ ጌጣጌጦች እና የጥሬ ገንዘብ ሃብትዋ አራት ሚሊየን ዶላር ሲሆን በጂዳ ከተማ የአራት ትላልቅ ህንጻዎች ባለቤትም ነበረች።

የአይሻን ንብረት የሚወርስ ዘመድ የለም። አብሮ አደግ ነኝ የሚል አህመድ አል ሰይድ የሚባል ሰው ግን የውርስ መብት አለኝ ብሏል። በእርግጥ አይሻ ሌላ ዘመድ የላትም። እህትና እናትዋ ለማኞች ነበሩ። ወላጆችም በልመና ይተዳደሩ የነበሩ መሆናቸውን የጠቀሰው የአረብ ኒውስ፣ አይሻ ንብረታቸውን በከፊል ከነሱ በውርስ እንዳገኙም ዘግቧል። አሁን ሁለቱም ሞተዋል።

አህመድ አል ሰይድ ንብረቱን “አይሻ ለኔ አውርሳኝ ሞታለች እኔም ተቀብዬ ለድሆች እንዳከፋፍል ይፈቀድልኝ” ብሎ ነበር። ከመንግስት ያገኘው ምላሽም ግን የለም።

ልመናውን እንድትተው ቢወተውታትም አሻፈረኝ ማለቷን ለመገናኘ ብዙሃን ገልጿል።

ሌላው የሚገርመው ነገር አይሻ ህንጻዋ የሚኖሩትን ሰዎች የቤት ኪራይ አታስከፍላቸውም ነበር።

millwm2አይሻ ሚሊየነር ነበረች። አንድ ቀን ጥሩ ምግብ ሳትበላ፣ ጥሩ መኝታ ላይ ሳትተኛ፣ ጥሩ ቤት ውስጥ ሳትኖር፣ ጥሩ ልብስ ሳትለብስ ኖራ ለዘላለሙ አሸለበች። ግን ይህ ለምን ሆነ የሚለው ጥያቄ ምላሽ አላገኘም።

አልፎ አልፎ የዚህ አይነት ክስተቶችን በአለም ላይ እናያለን። በሺዎች የሚቆጠሩ የኔብጤዎች ያሉባት ኢትዮጵያም በዚህ ስራ ከፍተኛ ሃብት እና ንብረት ያፈሩ ለማኞች አጋጥመውኛል።

እርግጥ የልመና ገንዘብ ስላልተለፋበት ይጣፍጥ ይሆናል። ልመናም እንደ አደንዛዥ እጽ ሱስ ያስይዝ ይሆን?

በረከተ መርገም (አንተነህ ሽፈራው)

ድምፃዊ ጌድዮን ዳንኤል የጎዳና ተዳዳሪ ሆኗል፤ የሕዝብን እርዳታ ይሻል

$
0
0

Gedion daniel (ዘ-ሐበሻ) “ላጽናናሽ”፣ “በተራ” እና በሌሎችም በተሰኙት ሙዚቃዎቹ የሚታወቀውና 2 ሙሉ አልበም የሰራው ድምፃዊ ጌድዮን ዳንኤል በአዲስ አበባ የጎዳና ተዳዳሪ ለመሆን እንደተዳረገና እርዳታ እንደሚያስፈልገው አዲስ ጉዳይ መጽሔት ዘገበ።

በአዲስ አበባ ታትሞ የሚሰራጨው አዲስ ጉዳይ መጽሔት ጓደኞቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ድምፃዊው የአእምሮ ህመም ምልክቶች ከታዩበት ረዥም ጊዜ ሆኖታል። መጽሔቱ ያነጋገረው የድምጻዊው ጓደኛ “ጌድዮን ካልጠጣ ሰላማዊ ሰው ነው ከጠጣ ግን በጣም ኃይለኛና ሰውን የሚያስቸግር ሰው ነው” ሲል ይገልጸዋል። ሌሎች ደግሞ ድምጻዊው ሊያገኝ የሚገባውን የሳይካትሪስት ህክምና አለማግኘቱ ለዚህ እንዳበቃው ይናገራሉ::

ጌድዮዎን በተለይ 2ኛ አልበሙን ካወጣ በኋላ ብዙም ተቀባይነት አለማግኘቱ ለዚህ የአእምሮ ችግር እንዳበቃው የሚገልጹ የቅርብ ወዳጆቹ አሉ። እንደ አዲስ ጉዳይ መጽሄት ከሆነ ይህ ወጣትና ጥሩ ብቃት ያለውን ድምጻዊ ሕይወት ለማስተካከል የሙያ አጋሮቹ፣ ማንኛውም ተቋም፣ እንዲሁም ግለሰቦች ሊተባበሩት ይገባል።

የጌድዮን 3 ሙዚቃዎችን ያድምጡ።



Smart Car: ስለአዲሱ ኒውዮርክ የፖሊስ መኪና ምን ያህል ያውቃሉ?

$
0
0

nypd-smartcar1
ከአብዱ ይማም

የኒዮርክ ፖሊስ ዲፓርትመንት አባላት በሚንሸራሸሩባቸው የከተማይቱ ጎዳናዎች ሁሉ ሲሆን የሚውለውን እና የሚያድረውን ለማወቅ ምን ቢኳትኑ አደጋች ነው፡፡ ታዲያ የከተማይቱ ፖሊስ ዲፓርትመንት ቀደም ሲል ሲጠቀምባቸው ከነበሩ የወንጀል መከታተያያ ዘዴዎች የላቀ ብቃት የለበሰ ስለመሆኑ የተነገረለት የዘመኑ ምጡቅ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆነ የፖሊስ ተሸከርካሪ ፈጣሪዎቹ እነሆ ብለዋል፡፡

ይህ ዘመን አፈራሽ ቴክኖሎጂ የኒዮርክ ፖሊስ ዲፓርትመንት አባላትን የሥራ ጫና በእጅጉ የሚያቀል ስለመሆኑም እየተነገረለት ይገኛል ‹‹ስማርት ካር›› ሲሉ ፈጣሪዎቹ የሰየሙለት ይህ ተሽከርካሪ የሕዝቡን ደህንነት በተገቢው ሁኔታ ለመጠበቅ በሚያስችሉ ሙሉዕ በኩለሄ በሆኑ መረጃ ሰብሳቢ መሣሪያዎች የተደራጀ ነው፡፡

ተሸከርካሪው በተገጠሙለት ሁለት የኢንፍራሬድ መቆጣጠሪያዎች ያያቸውን ቁጥሮች ሁሉ ይመዘግባል፡፡ የተፈቀደለት ሰሌዳና አድራሻም ጭምር የመለየት አቅም ያለው ይኸው በተሽከርካሪው ላይ የተገጠመ ኢንፍራሬድ በዚያው መጠን የተጭበረበሩ ሰሌዳዎችና ሀሰተኛ አድራሻዎችንም ጭምር በመለየት የማጋለጥ ስራ ይሰራል፡፡ ዘመናዊ እና ‹‹ስማርት ካር›› የተስኘው የፖሊስ ተሸከርካሪ የክትትል ካሜራዎች የተገጠሙለት ሲሆን የሚቃኛቸውን አካባቢያዊ ጠባያት ሁሉ ወዲያውኑ ወደ ፖሊስ ዲፓርትመንት ማዕከል የመላክ ብቃትም የለበሱ ናቸው፡፡

የ‹‹ስማርት ካር›› ፕሮጀክት በረጅም ጊዜ ዕቅድ ሊከናወኑ ከተያዙት BYPO 2020 መጠነ ሰፊ ፕሮጀክቶች አንዱ ሲሆን የ ‹‹ስማርት ካር›› ፕሮጀክት የኒዮርክ ፖሊስ ዲፓርትመንት እስከ 2020 ሊያከናውናቸው ይዟቸው ከነበሩ በርካታ ዕቅዶች መካከል አንዱ እንደሆነ የገለፁት ኮሚሽነር ሬይምንድ ኬሊ በ2011 ከማክ ኪንሲና ኩባንያው ጋር የተጀመረው ፕሮጀክት ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት ለዲፓርትመንቱ የሚጠቅሙ የመንገድ ላይ ካርታዎች ለመስራት ዕቅድ ሰንቋል፡፡

የኒዮርክ ፖሊስ ዲፓርትመንት በቅርቡ ሊተገብራቸው የያዛቸው 260 ያህል ፕሮጀክቶች ያሉ ሲሆን የተቋሙ ሰባት ያህል ሰዎችም ቴክኖሎጂውን ለማምረት የሚያስችለቸው ክህሎት እንዲለብሱ ተደርጓል፡፡

የኒዮርክ ፖሊስ ዲፓርትመንት የስማርት ካርን ጽንሰ ሃሳብ ያመነጨው ትኩስ የምስልና መስል መረጃዎችን ለማሰባሰብ የሚያስችለውን አዲስ አስራር ለመዘርጋት ከማስቡ ጋር ተያይዞ ሲሆን ክስተቱን የሚመለከቱ ባለስልጣናት ሊደረጉ የሚገባቸውን በተመለከተ መዲያውኑ መመሪያ እንዲያወርዱም ያስችላቸዋል፡፡
እነዚህ ሙሉ መሣሪያዎች የተገጠሙላቸው ‹‹ስማርት ካር›› የተሰኙት እነዚህ ተሸከርካሪዎች ቁጥራቸው እምብዛም ባይሆንም ቀጣይ ግን የጣት አሻራ ሊቀበሉ እና የፊትን ገጽታ ለመለየት የሚያስችል መሳሪያ የተገጠመላቸው የፖሊስ ተሽከርካሪዎች የኒዮርክ ፖሊስ ዲፕርትመንት የአጭር ጊዜ ዕቅድ ናቸው፡፡ ይህ ሁናቴ የፖሊስ መኮንኖቹ ሙሉዕነት ያለው መረጃ እንዲያገኙ በማድረግ ስራቸውን ቀና የሚያደርግላቸው እንደሆነና ውሳኔ ለመስጠት ችግር እንዳይገጥማቸው እንደሚረዳቸውም እየተነገረ ነው፡፡

በከተማ ውስጥ ሊኖር የሚችል ስውር የሽብርተኝነት ሴራ ለማጋለጥና ለትራፊክ አደጋ መከላከል ሰራተኞች ተጠርጣሪዎችን ለመለየት ዘመን አፈራሹ የፖሊስ ተሸከርካሪ ፍቱን ነው ተብሏል፡፡

በአስተዳደራዊ ስራ ረገድም የኒዮርክ ፖሊስ አባላትን ከዚሁ ዘመነኛ የቴክኖሎጂ ውጤት ጋር ማስተዋወቅም የኒዮርክ ፖሊስ የቤት ስራ እንደሚሆን ተጠቅሷል፡፡

የፖሊስ ዲፓርትመንቱ ፈተና እንደሆነ እየተነገረለት ያለ እውነትም አለ፡፡ የበጀት ጉዳይ ብዙዎቹ ሥራዎች ሊሠሩ የታቀዱት ዘመናዊ ፈጠራዎች በተሳካ ውጤት ይታጀቡ ዘንድ በየጊዜው የማሻሻያና የጥገና ሥራዎች ሊከናወኑለት እንደሚገባ ነው እየተገለፀ ያለው፡፡
እነዚህ ዘመነኛ የፖሊስ ተሸከርካሪዎች የዘመነ ወንጀል በተንሰራፋባቸው ታላላቅ ከተሞች ልበ ብርሃን በሆነው የማየት፣ የመቅመስ፣ የማሽተትና የማድመጥ ችሎታቸው ታግዘው ለፖሊስ ዲፓርትመንቶች የሚመጣበት መረጃ የዋዛ አይደለም፡፡ ዝ

ጊዜ የወጣለት ፌደራል 5 ህጻናትን አንበርክኮ ፎቶ ይነሳባቸዋል (ፎቶ)

$
0
0

“… ግን እስኪያልፍ ያለፋል” ያለው ማን ነበር? ተመልከቱ በአዲስ አበባ ጊዜ የወጣለት ፌደራል ፖሊስ 5 ህጻናትን አንበርክኮ ፎቶ ሲነሳባቸው።
federal


የሽረ ባጃጆች አድማ መቱ: መንግስትም አገደ

$
0
0

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

የሽረ እንዳስላሴ ከተማ ባለስልጣናት ከ450-500 የሚሆኑ የባጃጅ ሹፌሮች ሰብስበው ኩንትራት (ኮንትራክት) እየጫናቹ ነው፤ መንግስት የማይፈልገውን አገልግሎት እየሰጣቹ ነው በሚል ሰበብ ማስፈራራታቸው ተከትሎ የባጃጅ ሹፌሮች የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ባጃጆቹ ከከተማ ዉጭ በማስቆም ተቃውሞአቸውን እየገለፁ ይገኛሉ። የመንግስት አካላትም አድማው ተከትሎ ባለባጃጆቹ መንግስት ባዘዛቸው መሰረት ለመስራት ፍቃደኛ ካልሆኑ ፍቃድ እንደማይሰጣቸው በመግለፅ እንዳይንቀሳቀሱ አግዷቸዋል። አሁን ባለባጃጆቹ አድማ ላይ ናቸው፤ መንግስትም አግዷቸዋል። በከተማው ምንም የባጃጅ እንቅስቃሴ አይታይም።
Abrha Desta
ብዙ የከተማው ኗሪዎች ታክሲ አጥተው በመንግስት አካላት ላይ ጫና በመፍጠራቸው ባለስልጣናቱ አምስት ሚኒባሶች ከመነሃርያ የታክሲ አገልግሎት እንዲሰጡ ቢያዙም ህዝቡ በቂ አገልግሎት ማግኘት አልቻለም። ባለ ባጃጆቹ መንግስት መፍትሔ ካልሰጣቸው ሰለማዊ ሰልፍ እንደሚወጡ ለዓረና ፅሕፈትቤት (የሽረ ከተማ ቢሮ) አስታውቀዋል። ከወር በፊት በመቐለ ከተማ ተመሳሳይ ችግር እንደነበር ይታወቃል።

በሌላ ዜና ዓረና ከሀገረሰላም ህዝብ ጋ ተወያየ።

ትናንት እሁድ (መጋቢት 14, 2006 ዓም) ዓረና ፓርቲ በደጉዓ ተምቤን ወረዳ ሀገረሰላም ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ አካሂደዋል። ለእሁዱ ስብሰባ ቅዳሜ ቅስቀሳ የተደረገ ሲሆን የሀገረሰላም ህዝብ በጥሩ ሁኔታ ተቀብሎናል።

የህዝቡን ስሜት ያስደነገጣቸው ባለስልጣናት የከተማው ወጣቶች ሰብስበው በስድስት መኪኖች ጭነው ስልጠና አለ፣ ስራ ይሰጣችኋል፣ አበል ይሰጣችኋል ወዘተ በማለት ሕዋነ ወደሚባል ከተማ ሲያጓጉዟቸው አመሹ። ሌሊትም ቁጥራቸው በዉል ያልታወቁ ወጣቶች ሲጓጓዙ አደሩ። ቁጥራቸው ያልታወቀ ወጣቶችም ቅዳሜ ማታ በፖሊሶች እየታደኑ ታስረዋል፤ የዓረና ስብሰባ እስኪጠናንቀቅ ድረስ። ጥረቱ ግልፅ ነበር። ወጣቶቹ በዓረና ስብሰባ እንዳይሳተፉና በአባልነት እንዳይመዘገቡ ለማራቅ ነው፤ ዓረና ከወጣቶች ጋር እንዳይገናኝ ለማድረግ ነው። በብዙ አከባቢዎች በዓረና ስብሰባ የሚሳተፉ ወጣቶች ናቸውና።
ወጣቶቹ ከከተማ በመውጣታቸው ምክንያት የስብሰባው ተሳታፊ ብዙ አልነበረም። ነገር ግን ከብዙ የገጠር ጣብያዎች የተወከሉ አርሶአደሮች፣ መምህራንና የተመሪዎች ተወካዮች ነበሩ። እናም ስብሰባው የተሳካ ነበር ማለት ይቻላል።
አንዳንድ የህወሓት ካድሬዎች (የከተማው የካቢኔ አባላት) በዓረና አባላት ላይ ችግር ለመፍጠር ሞክረው ነበር። አልጋ እንዳንይዝ ባለሆቴሎችን ያስፈራሩ ነበር፣ በአንዳንድ አባሎቻችንም አክታ የመትፋትና የመሳደብ እንዲሁም ለመረበሽ ጥረት ሲያደርጉ ነበር። ግን እነዚህ ተግባራት የፈፀሙ የከተማው የካቢኔ ሐላፊዎች በተናጠል (በግል) የሰሩት እንጂ እንደ የዓዲግራቱ ቀውስ ሆን ተብሎ በፓርቲ ደረጃ የተፈፀመ አልነበረም። ምክንያቱም በሀገረሰላም ካድሬዎች ችግር ሲፈጥሩ ፖሊስ ያስቁመው ነበር። በዓዲግራት ግን ፖሊስ የችግሩ ተሳታፊ ነበረ።
እሁድ ጧት ስብሰባ የጠራንበት የከተማው ማዘጋጃቤት በፖሊሶችና ካድሬዎች ተከቦ ለስብሰባ የመጣ ህዝብ ለማስፈራራት ጥረት ተደርጓል። ብዙዎች እንዲመለሱ ተደርጓል። ባጠቃላይ የህወሓት ባለስልጣናት በዓረና አባላት ላይ ይፈፅሙት የነበረ ግፍ ወደ ተሰብሳቢው ህዝብ አሸጋግረውታል።
አሁን ጥቃት የሚፈፀመው በዓረናዎች ሳይሆን ጥያቄ በሚያነሳና በዓረና ስብሰባ ለመሳተፍ ፍላጎት ባለው ሰለማዊ ህዝብ ላይ ነው። የህዝብ የመሰብሰብ መብት እየጣሱ ነው ማለት ነው። የደጉዓ ተምቤን ህዝብ ለውጥ እንደሚፈልግ አረጋግጦልናል።

Hiber Radio: “ቦሌ ኤርፖርት ፓስትፖርቴን የሰጠሁት ሰራተኛ አለቃዬን ላነጋግር ብሎ ገብቶ የፓስፖርቴን አንድ ገጽ ቀዶ በመጣል አንድ ገጽ ጎሎታል አለኝ፤ ቀረሁ”–ኢንጂነር ይልቃል

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ መጋቢት 14 ቀን 2006 ፕሮግራም

<<...አሜሪካ ለመምጣት ቦሌ ፓስፖርቴን የሰጠሁት የኢሚግሬሽን ሰራተኛ ቆይ አለቃዬን አነጋግሬ ልምጣ ብሎ ወደ ሌላ ቢሮ ገብቶ ተመልሼ ሲመጣ ፓስፖርትህ አንድ ገጽ ጎሎታል አለኝ። አንድ ገጽ ቀዶለት ነበር የመጣው። ድርጊቱ ከአገር እንዳልወጣ የተደረገ ነው ..አገሪቱም እነሱም ምን ያህል የወረደ ደረጃ ላይ እንዳሉ የሚያሳይ አሳፋሪም አስቂኝም ድራማ ነበር.. .>>

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር ወደ አሜሪካ እንዳይመጡ ስለታገዱበት ሁኔታ ለህብር ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ

<<...ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት በኩዌት ያሉ ወገኖቻችን ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ ማጣራት እያደረግን ለኩዌት መንግስትም በየኤምባሲያቸው በኩል በኢትዮጵአውያን ላይ በኩዌት ሚዲያ የሚደረገውን ቅስቀሳ ተከትሌ የጥቃት ሰለባ እንዳይሆን መብታቸው ተጠብቆ አገራቸው የሚሄዱትም እንዲሄዱ እንቅስቃሴ ጀምረናል። ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችንም ስለ ጉዳዩ እናሳውቃለን...>>

ወ/ት ሜሮን አሀዱ የዓለም አቀፉ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ተቆርቋሪ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ በኩዌት ስላሉ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ከህብር ጋር ካደረገችው ቆይታ

ደብዛው የጠፋው የማሌዢያ አየር መንገድ ጉዳይ እና ያልተሳካው ፍለጋ እስከምን ይዘልቃል (ልዩ ዘገባ)

በቬጋስ ለስራ ማቆም አድማ ወጥቶ ሕይወቱ ስላለፈው የታክሲ አሽከርካሪ መታሰቢያና የተቃውሞው ተሳታፊዎች የወደፊት እርምጃ ውይይት

ሌሎችም ዝግጅቶች

ዜናዎቻችን

* በኦጋዴን የልማትና የኢኮኖሚ ጥያቄ ያቀረቡ የአገር ሽማግሌዎች መታሰር በአካባቢው ውጥረትና ስጋት ማስነሳቱ ተነገረ

* የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ቦሌ ላይ በድንገት ከፓስፖርታቸው አንድ ገጽ ተቀዶ ወደ አሜሪካ እንዳይወጡ የታገዱበት ሂደት አስገራሚ ድራማ ነበር አሉት

* በወላይታ ተደብድበው የታሰሩት የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ትላንት ተለቀቁ

- የተነጠቁት ሞባይላቸው ባልታወቀ ነገር ተነክሮ እንዲበላሽ ተደርጓል

* አሜሪካ ከኢትዮጵያ የምትወስዳቸው የማደጎ ህጻናት ቁጥር ማሽቆልቆሉ ተገለጸ

* በአዲስ አበባ ተሳፋሪዎችን የጫነ አንበሳ አውቶብስ ድልድይ ውስጥ ገብቶ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈ

* ኤርትራ በጥቂት ቀናት ውስጥ ሶስት ጄኔራሎቿን በሞት አጣች

* የአስመራው መንግስት ኢትዮጵያ አዲስ የዲፕሎማሲ ዘመቻ ከፍታብኛለች አለ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

ኑ! እንዋቀስ፤ ኢህአዴግንም እናፍርሰው! (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)

$
0
0

(ይህ “ኑ! እንዋቀስ” የሚለው ስር ነቀል የለውጥ ጥሪ ቀጥታ የሚያነጣጥረው በኢህአዴግ አባላት ላይ
ብቻ ነው፤ አመራሩን በፍፁም አይመለከትም)

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ


ኢህአዴግ ራሱ በይፋ ሲናገር እንደተደመጠው፣ በአሁኑ ጊዜ የአባላቱ ቁጥር ወደ ሰባት ሚሊዮን ገደማ
ደርሷል፡፡ ይህም የአገሪቱ ቁጥር አንድ ግዙፍ የፖለቲካ ፓርቲ ያደርገዋል፡፡ በርግጥ ግዙፍ እንጂ ጠንካራ
እንዳላልኩ ልብ ይሏል፡፡ ምክንያቱም ጥንካሬ የሚለካው በአባላት ቁጥር ሳይሆን በድርጅት ፍቅር፣
በዓላማ ፅናትና በሚሰጡት ልባዊ አበርክቶ ነው፡፡ እንዲህ ያለ አቋመ-ብርቱነት ደግሞ ድሮ በያ ትውልድ
ጊዜ ቀርቷል፡፡ በዘመነ-ኢህአዴግ የተንሰራፋው ጥቅመኝነት (በእነርሱ ቋንቋ ኪራይ ሰብሳቢነት) ብቻ
ነው፡፡ ለዚህም በደቡባዊቷ አዋሳ ከተማ ስድስተኛው የድርጅቱ ጉባኤ በተካሄደበት ወቅት፣ አቶ በረከት
ስምኦን በብስጭት እየተትከነከነ በደፈናው ለጥቅም ድርጅቱን የተቀላቀሉ አባላት በርካታ መሆናቸውን
አምኖ በአደባባይ መናገሩ አስረጂ ሊሆነን ይችላል፡፡ ይህን ንግግሩንም አፍታተን ስናብራራው
እንደሚከተለው ሆኖ እናገኘዋለን፡- የግንባሩ አባላት ቁጥር ሰባት ሚሊዮን ገደማ የደረሰው በጥቅም በመደለል፣ በአንድ ለአምስት የጥርነፋ
መዋቅር በፍርሃት ተጠፍንጎ በመያዙና በመሳሰሉት ነው (መቼስ አቶ በረከት ከድርጅቱ ጉምቱ መሪዎቹ አንዱ ነውና ዘርዝሮ እንዲያስረዳን
አይጠበቅበትም)

የሆነው ሆኖ አባላቱ እንዲህ የመብዛታቸው ምስጢር የድርጅቱ አምባ-ገነንነት ባህሪይ መገለጫ እንጂ አመላይ አጀንዳ አሊያም
ምትሀታዊ ችሎታ እንዳለው የሚያሳይ አይደለም፡፡ ይህ የትኛውም መሰል ሥርዓት ከተጠናወተው ሁሉንም ከመቆጣጠርና መጠቅለል
(Totalitarianism) አስተሳሰብ የሚሰርፅ ማኪያቬሊያዊ አስተምህሮ ነው፡፡ የሆነው ሆኖ ‹‹አምባገነኖች የአንድ እናት መንትያ ልጆች
ናቸው›› እንዲሉ፤ በ‹‹ቆራጡ መሪ›› ዘመነ-መንግስትም በጊዜው ከነበረው የሀገሪቱ ሕዝብ ቁጥር አኳያ መሳ-ለመሳ ሊባል በሚያስደፍር
ሁኔታ ሳር ቅጠሉ ሁሉ ሰማያዊ ካኪ ለባሽ የኢሠፓ አባል ሆኖ ነበር፡፡ ግና፣ ያ ካኪ ለባሽ ሕዝብ፣ የልቡን በልቡ ይዞ ‹‹ቪቫ መንጌ!›› እያለ
አሳስቆ በስተመጨረሻ ጉድ እንደሰራው ሁሉ፤ ‹‹ይህ የህዝብ ማዕበል…›› ተብሎ በአቶ መለስ ዜናዊ የተሞካሸው የ97ቱ የቅዳሜው መሬት
አንቀጥቅጥ የሰልፍ ትዕይንትም፣ በድጋፍ ሳይሆን በግዳጅ የሰመረ መሆኑን ለማየት፤ አይቶም ለመመስከር ከሃያ አራት ሰአት ጊዜ በላይ
አልወሰደብንም፡፡ እንዴት? ቢሉ በማግስቱ (ሚያዚያ 30) ለተቃውሞ ከወጣው ሕዝብ የቅዳሜዎቹም በብዛት መሳተፋቸውን በራሳቸው
አንደበት ‹‹ትላንት ለቲሸርት፤ ዛሬ ለነፃነት!›› በሚል ሕብረ-ዝማሬ ከአደባባዩም አልፎ ከተማዋን በሚያናውፅ የለውጥ ጩኸት
የመሰከሩበት ‹‹ፖለቲካ›› መቼም ቢሆን አይዘነጋምና፡፡

እንግዲህ ይህ ሁሉ ታሪካዊ ሀቅ የሚገልፅልን አንድ ታላቅ እውነት-በጥቅም እየደለሉ አባልን ማብዛት በክፉ ቀን የማይታደግ መሆኑን ነው፡
፡ ጥቅመኝነት ግፋ ቢል የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ‹‹ፀበል›› ያስጠምቅ፣ ‹ኢህአዴግ ጌታ ነው!›ን ያስፎክር ያሸልል ይሆናል እንጂ
የኢትዮጵያን ትንሳኤ መሻትን አያስቀይርም፡፡ ነብር ዥንጉርጉርነቱን እንደማይለውጠው ሁሉ የኢህአዴግ አባላትም ምንም ቢሆን ምን፣
እንደሌላው ሕዝብ የሀገር አንድነት የሚያሳስባቸው፣ ብሔራዊ ውርደት (ረሀብተኝነት) በቁጭት የሚያንገበግባቸው፣ ከዘውግ ልዩነት
የሕዝብ ለሕዝብ መተማመንና አንድነታዊ ጥንካሬው የሚበልጥባቸው፣ የኃይማኖት ነፃነት የሚያስተቃቅፋቸው… ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡
ምክንያቱም ጥቅመኝነት የእጦትን ክፍተት ለመሙላት ለጊዜው ያሰግዳል እንጂ ክብርንና ማንነትን አስሽጦ በባርነት ቀንበር አያሳድርም-
በተለይም ዥንጉርጉርነቱን ጠንቅቆ ለሚያውቀው ኩሩ-ሀበሻ!

ደግሞስ ምን ያህሉ አባል ነው፣ የድርጅቱን መታወቂያ በመያዙ ብቻ የረባ ጥቅም ያገኘው? በግላጭ እንደሚታየው በግል ጥቅምም ሆነ
በተጭበረበረው የዘውግ ፖለቲካ ሳቢያ ኢህአዴግን የተቀላቀሉ የአብዛኞቹ አባላት የኑሮ ደረጃ ዛሬም እንደ ብዙሃኑ የኢትዮጵያ ህዝብ
ከችግር የመቆራመድ አስከፊ ሕይወት አልተላቀቀም፡፡ ፓርቲውን መታከካቸውም በማይጨበጥና በማይታይ እንቅልፍ የለሽ ሕልም
አናውዞ ይበልጥ ደቁሷቸዋል እንጂ በቀን ሶስቴ መመገብ እንኳ አላስቻላቸውም፡፡ ሌላው ቀርቶ የድርጅት አባልነታቸው እንደተርታው
ሕዝብ በአድሎአዊ አሰራር መማረርን እንዳላስቀረላቸው በርግጠኝነት መመስከር ይቻላል፡፡

ይህ አይነቱም እርግጠኝነት ነው ‹ኑ! እንወቃቀስ (እንነጋገር)፤ እንተማመንምና ሀገርና ትውልድ እየገደለ ያለውን ፓርቲያችሁን አብረን
ተጋግዘን እናፍርሰው› የሚል የማንቂያ ደውል ላሰማችሁ ገፊ-ምክንያት የሆነኝ፡፡ እናም ድርጅታችሁን ትመረምሩ ዘንድ ወደድኩ፡-
ድርጅታችሁ ሥልጣን ላይ ተፈናጥጦ ባሳለፋቸው ሁለት አስርታት የተጓዘበትን መንገድ በአስተውሎት ብትመረምሩ፤ በእርግጠኝነት እንደ
ግዙፍ ዐለት ካገጠጡ ሀገራዊ ውድመቶች እና ከበባድ ኪሳራዎች ጋር መፋጠጣችሁ አይቀሬ ነው፡፡ ይህም ሆኖ በቅድሚያ በተልካሻ
ፕሮፓጋንዳ ያሰለቸንን የብሔር ጉዳይ (የተወሰኑ ሰዎችን አማልሎ አባል ለማድረግ አስተዋፆ እንዳለው ባይካድም) ወደጎን ብለን፤
የትኛውም ብሔረሰብ ባህላዊ እሴቶቹን ማክበር፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋው መጠቀም… የፖለቲካ ፓርቲ በችሮታ የሚሰጠው ሳይሆን፣
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
2

የማንም ተፈጥሮአዊ መብት መሆኑን ማስረገጥ አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡ ይህ ማለት ግን የድርጅታችሁ ሀቲት፡- ‹አንዱ በሌላው እድሜውን
ሙሉ ሲጨቆን እንደኖረ፤ ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተለየ እንደሆነ፤ ከብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን ይልቅ የክልሉን እንዲያስቀድም
መቀስቀስና መስበክን የብሔር ብሔረሰብ መብትን ማክበር ነው› የሚለውን አምኖ መቀበል አይደለም፡፡ በግልባጩ ስርዓቱ እንዲህ አይነት
ጉዳዮችን ሰማይ ጥግ አጉኖ፣ ሕዝብን ከፋፍሎና በጥርጣሬ (በጎሪጥ) ወደሚተያይበት ጠርዝ ገፍቶ፣ የሥልጣን ዕድሜውን ያራዘመበት
ሁለት አስርታትን ያሳለፈ ስልቱ መሆኑን መረዳት አይሳናችሁም ብዬ አስባለሁ፡፡

ሌላ ሌላውን ትተን እንኳ የኢህአዴግን አመሰራረት ብንመለከት ግንባሩን ከፈጠሩት አራቱ ድርጅቶች መካከል ከሞላ ጎደል ህወሓት እና
ኢህዴን/ብአዴንን እንደ ፖለቲካ ድርጅት መውሰድ ይቻል ይሆናል እንጂ፤ ኦህዴድና ደኢህዴን፣ በህወሓት ‹‹አባ መላ››ዎች እንደ
የፋብሪካ ሳሙና በሚፈለጉበት መጠንና ቅርፅ ተጠፍጥፈው ከተሰሩ በኋላ በኦሮሞና በደቡብ ኢትዮጵያ ተወላጆች ላይ እንደ አለቅት
የተጣበቁ የመሆናቸውን ምስጢር እነርሱም ራሳቸው የሚክዱት አይመስለኝም (ምናልባት በሽግግሩ የመጀመሪያ ዓመት ላይ
እንደአስተዋልነው ከኦህዴድ ይልቅ፣ ኦነግ ኦሮሚኛ ተናጋሪዎችን ወክሎ ቢቀጥል ኖሮ ይህ ጉዳይ በዚህ አውድ ላይነሳ ይችል ነበር፡፡ የሆነው
ግን ተቃራኒው ነው፤ የራሱ የፖለቲካ ቁመናና ራዕይ የነበረው በኃይል ተገፍቶ፤ በምትኩ በሌሎች እስትንፋስ ህልው ሆኖ
‹‹የሚያስተዳድረው››ን ሕዝብና ራሱንም ጭምር ቀን ከሌት ‹‹ከብሔር ጭቆና ነፃ አወጣናችሁ›› ስለሚሉት ሞግዚቶቹ ገድል መተረክን
‹‹ፖለቲከኛነት›› አድርጎ የወሰደው ኦህዴድን ያነገሰ ነውና)

በነገራችን ላይ የፖለቲካ ፓርቲን እንደ ፋብሪካ ምርት ጣጣ-ፈንጣጣው ተጠናቅቆለት ሲያበቃ የመጫኑ አሰራር በሁለቱ ክልሎች ብቻ
ተገድቦ የቀረ አይደለም፤ አጋር ፓርቲዎችንም ይመለከታል፡፡ ከአፋር እስከ ጋምቤላ እና ቤንሻንጉል፤ ከሀረር እስከ ሶማሌ ሲተገበር
በትዝብት የተመለከትነው ጉዳይ ነው፡፡ መቼም ገና ከስር መሰረቱ ‹‹እኛ እናውቅልሀለን!›› በሚሉ ‹‹የፖለቲካ ሞግዚቶች›› የተፈጠረ
ድርጅት በምደባ ቦታውን ያገኙ የአመራር አባላቱን በቅምጥል ኑሮ ከማንፈላሰስ በዘለለ፣ ‹‹እወክለዋለሁ›› ለሚለው ሕብረተሰብ ትርጉም
ያለው ስራ ይሰራል ተብሎ የሚታሰብ አይደለምና ‹በኦሮሚያ ሙስና እንደሰላምታ እጅ መጨባበጥ ተዘውታሪና ተራ ነገር ነው›፣ ‹በአፋር
ባጀት መቀለጃ ሆኗል›፣ ‹በሐረር ቤተሰባዊ ኢምፓየር ተገንብቷል›፣ ‹ቤንሻንጉል በድህነት ማቀቀ›፣ ‹ሶማሌ ክልል የአስተዳዳሪው አብዲ
ርስተ-ጉልት ሆነ› ጂኒ ቁልቋል እያሉ ሮሮዎችን ማሰማት ለውጥ አያመጣም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ህወሓትን እንደ ‹‹ግል አዳኝ››
በመቀበላቸው ብቻ ‹‹የአስተዳዳሪነት›› ካባ የተደረበላቸው ምስኪን የአመራር አባላት በቀላል ጉዳይ ላይ እንኳ የመወሰን ሥልጣን
የላቸውምና ነው፡፡

ይህ እንግዲህ በቀጥታ ከኢህአዴግ ስነ-ተፈጥሮ ጋር የሚጋመድ ችግር ነው፡፡ ሆኖም የመንግስት ሥልጣን መዘውር ከጨበጠ በኋላ
የጨፈለቃቸውን የዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች ተከትሎ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የደረሱ የአያሌ ሰላማዊ ዜጐች ግድያ፣ እመቃ፣
ከስራና ቤት ንብረት መፈናቀል፣ ስደትን… አንድ በአንድ ጠቅሰን ለማውገዝ ብንሞክር ሰማይ-ብራና፣ ቀይ ባህር-ቀለም ሆነው
ካልተመቻቹልን በቀር የሚደፈር አይመስለኝም፡፡ በርግጥ በኢህአዴግ ውስጥ ታላቅና ታናሽ ንጉሠ-ነገሥት የሆኑት ህወሓትና ብአዴን
ብረት ነክሰው፣ ሳንጃ ወድረው በትጥቅ ትግል ያለፉ ከመሆናቸው አኳያ ለየትኛውም አይነት ቅራኔም ሆነ ልዩነት ከመግደልና መጋደል
ውጪ ያለ ሌላ ሰላማዊ አማራጭ ላይዋጥላቸው እንደሚችል መዘንጋት የለበትም፡፡ ኦነግ ከሽግግር መንግስቱ ከተገፋበት ጊዜ አንስቶ
በኦሮሚያ፣ በአዋሳ፣ በሶማሌ… ግፉአን ያለቁበትን፤ እንዲሁም በድህረ-ምርጫ 97 የታየው የጎዳና ላይ ጭፍጨፋ ይህንኑ ሀቅ ያስረግጣሉ፡፡
ኩነቱም ግንባሩ በመጣበት አይነት የነፍጥ የበላይነት ያለፉት ሶቪየት ህብረት፣ ቻይና፣ ቬትናም፣ ኩባ፣ ኤርትራ ባሉ ሀገራት ከታየው
የሕዝቦች እልቂት፣ የተቀናቃኝ ድምፆች መታፈን፣ የጋዜጠኞች መጨፍለቅ… ጋር ቀጥታ ዝምድና አለው፡፡ እነዚህ ሀገራትንም ሆነ
ኢህአዴግን የተለየ ሃሳብ ለማስተናገድ ትዕግስቱም ፍላጎቱም እንዳይኖራቸው ያደረገው ይህ ከውልደታቸው ጀምሮ ከደም-አጥንታቸው
ጋር የተዋሃደው ተፈጥሮአቸው ይመስለኛል፡፡

በአናቱም ኢህአዴግ ከአባላቱ ይልቅ የአመራሩ ‹‹ፓርቲ›› ብቻ ስለመሆኑ ለመረዳት የውስጥ አሰራሩን መፈትሽ የተሻለ ይሆናል፤
እናንተም በቅርበት እንደምታውቁት በድርጅቱ ያልተፃፈ ሕግ ከላይ ወደታች የሚወርድ መመሪያን ትክክል ሆነም አልሆነ ‹‹ለምን?›› ብሎ
መጠየቅ የሚያስቀስፍ ሀጢያት ነው፡፡ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመወያየት መሻት፣ ጥያቄ ማቅረብ፣ ሃሳብን መቃወም፣ ስህተቶችን
ማጋለጥ… አሳድዶ በድንጋይ የሚያስወግር አሊያም ከሀገር ሀገር የሚያሰድድ ታላቅ ጥፋት ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ይህ ሁናቴም ነው
የአስተዳደር ድክመቶቹንም ሆነ አውዳሚ ጉድለቶቹን በፍጹም ለሕዝብ እንዳይደርሱ ገትሮ መያዝን የማይዘናጋበት ዋነኛ መንግስታዊ ስራ
ያደረገው (የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞችን እና የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን በውሃ ቀጠነ ወደ እስር ቤት ሲያግዝ መክረሙን ልብ ይሏል)
በጥቅሉ ድርጅቱ ለአመራሮቹ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በተደረገባቸው ዘመናዊ “V8” መኪናዎች እንዲምነሸነሹ እና በቢሊዮን
የሚቆጠር የሀገር ሀብት እንዲዘርፉ የሚያስችል ስልጣን ከማጎናፀፉ ባለፈ፤ እናንተ (ብዙሀኑ አባላት) ያተረፋችሁት ምንድር ነው?
በአነስተኛና ጥቃቅን ከመደራጀት፣ ‹‹ኮብል-ስቶን›› ፈልጦ ከመደርደር የዘለለስ ማን ምን ሊጠቅስ ይችላል? እስቲ! የተራቆተችና በድህነት
ወጀብ የተንገላታች ሀገራችሁን በዓይነ-ልቦናችሁ ለማስተዋል ሞክሩ፡፡ ያን ጊዜም ገና ጀንበር ስታዘቀዝቅ ስጋቸውን ለመቸርቸር ጎዳናዎችን
የሚያጥለቀልቁ እምቦቀቅላ እህቶቻችን፣ ‹‹ማምሻም ዕድሜ ነው›› እንዲሉ የመፅዋች ዓይን እየገረፋቸው በልመና ቁራሽ ሕይወታቸውን
ለማቆየት የሚውተረተሩ አዛውንትና ህፃናት፣ በየጎዳናው በየሰፈሩ ሲንገላወዱ የሚውሉ ስራ-አጥ ወጣቶች፣ በቀን አንዴ ለመመገብ ላይ
ታች የሚማስኑ ለፍቶ አዳሪዎች… ምድሪቷን እንዳጨናነቋት ይገለፅላችኋል፡፡ የዚህ ሁሉ መንስኤም የፈጣሪ ቁጣ ሳይሆን ፅንፈኛው
3

ድርጅታችሁ በሚከተለው በተግባር ያልተፈተነ (የሀገሪቱን ተጨባጭ እውነት ያላገናዘበ) ርዕዮተ-ዓለም፣ ፖሊሲ፣ አድሎአዊ አሰራር፣
ሙስና እና ለኃላፊነት የማይመጥኑ ‹‹አስፈፃሚዎች›› ችግር ስለመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ጥርጣሬ አይግባችሁ፡፡ እናም ጉዳዩ የሀገር ነውና
በግልፅ እንወቃቀስ (እንነጋገር)፤ ስለምንድነው በአባልነት በምታገለግሉት ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት ‹ዛሬም በስኬት ጎዳና
እየጋለብኩኝ ነው› ብሎ እንደ ቁራ እየለፈፈ በተግባር ግን፡- መብራት፣ ውሃ፣ መንገድ፣ ኔት-ወርክ እንደ አደይ አበባ በዓመት አንዴ ብቻ
ብቅ የሚለው? በአገልግሎት ተቋማት መጠቀምስ እንዲህ የአሲምባን ያህል ያራቀው ማን ነው? ፍትሕን የጠሉትን መበቀያ መሳሪያ
አድርገው ያረከሱት እነማን ናቸው? ሰርቶ መብላት የማይጨበጥ ጉም የሆነብንስ በማን የተነሳ ነው? …በርግጥ ይህንን ጥያቄ ለጠቅላይ
ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ብናቀርብለት እንደ መለስ ዜናዊ በተረት መሳለቁ ባይሆንለትም፣ ‹‹ሰለሜ ሰለሜ››ን እየጨፈረ፤
እነ‹‹ሚካኤል ስሁል›› በቀደዱለት ልክ ዳናኪራውን እያስነካው ‹‹ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም!›› ብሎ ከመዘባበት አይመለስም፡፡
መቼስ እንደዚህ ሕዝብ የተናቀ የትም አይገኝም፡፡

ኢህአዴግ መፍረስ ያለበት ለምንድን ነው?

ይህንን አጀንዳ ለማንሳት መግፍኤ የሆነው ከላይ ለማሳያ ያህል የተጠቀሱት ስርዓታዊ ጥፋቶች በግላጭ የመታየታቸው እውነታ ብቻ
አይደለም፤ ይልቁንም ድርጅቱ ከስሁት መንገዱ ለመታረም (ለመታደስ) ፍፁም ዝግ-በር የመሆኑ ጉዳይ ጭምርም ነው፡፡ አዎን፣ እነዚህ
አሁን ሁላችንንም እያማረሩ ያሉ አብዛኞቹ ችግሮች የተከሰቱት አንጋፋው ድርጅታችሁ የ‹‹ኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ
ግንባር›› የሥልጣን መሰረቱን ለማፅናት ይሁነኝ ብሎ ከደፈጠጣቸው መብቶች ጋር ተያይዘው ከመሆናቸው በዘለለ ለኢኮኖሚያዊ
ጥያቄዎች በቂ ምላሽም ሆነ ሁነኛ መፍትሔ የሌለው ፀረ-ሕዝብነቱ የተረጋገጠ፣ ለመታረም ዝግጁ ያልሆነ፣ ተስፋችንን ያሟጠጠ ስርዓት
ስለሆነም ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመሪያ እነበረከት ስምኦን ልባቸው ከኢህአፓ ለመኮብለሉ አብይ ምክንያት አድርገው ያቀረቡትን ችግር
ታዬ የተባለ ታጋይ ‹‹ሞናሊዛ›› በሚለው ግጥሙ ግሩም አድርጎ ገልጦት እንደነበረ በ1993 ዓ.ም ‹‹ፅናት›› በሚል ርዕስ የተጋድሎ
ታሪካቸውን ባሳተሙበት መጽሐፍ ላይ ተርከውታል፡፡

‹‹አንተ ሌዎናርዶ የሮማ ጅል
የሰራሀትን ልታሻሽል
ልታፈርሳት ልትገነባት
ደግመህ ደጋግመህ ልትሰራት
ሰልሰህ ልትሰራት ስትችል
ጣኦት አደረግካት በሞትህ አጉል አጉል
ለራስህ ፍጡር እግዚኦ ልትል››

ይህ ግጥም በሰፈረበት ገፅ ላይ የተጠቀሰው የግርጌ ማስታወሻ ደግሞ ሊተላለፍ የተፈለገውን መልዕክት እንዲህ በማለት አብራርቶታል፡-
‹‹ታዬ የሚባል የኢህአፓ ታጋይ ‹ራሳችን የፈጠርነውን ድርጅት ማስተካከል አለብን› የሚል እምነት የነበረው ሲሆን፣ ዳ ቪንቺ እራሱ
ለሳላት ሞናሊዛ ፍቅር እንደተማረከ ሁሉ እኛም የፈጠርነውንና የተበላሸውን ድርጅት አመለክነው፤ ማስተካከልም ተሳነን በማለት ፓርቲው
ላይ እምነት ማጣቱን ‹ሞናሊዛ› በሚል ርዕስ በፃፈው ውብ ግጥም ገለፀ፡፡›› (ገፅ 61)

እነሆም አብዮታዊ ግንባሩ፣ ከመስራቾቹ አንዱ የሆነው ኢህዴን/ብአዴን፣ ያን ጊዜ ኢህአፓን መክሰሻ ባደረገበት ‹‹ድርጅታዊ አምልኮ››
ራሱም ተጠልፎ ከወደቀ ዓመታት ነጉደዋል፡፡ ታዬ እንዳለውም መሪዎቹ ኢህአዴግን ናቡከደናፆር አሰርቶት እንደነበረው አይነት እጅግ
ግዙፍ ‹‹አምላክ›› (ጣኦት) አድርገው ሀገርና ሕዝብን እየገበሩለት (እየሰዉለት) ነው፡፡ ርዕዮተ-ዓለምም ሆነ ፖሊሲ (በተለይ መሬትን
በተመለከተ) ‹‹የሚቀየረው በመቃብራችን ላይ ነው›› ሲሉም አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ የትምህርት ፖሊሲውም እንዲህ ትውልድን
እየገደለም እንዲሻሻል ያልተሞከረው በዚሁ እምነታቸው ይመስለኛል፡፡ ይህ ሁኔታም ነው እናንተም የምትስማሙባቸውን ታላላቅ ሀገራዊ
ችግሮችን ለመፍታት ኢህአዴግን ከማፍረስ ውጪ አማራጭ እንዳይኖር ያደረገው፡፡ ከእንግዲህ ወዲያም ከጥፋቱ ታርሞ ለሀገር የሚጠቅም
ዲሞክራሲያዊ የህዝብ ሥርዓት ሊያነበር ይችላል ብሎ ተስፋ ማድረግ ተላላነት ነው፡፡ እንኳን እናንተ ከተማ ላይ የተቀላቀላችሁት አባላት
ቀርቶ፣ ከበርሃ አቅፈው ደግፈው እዚህ ያደረሱት አንጋፋ ታጋዮችና አንዳንድ አመራሮቹም በድርጅቱ ተስፋ ቆርጠው ጥለውት መሄድ
ከጀመሩ ሰንብቷል፡፡ ታጋይ የውብዳር አስፋው ‹‹ፊኒክሷም ሞታ ትነሳለች›› በሚለው መጽሐፏ እውነታውን እንዲህ በማለት ገልፀዋለች፡-
‹‹የድርጅቱ አመራር የወሰዳቸውን የተሳሳቱ እርምጃዎች ቀድሞ ከነበረኝ የድርጅቱ ግንዛቤ ጋር በማጣመር ለዓመታት የታገሉለትንና
የደከሙለትን አባላት በነፃ እንዲንቀሳቀሱ ያላስቻለ ድርጅት፣ ለሕዝብ ነፃነትና ለዲሞክራሲ እታገላለሁ ቢል ከይስሙላ የማያልፍ ከንቱ
መፈክር መሆኑን ደምድሜ፣ ከመጋቢት 5 ቀን 1993 ዓ.ም ጀምሮ ራሴን ከድርጅቱ አገለልኩ፡፡ ይህም በሕይወቴ ጉዞ ዋነኛውና ወሳኝ
እርምጃ ነበር፡፡›› (ገፅ 16)

እንግዲህ ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የድርጅት፣ የሴቶች ጉዳይና የመንግስት ሥራዎች ተሰማርታ ልጅነቷን በትግል የጨረሰችው የአቶ
ገብሩ አስራት ባለቤት፣ የውብዳር አስፋው እንዲህ አይነቱን ከባድ ውሳኔ በማሳለፍ ከኢህአዴግ ከተቆራረጠች እነሆ አስራ ሶስት ዓመታት
4

ነጉደዋል፡፡ በግልባጩ እናንተ ደግሞ እስካሁን ድረስ አንቀላፍታችኋል-ገና አልነቃችሁም፡፡ እናም እውነት እውነት እላችኋለሁ፡- ከዚህ
በላዔ-ሰብ ሥርዓት ለመገላገል የምንችለው፣ ዛሬውኑ ይህንን ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ዋነኛና ወሳኝ እርምጃ በቆራጥነት መውሰድ
ስትችሉ ብቻ ነው፡፡ አለበለዚያ…

(የዚህ ጽሑፍ ሃሰበ-መልዕክትን በቅንነት ትቀበሉታላችሁ በሚል መተማመን አፈፃፀሙን፡- በምን አይነት መንገድ ተቀራርበን ልንወያይ
እንችላለን? በየትኞቹ ጉዳዮች ላይ መግባባት ይቻላል? ሃሳቡንስ ከግብ ለማድረስ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል? የሚሉትንና መሰል
ጥያቄዎችን በሌላ ዕትም ተገናኝተን በስፋት እንመክርባቸዋለን)

አትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

የሒሳብ አያያዝ ባለሞያ የለም ወይ ባገሩ? (በለንደን ለምትገኝ ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን አባላት)

የመስዋዕትነት ወንጌል –ከጸጋዬ ገ.መድኅን አርአያ

$
0
0
በአጤ ኀይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት (በ1960 አካባቢ) ኤድመንድ መሪ የተባለ አሜሪካዊ የዕለታዊው ኢትዮጵያ ሔራልድ ጋዜጣ አማካሪ ሆኖ ይሰራ ነበር። እኛም እንጠረጥረው እንደነበረ ሁሉ የአሜሪካ ስለላ ድርጅት ሠራተኛ (ኮንታክት ማን) ነው። (እግዜሩ ይይላቸውና ለካ በእኛም መሐል ሰዋቸውን ይተክሉ ነበር) ኤድ መሪ የሥነ ጽሑፍ ሰው ስለሆነ በማስታወቂያ ሚኒስቴር “ተረፈ ዜና” የምንለውን – የማይታተመውንና የማይታወጀውን (በራዲዮና በቴሌቪዥን) በንጥረ ነገሩ መውሰጃ ሥፍራ የተነፈስነውን ሁሉ ሰብስቦ ካገጣጠመው በኋላ ወደ አሜሪካ ሲመለስ Kulubi የሚል መጽሐፍ አወጣ። እንግዲህ ተረፈ ዜና የገባችሁ ይመስልኛል። ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ብዙ ሳንርቅ- ጠባያችንን ወደማያውቁ ሰፈሮች በወረራ መልክ ሳንዘምት እዚያችው ከባዕታችን እንደልማዳችን እንቀማምስና (ከቢራ አያልፍም) ቶሎ ወደ ማተሚያ ቤት እንመለሳለን። እንግዲህ ደግሞ ወደ ማተሚያ ቤት እንመለሳለን። “ምሳችንን እንጠጣ” ይላሉ አንዳንዶቻችን። ቀስ ብሎ ሁላችንም እንዲህ እንደምንል ተደርጐ ተወርቶብናል።
Pen
 በምሽቱ የቢራ ታይም አውት ሰዓት እንደ ሚዚዬ (መክሰስ) ልትታተም ያልቻለችና የማትችል ወሬ ትቀርባለች። ድሮ ድሮ እኔ በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ሪፖርተርነት ስሠራ አንዳንዶቹን ተረፈ- ዜና ውሃ እየጨመርሁባቸው “የአዲስ አበባ ሹክሹክታዎች” ብዬ ለማውጣት ሞክሬያለሁ። ያም ሆኖ “የማይታተሙና የማይታወጁ” “ተረፈ ዜና” ደኅና አድርገን ሰልቀን እንመለሳለን። አሉባልታ አልተከለከለም። የተከለከለው በጋዜጣና በራዲዮ ላይ ነው። የኤድመሪ “ቁልቢ” እንዲህ ያሉና የበለጠ በፖለቲካ ትካዜያችን ወቅት በብቅል የመጣ አሳብ ከእኛው ለቃቅሞ ጥሩ ውበትና ስላቅ ለብሶ የመጣ መጽሐፍ ነው። አይ የሰላይ ነገር! ( በኋላ ጊዜ- በ2006ዓ.ም ላይ ሰውየው ሲሞት ሰላይ እንደነበረ በኦፊሲያል ተነግሮናል። ያለፈ ነገር አንዳንድ ጊዜ ይጥመናል። ደራሲያችን አቤ ጉበኛ አንድ ጊዜ- በዚያው በአጤው ሥርዓት አሜሪካ ሄዶ ሲመለስ በመጀመሪያ ያወራልኝ ኤድመሪን በገዛ አገሩ እንደደበደበው ነው። እኔም “የእኔ ዘርዓይድረስ!” አልሁት።)
 አዎን ኤድ መሪ- በኋላ ጊዜ በዓሉ ግርማ ሲጽፍ በነበረበት ስታይል – የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሹማምንት አጣምሮ በአንድ ስም እያቀረበ በማናገር መጽሐፉን አጣፍጦታል። በዚያ ጽሑፍ ላይ በቅርብ የሚያውቀውን በመጨረሻው የአጤው ሥርዓት የኅትመቱ ፕሬስ ምክትል ሚኒስትር የነበረውን አቶ ተገኘ የተሻወርቅን “ተስፋዬ” ብሎ ዋናው ገጸ ባሕርይ ያደርገዋል። (የኅትመቱ ፕሬስ መምሪያ የመጨረሻው የደርግ ዘመን ኅላፊ ይህ ጸሐፊ ነበር።) (ተረፈ- ዜና ማቅረቤ ነው- ባያምርልኝም) ለቁም ነገሩ ኤድ መሪ ትንንሹንም (ለምሳሌ የትልልቆቹን ሰዎች የወሲብ ሕይወትና አንዳንድ ባለሥልጣኖች እጅግ ወራዳ በሆነ ሁኔታ ቆነጃጅት እየመረጡ ለትልልቆቹ (ስም አላነሳም) ስለሚያቀርቡበት ሁኔታ ይወሳል። አንዳንዶች ደግሞ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሕይወት ምን አቅጣጫ እንደሚይዝ እየታያቸው የጭንቅ ሕይወት እያሳለፉ እንደሚገኙ ቃኝቶአል። እንዲያውም ዋና ገጸ- ባሕርይ አድርጐ የሳለው “ተስፋዬ” (ማለትም ተገኘ የተሻወርቅ) በዚህ ረገድ እየተቃጠለ- እየከሰለ እንደሚገኝ ያወሳል። የትዮጵያ ውድቀት፣ የክብርዋ ድቅት፣ -የአንድነትዋ መፍረስ- በአንድ ወቅት ደሀዋ ኢትዮጵያ እንደ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ… ካሉ አገሮች እኩልና ከቶውንም ጐላ ብላ የመታየትዋን ሁኔታ..ወዘተ ይነግረናል። የፖለቲካውን ሁኔታ ይመረምራል። አዎን ተስፋዬ ከአንድ ትልቅ ተራራ ላይ ያቆመዋል። ኢትዮጵያን በሙሉ ያያል። የተስፋዬ አእምሮ በአንድ ሴኮንድ እይታ ሰማያት ሲደፉበት፣ ያታየዋል። አእምሮው ሮጠ። ሮጠ። እዚያ ተራራ ላይ ደራሲው ለምን ተስፋዬን አወጣው? ወደ ሲና ተራራ፣ ወደ ካርሜል ተራራ፣ ወደ ደብረዘይት ተራራ ሄደው ከአምላካቸው የሚቀበሉትን ቃልና መልእክት ስለተረከቡትና በነዚያው ተራሮችም (ለምሳሌ ጌታ ኢየሱስ በደብረዘይት ተራራ) ለሕዝቡ ሲያስተምሩ እናነብባለን። የግሪክ አማልክት መኖሪያ በሚባሉት በኦሊምፐስ፣ የሮማውያን አማልእክት ቤቶች መገኛ በሚባለው አልፕስ- በሒማላያስ ተራሮች የሕንድ ሺህ በሺህ አማልእክትና መልእክቶቻቸው ብዙ አንብበናል።
 የኤድ መሪው “ተስፋዬ” ከእንጦጦ ተራራ ላይ ይቆምና ትልቂቱን ኢትዮጵያ ለማየት ይሞክራል። ትልቂቱ ኢትዮጵያ ለትናንሽ ዓይኖቹ ኮሳሳና ትንሽ ሆና ታየችው። የልጅ ኢያሱ ወዳጅና ባለሟል የነበሩት አባቱ በግዞት በነበሩበት ጊዜ ደሴ ተወልዶ ያደገበትና ከእሳቸውም ስለውብ አገሩ ሲሰማ ያደገበት ሁኔታ …ወደ ሐረር ሄዶ የልጅነት መንፈሱን ስለአገሪቱ ታላቅነት እየተረዳ የኖረበት፣ አብሮ አደጉ የለውጥ መንፈሱ የዳበረበትን ሁኔታ፣ በኮተቤ ሁለተኛ ደረጃ…በዩኒቨርሲቲ ኰሌጅ ያሳለፈው የፖለቲካ ንቅናቄ ሕይወት፣ ከቦስተን ዩኒቨርሲቲ ሲመለስ ምን ለማድረግ፣ ምን ለመሆን የነበረው ህልም ግጥም አለበት። ለትናንሽ አይኖቹ፣ ለትንሽዋ ጭንቅላቱ ኢትዮጵያ ኮስሳና ኰስምና ታየችው። “ኢትዮጵያ! ወይ ኢትዮጵያ!” አለና ሲጨርስ ከእነዚያው ልም-ዓይኖቹ ውሃ ይቀዳ ገባ። አለቀሰ።
 እንዲህ ዓይነት ታሪክ ፍጻሜና የሌላ ታሪክ ጅማሬ ለትረካው ባለቤት (ኤድመሪ) እንዴትና ለምን እንደመጣበት አላውቅም። ለማንኛውም ግን “የሳይኪ ጉዳይ” እስካሁን በምንም ሁኔታ ተዘርዝሮ እንደማይነገር የታወቀ ነው። ብቻ በአገራችን የተከፋ ተደፋ – ይባላል። ተገኘ የተሻወርቅ ጥቅምት 13-1967 ሌሊት ላይ በጥይት ከተደበደቡት ስድሳዎቹ የአጤ ኅይለሥላሴ ባለስልጣኖች አንዱ ሆነ።
 እንደ ጥንቱ ነቢይ- እንደ ኤርምያስ እኔንም አልቃሻ ሳያደርገኝ አልቀረም። “ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ!..” እያሉ ሲያለቅሱ ከነበሩትና ትንሣዔዋን (እሱም ካለ) ሳያዩ ዓለምን ከተሰናበቱት ግዙፋን ኢትዮጵያውያን መካከል አለቃ አያሌው ታምሩም ትዝ ይሉኛል። አለቃ አያሌው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሊቃውንት ጉባዔ ፕሬዝዳንት ነበሩ። አዲስ አበባ በነበርሁበት ጊዜ እሳቸው የሚመሩት “ማኅበር በኩር” ከሚባለው በየሳምንቱ በሚሰበሰብ ጉባዔ ላይ ብዙ ጊዜ ተካፍያለሁ። ለመንፈሳዊ ልጆቻቸው “በኢትዮጵያ ቤተ መንግሥቱም ቤተክህነቱም ያለ መሪ የቀረውና መከራችሁ የበዛው በእኔ ምክንያት ነው። ኅጢያተኛው እኔ ነኝ።” እያሉ መንታ መንታ እንባ ሲያፈሱ አስታውሳለሁ። አለቃ አያሌው “የእኔ ኅጢያት..” ሲሉ የሃይማኖት አባቶችም እንደ ፖሊቲካ መሪዎች እልም ብለው የጠፉበትን ሁኔታ መግለጣቸው መሆኑ ይሰማኛል። በዚህም እምነት በመነሳት ከሩሲያ ዛሪና ጋር ተባብሮ በተራ ሴሰኝነት ተጠምዶ ክፉ እየመከረ፣ ሕዝብ እያስገደለ ለኮሚኒዝም መግቢያ አውራ ጐዳና ጠራጊ የነበረውን የውሸት መነኩሴ ራስ ፑቲንን (አቡኑን) ያወግዛሉ። የአባ ጴጥሮስን ፈለግ በመከተል እስከ ማዕዜኑ (እስከ ወዲያኛው) አትቀበሉት ብለዋል። ለነገሩ ከሞቱ ከአሥር ዓመት በኋላ የቤተክህነቱም የቤተ መንግሥቱም መሪዎች በጥቂት ቀናት ልዩነት ተያይዘው ሄዱ።” ባለፈው መጣጥፌ የጠቀስሁት ሥዩም ሐረጐት እንዲህ ዓይነት ፍጻሜን “የክብረ ነገሥት ፍጻሜ” ይለዋል። ይህ ፍጻሜ የአጤው ሥርዓት መደምደሚያ ብቻ አይደለም። ለራሳቸው አጤያዊ ሥርዓት የቆረቆሩትን ዘመናዊ አጤ በጉልበቱና ራስፑቲኖችን ፍጻሜ ይመለከታል። የሚገርመው ከእነሱ በኋላም ቢሆን የአለቃ አያሌው እንባ አልተገደበም። በሥጋ ረገድ ዓይነሥውር የነበሩት የእኒህ አባት እንባ ደግሞ ሕሙም ከነበረው አንጀታቸውና ልባቸው የሚቀዳ እንባ ነበር። “ኢየሩሳሌም! ኢየሩሳሌም ለራስሽ አልቅሺ!” ነበር ጌታ ኢየሱስ ያለው? ለራሳችን የማናለቅስ ነንን? አለቃ አያሌው እንደ ተገኘ የተሻወርቅ የታያቸው ገና ያልመጣ – እንደሚመጣ የተረጋገጠ- የኢትዮጵያ አደጋ አለ። ጠብቁ ልበል ወይስ ይበቃናል?
 ከታገሳችሁ ሌላ አጋጣሚ ላውራችሁ። “የሸዋ ጠቅላይ ግዛት” እንደራሴ የነበሩትንና ከአውራ አርበኞቻችን አንዱ የሆኑትን ራስ መስፍን ስለሺን በ1966 መጋቢት ላይ አነጋግሬያቸው ነበር- ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ። የካቲት “ግም” ካለ በኋላ ስለ ለውጡ የተለያዩ የሕብረተሰቡ አባላትን “ስለ ለውጡ ምን ይሰማሃል? ወዴት የምጓዝ ይመስልዎታል? ከአድማስ ባሻገር ምን ችግር- አደጋ- ያታይዎታል? ወንድሜን ማን ልበል?..” የሚሉ ጥያቄዎችን ይዘን መዞራችን አልቀረምና ጌታ ራስ መስፍንን በቢሮአቸው አነጋግሬአቸዋለሁ- እንዲያውም የሾረ ጋዜጠኛ ከምለው ከሀብተ ዮሐንስ ዲሳሳ ጋር። በግልጽ እንደ ነገሩን የኢትዮጵያ ሰማያት ያረገዙት ዝናም የምሕረት አይመስልም። “አየኸው ጌታዬነህ! የኢትዮጵያውያን ደም የተከበረ ነው። በከንቱ መፍሰስ የለበትም። አንድ ጊዜ መፍሰስ ከጀመረ ማቆሚያ የለውም። ለውጥ አያስፈልግም አንልም። ያስፈልጋል። ደም በመፋሰስ የሚመጣ ለውጥ ለማን ሊጠቅም ይችላል?” ነበር ያሉኝ። ብዙ ጊዜ የምጠቅሰው የሼክስፒየር ቃል አለኝ። መጭ ሁኔታዎች አስቀድመው ጥላቸውን ያሳያሉ፤ Coming events cast their Shadow- አዎን ለራስ መስፍን እንደታያቸው ሁሉ በዚያ ወቅት የኢትዮጵያውያን ደም መፍሰስ የጀመረ እነሆ አርባ አመት ሆነው። ራስ መስፍን በዚያን ወቅት ለማልቀስ አልዳዳቸውም አይባልም። እንባቸውን ከመታገላቸው በስተቀር።
  ኔልሰን ማንዴላ በ Long Walk to Freedom ስለ ፍርሃትና ድፍረት የነገሩን ቁም ነገር አላቸው። በየሰው ልብ ውስጥ ፍርሃት አለ። የድፍረቱ መጠን (ዶዜች) ትንሽ ከፍ ያለውና ያንንም በተግባር የሚያውለው ጀግና ይባላል። ደፋር ይባላል። አለዚያ ሁላችንም በተፈጥሮአችን ውስጥ- ከተፈጥሮ የወረስነው ፍርሃት አለ። ጀግኖች ደግሞ ከፈሪ ሕዝብ አየፈጠሩም። አባ ኮስትር በላይ ዘለቀ በኅብረተሰቡ መሐል ሲወጣ በአንድ እጁ ጐራዴ፣ በሌላ እጁ ሰነኔ ይዞ አይደለም። ጀግና የሚፈልግ ታላቅ ሕዝብ ፈልጐ ያገኘው ነበር። ድፍን በረንታ፣ ድፍን ሶማ፣ ድፍን የዳባት፣ ድፍን ብቸና…እቅፉን ዘርግቶ ባይቀበለው ኖሮ በላይ አልነበረም። ታሪክም ባልሆነ ነበር።
 ጉራ እንደማይሆንብኝና እናንተም በዚህ እንደማትጠረጥሩኝ ተስፋ አለኝ። በመሠረቱም በእውቀትም፣ በማሕበራዊ ደረጃም ማንንም ወደ ታች ለመመልከት የማልችል ምስኪን ዜጋ ነኝ። እንዲህ የምልበት ምክንያት አለኝ። ማንንም ወደ ታች መመልከት ኅጢያት ሆኖ ይበላሃል። ወንድምህን ወደ ታች የምትመለከተው መንጥቀህ ልታወጣው የምትችል ከሆነ ብቻ ነው። እንዲሁ አንዳንድ ማስታወሻዎች እያየሁ፣ ከአንዳንድ ታላላቅ ዜጐች (በየአጋጣሚው) ጋር በመገናኘት ትዝታቸው የእግር እሳት እየሆነ እንቅልፍ የሚነሳኝ ነኝ። የልጅ ልጆቼን (ስድስት ሆነዋል) እያጫወትሁ፣ ቁም ነገር እየነገርኋቸው በሚገባኝ የዕድሜ ርበት ላይ አገር አጥቼ ስኖር (እግዜር ይመስገን መንፈሳዊ አገር አላጣሁም) በየጊዜው በርበሬ እንደታጠነ ወጣት የሚነቀንቀኝ ነገር አልጠፋም። እንግዲህ “በወረቀት ማበላሸቱ ሥራ” (በጋዜጣ ሥራ እንዳልል ያበረከትሁት አስተዋጽዖ ያሳፍረኛል- ከልብ) ብዙ ዘመን ስላሳለፍሁ ብትፈቅዱልኝ አንድ ሌላ ትዝታ አየመጣብኝ ነው። እንደ መረማመጃ አሳብ ከሆነ ደስ ይለኛል።
 በአጤ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ጊዜ እንደ መጀመሪያው ጋዜጠኛ ሲጠቀሱ የነበሩትን ጋዜጠኛ (ከንቲባ) ደስታ ምትኬን ከአንዴም ሁለት ሦስቴ አነጋግሬያቸዋለሁ። ደስታ ምትኬ ምኒልክን ተከትለውና እንዲያውም የእቴጌ ጣይቱን ቀሚስ እየጐተቱ ወደ አድዋ ጦር ግንባር ከዘለቁ ለጋ ወጣቶች አንዱ ነበሩ። ወደ አድዋ ስለተደረገው ጉዞ፣ ስለአገራቸው ሠራዊት ልበ-ሙሉነት፣ ስለ ጦርነቱ ውሎ ደኅና ሲያወሩላችሁ ቆይተው አፈፍ ብለው ቆመው እየየ ይላሉ። የወደቀው የአገራቸው አርበኛ ከፊታቸው ይመጣባቸዋል። ይሰለፋል። ታንክ በጐራዴ የተባለበትን እሾሁ እንኳ ስለማይወጋው ጦረኛ ያወጉአችኋል። እየየ ይላሉ። አንዳንድ ሰነፍ ተዋጊ ለመሸሽ ሲሞክር እቴጌይቱና ደንገጡሮቻቸው “አንተ ወዴት ነው የምትሸሸው- እያሸነፍህ? እየረፈረፍኸው? የምኒልክ ጮማ- የምኒልክ ጠጅ ይኽ ነው?” እያሉ የፈሪ ልብ ሆነው ሲያዋጉ የነበረበትን ሁኔታ ያነሡና ያለቅሳሉ።
 ጦርነቱ አልቆ በምኒልክ ድንኳን ውስጥ ከነበሩት መሳፍንት መካከል ራስ መኰንን የተናገሩትን ያስታውሳሉ። ደስታ ምትኬ እንድሚሉት ራስ መኰንን “ግርማዊ ጃንሆይ! እናቴ እቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ እግዚአብሔር በዚች ዕለት ወደፊት በሚነሡ የኢትዮጵያ ትውልዶች ላይ የሚያመጣውን ጦርነት ሁሉ እኛው እንድንገላገለው ቢሰጠን ምንኛ መታደል ነበር?” እንዳሉ ይጠቅሳሉ። ይህን ትዝታ ያወርዱና ከንቲባ ደስታ እየየ ይላሉ። በእንባ ይጠመቃሉ። ራስ መኰንን ከእነሱ በኋላ የሚበቅለውን ትውልድ የተጠራጠሩ ይመስላል። ለአገር አንድነት የሚኖረውን እሴት፣ የወገንን ሉዓላዊነትና ክብር በማስጠበቁ በኩል የሚያድርበት የውጊያ መንፈስ፣ “የኢትዮጵያ እና የመስዋዕትነት ፋይዳ ምን ያህል ለትውልዶች ሊወርድ እንደሚችል ጠርጥረዋል። በእኛ ላይ ተስፋ የቆረጡ ነበር…ልበል? ” ደስታ ምትኬ አለቀሱ። አለቀሱብኝ። መላልሼ አነጋግሬያቸዋለሁ። ደጋግመው አለቀሱብኝ። ደስታ የሉም። እኔ ቀርቻለሁ። አላቅሱኝ ልበል ወይ? ወይስ የደስታ ምትኬ ስሜት ያላችሁን ሁሉ እናላቅሳችሁ ወይ? (በነገራችን ላይ ከንቲባ ደስታ ምትኬ የኮሎኔል መንግሥቱን ሥርዓት ለመለወጥ ተነሥተው ከተሰውት ጄኔራል መኰንኖች የአንደኛው የጄኔራል አምሐ ደስታ አባት ነበሩ። የጀግና ልጅ ጀግና)  - በተጨማሪ ሊነሳ የሚችለው የጋዜጠኝነቱ ጉዳይ ሲወሳ ደግሞ ኤርትራ በወቅቱ በኢጣልያ ሥር ስለነበረች እንጂ በጋዜጣ ባለሙያነት ረገድ ምጽዋ ውስጥ ይታተሙ የነበሩት ጋዜጦች አዘጋጅ የነበሩት ብላታ ገብረ እግዚአብሔር ጊላይ ይጠቀሳሉ። እኒህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ደግሞ በጋዜጣቸውና በሌሎችም ጽሑፎቻቸው ቅኝ ገዥውን አምርረው የታገሉ አርበኛ ናቸው። የብላታ ገብረ እግዚአብሔር ጊላይ There is no medicine fot the bite of the White Snake ዋናው ነው። የስካንዲኔቪያው ምሁር የፕሮፌስር ተከስተ ነጋሽ ሥራዎች ለዚህ ምስክር ናቸው።
 ያ ሁሉ የአርበኝነትና የጀግንነት እሴት አንድ ጊዜ ሟሽሾና ከውስጣችን እንደ ፈጣን ወፍ ሸሽቶ ከላይ የጠቀስኋቸው ሰዎች ሁሉ የፈሩት እየደረሰ መጣ። እኛው በእኛው፣ እኛው ከእኛ ጋር ጠላትነት አበቀልንና እኛንም አገሪቱንም የሚያድን ጠፋ። በአገሪቱ ጀግኖቻችንና ዋናው የሃይማኖት አባት ላይ ሳይቀር ሞት ስናስተላልፍ ተገኘን። በፋሺስቶች ዘመን፣ ሚስት በባልዋ፣ አባት በልጁ፣ ኦሮሞው በኦሮሞው፣ አማራው በአማራው፣ ትግሬው በትግሬው ላይ ጦር የሚመዝበት፣ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ “ይሙት በቃ” የሚልበት፣ የሚጠቁምበትና የሚተኩስበት አሳዛኝ ገድል አየን። የምታውቁት ታውቁታላችሁ…ለማታውቁትም እንደ መርዶና የታሪካችን ቆሻሻ ምዕራፍ ላነሣ እችላለሁ። አንዱንና ጉልሑን ማለቴ ነው። የሰማያዊው ንጉሥ አገልጋይና የኢትዮጵያ የቃልኪዳን ልጅ የሆኑት አቡነ ጴጥሮስ ግንባራቸውን ሳያጥፉና የሞት ፍርሃት ሳያስደነግጣቸው በፋሺስቶች ጥይት መደብደባቸውን ታውቃላችሁ። እውን ጣልያን ብቻ ነው ይሙት በቃ ያላቸው? አንድ የመሐል ዳኛው ነው ጣልያን የነበረው። የቀኝና የግራ ዳኞች ተብለው የተሰየሙት ኢትዮጵያውያን ነበሩ። ብላታ አየለ ገብሬና ነጋድራስ ወዳጆ አሊ። “በጥይት ይደበደቡ ዘንድ ፈርደናል። ከማንዳንቴ ባሪሴሮ፣ ብላታ አየለ ገብሬ፣ ነጋድራስ ወዳጆ አሊ!” አቤት ጭካኔ! አቤት ጭካኔ! ከዚያ በኋላ የነበሩትን ብዙ ብዙ ክህደቶች ላጫውታችሁ እችላለሁ።
  ክህደቶቹ የባሰ የሆኑት “ጨው አልጫ ሆነ” ብሎ የክርስትና መሥራች ራሱ የሚመሰክርባቸው ካሕናትና መነኰሳት ሲሆኑስ? አቡነ ጳውሎስ (ራስ ፑቲን) እና አያሌ መነኮሳት ሲሆኑስ? አዎን አቡነ ጴጥሮስና አቡነ ሚካኤል በክርስቲያናዊ አርበኝነትና ለአገርም ለሕዝብም ሰማዕታት ሲሆኑ አቡነ ገብርኤልና ሌሎችም የፋሺስቶች አስተናጋጆች እንደነበሩ ሌላው የታሪካችን ገጽታ ነው። ጄኔራል ቦዳልድ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ ነው ሲባል ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ካሕናትና መዘምራን ሰላሳ ኪሎ ሜትር ርቀት ተጉዘው ልብሰ ተክህኖአቸውን ለብሰው፣ ከበሮአቸውን እየደበደቡ፣ ጸናጽሉን እያንጻለሉ…ተቀበሉት ይባላል። በጽሑፍ ጭምር ቆይቶልናል።…ቆይ ቆይ እንጂ ወዳጄ ዶክተር አረጋዊ በርሔ የሚነግረን ምሥጢር አለው። ወያኔ ሥልጣን ከመያዙ በፊት – ጫካ በነበረበት ዘመን ከአንድ ሺህ በላይ ካህናትና መነኮሳት ካድሬዎች ነበሩት። ስለ አስቆሮቱ ይሑዳ ማውራት የማይሰለቻቸው ከሐድያን ደባትር! ሃይማኖቱ በዚህ የተነሳ ሊወቀስ አይገባውም። ቆቡን ያጠለቁ ደካሞች፣ ጸናጽሉን የሚያንሹዋሹ ሰነፎች እንጂ። ራስ መኰንን እንዲህ ያሉ ሰዎችን እያሰላሰሉ፣ ራስ መስፍን የሚመጣውን የደም ጐርፍ እያሰቡ፣ የኤድመሪ “ተስፋዬ” የአገር መቅለጥ ትካዜ እያስጨነቀው ቢያለቅስ- ቢያለቅሱ- ይብዛባቸው?
                                የሚሰውት አለቁ?
ቀደም ሲል ለጠቀስኋቸው ጋዜጠኛ (ደስታ ምትኬ) ሁለት ጥያቄዎችን አንስቼባቸው ነበር። አንደኛው ጥያቄ “ለመሆኑ የአርበኝነቱ ዘመን- የጀግንነቱ ፍጻሜ” አድዋ ነው ብለው ያምናሉ?” ሁለተኛው ጥያቄ “እቴጌይቱ የምኒልክ ጮማ- የምኒልክ ጠጅ እንዲህ ነው ወይ? ሲሉ ለመሆኑ ያ ሁሉ ሠራዊት የምኒልክን ጠጅና ጮማ ያውቅ ነበር ማለት ነው?” አልኳቸው። አረጋዊው ከንቲባ የምኒልክ ጮማና ጠጅ ይትበሐል ነው። በምኒልክ ጊዜ ሕዝቡ ሰላም ነግሦለት፣ ፍትሕ አግኝቶ ያለሥጋት የሚኖርበት መሆኑን በሙሉ እርግጠኝነት ይናገራሉ። አገር የመጠበቅን እሴት አንሥተው በዚያ መንፈስ ሕዝቡ በአንድነት እየተመመ ወደ ጦር ሜዳ በደስታ እንደ ዘመተ ያወሳሉ። ኢትዮጵያን የጠበቀ ይህ መንፈስ ነው። ይህ እምነት ነው። ያ ወኔ ነው። የእነዚህ የሦስቱ ባሕርያት ውህደት እየተሸረሸረ መምጣቱን ደግሞ በዓይናቸው በብረቱ አይተውታል። በፋሺስቱ ወረራ ወቅትና በኋላም። በኋላም እስከ እኛ ድረስ! አዎን እንደሚባለው ምኒልክና ጣይቱ ብቻ ሳይሆኑ እንደ ራስ መኰንን፣ ራስ መንገሻ ወዘተ ያሉትም በማዕዳቸው ከበርካታ ሕዝብ ጋር ይመገቡ እንደነበረ ይታወቃል።
 እነዚህ የጠቃቀስኋቸውና እንደ ነብዩ ኤርምያስ ባለሙያ አልቃሽ የሚመስሉት አባቶች ፍርሃት ሊሰመርበት የሚገባ መሆኑን እረዳለሁ። ወርቁም ሚዛኑም በጠፋበት በዚህ ሰዓት ለአገሪቱ ጥሪ ማነው “እነሆኝ እኔ” የሚል? እኔም እንደነሱ በተራዬ እጠይቃለሁ። በግፈኞች አማካይነት ወደ ግፈኞች የስቅላት “ስካፎልድ” ሲወሰዱ ቀጥ ብለው በኩራት የሚራመዱ ሰዎች አሉን? አዎ…አዎ…አዎ…ቁጥራቸው አነሰ እንጂ!
 አቶ ተፈራ ደግፌ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ሥርዓት በማስያዝ፣ የባንክን አገልግሎት ለማስተዋወቅና ራሳቸውም በንጽሕናና በሕጋዊነት በመኖር የተደነቁ አገር ወዳድ ሰው ናቸው። አቶ ተፈራ በደርግ ጊዜ በግፍ ከታሰሩ ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው። ከእሥራት ከተፈቱ በኋላ Tipping Points የሚል የትዝታ መጽሐፍ አውጥተዋል። ለመድገም ያህል አቶ ተፈራን በንቅዘት፣ በቅብጠትና በውስልትና መጽሐፉ አይጠራቸውም። ታዲያ አቶ ተፈራ በጠቀስሁት መጽሐፋቸው ላይ መላልሰው የሚጠይቁት ጥያቄ አለ። “ለምን እኔ?” Why me? Why me? Why me? ለምን እኔ? ሌሎችም ሰዎች ሁሉ ይህን ጥያቄ ሊያቀርቡ ይችላሉ። የሞቱት ስድሳ ጓደኞቻቸው- በኋላም በሰማዕትነት የወደቁት እነ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ ቄስ ጉዲና ቱምሳ፣ ደጃች ካሣ ወልደማርያም- አበበ ከበደ- ሐረጐት ዓባይ…ከመቃብርም ሆነው ለምን እኔ? ሊሉ ይችላሉ። አባ ኮስትር በላይ ዘለቀ…አፈ ንጉሥ ታከለ ወልደ ሐዋርያት…አቶ ፈጠነ…ራስ አበበ…ሙሉጌታ ቡሊ…ለምን እኔ? የሚል ጥያቄ ሊኖራቸው ይችላል። ባልፈው መጣጥፌ ቅጥፈትና ወንጀል ወደ ቤተ መንግሥት…ንጽሕናና መስዋዕትነት ወደ ቀራንዮ እንደሚሄዱ – አድራሳቸው ያ መሆኑን ለማመልከት ሞክሬያለሁ። በእምነታቸው የሚያመነዝሩ፣ አደራ የተሰጣቸውን የሚዘርፉ ቤተ መንግሥቱ ይመቻቸዋል። የየዘመኑን የአገራቸውን ጥሪ ለመስማት የሚችሉት ደግሞ የጽጌረዳ ፍራሽና የወርቅ አልጋ አይደለም የሚጠብቃቸው። “እንዲህ ዓይነቱን” የጊዜ ድምፅ- የእናት አገር ጥሪ የሚሰሙ ሰዎች በምንም ዓይነት ለምን እኔ” አይሉም። ልጆቼ እነ እስክንድር፣ በቀለ፣ አንዱዓለም…ርእዮት ይህን ጥያቄ አያነሡም። መስዋዕት መሆንኮ የታሪክ ዕጣና ዕድል ነው። ኩራት!
  አዎን ምኒልክም፣ ጐበናም፣ በላይም፣ አበበም፣ አብዲሳም..በሌሉበትና የኢትዮጵያን ጥሪና የጊዜ ድምፅ ( The Voice of Time) ለመስማት የቻሉ ጥቂቶች በሚመስሉባት አገር በከፍተኛ ደረጃ ሊሰበክ የሚገባው የመስዋዕትነት ወንጌል (The Gospel of Sacrifice) ነው። The Gospel of Sacrifice የአሜሪካ ጥቁሮች በ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ላይ ያነሡት የእኩልነት መታገያ ዓርማቸው ነበር። የሥልጣኔ ምሥጢር፣ የባላአገርነት ትርጉም፣ የሰለጠነ ሕዝብ የሕልውና ዋስትና ከዚህ ሰፊ ውቅያኖስ (ከመስዋዕትነት ወንጌል) ውስጥ ለመቅዳት እንችላለን።
 ስለ ልቅሶና አልቃሽ ግለሰቦች ነበር በሰፊው ለማስረዳት ወዲያ ወዲህ ስረግጥ የቆየሁት። ለአገራችን ማልቀሱ፣ ስለተረጋገጠው ሰብእናችን መተከዙ፣ ስለተሸነሸነው አንድነታችን መቆዘሙ አንድ ነገር ነው። አልቃሽና አልቃሽ ሕዝብ ሆነንና ወሬ ስንሰልቅ መኖርም አይገባንም። ወንዶችም- አዎን ሴቶችም ሆኖ መነሳቱ ነው መድኅኒቱ። ጠላቶቻችን እስከታወቁ ድረስ በገቡበት ዱር ለመግባት፣ በቆሙበት ሥፍራ ደርሶ መገኘት የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ከቶውንም ከምር አምኜበታለሁ። የእነሱ እጅ የሚተኩስ፣ የእኛ ፈንታ መገደል ብቻ ከሆነ ፍልስፍና ራስዋ ማደሪያ አጣች ለማለት ይቻላል። ስለ መስዋዕትነት ነው የማወሳው። ለመሆኑ መስዋዕትነት መገደል ማለት ነው ያለው ፈላስማ ማነው? ከዚያ የተሻለ ማሰብና ማቀድ እንዴት አንችልም? ለመሆኑስ ሰላማዊ ትግል ማለት “ያውልህ ግደለኝ! ዋጋውን በመንግሥተ ሰማያት አገኘዋለሁ” ማለት ነውን? የዚህ ዓይነቱ ሰው ሥፍራ ገዳም ነው። እኔ የማነሳው ስለ ምድራዊት ኢትዮጵያ ነው።
 መለስ ዜናዊ ከመሞቱ አንድ ዓመት በፊት “መለስ ዜናዊ ከምርጫ ሳጥን ይልቅ የሬሳ ሳጥን መርጦአል” በሚል ርእስ የጻፍሁትን መጣጥፍ አስታውሳለሁ። ሰፊና የተንዛዛው መጣጥፌ እንደ መለስ ያሉትን ግፈኞች አምባገነኖች መታገል እንደ ጽድቅ ሊታይ እንደሚችል ገልጫለሁ። ለዚህም ስለ Just war, Holy war ወዘተ የሰበኩትን ታላላቅ የክርስትና መሪዎች አሳቦች አንስቻለሁ። ዛሬ ራሴን ለመጥቀስ አልወድድም። ብቻ ልደግም የምፈልገው ግፈኞችን ማስወገድ፣ አለዚያም መቃወምና መቋቋም እግዜርን መታዘዝ መሆኑን ላሰምርበት እሻለሁ።
 ግፍና ጭቆና በደም ሥሮቹ ውስጥ “ቁጡ ቀይ ደም ያለውን” ግለሰብ ያሳብዳል። ወላጆቻችሁ በአብዛኛው ይህ ቀይ ደም በሥራሥሮቻቸው ውስጥ ነበራቸው። ይህ ግፍና ጭቆና ደግሞ ዛሬ ባለበት ሁኔታ፣ ሥፍራና ጊዜ (ታይም ኤንድ ስፔስ) ሊሽር- ሊድን -አይችልም። ጠንካራ ዜጐች ካሉን መድኅኒቱ ቅርብና ቀላል ነው። ጠላቶቻችን በእኛ ላይ የደገኑትን መሣሪያ ጭምር አስጥለን ወደነሱ ማዞር በዓለማዊውም ሕግ ወንጀል፣ በመንፈሳዊውም ዓለም ኅጢያት አይደለም።  ከማንም ጋር ለመከራከር እችላለሁ። ቶማስ አኳይነስን፣ አቡነ አትናትዮስን፣ የንጽሕና ማስረጃ የሆነውን ፍራንሲስ ኦፍ አሲሲን፣ የላዮላ ዩኒቨርሲቲ ሥፍር ቁጥር የሌላቸውን መነኰሳትን ምስክርነት አቀርባለሁ። ሒትለርን ለመግደል ስንት ፓስተሮች የየራሳቸው እንቅስቃሴ አድርገዋል? በአመጽ ላይ አመጽ በተካሄደበት ወቅት እንደ ፓስተር ዎልፍጋንግ ያሉ ሰባክያን ያካሄዱአቸውን ትግሎች ያጤኑአል። የእኛንም አቡነ ጴጥሮስና አቡነ ሚካኤልን እንደገና እጠቅሳለሁ። ስለዚህ የጊዜን ድምጽና የአገርን ጥሪ የማይሰማና የማይቀበል ትውልድ ርጉም ስለሚባል ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚጠበቅበት የትግል አስተዋጽዖ አለ። ወጣቱ ተባባሪ ፓይለት ምን የመሰለ አኤሮፕላን ይዞ ወደ ስዊትዘርላንድ በመሄዱ አንድ የትግል ግንባር ወይም አስተዋጽዎ አበርክቶአል። አንድ የወያኔ ሹመኛ ቀጣሪዎቹን በአደባባይ ቢያጋልጣቸው (በተወከለበት ሁነኛ መድረክ) አንድ ሌላ ጠንካራ ተጋድሎ ነው። ዋነኞቹ ወሳኝ ገዥዎች በአንድ አካባቢ ሲያድሙ (መቸም ለእድገትና ልማት ተሰበሰቡ አይባልም) በቁጥጥር ሥር ማዋል…ወዘተ ከፍ ያለ የትግል እድገት ይመስለኛል። ማዕከላዊ መንግሥቱን መገላገል በእርግጥ መስዋዕትነትን ይጠይቃል። ለሚፈለገው ውጤትም አስተማማኝ ርምጃ ይመስለኛል።
 እንደልባቸው በመናገር የታወቁ አንድ የድሮ መንግሥት ማስታወቂያ ሚኒስትር በስልክ ከመከላከያ አቻቸው ጋር ሲነጋገሩ በሠራዊቱም በወጣቱም ተስፋ የቆረጡበትን ሁኔታ መፈንጠቃቸውን አስታወሳለሁ። “ስማ ጄኔራል! የአንተም ወታደሮች የደሀ ጐተራ የሚገለብጡ እንጂ መንግሥት መገልበጥ የሚባል ቋንቋ ሰምተው የማያውቁ ናቸው። እነዚህ ምላሰኛ ተማሪዎች ደግሞ የሚያደርጉትን የማያውቁ፣ ያልተረዱትን የሚያነግሱ ናቸው። ትውልዱን በአጭሩ በፋንድያ ላይ የበቀለ እንጉዳይ ልለው እፈልጋለሁ” ይላሉ። አነጋገሩ ጭካኔ የበዛበት ቢመስልም መሠረቱ ያልጠበቀ፣ በብስለት ያልታነፀና፣ ለመስዋዕትነት ያልተዘጋጀ መሆኑን እያጉረመረምንም ቢሆን እንቀበለዋለን። እግረመንገዳችንን ለዚህ አደጋ ተጠያቂ የምንሆንበትም መጠን ማመን አለብን።
 አዎን ሁላችሁም ቆም ብላችሁ እስኪ የዛሬዪቱን ኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የአመራር፣ የሚሊተሪ ሥዕል እናሰላስል። የአገር አንድነት ፈረሰ ብለን ልቅሶአችንን ሳንጨርስ በየክልሉ ያሉ “በፋንድያ ላይ የበቀሉ እንጉዳዮች” ከቶውንም ገና ምኑ ታየና በማለት በመጨረሻ ትንፋሻቸውን እያጮኹ ናቸው። ከዚህ የባሰ ምን ሊያደርጉን ፈልገዋል? በሥልጣን ላይ ያለው አፍራሽ ኅይል ራሱ የትውልድ ትውልድ ብሔራዊ ወንጀል እየፈጸመ- ሕዝባችንን እያረደ፣ የአገሪቱን ሀብቶች እየዘረፈ፣ የሞራል ድቀት እያስፋፋ- ባሕልና እምነትን እያጎደፈ-ይገኛል።
 ቀደም ሲል የጠቀስሁት ቁጡ ቀይ ደም በውስጣችን መኖሩን መጠራጠር አይገባንም? በዚህ ዕድሜዬ ማሰብ የማይገባኝ (ምናልባት) አሳብ ድቅን ይልብኛል። በአንድ በኩል ኢሕአፓ ትናፍቀኝ ጀምራለች። ቆራጥነት ማለት በራስም በጠላትም ሕይወት ላይ ውሳኔ ለመውሰድ መወሰን ነው። ኢሕአፓ ናፈቀችኝ። የአባቶቻችን አዋራጆች- ልጆቻችንን በጠራራ ፀሐይ የሚረሽኑ፣ አገራችንን በግላጭ የሚሸጡ ወንበዴዎች በየአደባባዩ ሲጐማለሉ ሁላችንም ሊያቃጥለን አይገባም? ኢሕአፓ እንደ ሞተ ዘመድ ናፈቀችኝ። ኢሕአፓ ብትኖር ይኸ ሁሉ ሽፍታ መሪ መንፈሱ አርፎ ከመሸታ ቤት መሸታ ቤት እየዞረ- ሽጉጡን መሬት ለመሬት እየጐተተ- የፈገውን እያሰረና እያስገደለ፣ በእብሪት ይንቀባረርብን ነበርን? ኢሕአፓን እንዳላማኋት ዛሬ ሙት መንፈስዋን መቀደስ ይዣለሁ።
  ቁጥራችንን- ንዴታችንን- በደላችንና የተዋለብንን ሁሉ ሳስብ ለመሆኑ የአዲስ አበባ ሲሦ ሕዝብ አንድ ማለዳ ላይ በእነዚህ ሰዎች ላይ ቢንቀሳቀስ ለወሬ ነጋሪ የሚተርፍ ይኖር ይሆን? ብዬም ራሴን እጠይቃለሁ። በውስጤ ውስጥ ያለው የሕሊና ድምፅ ደግሞ የሚነግረኝ ሌላ ሐቅ አለ። ወደ ሚዲየቫል እንግሊዝ ልውሰዳችሁ። ከሀብታም ቀምቶ ደሀ የሚቀልበው Robin Hood ከአሥር የማይበልጡ Mery men ) ይዞ አይደለም ወይ ለንደንን በቁጥጥሩ ሥር ያደረገው? እንኪያስ አሥር የቄራ ቦምባርዶች አዲስ አበባን በቁጥጥራቸው ውስጥ ሊያደርጉ አይችሉም? ይኸ ሁሉ ባለሙሉ ገላ ወጣት- ይኸ ሁሉ አንጀቱ የተኮማተረ ጐረምሳ በቡድን ተከፋፍሎ አንዱ ዘርፍ አጥቂ፣ ሌላው ዘርፍ ደጀን ሆኖ አዲስ አበባንና – ባለሥልጣኖችዋን በቁጥጥር ሥር ሊያደርግ- የተወሰኑ ግለሰቦችን መፋረድ አይችልምን? ሞት አይኖርም አይባልም። ጦርነት ታውጆ የለምን? ይህ መንግሥት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጦርነት ማወጁን አልሰማንም የሚል ማነው? ዋናው ነገር ከውሳኔ ላይ ነው። ዋናው ነገር እንዲህ ላለው ጦርነት መዘጋጀትና ለመስዋዕትነት የተቆጣ ወኔ፣ የገነፈለ ቀይ ደም መኖር ነው። ቀደም ሲል ያነሣሁትን የመስዋዕትነት ወንጌልን መቀበል ነው። The Gospel of Sacrifice
  የጀርመንን ፍልስፍናና ሥነ ጽሕፈት ያነበቡ (በጀርመንኛው) ሰዎች Goe the የገቴ ስም ሲጠራ ልዩ ስሜት ይፈጥርባቸዋል። እኔ ገቴን ልጠቅሰው የምወድደው (ፋውስት ክፍል አንድ ..Faust Part One ላይ በተጠቀሰው ፍልስፍናው ነው። የገቴ ፍልስፍና በአጭሩ እንዲህ ይጠቀሳል። “ራስህን ካድ- ራስህን መካድ ይገባሃል- Deny yourself, you must deny yourself) አዎን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የደመደመው ነው- የሚከተለኝ ቢኖር ራሱን ይካድ- የሚከተለኝ ቢኖር ግማደ መስቀሉን ይሸከም! ኢትዮጵያን ያለ ዛሬ ጥሪው ይኸ ነው። የጊዜ ድምፅ!
 ጠላትን ሲሆን ከያዘው መሣሪያ በበለጠ ትጥቅ- አለዚያም በተስተካከለ መሣሪያ- በተሻለ ወኔ ለመግጠም ማመንታት የአገርን ዕድሜና ዕድል ማበላሸት – ማሰናከል ነው። ከፊት ለፊታችሁ ያማረ ሸለቆ የለም። ከፊት ለፊታችሁ ማለፊያ ድልድይ የለም። ከዚያ ማዶ ከሚታየው ተራራ ላይ ወጥተህ ከአምላክህና ከአገርህ ጋር ቃልኪዳን ትገባለህ። ከተራራው ላይ ሆነህ ከአምላክህ ጋር በቅርበት ትነጋገራለህ። ከኢትዮጵያ ጋር በመንፈስ ትነጋገራለህ። ለመሞት ብቻ ሳይሆን ለመግደልም ቃል ትገባለህ። ከአሥርቱ ትእዛዛት ስድስተኛውን መጣስህ ሊሰማህ አይገባም። ከሕጉ ባለቤት ጋር ተነጋግረሃል።
 ወደፊት የመስዋዕትነቱን ወንጌል ቃል አስፋፍተን እናቀርባለን።
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>