Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የአቶ ሌንጮ ለታ ፓርቲ ከኦዴፓ ጋር ተዋሃደ

$
0
0
በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) እና የቀድሞው ኦህዴድ የአሁኑ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኦዴፓ) ጋር ተዋሃዱ። የሁለቱ ፓርቲዎች አመራሮች ዛሬ ከቀትር በኋላ በኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ቢሮ የውህደት ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡ ተዋህደው በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረሙት ከኦዴፓ አቶ ለማ መገርሳ ናቸው፡፡ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት እና የኦዴፓ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ለማ መገርሳ፤ ”በአንድ አዕምሮ እና […]

የአብን አመራር ክርስቲያን ታደለ ዶ/ር አብይን ፊት ለፊት የጠየቃቸው ወሳኝ ጥያቄና እና የሰጡት ምላሽ

$
0
0
የአብን አመራር ክርስቲያን ታደለ ዶ/ር አብይን ፊት ለፊት የጠየቃቸው ወሳኝ ጥያቄና እና የሰጡት ምላሽ

በታጣቂዎች ለተገደሉ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት ሽኝት ተደረገላቸው |ኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ በኦሮሚያ ጸጥታ ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባ ተቀመጠ

$
0
0
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልልና በኦሮሚያ አዋሳኝ ሊሙ ወረዳ አርቁምቤ በሚባል አካባቢ በታጣቂዎች የተገደሉ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት በአምቦ ከተማ ሽኝት ተደረገላቸው። ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልልና በኦሮሚያ አዋሳኝ ወረዳዋች ቢያንስ 35 የኦሮሚያ ፖሊስና የኦሮሚያ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ አባላት በታጣቂዎች መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን ለጥቃቱ ሃላፊነቱን የወሰደ የለም:: ከዚህ ቀደም በቤኒሻንጉል ሕዝብ ነጻነት ንቅናቄ ወታደሮች ህጻናትን ጭምር በክልሉ […]

በዜጎች ላይ የተፈጸሙ በደሎችን የሚያክም የዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

$
0
0
ለበርካታ ዓመታት በተለያዩ ማኅበረሰባዊና ፖለቲካዊ ግጭቶች ምክንያት በሕዝቦች መካከል የተደራረቡ የቁርሾ ስሜቶችን ለማከም፣ እውነትና ፍትሕ ላይ መሠረት ያደረገ ዕርቅ እንዲወርድ የሚሠራ የዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ሐሙስ ኅዳር 20 ቀን 2011 ዓ.ም. ለፓርላማ ቀረበ። ኮሚሽኑን ለማቋቋም ያስፈለገው በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ሌሎች በደሎች ተጠቂ የሆኑ ወይም ተጠቂ ነን ብለው የሚያምኑ ዜጎች፣ በደላቸውን […]

ከማንነትና ከክልል አስተዳደር ጋር የሚነሱ ጥያቄዎችና በኃይል ለመፍታት መሞከር የተጀመረውን የለውጥ ሒደት ብቻ ሳይሆን፣ አገሪቱንም ጭምር አደጋ ላይ እንደሚጥል ተገለጸ

$
0
0
ከማንነትና ከክልል አስተዳደር ጋር የሚነሱ ጥያቄዎችና በኃይል ለመፍታት መሞከር የተጀመረውን የለውጥ ሒደት ብቻ ሳይሆን፣ አገሪቱንም ጭምር አደጋ ላይ እንደሚጥል የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ጻድቃን ገብረትንሳኤ ገለጹ:: ጀነራሉ ይህን ያሉት በ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) በሳምንቱ መጨረሻ ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት አጠቃላይ ፖለቲከዊ ሁኔታ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ምን መደረግ አለበት በሚል አጀንዳ […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
የኦነግን አቀባበል ተቀብሎ በቡራዩና አካባቢው ከተፈጠረው ብጥብጥ ጋር በተያያዘ የታሰሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ተኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት 10 ተጠርጣሪዎች ሲሆኑ መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ምርመራውን አጠናቆ ለአቃቤ ህግ እንዳስረከበ ተናግሯል፡፡ አቃቤ ህግም በችሎቱ ውስጥ የምርመራ መዝገቡን ከፖሊስ እንደተረከበ ገልፆ ክስ ለመመስረት ጊዜ እንዲሰጠው ችሎቱን ጠይቋል፡፡ ችሎቱም የአቃቤ […]

ይድረስ በተለይ ለተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች –ነፃነት ዘለቀ (አዲስ አበባ)

$
0
0
በሰው የሚጠሉት ወይም እንደሚጠሉት የሚናገሩትን ራስ ሲያደርጉት የማያስጠላ ከሆነ የተሳከረ ስብዕና (MPD) ባለቤት የመሆን ችግር አለ ማለት ነውና በቶሎ መታከም ያስፈልጋል፡፡ እኔ ለምሣሌ በወንድሜ ወይ በጓደኛየ ላይ የማየውንና የምቃወመውን መጥፎ የመሰለኝን ምግባር እኔ ራሴ ባደርግና እንደነውር ባልቆጥር ትክክል አይደለሁም፡፡ ጨለማና ብርሃን ኅብረት እንደሌላቸው ሁሉ በአንድ ሰውነት ውስጥ ሁለትና ከዚያ በላይ ተቃራኒ ሰውነቶች ሊኖሩ አይችልም፡፡ እንደዚያ […]

በምዕራብ ወለጋ የተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ተካሄዱ

$
0
0
በቤኒሻንጉል ጉምዝና በኦሮሚያ አዋሳኝ ወረዳዎች ሰሞኑን በታጣቂዎች የተገደሉ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላትን የሚዘክሩ ሰልፎች ጊንቢንና ነጆን ጨምሮ በተለያዩ የምዕራብ ወለጋ ከተሞች ተደረጉ። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በተሳተፉበት በዚህ ሰልፍ ላይ ፖሊሶች እና ወታደሮችም ከነዩኒፍርማቸው ተሳትፈውበታል:: በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች በተደጋጋሚ ከሚፈጸመው ጥቃት ውጭ ሰሞኑን ብቻ ከ34 የማያንሱ የኦሮሚያ ፖሊስ እና ጥብቃዎች መገደላቸው ይታወሳል:: ይህን ተከትሎም […]

በደቡብ ክልል 42 ሚሊዮን 284 ሺ 908 ብር ጎደለ

$
0
0
የደቡብ ክልል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ዋና ኦዲተር አቶ ተስፋዬ ታፈሰ በክልሉ 42 ሚሊዮን 284 ሺ 908 ብር ጉድለት መታየቱን ተናገሩ አቶ ተስፋዬ ከመንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲት ከተካሄደባቸው መሥሪያ ቤቶች የገንዘብ አስተዳደር ሥርዓት ሕጉን የተከተሉ መሆኑን ለማረጋገጥ በተደረገው ኦዲት ስምንት መሥሪያ ቤቶች የገንዘብ አያያዛቸው ላይ ጉድለት መኖሩ መታወቁን ጠቁመው […]

ኦምሃጅር ከተማ ቀን እየወጣላት ነው

$
0
0
በደቡባዊ ምእራብ ኤርትራ የምትገኘውና ሱዳንና ኢትዮጵያን የምትዋሰነው ኦምሃጅር ከተማ ቀን እየወጣላት ነው ተባለ፡፡ የኤርትራ መንግስታዊው የዜና አውታር እንደዘገበው ይህች ከተማ ወደ9500 ያህል ነዋሪዎች ያሏት ስትሆን በአሁኑ ወቅት በሰቲት ድልድይ አማካኝነት ኢትዮጵያና ኤርትራን እያገናኘች ነው፡፡ የከተማዋ ነዋሪዎችም በአዲሱ የኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት ከማንም በላይ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተስፋ መሰነቃቸው ተዘግቧል፡፡ ለአካባቢው ነዋሪዎች መስኖ እርሻ እንዲያገለግል ታስቦ ከ8 […]

በጎንደር መካነ ብርሃን ከተማ በአይነቱ ለየት ያለ ሰልፍ ተካሄደ

$
0
0
ይህ የምትመለከቱት ሰው አደባባይ የወጣው ለተቃውሞ አይደለም፡፡ ዛሬ በመካነ ብርሃን ከተማ ለአንድ ታዳጊ አቀባበል ለማድረግ ነው፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይልን ያለገመድ ማስተላለፍ ለቻለው ታዳጊ ሃምዛ ሃሚድ የተደረገለት አቀባበል ነበር፡፡ የፈጠራ ባለቤቱ ሃምዛ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተሰጠውን ዕውቅናና ሽልማት ይዞ ወደ ትውልድ አካባቢው ሰሜን ጎንደር ዞን ጃናሞራ ወረዳ ዛሬ ገብቷል፡፡ ሃምዛ በተማረበት የመካነ ብርሃን 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
የታገቱትን ህንዳዊያን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን የህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለፀ፡፡  ኢንዲያን ታይምስ ጋዜጣ ዛሬ እንደዘገበው የታገቱት ሰባት ህንዳዊያን ዛሬ ስድስት ቀን ሆኗቸዋል፡፡ ኦሮሚያን ከአማራ ክልል የሚያገናኘውን መንገድ ይሰሩ የነበሩት እነዚህ ህንዳዊያን የታገቱት ለአካባቢው የቀን ሰራተኞች ለወራት ደመወዝ ባለመክቸላቸውና ብዙ እዳ ስላለባቸው መሆኑን ከትላንት በስቲያ መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ህንዱ ጋዜጣ በዛሬው ዘገባው ደግሞ ስለጉዳዩ የኦሮሚያ ፖሊስ […]

ከደብረ ጺዮን ወደ አክሱም ጺዮን |ክንፉ አሰፋ

$
0
0
መቀሌ ለደበቀቻቸው “ጀግኖች” ባለ ውለታ ናቸው። ከዚህም በላይ ይገባቸዋል የሚሉ አሉ። እምነት ለነሱ ኢምንት ነው። ሃይማኖት ደግሞ ፖለቲካ። ልብ ያለው ፈጣሪን ያስባል። ይሉኝታ ያለው አምላኩን ይፈራል። ህሊና ያለው ደግሞ የእግዚአብሄርን ስም ይጠራል። ይህ ሁሉ የሌለው ግን በባዶነቱ ዝም ብሎ ይቁነጠነጣል። ይህ አዲስ አይደለም። ራስ እንጂ ጭንቅላት ከሌለው ሰው ተቃራኒው ቢፈጸን ነበር የሚደንቀው። አንዱ ሰው ጓደኛውን […]

በመቱ ከተማ ሰልፍ ተካሄደ |በቤኒሻንጉል 66 ሰዎች በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ

$
0
0
በቤኒሻንጉል እና ኦሮሚያ ክልል ድንበር ከተሞች አካባቢ በርካታ የኦሮሞ ተወላጆች እና የክልሉ ፖሊሶች መገደላቸውን ተከትሎ በም ዕራብ ኦሮሚያ የሚደረገው ሰልፍ ቀጥሏል:: በዛሬው ዕለት በመቱ ከተማን ጨምሮ በሌሎችም የም ዕራብ ወለጋ ከተሞች መንግስት የዜጎችን ደህንነት እንዲያስጠብቅ የሚጠይቁ ሰልፎች ሲካሄዱ ውለዋል:: ኦዴፓ በዜጎች ላይ ደም ማፍሰስ የፈጸሙትን እና ሌቦችን የገቡበት ገብቼ እይዛቸዋለሁ ሲል መግለጫ ማውጣቱን ዘ-ሐበሻ ዘግቦ […]

እነገዱ አንዳርጋቸው አሜሪካ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል – Video

$
0
0
በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራው የአማራ ክልል ልዑክ ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ ሲገባ አቀባበል ተደረገለት:: ለአማራ ህልውና ለኢትዮጵያ ል ዕልና በአንድነት እንሥራ በሚል ይህ በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራው ልዑክ በዛሬው ዕለት በዚያው በዋሽንግተን ዲሲ ህዝባዊ ስሰብሰባ ያካሂዳል:: አቶ ገዱ ስለጉዞው ዓላማ ሲናገሩ “የጉዞው ዓላማ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአማራ ልማት ላይ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማስቻል ነው፡፡ ለውጡን ተከትሎ […]

መታገስ ፍርሃት አይደለም በሚል ሕዝብ ሰልፍ አደረገ

$
0
0
በመስቃንና ማረቆ ወረዳ በተከሰቱ የርስ በርስ ግጭቶች ቁጥራቸው ከ50 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ሞተዋል። ከ300 በላይ የሚሆኑ ቤቶች ተቃጥለዋል።በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለው በቡታጅራ ከተማ ውስጥ በግዜያዊ መጠለያ ዉስጥ ተጠልለው ይገኛሉ።ጉዳዩ በጣም አሳሳቢና የማእከላዊ መንግስት ጣልቃ ሊገባበት የሚገባ ቢሆንም በክልል የስልጣን መዋቅር ዉስጥ የተሰገሰጉ ለዉጥን የማይሹ ባለሰልጣናት የህዝቡ ድምጽ እንዲታፈን አድርገዋል።አፈናዉን በመቃወም ቁጥራቸው ከ120000ሺ የሚደርስ የከተማና የገጠር […]

እነ ዶ/ር አብይ አህመድ ሰሜን ሸዋ ዋሉ

$
0
0
እነ ዶ/ር አብይ አህመድ ሰሜን ሸዋ ዋሉ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ,ም/ጠ/ሚር ደመቀ መኮንን እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞረት እና ጅሩ ከተማ ዋሉ:: መሪዎቹ በዚህ ጉብኝት በሰሜን ሸዋ የሚገኘውን የኩሳኤ ቀበሌ በሔክታር እስከ 60 ኩንታል ስንዴ የሚመረትበትን ማሳ ጎብኝተዋል:: እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ መረጃ መሰረት የሀገራችን የግብርና ኮመርሻላይዜሽን […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በልማት ምክንያት ከቀያቸው ከተፈናቀሉ የአዲስ አበባ ዙሪያ አርሶ አደሮች ጋር ተወያዩ። ምክትል ከንቲባው መንግስት ከቀያቸው የተፈናቀሉ አደሮችን ለመርዳት መዘጋጀቱን ተናግረዋል። – በተለይ በስድተኛነት ቀርቦበት የነበረው ክስ አቶ ታምራት ብቻ የተከሰሰ ሲሆን፤ ከሕመማቸው ለመዳን የመጡ ሦስት ሴቶችን አስገድዶ ደፍሯል የሚል ክስ ነበር:: በቅርቡ የተፈታው ታምራት ዛሬ በሰላሌ ከተማ ለጀዋር […]

የእምብርትና እሾክ ሴራን (Hub-and-Spoke Conspiracy) እናክሽፍ! (ሐይሉ አባይ)

$
0
0
የጠ/ሚ አብይ መንግስት የብሔራዊ የፀጥታ ምክር ቤት የሠጠውን መግለጫ እደግፋለሁ:: ከጎናቸውም እቆማለሁ:: ‘አመላችንን በጉያ፤ ስንቃችንን በአህያ’ የአድዋ ጦርነት የኢትዮጵያዊው ሕብረትና የድል ሚስጥር መሪ ቃል (Motto) ነበር:: ዛሬም ይሁን:: ሕገ መንግስቱ መሻሻል አለበት:: እኔ የሕገ መንግስቱ መሻሻል አሁን አያሣስበኝም:: “የጎሣ ፌደራሊዝምና ርዕዮቱ አብዮታዊ ዴሞክራሲ” በሲቪክ ብሔረትኛነትና በሊብራል ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት መተካት አለበት:: እኔ “የጎሣ ፌደራሊዝምና ርዕዮቱ አብዮታዊ […]

የታምራት ገለታ አዲስ ጨዋታ

$
0
0
ዶ/ር አብይ አህመድ ሰሞኑን “ጥፍር ሲነቅል ሕዝብን ያላማከረ፤ ጥፍር መንቀል ሕጋዊ አይደለም ስንለው ብሔሩ ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራል” በማለት ወንጀለኞች ከተጠያቂነት ለማምለጥ ብሔራቸውን መደበቂያ እንደሚያደርጉ በአጭር ቃላት ገልጸውልን ነበር:: ይህ አባበል መቀሌ ላይ ለተደበቁት የሕወሓት ወንጀለኞች ብቻ ሳይሆን ዛሬ ለጠንቋዩ ታምራት ገለታም ሰርቷል:: ከሁለት ወር በፊት በምህረት የተፈታው ጠንቋዩ ታምራት ገለታ (እያንጓለለ) ዛሬ ሰላሌ ከተማ ውስጥ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>