Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ፍራንክፈርትና በርሊን አዲስ አበባ ባህርዳር አይደለም !!!

$
0
0
የባለ አደራው ስብሰባ በህብረት ይሳካል !!!!  የባለአደራው ምክር ቤት ስብሰባ በፍራንክፈርትና በርሊን መጪው ቅዳሜና እሁድ ይካሄዳል። አዲስ አበባ ባለ አደራው ከህዝብ ጋር እንዳይገናኝ ሲሰበሰብም ለመበተን በ ገዢው ኦዴፓ አፈና እየተፈፀመበት ሲሆን አመራር አባል ኤልያስ ገብሩ በባህር ዳር ናአዲስ አበባ ግድያ ተከሶ ወህኒ ተጥልዋል። ስንታየሁ ቸኮል ከባህር ዳር አዲስ አበባ የ 21 ሰዐት ጉዞ ከእስክንድር ነጋ […]

“ሕገ መንግስቱ ሲጸድቅ እኔ ሐሳብ ሰጥቼበታለሁ፣ ህዝብ ተወያይቶበታል”አቶ በቀለ ገርባ

$
0
0
በርካታ የኦሮሞ ብሄረተኛ ፖለቲከኞችና ልሂቃን ጉዟቸውን ወደ መቀሌ በማድረግ፣ በዚያም፣ በተለይም አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሕግ መንግስትና ፌዴራል አወቃቀር ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው። ከአንድ ሳምንት በፊት ዶር ሕዝቄል ጋቢሳ ፣ እርሳቸው “ሕብረ ብሄራዊ ፌዴራሊዝም” የሚሉት ግን በብዙዎች ዘንድ የጎሳ ፌዴራሊዝም ተብሎእ የሚጠራው የአሁኑ የፌዴራል አወቃቀር እንዲቀየር የሚፈለጉ አካላትን፣  በኢትዮጵያ አሃዳዊ ስርዓት እንዲመጣ የሚፈልጉ ናቸው በማለት፣ […]

‎ዶ/ር አቢይ የአክራሪ ኦነጋዊያን አይዲኦሎጂ የትሮዣን ፈረስ ወይስ ኢትዮጵያዊነት የዶ/ር አቢይ የትሮዣን ፈረስ??-ወንድወሰን ተክሉ

$
0
0
ወንድወሰን ተክሉ **አንድ -መነሻየዶ/ር አቢይ መራሹ የኦዴፓ መንግስት በትረስልጣኑን የጨበጠው በሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ትግልና ብሎም መጨረሻ ላይ የማሸነፊያዋን ጎል (Penalty )ባስቆጠረው በአዴፓ ቢሆንም ይህ የአዴፓና ብሎም መላው የአማራ ህዝብ ለለውጥ ያደረገው ታላቅ ተጋድሎ፣መስዋእትነትና ወዳጃዊ ወገንተኝነት በዶ/ር አቢይ የሚመራውን ኦዴፓ መሰሪ የሆነ የክህደት እርምጃ እንዲወስድበት የልብ ልብ ከመስጠትና አማራ ተኮር ሴራ እንዲያራምድ ከማድረግ ውጭ ለነገደ አማራ […]

መለያየት ቀላል ነው፣ አንድ ማድረግ ከባድ ነው #ግርማካሳ

$
0
0
ጃዋር የኦሮሞ ብሄረተኛ አክቲቪስት ነው። ኢትዮጵያዊ ነኝ ስለማለቱ የማውቀው ነገር የለም። ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ያለን ሰው በግድ ኢትዮጵያዊ ነህ ልለው አልችልም። ኢትዮጵያዊ አይደለሁም የማለት መብቱ ነውና። ኦሮሞ ነኝ ስለሚል ግን ኦሮሞ ነው። እኔ ግን የኦሮሞ አያቶች ቢኖሩኝም ራሴን ኦሮሞ ነኝ ብዬ አልጠራም። በጎጃሜና መንዜ አያቶቼ ምክንያት አማራ ነኝ እንደማልለው። እንኳን “ኦሮሞ፣ አማራ” ልል ቀርቶ ሌላውም ኦሮሞ፣ […]

የባላደራው አባላት ”መንግስታዊ በቀል እየተፈጸመብን ነው ! ”  አሉ

$
0
0
ይድነቃቸው ከበደ፣ የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ፣ በወህኒ የባላደራው አመራር አባላትን አለማግኘት ሞክሮ የሚከተለውን ዘገባ አስፍሯል። ————— ዛሬ ጠዋት ወንድሞቼን የእውነት አምላክ ያስፈታችሁ ለማለት ፤ በግፍ ወደ-ታጎሩበት እስር ቤት ለመጠየቅ ሄጄ ነበር ። የእስር ቤቱን የአሰራር ደንብ ተከትዬ ለ1 ሰዓት ያህል ወረፋዬን ጠብቄ ፤ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ፣ አቶ መርከቡ ሀይሌ እና አቶ ስንታየሁ […]

እሩብ ባንዳ የለም! –በላይነህ አባተ

$
0
0
ባንዳ እያበላለጥክ የምትጎሻሸም፣ ተዝንጀሮ ቆንጆ ልትመርጥ የምታልም፣ ስትቃዥ አትደር እሩብ ባንዳ የለም፡፡   ለገሰ ፈብርኮት አብዮት የገዛው፣ ከከርስ በስተቀር አሞት ልብ የሌለው፣ ለሰላሳ ዓመታት አማራን ያስብለው፣ የብአዴን መሪ ጠቅላላ ሎሌ ነው፡፡   ስታስጌጠው ብትውል ጀግና ልታደርገው፣ ሊፕስቲክ ከንፈሩን ሶስት ዙር ብትቀባው፣ ብአዴን አመራር ሁሉም አሳማ ነው፡፡   ትናንትናም ወይ ጉድ ዛሬም እየየ ነው፣ አሽከር እየመራህ […]

በሀሰት የመፈንቅለ መንግሥት እና እነ ዶ/ር አምባቸው ግድያ የተከሰሰው ጋዜጠኛ ጉዳይ በዝግ ችሎት ታየ -ፖሊስ ቃታ ይዞ ቤተሰቦቹን እና ጓደኞቹን አስፈራራ

$
0
0
ህብር ራዲኦ ፖሊስ በፈጠራ የሀሰት ክስ የሰኔ 15ቱን የመፈንቅለ መንግስት አካሂዱዋል፣በእነ ዶ/ር አምባቸው እና የጄኔራሎቹ ግድያ አለበት ሲል ክስ የመሰረተበት የአዲስ አበባ ባለ አደራ ም/ቤት ዋና ጸሐፊ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ የአርብ የጁላይ 26/2019 የፍርድ ቤት ውሎን ለመከታተል የሄዱ ሁሉ ታግደው ጉዳዩ በዝግ ችሎት ታየ። ፖሊስ ጉዳዩን ለመከታተል የሄዱ ቤተሰቦቹ እና ጉዋደኖቹን ጨምሮ ፎቶ ግራፍ አንስታችሁዋል […]

አገራችንን ከጥፋት፤ ሕዝባችንን ከመከራ ለመሰወር፤ በጌታ ፍቃድ –ከዶ/ር በቀለ ገሠሠ

$
0
0
መንደርደሪያ፤ ሁላችንም የወጣነዉ ከየእናቶቻችን ማህፀን ዉስጥ ነዉ፤ ለ9 ወራት በማህፀን ተሸከሙን፤ ወለዱን፤ አጠቡን፤ አበሉን፤ ሳሙን፤ አቅፈዉ አሳደጉን። በዚህም ምክንያት እናቶቻችንን ከማንም አስበልጠን እንወዳቸዋለን። እንደዚሁም አገር እናት ናት። ዕትብታችን የተቀበረዉ በርስዋ ዉስጥ ነዉ። ከመሬትዋ እህሎች በቀሉልን፤ በልተን አደግን። ከከርሰ ምድርዋ የሚወጣዉን ዉሃ ጠጥተን አደግን። ወተትና ምግብ የሚሰጡን ከብቶቻችን የሚግጡትና የሚጠጡት ዉሃ የሚገኘዉ ከዚያችዉ ምድር ነዉ። የምንተነፍሰዉ […]

“ሰኔ 15 ድርጊቱን ያስቆምኩት እኔ ነኝ” – ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ

$
0
0
ሰኔ 15 በአማራ ክልል ተሞከረ ከተባለው ‘መፈንቅለ መንግስት’ ጋር በተያያዘ የጸጥታ ኃላፊዎችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩና በቁጥጥር ሥር የዋሉ ግለሰቦች ጉዳይ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ታይቷል። ፖሊስ በአጠቃላይ የ90 ሰዎችን ቃል መስማቱን ገልጾ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል። ለዚህ ደግሞ ተጨማሪ የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ማስፈለጉን በምክንያትነት አስቀምጧል። በእለቱ ጥቃት የደረሰባቸውና ጥቃቱን ለመመከት […]

የትነበርሽ ንጉሴ ዝምታውን ሰበረችው አክራሪ ኦሮሞ ሀገር ከማፍረስ ሰከን ቢሉ ይሻላል:: አለማየት ወንጀል አይደለም አለማስተዋል ግን ስህተት ነው

$
0
0
የትነበርሽ ንጉሴ ዝምታውን ሰበረችው አክራሪ ኦሮሞ ሀገር ከማፍረስ ሰከን ቢሉ ይሻላል:: አለማየት ወንጀል አይደለም አለማስተዋል ግን ስህተት ነው

 የአፋልጉኝ ጥሪ ለምንና ለማን ? –ጠገናው ጎሹ

$
0
0
July 28, 2019 ጠገናው ጎሹ ሊያስከትል የሚችለው አሉታዊ ተፅዕኖ እንደ ተጠበቀ ሆኖ ለኢንፎርሜሽን ተክኖሎጅ መዘመን ምሥጋና ይግባውና  በዓለም ዙሪያ የሚሆነውን ደግ  ወይም ክፉ ነገር  ከመደበኛው (ከተለመደው) የኮምፒዩተር ላይ አጠቃቀም  አልፎ  በየኪሶቻችን በምንይዛቸው  ስልኮች   እጅግ ከሚገርም ፍጥነት ጋር  ለማወቅ አስችሎናል ። እንደማነኛውም የዓለምን ወቅታዊ ሁኔታ ለማወቅ እንደሚፈልግ ግለሰብ እና በተለይ ግን ተወልዶ ያደገባትና በተፈጥሮ ሥጦታውም ሆነ […]

ሰኔ 15 በአማራ ክልል በተፈጠረው የከፍተኛ ባለስልጣናት ግድያና ተያያዥ ጉዳዮች የተጠረጠሩ 57 ተከሳሾች ከእስር ተፈቱ

$
0
0
ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በአማራ ክልል በተፈጠረው የከፍተኛ ባለስልጣናት ግድያና ተያያዥ የፀጥታ መደፍረስ ችግሮች የተጠረጠሩ 57 ተከሳሾች ከእስር ተፈተዋል፡፡ ከተጠረጣሪዎች መካከል በነ ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል 57ቱ ጉዳያቸው ተጣርቶ ሐምሌ 19 ቀን 2011 ዓ.ም ከእስር እንዲፈቱ ተደርጓል። እነ ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ፣ ኮሎኔል አለበል አማረና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን በተመለከተ ደግሞ […]

የወላይታ ህዝብ ታላቋን ኢትዮጵያ እንዲገነባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጥሪ አቀረቡ

$
0
0
የወላይታ ህዝብ ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ አንድነትና ሰላም የከፈለውን መስዋእትነት አሁንም ታላቋን ኢትዮጵያ ለመገንባት ለተጀመረው ጥረት ሊጠቀምበት እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አሳሰቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከወላይታ ሶዶ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪ በከተማው ስታዲየም ተገኝቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደማቅ አቀባበል አድርጓል። በዚሁ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር የወላይታ ህዝብ የአገሩን ዳር ድንበር […]

አህያየን የሰረቃት ሌባ –ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

$
0
0
ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ nigatuasteraye@gmail.com ሐምሌ 16 ቀን 2011 ዓ/ም አህያየን የሰረቃት ሌባ፤ ራሱ ደብቆ አፈላላጊየ ሲሆን አህያየን እንዴት ላገኛት እችላለሁ? ይህ አባባል ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብሎሽ እየተሻገሩ ዘመን ካቌረጡት ከብዙ ክስተቶች አንዱ እንደሆነ አበው ይናገራሉ። እኛ የኦርቶዶክስ ይማኖት መምህራን፤ “ለትውልደ ትውልድ ዘኢየኀልቅ ለዓለም ዓለም” ብሎ በሚደመድመው በየመንፈቀ ሌሊት በምናደርሰው ጸሎተ ኪዳናችን ትንሹንና ትልቁን ህዳጡንና መንጋውን […]

የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ 116 ሚሊዮን ብር ለልማት ፕሮጀክት ድጋፍ መመደቡን አስታወቀ

$
0
0
ቃለየሱስ በቀለ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በውጭ አገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዕርዳታ ያሰባሰበውን 116 ሚሊዮን ብር (አራት ሚሊዮን ዶላር)፣ በኢትዮጵያ ለሚካሄዱ ማኅበራዊና ኢኮኖሚዊ ችግሮች ለሚፈቱ ፕሮጀክቶች እንደመደበ አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ከአንድ ዓመት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ከጎበኙ በኋላ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለአገራቸው በቀን ከሚጠጡት ማኪያቶ ላይ ቀንሰው አንድ ዶላር እንዲያዋጡ […]

“ዋርካ ምድር ነካ ንገሩት ለዋንዛ ፍቅር ለባለጌ ይመሥለዋል ዋዛ ”መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

$
0
0
“ዋርካ ምድር ነካ ንገሩት ለዋንዛ ፍቅር ለባለጌ ይመሥለዋል ዋዛ። “ መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ    ዋርካ ትሑት ነወ። የፍቅር አሥተማሪ ነው። ዝቅ በማለት ለምድር ያለውን አክብሮት ገለፀ።እንዲህ በማለት ፥ ” ምድር ሆይ! ሥለሰጠሺኝ ማዕድን  ፣ ሥለአጠጣሺኝ ውሃ በእጅጉ አመሰግናለሁ።እኔ ያለአንቺ ፍቅር ና እንክብካቤ ምንም ነኝ። ሳትሰስቺ ሥለሰጠሺኝ ፍቅር ይኸው ዝቅ ብዬ አመሰግንሻለሁ።” አለ።ከልቡ።    ” ዋንዛ […]

የፍትህ ችግኝ ትከላ! –በላይነህ አባተ

$
0
0
ኢትዮጵያ እንድትሆን ኤደንን፣ መቀነት ታጥቃ ግዮንን፣ በላ ትከላ ፍትህን፣ ቅጥፈትን ነቅለህ እውነትን! ችግኝ ተተክሎ እንዲበቅል፣ ፀድቆ አገፍግፎ እንዲያብብ፣ ይልቅስ እውነት ተናገር፣ ንስሃ ግባ ለወንጌል፡፡ በሰእማት አጥንት ፍርስራሽ፣ ከንፁሐን ደም መስኖ ቅጅ፣ ችግኝ ተከላ ተማወጅ፣ ቅድሚያ እጅ ታጠብ ቀላማጅ፣ ተአቡነ ጴጥሮስ ተደፍተህ፣ ንስሃ ግባ ባማላጅ፡፡ ለሃያ ዓመታት እንደ ደን፣ ሕዝብ በባሩድ ጨፍጪፎ፣ አፈሩን በደም ለውሶ፣ በአጥንት […]

  ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ህብረት (ደምኢህህ) በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተላለፈ የአቋም መግለጫ

$
0
0
በአገራችን ኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው ብሎም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያለመረጋጋት እንዲኖር በደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ እና በፌዴራል መንግስት እየተካሄደ ያለውን የተዛባና ኢፍትሐዊ አሰራር ድርጅታችን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ህብረትን በእጅጉ ስላሳሰበው ከዚህ የሚከተለውን የአቋም መግለጫ ለማውጣት ተገዷል::   እንደሚታወቀው ሀገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት 27 ዓመታት በአፋኝና ጨቋኝ ሥርዓት ሥር ወድቃ ህዝቧ ለከፋ እንግልትና […]

“ብራንድ ይሠረቃል እንዴ? –በስንታየሁ ግርማ

$
0
0
እ.አ.አ. በ2ዐ14 በአለም ታዋቂ የሆኑ የቡና ቆይዎች እና ባለሙያዎች በሰጡት ምስክርነት ለኢትዮጵያ ቡና 25 ነጥብ በመስጠት ከአለም የ1ኛ ደረጃ ሲያጐናንፅፉት የኬንያ በእጥፍ አንሶ ከ12 ነጥቦች 2ኛ፣ ኮሎምቢያ በ1ዐ ነጥብ 3ኛ ደረጃ አጐናፅፋዋታል፡፡ እ.አ.አ. ለ2ዐ18 ለአሜሪካ የጥሩ ምግብ ሽልማት ከታጩት 27 ተወዳዳሪዎች መካከል 26 በኢትዮጵያ ቡና የሚወዳደሩ ነበሩ፡፡ (Daily coffee new, 2017). ለነገሩማ ገና ከጠዋቱ ነው አሜሪካኖች በኢትዮጵያ […]

ከአንጀት ከአለቀሱ ዕንባ አይገድም –በገ/ክርስቶስ ዓባይ  

$
0
0
ነሐሴ 24 ቀን 2011 ዓ/ም የችግኝ ተከላው ፖለቲካ እኔን ተስማምቶኛል። እኔን ብቻም ሳይሆን መላውን ኢትዮጵያዊ የተስማማው ይመስለኛል፤ ኧረ የዓለም ሕዝብም የሚደግፈው ጉዳይ ነው። ይሁን እንጂ የችግኝ ተከላው የወቅቱ እንቅስቃሴ ዋናውን የሕዝብ ጥያቄ ለማዘናጋትና ሥውር የፖለቲካ አመለካከትና የትኩረት አቅጣጫ ማስቀየሻ እንዳይሆን ከፍተኛ ስጋት አሳድሮብኛል። ሁኔታው እንደ እኔ ያሉ ሌሎች ኢትዮጵያውያንንም እንደሚያሳስብ ምንም ጥርጣሬ የለኝም። ምክንያቱም ችግኝ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>
<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596344.js" async> </script>