Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ፍርድ ቤቱ በኮሚቴዎቹ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላለፈ ኮሚቴዎቹ አስገራሚ ታሪካዊ ንግግር አደረጉ (ቢቢኤን ልዪ የችሎት ዘገባ)

$
0
0

ቢቢኤን ልዪ የችሎት ዘገባ

የኮሚቴዎቻችን አስገራሚ የችሎት ውሎ በችሎት የተናገሩት አስገራሚ ንግግር ዳኞቹን ያንቀጠቀጠ የኮሚቴዎቻችን ጀግንነት ድጋሜ የታየበት ዳኞች በሕሊናቸው ላይ የፈረዱበት መንግስት ታሪካዊ ስህተት የሰራበት እና ኮሚቴዎቻችን በችሎቱ ግልጽ መልክት ለሕዝቡ አስተላልፈዋል፡፡ ይህንን ልዩ ዘገባ ዳውንሎድ አድርገው ያዳምጡ ለሌሎችም ያስተላልፉ::


muslim dim

The post ፍርድ ቤቱ በኮሚቴዎቹ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላለፈ ኮሚቴዎቹ አስገራሚ ታሪካዊ ንግግር አደረጉ (ቢቢኤን ልዪ የችሎት ዘገባ) appeared first on Zehabesha Amharic.


ውስጤ! – (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ሥርጉተ ሥላሴ 06.07.2015 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

ጤናይስጥልኝ ወንድሜ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ እንዴት ሰነበትክልኝ። መልክትህ ከደረሰኝ ወራት – አስቆጥሯል። የጹሑፌ ታዳሚ በመሆንህ ልገልጸው የማልችለው ደስታ – ተስምቶኛል። ስልክህም ተስጥቶኝ ነበር። ነገር ግን እኔ የስልክ ሰው ስላልሆንኩ ብቻ ነው – ያልደወልኩልህ። ባለመደወሌም ይቅርታ – እጠይቅኃለሁ። የተሰጠኝን ስልክ ቁጥር ግን በክብር ስልኬ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል። መጸሐፍቶቼን ብትገዛቸው ደግሞ የበለጠ እኔን ውስጤን ማዬት – ትችላለህ። ትንሽ ማስታወቂያ ቢጤ … ሽልንግ አሰኝቶኝ።

አሁን ወደ ተነሳሁበት መሰረታዊ ጉዳይ ….

የማከብርህ ወንድሜ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ከልብ ሆኜ ነበር ጹሑፍህን – ያነበብኩት። በመናገር – በማሰብ – በመጻፍ ነፃነት ላይ ነበር – ያተኮርከው። ትክክል ነው። ትግሉም ለዚህ ነው። ነገር ግን ጋዜጠኝነት ሙያ እና ካድሬነት እጅግ የማይቀራረቡ መሰረታዊ ጉዳዮች ናቸው። ባይገርምህ ወንድምዓለም እኔ ሁሉንም ሆኜ – አይቸዋለሁ።

  1. የኢሠፓ ፓርቲ ካድሬ ሆኜ – ሳይከፈለኝ።
  2. መደበኛ የፖለቲካ ቋሚ ሠራተኛ ወይንም ፋንክሽነሪ ሆኜ – እዬተከፈለኝ።
  3. ዬዬትኛውም የፓርቲ አባል ሳልሆን በጋዜጠኛነት ከፍተኛ አበል – እዬተከፈለኝ።
  4. ዬዬትኛውም ፓለቲካ ፓርቲ አባል ሳልሆን በጋዜጠኝነት በራሴ ወጪ – ሳይከፈለኝ

የኢሠፓ ፓርቲ አባል ሆኜ በካድሬነት ሥሠራ በነበረበት ጊዜ እማስበው የፓርቲዬን ፕሮግራም ዓላማና ግብ ተፈጻሚነት ብቻ ነበር። ጉዞዬ አንድ አቅጣጫ ግቤም አንድ ብቻ ነበር። ጋሬ – ዓይነት። መደበኛ የፖለቲካ ፓርቲ ሠራተኛ በሆንኩበት ጊዜ ግን ከካድሬነት መንፈስ ጋር በፍጹም ሁኔታ ነበር – የተለያዬነው። ዬተለዬ ሁኔታ ነበር ማለት – እችላለሁ። ተከታታይ ስልጠናዎችና የተፈጠሩልኝ ሌሎች በርካታ አጋጣሚዎች ታክለው ወጣትነቴን ታግሎ አሸንፎልኛል። አለቆቼ ደግሞ ዘመን የማይተካቸው እንደነ ጓድ ገ/ መድህን በርጋ ዓይነት – ነበሩ። እራሳቸው ድርጅት – የሆኑ። በፓርቲዬ ፕሮግራምና ደንብ አፈፃፀም በሚመለከት በአባልነቴ በፓርቲዬ መሠረታዊ ድርጅት ያለብኝን ግዴታ እዬፈጸምኩኝ ግን በማደረጀት ከፍተኛ ዬኃላፊነት ተግባሬ የበለጠውን እጅ ለሙያው ሥነ ምግባር ኃይሌን በመገበር – ነበር።

በጋዜጠኝነት ሙያ እዬተከፈለኝ ሥሠራ የተቃዋሚው ጎራና የገዢው ድርጅት ጎራ በሚመለከት ወገናዊነቱ ለተቃዋሚው ቢያጋድልም ግን ሌላውንም መንፈስ በቅንነት እከውን ነበር። ምርጫ አልነበረኝም በማልፈልገው ቦታ አልገኝም – የማለት። በምታዘዘው ቦታ ሁሉ መገኘት ግዴታዬ ነበር። ነገር ግን ያዬሁትን በትክክል ሳላጋንን ሳልቀንስ ሳልጨምር አስተላልፍ – ነበር። በምልሰት ሳስበው የነበረብኝን ኃላፊነት ከሃቅ ጋር ሳልጣለ ስለነበር ጸጸት ኖሮብኝ – አያውቅም። እንዲያውም የተቃዋሚ ኃይሎችም እኩል ድርሻ እንዲኖራቸው፤ እኩል የአዬር ጊዜ እንዲኖራቸው በጣሙን – ጥሬያለሁ፤ እኩልም አገልግያለሁ ማለት – እችላለሁ። ነፃነቱ ምን ነበር ብትለኝ የተጎዳውን ስሜቴ ለመግለጽ አቅም ነበረው። በሌላ በኩል የምንም ፓርቲ አባል ባልሆንም ግን ህዝቡ የወያኔ ሃርነት ትግራይን መሰሪ ደባ ያለወቀበት ጮርቃ ላይ ስለነበር እኔ ደግሞ በተለያዬ ሁኔታ ስለታገልኩት መጪው ጨላማ ጊዜ በሚመለከት አምቄ የምዬዘው አመክንዮ ስለነበረ መንፈሴ ምቾት በፍጹም ሁኔታ አይሰማውም – ነበር። እርግጥ ሰፊ ተግባር – ከውኝበታለሁ። ሰፊ ልምድም ከአዛውንታት ሊቃናት ባለሙያዎች – ቀስሜበታለሁ። ቀደምቶቹ ቅኝታቸው ቅኔነት ነበር። ቀደምቶቹ ፓን አፍሪካንስት ነበሩና።

ሳይከፈለኝና የፓርቲ አባል ሳልሆን የምሠራው የጋዜጠኝነት ተግባር ግን ወጪው፤ እረፍት – ማጣቴ፤ የሚገጥሙኝ የማያልቁ መከራዎች መጠነ ሰፊም ቢሆኑም በተግባሬ ሆነ በተልዕኮዬ በሙያው ሥነ ምግባር ውስጥ መኖሬ በራሱ ገነት ነው። አብሶ ማንም የማያዝበት የወልዮሽ ያልሆነ፤ የግል መተንፈሻ ቧንባዬን ከአደራጀሁ በኋላ እጅግ ሰላም፤ ጸጥታ፤ መረጋጋት፤ ፍጹም የሆነ ደስታ አለኝ። እማስበውን፤ የሆንኩትን፤ ህመሞችን ካላንዳች ማዕቅብ – እግልጻቸዋለሁ። ፍጹም የሆነ የነፃነት – የጤንነት – መንፈስን ተጎናጽፌያለሁ ማለት – እችላለሁ። ይህ የምድር ጽድቅም ነው። እርግጥ ቲፎዞ – የለኝም። ወይንም ደጋፊ – የለኝም። ወይንም የሚረዳኝ የለም። ወይንም አይዞሽ ባይ – የለኝም። እንኳንም ልታገዝ እልቀተ ቢስ እንቅፋቱን ታሪክ አንድ ቀን ይዘግበዋል። ዛሬ እንዲያውም አንድ ቃለ ምልልስ ነበረኝ። የገጠሙኝን ፈተናዎች ላልተወለዱኝ ስገልጽላቸው እንዴት በተመስጦ እንዳደመጡኝ ለአንድ ዓመት ስንቅ – ይሆነኛል። በእቅፋቸው ውስጥም ህቅታዬን እስክሰበሰብ ስላቆዬዩኝም አምላኬን – አመስግኜበታለሁ።

የሆኖ ሆኖ ፍጹም የሆነ እንክን የለሽ ውሳኔዬ የሐሤቴ ጌታ እንድሆን – አድርጎኛል። ይህ ጉዞዬ ሌላም ነገር – ሸልሞኛል። በተለይ „ሰው“ በሚለው ማዕከላዊ አጀንዳ ላይ ተግቼ እንዳተኩር መሆኔ በራሱ አዲስ የተመቸ አለም ውስጥ እንድኖር ባለ አዲስ መንፈስ ሙሉዑ ሰው እንድሆን – አድርጎኛል። ዛሬ ሃይማኖቴ – ፓርቲዬ – ኑሮዬ – ተስፋዬ „ሰው“ ብቻ ነው። እውነት እውነትነቱ ሊረጋገጥ የሚችለው „ሰው“ በሚለው አምክንዮ ውስጥ መኖር ስትፈቅድ ብቻ ነው። መጀመሪያ „ሰው“ ይተርጎም። „ሰውን“ የተረጎመ እሱ የሁሉም ሙያ ባለቤት ይሆናል። ፍርድ ላይ ቢቀመጥ፤ ወንበር ላይ ቢቀመጥ፤ አዬር ላይ ቢቀመጥ፤ ብቻ ምን አለፋህ ወንድምዓለም „ሰውን“ ማዬት ያስችለዋል። እራሱንም ሰው ነኝ ማለት ይቻለዋል።

ከዚህ ላይ አንድ ነገር ልከልልህ አያቶቼ የቤተ ክህንት ዓራት ዓይናማ ሊቃናት ነበሩና እናቴ ስትነግረኝ ሲያድጉ መሬትን ሲረገጡ መሬት የታመመች ያህል ወይንም የቆሰለች ያህል እንዲጠነቀቁላት ይቆጣጠሯቸው ነበር። መሬት ላይ መዝለል አይፈቅድላቸውም ነበር። አሞከሞም – ሰኞ ማክሰኞም አይፈቀድላቸውም ነበር። ሌላው ቀርቶ ገበጣ ቆፍረው እንዲጫወቱ ማዕቀብ – ነበረባቸው። እኛም ስናድግ ጠረኑ እንዲኖር ተደርጎ ቢሆንም፤ አሁን የሚገርምህ ነገር የበለጠ በላቀ ሁኔታ ተፈጥሮን እማይበት መንፈስ ያ የአያት ቅድመ አያቶቼ መንፈስ አፅመ ቅዱስ ቅርስ የላክልኝ – ይመስለኛል። መሬትን ስረግጥም – የበለጠ ከልጅነቴ ጊዜ ተጠንቅቄ ነው።

አሁን ወደ አነሳኸው ነጥብ ልመጣ አቶ ሄኖክ ሰማእግዚር ለእኔ ጋዜጠኛ ነው ለማለት እጅግ – ይከብደኛል። ራሱ የድምጹ ምቱ ትንት – አለበት። ኢትዮጵያዊ ጠረን የሌለበት መሆኑ መንፈሱን – ይተርጉምልሃል። ምክንያቱም በሙያው ሥነ ምግባር ውስጥ ስሌለ። ጋዜጠኝነት የጎጥ ችግኝ – አይደለም። ጋዜጠኝነት የመንደር እርሾ – አይደለም። ጋዜጠኝነት የበቀል ተክል – አይደለም። ጋዜጠኝነት የቁርሾ ቁርስ – አይደለም። ጋዜጠኝነት ሲሞቅና ሲቀዘቅዝ „በስብዕ ተፈጥሮ ላይ“ ሙከራ የሚሠራም – አይደለም። ጋዜጠኝነት የሰውን ልጅ ተፈጥሮ የመተርጎም ልዩ የመንፈስ ብጡል አቅምና ልቅና ነው። ይህን አመክንዮ በአቶ ሄኖክ ሰማእግዚር አላዬሁበትም። እሱ ካድሬ ነው።

… ካድሬነቱ ደግሞ ለፋሽስቱ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ አስፈጻሚነት ጠበቃ፤ ድልዳል፤ ሽፋን በመሆን በግንባር ቀደምትንት የሙያውን ሥነ ምግባር በመርገጥ የጎጡን ዓላማ አስፈጻሚ በመሆን ነው። እሱ እራሱ ገና ካላደገው አስተሳሰብ ላይ ነው ያለው። ጎጠኝነት መንደርተኝነት ማለት እኮ ያልተመጣጠነ የአስተሳሰብ እድገት ማለት ነው። ያልተመጣጠነ የአስተሳስብ እድገት ማለት ደግሞ የአስተሳሰብ ድህነት ነውና ከጋዜጠኝነት ሥነምግባር ጋር አይተዋወቅም ማለት ነው። ካድሬ ነው፤ የካድሬነቱን ተግባር በዚህ ታላቅ ክቡር ሙያ ሽፋንነት ሊሸቅጥበትና ሊመቅጥበት አይችልም። ስለዚህ ምርጫው አንድ ነው። በሙያው ለመቆዬት የካድሬነቱን ውስጥነት – መርገጥ። ወይንም በካድሬነት ለመቀጠል የጋዜጠኝነቱን ጭንብል – ማውለቅ። በሁለቱ ሥም መነገድ – አይቻልም። እኔ እንደ ሥርጉተ ጋዜጠኝነትን የመረጠ ዜጋ ከብዙ ነገር እራሱን ማቀብ እንዳለበት ነው የማምነው። በስተቀር እውነቱን የማዬት አቅም – ያንሰዋል። መንፈሱ ስስ ስለሚሆን ያገኘ – ይበሳዋል። የመንፈሱ ሰበል የማደግ አቅም አይኖረውም – በአረም ስለሚዋጥ። ከእውነትም በጣም እጅግ በጣም – ይርቃል። ስለዚህ የሙያው መንፈስ መንገድ አዳሪ ይሆናል …..

ጋዜጠኛ ለተገፋ፤ ለተበደለ፤ ለታፈነ፤ ለሚገደል፤ ለሚሞት፤ ለሚደበደብ፤ ለሚደፈር፤ ለሚፈናቅል፤ አድሎ ለሚፈጽምበት፤ ለሚታሰር፤ በግፍ ለሚሰደድ መቆም አለበት። ለነዚህ ምንዱባን ግን ጠበቃ ነው ጋዜጠኛ። አንድ ጋዜጠኛ ይህን ፍላጎቱን ለማስፈጸም ፈቃድ ከማንም መጠበቅ – የለበትም። ሙያው እኮ መከራን አብዝቶ የሚቀበለው፤ የሰቆቃ ኑሮን ፈቅዶ ማድመጥ መቻሉ ነው። የሰቆቃን ኑሮ ማድመጥ መቻል ደግሞ በውስጥ አንጀት ላይ ከፍተኛ ህውከት – ይፈጥራል። ስለምን? ጫናው ሁሉ የሚያርፈው አንጀት ላይ ነውና። ከዚህ መስፈርት በዜሮ ፐርሰንት ላይ የሚገኘው አቶ ሄኖክ ሰማእግዚር እራሱን ያጣው ዛሬ ሳይሆን ከሙያው ሥነ ምግባር ሲወጣ ነው። እራሱን የደበደበው ከተከበረውና ከተቀደሰው የጋዜጠኝነት ሙያዊ ሥነምግባር ይልቅ የጎጥ ካድሬነቱን የመረጠ ዕለት ነው። ከሙያው ዓለም ዐቀፍ ህግጋት ይልቅ መንደር ላይ ከተቀረቀረ የጎጥ ካርድ ላይ ሲወድቅ ነው። ያን ጊዜ ነው ከባህር የወጣ አሳ የሆነው።

የሃሳብ ነፃነት፤ የመናገር ነፃነት፤ የመፃፍ ነፃነት በሰው ስቃይና መከራ እዬተደነሰ ወይንም ፈንድሻ እዬተረጨ – አይደለም። ሰሞኑን አንድ አውዴዎ ወጥቶልሃል። ሊንኩን አልጥፍልህም፤ የቤት ሥራ ነው ፈልገህ አድምጠው ማንና መቼ እንደ ተነገረ „ ብዙ የውጭ ጋዜጠኞች ስለሚመጡ እንዳትደናገጡ!“ ይህ መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ ሲነገር ዕድምታው ኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኛ የለም። ያሉን ካድሬዎች ብቻ ናቸው ነው። ነፃ ጋዜጠኞቹ ደግሞ እስር ቤት ጉድጓድ ወስጥ የተጨመሩ – ናቸው። ይህም ብቻም አይደለም ጋዜጠኝነት ሙያው ማስፈራሪያ ስለመሆኑ ነበር የወያኔ ሃርነት ትግራይ በሚ/ር ደረጃ ያሉ – የገለጹት። ያሳፍራል። ኢትዮጵያ የምትመራው ዓለም ዓቀፍ በሚመራው ህገ – መግስት ድንጋጌ በ1948 ሳይሆን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሲመሰረት በተፈጠረው ናዚያዊ መርዝ ማኒፌስቶ ነው። ውጪ ወያኔ ያሰማራቸው ካድሬዎችም ከኢትዮጵያ ጋር ንኪኪ ያላቸውን ተቋማት ሁለ በዚህ መስፈርት እንዲሄድ ነው ዘመቻው ትልሙም። ኢሳትም ተፈትኖ ነበር … ስላልተደፈረና ስላለፈ – ይረሳልን? በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ለሚኖር ባለሙያ ሙያውም የሙያው ታዳሚም ቦታ የላቸውም። የተከበሩ ዶር ወ/ሮ አንጅላ ሜርክል የጀርመን የመጀመሪያዋ ሴት ጠንካራ ጠ/ሚር 70ኛውን ዓመት የቤተ ይሁዳን ጭፍጫፋ በሚመለከት በተዘጋጀው ህዝባዊ ስበስባ ላይ ውስጠ መንፈሱ „ ለዛ ናዚያዊ አስተሳሰብ ዛሬ ቦታ የለንም“ ይል ነበር። እኛም ለእነሱ ቦታ የለንም።

ሌላው ያነሳኽው ሰላማዊ ሰልፍን በሚመለከት ነው። ሰላማዊ ሰልፍ የተፈቀደ አመጽ ማለት ነው። ህግ የለውም። ጥሰት ሊኖር ይችላል። እንዲያውም – ምረውታል። ፍቅር እኮ አይገዛም። የህዝብ ፍቅር አሽዋ አይደለም ከመሬት – የምታፍሰው። የህዝብ ፍቅር ወንዝ ሄደህ የምታወጣው – አሳም አይደለም። የህዝብ ፍቅር ህግ ደንግገህ የምትሸምተው አይደለም። የህዝብ ፍቅር ዋርካ ላይ ወጥተህ የምትለቅመው ፍሬ – አይደለም። በተግባርህ ልክ የምታገኘው ከሃብቶች ሁሉ ሃብት የሆነ የመንፈስህ ሰብል ነው። ስለዚህ የጠላኸውን፣ አንደበትህ ያልሆነውን ለዛውም በከፋህ ቀን መከፈታህን ሊረግጥ፣ ሊሳለቅበት፣ ሊጠቀጥቀው፣ ሳያፍር ሲመጣ አንገቱን ማስደፋትና ከባህር የወጣ አሳ ስለመሆኑ ማሳዬት የነፃነት ትግሉ አንዱ ዘርፍ ነው። ጋዜጠኛ በጠባቂ – በጠበንጃ ታጅቦ ሳይሆን ጋዜጠኛ በህዝብ ፍቅር ታጅቦ ነው የኖረው።

እንዲሁም – „ለከፋው ማጭድ አትዋስው“ ይባላል። የእነዛ ሰማዕታት ደም በሀገር ውስጥም ተደግሞ ደም እዬፈሰሰ፤ በታመቀ የሃዝን ቁስላዊ ምጥ ውስጥ ላለ ሥጋ ሌላ ጠቅጣቂና ፌዘኛ ማስተናገድ አቅም ያነሰዋል እጬጌው ዕውነት። ይወቀው ሃቅን እስከዳ ድረስ ነገም መጠጊያ የሌለው – እርቃኑን ስለመሆኑ። ነብዬ እግዚአብሄር ዳዊት „ሐገርን ህዝብ ካልጠበቀ ሠራዊቱ በከንቱ ይደክማል“ ብሏል። አጋዚ አሜሪካን የለም – እንዳይከላከልለት። ለጽንስ የማያዝኑ አውሬዎች፤ „ምን አለሽ መቲ“ አንድ ድንቅ ዝግጅት ነበራት። ከወርቆቻችን ጋር አዳምጠው ወይንዬ ያለችውን … 15 ጊዜ ሰምቼዋለሁ እንባዬ እንደ ጎርፍ እዬወረደ „ እኔ ሞቼ፤ እኔ ታስሬ፤ እኔ ተንገላትቼ“ ትላለች ያቺ የነፃነት ቀንበጥ …. ያን ሁሉ አሳር ነፍሰጡሯ ችላ፤ ገና መንፈሱ ከእንሰሳነት ከትንሿ ጉልት ላልወጣ፣ ያ ታላቅ ሙያ እንደ እሱ ላለ በጎጥ በሽታ ላበደ ጥንዝልና ዝንጥል ቦታ – የለውም። ሙያውም ጥብቅናም – አይቆምም። ጋዜጠኛ አብርሃ ደስታ ነው የእኛ። ሁሉ ሲቻለው መከራን ለመቀበል በቃኝን በአሳር – ያቀለመው። ናፍቆቴና ውዴ … የ እነሱን መታሰር ለ አምንስት ኢንተርናሽናል ስልክ የቀደመኝ እንደሌለ በጣም እርግጠኛ ነኝ። አዬህ ለእውነት አርበኞቻችን ፈጣኖች ነን። ለካህዲዎችና ለባንዳዎች ደግሞ ጦሮዎች።

በተጨማሪ ያነሳኸው ነጥብ አለ። አዎን የተወጣው መሰረታዊ ምክንያት ዕንባችን – ይደመጥ ነው። ስለዚህ ወሰን ደንበር ተሰርቶለት በዚህ ብቻ በዛኛው ብቻ ሊባል – አይችልም። አኔ አንድ ነገር ለዓለምአቀፉ ማህበረሰብ መላክ ስፈልግ ተያያዥ ሊንኮችን ጨምሬ ነው – እምልከው። ጥያቄ ስለ ድምጽ አልባዎቹ መከረኛ እህቶቼ ሊሆን ይችላል። ግን ሌለችንም አክዬ – እልካለሁ። ሊንኮችም ዕውቅና እንዲያገኙ ስለምፈልግ። አዬህ አባትዬ ግፉ በዝቶ ተርፎ ፈሶል …. አቅም የለም ህግ የምንሠራበት – ይህን አትንኩ ያኛውን ብቻ የሚባልበት – ጊዜ ላይ አይደለም። ሰላማዊ ስለፈኛን ማስተዳደር – አይቻልም። ለዛውም – የተከፋን፤ በሃዘን – የተረመጠ፤ በዕንባ – የተቃጠለ ….. ብሶተኛ ሰላማዊ ጦረኛ ነውና!

ወንድምዬ ስለ አቤ በለውም አንስተሃል። አቤን ማንም – አልተጋፋውም። ራዲዮ ፕሮግራሙ አማርጭ ነው። በከፍተኛ ደረጃ ሲደመጥ – ኖሯል። ሰፊ ተከታይና አድናቂም – ነበረው። ያቀረበውን ቢያቀርብ፣ የጠዬቀውን ቢጠይቅ ማን ተናግሮት ያውቃል? እንዲያውም አንድ ጊዜ እኔ „ቤት አለው“ በሚል አንድ ጹሑፍ አንብቤ የጻፍኩት ነበር። ተከላካይ ሆኜ። ይሄ ብቻ አይደለም የልጅነት ፍቅር እስከ የሰብዕ መብት ጠበቃነት በሚል ለልጆች በጻፍኩት ላይ ስልማውቃቸው መንትያ ወንድሞቼ ስለ ታማኝና ስለ እሱ – ጽፌያለሁ። ታትሟል መጸሐፉ። እንዲህ ዓይነት ሰብዕና ሲያመጣ – አመመኝ። ስለ – አዋረደኝ። አንድ ጋዜጠኛ በአድማ መግባት – በፍጹም የለበትም። በ21ኛው ክፍለ ዘመን ለዛውም በታላቋ አሜሪካ በአንድ እንፍራዝ ላይ እንደሚካሄድ ስብሰባ በዛ ነክና ውሎ ጉዞ የሌለው ማይክራፎን ይቅርታ ሲጠይቅ ድምጹን – ሰምቼያለሁ። ይቅርታ መጠዬቁ መልካም ነው። ግን ችግሩ ማይክ ነበርን? ቦታ – ቅጥል ሥም ነውን የሚያሰኘው? ምን ያደርግለታል – ለአንድ ሞት ለተፈረደበት ጋዜጠኛ? …. ይሄን ነበርን የሚፈልገው ወይንም የከነከነው? እኔ እንደማስበው ለጋዜጠኛ ወንበር ቦዶ …. ቦደ ወና ነው። ሥልጣን ጭድ – ምደረ በዳ ነው ነው። ክብርም – ልጥፍ ነው። እኔ ሀገሬ ኢትዮጵያ በህዝብ ፈቃድ ምርጫ ብታካሄድ የምርጫ ካርድ – አልወስድም? ለምን? ሚዛኔን – አጣለሁ። ክብሬን እሸጣለኋ! ምርጫው – ቢዛባ፤ ቢጨበረበር በምን አንደበቴ – እናገራለሁ? እኔም ተሳታፊ ነኝና። እኔም ታዳሚ ነኝና። እኔም ድምጽ ሰጥቻለሁ፤ እና ነፃ ጋዜጠኛ የመክሊቱ ዳር ድንበር አሁን በከፈተው ዘመቻ መሆን አይገባውም።

ዛሬ ኢትዮጵያ ላይ የጋዜጠኛ ኃላፊነት ዕውነት መሆን ይገባዋል። ጋዜጠኝነት የዕንባ ተጠሪነት ነው። ለዛውም አማራጭ የሆነ ራዲዮ በብዙ መልኩ በሁሉም ዘርፍ ተሸሎ ሠልጥኖ መገኘት አለበት። የአቲካራ ቤትም መሆን የለበትም። ቤተ – እርቅ ነው መሆን ያለበት። የእሱ ደግሞ ቤተ – እሳት – ነዲድ፤ ቤተ አድማ – አደረገው። ሌላው ያነሳኸው መልስ አልተሰጠም ብለህ የወቀስከው ነገር አለ። እኔ ለአቤ አንድ ችግር ገጥሞኝ ጽፌለት ነበር በአንድ ወቅት እሱ እራሱ መልስ – አልሰጠኝም። መልስ በመስጠት፤ መልእክት በማድመጥ – በማክበር ከማንም ያላገኘሁትን፣ ያለዬሁትም የሰጠኝ ጋዜጠኛ አበበ ገላውን ብቻ ናሙና ማድረግ ይቻላል። በስተቀር የትም ቦታ ጽፈህ መልስ – የለም። ሆም ፔጆች ሁሉ። ተባባሩን ይላሉ፣ ስትጽፍላቸው መልስ የለም። አንድ ጹሑፍ ገርሞኝ አደባባይ ላይ ከምወርፋቸው ብዬ ለቀድሞው ብቸኛ የፓርላማ ተመራጭ ለአቶ ግርማ ጽፌ ነበር – መልስ አልሰጡኝም። ምን አልባት እኛ እምንፈልገው ክረት እንጂ ለዘብ ማደረግ ስላልሆነ እንዲሁም ቶሎ ሆድ ስለሚበስን እንጂ ብዙ ሰው ባህሉ አይደለም። ታላላቅ ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ግን መለስ ይሰጡኃል። ወይ ደውለው – ያነጋግሩሃል። ወይ በኢሜልህ መልስ – ይልኩልሃል። ለማንኛውም እምትፈልጉትን ለአቤዋ ገላው – ላኩለት። ለምትፈልጉት አካል – ይልክላችኋል። አንድ ዓመት ሙሉ ስሜቴን፣ ቅሬታዬን፣ የማጠናከሪያ ሃሳቤን – እንደዛሬው ቤቴን ዘሃበሻን ሳላገኝ ለእሱ ነበር – እምልከው። ደከመኝ አይልም፤ ሰለቸኝ አይልም፤ በዛብኝም አይልም፤ አይቆጣኝም፤ ሁሉንም እንደምፈልገው በፈለግኩት ደረጃ አስተናግዶልኛል። አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም የላከበትን ጨምሮ ይልክልኝ ነበር። እኔ ጽፌለት መልስ ሳይሰጠኝ የቀረበት አንዳችም ጊዜ – የለም። የዘሃበሻ መኖር እኔም የማይደክመኝ ሰውንም ይደክመዋል የማይመስለኝ ስለሆንኩኝ አሁን እርግጥ ጫናው  – ተቃሎለታል። አስቸግሬው አላውቅም።

ክንዴ! – ከዚህ በተረፈ የሰው ተፈጥሮ የተለያዬ ነው። የእኔን – ልንገርህ። ስልክ – አልመልስም። አራት የእጅ ስልክ አለኝ። ሲዊዝ ጓደኞቼ ገዝተው – የሰጡኝ። እውነት ልንገርህ – የሁለቱን ቁጥር – አላወቀውም። የቤትም አለኝ። አስቤም – አልደውልም። ሲደወልልኝም – አላነሳም። በቃ ተፈጥሮዬ ነው። ኢሜል ከሆነ ብቻ አፋጣኝ መልስ – እሰጣለሁ። ስለዚህ ከመናቅ ወይንም ቸል ከማለት ወይንም አልደፈርም ከማለት ላይሆን – ይችላል። የሰው ልጅ ሴሎች ህወሶች ከአንዱ ሰው የሌላኛው የተለዬ ነው። የጭንቅላታችን፤ የእግራችን፤ ዬእጃችን አሻራዎች ኮፒ የላቸውም። በቃ ሃቁ ይሄ ነው። አንድ ሰው እራሱን ሆኖ ነው – የተፈጠረው። ሌላው ስለሚያደርገው ነገር የእሱ አይደለም። በእሱ ውስጥ ያለው እሱ ብቻ ነው። ስለዚህ ወቃሽም ተወቃሽም ሊኖር አይገባም። ባህሬው ሊሆን ይችላል።

አሜሪካኖችን ጠባይም የጠቋቋምከው አለ። የተዘጋ በር እኮ ከፍተውላቸዋል። መከራ የበዛበት ህዝብ ደግሞ የዕንባ መውረጃ ቦይ እንጂ በዛች ቅጽበት ይሄን የሚያገናዝበብት አቅም ካላመጣህ ተብሎ ሊወቀስ አይገባም። ስለምን? ሃዘናቸው – ሃዘናችን ነው። እኛ ባልተገኘንበት ቦታ ሁሉንም ሆነው የዕንባችን ተጠሪ መሆናቸው ሊያስመሰግናቸው እንጂ ሊያስወቅሳቸው – አይገባም። አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ የተሠሩ ጊዜ በተባባሩት መንግሥታት ቢሮ ፊት ለፊት የወያኔ ሃርነት ትግራይ አርማ ተቃጥሏል። በዛን ጊዜ ለተወሰነ ጊዜ ራስን መግዛት – ይሳናል። አማትፈልገውን ነገር እንድታደርግ የሚያሰገድዱህ ሁኔታዎችና አጋጣሚዎች  – ናቸው። ስለዚህ – አይፈረደም። ለተወሰነ ጊዜ ሌላ ሰው ትሆናለህ። ከተረጋጋው ሰብናህ ጋርም ልትተላለፍ ትችላለህ። አቅደው ደግሞ አልሠሩትም ድንገት የተፈጠረ ነው።

ክወና …. እኔ ቅጣት ነው አልልም። ትምህርት ነው። ሀገር ቤት ያሉትም የኢትዮጵያ ህዝብ አጋጣሚ ቢያገኝና ቢፈቀድለት ከቤተ ክርስትያን እንደገባ ውሻ እንደሚያደርጋቸው – አትጠራጠር። 24 ዓመት ሙሉ በአግላይ ፖለቲካ የተቀጠቀጠ የህዝብ አካል …? ወደ አሜሪካ ከሚላኩትና ከሚዋረዱት ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ አስፈጻሚዎች አቶ ሄኖክ ሰማእግዚር ከቶ በምን ይለያል? በምንም ነው – ለእኔ። ለዛውም በነፃነት ሀገር – ተቀምጦ። ማዬቱን ሰጥቶት ከውሳኔ ላይ ያደርሰው፤ እንደ ሥሙ ለመሆን ያብቃለት የምህረት አባት ቻይ ነውና አዲስ ልብ ይላክለት። አሁንም አልመሸም ይቅርታ ጠይቆ ሥጋና ደምን ከዕንባ ጋር ለማጋባት። ቢያንስ የሚያነብበትን ቶኑን ትንሽ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊ እንዲሸት ይታደገው – አንድዬ። ጉድፍና ግድፈት ይናኘኝ ካለም ከዛሬ የባሰም ሊገጥመው – ይችላል። የሰማይ ቅጣትም እኮ አለ። ለማንኛውም ወደ ልቦናው ድንግል ትመልሰው። እሷ የይቅርታ እመቤት ናትና!

ውዶቼ ሳላስበው ነው ዛሬ ከች ያልኩት፤ መሸቢያ ሰሞናት። ክብሮቼ – ዘሃበሻ ኑሩልኝ ውድድድ …..

ኃላፊነቴን የገደልኩት ቀን አኔን ቀድመህ ውሰደኝ – ፈጣሪዬ።

ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል!

 

 

The post ውስጤ! – (ሥርጉተ ሥላሴ) appeared first on Zehabesha Amharic.

“የፍርድ ቤት ብያኔው መንግስት ከሙስሊሙ ጋር ያለውን ቅራኔ ለመፍታት እያሰበ እንዳልሆነ የሚያሳብቅ እርምጃ ነው –ድምፃችን ይሰማ

$
0
0

ወቅታዊውን የሕዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች የፍርድ ሂደት አስመልክቶ ከ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› የተሰጠ መግለጫ
ሰኔ 29/2007፤ አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ
በሙስሊሙ ህብረተሰብ ወኪሎች ላይ የተላለፈውን የግፍ ፖለቲካዊ ፍርድ አንቀበልም!
በአንድነት በመቆም ለረጅም የትግል ጉዞ በአዲስ መንፈስ እንነሳ!

ላለፉት ሶስት ዓመታት በበርካታ አስቂኝ እና አሳዛኝ ድራማዎች ታጅቦ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ ዳዒዎች፣ ጋዜጠኞች እና አርቲስቶች የፍርድ ስነ-ስርዓት እንደተጠበቀው የኢትዮጵያ የፍትህ ስርዓት የደረሰበትን ዝቅጠት በሚያሳይ መልኩ እነሆ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ ኮሚቴዎቻችንም በግልፅ ከችሎት ፊት ‹‹አሁን ባለው የፍትህ ስርዓት ሚዛናዊ የሆነ ፍትህ እናገኛለን ብለን ሳይሆን ለታሪካዊ እማኝነቱ ብለን ቀርበናል›› ሲሉ የተቹት የችሎት ክርክር መንግስት ራሱ ከሳሽ ራሱ ዳኛ የሆነበት እና ፍትህ የተዘነበለበት አሳዛኝ ክስተት ሆኖ አልፏል፡፡ ሂደቱ የተጠርጣሪዎች ከፍርድ በፊት እንደ ነፃ የመታየት መብት በመንግስት መገናኛ ብዙሃን የተጣሰበት፣ መንግስት የሃሰት ምስክሮችን በፕሮጀክተር ታግዞ በግልጽ ያሰለጠነበት፣ አቃቤ ህግ የዳኞች አለቃ መሆኑ የታየበት እና ዳኞች ማረሚያ ቤቱን እንኳን ማዘዝ እንደማይችሉ የታዘብንበት ትልቅ የፍትህ ክስረት ነበር፡፡
muslim
መንግስት ላለፉት ሶስት ዓመታት ይህንን ሰላማዊ እና ህገ-መንግስታዊ የሃይማኖት ነፃነት ትግል በኮሚቴው ላይ ከሚበየነው የፖለቲካ ፍርድ በፊት ለማኮላሸት ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ እንደነበር ከማንኛውም ታዛቢ የሚደበቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ እንቅስቃሴው ሙስሊም ባልሆኑ ወገኖቻችን ላይ የተቃጣ ሴራ እንደሆነ በማስመሰል እና የኢትዮጵያውያንን ተቻችሎ የመኖር ባህል አደጋ ውስጥ ሊከት በሚችል መልኩ ትግሉን ለማጠልሸት ሲጥር ቆይቷል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ህዝቡ በኮሚቴው እና በእንቅስቃሴው ላይ እንዲዘምት ሰላማዊ ሰልፍ ከማስጠራትም ባለፈ የኮሚቴውን እና የእንቅስቃሴውን ህልውና ለመናድ ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም፡፡ በአላህ እርዳታ፣ ከዚያም ሙስሊሙ ማህበረሰብ በተከተለው ውጤታማ የትግል ስልት ምክንያት ሁለቱም የመንግስት እኩይ ዓላማዎች ሳይሳኩ የቀሩ ሲሆን እንቅስቃሴው ከጊዜ ወደ ጊዜ አድማሱን እያሰፋ እና በዳዮችን እያሳፈረ አሁን ካለንበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ እንቅስቃሴው በጥቅሉ የሙስሊሙን አንድነት ከማጠናከሩም በተጨማሪ የመንግስትን የጥፋት ፕሮፓጋንዳ ባዶ በማስቀረት ሙስሊም ያልሆነውን ኢትዮጵያዊ በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ ከእንቅስቃሴው ጎን ማሰለፍ ችሏል፡፡

እንቅስቃሴውን እና ኮሚቴውን ከህዝብ መነጠል ያልቻለው መንግስት እንደ 1987ቱ የአንዋር መስጂድ ግርግር ሙስሊሞችን የመከፋፈልና የማዳከም ሴራውን በመቀጠል ኮሚቴውን ለመሰንጠቅ ከመባከን አልታቀበም ነበር፡፡ በመላው የኮሚቴው አባላት ላይ ማስፈራሪያዎች እና የግድያ ዛቻዎች መሰንዘር የጀመሩትም ገና ከመነሾው ነበር፡፡ የተወሰኑትን የኮሚቴ አባላት በቁም እስር አቆይቶ ሌሎቹን ማዕካላዊ ሲያሰቃይ፤ ለአንድ ዓላማ በአንድ ላይ ሲሰሩ ከነበሩት ታሳሪዎች የተወሰኑትን በነፃ አሰናብቶ የተወሰኑትን ተከላከሉ ሲል የመንግስት ስሌት ኮሚቴውን በመክፈል ህዝቡንም በዚያው ልክ አቅጣጫ ለማሳት ያለመ ነበር፡፡ በእስር ላይ ያሉትን የኮሚቴው አባላት ስብዕና በሚጎዳ ኢሰብዓዊ አያያዝ በመያዝ፣ በቁም እስር ያሉትንም መፈናፈኛ በማሳጣት ህዝቡ እና ኮሚቴው ተስፋ እንዲቆርጥ ለማድረግም አድካሚ ጉዞ ተጉዟል፡፡ ይሁንና ህዝቡም ሆነ መላው የኮሚቴው አባላት ይህንን እኩይ ሴራ አስቀድመው በመገንዘባቸው የመንግስትን ስሌት ፉርሽ ማድረግ ተችሏል፡፡ ዛሬ በፍርድ ቤት ሽፋን የተላለፈው የፖለቲካ ብይን የእስካሁኑን ሂደት በጥሞና ለተከታተሉ ከዚህ ያለፈ ትርጉም እና ፋይዳ የለውም፡፡ ህዝቡ ደግሞ የኮሚቴዎቹን ማንነት ከማንም በላይ የሚያውቅ እንደመሆኑ ወኪሎቹ በእስር እስካሉ ድረስ ህዝበ-ሙስሊሙ ራሱ እንደታሰረ መቆጠሩ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡

መንግስት ሊያውቀው የሚገባው መሰረታዊ ነጥብ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሃይማኖት ነፃነት ንቅናቄ በኮሚቴው ላይ በሚተላለፍ ማንኛውም ዓይነት ፍርድ እንደማይገታ ነው፡፡ እንቅስቃሴው ኮሚቴውን ወለደ እንጂ ኮሚቴው እንቅስቃሴውን አልወለደም፡፡ እንቅስቃሴው ያለ ኮሚቴው ራሱን ችሎ ከመቆም የሚያግደው አንዳችም ምድራዊ ሃይል እንደሌለ ለማሳየትም ያለፉት ሶስት ዓመታት ህዝባዊ ትግል ህያው ምስክር ነው፡፡ ኮሚቴውን በማሰር፣ የእንቅስቃሴውን አራማጆች በማሳደድ፣ በሰላማዊ መንገድ ብሶቱን በሚገልፀው ማህበረሰብ ላይ የጥይት ቃታ በመሳብ እና በመደብደብ ህዝባዊውን እንቅስቃሴ ከቶም ቢሆን ማስቆም አልተቻለም፤ አይቻልምም! ንቅናቄው የህዝባዊ ብሶት ውጤት እንደመሆኑ ማቆሚያውም ብሶቱን አድምጦ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ብቻ ነው፡፡ ‹‹ኮሚቴው ይፈታ!›› የሚለው ጥያቄም ተጨማሪ ጥያቄ እንጂ የንቅናቄው መነሻ አለመሆኑን ደጋግመን እናረጋግጣለን፡፡

ላለፉት ሶስት ዓመታት ሰላማዊ እና ህገ መንግስታዊ በሆነ መንገድ ጥያቄያችንን ለመንግስት በተለያዩ መንገዶች ስናቀርብ ቆይተናል። መንግስት የመጅሊሱን ምርጫ በሚፈልገው መንገድ ጠፍጥፎ ከጋገረው በኋላ እንኳን የተካሄደው ሹም ሽር፣ በሙስሊም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የሚደርሰው ጫና፣ በሴት ሙስሊም ተማሪዎች ላይ የሚደርሰው የሂጃብ ገፈፋ፣ በመስጂድ ኢማሞች እና በዳዒዎች ላይ እየተሰራ ያለው ማፈናቀል እና ማስፈራራት፣ በኢስላማዊ ጋዜጦች እና መፅሄቶች ላይ የተወሰደው እርምጃ… ይህ ሁሉ መንግስት ለኢትዮጵያ ሙስሊም ካሰበለት እኩይ ዓላማ ጥቂቱ እና መሬት ላይ የዋለው ነው፡፡ ለዚህ ሰላማዊና ህጋዊ ጥያቄያችን የመንግስት ምላሽ ስም ማጥፋት፣ እስር፣ ድብደባ፣ እና ግድያ በመሆኑም ነበር ከመብት ጠያቂነት ወደ መብት ማስከበር የትግል ምእራፍ የተሸጋገርነው፡፡

አዎን! ያለፉት ሶስት ዓመታት ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ከመቼውም ጊዜ በላይ ኢስላማዊ አንድነቱን ያጠናከረባቸው፤ መንግስት ለክቶ የሰፋለት የሃይማኖት ነጻነት መብቱ እስከምን እንደሆነ በግልፅ ያየባቸው፣ እንዲሁም የወደፊቱን የትግል አቅጣጫ መስመር ያሰመረባቸው ወሳኝ የትግል አመታት ሆነው አልፈዋል፡፡ በየትኛውም መመዘኛ የዛሬ ሶስት ዓመት ከነበርንበት በተሻለ ማኅበረሰባዊ ንቃት ላይ እንደመሆናችን በኮሚቴዎቻችን ላይ የተበየነው የፖለቲካ ፍርድ ያለንን ሃይል በሙሉ አሟጠን እንድንታገል ቢያደርገን እንጂ አንድ ጋት እንኳ ወደ ኋላ ሊያፈገፍገን እንደማይችል እንገልጻለን፡፡ ህገ መንግስታዊ ሃይማኖታዊ መብቶቻችንን ከጥቃት ለመጠበቅ የአምባገነኖችን እርምጃ ፈርተን የምንሸበብበትም አንዳች ምክንያት አይኖረንም፤ እምነታችን በእኛ ዘንድ ከደማችን እና ከአጥንታችን በላይ ውድ ነውና!

ውድ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሆይ!

በአምባገነን ስርዓት ውስጥ አንገትን ሰብሮ፤ ውርደትን ተከናንቦ ከመኖር ባህል ውጪ በሆነና በሚያኮራ አኳኋን ላለፉት ሶስት ዓመታት ‹‹እምቢ ለእምነቴ!›› ብለን በሰለጠነና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለሃይማኖት ነፃነታችን መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት ያለምንም ስስት እየከፈልን እዚህ ደርሰናል፡፡ ትእግስትን የሚፈታተኑና ጠብ አጫሪነት የተሞላባቸውን የመንግስት ትንኮሳዎች እና እርምጃዎች አልፈን ያልተቆጠበ የህይወት፣ የጉልበት፣ የሃሳብ እና የገንዘብ መስዋዕትነት ያለ ዘር፣ እድሜ እና ፆታ ልዩነት ስንከፍል ቆይተናል፡፡ ሶስት ቀላል የሃይማኖት ነፃነት ጥያቄዎችን ያቀረብንለት መንግስት ላለፉት ሶስት ዓመታት የመለሰልን መልስ ይበልጥ ወኔ እና ቁርጠኝነት ቢጨምርልን እንጂ አንገታችንን አያስደፋንም፡፡ በመሆኑም የትግላችንን አድማስ በማስፋት በአዲስ መንፈስ ረጅሙ የትግል ጉዟችን የሚቀጥል ይሆናል። ሁሉን አቀፍ የሆነ የሃይማኖት ነፃነት ጥያቄያችንን አጠናክረን ከመቀጠል ውጪም ሌላ እርምጃ አይኖረንም፡፡ ድክመቶቻችንን አርመን፣ ጠንካራ ጎኖቻችንን አጠናክረን፣ በአላህ የእምነት ገመድ ተሳስረን ቃል የተጋባንበትን የትግላችንን ግብ በአላህ ፍቃድ እናሳካለን፡፡

የፍርድ ቤት ብያኔው መንግስት ከሙስሊሙ ህብረተሰብ ጋር ያለውን ቅራኔ ለመፍታት እያሰበ እንዳልሆነ የሚያሳብቅ እርምጃ እንደመሆኑ የመብት ጥሰቱን ሂደት እና ውጤቱን በትክክል ያሳየ ነው፡፡ መንግስት የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ከመጨፍለቅም አልፎ ሙስሊሙ በገዛ አገሩ ላይ የይገባኛል ጥያቄ እንዳያነሳ እና ሁልጊዜም ተጨቋኝ ሆኖ እንዲቀር የሚያስችል የረጅም ጊዜ እቅድ እንዳለው የሚያሳብቅ ግልጽ በደል ነው፡፡ ለዚያም ነው ለእንቅስቃሴው የጀርባ አጥንት፣ ለመንግስት ደግሞ ራስ ምታት የሆነውን አንድነታችንን ለመፈረካከስ የሚጥረው፡፡ በመሆኑም ካሁን ቀደም የተደረጉ የመከፋፈል ሙከራዎችን እንደህዝብ እንዳከሸፍን ሁሉ አሁንም ይህንን የፍርድ ሂደት በማስታከክ በመንግስት በኩል የተጠነሰሰልንን የመከፋፈል ሴራ በመገንዘብ ሁላችንም በአንድነት ለረጅሙ ጉዞ በተጠንቀቅ መቆም ይኖርብናል። እስከዛሬ በነበረው በሳል ሂደት ያካበትናቸውን ልምዶች መሰረት በማድረግ በተጠናከረ ውሳኔ ሰጪነት መብቶቻችን እስኪከበሩና ወኪሎቻችን፣ እንዲሁም በትግሉ ስም የታሰሩ ጀግኖች ሁሉ እስኪፈቱ ድረስ ሕዝባዊ ሰላማዊ ትግላችን በአላህ ፈቃድ እስከድል ደጃፎች ድረስ ይቀጥላል። ህብረተሰባችንም ይህንን ከግንዛቤ በማስገባት ራሱን የማንቃትና የማጎልበት ስራ እየሰራ በትእግስት ቀጣይ መልእክቶችን እንዲጠባበቅ በአላህ ስም እንጠይቃለን።

የትግሉ ሰማዕታት፣ እስረኞቻችን እና የአካል ጉዳተኞቻችን ሆይ!

አላህ መስዋዕትነታችሁን ተቀብሎ ምንዳችሁን አጥፍ ድርብ ያበዛላችሁ ዘንድ ዱዓችን ነው! እኛም በእናንተ ፋና እየተጓዝን አብረን የጀመርነውን ትግል ሳናሳካ ከቶም እንደማንመለስ ቃል እንገባላችኋለን፡፡ እስካሁን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከጎናችን ለቆማችሁ፣ የመንግስትን አጥፊ ፕሮፓጋንዳ ችላ በማለት ድምፃችንን ስታሰሙልን ለነበራችሁ ክርስቲያን እና የሌሎችም ሃይማኖቶች ተከታይ ወንድም እና እህቶቻችን፣ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት እና ለመላው የአገራችን ህዝቦች በሙሉ የአክብሮት ምስጋናችንን እናቀርባለን! ወገናዊ አጋርነታችሁ ወደፊትም እንደማይለየንም ተስፋ እናደርጋለን!

በአንድነት በመቆም ለረጅም የትግል ጉዞ በአዲስ መንፈስ እንነሳ!
ትግላችን በአላህ ፈቃድ አስከድል ደጃፎች ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

The post “የፍርድ ቤት ብያኔው መንግስት ከሙስሊሙ ጋር ያለውን ቅራኔ ለመፍታት እያሰበ እንዳልሆነ የሚያሳብቅ እርምጃ ነው – ድምፃችን ይሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: ፒያኖ መጫወት ለአዕምሮ ጤና የሚያስገኘው ጠቀሜታ

$
0
0

Piano and Brain Health
ይህ ጽሁፍ በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ላይ ታትሞ ወጥቷል::

ብዙ ሰዎች የዕለት ተዕለት ህይወታቸውን አስደሳች ለማድረግ ይረዳል ብለው የሚያስቡትን ነገር ለማከናወን ይጥራሉ፡፡ ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ ብዙዎች አመጋገባቸውን ጤናማ ለማድረግ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚሞክሩ ናቸው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከዚህም እዚያም የአትክልት ቤቶች ከስጋ ቤቶች እኩል እየተስፋፋ መምጣት፣ የአካል ማጎልመሻ ጂምናዚየሞች ቁጥር መብዛት የዚህ ማሳያ ነው፡፡ ምንም እንኳን እነዚህ ድርጊቶች ጤና በመጠበቅ እና ደስታን በማጎናፀፍ ረገድ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ቢሆንም ሌሎች በተለይ ደግሞ ለአዕምሮ ጤና የሚጠቅሙ ልምምዶችም ይኖራሉ፡፡አንዱ ሙዚቃ መጫወት ነው፡፡ ከሙዚቃም መሳሪያዎች መካከል ፒያኖ መጫወት፡፡

ሙዚቃ መጫወት የአንድን ሰው ሁለንተናዊ ጤንነትን ለማሻሻል ይረዳል፡፡ ለአዕምሮ ጤና መጠበቅም ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡

ከሙዚቃ መሳሪያዎች መካከል ደግሞ አንዱ እና ዋነኛ የሆነውን ፒያኖ መማር እና መጫወት መቻል ማንም ሰው ሊገምተው ከሚችለው በላይ በርካታ ጥቅም ለአዕምሮ ጤና ይሰጣል፡፡

አንድ ሰው ፒያኖ መማር ከሚጀምርበት ወቅት አንስቶ ዕድሜ ልኩን አብረው የሚዘልቁ ጥቅሞችን ያገኛል፡፡ ልጅም ይሁን አዋቂ ያለምንም ልዩነት ፒያኖ የሚጫወት ከሆነ ዘርፈ ብዙ ጤና ነክ ጥቅሞችን ይቋደሳል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ነጥቦች ፒያኖ በመጫወት የሚገኙ ልዩ ልዩ ጥቅሞች ናቸው፡-

– ፒያኖ መጫወት የአንድን ሰው የማሰብ እና የማሰላሰል አቅም ይጨምራል፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ሙዚቃ እየፈጠሩ መጫወት ሌሎች ድርጊቶች የማይወጡትን በከፍተኛ ሁኔታ አንጎልን የማነቃቃት ስራ ይሰራል፡፡ አንድ ሰው ፒያኖ በሚጫወትበት ጊዜ አንጎሉ ውስጥ የሚገኙ ኒውሮኖች ትስስር ይጨምራል፡፡

– ፒያኖ መጫወት የዓይንን እና የእጅን ቅንጅት ያጠናክራል፡፡ አንድ ሰው የፒያኖ መጫወቻ መምሪያን እያነበበ በሚጫወትበት ወቅት ዓይኑ እና እጁ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መልኩ ወዳጅነታቸው ጥብቅ ይሆናል፡፡

– ፒያኖ መጫወት የቀላል ጡንቻዎቻችንን ቅልጥፍናም ይጨምራል፡፡ የእጅ መጠን የፒያኖ ጨዋታ ክህሎትን አይወስንም፡፡ ወሳኙ ነገር ጣቶቻችን የፒያኖ ጨዋታ የሚጠይቀውን ቅልጥፍና እንዲለማመዱ ማድረግ ነው፡፡

– ፒያኖ መማር ቀላል የማይባል ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ ሥራ ነው፡፡ የታወቀ ፒያኒስት ለመሆን በትጋት ለረጅም ጊዜ ልምምድ ማድረግ የግድ ነው፡፡በየቀኑ የፒያኖ ትምህርት ያለ ማቋረጥ መውሰድም አንድ ሰው በህይወቱ ይበለጥ ስርዓት ያለው ሰው እንዲሆን ያግዘዋል፡፡ እንዲህ አይነት ስርዓት ደግሞ በሌሎች የህይወታችን ክፍሎች ውስጥም ጠቀሜታ ይኖዋል፡፡

– ፒያኖ መጫወት ውጥረትን እና ጭንቀትንም ይቀንሳል፡፡ አንድ ሰው ፒያኖ ለመጫወት ሌላው ቀርቶ ለጥቂት ደቂቃዎች እንኳን ቁጭ በሚልበት ወቅት ሃሳቡ አንድ ስፍራ ላይ ይሰበሰባል፡፡ ይሄ በበኩሉ የደም ግፊትን መጠን ዝቅ በማድረግ ወይም በማስተካከል የሚሰማን ውጥረት እና ጭንቀት እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡

– ፒያኖ መጫወት የአዕምሮን ጤናማ ይጠብቃ፡፡ ብዙ ፒያኒስቶች እንደ ድብርት ባሉ የአዕምሮ ጤና ጠንቆች እምብዛም አይቸገሩም፡፡ ማህበራዊ ችግሮች ብቸኝነት የመሳሰሉ ፒያኖ በመጫወት ሊቃለሉም ይችላሉ፡፡

ፒያኖ በማወት የሚመጣ አንድም ችግር የለም፡፡ ይልቁንም የፒያኖ ትምህርት እና ስልጠና መውሰድ እና መጫወት በጥቅሉ ለአካልም ሆነ ለአዕምሮ የሚያስገኘው ጥቅም የትየለሌ ነው፡፡ አንድ ሰው ፒያኖ በሚጫወትበት ወቅት ህይወቱን በስርዓት መምራትን ከመማር ጀምሮ የፈጠራ ችሎታውን እስከማሻሻል ድረስ ቀላል የማይባሉ ለውጦችን ያመጣል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ፒያኖ መማርም ሆነ መጫወት ምንም አይት የዕድሜም ሆነ አዕምሮ ገደብ የለውም፡፡ ወሳኙ ነገር ፍላጎቱ ብቻ ነው፡፡

The post Health: ፒያኖ መጫወት ለአዕምሮ ጤና የሚያስገኘው ጠቀሜታ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአፋር ክልል ወጣቶች ለውትድርና በግዴታ እየታፈሱ ነው

$
0
0

(ፎቶ ፋይል)

(ፎቶ ፋይል)

ከአኩ ኢብን አፋር

በአፋር ክልል የህዝባዊ ወያነ ሐሪነት ትግራይ መንግስት የአፋር ህዝብን ደካማ ጎኑን በመጠቀም ወጣቶችን ለውትድርና እያፈሰ ይገኛል።

አለም አቀፍ የምግብ ተረድዖ ድሪጅት በእንግለዘኛ ምህጻሩ WFP ( worlid food program ) ለኢትዮጲያ ህዝብ የሚሰጠው የእርዳታ እህል ለውትድር መደልያ በመጠቀም በአፈር ክልል በብዙ ወረዳዎች እርዳታን ለማገኘት ከአንድ አባወራ ቢያንስ አንድ ሰው ለውትርና መመዝግብ አለበት።

የወያነ መንግስት የመዕራባዊያን ድጋፍ ላለማጣት የገዛ ወታደሮቹን በሰላም አስከባሪነት ሽፋን በሶማሊያ እና በደርፎር በማሰማራት እየፈጃቸው መሆኑን የሚታወቅ ሲሆን በአሁኑ ወቅት አፈሳው እየተካሄደ ይገኛል።

በአፋር ክልል 80% የሚሆን ህዝብ ከውጭ በሚገኘው እርዳታ የሚተዳደር ሲሆን ወያነ ይህን ደካማ ጎናቸውን በመጠቀም እርዳታ ለማገኘት አንድ ሰው ከአንድ አባወራ ለውትድሪና ሰልጠና መመዝግብ አለበት ይላል።

በአፋር ክልል ይህ ህግ ወጥ ድሪግት ተግባራዊ የሚሆነው በአብደፓ የአፋር ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ መሪነት ስሆን በየቀበሌው አስተዳደሮች አማካኝነት ትዕዛዙ ወደ ህዝብ እንዲወርድ እየተረገ ይገኛል።

በአፋር ክልል ባሉ በ32 ወረዳዎች ይህ ጉዳይ ወቅታዊ እና አሳሳቢ ሆኖ ይገኛል።

The post በአፋር ክልል ወጣቶች ለውትድርና በግዴታ እየታፈሱ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: አናናስን ከውሃ ጋር ቀላቅሎ የመጠጣት የጤና በረከቶች

$
0
0

Pineapple with water
በሙለታ መንገሻ

ሁሌም ጠዋት ጠዋት የምንጠጣው ውሃ ውስጥ አናናስ ጨምሮ መጠጣት ለጤናችን ጠቃሚ መሆኑን ይነገርለታል።

ሰውነታችን ጤነኛ እንዲሆን እና በሽታን የመከላከል አቅሙ እንዲጨምር ከፈለግንም ሁሌም ጠዋት ጠዋት የምንጠጣው ውሃ ውስጥ አናናስ ጨምረን መጠጣት ይመከራል።

አናናስ ለጤና ጠቃሚ የሆኑ እንደ ቪታሚን C እና ብሮሜሊን ንጥረነገሮችን በውስጡ በመያዙ ነው ለጤና ተመራጭ የሚያደርገው።

ስለዚህም ቢያንስ ለአንድ ዓመት ያክል ሳናቋርጥ የምንጠጣው ውሃ ውስጥ አናናስ ጨምረን ከጠጣን በጤናችን ላይ ከፍተኛ ለውጥ ልናይ እንደምንችልም ተነግሯል።

ስለዚህም ይህን ውህድ በምንጠጣበት የምናገኛቸው የጤና ጠቀሜታዎችም፦

ለካንሰር እንዳንጋለጥ ይረዳናል

የምግብ መፈጨት ስርዓታችንን ያግዛል

ጤናማ እና ጠንካራ ጥርስ እንዲኖረን ይረዳናል

ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል

የሰውነት መቆጣትን ይከላከላሉ

ጉበታችንን እና አንጀታችንን ለጉዳት ከሚዳርጉ ጥገኛ ህዋሳት ይከላከላል ።

ምንጭ፦ naturalmedicinehouse.com

The post Health: አናናስን ከውሃ ጋር ቀላቅሎ የመጠጣት የጤና በረከቶች appeared first on Zehabesha Amharic.

ወያኔ ሆይ የባሩዱ ሽታ ይሽተታችሁ!!!!! –መርጋ ደጀኔ

$
0
0

መርጋ ደጀኔ  ከ- ኖርዌይ


ወያኔን ከማስተማር አህያን ማስተማር ይቀላል። ምክንያቱም ሂጂ ሲሏት ትሄዳለች ቁሚ ሲሏት ትቆማለች ዙሪ ሲላትም ትዞራለች ወያኔዎች ግን እኛን የሚያቆመን የለም እኛን የሚያዞረን የለም ብለው ደደብነታቸውን በደደብ መሪዎቻቸው እየተናገሩ ኢትዮጵያ ላይ መቀለድ ከጀመሩ 24 ዓመት አለፋቸው። በጣም ስልችት የሚል ቃልና ማንም ኢትዮጵያዊ ያልተቀበላቸው የይስሙላ ቃላቶች በመደርደር እኩልነትን ኢህአዴግ ነው ያመጣው፤ ልማትን ኢህአዴግ ያመጣው ፤ዕድገትን ኢህአዴግ ያመጣው ወ.ዘ.ተ. ወያኔ ያመጣውን የብሔር እኩልነትን ስንፈትሽ በሰላም አቅጣጫ 90% በላይ ቅድምያ የሚሰጠውና ስልጣን የሚያገኘው በየትኛውም ዘርፍ ትግሬ ነው፣ተሰሩ የተባሉትም ፎቆችና ፋብሪካዎችንም ስንቃኝ 90%የወያኔ ሰዎች ናቸው እኩልነት የሚሉት እኩልነት ትግሬኛ ቌንቌ እንደ ማስፈራሪያ እንደመጠቀምያ የደረሰው የወያኔ ቡድን የሚናገረውን በሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደማይቀበለውና ነገር ግን የሚሰማውን የወያኔ ውሸቶች ከመሰልቸቱ አልፎ የሚያናድድ የደደቦች ንግግር መሆኑን ተረድታል።

ከዚህ ቀደም ባሩዱን የሚያስጨሱት እነርሱ ነበሩ፣ መቼስ የወያኔ ባሩድ ያልጨሰበት የኢትዮጵያ ግዛት አለ ብሎ ለመናገር ይከብዳል ፣ሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች በወያኔ ባሩድ የተጎዱ ናቸው፣ቢመከር ቢዘከር  አልመለስ ያለው ወያኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ታግሶ ታግሶ ወያኔዎችን ባሩዱን ሊያሸታቸው በወኔና በሙሉ ልበኝነት የነጻነት ታጋዮች አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔዎች ላይ ባሩዱን ማሽተት ጀምራል፣ በመጀመሪያ የባሩድ ሽታ ላይ ወያኔዎችን ያስደነገጠ እና ያሸበረ ባሩድ በመልቀቅ ቀላል የማይባል የወያኔ ቅጥረኛ ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ አድርገዋል።

ትንቅንቅ ተጀምራል በወያኔዎች መንደር ድንጋጤ ነግሳል ፣የውስጥ ግጭትም አይሏል መክፋፈል ቀጥላል ወታደሩም በሙሉ ልቡ የመታገል ወኔው ጠፍታል፣ በአሁኑ ሰዓት የወያኔ ሀይል ሆኖ እያገለገለ ያለው የወያኔ ሚዲያ የሆነው ETV,ብቻ ነው፣በETVየውሸት ዲስኩር ይደሰኩራሉ እውነቱ ግን ከፍለፊታቸው መጥታል የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ለመቀበልና  ከጎን እንዳልሆነ ስለሚያውቁ ድንጋጤ ውስጥ ናቸው ።

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝባዊ ሀይልም ደግሞ 100% በሙሉ ልብ የሚታገሉ በሙሉ ልብ ወያኔን ለመደምሰስ የቆረጡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰላምና ነጻነት የቆሙ የህዝብ ድጋፍ ያላቸው የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፥

እንግዲህ ወያኔ ሆይ ባሩዱ ይድረሳችሁ የኢትዮጵያ ህዝብ በየቤቱ አኴኩታችሁ እንዳሰቃያችሁት በመደሩም ሄዳችሁ እንደገደላቹሁት ያ መከራና  ሞት፤ እንግልትና እስራት፤ ስደትና ረሃብ፤ አንተም ደጃፍ መጥቷል።

ትግስት ፍራቻ የመሰላችሁ፤ ዝምታ ሞኝነት ያረጋችሁ፤ እናንተን ለመቅበር የኢትዮጵያን ነጻ አውጭዎች ተነስተዋል። የክፋትን ጉድጋድ አርቀህ አትቆፍረው ምክንያቱም አንተ ልትገባበት ትችላለህ የሚባለው ለዚህ ነው አሁን የት ተደብቃችሁ እንደምታመልጡ እናያለን የትኛው ህብረተሰብ መሀል ገብታችሁ መኖር እንደምትችሉ እንመለከታለን በቌንቌ ማስፈራራት የጀመርክ በሙሉ በቌንቌ የሰውን ህይወት ያጠፋህ በሙሉ ስልጣንህን በመጠቀም ጉዳት ያደረሰ ነገ በሙሉ ነጻነቱን በማወጅ ብድራቱን ለመመለስ ወገኔ ተነስታል የባሩዱንም ሽታ ማሽተቱን ጀምራል፣በፍቅር መማር ካልቻላችሁ መከራው እራሱ ያስተምራችሃል በሰላም ህዝብን ማኖር ካልቻላችሁ ሰላም ናፋቂው ህዝብ ያጠፋችሃል።

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ከወያኔ ጉያ በፍጥነት ውጡ ወያኔ ውስጥ ሆናችሁ የወያኔ አገልጋይ የሆናችሁ ከዚህ አገር አጥፊ ጋር ቆማችሁ ሁለተኛ ሞት እንዳትሞት በፍጥነት ውጡ ውድ የመከላከያ ሰራዊት ወያኔ እየሰራ ያለውን ሁላችሁም ታውቁታላችሁ ከራሱ ወገን ውጭ ለሌላው ኢትዮጵያዊ ምንም ግድ እንደሌላቸው ኢትዮጵያን እያጠፋ እንደሆነ ሁሉም የመከለከያ ሰራዊት በደንብ ጠንቅቆ ያውቃል በኢትዮጵያዊያኑ በስተጀርባ ሌላ የነሱ ሰላይ ወይም ሃላፊ  ያለ አግባብ እንደሚያዝህ ታውቃለህ በሌላው ኢትዮጵያዊ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ፈጽሞ ምንም አይነት እምነት እንደሌላቸው ታውቀዋለህ ።

እንግዲህም እናተም ከወያኔ ግዛት ነጻ ወጣችሁ በነጻነት በሀገራችሁ የምትሰሩበት ስራዓትን በማምጣት ከፍተኛ ድርሻችሁን ተወጣችሁ ኢትዮጵያን በማዳን ስራ ላይና ዲሞክራሲያዊ ሀገር ግንባታ ላይ ትሳተፉ ዘንድ ግድ ይላችሃል፣ሌላው ህብረተሰብ ከወያኔ ጉያ በመውጣት ወያኔን አጋልጦ በመስጠትና በማጥፋት ስራ ላይ በመሳተፍ ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ወያኔን ደምስሰን የምንኖርበት ሀገር እንዲኖረን ሁሉም የበኩሉን መወጣት አለበት።

ወያኔዎች ከእንግዲህ በሃላ የኢትዮጵያ እናትና አባቶች ልጆቻቸው በወያኔ ተገለው ልጄ ልጄ ብለው አያለቅሱም ፣ልጆችም እናቴና አባቴን ብለው አያለቅሱም፣የኢትዮጵያ ህዝብ 24 ዓመት ሙሉ ስትገሉና ስታሰቃዩ ትለወጣላችሁ ብሎ በትግስት ዝም ብሎ ነበር አሁን ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ከወያኔ መልካም ነገር ያስባሉ ማለት ጥቁር ድንጋይ ላይ ውሀ አፍስሶ ወደ ውስጥ ይገባል ብሎ እንደመጠበቅ መሆኑን ተረድቷል።

አሁን ግዜው ይቀየራል የመከራው ዘመን ወደ እናንተ ይዞራል የባራዱ ጭስ ወያኔዎች ላይ ይጨሳል ኢትዮጵያዊ ሲያለቅስ ወያኔውና ደጋፊው የሳቁት ሁላ አሁን ተራው ልጄን ልጄን አባት እናቴን ብሎ የማልቀሱ የናንተ ይሆናል ግዜውን ጠብቆ ሁሉም የስራውን ግፍ የእጁን እንደሚያገኝ የታወቀ ነው፣የዘራችሁትን የግፍ ዘር በየተራ ታጭዱታላችሁ ሞት ለዘረኛው ወያኔ

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Comment መርጋ ደጀኔ  ከ- ኖርዌይ

Mergadejene50th@gmail.com

The post ወያኔ ሆይ የባሩዱ ሽታ ይሽተታችሁ!!!!! – መርጋ ደጀኔ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሔኖክ ሰማእግዜር በገዛ እጁ የሳት እራት ሆነ

$
0
0

ለጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ምላሽ 

ከቢላል አበጋዝ፡ ዋሽግቶን ዲ፡ሲ 7/7/15

Voa-amharic-አቶ ደምስ በለጠ “ጋዜጠኛ ሔኖክ ሰማእግዜር ላይ የተደረገውን ወከባ አወግዛለሁ!” በሚለው ጽሁፋቸው ሃሳብ በነጻ ስለመግለጥ፡የዓለም አቀፍ ህግጋትን ጠቅሰው፡የአማሪካ ዜግነትም ለዜጋው የሚደነግገውን መብት አስገንዝበዋል።በዚሁ ባአማሪካ ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ይወጣል።ጠብ ዱላ ፍጽም የለም ማለት አይቻልም።አፍሪካዊ አሜሪካውያን የሆኑት ወይም ጥቁሮች በየከተማው በግፍ የተገደሉ ወገኖቻቸው ስም ጠርተው ይጮሃሉ። በሰላማዊ ሰልፍ ስሜት ይቀሰቀሳል።ከቁጥጥርም ይወጣል። በቅርቡ የወጣ ፊልም “ሴልማ” የተሰኘ ትዝ ይለኛል። እኔም የየካቲት 66 ትወልድ ስለሆንኩ ከልምድ ከትዝታ ነው ግንዛቤ የምወስደው። የኦባማን የኢትዮጵያ ጉብኝት ሊቃወሙ የወጡ ወጣቶች በሔኖክ ሰማእግዜር ጉዳይ ጩኅታቸው ተቀሙ እላለሁ። የአላማቸውን ግዝፈት ከሔኖክ ኢምትነት ጋር እንዲመዘን ፈቀዱ።ስሜት ዋጣቸው።ተንኩሶም ይሆናል ሔኖክ አናውቅም። ብቻ የሳት እራት ሆንዋል።ቪኦኤ ችግር እንዳለበት በግልጽ እያወቀ ለምን መደበው? ምን ተንኮል ነው? እራስዎ አቶ ደምስ አበበ ገላው እንደሞገተው አንስተዋል። ሔኖክ ሰማእግዜር ሆን ተብሎ የቀረበ የሳት እራት ነው። ሰልፈኞቹ አላሰቡትም።ብሽቀት፡እልህ ምሬት። ስሜት አቸንፏቸው ነበር እላለሁ።ልምድ ሊያርመው የሚችል ስተት ነው።

የነበረውን ሰልፍ ሰልፈኛው በልቡ አምቆ የያዘውን ሳናነሳ ህግና ደብን ብቻ መጥቀስ “አታውቁም ላስተምራችሁ” ወደሚል የእብሪት ጎዳና ይወስዳል።እንደምገምተው ሰልፈኛው ንዴቱ በፕሬዚዳንት ኦባማ ላይም ይመሰለኛል።እንዳቶ ደምስ ዜጎች የሆኑ ሁለቴ መርጠዋቸው ተከድተዋል።ፕሬዚዳንቱ ህወሃት ጋር አዲሳባ መሄዴ ነው በማለታቸው። በግሌ ለአካባቢው ሰላም ለኢትዮጵያ ይፈይዳሉ የምለው የለም። ሰልፈኛው ይህን ምክኛት ያደረገ ትኩሳት ያጣዋል? ሔኖክ የሳት እራት ሆንዋል። ምነው ባልሆነ! ስለተመስገን ደሳለኝ፡ስለ እስክንድር ነጋ፡ስለ ርዕዮት፡በግፍ ተይዘው የሚሰቃዩትን ትተን እንደማንኛችን እንጀራ በወጡን ስለሚዚቅ ሔኖክ እንዲወራ ሆነ። ይህ ልጅነት ነው። የፖለቲካ ትግል ውጣ ውረዱ ብዙ ነው። ከስተት ይማሯል። “እኔ በበኩሌ ጨቋኞችን አንስቼ ሌላ ጨቋኞች ትከሻየ ላይ የምጭንበት ምክንያት ስለሌለ ትግሉ ባፍንጫየ ይውጣ።” ብለዋል አቶ ደምስ። መቸስ አፍንጫ ግም ነገርም ይወጣበታል። አቶ ደምስ በለጠ ጨቋኙን ከትከሻቸው የማውጣት የማውረድ ችሎታ አለኝ ብለዋል። ወጣት ታጋዮቹን ዘዴ ቀይሱ።በህብረት፡ክስተት ተማሩ እላቸዋለሁ።የሽምግልና ምክሬ ይህ ነው። በተረፈ የካቲት 66 ውስጤ ያለው ትግል የወንድሞቸ ደም ስላለበት የአካሌ ክፋይ ነው ከውስጤ አይወጣም። “ባፍንጫየ ይውጣ።”  በፍጹም አልልም፤ ወያኔ ሆዳም ሳይሰናበት። አቶ ደምስ ዛሬ እኮ የህወሃትን የመጨረሻ ምእራፍ እያነበብን ነው። መለስ ሲሞት ህወሃት እኮ አብቅቷል። ትግሉ ባፍንጫዎ መውጣቱን መብት ካሉት እሱም ይከበራል። ዝም ማለትም ብልህ ምርጫ ነው።

ወደለላው ትችቴ ሳላልፍ ግልጽ እንዲሆን ልድገመው።ሄኖክ ዝንቡ እሽ መባል አልነበረበትም። ቢሳደብ ቢማታ እንኳን ትዕግስት የሚጠበቀው ክሰላማዊ ሰልፈኞቹ ነወ።

አሁን ወደ ሁለተኛው የምላሼ ክፍል ልሂድ። አቶ ደምስ በለጠ ሔኖክ ሰማእግዜርን አንስተው አልቆሙም።በግራበቀኝ ተቌሞችን የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎችን ተችተዋል። የሚካሄደው ትግል አርቢት ይመስላሉ:: ቢጫ ካርዶች ሰጥተዋል። አንድ ባንድ እንመልከት። እንዲህ ብለዋል።

“ኢሳት ወያኔ ሃሳቤን በነጻነት ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዳላስተላልፍ ከለከለኝ ብሎ የሚከስ ሚዲያ ነው።

የኢሳት አባላት በምን የሞራል የበላይነት ነው ጋዜጠኛውን ሄኖክ ሰማእግዜርን ያን ያህል ወከባ ሊያደርሱበት የቻሉት ?”

ኢሳት ምን አገባው ? የደምስ በለጠ ክስ ጭብጡ የት ነው ? ሰልፉን ያደራጀው የመራው ኢሳት ነኝ አላለም። ሰልፉን አደራጀሁ መራሁት የሚለው የዲሲ ወጣቶች ግብረሃይል ነው። አቶ ደምስ በስተት ይሆን ወይስ እሶም እንደህወሃት የኢሳት ስሙ ሲነሳ ያንገሸግሽዎታል? ኢሳትን ሲከሱ ያቀረቡት ማስረጃ ሰልፈኞቹ የኢሳት ቲ ሸርት ለብሰው ነበር ነው። የስፖርት ፌዴሬሽን ባዘጋጀው በዓል ከኢሳት በብዛት ቲ ሸርት  ሰዎች ገዝተዋል። ወንጀለኛ መሆናቸው ነው? አዝናለሁ ለሔኖክ መብት የምክራከረውን ያህል ለኢሳትም እቆማለሁ። ኢሳት በጥቅል ለሁላችንም ህወሃት ጨርሶ እንዳያፍነን እምቢኝ የምንልበት ተቋም በመሆኑ። አቶ ደምስ ኢሳት ዛሬ የሚያስተዳድሩት ሰዎችም ታዛቢዎችም እንደሚያስተውሉት የህዝብ ንብረት አለኝታ ነው።ስለዚህ አይድከሙ። ወያኔም ታክቷል።

 

አለፍ ብለው ደግሞ ስለአንዱ የሳምንት መጨረሻ የራዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅ መበደል ያወሳሉ። ስለ አበበ በለው። እዚህ በሰፊው ማቅረብ ከገዘፈው ያገራችን ችግር ይልቅ በአንድ የሳምንት መጨረሻ ቱሪናፋ ላይ ማተኮር ይሆናል። የጠቀሱት ኢንተርቪው (እነ ልኡል ቀስቅስንና እነጋዜጠኛ ክንፉ አስፋን )እንዳቀረበ ያደረግከው ደግ አይደለም። አንዱን ወገን ብቻ ይዞ አይቀርቡም ተብሎ ተተችቷል። “አበበ በለው ራሱ ባይልክልኝም ጉዳዩን አስመልክቶ ለነአምን ዘለቀና ለብርሃኑ ነጋ የጻፈው ደብዳቤ ደርሶኛል በጎንዮሽ።”  ብለዋል አቶ ደምስ። ይህ አርበኞች ግንቦት 7ን ሊጎሽሙ ውስጥ ውስጡን የሚሰሩ ያስመስልዎታል። አርበኞች ግንቦት 7 ጋር ምን አጋፋዎት ?ለኢትዮጵያ የሚቆረቆሩ ከሆነ ለህወሃትና በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ በሚገቡ ላይ ይበርቱ::

በመጨረሻ “በአጠቃላይ የሰዎችን የማይሻርና የማይገሰስ መብት የማክበር ልምድ ይኑረን።” ብለዋል:: አሚን። አላህ ጤናዎን ይስጥዎት።

The post ሔኖክ ሰማእግዜር በገዛ እጁ የሳት እራት ሆነ appeared first on Zehabesha Amharic.


ወዴት እየሄድን ነው? ለኢህአፓ ሲምፖዝየም የቀረበ (ክፍሉ ታደሰ)

$
0
0

 

kiflu tadesseዛሬ፣ የኢትዮጵያን ህልውና የሚፈታተኑ፣/ መኖሯን የማይሹ፣/ ከቻሉም የየራሳቸውን የጎጥ መንግስታት ለማቋቋም የሚፈልጉ ኃይሎች አጋጣሚው እስከሚፈጠርላቸው እየጠበቁ ነው።

ዛሬ ኢህአዴግ በሚከተለው ፖሊሲ ኢትዮጵያ ለክፋ አደጋ እየተጋለጠች ነው።

ዛሬ፣ በዘር የተደራጁ ኃይሎች አመቺ አጋጣሚ እየጠበቁ ናቸው።

ዛሬ እነ አይሲስና መሰል ኃይሎች ምን እንዳዘጋጁልን አናውቅም። አርፈው እንደማይተኙ ግን የተረጋገጠ ነው። እናም/ ኢትዮጵያዊው ባለቅኔና ደራሲ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ በኢጣሊያን ወረራ ዘመን የቋጯትን ስንኝ ጠቅሼ፣/ ያለፈውን መሰረት ያደረገ፣/ የዛሬውን የሚመለከተውንና ስለነገው የሚጠቁመውን ንግግሬን እጀምራለሁ።

አገሬ ተባብራ ካልረገጠች እርካብ፣

ነገራችን ሁሉ የእንቧይ ካብ፣/ የእንቧይ ካብ፣ ብለዋል።

  • ከ40 አመት በፊት የተጀመረው የለወጥ እንቅስቃሴ ዛሬም ዕልባት አላገኘም። በዚያ ዘመን የተነሱ ጥያቄዎች ገሚሱ መልካቸውን ቀይረው እንደገና ቀርበዋል። ታሪክ ፖለቲካ፣ ፖለቲካም ታሪክ የሆነበት ወቅት ላይ ደርሰናል። በተለይ አፄ ምንሊክ፣ የተፋላሚ ሀይሎች አጀንዳ የሆኑበት ወቅት ነው።
  • የአፄ ምንሊክ አስተዳደርና አገዛዝ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ የወሰዱት እርምጃ ስለሆነ አበጀህ ሊባሉ ይገባል ይላል የመጀመሪያው ወገን። የዚህ ተጻራሪው ክፍል፣ ነፃ የነበሩ መንግስታትን በመጨፍለቅ ሸዌው አፄ ምንሊክ ‘ቅኝ ግዛታቸውን’ አስፋፉ፣ እሳቸው በነገሱበት ዘመን የቅኝ ገዢዎች አፍሪቃን የሚቀራመቱበት ጊዜ በመሆኑ፣ የቅርጫው ተካፋይ ለመሆን በቁ ይላል።
  • ከዚህ በተጨማሪ፣ የአፄ ምንሊክንም ሆነ በዙሪያቸው የነበሩ ረዳቶቻቸውን የዘር ግንድ በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል። ልክ ሊሆኑም ላይሆኑም ይቻላሉ። ዋናው ቁም ነገር ግን፣ እነዚህ የታሪክ ሰዎች ያጠፏቸውም ይሁን ያለሟቸው ስራዎች ከዘር ግንዳቸው ጋር የተያያዙ አልነበሩም። ራስ ጎበና ዳጬ የኦሮሞ/አማራ፣ ፍትአውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ቢነግዴ የጉራጌ/የኦሮሞ፣ ወይም የአማራን የበላይነት ለማንገስ አልተሰለፉም። አጼ ምንሊክም ሆኑ ረዳቶቻቸው የኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ የታሪክ ውጤት እንደመሆናቸው እነሱ ሳይሆኑ ኢትዮጵያን የፈጠሯት፣ ኢትዮጵያ እነሱን አስቀድማ ፈጥራቸዋለች፣ ኢትዮጵያዊ ማንነትን ተላብሰዋል። ስለሆነም፣ የዚያን ዘመኑን ሁኔታ የሚመረምሩበት፣ የሚመለከቱበትና የሚለኩበት መነጽር በዘር ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነታቸው ላይ የተመረኮዘ ነበር ማለት አግባብ አለው።
  • አፄ ምንሊክም ሆኑ ረዳቶቻቸው ኢትዮጵያዊነታቸው የተረጋገጠው በ19ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያን ብለው አድዋ በዘመቱበት ጊዜ ነበር። ኢትዮጵያዊነት እነ አፄ ምንሊክን ይቀድማል ሲባል አንድም አድዋን በማስታወስ ነው። የአንድ አገር ህዝብ አንድነትም ሆነ የጋራነት በውል ሊገለጽ የሚችለው በተለይ ሀገርን በሚመለከተ ከሚነሳ ጦርነት ጋር ነውና።
  • በእርግጥ፣ አፄ ምንሊክ ሥልጣን በያዙ ማግስት ነበር ህልማቸውን ለማሳካት፣ ግዛታቸውንም ሆነ መንግስታቸውን ማስፋፋት የጀመሩት። በካሄዷቸው ዘመቻዎች፣ አንዳንዶቹን በወድ አንዳንዶቹን በግድ አስገብረው በቁጥጥራቸው ስር አድርገዋል።
  • የያ ትውልድ ቀዳሚ መሪዎች ወደ ፖለቲካ መድረኩ ብቅ ባሉበት ወቅት፣ በአፄ ምንሊክም ሆነ ከእሳቸው በፊት የተፈጸሙ ታሪካዊ ኩነቶች አእምሮአቸውን በመፈተናቸው ደግ ደጉን ወርሰው ክፉውን ማስወገድ እንዳለባቸው አመኑ። ጠባሳዎቹ ይሽሩ ዘንድ የትውልድ ግዴታና ሃላፊነት ተረከቡ። መፍትሄ መሻትም ጀመሩ።
  • የያ ትውልድ አባላት፣ የሕዝቦች የእኩልነት መብት መከበርና የኢትዮጵያ ህልውና እና ኢትዮጵያ እንደ አገር ፀንታ መቆየት የማይነጣጠሉ መሆናቸውን በመረዳት አምርረው ታገሉ። ወታደራዊ መንግስት ጥያቄውን በነፍጥ ለመፍታት በማሰቡ፣ ያ ትውልድ ያቀረበውን አማራጭ፣ ትጥቅ አስፈቺና መርዘኛ ነው ብሎ አመነ። ከዚያም፣ ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ሂዶ ቀይ ሽብር ተወለደ። በአንፃሩ ደግሞ፣ የያ ትውልድ አካሄድ ያልተመቻቸው ብሄረተኛ ኃይሎች፣ የየራሳቸውን መንግስት ለማቋቋም በሚያደርጉት ጥረት፣ እንቅፋት ነው ብለው የቆጠሩት ሕብረ ብሄራዊ መርሃ ግብርንና ያስተናግዱ የነበሩትን የያ ትውልድ አባላት እንደጠላት ቆጠሩ። ሕብረ ብሄራዊ ኃይሉ ህ/ሰባዊ መሰረታቸውን እንዳይንድ በመስጋት ከወታደራዊ መንግስቱ ባላነሰ በጠላትነት ፈረጁት። “…ሶስት ገጽታ በነበረው የትግል ሂደት ውስጥም፣ ሕብረ ብሄራዊ ኃይሎች በወታደራዊው አገዛዝ ጨካኝ የእመቃ ዘመቻና በብሄርተኛ ኃይሎች አፈና…አጣብቂኝ ውስጥ ገቡ።…ወታደራዊው አገዛዝና ብሄረተኛ ኃይሎች…ሀገሪቱ እንዳትበታተን ድጋፍ ሊሰጥ የሚችለውን አንድ ኃይል ኢትዮጵያ እንድታጣ አደረጉ።” (ያ ትውልድ፣ ቅጽ 3፣ ገጽ 431) የያ ትውልድ አባላትም በምዕራብ ሶማሌ ድርጅት፣ በወያኔ ሃርነት ትግራይና በሻዕቢያ እጅ ወደቁ።
  • ሕብረ ብሄራዊው ኃይል ሲዳከም፣ መድረኩ ለወታደራዊው መንግስትና ለብሄረተኛ ኃይሎች ተለቀቀ። ጉልበትና መሳሪያ የነበረው የበላይነት እየያዘ ሄደ።
  • በዚህ ወቅት፣ ትግሉ መልኩን ቀይሮ፣ ኢትዮጵያ የቀዝቃዛው ጦርነት አካል ሆና አሜሪካና የቀድሞዋ የሶቭየት ሕብረት ጡንቻቸውን የሚፈትሹባት አውድማ ሆነች። በሶስት የሚፈረጅ አዲስ የኃይል አሰላለፍም ገሀድ ሆነ፤ በዚህ አሰላለፍ መሰረት፤ 1/ ሶቭየት ህብረትና አጋር አገሮች እንዲሁም ደርግ በአንድ ወገን፣ 2/ የምዕራቡ ዓለምና የቀድሞ የገዢ መደብ አባላት እንዲሁም ብሄረተኛ ሃይሎች በሌላ፣ 3/ በነፃነት ይንቀሳቀሱ የነበሩና ከማንም ያልወገኑ ሶስተኛ ሆነው ተሰለፉ። በዚህ በሶስተኛው ስብስብ ስር በአጠቃላይ የያ ትውልድ አባላት ይገኛሉ።
  • እንደ ኢህአፓ ከሁለቱም ኃይሎች ሳይወግኑ በነፃነት ትግላቸውን ለማካሄድ የወጠኑ ኃይሎች ‘ድንጋይ ተሸክሞ የአቀበት ጉዞ’ ሆነባቸው።
  • የምዕራቡ ኃይል መጀመሪያ ላይ የቀድሞ የገዢ መደብ አባላትን ደገፈ። እነዚህ ኃይሎች የሰንበሌጥ ምርኩዝ ሲሆኑበት፣ በመጎልበት ላይ ወደነበሩት ብሄረተኛ ድርጅቶች ፊቱን አዙሮ፣ ከሱማሌ መንግስት ጎን በመሰለፍ ኢትዮጵያን በሚቻለው ሁሉ ጎዳ። ይህ እርምጃም፣ የምዕራቡ ኃይል የብሄረተኛ ሃይሎችን አጀንዳ ደግፎ መውጣቱንና ኢትዮጵያዊነት አደጋ ላይ መውደቁን የሚጠቁም ሲሆን፣ በአንፃሩ ደግሞ የሶቭየት ህብረትና አጋሮቹ፣ ኢትዮጵያን በመሳሪያ ሃይል አንድ ለማድረግ ቆርጦ ለተነሳው ደርግ ሙሉ ድጋፍ ሰጡ። ሁለቱም ያለ የሌለ መሳሪያ አራገፉ። ገንዘብ በገፍ ረጩ።
  • የምዕራቡ እርዳታን በተመለከተ የህወሃት መሪ ከነበሩት አንዱ አቶ ገብሩ አስራት በቅርቡ ባወጣው መጽሀፍ፣ “…ምዕራባዊያን በተለይ ከ1977 ዓም ጀምሮ ስፍር ቁጥር የሌለው እርዳታ ለህወሓትና ለሕዝቡ ለግሰዋል።…የተለያዩ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች የቁሳቁስና የገንዘብ እርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶችና መንግሥታት ቁጥራቸው እየጨመረ ሄዶ ነበር” ሲል ያብራራል። (ገብሩ አስራት፣ ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ፣ ገጽ 145)
  • የሶቭየት ስትራቴጂ አንድ ወጥ ሲሆን፣ የደርግ ጠላት ጠላታችን ነው ብለው በመቁጠር በሙሉ ኃይላቸው ከጎኑ ተሰለፉ። በአንጻሩ፣ የአሜሪካ መንግስት አካሄድ መንታ ስትራቴጂ ላይ የተመሰረተ ነበር። በአንድ በኩል፣ በታዛዦቹ በሱዳን፣ ሳዓውዲ አረብያና በሌሎች መንግስታት አማካይነት የደርግ መንግስትን ለመገልበጥ ተቃዋሚዎችን ረዳ። በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ጦር ምስጥ እንደበላው እንጨት ከውስጥ በራሱ እንዲገነደስ ለማድረግ ብዙ ጣረ። የ1981 ዓም መፈንቅለ መንግስትን ልብ ይሏል!
  • የምዕራቡ ኃይል የበላይነት እየያዘ ሄደ። በ1983 ዓም ለሁለተኛ ጊዜ ማዕከላዊ መንግስቱ ተዳከመ። ሁለቱ ጉልበተኛ ብሄረተኛ ኃይሎች፣ ህወሃትና ሻዕቢያ፣ መንግስት መሰረቱ። ኢትዮጵያም ተከፈለች፤ ወደብ አልባም ሆነች። ኢህአዴግ ሥልጣን በያዘ ማግስት በርካታ ብሄረተኛ ድርጅቶች ተፈለፈሉ። ብሄረተኝነት የመንግስቱ ርዕዮትና ፖለቲካ ሆነ።
እኛና እነሱ – ልዩነቶቻችንና አንድነታችን
እኛ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አንድነት አልን። እነሱ በልዩነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ አራመዱ።
እኛ የኢትዮጵያን አንድነት ሰበክን። እነሱ የኢትዮጵያ ሕዝቦችን ልዩነት ሰበኩ።
እኛ የኢትዮጵያ ሕዝቦችን ከሚያለየያቸው የሚያመሳላቸው ይበልጣል አልን። እነሱ ከሚያመሳስላቸው የሚያለያያቸው ይበልጣል አሉ።
እኛ ሁሉንም የኢትዮጵያ ሕዝቦች የሚያመሳስለውና አንድ የሚያደርገው የመደብ ትግል ነው አልን። እነሱ ሁሉም ብሄረሰቦች ለየራሳቸው ዘብ መቆም አለባቸው አሉ።
እኛ በሥርዓት ላይ ያተኮረ ትግል አደረግን። እነሱ በአማራው ላይ ያተኮረ ስብከት አካሄዱ።
እኛ ፊውዳሊዝምና ኢምፔሪያሊዝም ዒላማዎች ናቸው አለን። እነሱ አማራውን ዒላማ አደረጉ።
እኛ ለኢትዮጵያ ታገልን። እነሱ በየብሄረሰባቸው ላይ አተኮሩ።
እኛ ኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ ባለታሪክ ናት አልን። እነሱ የመቶ አመት ታሪክ ነው ያላት አሉ።
እኛ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ናት መፍትሄውም በኢትዮጵያ የፖለቲካ ቢጋር ክልል ሊታይ  ይችላል አልን። እነሱ ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ናት አሉ።
እኛ የኦሮሞም ሆነ የተቀሩት ሕዝቦች የእኩልነት መብት የሚከበርበት ሥርዓት መዘርጋት አለበት አልን። እነሱ ኦሮምያ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነው አሉ።
እኛ የኢትዮጵያ ታሪክ ከአክሱምና ከዚያ በፊት የዘለቀ ነው አለን።  እነሱ አክሱም ሌላውን አይመለከትም ለወላይታው ምኑ ነው አሉ።
ሁለቱ ሃይማኖቶቻችን፣ ፊደላችን፣ የኢትዮጵያ ኦፊሴላዊ ቋንቋ የሆነው አማርኛ፣ ሸማን የመሳሰሉ ባህላዊ አለባበሶቻችን፣ የተቀየጠው ኢትዮጵያዊ ገጽታችን፣ ጤፍን የመሰለው በየትኛውም አገር የማይበላው ምግባችን፣ የኢትዮጵያ መንፈሳዊም ሆነ ዘመናዊ ያሬድያዊ ሙዚቃችንና የመሳሰሉት መሰረታቸው አክሱም ነው። የኢትዮጵያ ማንነት ተለይቶ ማህተም የተደረገበት ከአክሱም ጊዜ ጀምሮ ነው እልን።  እነሱ ኢትዮጵያ አፄ ምንሊክ በጉልበት ጠፍጥፈው የፈጠሯት አገር ናት አሉ።
እኛ የኢትዮጵያ ታሪክም ሆነ የዓለም ታሪክ በዲሞክራሲ አልተገነባም። አማራው ከትግራዩ፣ ኦሮሞው ከሲዳማው፣ ኦሮሞው ከአማራው፣ ክርስቲያኑ ከሞስሊሙ፣ ወዘተ ሲስማማ፣ ሲዋጋ፣ መልሶም ሲስማማ፣ ሲገዛ፣ ሲገዛ፣ ሲወር፣ ሲወረር፣ ሲያጠፋ፣ ሲጠፋ የዘለቀ ታሪክ ነው እንላለን። እነሱ ታሪካችን በአፄ ምንሊክ ጭፍጨፋ ይጀምራሉ ይላሉ።
እኛ ኢትዮጵያን በብሄረሰብ ሳንለያይ፣ አርሶ አደሮችና ላብአደሮች ይቀድማሉ አልን። እነሱ የተመረጠ ብሄረሰብ ይቅደም ይላሉ።
እኛ ፍትሃዊ የሀብት ሽግሽግ ይደረግ አልን። እነሱ ሀብት በተመረጡ ብሄርተኛ ልሂቃን እጅ እንዲገባ እያደረጉ ናቸው።
እኛ ኢትዮጵያ አፄ ምንሊክን ፈጠረች አልን። እነሱ አፄ ምንሊክ ኢትዮጵያን ፈጠሩ ይላሉ።
እኛ አፄ ምንሊክ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ሥርዓተ-ታሪክ ተከትለው የገበረውን በሰላም አሻፈረኝ ያለውን በጉልበት ገዙ አልን። እነሱ፣ በተለይ ክፉው ታሪክ በአፄ ምንሊክ ዘመን ተጀመረ አሉ።
እኛ አፄ ምንሊክ የክፉ ታሪካችን ተቋዳሽ ቢሆኑም፣ የአድዋ ባለቤትና የነፃነት ቀንዲላችን ናቸው አልን። እነሱ አፄ ምንሊክ ከፊል ግዛታቸውን ለቅኝ ገዢዎች አሳልፈው የሰጡ የቅኝ ገዢዎች አጋር ናቸው ይላሉ።

 

  • ባለፉት 25 አመታት፣ ባለሀብቶች ትላልቅና ዘመናዊ ሕንፃዎች ገንብተዋል። በርካታ መንገዶችም ተዘርግተዋል። የትምህርት ይዞታው እጅግ ቢዳከምም፣ በርካታ ትምህርት ቤቶች ተከፍተዋል። ብዙ የጤና ጣቢያዎች ተቋቁመው፣ በወሊድና በመሳሰለው ሊመጣ የሚችለው በሽታ በመጠኑ ሊቀረፍ ችሏል። የቤት ችግርን በመጠኑም ቢሆን ለማስወገድ እየተሞከረ ነው። በውጭ እርዳታና በምሁራን ትብብር ጭምር፣ በካታራክትና በሌሎች በሽታዎች ይጠቁ የነበሩ ዜጎች እርዳታ አግኝተዋል። ይሁንና፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የለውጥ ሂደት ከጀመረ 40 አመት ቢያስቆጥርም፣ አርቲስት ቴዲ አፍሮ እንዳለው፣

በ17 መርፌ፣ በጠቆመው ቁምጣ

ለለውጥ ያጎፈረው፣ ዙፋን ላይ ሲወጣ፣

እንደአምናው ባለቀን ሌላውን ከተካ፣

አዲስ ንጉስ እንጅ ለውጥ መቼ መጣ፤ እንላለን።

  • ዛሬም፣ 87 በመቶ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በኑሮ ጠርዝ ላይ (deprivation) እንደሚገኙ መልታይ ዳይሜንሽናል ፖቨርቲ ኢንዴክስ የተባለው የዓለም ባንክ ድርጅት ይገልጻል። (UNDP) የተባለ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካል፣ ከድህነት ጠርዝ በታች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከ25 ሚሊዮን በላይ እንደሆነ ያሳያል። በዩኒሴፍ መሰረት 5 ሚሊዮን እጓለ ምዑታን ይገኛሉ።
  • ዛሬ፣ የዕቃዎች ዋጋ አይቀመስም፡፡ ሠራተኞች ከወር ወር መድረስ የሚችሉት በተዓምር ነው ማለት ይቻላል። ብሩ መቅኖውን እያጣ ሄዷል። ድህነቱ እየከፋ በመሄዱ፣ ጥቂቶች ከሚገባው በላይ ሀብታም ሆነዋል፣ በሚሊዮናት የሚቆጠሩ ብዙሃኑ ደግሞ ደህይተዋል። ዛሬ ከድህነት ጠርዝ በታች በሚገኘው ዜጋና ትንሽም ብትሆን ሰርቶ በሚያድረው መሀል ያለው ልዩነት ጠቧል። ሁለቱም ወገኖች ተርበዋል። ታርዘዋል። ሁለቱም መናጢ ደሀ ሆነዋል። ድህነት ክፉ ነው። ያጨካክናል።

 

  • በእርግጥ ጥቂቱ ደግሞ እጅግ ከብረዋል። በተለይ ነጋዴዎች። የንግድ ስርዓቱ የተዛባና ፍትሃዊ ባለመሆኑ ሁሉም ነጋዴ አይደለም የከበረው፣ ወይም የሚከብረው። ከገዢው ፓርቲ አባላትና ከመንግስት ጋር የተቆራኘው ነው በልቶ እያበላ፣ ስኳር ልሶ እያላሰና መንግስታዊ መዋቅሩን እያነቀዘ በአቋራጭ የሚከብረው።
  • ሃይ ባይ በሌለበት ሁኔታ ሙስናው ሰፍቷል። ትላልቅ የመንግስትና የገዥው ፓርቲ አባላት ሳይቀሩ በሙስና በመዘፈቃቸው ወህኒ ወርደዋል።
  • ዛሬ ዛሬ፣ ኢትዮጵያም ሆነች ሌሎች የአፍሪቃ አገሮች፣ የሩቅ ምስራቅ፣ በተለይም የቻይና የሸቀጥ ማራገፊያ ሆነዋል። አገር በቀል ኢንዱስትሪዎች በርካሽ የሚገቡ ዕቃዎች ዋጋን መወዳደር ስለማይችሉ ይከስራሉ። ጥገኝነታችንም እየሰፋና እየከፋ በመሄድ ላይ ነው።
  • የቤት ኪራይም የሚቀመስ አልሆነም። አብዮታዊ ዴሞክራሲም ተባለ ዴቬሎፕመንታል ዴሞክራሲ፣ የሲዖል በሩ ብርግድ ብሎ ተከፍቶ ዜጎች እየተንደረድሩ እየገቡበት ናቸው።

 

  • አርሶ አደሩ የመሬት ተጠቃሚ ቢደረግም፣ ዛሬ ኑሮው ከፍቷል። ከአርባ አመት በላይ የያዛት መሬት ለልጅና ለልጅ ልጅ ተሸንሽና ተመናምናለች። በማዳበሪያ ስም ዕዳ ተሸካሚ ሆኗል። በዲቬሎፕመንታል ዴሞክራሲ ስም የሚፈናቀሉት ቁጥርም በርካታ ነው።

 

  • የእምነት መብት ሊከበር ይገባል። ስለዚህ ጉዳይ ዱሮ ተናግረናል። ይሁንና፣ የኢህአዴግ መንግስት የሁለቱ ታላላቅ ሃይማኖት ተከታዮችን አስከፍቷል። በአንፃሩ ደግሞ ከሁሉም ወገን አክራሪዎች እየተፈጠሩ ነው።

 

  • ከጥቂት አመታት በፊት ወደ ሻሸመኔ በመጓዝ ላይ ሳለን፣ ጥቅም ላይ ያልዋሉና ሳር ያበቀለባቸው በርካታ መስጊዶች ተመለከትን። በካባቢዎቹ ብዙ ነዋሪዎች አላየንም። ቢኖሩም፣ እነዚያን የመሳሰሉ ዘመናዊ መስጊዶች ለማሰራት አቅም አላቸው ብሎ መገመት ይከብዳል።
  • እነዚያ መስጊዶች ዛሬ ጥቅም ላይ ውለው እንደሁ አላውቅም። ግን በርካታ ወጣት ሙስሊሞች ዋሃቢዝም የተባለ ጽንፈኛ እምነት ተከታይ ሆነዋል። በእርግጥ እምነት እምነት ነው። ሰው የፈለገውን የማመን መብቱ ሊከበር ይገባል። ጉዳዩ አሳሳቢ የሚሆነው በእምነት ስም የሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ላይ ጥቃት ሲደረግ ነው። ይህ ዝንባሌና አካሄድ በዓለም ዙሪያ በዝቶና ተባዝቶ ዛሬ እነ አይሲስን የመሳሰሉ ትናንት ያልነበሩ ጉልበተኞች በቅለዋል። ኢራቅ፣ ሊብያ፣ የመንና ሶሪያ እየወደሙ ናቸው። ሕዝቦቻቸውም ተፈናቅለዋል።

 

  • ፊታችንን ወደ ኢትዮጵያ ሁኔታ መለስ ስናደርግ፣ ከ1997 ዓም ምርጫ ውጤት በኋላ፣ የኢህአዴግ መንግስት የፖለቲካ ምህዳሩን እያጠበበ በመሄድ ላይ ሲሆን፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ነፃነታቸው ተገፏል፣ ከምርጫው በፊት አንፃራዊ ነፃነት ኖሮት ይንቀሳቀስ የነበረው ሚድያ እስከነአካቴው በመዘጋት ላይ ነው። የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ የሚደርሰው ወከባና እንግልት ቀላል አይደለም። የገጠርም ሆነ የከተማው ሕዝብ አንድ ለአምስት በሚለው አሰራር መሰረት እንዲሰናሰል ተደርጎ፣ የመንግስት ጆሮ በሁሉም ቤት ለመግባት በመሞከር ላይ ይገኛል።

 

  • ኢህአዴግ የሚከተለው የፖለቲካ አካሄድ ምን ሊያስከትል እንደሚችል በሶስት ከፍሎ ማየት ይቻላል።

 

  • አቅጣጫ ወይም ሲናርዮ 1 – የኢህአዴግ ‘ዲቨሎፕመንታል ዴሞክራሲ’ ሰራ ላይ ውሎ አገሪቱ በኢኮኖሚ ትበለጽግና እንደተተለመው በ2025 ሰፊ መካከለኛ መደብ ተፈጥሮ ኢኮኖሚውን ሊሸከም ይችላል። ዲቨሎፕመንታል ዴሞክራሲ የካፒታሊዝም ሌላ መጠሪያ ሲሆን፣ በመንግስት ከፍተኛ ተሳትፎ ሊፈጠር የሚችል ካፒታሊዝም ነው። በአሁኑ ሰዓት፣ ዲቬሎፕመንታል ዴሞክራሲን መሰረት አደረግሁ በሚለው የዕድገት እቅድ መሰረት፣ የሚቋቋሙት ፋብሪካዎች ገቢ ንግድ የሚተኩና የውጭ ንግድ ላይ የሚያተኩሩ ይሆናሉ። (import substitution and export oriented economy ይሉታል)

 

  • የዲቬሎፕመንታል ካፒታሊዝም ተምሳሌ ሆነው የሚጠቀሱት እነ ኮርያ፣ ሲንጋፖርና ሌሎች “the four tigers” በመባል የሚታወቁት አገራት የደረሱበት ደረጃ ሊደርሱ ከቻሉባቸው ዋነኛ ምክንያቶች መሀል አንዱ አገራዊና ብሄራዊ ራዕይ አራማጅ መንግስታት የበላይነቱን መያዛቸው ሲሆን፣ ዘር ላይ የተመሰረተ ራዕይም ሆነ አተያይ አንግቦ፣ አንዱን አራቁቶና ሌላውን ሸልሞ እደገትም ሆነ ዴሞክራሲ አይመጣም።

 

  • ለእድገታቸው ምክንያት የሆነው ሌላው ጉዳይ ደግሞ፣ የአሜሪካና የጃፓን በአጠቃላይም የምዕራቡ ዓለም ከቻይናና እና ከሶቭየት ሕብረት ጋር ያደርግ በነበረው ትንቅንቅ፣ በእነዚህ አገራት ውስጥ ለካፒታል ክምችት (capital accumulation) የተመቻቸ ሁኔታ መፍጠሩ ነበር። የኢትዮጵያ ሁኔታን ስናይ፣ ካፒታል የአገሪቱን ሰማያት አቋርጦ መኮብለል ከጀመረ ሰንባብቷል።

 

  • ለካፒታሊዝም ዕድገት ቁልፍ ከሆኑት ጉዳዮች መሀል አንዱ የተማረ ሰው መኖር ሲሆን፣ እጅግ ብዙ ምሁራን አገሪቱን ለቀው በመሄድ ላይ ናቸው። በአጭሩ፣ ዲቬሎፕመንታል ካፒታሊዝም ነፍስ ዘርቶ ማየት አዳጋች ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ራሷን መቻል እንኳን ሊሳናት ይችላል።

 

  • አቅጣጫ ወይም ሲናርዮ ሁለት – ኢህአዴግ ህይወት ያለው የምርጫ ፖለቲካ እንዲካሄድ ሊያደርግ ይችላልን? በ1997 ዓም ኢህአዴግ ከገበየው ሙከራ በኋላ ያን ዓይነት ምርጫ ይደገማል ብሎ መገመት የዋህነት ነው። የዚያ ምርጫ መጨናጎል እስከዛሬ ድረስ ህዝቡን የዕዳ ከፋይ አድርጓል። ይህ ሁኔታ የተፈጠረው ደግሞ በኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን በተቃዋሚ ኃይሉም ጭምር ነው። ከ1997 ዓም በኋላ ባሉት አመታት ኢህአዴግ የሀገሪቱን የፖለቲካ አድማስ እያጠበበ በመሄድ ላይ ሲሆን፣ የፖለቲካ ምህዳሩ ሊሰፋ የሚችለው በኢህአዴግ በጎ ምኞትና ፍላጎት አይሆንም። በንግዱ፣ በፖለቲካው፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች፣ በሚድያው፣ ወዘተ የተሰማሩ ኃይሎችና የሕዝቡ የዕምቢተኝነት መንፈስ ሲጎለብት፣ ድምጻቸውን ማሰማት ሲችሉና መንግስቱን ሲያስገድዱ ብቻ ነው።
  • አቅጣጫ ወይም ሲናርዮ ሶስት – ኢህአዴግ አሁን በጀመረው ሂደት ከቀጠለ ወደ ፍጹም ብሄረተኛ አምባገነናዊ አገዛዝነት ይቀየራል። በጉልበት አሰራር ላይ የተመረኮዘው ይህ አካሄድ የማያዋጣ ሲሆንና ውጥረት እየጨመረ ሲሄድ የዘርና የፖለቲካ ካርዱን በመምዘዝ ኢህአዴግ አንዱን ከሌላው ሊያናክስ ይችላል። ኢህአዴግ ወታደራዊና የፀጥታ ኃይሉን እንዲሁም አለአግባብ ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ በሚያገኘው ገንዘብ በመጠቀም ህ/ሰቡን በማያላውስ ፖለቲካ ተብትቦ እንዲቆይ አድርጓል፣ ያደርጋልም። የኢህአዴግ የጉልበት ፖለቲካ ከኢኮኖሚ ችግሮች ጋር ተዳምሮ ስር የሰደደ እምቢተኝነትና አመጽ እንዲያረግዝ ያስገድዳል። ኢህአዴግ የሚከተለው ይህ ፖለቲካ መጨረሻው የኢህአዴግ መቃብርን የሚቆፍር ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያም አስከፊ ሁኔታ ሊገጥማት ይችላል። በየቦታው አመጽ ይበረታል፣ ረሃብ፣ ፍትሃ አልባነት፣ ጎሰኛነት፣ የሃይማኖት አክራሪዎች መንገስ፣ ወዘተ ሊከተል ይችላል። በሱማሌ፣ ሊብያ፣ ኢራቅ፣ የመን ላይ ያጠላው ጥቁር ደመና ወደ ኢትዮጵያ ሰማዮችም ይዘልቃል።

 

  • የኢህአዴግ አምባገነናዊ አገዛዝን በመቃወም ከሥልጣን እንዲወርድ በትጥቅ መፈታተን ይቻላል። የትጥቅ ትግል ለማካሄድ መሟላት ስላለባቸው ዝግጅቶች መዘርዘር ቢቻልም፣ ዋነኛው ጉዳይ ግን የዛሬ 40 አመት የነበረችው ኢትዮጵያ ዛሬ አለመኖሯን መረዳት ነው። ኢህአዴግ ሥልጣን ሲይዝ የተወለዱ፣ በዘር ፖለቲካ ተከትበውና ተጠምቀው ካደጉ ዜጎች መሀል አንዳንዶቹ መተካካት በሚለው መርህ መሰረት ለሥልጣን እየበቁ ናቸው። የሕብረ ብሄራዊ ፖለቲካ አራማጅ ወገኖች ቢኖሩም፣ የኢህአዴግ ደጋፊም ሆኑ ተቃዋሚ ብሄረተኞቹ ቁጥር በቀላል የሚገመት አይደለም።

 

  • ያም አለ ይህ ግን፣ ኢህአዴግ የሚከተለው የግፍ አገዛዝ አይቀጥልም። ውጥረቱ እያየለ ሲሄድና ማዕከላዊው መንግስት ሲዳከም ህብረ-ብሄራዊ ኃይሎች ሳይሆኑ በርካታ የጎጥ ባለነፍጠቾ ሊፈለፈሉ ይችላሉ። ማዕከላዊ መንግስት ለስሙ ቢኖርም፣ ባለነፍጦቹ ራሳቸውን የቻሉ መንግስታት ይሆናሉ። እነዚህ ቡድኖች 10ሺህና መቶ ሺህ አባል ያላቸው መሆን አይኖርባቸውም። ማዕከላዊ መንግስት ሲዳከም፣ 2000ሺህ እና 3000ሺህ ጦር ያለው የየአካባቢው ጉልበተኛና አድራጊ ፈጣሪ ይሆናል።
  • ሌላ መረሳት የሌለበት ጉዳይ፣ አብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል የኢይሲስ ካርታ አንድ አካል ሆኗል። ነገ ማዕከላዊ መንግስቱ ቢዳከም፣ አይሲስም ሆነ ካባቢያዊ የአክራሪ ሃይማኖት ድርጅቶች ወይም እንቅስቃሴዎች ኢትዮጵያ ጉዳይ ውስጥ በነፍጥ ጭምር እጃቸውን ሊያስገቡ ቢችሉ ሊያስገርም አይችልም። ያ ደግሞ በፊናው ጥቃት ሊደርስብኝ ይችላል ብሎ ከሚያስብና ከሚያምን ሌላ ወገን፣ በተለይም ከክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በኩል ተመሳሳይ ዝግጅት ሊደረግ እንደሚችል መገመት አይከብድም። ይህ ሁኔታ የሚያስገነዝበን፣ ኢትዮጵያ የማያባራ የሀይማኖት ጦርነት ውስጥ ልትዘፈቅ እንደምትችል ሲሆን፣ በእምነት ላይ የሚቀሰቀስ ግጭት መግቻ አይኖረውም።
  • በአጠቃላይ፣ በአሁኑ ሁኔታ የኢትዮጵያን ችግር ባልተማከለና በተናጠል በሚካሄድ የትጥቅ ትግል ለመፍታት የሚደረገው ሙከራ፣ መፍትሄ በማምጣት ፈንታ አገሪቱ እንድትበታተን ተጨማሪና አጋዥ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ ተገቢ ነው።

 

  • ስለሆነም፣ ተቆርቋሪ የሆኑ ወገኖች አንድ ጥያቄ ሊያነሱ ይገባል፤ ከፊታችን የተደቀነው ትልቁና ሀገራዊው ግዴታ ኢህአዴግን መጣል ወይስ አገርን ማዳን የሚል ነው? (እደግመዋለሁ) በእርግጥ አብዛኛዎቹ የተቃዋሚ ሀይሎችም ሆኑ ብዙሃኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢህአዴግ መወገድ እንዳለበት፣ ቢያንስ ደግሞ የበላይነቱን መነጠቅ እንዳለበት ያምናሉ። ትክክለኛ አስተያየት ነው። ይሁንና፣ ኢህአዴግን ለመጣል በሚደረገው ርብርብ ምክንያት የማዕከላዊ መንግስት ቢዳከም አገር ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት እንዴት መቋቋም ይቻላል? አገር ላይ ጉዳት ሳይደርስ እንዴት ኢህአዴግን መታገል ይቻላል? ምን ዓይነት ስትራቴጂስ ሊንደፍ ይገባል? እነዚህ ጥይቄዎች ተገቢው ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል እላለሁ።
  • በኢህአዴግም ሆነ በብሄረተኛ ሀይሎች አማካይነት እንዲስፋፋ እየተደረገ በመሄድ ላይ ያለውን የዘር ፖለቲካ መቋቋም የዜጎች ሃላፊነት አይደለምን? ዛሬ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የአማርኛ ተናገሪዎች ከቄያቸው እንዲፈናቀሉና እንዲዋረዱ እየተደረገ ነው። ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ ሆነና ህወሃት በሚያራምደው ፖለቲካ ምክንያት ፀረ-ትግራይ ስሜት እያደገ ሂዷል። እነዚህና የመሳሰሉ አካሄዶች በሕዝቦች መሀል ጥላቻው እየከረረ እንዲሄድ የሚያደርጉ ሲሆን፣ ከ40 አመት በፊት የብሄረሰቦች መብት ይከበር ብለን እንደተነሳነው ሁሉ በኢህአዴግ የዘር ፖለቲካ ሳቢያ ዛሬ መብታቸውን ለተነፈጉ ዜጎችና የህ/ሰብ ክፍሎች መብት መቆም አግባብነት የለውምን? ኢህአዴግ የተለያዩ የሃይማኖት ተከታዮች ላይ የሚያደርሰው ኢፍትሃዊ አሰራር ችግር እያስከተለ እንደሆነ ተግልጿል፣ ይሁንና፣ በሕዝቦች መካለል ክፍተቱ እየሰፋ ሄዶ ለአክራሪ ወገኖች የተመቻቸ ሁኔታ እንዳይፈጠር የሁሉም እምነት ተከታይ መሪዎች በጋር ሊመክሩ የሚችሉበትና ደቀ መዝሙሮቻቸው ከጥፋት ጎዳና ሊታቀቡ እንዲችሉ መፍትሄ መሻት አይኖርባቸውምን? የኢህአዴግ ሃላፊነት የጎደለው አካሄድ በተመሳሳይ ሌላ ሃላፊነት በጎደለው እርምጃ መተካት የለበትም። ተቆርቋሪ ወገኖች የሩቅ አላሚ፣ የቅርብ ርቀት አሳቢ ሊሆኑ ይገባል።
  • ዛሬ በዘር የተደራጁ ኃይሎች አጋጣሚውን እየጠበቁ ናቸው። እነ አይሲስና መሰል ኃይሎች ምን እያዘጋጁልን እንደሆነ አናውቅም። አርፈው እንደማይተኙ ግን የተረጋገጠ ነው። ሌሎች የተከፉ ኃይሎችም የማዕከላዊ መንግስት መዳከሙን ሲረዱ አጋጣሚውን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ መረዳት አይከብድም። የኢትዮጵያ ህልውና አሳሳቢና አደገኛ ሁኔታ ላይ ሊወድቅ ይችላል የሚሉ ወገኖች፣ እየተቀጣጠለ ባለው ቋያ ላይ ቤንዚን በማርከፍከፍ ፈንታ ቆም ብለው አስበው ሃላፊነት የተላበሰ ፖሊሲ መንደፍ ይኖርባቸዋል። ኢትዮጵያ ከሁሉምና ከማንም በላይ ናትና ዜጎች ሁሉ ይህን ሀገራዊ ግዴታ ልንወጣና ልንሸከም ይገባል።
  • በመጨረሻም፣ አንድ ብልህ አዛውንት ከ30 አመት በፊት የተናገሩትን ልጥቀስ።
  • ፊታውራሪ አየለ አባ ጓዴ ይባላሉ። የኢህአፓ አባልና ኢህአሠ ጫቆ አካባቢ እንዲንቀሳቀስ ይህ ነው ተብሎ የማይገመት አስተዋጽኦ ያበረከቱ ታላቅ ሰው። ዛሬ ፊትአውራሪ አየለ ባይኖሩም፣ የተናገሩት ሁሌም ሲታወሰኝ ይኖራል። ደርግን እናወግዛለን፣ መወገድ አለበት ብለን አምርረን ታግለን ትግላችን ተዳክሞ ሱዳን እንገኛለን። ውይይት በምናደርግበት በአንዱ አጋጣሚ፣ ‘ጎበዝ አሉ’ ፊታውራሪ አየለ ‘ይሄ ጎበዝ (መንግስቱ ኃይለ ማርያምን መሆኑ ነው) ይውረድ፣ ይውረድ እንላለን። ለመሆኑ አማራጩንና ምን ሊከተል እንደሚችል አስበንበታልን’ ሲሉ ጠየቁ። ውይይቱ ላይ ተሳታፊ የሆንነው መብረቅ እንደመታን ደርቀን ቀረን። ያዘጋጀነው ነገር አልነበረምና መልስ የሰጠ አልነበረም። ጥያቄውን ለምን እንዳቀረቡም ገብቶናል። በዚህ ወቅት በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል ይንቀሳቀሱ የነበሩት ብሄረተኛ ኃይሎች እየጎለበቱ በመሄድ ላይ ነበሩ። ዛሬስ? ዛሬም ፊትአውራሪ አየለ እንዳሉት አማራጩንና ምን ሊከተል እንደሚችል አስበንበታል? ይህ ጥያቄ መልስ ያሻዋል። አስቡበት!
  • እንደገና ንግግሬን በታላቁ ባለቅኔ በቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ ስንኞች ልቋጭ፤

አገሬ ተባብራ ካልረገጠች እርካብ፣

ነገራችን ሁሉ የእንቧይ ካብ፣ የእንቧይ ካብ። አመሰግናለሁ!

The post ወዴት እየሄድን ነው? ለኢህአፓ ሲምፖዝየም የቀረበ (ክፍሉ ታደሰ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ወያኔን የትግሬ ነጻ አውጪ ማለት ያለ ግብሩ ስም መስጠት –ይገረም አለሙ

$
0
0

tplf-rotten-appleአቶ አንዱአለም ተፈራ ከገዢው መደብ የምንለይበት በሚል ርእስ ባስነበቡን ጽሁፍ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት የሚለውን አጠራር ለምን እንደመረጡ ያስረዳሉ፡፡ መጠሪያው ለወያኔ የማይገባው በመሆኑና  አቶ አንዱዓለም  መጠሪያውን ለመጠቀም ያአስቻለኝ ብለው  ያቀረቡት ምክንያት   በቂና ተገቢ ሆኖ ስላልተሰማኝ ይህችን አስተያየት ጻፍሁ፡

ትግሬ ስንል የኢትዮጵያ አንድ ክፍል በሆነው ትግራይ የተወለዱና ትግረኛ ቋንቋ የሚናገሩ ወይንም የወላጆቻቸው ስር ከዛ ሆኖ የትም ይሁን የት የተወለዱና ቋንቋውን ሊናገሩም ላይናገሩም የሚችሉትን ሁሉ የሚያጠቃልል ነው፡፡ ስለሆነም የትግሬ ነጻ አውጪ ስንል ወያኔ ትናንትም የታገለው ዛሬም ሥልጣን ላይ ሆኖ የሚሰራው እነዚህን ነጻ ለማውጣት ነው፣ እነርሱም ነጻ አውጪነቱን አውቀውና አምነው የተቀበሉት ነው ወደሚል አንደምታ ይወስዳል፡፡ይህ ደግሞ ወያኔ የሚፈልገው ነው፡፡

እሱ የሚለውን ተቀብሎ ትግሬና ወያኔን አንድ አድርጎ የመመልከቱ  አደገኛነት የታያቸው ኢትዮጵያውያን ገና ከጅምሩ ወያኔንና  ትግረኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ለይቶ ማየት እንደሚገባ፣ ሁለቱን መቀላቀል ትግሉን የሚጎዳና ወያኔን የሚጠቅም ብሎም በወደፊት የኢትዮጵያ አንድነት ላይ መጥፎ  ደንቃራ የሚያስቀምጥ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፣ጽፈዋል፡፡ ይህም ሙሉ በሙሉ ባይሆንም በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ተቀባይነት በማግኘቱ ወያያኔ ባሰበውና በተመኘው መጠን ትግረኛ ተናጋሪውን ከቀሪው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ነጥሎ የርሱ ብቸኛ መከታ ማድረግ አልቻለም፡፡

ወያኔዎች ትናንትም ሆነ ዛሬ አላማ ፍላጎታቸው ስልጣን ነው፡፡ ትግል ሲጀምሩ መላ ኢትዮጵያን መያዝ አንችልም ብለው ስላመኑ ትግራይን ይዘው  የሥልጣን ፍልጎታቸውን ለማርካት ስማቸውን ተሀህት፣ማገብት ህውሀት እያሉ ለትግረኛ ተናጋሪው ወገን የሚታገሉ መስለው ተጓዙ እንጂ ከራስ ጥቅም ያለፈ አላማም አጀንዳም ያላቸው አይደሉም፡፡ ይህን ደግሞ በሀያ አራት አመታት አገዛዛቸው በሚገባ የተገነዘብን ይመስለኛል፡፡ በዓላማም በግብርም የማይመስሉትን የቀዳማይ ወያኔን ስም የያዙትም በእምነት ሳይሆን ድጋፍ ለማግኘት ካልሆነም ተቃውሞን ለመቀነስ እንደሆነ የትግራይ አባቶችን ጠጋ ብሎ ጠይቆ መረዳት ይቻላል፡፡ በኢትዮጵያዊ እምነትና ስሜታቸው ጥያቄ የማይነሳባቸው ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ በአንድ ጽሁፋቸው  እነዚህ ሰዎች ከቀዳማይ ወያኔ ጋር በዓላማም በተግባርም ስለማይመሳሰሉ ወያኔ ተብለው መጠራት የለባቸውም አስመሳይ ወያኔዎች ናቸው ማለታቸውን አስታውሳለሁ፡፡ ስለሆነም የትግሬ ነጻ አውጪ ማለት ለግብራቸው የማይመጥን  ስም ነው፤ ይበዛባቸዋል፡፡ እንደውም ለእነርሱ ፍላጎት መሳካት የሚበጃቸው ነው፡፡

አቶ አንዱአለም  በጽሁፋቸው እኔ ራሳቸውን እንዲጠሩበት በመረጡት ስም ነው የጠራኋቸው ይላሉ፡፡ ሰይጣን ለተንኮሉ ከመጽሀፍ ቅዱስ ይጠቅሳል እንዲሉ ወያኔ ትክክለኛ ማንነቱን የሚከልልለትንና ትግረኛ ተናጋሪውን ኢትዮጵያዊ ወገን ጋሻ ማድረግ ያስችለኛል ብሎ የመረጠውን ግብሩን የማይገልጽ  ስም ለራሱ ስለሰጠ   እኛ ተቀብለን ማስተጋባት የለብንም፡፡ ይህን አደረግን ማለት በተዘዋዋሪ የወያኔን ፍልጎት ማሳካት ነው የሚሆነው፡፡ የወያኔ ስብከትና ማስፈራራያ ያልበገራቸው በርካታ ትግረኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን በተቃውሞው ጎራ ጥንቃቄ የጎደለው ተግባር ያለፍላጎታቸው ወያኔን ለመደገፍ  መገደዳቸው የአደባባይ ምስጢር ይመስለኛል፡፡ የሚወዱትን ሲያጡ እንደሚባለው ሆኖባቸው፡፡

አቶ አንዱአለም ትግሬዎችን ነፃ አወጣለሁ ብሎ የተነሳ ግንባር፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ነኝ ሲል፤ ሌላ ምን ብዬ ልጠራው ይላሉ፡፡ ይህን አባባል ከላይ ለመግለጽ በሞከርኩት አስተሳሰብ ስናየው ሶስት ጉድለቶች አሉት የመጀመሪያው ትግሬዎችን ነጻ አወጣለሁ ብሎ የተነሳ የሚለው ሲሆን ይህን ከላይ ለማሳየት ሞክሬአለሁ፤ ሁለተኛው ግንባር የሚለው ነው፡ከመጠሪያው ጋር ሊቀራረብ የሚችለው ህወሀት ነው እሱ ደግሞ ግንባር አይደለም፤ ግንባሩ  ኢህአዴግ ነው፡፡ እሱን በጥቅሉ የትግሬ ነጻ አውጪ ለማለት ተፈልጎ ከሆነ ደግሞ ወያኔ ሀገራዊውን የፖለቲካ ትግል የጎሳ ትግል ለማድረግ ሌት ከቀን የሚማስንበትን ስራ እያሳካንለት ነው ማለት ነውና አደጋ አለው፡፡ ሶስተኛው ነኝ ሲል እኔ ምን ብዬ ልጥራው የሚለው ነው፡፡ እኛ መጠራት ያለብን እሱ ነኝ በሚለው ማንነቱን በማይገልጸው ሳይሆን ለማንነቱ በሚመጥነው ለግብሩ መገለጫ በሚሆን መጠሪያ መሆን አለበት፡፡ አሁን ልማታዊ መንግሥት እያለ ራሱን እየጠራ ነው ታዲያ እኛ በዚህ  እንጠራዋለን?

ነገርን ነገር ያነሳዋል አንዲሉ በዚህ ረገድ ሌሎች ስህተቶችም ስንፈጽም ኖረናል አሁንም እየፈጸምን ነው፤  ብሶት የወለደኝ ሲል ተቀብለን ብሶት የወለደው ብለናል፣ በረሀ የወረድነው አንባገነኑን የደርግ መንግስት ለማስወገድ ነው ሲሉ ሰምተን አሰምተናል ተቀብለን ተናግረናል፡፡

እንደሚነግሩን ጫካ የገቡት የካቲት 1967 ነው፡፡ በዚህ ወቅት ንጉሱን ከሥልጣን ያወረዱት ወታደሮች ይይዙት ይጨብጡት የጠፋባቸው፣ ይሆኑት ያደርጉት ነገር የቸገራቸው ነበሩ፡፡ እናም ወያኔዎቹ ብሶት የወለደን ለማለት የሚያበቃቸው ምክንያት አልነበረም፤ሊሆን የሚችለውን የመተንበይ ችሎታ ነበረን ወይም ጠንቋይ እንቀልብ ነበር ካላሉ በስተቀር  ደርግም በዛን ወቅት አንባገነን የሚባል አልነበረም፡፡

የሀገሬ አርሶ አደር አልጋ ፈርሶ አልጋ እስኪደላደል

ይህን ግዜ ነበር የጠሉትን መግደል

እንደሚለው የንጉሱ ሥርዓት ፈርሶ መጪው ማንና ምን እንደሚሆን በውል ባልታወቀበትና የመንግስት ክፍተት በተፈጠረበት አጋጣሚ ሲያልሙት የኖሩትን ከአጼ ዮሀነስ በምንይልክ ከትግሬ በሸዋ ተነጠቀ ብለው የሚቆጩበትን ስልጣን የሚያገኙበት አጋጣሚ ያገኙ መስሎአቸው  ምኒልክ ቤተ መንግሥት መድረስ ባይችሉም ከዮሀንስ ቤተ መንግሥት ሰተት ብለው ሲገቡ እየታያቸው  ተጠራርተው ደደቢት ወረዱ፡፡ ነገር ግን ያሰቡት ያለሙት ሳይሆን ያልጠበቁት ሆነ፡፡ የ17 አመታት ትግልና ምኒልክ ቤተ መንግስት የመግባት ድል፡፡ ታዲያ እነዚህ እንደምን ብሶት የወለዳቸው፤የደርግን አምባገነን ሥርዐት ለመታገል በረሀ የወረዱ ፣የትግሬ ነጻ አውጪ ሊባሉ ይችላል፡፡

The post ወያኔን የትግሬ ነጻ አውጪ ማለት ያለ ግብሩ ስም መስጠት – ይገረም አለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

ፖለቲካ ሀጢአት የሆነባት አገር –ናትናኤል በርሔ

$
0
0

ኖርዌይ

unnamedሰሞነኛ በአለም ላይ ካሉት አበይት ክስተቶች አንዱ የሆነው የግሪክ መንግስት የኢኮኖሚ ውድቀት እና የፖለቲካ አለመረጋጋት የተከሰተበት ነው።አለም አሁን ለሰለጠነበት ዘመን ትልቅ አስተዋጽኦ ካበረከቱ አገሮች መሀከል በቀደምት ደረጃነት የምትመደብ ግሪክ ዲሞክራሲ የምንለውን ፅንሰ ሀሳብ በማምጣት እና ስራ ላይ በማዋል የሚቀድማት አገር የለም።የጥንታዊታ ግሪክ በ5ኛው መቶ ክርስቶስ ልደት በፊት ሀያል ልኡላዊት አገር ካደረጉዋት ነገሮች ውስጥ ዲሞክራሲ የሚለውን ቃል ዲሞ /Demo/ “people” እና ክራሲ “ power” በማለት በወቅቱ ፍችውን አስቀምጠውታል። ግሪክ በ21 ክፍለ ዘመን ከሀያላን አገራት የተበደረችውን ብድር መክፈል ባለ መቻልዋ ስር በሰደደ የመልካም አሰተዳደር ጉድለት በሙስና በዕዳ ቀውስ ምክንያት አሁን ላለችበት በአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት /IMF/ ፤ አውሮፓ ህብረት እንዲሁም የአውሮፓ ሴንትራል ባንክ ዕዳ አጣብቂኝ ውስጥ ከቷቷል።

ወደ አገራችን ስንመለስ ኢትዮጵያም ለአለም አቀፍ አንድ ሚልዮን ዶላር Sovereign ቦንድ ሽያጭ ለገበያ አቅርባ ነበር ወለዱም 6% ነው አሁን ባለው የኢኮኖሚ ገባያ ከ 6% ወደ 7% አድጎዋል ይህም ማለት የመክፈል ዕዳችንም መጠን ጨምሮዋል ። ኢትዮጵያ ዛሬ ያለችበትን ጂዮግራፊያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ሌሎች ገጽታዎች ለመላበስ ያበቋት እጅግ በርካታ ክፉ እና በጎ ተበለው የሚጠቀሱ የታሪክ ክስተቶችን አስተናግዳለች ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ እንዲህ አሳሳቢ ሁኔታና ውድቀት አፋፍ ላይ ባለችበት ሁኔታውን ዝም ብሎ በመልከት በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር የምንኖር ኢትዮጵያዊያኖች ዛሬ ህወሃት/ኢህአዴግ ጨቋኝ አገዛዝ በገዛ ልጆቿ ወድቃ ልትፈርስ እየተንገዳገደች ነው፡፡ እርቀን ሳንሄድ የቅርብ ጊዜ ታሪካችንን እንኳን ብንፈትሽ ዛሬ ለምንገኝባቸው እጅግ ውስብስብ እና ፈታኝ ችግሮች መንስዔ የሆኑትን ነገሮች በቀላሉ ልንገነዘብ እንችላለን። የችግሮቻችንን ምንጮች እና ያስከተሉብንን መዘዝ በቅጡ መረዳት ከቻልን ከተዘፈቅንበት አረንቋ ውስጥ ለመውጣት ጊዜ ላይ ወስድንብ ይችላል።

ይህ አካሄድ በሌላ አንጻር በኢትዮጵያችን እየደረሰ ያለው ረሃብ፣ የዋጋ ግሽበት፣ የኑሮ ውድነት፣ ሙስና፣ ፍትሕአልባነት፣ አፈና፣ ግድያ ወዘተ የተወሰነ የኅብረተሰብ ክፍልን ብቻ ሳይሆን ከሲቪሉ ጀምሮ ጦር ሠራዊቱን፣ ደኅንነቱ፣ ተማሪውን፣ ገበሬውን፣ የመንግሥት ሠራተኛውን፣ ወዘተ ቤት ያንኳኳ በመሆኑ ለኢትዮጵያ አንድነትና ብልጽግና በሰላም የሚታገሉ ሀይሎችን በስውርና በአደባባይ አስሯል፥ ደብድቧል፥ ገሏል፥ የተረፉት አገር ጥለው እንዲሰደዱ አስገድዷል። ድምጻችን ይከበር በማለት ሠላማዊ ሰልፍ የወጡ ንጹህ ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ በአደባባይ በጥይት ተደብድበዋል። ህዝብን እርስ በርስ በማናከስ ሆድና ጀርባ ለማድረግ ሞክሯል። የአገራችን መሬት እየተሸነሸነ ለባዕዳን በመከፋፈል ላይ ይገኛል፡፡ የሀገሪቷን መዋዕለ ንዋይ ጨምሮ ዋና ዋና የኢኮኖሚ አውታሮች በወያኔ አባላትና የጎሳ ትስስር ባላቸው ባለሥልጣናት ተይዟል። ዜጎች በገዢው ፓርቲ ሰላዮች፥ ካድሬዎችና ታጣቂዎች እየተዋከቡ በገዛ ሀገራቸው ሰርተው መኖር አቅቷቸው ለመሰደድ እየተገደዱ ነው። ህወሃት/ኢህአዴግ ጨቋኝ አገዛዝ እንደመሆኑ ከእነዚህ አምባገነን መንግሥታት በላቀ መልኩ ኢትዮጵያውያንን አፍኖ ያለው ህወሃት አገዛዝ በሕዝባዊ ለውጥ ከሥልጣን መነሳት አለበት፡፡ ሕዝባችንም ለዘመናት የተጠማውን ነጻነትና ፍትሕ ለማግኘት ለለውጥ እንመካከር! እንዘጋጅ !! እንተባበር !! “በቅርብ ጊዜው የኢትዮጵያ ፖለቲካ አሣዛኝ የሆነው ጉዳይ መንግሥቱም፣ ገዥ ፓርቲውም፣ ሕግ አውጭውም ሁሉም አንድና እርሱው መሆኑ ነው፡፡ ባለፉት ዓመታት ጉዞ ውስጥ የጋራ አመራር የሚባል ነገር ተመናምኖ ህወሃት/ኢህአዴግ በፓርቲያቸው ውስጥ ብቻ ሣይሆን ዛሬ በደረስንበት ሁኔታ በሃገሪቱና በመንግሥቱ መዋቅሮች ውስጥ በሚከናወነው ሥራ ሁሉ ብቸኛ ፈላጭ ቆራጭ ሆነዋል፡፡”

ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችን የመደገ ፍልማድ አነስተኛ በሆነባት ሀገርና ተቃዋሚ ፓርቲዎችን መደገፍ መንግስትን እንደ መቃወም በሚቆጠርበት ሁኔታ ሊገኝ የሚችለው ድጋፍ አናሳነው:: “ምንም እንኳ ምዕራቡ የገንዘብ አቅም ቢኖረውም በሃገር ውስጥ ባለው ፖለቲካ ላይ ግን ጫና የማሣደር ጉልበት እንደሌለው የኢትዮጵያው ገዥ ፓርቲ የተረዳ ይመስለኛል ።ኢትዮጵያ አሁንም ቢሆን የምዕራቡን ድጋፍና የልማት እርዳታ ትፈልጋለች፤ ብቅ ብቅ እያሉ ያሉትን እንደ ቻይናና ሕንድ አይነቶቹን ኃያላን ቦታም ደግሞ ትገነዘባለች፡፡ ጉዳዩ መርህና ርዕዮተ ዓለም ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን የመመቻቸት ወይም የመጠቃቀምም ጉዳይም ነው፡፡” ጨቋኝ አምባገነኖች ከሌሎች አገሮች እየተወገዱ እኛ ዝም ብለን የምንመለከትበት ምንም ምክንያት ሊኖር አይገባም፡፡ በእነዚህ የሰሜን አፍሪካ አገራት የኑሮ ውድነት፣ የነጻነት ዕጦት፣ ጭቆና፣ ግድያ፣ ሕገወጥነት ወዘተ ያንገፈገፈው ሕዝብ የደረሰበትን የምሬት ደረጃ የኢትዮጵያ ሕዝብ አልደረሰበትም ማለት ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ምናልባትም ግፉ ከዚህ የበለጠ ሊሆን ይችላል ። ለኢትዮጵያ ፖለቲካ መፍትሄው ራሱ የኢትዮጵያ ሕዝብና ከጠላቶቿ ጋር የማያብሩት የፖለቲካ ድርጅቶቿ ብቻ ናቸው። ወያኔንና ግብረአበሮቹን ከሥር መንግለው ኢትዮጵያን ነጻ የሚያወጧት ቆራጦቹ ልጆቿ ናቸው።
በአብዛኛው ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከነመኖራቸው ራሳቸውን ለማህበረሰቡ የሚያስተዋውቁት ምርጫ የተወሰነ ጊዜ ሲቀረው ብቻ ነው:: ከምርጫ በኋላ እንቅስቃሴ ቢኖር እንኳን መሪዎቹ ጎልተው የሚወጡበትና እንደ ድርጅት ፖለቲካ ፓርቲዎች የማይታዩበት ነው:: “የምርጫ ፖለቲካ ፓርቲ” የሚለው አሰያየም በተለያዩ ሙሁራን እየተንጸባረቀ ያለው ለዚህ ነው:: በሌላ በኩል ደግሞ ከማህበረሰባዊው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የተገናዘበ ፖለቲካል ስትራተጂና ታክቲክ ያላቸው ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች በቁጥር እጅግ አናሳ ናቸው:: ፖለቲካል ስትራተጂና ታክቲክ ያላቸው እንኳን በማህበረሰቡ ውስጥ ዘልቀው ስላልገቡ አይደለም በአጠቃላይ ህዝቡ ይቅርና የፖለቲካ ንቃተ-ህሊናቸው ከፍ ብሏል በሚባለው የህብረተሰብ ክፍል እንኳን በተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ያለው ዋናዋና ልዩነቶች እንኳን አይታወቅም:: በሀገር ውስጥ ሆነ በውጭ የሚገኙ አብዛኞቹ ባለሃብቶችም አንድም ማህበራዊ ግዴታቸውን ጠንቅቀው የማይረዱ መሆናቸው፣ሁለትም ”ጎመንበጤና“ ብለው ከፖለቲካ ራሳቸውን የሚያገሉት አንድ ፖለቲካ ፓርቲ የመደራደርና የመገዳደር አቅሙን ለመገንባት በዋናነት ፖለቲካል ስትራተጂውንናታክቲኩንከማህበረሰባዊው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ያገናዘበና በማህበረሰቡ ውስጥ ዘልቆ በመግባት ማህበረሰቡን ማደራጀትና ማሰባሰብ አለበት:: በዚህ ሂደት ውስጥ አንደኛ ፖለቲካ ፓርቲው በማህበረሰቡ ውስጥ ተቀባይነትን ያተርፋል:: እንዲሁም ደግሞ በሌሎች ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋርም የመደራደር አቅሙንከፍ ያደርገዋል:: በተያየዘ መልኩም ከሌሎች ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመደራደር የጋራ ፖለቲካ አጀንዳ ነድፈው የጋራ ተጠቃሚነትን

The post ፖለቲካ ሀጢአት የሆነባት አገር – ናትናኤል በርሔ appeared first on Zehabesha Amharic.

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ አጭበርብረዋል የተባሉ እስራት ተፈረደባቸው

$
0
0

–የባንኩ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ የተቀጡት በሌሉበት ነው

መንግሥታዊ ሰነዶችን በሐሰት በማዘጋጀት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰባራ ባቡር ቅርንጫፍ፣ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ ማጭበርበራቸው የተረጋገጠባቸው የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅና ሁለት ግለሰቦች፣

national bank of ethiopiaሰኔ 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ከአምስት እስከ 12 ዓመታት ከስድስት ወራት የሚደርስ ጽኑ እስራት ተፈረደባቸው፡፡

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ በሙስና ወንጀል ክስ የመሠረተባቸው፣ የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ አቶ መኳንንት አበጀ፣ ይፈመን ቲምበር ፕሮሰሲንግ የተባለ ድርጅት ተወካይ አቶ ብርሃኑ አዳፍሬና የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ይትባረክ አፈወርቅ ናቸው፡፡

የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረዳው፣ የባንኩ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ መኳንንት በ2005 ዓ.ም. የተለያዩ ሀሰተኛ የባንክ ዋስትና ሰነዶችን አዘጋጅተዋል፡፡ ያዘጋጁትን ሐሰተኛ ሰነድ ይፍመን ቲምበር ፕሮሰሲንግ ለተባለው ድርጅት በመስጠት ወንጀሉን መፈጸማቸውን ያስረዳል፡፡

በሥራ አስኪያጁ የተዘጋጀውን ሐሰተኛ ሰነድ የድርጅቱ ተወካይ አቶ ብርሃኑ በመቀበልና ሐሰተኛ የሽያጭ ዋስትና በማስያዝ፣ ከአንድ የማደያ ድርጅት ውል ተዋውለው 900,000 ብር የሚያወጣ የሞተር ዘይት፣ ቅባቶችና የነዳጅ ኩፖን ወስደው በወንጀሉ መሳተፋቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡

የይፈመን ቲምበር ፕሮሰሲንግ ሥራ አስኪያጅ ናቸው የተባሉት አቶ ይትባረክ፣ ከአቶ ብርሃኑ ጋር በመተባበር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ላደረጉት የእንጨት ምሰሶዎች አቅርቦት ውል፣ ሐሰተኛ ሰነዱን በዋስትና በማቅረብ 4,908,623 ብር ቅድመ ክፍያ ከኢትዮ ቴሌኮም በቼክ መውሰዳቸውን ይገልጻል፡፡ ገንዘቡንም ወደ ድርጅታቸው አካውንት በማስገባትና አውጥተውም ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውም በክሱ ተጠቁሟል፡፡

የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ሦስቱም ተከሳሾች ድርጊቱን መፈጸማቸውን በምስክሮችና በሰነድ በማረጋገጡ፣ የባንኩ ሥራ አስኪያጅ አቶ መኳንንት በሌሉበት በስምንት ዓመታት ጽኑ እስራት፣ አቶ ብርሃኑ አዳፍሬ በ12 ዓመት ከስድስት ወራት ጽኑ እስራትና አቶ ይትባረክ አፈወርቅ በአምስት ዓመታት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 18ኛ ወንጀል ችሎት ሰኔ 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ፍርድ ሰጥቷል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

The post የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ አጭበርብረዋል የተባሉ እስራት ተፈረደባቸው appeared first on Zehabesha Amharic.

[ትንታኔ] የናይጄሪዉ ፕሬዝዳንት እና የቦኮ ሐራም አሸባሪ ቡድን ፍጥጫ –ሳዲቅ አህመድ (በድምጽ)

በሄኖክ ሰማእግዜር ላይ ለተፃፈ አስተያየቴ ፤ ይድረስ ለስርጉተ ስላሴና  ለቢላል አበጋዝ

$
0
0

ከጋዜጠኛ ደምስ በለጠ  

 

Voa-amharic-የተከበርሽው ወድ እህቴ  ሰርጉተ ስላሴ አንቺስ እንዴት ሰንብተሽልኛል ።   አዎ !በጋራ መድረካችን ዘ-ሃበሻ የሚወጡትን ፅሁፎችሽን እከታተላለሁ ። ይገርምሻል የጋራ ወዳጃችን ስላንቺ በጥቂቱም ቢሆን አውግተውኝ ስለነበር በተወሰነ ደረጃ የማውቀው ነገር አለ ። እህቴ ስርጉተ ስላሴ፤ እንደዛሬ ግን ውስጥሽን ለማየት አልቻልኩም ነበር። የሰዎችን ሰብአዊ መብት መከበር በተለይ ደግሞ እዚህ አሜሪካን እየኖርን ለምን እንደፈጥጣለን በሚል መሰረት ላይ ያጠነጠነውን ፅሁፌን አንብበሽ ለሰጠሽው የራስሽ አስተያየት፤ አክብሮቴን ልገልፅልሽ እወዳለሁ። አክብሮቴን እንድቸርሽ አቢይ ምክንያት የሆነኝ ደግሞ ከፅሁፍሽ “ውስጤ” መጀመሪያ እስከመጨርሻ ድረስ፤ እኔ በሄኖክ ሰማ እግዜር ላይ ካቀርብኩት የፅሁፉ መሰረታዊ ሃሳብ ሳትወጪ ወይም ሌላ ትርጉም ሳትሰጪ ወይም ሃሳቡን ወደምትፈልጊው አቅጣጫ ሳጥጠመዝዢ  መልስ በመስጠትሽ ነው ። ምን ለማለት እንደፈለግሁ ይገባሻል ብየ እጠብቃለሁ።

 

አንዳንድ ለፅሁፌ የሚሰጡ መልሶች እንደ አለሽበት አገር እንደ ስዊስ ቺዝ የተቀዳደዱ ስለሚሆኑ የትኛው ሐሳብ ላይ ላይ ቆመሽ በየትኛው ቀዳዳ ሾልከሽ የትኛውን እንደምትመልሺ ይቸግራል ። እህት አለም ተመልከቺ ስለሄኖክ ሰማእግዜር ስናገር እዚህ አሜሪካን ሃገር ስለተፈፀም ጉዳይ ብቻ ነው የተናገርኩት ። ኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔ ጋዜጠኞች አላሰረም ፤አላሳደደም፤ የሙስሊም አማኞችን የእምነት ነፃነት አልተጋፋም፤ ሰላማዊ ታጋዮችን አላሳነቀም የሚል ክርክር ውስጥ አልገባሁም ። ስለአንድ ነጥብ ስናገር የምናገረው ስለዚያ ነጥብ ብቻ ነው ። የማሰብና የመናገር ነጻነት ስል  ሌላ ትርጉም ሳይኖረው አንድና አንድ የማሰብና የመናገር ነጻነት ማለት ብቻ ነው ።

 

በምሳሌ ላስረዳ ። ስቴት ኦፍ አሪዞና ውስጥ አንድ ሰው ሌላውን ሰው በስለት ገደለና ለፍርድ ቀረበ ። ሟችን ለሞት የበቃው ሁለቴ መወጋቱ ነው ። ገዳይ ደግሞ ጠበቃ ቆሞሎት ጥፋተኛ አይደለሁም እያለ እየተከራከረ ነው ። “ጥፋተኛ ያልሆንክበትን ምክንያት አቅርብ” ሲባል፤

“ኢንዶኔዥያ ውስጥ በአንዲት ደሴት ላይ የሚኖሩ ጎሳዎች አሉ ። እነዚህ ሰዎች ጎሽ የሚመስለውን በሬያቸውን  በገመድ ዘርጥጠው ከጣሉት በኋላ  ሃምሳ የሚሆኑ ሰዎች ከየአቅጣጫው በአምሳ ጩቤ ወግተው ይገድሉታል ። ሰውነቱን ዘነጣጥለው ስጋውን እየቀቀሉ ይበሉታል ። እኔ የገደልኩትን ሰው በአንዲት አነስተኛ ጩቤ ሁለቴ ብቻ ነው የወጋሁት ። በገመድ አልዘረጠጥኩት፤ በአምሳ ጩቤ ወርሬ አላሰቃየሁት ፤ ስጋውንም ዘልዝየ አልበላሁት በምን ምክንያት ነው እነዚህ በጭካኔ የተሞሉ የኢንዶኔዥያ ሰዎች ሳይከሰሱና ጥፋተኛ ሳይባሉ እኔ ጥፋተኛ ተብየ የምከሰሰው?”

የሚል ክርክር አቀረበ ። ሳሙና ሌላ እንዶድ ሌላ !

 

እኔም እንዳቺው የራሴ ባህሪ አለኝ ። ምን መሰለሽ እመቤት!  አንድ ሰው ከፃፍኩት ርእስ ውጪ መሰረተ-ሃሳቡን ሳይሆን ቃሉን ብቻ ጎትቶ የራሱን ትርጉም ሰጥቶ ሊሞግተኝ ቢሻ መልስ ለመስጠት ይቸግረኛል ። መነሻው የራሱ ትርጉም እንጂ  የእኔ አይደለምና !

 

ሰው! ሰው! ሰው! እያልሽ የሰጠሽው ትንታኔ ለኔም ተመችቶኛል። የምንም ነገር መሰረቱ ሰው ነውና ። ሄኖክም ሰው ነው ። ሰዋዊ መብቱ ይከበርለት ነው ሙግቴ ። የጠላነውን የሄኖክን መብት  ስናከብር የኛንም መብት እያከበርን እንደሆነ መዘንጋት አያስፈልግም ።

 

በፅሁፍሽ ላይ “አያቶቼ የቤተ ክህንት ዓራት ዓይናማ ሊቃናት ነበሩና እናቴ ስትነግረኝ ሲያድጉ መሬትን ሲረገጡ መሬት የታመመች ያህል ወይንም የቆሰለች ያህል እንዲጠነቀቁላት ይቆጣጠሯቸው ነበር። መሬት ላይ መዝለል አይፈቅድላቸውም ነበር።” ብለሻልና በነገረ መለኮት ጥበብ ዘልቋቸው ፤ እውቀትን ተነክረውበት በፍልስፍናው ረቅቀውበት፤ አራት አይን የበራላቸው ፤ ለግኡዟ መሬት ህመም የሚጠነቀቁ ሰዎች የልጅ ልጅ የሆንሺው ስርጉተ-ስላሴ ፅሁፍሽ ላይ “እኛም ስናድግ ጠረኑ እንዲኖር ተደርጎ ቢሆንም፤ አሁን የሚገርምህ ነገር የበለጠ በላቀ ሁኔታ ተፈጥሮን እማይበት መንፈስ ያ የአያት ቅድመ አያቶቼ መንፈስ አፅመ ቅዱስ ቅርስ የላክልኝ – ይመስለኛል። መሬትን ስረግጥም – የበለጠ ከልጅነቴ ጊዜ ተጠንቅቄ ነው።” ያልሺው ድንቅ ነውና በአርአያ ስላሴ ለተፈጠረው ምንኛውም አይነት ለምትወጂውም ሆነ ለማትወጂው ሰው መብት መጠንቀቅ ይጠፋሽል ብዬ አልገምትም ።

 

ሔኖክ ጋዜጠኛ አይደለም ካድሬ ነው ብለሽዋል ።  ለመግባባት እንዲመቸን እኔም ካንቺ ጋር ልስማማና እንደገና ከፅሁፍሽ ልዋስ ። እንዲህ ይጠቀሳል፦ “የኢሠፓ ፓርቲ አባል ሆኜ በካድሬነት ስሠራ በነበረበት ጊዜ እማስበው የፓርቲዬን ፕሮግራም ዓላማና ግብ ተፈጻሚነት ብቻ ነበር። ጉዞዬ አንድ አቅጣጫ ግቤም አንድ ብቻ ነበር። ጋሬ – ዓይነት።”  እንግዲህ ሄኖክም ዛሬ ከዚህ በላይ እንደጠቀሽው አንቺ እህቴ ያኔ የነበርሽበት ደረጃ ላይ ያለ ቢሆንስ? አንቺ ያለፍሽበትን ደረጃና መብት ሊነፈገው ይገባል ? ሌላ ምንም አይነት ትርጉም ሳይሰጠው ማለቴ ነው ። እኔ ሳደርገው ልክ ነው እሱ ሲያደርገው ግን ስህተት ነው እንደማትይኝ ተስፋ አደርጋለሁ ።

 

“ሌላው ያነሳኽው ሰላማዊ ሰልፍን በሚመለከት ነው” ብለሽኛል ። እኔ ያነሳሁት ሰላማዊ ሰልፍን ሳይሆን  የሰላማዊ ሰልፉን አላማ ከሃዲድ መውጣት ወይም መንገዱን መሳቱን ነው ። ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው ።እንደገና ፅሁፌን ተመልከቺው ። እህቴ ስርጉተ  እዚህ ፅሁፍ ላይ ከላይ እንዲህ ብያለሁ እኔም እንዳንቺው ስለባህሪዬ ስገልፅ  ። “አንድ ሰው ከፃፍኩት ርእስ ውጪ መሰረታዊ-ሃሳቡን ሳይሆን ቃሉን ብቻ ጎትቶ የራሱን ትርጉም ሰጥቶ ሊሞግተኝ ቢሻ መልስ ለመስጠት ይቸግረኛል ። መነሻው የራሱ ትርጉም እንጂ  የእኔ አይደለምና !” ፅሁፍሽ ላይ ከዚህ ሌላ ከፅንሰ-ሃሳቡ የወጣ ሃሳብ አላገኘሁም ። ሆኖም ግን አስከትለሽ “ሰላማዊ ሰልፍ የተፈቀደ አመፅ ማለት ነው” ብለሻልና እኔም አንድ ነገር ጥያቄ አለኝ ላንቺ ። ሰላምና አመፅ እንዴት አድርጎ ነው አንድ  የሚሆነው? ሰላማዊ ሰላም ነው ፤ አመፅም አመፅ ነው ።

 

ይገርምሻል እዚህ ዋሽንግቶን ዲሲ ከ50 ሰዎች በላይ ለሰላማዊ ሰልፍ የምትጠብቂ ከሆነ ከዲሲ ገቨርንመንት ፈቃድ ማውጣት ይኖርብሻል ። የተፈቀደ አመፅ ላደርግ ነው የመጣሁት ብለሽ ብትነግሪያቸው እዚያው ነው ለእስር የሚዳርጉሽ ። ጠላትሽ ይታሰር ።

 

ስለአበበ በለው “እንዲህ ዓይነት ሰብዕና ሲያመጣ – አመመኝ።” ብለሻል ። ምን አይነት ሰብዕና ይሆን ያመጣው?  ለኔ ግልፅ አይደለም ።  “ስለ – አዋረደኝ” ያልሺውንም ልገምትና አንቺ ስለመንቶቹ ስትፅፊና በምናብሽ የሳልሺውን በወረቀቱ ላይ ስታወራርጂ አበበን የሳልሺው በራስሽ እይታ ይመስለኛል ። አበበም ፤ “ስርጉተ እባክሽ ስለእኔ ስትፅፊ እንዲህ፡ እንዲህ ብለሽ ፃፊልኝ” እንዳላለሽ እገምታለሁ ። ብሎሽ ከሆነ እውነት ነው አዋርዶሻል ፤ ካላላሽ ደግሞ ውዳሴ ከንቱው የቱጋ እንዳለ ፈልጊው እሱ አላዋረደሽም እላለሁ ። “አንድ ጋዜጠኛ በአድማ መግባት – በፍጹም የለበትም።”  ብለሻል ስለአበበ በለው ። የትኛው አድማ ላይ እንደገባ ግልፅ ስላልሆነልኝ  የምለው ነገር ይቸግረኛል ።

 

በተረፈ ፅሁፌን አንብበሽ የተሰማሽን በጨዋነት በመግለፅሽ አመሰግናለሁ ። በሰነዘርሻቸው ሃስቦች ላይ የምስማማባቸውም ሆኑ የማልስማማባቸው ሃሳቦች ቢኖሩም  የሃሳብ ነፃነትሽን አከብራለሁ ።

ለምወዳቸውም ሆኑ ለማልወዳቸው ሰዎች እኩል መብት እንዲኖራቸው ነውና ጥረቴ በዚህ እንደምንተጋገዝ  ተስፍጋ አደርጋለሁ ።

 

ደሕና ሁኝልኝ እህት አለም።

 

\\\\\\

 

 

ይድረስ ለአቶ ቢላል አበጋዝ በቅድሚያ የከበረ ሰላምታየ ይድረስዎ ። ከርስዎ ጋር በሃሳብ አልተለያየንም። የሄኖክ መብት መከበር እንደነበረበት፤ ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ነገሮች ከመስመር መውጣት እንዳልነበረባቸውና ያም ከብስጭት የመጣ እንደሆነ ገልፀው ልምድ ሊያርመው የሚችል ስህተት ነው ብልዋል ። እኔ መኖሪያየን ቀይሬ አሁን ወደምኖርበት ስቴት እስከተዛወርኩ ድረስ ለ15 አመታት ወያኔን በመቃወም በዋሽንግተን ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቻለሁ። ያስታውሱ እንደሆነ በ2005 ኖበምበር 14 ቀን 30ሺህ ኢትዮጵያዊ ሰላማዊ ሰልፍ ውጥቶ ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የተነሳው ሰልፍ እስከ ኮንግረሱ ፅህፈት ቤት ድረስ ተጉዟል ። ያን ሰላማዊ ሰልፍ ክጅምሩ እስከ ፍፃሜው ካስተባበሩትም ከመሩትም ሰዎች አንዱ እኔ ነበርኩ ። ለቨርጂኒያ ዲሲና ሜሪላንድን መገናኛ የሆኑት አውራ መንገዶች ሙሉ ለሙሉ ተዘግተው ነበር።  የሰልፉ አላማ ግብ በወያኔ ጥይት የተገደሉ ወገኖቻችንን መከራ ማሳየትና ብሎም እስር ቤት የተወረወሩት የቅንጅት መሪዎችን መስዋእትነት ማሰብ ነበር ። ታዲያ ሰላማዊ ሰልፉ በራሱ ግብ አልነበረም ። ስለዚህ የሚደረጉ ሰልፎች ሁሉ  በመሰረቱ ግቦች አይደሉም ። የአንድ ትልቅ አላማ ተጨማሪ ማሳያ   ብቻ መሆን ይገባቸዋል ።  ፅሁፍዎ ላይ  እንዳሉት ሄኖክ ወጥ እየዛቀ በላ አልበላ ቤቱ ችሎት ስለሚኖር የኔ ጉዳይ አይደለም ።

 

ሌላው አንዱ አረፍተ ነገርዎ ከቀጣዩ ጋር አልያያዝልኝ እያለ ተቸግሬ ነበር። ስሜት አልሰጥ ያሉኝን እያለፍኩ ግንዛቤ በሰጡኝ ላይ ብቻ ነው መልስ ለመስጠት የሞከርኩት ። እኔ እርስዎን ብሆን የሆሊውድን “ሴልማ” ፊልም የታሪክ ማጣቀሻ አድርጌ ላቀርብ አልደፍርም ነበር ፤ ፊልሙንም አላየሁትም ። ታሪኩ ግን በስቴት ኦፍ አላባማ ፤ ወደርዕሰ-ሰከተማይቱ ሞንትጎመርይ በደቡባዊ የአሜሪካ ስቴቶች ለሚኖሩ ጥቁሮች የመምረጥ መብት መከበር ላይ ያነጣጠረ ሰላማዊ ሰልፍ እንደነበር አውቃለሁ ። አቢይ አላማው ከሰልፉ በፊት ቀድሞ የታሰበበት  ለጥቁሮች የመምረጥ መብትን ማጎናፀፍ ሲሆን ለዚህ መብት መከበር ሰላማዊ ሰልፉን እንደማሳያ ተጠቅመውበታል ።  በአላባማ ስቴት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኛና በባለስልጣናቱ ድጋፍ  መከራ የደረሰባቸውና ይተደበደቡት ጥቅሮቹ ሰላማዊ ሰልፈኞች ፤ የእርስዎን አባባል ከፅሁፍዎ ልዋስና በብሽቀት ፤ እልህና ምሬት፤ ደብዳቢዎቻቸውን ነጮቹን እነሱም መደብደብ ቢጀምሩ ኖሮ ፤ የሰልፉ አላማ መንገዱን ስቶ የዛሬው ታሪክ ሌላ በሆነ ነበር ።

 

አቶ ቢላል አበጋዝ ጨቋኞችን የማውረድ ስልጣን አለኝ አላልኩም ። ይህ እርስዎ ፅሁፌን ሲያነቡ በራስዎ ልምድ የተረጎሙት ነው ። ደሞ አያስጎምጁኝ ፤ ይህማ ስልጣን ቢኖረኝ ኖሮ በአለም ያሉትን የሰው መብት ገፋፊዎች ሁሉ ገንድሼ ገንድሼ እጥላቸው ነበር ። ወይ ነዶ !

በደጋፊም መልኩ ይሁን በተቃዋሚ ፤ እኔ ጨቋኝ በኔ ላይ እንዲነግስብኝ አልፈቅድም ነው ያልኩት ። ያ የኔ ምርጫና መብት ነው ።

 

“ለሄኖክ መብት የምከራከረውን ያህል ለኢሳትም እቆማለሁ ።” ብለዋል እኔም ከእርስዎ ጎን እቆማለሁ ። በተለይ የሚዲያ  መብት እንዲከበር ስለምጥር ፡ በነፃነት የመናገሪያና ሃሳብን መግለጫ መድረኮችን ሁሉ እደግፋለሁ ። ሁለት ነገሮች ደግሞ አልወደድኩልዎትም ። በምርጫ ይሁን በግዴታ ዝም በል የሚለኝን ሰው እንቀዋለሁ ። የኔ ትምህርቴም የግል ባህሪየም ዝም እንድል አይፈቅዱልኝም ። ስለዚህ ዝም እንደማልል እንዲያውቁልኝ ፍላጎቴ ነው ። በሰዎች መብት ላይ ስንስማማ ቆይተን  ስናበቃ አበበ በለው ላይ  “በሳምንት መጨረሻ አንድ ቀን ለሚመጣ ቱሪናፋ” ብለውታል ። አዘንኩብዎ በጣም አዘንኩ ። አበበ ላይ ቂም የያዙበት ነገር እንዳለ ተሰማኝ ። አዲስ ድምፅ ራዲዮም በነጻዋ አገረ አሜሪካ ፡ በነጻነት ሃሳብን መግለጫ መድረክ ነውና የእሱም መብት እንዲከበርለት መጣር ይኖርብናል  ።

 

አበበ በለው የጻፈውን ደብዳቤ በተመለከተ የጠቀስኩት አሁንም ከመብት ጋር የተያያዘ እንጂ እርስዎ እንዳሉት አርበኞች ግንቦት 7ን ለመጎሸም እንዳልነበረ ሊያውቁልን እፈልጋለሁ ፤ ይህ የርስዎ ትርጉም ነው ። እዚህ ላይ ፍንትው ብሎ እንዲታይዎ የምፈልገው አንድ ነገር አለ ።እኔ አርበኞቹን እንደቱሪስት መስህብ ለቀናት ብቻ አይደለም ጎብኝቻቸው የመጣሁት ። ወይም በሪሞት ኮንትሮል በቴሌቪዥን መስኮት አይደለም የማውቃቸው ። እኔ አርበኞቹን ደጋግሜ ተመላልሼ ፤ አንዴ እንዳውም ለስድስት ወራት ቆይቼ የሚበሉትን በልቼ የሚጠጡትን ጠጥቼ አብሬያቸው ኖሬ አውቃቸዋለሁ ። በኢሳትም ሆነ በሌሎች ሚዲያዎች የሚቀርቡትን ተዋጊዎች ፎቶዎች በስም እየጠቀስኩ ልነግርዎ እችላለሁ ።  የትኞቹ የድምሕት የትኞቹ ደግሞ የአርበኞች እንደሆኑም እየለየሁ ልነግርዎ እችላለሁ ።  ስለዚህ በኔ በኩል የምጎሻሸምበት ምንም ምክንያት የለም ።

 

እንዲያውም የኤርትራ ልምዴንና ያየኋቸውን ሁኔታዎች ሁሉ ፤ በቅርቡ በተከታታይ ካሉኝ የፎቶና የፊልም ክምችት ጋር እያያያዝኩ  አቀርባቸዋለሁና  እንዲከታተሉ እጋብዛለሁ ።

 

አዎ መብት ማክበርን ልማዳችን እናድርግ ። ሮም ሲሄዱ እንደሮማውያን እንደሚባለው የምንኖርበትንም አገር ህግ ማክበር የተገባ ነውና እናክብር ። አቶ ቢላል አበጋዝ ሆይ ፤ ጌታ ክርስቶስ ጤናዎን እንዲጠብቅልዎ  እፀልያለሁ ። ቸር ይግጠመን ።

 

 

 

ጁላይ 8 2015 ፡

ከላስ ቬጋስ ኒቫዳ ።

 

 

 

 

 

 

 

The post በሄኖክ ሰማእግዜር ላይ ለተፃፈ አስተያየቴ ፤ ይድረስ ለስርጉተ ስላሴና  ለቢላል አበጋዝ appeared first on Zehabesha Amharic.

የ ያ ትውልዱ አቶ ክፍሉ ምንድን ነው የሚሉ? –ይገረም አለሙ

$
0
0

 

kiflu tadesseአቶ ክፍሉ ታደሰ ወዴት እየሄድን ነው በሚል ርዕስ ኢህአፓ ሲፖዚየም ላይ ያቀረቡት ያለውን  ጽሁፍ ዘሀበሻ አስነበበን፡፡  ጽሁፉን ማንበብ ስጀምር አቶ ክፍሉ የያ ትውልድ ወኪል ናቸውና፣ ከጉልምስና እስከ እርጅና በፖለቲካው ያሳለፉ/ያሉ ናቸውና በጽሁፋቸው መነሻና መድርሻ የጠቀሱትን የእንቧይ ካብ መሰረት ካኖሩ ሰዎችም አንዱ ናቸውና ወዘተ ትናንትን አስታውሰው የ40 አመቱ ትግል መስዋእትነት እንጂ ድል ያልታየበትን ምክንያት ይነጉሩናል፣ ዛሬን ዳስሰው ከወያኔ አገዛዝ የመላቀቂያውን መንገድ ያመላክቱናል፣ ስለነገ አልመው ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መመስረት ስለመቻያው ዘዴ ይጠቁሙናል የሚል ጉጉት ነበረኝ፡፡ ግና በዚህ መልክ አላገኘሁትም፡፡  በአንድ ነገር ግን ከአቶ ክፍሉ እስማማለሁ፡፡ ኢህአዴግን ለማሸነፍ የሚደረገውን ትግል ያክል ከዛስ በኋላ ለሚለው ዛሬውኑ መስራት እንደሚገባ፡፡

አቶ ክፍሉ ምኒልክን  ለውይይት የቀረበ ጽሁፋቸው  አብይ ማጠንጠኛ የማድረጋቸው ምክንያት ባይገባኝምና ከጽሁፉም መረዳት ባይቻልም ምንሊክ፣ የተፋላሚ ሀይሎች አጀንዳ የሆኑበት ወቅት ነው በማለት ምኒልክን በተመለከተ አለ ያሉትን ልዩነት  ነግረውናል፡፡ ስለ ያ ትውልድ እንደ ሁልግዜአቸው ድክመት ስህተቱን ሳይነኩ አስታውሰውናል፡፡ እኛና እነሱ አንድነትና ልዩነታችን ብለው አንድነታቸውን ሳይነኩ  የልዩነቶቻቸው ማሳያ ያሉዋቸውን  አቅርበውልናል፡፡እንዲህ እንዲህ እያሉ ስጋት አጭረው ጥያቄ አስቀምጠው ሰባት ገጽ የሄዱበት ጽሁፍ በቅጡ ሲታይ  ለማስተላለፍ የፈለጉት ወቅታዊ ጉዳይ ሶስት መስመር በማይሞላ የሰፈረው ሆኖ እናገኘዋለን ፡፡  እንዲህ ነው የሚለው፡፡

“በአጠቃላይ፣ በአሁኑ ሁኔታ የኢትዮጵያን ችግር ባልተማከለና በተናጠል በሚካሄድ የትጥቅ ትግል ለመፍታት የሚደረገው ሙከራ፣ መፍትሄ በማምጣት ፈንታ አገሪቱ እንድትበታተን ተጨማሪና አጋዥ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ ተገቢ ነው። ”

ጥያቄ አንድ፤ ይህን ለማለት ይህ ወቅት ለምን ተመረጠ?

እንደለመድነው ማለባበሱን ካልመረጥነው በስተቀር በግልጽ መረዳት የሚቻለው ይህ ወቅት የተመረጠው አርበኞች ግንቦት ሰባ ውጊያ ጀመርኩ በማለቱ ነው፡፡ሁለቱም ድርጅቶች አላማና የትግል ስልታቸው በውል ይታወቃል፤ ተዋሀድን ሲሉ እየተዘጋጀን ሲሉ ወራ ተቆጥረዋል፣ታዲያ አቶ ክፍሉ የአርባ አመት ልምዳቸው የሀገራችን ችግር በትጥቅ ትግል አይፈታም የሚል ድምዳሜ ላይ እድርሶአቸው ከሆነ ለምን ያኔ  ይህን ሀሳብ አላነሱም፡፡ ወይንስ አያደርጉትም ብለው ንቀዋቸው?

ጥያቄ ሁለት፣ ባልተማከለና በተናጠል ሲሉ የእነተባበርን ጥሪ አልሰሙም ማለት ነው?

ጥድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነነኝ እንዲሉ በአንድ ማእከል እየተመሩ መታገሉ ቀርቶ  ተደጋግፎ መቆም እጅ ለእጅ ተያይዞ መራመድ ቢቻል መልካም ነበር፡፡ ግን ለዚህ አልታደልንም ፡፡ አሸነፈና አቸነፈ በሚል የፊደል ልዩነት ሳይቀር እስከ መገዳደል የደረሰው የእነ አቶ ክፍሉ ያ ትውልድ ያመጣው  ያለመስማማት በሽታ እስከ ዛሬ መድሀኒት አልገኝለት ብሎ  በግለሰብ ደረጃም ሆነ በፓርቲ መተባበሩ ቀርቶ መከባበሩ አይታይም ፡፡  የወያኔ አገዛዝ ሀያ አራት አመት የዘለቀውና መቶ በመቶ አሸነፍኩ እያለ ለመመጻደቅ የበቃውም በዚሁ ምንያት መሆኑን አሌ የሚል አይኖርም፡፡ ታዲያ ለበሽታው መድሀኒት መፈለግ ነው  የሚበጀው ወይንስ እንደምንም ብለው አንድ ርምጃ ለመሄድ የሚጥሩትን ለማሰናከል መሞከር?

ብዙዎች ቃልና ተግባራቸው አልገጥም እያለ በምንቸገርበት፤ብዙዎች ያልሆኑትን ነን እያሉ በሚያጭበረብሩበት  ብዙዎች ከተግባሩ ሳይኖሩ በቃላት እያደናገሩ በሚኖሩበት ወዘተ ወቅት ጥቂቶች  ቃላቸውን በተግባር ማሳየት ሲጀመሩ ያልተማከለና በተናጠል የሚካሄድ ትግል  በማለት ትግሉን ለማሳነስና ይበልጡንም በህብረተሰቡ ውስጥ ፍርሀት ለማንገስ መሞከር ተቢ አይሆንም፡፡  ትግሉን በተግባር የጀመሩት እነዚህ ወገኖች ትንሽ ትልቅ ሳንባባል፤ሰበብ ምክንያት ሳናበዛ ኢትዮጵያን ከወያኔ አገዛዝ ለማላቀቅ ነው የምንታገለው የምትሉ ሁሉ እንነጋገር እንተባበር በማለት ከመጠየቅ አልፈው ሲለምኑ ሰምተናል፤ምስክሮች ነን፡፡ አላማቸው ራስን ለቤተ መንግሥት ማብቃት ሳይሆን የኢትዮጵያን ሕዝብ የስልጣን ባለቤትነት ማረጋገጥ የሆነ ወገኖች ተጠራርተው በውህደትም በመተባበርም አቅም ፈጥረው አንድ ርምጃ መራመድ ሲጀምሩ ፈጥኖ ወጥቶ በተናጠል የሚካሄድ ያልተማከለ ትግል በማለት የአግድሞሽ መኮነንና በህብረተሰቡ ውስጥ ስጋት ለመጫር መመኮር የመጣንበት የሴራ ፖለቲካችን በአርባ አመቱም አለማረጀቱን ነው የሚያሳየው፡፡

ጥያቄ ሶስት አቶ ክፍሉ   ተቆርቋሪ የሆኑ ወገኖች አንድ ጥያቄ ሊያነሱ ይገባል፤ ከፊታችን የተደቀነው ትልቁና ሀገራዊው ግዴታ ኢህአዴግን መጣል ወይስ አገርን ማዳን የሚል ነው? ሲሉ ምን ማለታቸው ነው?

ኢህአዴገን ማሸነፍና አገርን ማዳን አንድ ላይ የሚታዩና የሚከናወኑ ሆነው ሳለ የተለያዩ ተግባራት ሆነው ሲበዛም ጥያቄ ተደርገው መቅረባቸው  በተለይ ደግሞ ከተነሱበት ወቅት አንጻር ሲታዩ በውስጣችን ስር ከሰደደው  የመደጋገፍ ሳይሆን የመጠላለፍ ፖለቲካ ዛሬም አለመላቀቃችንን  የሚያሳይ ነው፡፡ ወያኔዎች እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ ትበታተናለች የሚሉት አይነት መልእክትም በውስጡ ይታያል፡፡ ወያኔን መጣል ሀገር የማዳን ከፊል ተግባር ነው ኢትዮጵያን የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት፤ ሰብአዊ መብት የተከበረባት ዴሞክራሲያዊት ሀገር ማድረጉ ደግሞ ቀጣይ ተግባር ነው፡፣ስለሆነም ሁለቱ ወይስ በሚል አማራጭ ተነጣጥለው መቅረብ አይኖርባቸውም፡፡ ኢህአዴግ በሥልጣን ላይ እያለ ኢትዮጵያን ማዳን የሚቻልበት ዘዴና መንገድ አለ ካተባለ በስተቀር፡፡

ያ ትውልድ ደርግን እየተቃወመ በአንጻሩ የእኔ ብቻ ትክክል በሚል አስተሳሰብ፤ ተደጋግፎ ማለፍን ሳይሆን ጠልፎ መጣልን በተካነ የሴራ ፖለቲካ  ርስ በርሱ እስከመገዳደል በደረሰ ጠላትነት እየተቀዋወመ እንዳይሆኑ ሆኖ መከራ አወረሰን፡፡

የኢህአዴግ ተቀዋሚዎችም(አርባ አመትም አራት አመትም የሚሆናቸው በውጪም በውስጥም የሚኖሩ በሰላማዊም በጠመንጃም እንታገላልን የሚሉ)  ወይ ተባብረው መታገል ወይ ተከባብረው አንተም በመንገድህ እኔም በመንገዴ ብለው መታገል ተስኖአቸው ከጥሎ ማለፍ ጨዋታ መውጣት፣ ከሴራ ፖለቲካ መላቀቅ አልሆንልህ ብሎአቸው  ወያኔ ተደላድሎ እንዲገዛን አበቁት፡፡አንድ ተቀዋሚ ፓርቲ ጠንክሮ ታግሎ ለስልጣን ከሚበቃ የወያኔ አገዛዝ ቢቀጥል የሚመርጡ ይመስል ቀና ብሎ መራመድ ሲጀምርና ጠንከር ብሎ መታገሉ ሲታይ ጠልፎ ለመጣል የተካኑበትን ስራ ይጀምራሉ  ሴራ ይጎነጉናሉ፡፡በዚህም ተያይዞ ዘፍ ይሆንና፡ለገዢው ምቹ ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡

እነ አቶ ክፍሉ በግዜአቸው ታግለዋል፣ከመሪዎቹ በላይ ያ ወጣት በድፍረቱ በጽናቱ በተግባር ሰውነቱ ይደነቃል፡፡ ትግላቸው ግን መሪዎቹን ለስደት ወጣቱን ለእልቂት ሀገሪቱን ለወታደራዊ አንባገነን አገዛዝ ከመዳረግና እስከ ዛሬ ለቀጠለው ፖለቲካዊ ችግራችን አንዱ ምክንያት ሆኖ ከመጠቀስ ባለፈ ያስገኘው ድል ያስመዘገበው ውጤት የለም፡፡ በመሆኑም ዛሬ በግል ከእነ አቶ ክፍሉ በወል ከኢህአፓ (በተግባር ካለ)የሚጠበቀው አቶ አሰፋ ጫቦ ደጋግመው ይሉት እንደነበረ የድርሻ ተጠያቂነትን በድፍረት ወስዶ የእንቧይ ካብ ያሉትን መሰረት ያቆሙ እነርሱ ናቸውና የእንቧይ ካቡ ወደ ድንጋይ ካብ የሚቀየርበትን መንገድ ማመላከት ነው፡፡ የአሸነፈና አቸነፈ ልዩነት ያመጣውን መዘዝና ያስከተለውን እልቂት ያውቃሉና ልዩነትን በውይይት መፍታት እንዲቻል ግንባር ቀደም ሆኖ በቃል ሳይሆን በተግባር መሰለፍ ነው፡፡ተነጣጥሎ ትግል ለየብቻ መውደቅን እንደሚያስከትል በተግባር አይተዋልና የተራራቀውን አቀራራቢ የተጣላውን አስታራቂ ሆኖ መቆም ነው፡፡

ትናንት ዛሬ አይደለም፣ የሀገሬ ገበሬ እንኳን ይህን ሲገልጸው በትናንት በሬ ያረሰ የለም ይላል፡፡እናም የትናንቱ አልጠቀመንምና ለዛሬ የሚበጀንን ለነገም ወንዝ የሚያሻግረንን  በጋራ ማየቱ መልካም ይሆናል፡፡ እኔ ከሌለሁበት፣ እኔን ለስልጣን የማያበቃኝ ከሆነ፤ እኔ ካልመራሁት ወዘተ ከሚል ለመተባር ጠንቅ ከሆነና ትግሉን ሲያኮላሽ ከኖረ አስተሳሰብ ወጥቶ ኢትዮጵያን ከወያኔ አገዛዝ በማላቀቅ የህዝብ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት ሀገር ለማድረግ በግል፣ በድርጅት ብሎም በጋራ እንዴት እንንቀሳቀስ ብሎ ሁሉም የሚችለውን ለማበርከት መነሳቱ እንጂ ለማደናቀፍ ማለሙ ትናንትም አልበጀ ዛሬም ሆነ  ወደ ፊትም አይበጅም፡፡ ስለሆነም መጠላለፉ መወራረፉ ያለፈው ይበቃል፡፡  በዚህቺ የሎሬት ጸጋየ ገብረ መድህን ግጥም ሀሳቤን ልቋጭ፡

መተባበር የተሳነው ስንቱ ልቡ ቲአቲረኛ

ዲስኩር ፈታይ ላንቲከኛ

ቆምኩልህ ለሚለው ወገን ተአማኒነቱን ረስቶ

በትረ መንግሥት ለመጨበጥ ለነገ ሥልጣን ዋዥቶ

የዓለምን በደም መታጠብ እንዳላየ ሆኖ አይቶ

በተቃውሞ መተባበር ጥቅሜን ይጎዳል ሲል ሰግቶ

ልክ እንደ ገደል ማሚቶ

ይዋነያል በልሳኑ የራሱን ቃል ራሱ ሰምቶ፣

ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይጠብቅ፣

The post የ ያ ትውልዱ አቶ ክፍሉ ምንድን ነው የሚሉ? – ይገረም አለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.


5ቱ የዞን 9 ጦማርያን አባላት እና ጋዜጠኞች ከአንድ ዓመት በላይ እስር በኋላ ተፈቱ :: የአፈታታቸው ሁኔታ ጠበቃውን ጨምሮ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል

$
0
0

5ቱ የዞን 9 ጦማርያን አባላት እና ጋዜጠኞች ከአንድ ዓመት በላይ እስር በኋላ ተፈቱ ::
የአፈታታቸው ሁኔታ ጠበቃውን ጨምሮ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል
zone 9 today

The post 5ቱ የዞን 9 ጦማርያን አባላት እና ጋዜጠኞች ከአንድ ዓመት በላይ እስር በኋላ ተፈቱ :: የአፈታታቸው ሁኔታ ጠበቃውን ጨምሮ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል appeared first on Zehabesha Amharic.

የህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ የጥብቅና ሙያቸው ኮሚቴዎቹ የጥፋተኝነት ብይን በተላለፈበት ቀን መሰረዙ ታወቀ

$
0
0

ጠበቃ ተማም አባቡልጉ

ጠበቃ ተማም አባቡልጉ


ሰበር ዜና ቢቢኤን
ቢቢኤን ሃምሌ 2/2007

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ጠበቃ የሆነው ጠበቃ ተማም አባቡልጉ በፍርድ ቤት ላይ በሚያደርጋቸው ክርክሮች በተለይም መንግስት ከጅሃዳዊ ሀረካት ጀምሮ የሰራቸውን ሸፍጦችና ኢትዪጲያዊ ውስጥ የፍትህ ስርአቱን ዝቅጠት በመረጃና በህግ በማጣቀስ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ በማጋለጣቸው ምክኒያት ከዚህ ክስ ተመስርቶባቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ማስፈራሪያና ዛቻዎች ከመፈጸማቸውን ሌላ እብድ በሚመስል ሰው በመላክ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ይታወቃል፡፡

ይህ ሁሉ ግፍ ተፈጽሞባቸው በጀግንነት ከስራቸው ያልቆሙት እንዲሁም የህግ ክፍተቶችን ጭምር በማጋለጥ፤ ከኮሚቴዎቹ በተጨማሪ መንግስት የከሰሳቸው የነ አብራ ደስታ ጠበቃ የነበሩትን ተማም አባቡልጉን መንግስት በኮሚቴው ላይ የጥፋተኝነት ብይን ባስተላለፈበት እለት የጥብቅና ሙያቸውን ፍቃድ ፍትህ ሚኒስትር መሰዘረዙ ታውቋል፡፡
አቶ ተማም አባቡልጉ ያለ ምንም ፍርሃት እውነታውን በሚዲያዎች ላይ በማጋለጥ ታላቅ አስተዋጾ ያበረከቱ፤ በብዙዎች ዘንድ በጀግንነት የሚጠሩ ፤ ፤ለሙያቸው ያደሩ ጠበቃ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ቢቢኤን ጠበቃ ተማም አባቡልጉን በማነጋገር ተጨማሪ መረጃ ይዞ የሚቀርብ ይሆናል::

The post የህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ የጥብቅና ሙያቸው ኮሚቴዎቹ የጥፋተኝነት ብይን በተላለፈበት ቀን መሰረዙ ታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

2 ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን እስር ቤት ሆና ያሸነፈችው ርዕዮት ዓለሙ

$
0
0

reyot
ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ተፈታች

(ዘ-ሐበሻ) ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ ትናንት ጁላይ 9 ቀን 2015 ዓ.ም የ እስር ጊዜዋን አጠናቃ ተፈታች። የመንግስት ሚድያዎች ጋዜጠኛዋ የአመክሮ ጊዜ ተሰጥቷት እንደተለቀቀች አድርገው ቢዘግቡም እውነታው ግን ርዕዮት የአመክሮ ጊዜዋን ጨርሳ የነበረው ባለፈው ጥቅምት ወር ነበር።

በሽብር ወንጀል ተከሳ 14 ዓመት ተፈርዶባት የነበረችው ይህችው ጋዜጠኛ በይግባኝ ቅጣቱ ወደ 5 ዓመት ዝቅ ብሎላት የነበረ ሲሆን እነዚህን ዓመታት በእስር አሳልፋ ከቤተሰቦቿ ጋር ተቀላቅላለች።

በእስር በነበረችበት ወቅት በሚደርስባት የሰብአዊ መብት ጥሰት የርሃብ አድማ እስከማድረግ ደርሳ የነበረችው ርዕዮት እህቷ እስከዳር ዓለሙ ሳይቀር እንዳትጠይቃት ታግዳ እንደነበር የሚታወስ ነው።

ባለቤቷ ጋዜጠኛ ስለሺ ሃጎስ አንድነት በጠራው ስብሰባ ላይ ተገኝቷል በሚል በፖሊስ ጉዳት የደረሰበት መሆኑም ይታወሳል። ር ዕዮት እስር ቤት እያለችም የዩኔስኮን የፕሬስ ነፃነት አዋርድ እንዲሁም በዓለምአቀፉ የሴቶች የመገናኛ ብዙኃን ድርጅት – International Women’s Media Foundation – IWMF “በጋዜጠኝነት ለተሠራ ጀብዱ ሽልማት” የሚል አዋርዶችን አሸንፋለች።

The post 2 ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን እስር ቤት ሆና ያሸነፈችው ርዕዮት ዓለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

ጥቂት ስለአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጊ አርበኛ ሃና –ከጋዜጠኛ መሳይ መኮንን

$
0
0

የርዕዮትን: የማህሌትንና የኤዶምን ከህወሀት ማጎሪያ እስር ቤት ነጻ መሆን ውስጤ የፈጠረውን ደስታ እያጣጣምኩ እያለ ድንገት በትዝታ አምስት ወራት ወደ ሁዋላ ሄድኩኝ- -ከኤርትራ በረሃ:: ይህቺን ኢትዮጵያን ከህወሀት እስር ቤት ነጻ ለማውጣት ብረት ያነሳችውን እህታችንን ላስተዋውቃችሁ::
arbegnoch
አርበኛ ሀና ትባላለች:: የ23 ዓመት ወጣት ናት:: የአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጊ ወታደር ስትሆን በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ተሳትፋለች:: በኤርትራ በረሃ ስማቸው ከጀግንነት ጋር ከሚነሳላቸው አርበኞች መሃል ሀና ግንባር ቀደም ናት:: ስሟ በአርበኞች መንደር ገኖ ይነሳል::
………አንድ ጊዜ ላይ እንዲህ ሆነ::

ሀና የምትገኝበት ወታደራዊ ክፍል ግዳጅ ይሰጠዋል:: እስከ 30 የሚጠጋ አርበኛ የሚገኝበት ይህ ቡድን የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጦ በመግባት በአንድ የህወሀት ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ፈጽሞ የመመለስ ግዳጅ ተሰጥቶት ይሰማራል:: ሀና መትረየሷን ታጥቃለች:: ጠዋት ከመነሻቸው ወደ ኢላማ ቦታው ገሰገሱ:: እንደታቀደው ድንገተኛ ጥቃቱ ተሰንዝሮ የታሰበውን ጉዳት አድርሰው ወደ ካምፓቸው ሊመለሱ እያለ ድንገት በህወሀት ሰራዊት ይከበባሉ:: ምን ይደረግ? ብዙ ቁጥር ያለውንና እስከአፍንጫው የታጠቀውን የህወሀት ሰራዊት መክቶ ወደ ካምፕ መመለስ ከባድ ሆነ:: የዚህን ጊዜ ነበር አንድ ጀግና ታሪክ የሰራችው:: ….ሀና::

መትረየሷን መተረች:: ገዢ መሬት ያዘች:: ቦታዋን አስተካከለች:: ….እሷ መስዋዕት ሆና የትግል ጓዶቿን ልታስመልጥ ወሰነች:: ምሽት እየመጣ ነው:: ጓዶቿ ተስናበቷት:: ዳግም በህይወት እንደማያገኟት ታወቃቸው:: …እሷ መትረየሷን ወደ ህወሀት ሰራዊት ለቀቀችው:: ለጓዶቿ ሽፋን በሚሰጥ ስልት አስካካችው:: …ፍልሚያው በአንዲት ሀና እና በህወሀት ሰራዊት መሃል ሆነ:: የሀና መትረየስ ያስካካል:: ጓዶች በዚያ ሽፋን ወደ ጦር ካምፓቸው እየተመለሱ ነው:: የሀና የመትረየስ ድምጽ እየራቃቸው ነው:: እነሱ ይተርፉ ዘንድ አንድ አርበኛ መስዋዕት መሆን ግድ አለ:: በተሰጣቸው ግዳጅ ውጤታማነት እየተደሰቱ የሃናን መስዋዕትነት እያወደሱ ከካምፓቸው ምሽት ላይ ደረሱ:: በአርበኞች መንደር ህይወት እንዲህ ናት:: ታጋይ ይሰዋል:: ትግል ይቀጥላል::

…እኩለ ሌሊት ከመድረሱ በፊት ነው:: ጭው ካለው የኤርትራ በረሃ አንድ ሰው ወደ አርበኞቹ መንደር ከኢትዮጵያ ድንበር አቅጣጫ ይገሰግሳል:: በርቀት የተመለከቱት የሌሊት የካምፕ ተረኛ ዋርዲያዎች(ጠባቂዎች) መሳሪያቸውን አስተካክለው ጣት ከቃታ አገናኝተው ወደ ካምፑ እየገሰገሰ ያለውን ሰው ይጠብቃሉ:: ውድቅት ሌሊት ስለነበር ማንነት መለየት አልተቻለም:: የሚገሰግሰው ሰው እየቀረበ ሲመጣ ዋርዲያዎቹም ኢላማቸውን አስተካክለው እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጁ:: ….ሰውዬው ቀረበ:: ሴት ናት::ሃና:: ዋርዲያዎቹ አላመኑም:: የዕለቱን የይለፍ ቃል ጠየቋት:: መለሰችላቸው:: ደክሟታል:: ተአምር የሚያሰኘው ከዚይ የህወሀት ሰራዊት ከበባ ማምለጧ አይደለም:: ሁለት የጦር መሳሪያዎችንም ማርካ ተሸክማለች:: ከሷ መትረየስ ጋር ሶስት:: ዋርዲያዎቹ በሚያዩት ነገር ተደንቀዋል:: በአርበኞች መንደር ስለ ሃና እርም ወጥቷል:: ጉድ ተባለ::

….ሃናን በአካል ሳገኛት በጣም ቁጥብ ነበረች:: ብዙ አትናገርም:: ታሪኳን እንድታጫውተኝ ያደረኩት ጥረት አልተሳካም:: ሲበዛ ዝምተኛ ናት:: ጀግና አይናገርም::
…ሃና ከሰሞኑ ውጊያዎች በአንዱ እንደተሰለፈች እገምታለሁ:: ልብን በኩራት በሚያሞቀው ጀግንነቷ ሁሌም አስታውሳታለሁ:: የጣይቱ ልጅ!!!!!

The post ጥቂት ስለአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጊ አርበኛ ሃና – ከጋዜጠኛ መሳይ መኮንን appeared first on Zehabesha Amharic.

ትምህርት ሰጭ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ስብሰባ በዋሽንግተን ዲሲ * –ከእሸቴ ውለታው

$
0
0

ዘ-ሐበሻ ተከታታይ ቭዲዮዎችን እስከምትለቅ ድረስ ይህን ዘገባ ያንብቡ

ዘንድሮ ለ32ኛ ጊዜ በሰሜን አሜሪካ የስፓርት ፈዴሪሽን የተዘጋጀው የእግር ኮስ ጨዋታ በሜሪላንድ ግዛት ዋሽግተን ነበር ሜሪላንድ በውብ ኢትዪጵያውያን አምራና ተውባ ነበር የከረመች።
Elias Kifle

Kinfu Asefa

Soliana

Asegede Gebresilase

Aklog Birara

Dawit Tegegne
የዘንድሮ እግር ኮስ ዝግጅት እንደወትሮው ነገር ግን በጣም ባማረና በደመቀ ሁኔታ የእግር ኳስ ጨዋታው ፣ የንግድ ልውውጡ፣ባህላዊናዘመናዊ የሙዚቃ ፊስቲቫሉ ፣ኢትዪጵያን መሰረት ያደረገ ፓለቲካ ስብሰባዎችና ሰላማዊ ሰልፎች ወዘተ የተከናወነበት ነው።

በሁሉም ክንውኖች አቅም እንደፈቀደ ተሳታፊና ታዳሚ ሁኛለሁ ከሁሉ በላይ አቅሌን የሳበኝና የማረከኝ በአዲስ ድምፅ ራዲዪ በአበበ በለው አዘጋጅነት የነበረው የጋዜጠኞችና የሜዴያ አዘጆች ሚና በኢትዪጵያ የዲሞክራሲና የነፃነት ትግል ምን መሆን አለበት? በሚል የመወያያ ርእስ የቀረበው ውይይት እጅግ አስተማሪና ሚዲያዎች ያለባቸውን ችግር በግልፅ የተነጋገሩበት በመሆኑ በአይነቱ የተለየ ነበር።

በዚህ ስብሰባ በፓናል የውይይት አቅራቢ የነበሩት ታዋቂው፣ አንጋፋው ኢኮኖሚስትና አክትቢስት ዶ/ር አክሎክ ቢራራ ፣ የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ሶሊያና ሽመልስ፣የኢትዩጵያ ሪቭው አዘጋጅ ኢልያስ ክፍሌ፣የኢትዪጵያ ሜዲያ ፎረም (EMF) አዘጋጅ ክንፉ አሰፋ፣ ታዋቂው አክቲቭስት አበበ ገላውና የአዲስ ድምፅ አዘጋጅ አበበ በለው በየተራ ርእሱን መሰረት በማድረግ በሳልና ጠቃሚ ንግግር አድርገዋል።

የስብሰባው መሪ አቶ ዳዊት ተገኘ በመጀመሪያ ንግግራቸው ባለፈው ሀያ አራት ዓመት አምባገነኑን የወያኔን ኢህአደግ አስተዳደር በህዝባችን ላይ የሚደርሰውን ኢስብአዊ የሆነ ጭፍጨፋና ግድያ፣ ህዝባችንን በዘርና በኃይማኖት በመከፋፈል ማቆሚያ የሌለው እልቂትና ፍጅት በመፍጠር የሚሰራቸውን ሴራና ደባዎችን በማጋለጥና መረጃ በመስጠት፤ በተለይ በምርጫ 97 ኢትዪጵውያን ጋዜጠኞች የሰሩት ስራናያደረጉት አስተዋፅኦ በታሪክ የሚረሳ አይደለም።

እንደ እውነቱ ከሆነ ይህን ሥርአት ፊት ለፊት የታገሉትና እርቃነን ሥጋውን በማጋለጥ ለኢትዪጵያ ህዝብና ለዓለም ህብረሰብ ያሳወቁት ኢትዪጵያውያን ጋዜጠኞችና የሜዴያ ሰዎች ናቸው። በውጭም ማለት በዲያስፓራው ህዝቡን በማነቃነቅና በማደራጀት መረጃ በመስጠት፣ ትግሉና ምርጫ ለውጤት እንዲደርስ ከማንም በላይ ከፊት ሁነው የሰሩት በውጭ አገር ያሉ ጋዜጠኞች ና የሚድያ ሰዎች ናቸው። ለአብነት ያህል ከመሀላችን ካሉት የኢትዪጵያ ሪቭው አዘጋጅ ኢልያስ ክፍሌ፣ የኢኤምኤፍ (EMF) አዘጋጅ ክንፈ አሰፋ፣ የአዲስ ድምፅ አዘጋጅ አበበ በለው እነዚህ ወንድሞች በምርጫ 97 በተደረገው ትግልና ለቀጣዩ የዲሞክራሲ ና የነፃነት ትግል መሪ ተዋናይና ግንባር ቀደም አንቂና አስተባባሪዎች ናቸው ለእዚህ ነው አምባገነኑ የወያኔ ሥርዐት በለሉበት የረጅም አመት እድሜ የፈረደባቸው ዘረኛውን የወያኔ ከፋፋይና ፀረ ዲሞክራሲና አፋኝ ሥርዐት በሰላ ብእራቸው በማጋለጣቸውና በመታገላቸው በአምባገነኑ ሥርአት ሰለባ ሁነው በመከራ ቤት በእስር የሚገኙትን እነ እስክድር ነጋን፣ርእዪት አለሙ፣እነ ተመስገንን፣እነ ውብሸትን ወዘተ ስናስታውስ እና ለዲሞክራሲና ለነፃነት በመናገራቸው ና በመፃፋቸው ከግፈኛው ስርአት ደህንነቶች አምልጠው የሚወዶቸውን ልጆቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ተለይተው ሳድይወድ በግድ ተሰደው በባእድ ሀገር በአፍሪካና በመካከለኛ አረብ በስደትና በመከራ ያሉት ስናስውስ የኢትዩጵያ ጋዜጠኞችና የሚድያ ሰዎች ይህን ሥርአት ምን ያህል እንደታገሉትና ዋጋ እንደከፈሉበት የሚሳይ ነው።

አቶ ዳዊት ንግግሩን በመቀጠልበእስር፣ በግዞትና በስደት የሚገኙ ጋዜጠኞች መስዋአትነት የሚስተምረን ሁለት አደራ አለ። አንደኛው ለማይቀረው የነፃነት ትግል በርትተንናተጠናክረን እንድንታገል። ሁለተኛው ኢትዪጵውያን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሊኖራቸው ስለሚገባ የዲሞክራሲ መብት ማለት የመናገር፣የመፃፍ፣የመደገፍ፣ የመቃወምና የመተቸት ወዘተ.. እንደ ሰው ልጅ ማግኘት ማስከበርና ለዚህ የዲሞክራሲ መብትና ነፃነት በየትኛው ደረጃና በየትኛውም ቦታ መታገል እንዳለብን; በእነርሱ መስዋእትነት አስተምረውናል:: አደራ ብለውናል:: ከዚህ አንፃር እናንተ በውጭ ማለት በዲያስፖራ የምትገኙ ጋዜጠኞች ና የሜዴያ ሰዎች ምን ያህል ነፃ ናችሁ? ለህዝብ የምታቀርቡት ዘገባና ዜና ምን ያህል ከቀረቤታና ከፓለቲካ ድርጅት አፍቃሪነት ገለልተኛ ነው? የፓለቲካ ድርጅቶች ገለልተኛና ነፃ ሜዲያ መሆናችሁን አምነው ምን ያህል መብቶቻችሁን ያከብራሉ? የመሳሰሉት ጥያቄዎች በማቅረብ ለስብሰባው ታዳሚ ውይይቱን ክፍት አድርገውታል።

በቤቱ ተመሳሳይ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበዋል:: አብዛኛውን ከቀረቡት አስተያያቶች በአብዛኛው ያነጣጠረው የግለሰቦችን የመናገርናየመተቸት መብት እየተጋፋ ያለው ግንቦት ሰባት በሀገራችን ጉዳይ በተለይ ኤርትራና ሻዕቢያ በተመለከተ የሚደረጉትን ውይይቶች ህዝብ እንዳይወያይበትና አስተያየት እንዳይሰጥበት የሚደርገው የጉልቤና የአፈና አካሄድ መቆም አለበት በሀያ አራት አመት ትግል ፀንተው በፀረ ወያኔና ሻቢያ አቆም ታግለው ያታገሉ ወንድሞችን ስለ ሻቢያና ኢሳያስ አፈወርቂ አነሳችሁ በሚል እናንት የወያኔ ተላላኪዎች ተብለው እየተሰደቡ ነው።ይህን አካሄድም ትክክል አለመሆኑና ለማስቆም የድርጅቱ መሪዎች ያደረጉት ጥረት የለም ይልቁንም የድርጅቱ መሰረታዊ ፍልስፍ ናስድብ፣ ጩሆትና አድማ እስኪመስል ድረስ ቀጥለውበታል::

ታዳሜው ይህን አካሄድ ከምንትልገለው የወያኔ ሥርአት ተለይቶ ስለማይታይ አካሄድን እንታገለዋለን:: በተረፈ ትናንት በኢትዪጵያ ሪቭው አዘጋጅ በኢልያስ ክፍሌ ዛሬ በአዲስ ድምፅ አዘጋጅ በአበበ በለው እየተደረገና በመደረግ ላይ ያለው ጋጠ ወጥ ዘመቻ የተሰለፍበትን ድርጅት ሰብእና የሚሳይ ስለሆነ ሊታረም ይገባል። ኢልያስ ክፍሌ ሆነ አበበ በለውን ወያኔ ለማለት ቀርቶ ደጋፊዎች ሌላውም የሞራል ብቃት የላቸውም። በዚህ ጉዳይ በአጽኖኦት የተገለጠው ለግንቦት ሰባት ድርጅትና ለለውጥ ፈላጊው አባላት ከፍተኛ አክብሮት እንዳለው አስምሮበታል::

ድርጅቶችን አንተች የሚለው አባባል ስህተትና ወቅታዊ አለመሆኑ ተተችቶበታል:: ወያኔ ሀያ አራት አመት በግፍና በበደል ህዝባችንን እየከፋፈለና እያሰቃየ በአምባገነንነት መግዛቱን እኛም ያለመስልቸት በፅናት ሀያ አራት ዓመት አጋልጠነዋል:: ነገር ግን ህዝቡን መርተውና አደራጅተው ለድል ያበቁታል ያልናቸው የፓለቲካ ድርጅቶች ህዝቡን ለድልና ለነፃነት አለማብቃት ብቻ ሳይሆን ራሳቸው ወደህብረትና አንድነት ባለመምጣት የትግሉና የፖለቲካው አቅጣጫ ያጡ ይመስላሉ ስለዚህ ድርጅቶችን ራሳቸውን ሊያዩና እንዲፈትሹ ጥሪ ማድረግ እኛም ሆነ ህዝቡ ልንተቻቸውና ልንገመግማቸው ይገባል ይህ አካሄድ ለድርጅቶች ና ለትግሉ ብርታትና ጥንካሪ ይሰጣቸዋል:: የህዝብ ትችት የሚፈራ አምባገነን መንግስትና ራሱን በትእቢት ያሳበጠ ውስጡ በባዶ ጩኸት የሞላ ኃይል ብቻ ነው።

በመጨረሻ በፓናልአቅራቢዎችና በታዳሚው የተደረስበት መንፈስ
1ኛ/ የፓለቲካድርጅቶች፣አባሎቻቸ ውና ሊላው ማህብረተስብ የነፃ ሚድያን ሚና እንዲረድልን ጥረ ማድረግ፣ በሚድያ አቀራረብ በፅሁፍ ዘገባ፣ በዜና ሆነ በቃለ መጠይቅ የሚስራው ጥንቅር አቅራቢው ጋዜጠኛ ህዝብ ሊያውቀው ይገባል ብሎ ያመነበትን የማቅረብ ሙሉ መብት እንዳለው። አዘጋጅው ይህን ማቅረብ የእገሊን ድርጅት ያስከፋብኛል በሚል ስነ ልቦናዊ ሰቀቀን እንዲፈጠር የሚደረገው ዘመቻ መቆም አለበት ድርጅቶች ነፃ ሚዲያዎችን የእነርሱ ልሳን እንዲሆኑ በቀጥታ ሆነ በተዘዋሪ መሞከር ወንጀል ነው።ድርጅቶች የነፃ ሚድያዎችን ሽፋን ማግኘት የሚችሉት በሚሰሩት ሥራና መሪት ላይ በተግባር በሚደርጉት አስተዋፅኦ እንጅ ሚዲያዎችንና አዘጋጆችን በማንቆሸሽ ና በማሸበር አይደለም።

2/ኛ የሜዲያ አዘጋጆች የተመክሮ ልውውጥ ማድረግ አለብን በሚል የህሊና ራዲዮ አዘጋጅ ሳምሶም ውብሽት የሙያ ትንተና ትምህርት ሰጭ በመሆኑና በትክክል ከነፃ ሚድያነት አንፃር እየሰራን ስለመሆኑ ትምህርታዊ ግምገማ ለማድረግ አንድ ፎረም ማቋቋም ጠቃሚ በመሆኑ የአዲስ ድምፅ አዘጋጅ አበበ በለው በአስተባባሪነት ተመርጦ ሌሎች የሚዴያ ባለ ቤቶችን ጨምሮ አንድ ፎረም እንዲቆቆም ተወስኖአል።

3/ኛ በተለይ ዘ ሀበሻ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሄኖክ በሰጠው ማሳሰቢያ መሰረት ለሀገራቸው፣ ለህዝባቸው ነፃነት ሲሉ ሥርአቱን ተችታችኋል; ህዝብን አነሳስታችሆል በሚል በእስር ና በስደት የሚገኙ የጋዜጠኛ ቤተሰቦች ልንረዳቸውና ልናበረታታቸው ይገባል።ሄኖክ በመቀጠል በትናንት ቀን እኔና እዚህ ቤት ያለን የሚድያ ሰዎች የጀግናው ጋዜጠኛ ባለቤት ወ/ሮ ሰርካለምና ልጇን በማየታቸውና በመጎብኘታቸው ከፍተኛ የህሊና ደስታ እንደተሰማው ገልፆ እኛ በውጭ የምንገኝ ጋዜጠኞች፣ የፓለቲካ ድርጅቶችሆነ ዲያስፖራው እነዚህን ለህዝብ ልሳን በመሆን በወይኔ እስር ቤት ያሉ ፋኖ ቀዳጅ የሆኑ ትንና በስደት የሚገኙትን ልንረሳቸው አይገባም:: ስለዚህ የምንመሰርተው ፎረም በአገዛዙ እጅ የወደቁትንና ቧእድ ሀገር የተሰደድትን ጋዜጠኞችንና ቤተሰባቸውን የምረዳበት የምንደግፍበትና የምንዘክርበት መሆን አለበት ብሎል።

በአጠቃላይ ስብሰባው በጥሩ መንፈስና በበሳል አካሄድ የተካሄደ ነበር። ታዳሚው የሁሉንም ማህረሰብ አባላት ያካልተተ ሲሆን የቆየ የፓለቲካ ተመክሮ ያላቸው ፣ የፓለቲካ ንድፍ ፀሀፊዎች፣ ጦማርያንና የፓልቶክ ባለቤቶችን ያከተተ ነበር። በታዳሚነት ካየሆቸው መሀል ታዋቂው የሰብአዊ መብት ተማጎች ኦባንግ ሜቶና ታምረኛው ብእረኛ ተክሌ አበበ ነበሩ።

The post ትምህርት ሰጭ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ስብሰባ በዋሽንግተን ዲሲ * – ከእሸቴ ውለታው appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live