Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ሴቶች የታሰሩት ኮሚቴዎች ነጻ መሆናቸውን መሰከሩ “ሙስሊሙን ጨካኝ ለማስመሰል የሚደረገው ሴራ አይሰራም”

$
0
0

በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሴት ሙስሊሞች ባደረጉት ኮንፈረንስ የታሰሩት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ነፃ መሆናቸውን መሰከሩ:: ሙስሊሞችን ጨካኝ ለማስመስል የሚደረገው ሴራም በቅዱስ ቁርአን የማይፈቅደውና የማይገባ ነው ብለዋል:: ሙሉ ቭዲዮውን ይመልከቱ::
ይህን ታላቅ የሴቶች ኮንፈረንስ ያዘጋጀው ሪሳላ ኢንተርናሽናል ነው::

በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ሴቶች የታሰሩት ኮሚቴዎች ነጻ መሆናቸውን መሰከሩ “ሙስሊሙን ጨካኝ ለማስመሰል የሚደረገው ሴራ አይሰራም”

The post በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ሴቶች የታሰሩት ኮሚቴዎች ነጻ መሆናቸውን መሰከሩ “ሙስሊሙን ጨካኝ ለማስመሰል የሚደረገው ሴራ አይሰራም” appeared first on Zehabesha Amharic.


ሳሞራ የኑስ በዋሽንግተን ዲሲ እጅግ ተዋረዱ * ተቃውሞው ቀጥሏል

$
0
0

samora and azeb
በዋሽንግተን ዲሲ ማንደሪን ኦሪየንታል ሆቴል ድንገት የተገኙት የወያኔው መንግስት መከላከያ ሚኒስተር ጄነራል ሳሞራ የኑስ በኢትዮጵያዊያኑ ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባቸው ውርደትን መከናነባቸውን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ::

በአንድ ለሊት አዳር 12 ሺህ 700 ብር በሚከፈልበት በማንደሪን ኦሪየንታል ሆቴል ያረፉት ጀነራል ሳሞራ የኑስ ከዋሽንግተን ዲሲ ግብረሃይል ወጣቶች ጋር ፍጥጫ ገጥመው ከፍተኛ የሆነ ግብግብ ተፈጥሯል:: አካባቢው በዲሲ ፖሊሶች የታጠረ ሲሆን ሳሞራም ካረፈበት ከዚህ ሆቴል ሊወጣ እንዳልቻለ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ጠቁመዋል::

ኢትዮጵያውያኑ “ኢትዮጵያውያንን የሚያሰቃይ ወንጀለኛ ለፍርድ ይቅረብ” በሚል ሳሞራ ላይ ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ናቸው::

በሽንግተን ዲሲ መጥተው በኢትዮጵያውያኑ ውርደትን ከተናነቡ የወያኔ ተላላኪ ባለስልጣናት ውስጥ ስብሃት ነጋ; ሬድዋን ሁሴን; ሶፊያን አህመድና ሌሎችም ይገኙበታል::

ግብግቡ አሁንም የቀጠለ ሲሆን የደረስንበትን መረጃ እናሳውቃችኋለን::

The post ሳሞራ የኑስ በዋሽንግተን ዲሲ እጅግ ተዋረዱ * ተቃውሞው ቀጥሏል appeared first on Zehabesha Amharic.

ትናኤል ያለምዘውድ ለብይን ተቀጠረ

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር


መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም መስቀል አደባባይ ህዝቡን ከጠራው ሰልፍ ጋር በተያያዘ በትናንትናው ዕለት ለእስር የተዳረገው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ናትናኤል ያለምዘውድ ዛሬ ግንቦት 5/2007 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርቦ ክስ የተሰማበት ሲሆን ለግንቦት 11/2007 ዓ.ም ለብይን ተቀጥሯል፡፡
በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረበው ናትናኤል ቀደም ብለው ክስ እንደተመሰረተባቸው የፓርቲው አባላት በተመሳሳይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 490(3) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲረበሽ አድርጓል የሚል ክስ ቀርቦበታል፡፡
በዕለቱ ተከሳሹ ‹‹ከሌሎች ግብረ አበሮቹ ጋር›› በመሆን ወያኔ አሳረደን፣ ኢቲቪ ሌባ፣ መንግስቱ ናና እያሉ በመናገር ፖሊስ ላይ ድንጋይ በመወርወር ሁከት እንዲፈጠር አድርገዋል መባሉ በክሱ ላይ ተጠቅሷል፡፡ አቃቤ ህግ አሉኝ ካላቸው 5 የሰው ምስክሮች መካከል ሁለቱን ያሰማ ሲሆን ቀሪዎቹን የተለየ አያስረዱልኝም በሚል ሳያሰማ ቀርቷል፤ ናትናኤል በበኩሉ ምንም መከላከል አልፈልግም ብሏል፡፡ ምስክሮቹ ተከሳሹ ‹‹ወያኔ አሳረደን፣ እናት ኢትዮጵያ ያስደፈረሽ ይውደም፣ እኛን ከምትደበድብ አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ደብድብ…›› በማለት ሰልፉን ረብሹዋል ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት ለግንቦት 11/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በሌላ ዜና ናትናኤል ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት በስፍራው ከተገኙት ጓደኞቹ መካከል ዮናስ መኮነን የተባለ ወጣት ፎቶ አንስተሃል በሚል መታሰሩ ታውቋል፡፡
(ሙሉ የክሱን ይዘት ይመልከቱ)

11265050_708951002563894_6433793283434369431_n

The post ትናኤል ያለምዘውድ ለብይን ተቀጠረ appeared first on Zehabesha Amharic.

  የሀገር ሀብት ዘረፋ፤ስደት፤እሥራትና ግድያው እንዲቆም ህወሃትን ከሥልጣኑ አውርደን መጣል ግዴታችን ነው።

$
0
0

   ገብርየ በለው።  

ካልገደሉ አያቆሙንም ነው ያለው ሐብታሙ አያሌው?( ወጣቱ የፖለቲካ መሪ)ሟች ማን ገዳይ ማን?ታጋይ ይሞታል እንጅ ትግል አይሞትም።

    EPRDFፋሽስቱና አረመኔው የህወሃት ቡድን ፀረ-ሕዝብነቱን ፀረ-ኢትዮጵያዊነቱን አጠናክሮ ለ24 ዓመታት ያህል ሲዘልቅ ከባድና ከፍተኛ የሆኑ ጠባሳ የታሪክ አሸራዎችን እያስመዘገበ ማለፉ በግልጽ የሚታወቅ የሚጨበጥና የሚዳሰስ ታሪካዊ ክህደት ነው።በተለይ ከ1997 ምርጫ በኋላ በቀቢጠ ተስፋ የሚሠራውን አሳጥቶት ይገኛል ከ2007 ምርጫ በፊት በምርጫ መስናዶ ያሳያቸው የአውሬነት ባህርያትም በውል ሊስተዋሉ የሚገባቸው ናቸው።

     በአንፃሩ ደግሞ ይህን የህወሃት ታሪካዊ ክህደትና የቅጥረኝነት አስነዋሪ ተግባር ለመመከት በኢትዮጵያዊነታችን የምናምን ዜጎች የሄድንበት ርቀት ወንዝ የሚያሻግር ሆኖ አላገኘሁትም። ጉዳዩ ህወሃት የሰጠን የቤት ሥራ ብቻውን አቅም እንድናጣ አድርጎናል ብየም አልገምትም። የራሳችን ችግርም አስተዋፅኦ አድርጓል።እንደኔ አመለካከት ቁልፉ ጉዳይ እዚህ ላይ ነው ያለው ብየ አምናለሁ። ለምን ቢባል ሕዝቡ ለአመጽ ዝግጁ አይደለም ብለው ምክንያት ሲፈጥሩ የነበሩ የተቃዋሚ ድርጅቶች ሕዝቡ ጥሏቸው ሄዶ እነሱን ጭራ አድርጓቸው ይገኛል። የተቃዋሚ ኃይሎች በራሳቸው መካከል ያለውን ግንኙነት ስንመለከት ተስፋ ሰጭ አይደለም።

     የተቃዋሚ ኃይሎች መጀመርያ ራሳቸውን ሊፈትሹ ይገባል በተለመደው ስሌት እንደ ከዚህ ቀደሙ ሕዝብ ያገኘውን ድል ለመንጠቅና ሥልጣን ላይ ቁጢጥ ለማለት ከሆነ አድፍጣችሁ ያላችሁት የናንተ መደራጀት ገደል ይግባ እንድንል ይገፋናል።ምክንያቱም ሕዝቡ አሁን የሚፈልገው-፦ የድርጅት ብዛት ሳይሆን ጠንካራ የሕዝቡን ትግል በመምራት ወደ ፊት የሚያራምድ ሁሉም ጎሳዎችና ነገዶች በእኩልነት፤በአንድነትና በጋራ ተከባብረውና ተባብረው የሚኖሩባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የሚገነባ፤የሕግ የበላይነትና ፍትሕ የሰፈነባት፤ሉዓላዊነቷ የተከበረና የታፈረ ሥርዓት የሚያመጣ ለሕዝብ ተአማኒነት ያለውን ድርጅት ነው።

    ዛሬ በቅርብም ይሁን በሩቅ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወዳጅ አገሮች ፊታቸውን ዞረውብናል እንዲያውም በአገር ውስጥና በውጭ አገር ኢትዮጵያውያን እየታደኑ እንዲታሰሩ፤ለሰው በላው ህወሃት ተላልፈው እንዲሰጡና እንዲገደሉ እያደረጉ ነው።ኢትዮጵያውያን አገር ጥለው እንዲሰደዱ የሚያደርገውን አንኳር ጉዳይ እንመልከት ካልን፦ተወልደው ባደጉበት አያት ቅድመ አያቶቻቸው ደማቸውን አፍስሠው፤አጥንታቸውን ከስክሰው አስከብረው ባቆዩአት አገራቸው እንዳይኖሩ ያደረገው ህወሃት ነው።ህወሃት ሀብታቸውን ዘርፎ በድህነትና በችግር እንዲማቅቁ አድርጓል፤ያስራቸዋል፤ይገድላቸዋል፤አስሮ ክብርን በሚነካና በእጅጉ በየትኛውም አገር ታይቶና ተሰምቶ በማያውቅ ሁኔታ እርቃናቸውን ሆነው የሚመረመሩባትና ራሳቸውን ወደታች ዘቅዝቆ ወፌ ይላላ የመገረፉባት፤በፈላ ዘይት የሚጠበሱባት፤በቀዝቃዛ ውሃ የሚሰቃዩባት የባርያ ሽያጭ በቀረበት በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ወጣት ሴቶችንና ወንዶችን ወደ የተለያዩ አገሮች በኩንትራት ለዘመናዊ ባርነት አሳልፎ የሰጠ ከሃዲና ወሮበላ ቡድን በሥልጣን ላይ ያለባት አገር ናት ኢትዮጵያ ።ታዲያ ይህ ያላሰደደ የቱ ነው የሚያሰድደው?ከስደቱ ባሻገር ሌላ የተሻለ አማራጭ የለም ወይ?ለሚለው አማራጭ አለው።ራስን ነፃ ለማውጣት መታገል።ዳሩ ግን ትግሉን ከማን ጋር?የሚል ጥያቄ ሲነሳ የተቃዋሚ ኃይሎች የሚመልሱት ጥያቄ ይሆናል።

        አንድ በቅርቡ ኢትዮጵያ ደርሶ የተመለሰ ሰው እንዳወራኝ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሆቴል ሰዎች በልተው ያተረፉትን ምግብ(ቡላ) ከመደፋቱ በፊት ከሆቴሉ ሠራተኞች በመረከብ ከሰባት መቶ እስከ ስምንት መቶ ደመወዝ የሚከፈላቸው ቤተሰብ ማስተዳደር የሚያስችል አቅምና ተመጣጣኝ ክፍያ ስለማያገኙና የኑሮ ሁኔታው ጣራ ላይ በመወጣቱ የተመለሰ ምግብ ገዝተው ቤተሰብ እየመገቡ እንደሚገኙ ገልጾልኛል። በአንጻሩ ደግሞ እግረ-ደረቁ የህወሃት ቡድን ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ አደገች ተመነደገች እያለ የተለመደ የውሸት ቱልቱላውን ሲያናፍስ ይስተዋላል።

     ከሩቅ ሆኖ መተንበይ አዳጋች ቢሆንም በሕብረተሰቡ ላይ እየደረሱ ያሉት የደረሱት በውጭም በሀገር ቤትም የተፈጠሩት ሁኔታዎች እንደሚያመለክቱት በወርሃ ሚያዝያ የመን፤ደቡብ አፍሪካና ሊቢያ ላይ ብቻ በክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የተሠነዘረብን ወርሃ ሚያዝያ የኢትዮጵያ ጥቁር ቀን የሆነበት የካቲት 12 እንድናስብ ያደረገን የህወሃት ሥርአት አላኖር አላስኬድና አላስቀምጥ ብሏቸው ዳቦ ፍለጋ ሲንከራተቱ ሕሊናን በሚሰቀጥጥ ዘግናኝ ሁኔታ እንደ በግ ሲታረዱና በጥይት ሲቆሉ ተመልክተናል።ይህ በእውነቱ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ ለሚያምን ሁሉ እንቅልፍን የሚነሳ፤ብሔራዊ ሞራልን የሚሰብር ሁኔታ ተከስቷል፤ደርሶብናል።ይህን ሁሉ ችግር ያመጣብን የጠባቦችና የጎጠኞች የህወሃት ድናቁርቶች ስርአት ነው።በመግደል በማሰርና በማሰደድ የሀገር ሀብት በመዝረፍ የስርአት አልበኝነት ስርአትን በማራመድ የሥልጣንን እድሜ ለማራዘም በከንቱ መንደፋደፍ ይህንም እንኳን ለማድረግ አቅም ይጠይቃል። ህወሃትን፦ ሕገ-አራዊቱ ሕግ አያስጥለውም።

ይህ በአገር በቀል ጣሊያኖች እየተካሄደ ያለው ፋሽስታዊ ሥርዓት እንዲያከትምና እንዳይደገም እኛ ኢትዮጵያውያን ምን ልናደርግ ይገባል?

  • አንድ ላለመሆን በጋራ ጽናት እንዳይኖረን መደማመጥ፤መከባበር፤መተማመን እንዳንችል የተስማማንና ለህወሃት ለም አፈር ሆነን በግል ባኅርያችን አገርን በጠራራ ፀሐይ የሚሸጥ፤ሕዝብን የሚፈጅና የሚያስፈጅ ከባእዳን ወግኖ የሚሞግተንና የሚወጋንን ህወሃትን የስልጣን ዘመኑ እንዲራዘምለት በማድረግ እኛው ራሳችን ነዳጅ ሆነን እያገለገልነው ስለምንገኝ መጀመርያ ከዚህ አደጋ ራሳችን ማውጣት አለብን።
  • አሁን እንደምንመለከተው በተቃዋሚ ኃይሎች አካባቢ (እየተፈፀሙ)እየተሠሩ ያሉት ሁኔታዎች ችግሮችን ተባብሰው እንዲቀጥሉ የሚያደርጉ በመሆናቸው በድርጅቶች ዙርያ ያለው ችግር ሳይቀረፍ እታገላለሁ ማለት በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ ስለሚሆን ይህን የማጋለጥና ሕዝብ እንዲያውቀው ማድረግ ይህ ሲሆን ተገደው ለሕዝብ ፍላጎት ተገዥ መሆናቸውን ማረጋገጥ።(ለአብነትም የቅንጅት፤መኢአድና የአንድነት ወርሾች ህወሃት ያደራጃቸው የህወሃት ጉጅሌዎች ናቸው)፤በውጭም ኢህአፓን ብቻውን ብንጠቅስ በአሁኑ ሰአት ከሶስት የተከፈለበት ሁኔታ ይገኛል፤የአርበኞች ግንባር ከሁለት ከተከፈለ ቆይቷል።በሌሎች ዙርያም ቱጃሩ እጀ ረጅሙ ህወሃት ላለመኖሩ ማስተማመኛ የለንም።በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሰርጎ መግባትና ማደናቀፍ የህወሃት ተግባር ስለሆነ ራስን ማጥራት ያሻል።
  • ተጨባጩን የህወሃት ሁኔታ ስንመለከት በሕዝብ ዘንድ አመኔታን ያጣ ወይም ከሕዝቡ መነጠሉን አምኖ ሁሉንም ነገር በኃይል ለማስቀጠል እየጣረ ያለበትና አባላቱም እየጣሉ መጥፋትና ማጉረምረም መጀመራቸው አንድ በመጨረሻዋ ሰአት ላይ የሚገኝን ስርዓት የሚያመላክቱ መሆናቸውን ያሳየናል።እዚህ ላይ ትኩረት አድርጎ በመሄድም ብዙ ድክመቶች ይታያሉ፡ህወሃት የሕዝቡን የትግል ስሜት ለመስለብ አቅጣጫ ሲቀይር ህወሃት የሚያናፍሰውን መከተል ሳይሆን በተፃራሪው የመቀስቀሻ ነጥቦችን አውጥቶ ማጋለጥ ያስፈልጋል።ህወሃት ልማታዊ መንግሥት ሊሆን አይችልም ምናልባትም ፎቆች፤መንገዶችና ቤቶች ተገንብተው ሊሆን ይችላል እነዚያ ግን ሀብትነታቸው የማን ነው? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል።ህወሃትን ራሱን ሊጠቅም የሚችል ነገር ካልሆነ በስተቀር በፍጹም ለሕዝብ ጥቅም የሚሰጥ ልማት እንደማይሞክረው የተረጋገጠ ነው።
  • ጅብ እንደ አገሩ ይጮሃል እንዲሉ አንዳንዶች ህወሃትን በሰላማዊ መንገድ ታግለን እናስወግዳለን ብለው የተነሱ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ ህወሃት የሰላማዊ ትግል ምንነት የሚገባው ድርጅት ስለአልሆነ እሱ በመጣበት መንገድ በመሄድ የጫካ ሕጉንና ሰው በላውን የህወሃትን ስርዓት እናስወግዳለን ብለው ራሳቸውን በተቃዋሚ ኃይል የመደቡና የተሰለፉ ይገኙበታል።ይህ ሰልፍ ህወሃት በራሱ አምሳል የለጠፋቸውን አይጨምርም።ከዚህች ነጥብ ላይ አንድ መጨመር የምፈልገው ነገር ቢኖር ህወሃት በመሃላችን እየገባ አንድነታችን አብሮነታችን ሲንደው እኛስ ለምን እሱ በሄደበት ሄደን አንከፋፍለውም?እርስ በርሳቸው እንዲባሉ አናደርጋቸውም?ለምሳሌ ህወሃት ብአዴን ብሎ የሚጠራውን ድርጅት ወስደን አማራ የሆኑትን አማራ ያልሆነው ድርጅት እንደ በግ ሲነዳቸውና እጃቸውን ቆልምሞ ሲያስር ሲያሳድድ፤ሲገድል፤ሲዘርፍ በቃ እጅህን ሰብስብ እንዲሉት ማድረግ አይቻልም ወይ?ነበረብን አሁንም ማድረግ አለብን።
  • ከሁለቱም ሰልፎች አንዳንድ ወስደን ብንጠናከር ህወሃት የማይወድቅበት አንድም ምክንያት የለም። ነፍጥ ካነሱት አንዱን ከሰላማዊ ተሰላፊዎች አንዱን ብንመርጥና የመምራት ኃላፊነቱን እንዲወስዱ ብናደርግ በሰው ኃይል በገንዘብና በተለያዩ ቁሳቁሶች አቅም መፍጠር ይቻላል። ሁልጊዜ በአንድ አይነት መንገድ እየሄዱ መታገል ስልትን ማስበላትና ትግሉን ከምንኮላሸት አያድነውም። የትግል ስልቶች እንደየ ወቅቱ የፖለቲካ ትኩሳት መቀያየር ይኖርባቸዋል።በግሌ እንደተመለከትኩት ሁለቱም አሰላለፍ በብዛኛው እያስቀጨ ያለው የአማራውን ነገድ ሕዝብ ነው ለምን? ያልን እንደሆነ፦

       1/ ህወሃት ሰበበ-አስባብ ፈልጎ ማጥፋት የሚፈልገው ገና ድርጅቱ ሲመሰረት ዓላማየ ብሎ የተነሳበትም የአማራውን ሕዝብ  በመሆኑ፡ 2/ አሁን ላሉት የተቃዋሚ ኃይሎች የመታገያ ነጥብ መነሻ የሚሆኑ ብዙ ምንያቶች ያሉት በመሆኑና የአማራ ነገድ ሕዝብ የሚኖርበት አካባቢ ለትግል ጥሩ የተፈጥሮ አቀማመጥ ስለአለውና ከጎረቤት አገር የሚያዋስን በመሆኑ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሉዓላዊነት ጉዳይ የጎላ ታሪክ ያስመዘገበ ኃላፊነትና ግዴታውን የሚያውቅ ሕዝብ በመሆኑ አካባቢው ሊመረጥ ይችል ይሆናል። 3/ ከአንድ ጹሑፍ ያገኘሁት መረጃ እንደሚገልጸው በድሮ ጊዜ የወሎ የመሬት ቆዳ ስፋት 94.400 ኪ/ሜትር የጎንደር መሬት ቆዳ ስፋት 74.200 ኪ/ሜትር፤ የትግራይ 65.900 ኪ/ሜትር ሲሆን በአሁኑ ሰአት የትግራይ መሬት የቆዳ ስፋት 102.000 ሆኖ ይገኛል።ይህ ማለት ህወሃት ከሁመራ፤ወልቃይት፤ጠገዴ፤ጠለምት፤ዳንሻን ከጎንደር ራያና ሰቆጣ አበርገሌን ከወሎ በመውሰድ ያደረገውን ትግራይን የማስፋፋት ሊሎች አጎራባች ክፍለ ሀገሮችን የማሳነስና ሕዝቡን የማፈናቀል አብይ ዓላማ መሆኑን የሚገልጽ አንድ የመታገያ አጀንዳም ስለሚሆን የትግሉ ማዕከል ሊሆን ይችላል ዳሩ ግን ከጥቅሙ ጉዳቱን የሚያመዝን እዳይሆን በጥናት የተደገፈ የትግል ስልት መቀየስን ይጠይቃል ይህ የተሟላበት አካሄድ አይመስልም።

  • በሀገር ቤትና በውጭ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ማቀናጀትን በሚመለከት 1/ ዲያስፖራው ሊያበረክት የሚችለው አስተውጾ ምንድን ነው?ብሎ መለየት 2/ በሀገር ቤት ያለው ሕዝባዊ አመጽ ሊደረስበትና አመራር ሊያገኝ መቻል አለበት እንዴት ብሎ ለሚለው ጥያቄ፦1/ በሰላማዊ ትግል ላይ የሚገኙትን መጠቀም 2/ የህቡእ አደረጃጀትን ስልት መከተልና ቴክኖሎጅውን በመጠቀም መረጃ መለዋወጥ አስፈላጊ ናቸው ብየ አምናለሁ።በተለይ ለዚህ እኩይና ፀረ-ሕዝብ የሆነ የህወሃት የጀርባ አጥንት በሆኑት የደህንነት፤የመከላከያ፤የፌደራልና የየክልል ፖሊስ፤የክልል ፈጥኖ ደራሽ፤የአጋዚ ሠራዊት እየተባለ በሚጠራውና በካድሬው አካባቢ የሚደረጉትን እንቅስቃሴዎች በሰላ ሁኔታ መከታተል።

    አገርን ለመገንባትና ለማበልፀግ ጤናማ ሕብረትሰብ ፤የተማረና በሙያ የሰለጠነ ኃይል እንዲኖረን ለማድረግ ከድኻው ሕዝብ የሚሰበሰበውን ግብር ለትምህርት በመበጀት ሁኔታው በሚፈቅደው መጠን በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ በቁጥሩ የማይናቅ ምሁር ኢትዮጵያ እንዳላት ይታወቃል። ይሁን እንጅ ይህ አስተሳሰበ ኩድኩድ የህወሃት ቡድን የኢትዮጵያ ምሁራንን ኮቴ ኮቴያቸውን እያለ አገር ጥለው እንዲሄዱ አድርጓል፤የቀሩት ዱላውንም ችለን በሀገራችን ያሉትን ደግሞ የህወሃት አባል አይደላችሁም በማለት ከሥራ ገበታቸው እንዲፈናቀሉና ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እንዳያስተዳድሩ አድርጓል።በውጭ ያለው ምሁርም እባብ ያየ በልጥ ይሸሻል እንዲሉ ወደ ሀገሩ ተመልሶ ሕዝቡንና አገሩን እንዳያገለግል በመደረጉ የባእዳን አገልጋይ ሆኖ ይገኛል።

   እኛ ኢትዮጵያውያን በውጭው ዓለም የምንታወቀው ድህነትና በርሃብተኛነት ብቻ እንዲሆን ሆነ ተብሎ የተሸረበብን ተንኮል ፍጥነቱንና እድገቱን ጨምሮ ስደተኛ የሚለው ታክሎበት ወገኖቻችን በሀገር ውስጥ ከመዋረድና ሶስተኛ ዜጋ ሆኖ ከመገኘት ሞትን ለመጋፈጥ ወይም ለጊዜው ሞትን አምልጦ ዳቦ በልቶ ለማደር የሰሐራን በርሃ ሲያቋርጡ ርሃብ፤አውሬና የውሃ ጥማት የፈጃቸው፤ባህር አቋርጠው ሊወጡ ሲሉ ያለቁት፤በየመን፤በደቡብ አፍሪካ፤በሳኡዲ ዐርብያ በግፍ ያለቁት፤ሊብያ በጥይት የተቆሉትና በቢላ እንደ በግ የታረዱት በውስጣችን እንደ እሳት እያንገበገበን ባለበት ወቅት ህወሃትና የህወሃት ግብረ በላዎች መሳለቂያ ሲያደርጉን ተመለከትን ከዚህ ወዲያ ውርደትና ሞት የለም።ብሔራዊ ሞራላችንን ነክተውታል፤ከወላጆቻችን የወረስነውን አኩሪ ታሪክ አርክሰዋል፤ድንበራችን አስደፍረዋል፤ሉዓላዊነታችንን አስደፍረዋል፤አንገታችን ደፍተን እንድንሄድና አደባባይ እንዳንወጣ አድረገውናል። ጎበዝ!! ለትግልና ህወሃትን ለማስወገድ እነዚህ በቂ አይደሉም?ጥያቄየ አንድ እንሁን አንዲት አገርና አንድ ሕዝብ ነው ያለን የሚለው ነው።

     ድርጅቶች በበዙ ቁጥር የሕዝብ ኃይልና የገንዘብም ይሁን የቁሳቁስ(ማቴርያል) አቅማችን ያንኑ ያህል ነው የሚያንሰውና በውስን አቅም የጥቃት ሰለባ እንድንሆን የሚያደርገን።ለምን ለህወሃት የሚመች ለም መሬት ሆነን እንገኛለን? ሕዝባችን ሲጨርሱት፤ተራ በተራ ነጣጥለው፤ከፋፍለው ሲፈጁት ምን እየጠበቅን ነው?መካካዱ፤አለመተማመኑና በጥርጣሬ የመተያየቱ አባዜ ያብቃ !! ተራውን ለህወሃት እንስጠውና እኛ በአንድነት በጋራ ቆመን የጋራ ጠላታችን የሆነውን የህወሃትን ግባተ መሬት እናፋጥንለት።በምርጫው ዋዜማ እያሰማ ያለውና በምን መሰናዶ ላይ እንዳለ ይታወቃል ዛሬም እንደ ምርጫ 1997ቱ ወገኖቻችን የሞት ሰለባ እንዳይሆኑ እንታደጋቸው በግንባር ቀደምትነት የተደራጁ የተቃዋሚ ኃይሎች ኃላፊነት ቢኖርባቸውም እያንዳንዱ ሕዝቡን አገሩን የሚወድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ሊረባረብበት ይገባል።

               እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ከጥፋት ይጠብቃት!!

    በባእድ አገር በአሰቃቂ ሁኔታ የሞቱ ወገኖቻችን ነብስ ይማር ቢተሰባቸውን ጽናት ይስጥልን!!

                          ሕዝባዊ እንብኝተኝነቱ ይጠንክር!!!

                                       ገብርየ በለው።                                                                            

The post   የሀገር ሀብት ዘረፋ፤ስደት፤እሥራትና ግድያው እንዲቆም ህወሃትን ከሥልጣኑ አውርደን መጣል ግዴታችን ነው። appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢትዮጵያ፡ የምንወድሽ ሀገራችን ደግመሽ አልቅሽ!

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የኢትዮጵያውያን/ት ህይወት ያሳስበናል!

እ.ኤ.አ በ2005 ልክ የዛሬ 10 ዓመት በያዝነው ወር ገደማ አሁን በህይወት የሌለው እና እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አድራጊ ፈጣሪ አምባገነን መሪ የነበረው መለስ ዜናዊ በዚያን ዓመት ተካሂዶ የነበረውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ሁከት የደህንነት እና የጦር ኃይሉን በእራሱ ቁጥጥር ስር በማዋል በሰላማዊ እና ባልታጠቁ ንጹሀን ዜጎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት እልቂት እና መከራን ያዘለ ዘመቻ አካሂዷል፡፡
Cry-ethiopia
እ.ኤ.አ ግንቦት 16/2005 መለስ ዜናዊ የፖሊስ፣ የደህንነት እና ወታደራዊ ኃይሉን በእራሱ ቁጥጥር ስር በማደረግ እና የአዲስ አበባ ከተማን የፖሊስ ኃይል ከፌዴራል ፖሊስ እና ከልዩ ኃይል ጋር በማቀናጀት ሁሉንም የህዝብ ስብሰባዎች ህገወጥ ናቸው በማለት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ ነበር፡፡ በቀጣዮቹ ሳምንታት የመለስ የጭፍጨፋ ኃይሎች አረመኒያዊ ጭፍጨፋ በማካሄድ 193 ሰላማዊ ንጹሀን ዜጎችን ግንባራቸውን እና ደረታቸውን በጥይት እያነጣጠሩ በመምታት የገደሉ ሲሆን ሌሎች 800 የሚሆኑ ወገኖቻችንን ደግሞ በጽኑ እንዲቆስሉ አድርገዋል፡፡ ምንም ዓይነት ትጥቅ ያልነበራቸው ሰላማዊ አመጸኞች ያንን ሸፍጥ እና ተንኮል የተሞላበትን የተጭበረበረ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ በመቃወማቸው እና መብታቸውን ለመጠቀም በመምረጣቸው ብቻ በየመንገዶች እና በየቤቶቻቸው እንደ አውሬ እየታደኑ ያለምንም ርህራሄ በጥይት እየተደበደቡ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ ተደርገዋል፡፡ እነዚያ ጀግኖች ሰላማዊ አማጺ ወገኖቻችን በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን በጽናት ታግለው ውድ ህይወታቸውን በመገበር ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ማበብ ሲሉ መስዋዕት ሆነዋል፡፡

ያ የአረመኔዎች እና የፈሪዎች አሰቃቂ ዕልቂት ላለፉት አስርት ዓመታት በየዕለቱ የእራስ ምታት፣ የልብ ቁስል፣ የሆድ ቁርጠት እና የደረት ውጋት ሆኖብኝ ቆይቷል፡፡ ይህንንም ከግንዛቤ በማስገባት ስለዚሁ ጉዳይ አንዲትም ሳምንትሳታልፈኝ በማዘጋጀው ትችቴ ለበርካታ ዓመታት ሳስተምር እና ስሰብክ ቆይቻለሁ፡፡ እ.ኤ.አ በ2005 የተካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ውዝግብ የመለስን እልቂት በመቃወም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የሰብአዊ መብት ትግል ተቀላቅዬ በመታገል ላይ እገኛለሁ፡፡ የመለስ እልቂት ሰለባዎች የፍትህ ያለህ እያሉ በመጮህ ላይ ይገኛሉ፡፡ እኔ የእነርሱ ድምጽ ነኝ፡፡

ያ በሰላማዊ እና ንጹሀን ዜጎች ላይ በመለስ ትዕዛዝ ተካሂዶ የነበረው ሰይጣናዊ አሰቃቂ ዕልቂት የተፈጸመበት አስር ዓመት ከመሙላቱ ከአንድ ወር በፊት እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2015 እራሱን የኢራቅ እና የሊባኖስ እስላማዊ መንግስት (ኢሊእመ)/Islamic State of Iraq and the Levant (ISIL) (እንደዚሁም ደግሞ የኢራቅ እና የሶርያ እስላማዊ መንግስት (ኢሶእመ)/Islamic State of Iraq and Syria (ISIS) እያለ የሚጠራው አሸባሪ ቡድን በሊቢያ 30ኢትዮጵያውያንወገኖቻችንን አሳዛኝ እና አስደንጋጭ በሆነ መልኩ ያረደ መሆኑን በቪዲዮ ምስል ተመልክቻለሁ፡፡ (በዚህ በቀሪው ትችቴ ይህንን እየተስፋፋ የመጣውን ነቀርሳ/ካንሰር አሸባሪ ድርጅት “አሸባሪ ቡድን/ድርጅት/the terrorist group/organization“ እያልኩ እጠራዋለሁ ምክንያቱም በዓለም ላይ ከሚገኙ ታላላቅ ኃይማኖቶች መካከል አንዱ በሆነው የእስልምና እምነት ኃይማኖት ስም እየማለ እና እየተገዘተ ሆኖም ግን በተግባራዊ እንቅስቃሴው ግን የኃይማኖቱን ቅዱስነት ያዋረደ፣ የማያስብ፣ ኋላቀር፣ ደም የጠማው፣ ጨካኝ እና ስብዕና የሌለው አሸባሪ ቡድን ከእስላም ሃይማኖት ጋር አየገናኝም፡፡)

ይኸ በሊቢያ የሚገኘው ጨካኝ አሸባሪ ቡድን የወጣት ኢትዮጵያውያንን አንገት በማረጃ ቤት ውስጥ እንደሚታረድ የበግ ጠቦት እየቀነጠሰ አርዶ ጥሏል ምክንያቱም እነዚህ የኢትዮጵያ ወጣቶች ከኢትዮጵያ ጠላቶች በተለዬ መልኩ የክርስትና ኃይማኖት እምነት ተከታዮች የሆኑ እና እምነታቸውን ለመቀየር እምቢ አሻፈረኝ በማለት በእምነታቸው የጸኑ ዜጎች ናቸው፡፡ እነዚህ 30 ወጣት ኢትዮጵያውያን ለክርስትና ኃይማኖት እምነት ሲባል መስዋዕትነትን የተቀበሉ ብቻ አይደሉም፣ ሆኖም ግን ከዚህም በተጨማሪ ለሰው ልጆች እምነቶች እና አስተሳሰቦች ሲሉ ጭምር እንጅ፡፡ እነዚህ ወጣቶች ትክክለኛውን እምነታቸውን በመከተል የአምላክ የበግ ጠቦት በመሆን መስዋዕትነትን ተቀብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ወጣት ወንዶች እና በሌሎችም ከግብጽ፣ ከዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ፣ ከእንግሊዝ፣ ከጃፓን፣ ከኢራቅ እና ከሶርያ የመጡ ወጣቶችን ጨምሮ ሰለባ ያደረገው ይኸ ምንም ዓይነት ርህራሄ የሌው አረመኔ እና ጨካኝ አሸባሪ ቡድን ከፊል ኢራቅን፣ ሶርያን፣ ሊቢያን እና ናይጀሪያን ተቆጣጥሯል፡፡ እ.ኤ.አ ሰኔ 2014 ያ አሸባሪ ቡድን በነብዩ መሀመድ ቦታ አቡ ባከር አል ባግዳድን መሪ በማድረግ እራሱን ዓለም አቀፍ የእስልምና ኃይማኖት መንግስት አድርጎ አውጇል፡፡

ያ አሸባሪ ድርጅት የተለያዩ ሰብዕናየለሽ ቡድኖችን፣ ጀብድ ፈላጊዎችን እና ሌሎችን ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከአውሮፓ ደስተኛ ያልሆኑትን እና መብታቸውን የተነፈጉትን ሰብስቦች እየሳበ እንደሚጠቀምባቸው አምናለሁ፡፡ የዚህ ድርጅት አባላት በዓለም ላይ ጉዳት ለማድረስ በስሜታዊነት የተሞሉ ናቸው፡፡ የሮምን ወታደር (በተለምዶ በሮም ጳጳስ የተላኩ ተዋጊዎች ወይም ደግሞ የበለጠ በሚመሳሰል መልኩ እምነት የሌላቸው የምዕራብ ወታደሮች በዳቢቅ እና በሶርያ በሚገናኙበት ጊዜ የዓለምን ፍጻሜ የመጀመሪያ ምዕራፍ ይጠብቃሉ፡፡ እርግጠኛ ለመሆን ለዚያ አሸባሪ ቡድን እምነት የሌላቸውን እና ለአሸባሪ ድርጅቶች ርዕዮት ዓለም ድጋፍ የማያደርጉትን የሻአ ሙስሊሞችን እና ሌሎችን ሙስሊሞች እንዲሁም ማንኛውንም የሙስሊም መንግስት ያካትታል፡፡ ያ አሸባሪ ቡድን በአሁኑ ጊዜ በኢራቅ፣ በሶርያ፣ በሊቢያ እና በናይጀሪያ ተቆጥረው ለማያውቁ እልቂቶች ቀጥታ ተጠያቂ ነው፡፡ በዳቢቅ አሸባሪዎቹ እምነት የላቸውም ብለው የሚያስቧቸውን ማለትም ክርስቲያኖችን፣ ሙስሊሞችን እና ሌሎችን በማሸነፍ የእስልምና ግዛታቸውን በዓለም ላይ ሁሉ ለማስፋፋት እና ኃያል ሆነው ለመውጣት ይፈልጋሉ፡፡ ኋላቀርና ኢ-ሰባዊ ድርጊትን ማራመድ የዚያ አሸባሪ ቡድን መለያ ፍልስናው ነው፡፡ ፍልስናው የእነርሱን ዓይነት የሙስሊም እምነት የማያራምደውን የእስልምና እምነት ተከታይ፣ ምንም ዓይነት እምነት የሌለውን ወይም ደግሞ ይዞት የቆየውን እምነቱን ያቆመውን ሰው ለመግደል እንደምክንያት የሚጠቀሙበት ነው፡፡ የእነዚህ የተንሸዋረረ ፍልስፍና የያዙት አሸባሪዎች ዓለምን ለማጽዳት የሚቻለው እነርሱ አማኞች አይደሉም ብለው የሚያስቧቸውን ሰዎች መግደል ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት በአሸባሪ ቡድኑ ተቀርጾ በተለቀቀው የቪዲዮ ምስል የወጣት ኢትዮጵያውያን ወንዶችን ጭንቅላት ለመቅላት/አንገታቸውን ለመቁረጥ እጆቻቸውን ይዘው በረሀውን በማቋረጥ ወደ ባህሩ ዳርቻ ሲወስዷቸው ነበር፡፡ ጥቂቶቹ ወጥ የሆነ ብርቱካናማ ልብስ ለብሰው ነበር፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ጥቁር ልብስ ነበር የለበሱት፡፡ አሸባሪዎቹ የወጣት ኢትዮጵያውያንን ጭንቅላት ለመቅላት እንደ ምክንያት ማስረጃ አድርገው የሚያቀርቡት ጠላታቸው የሆነቸው የእትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እምነት የሆነውን የክርስትና ኃይማኖት እምነት ተከታይ የመሆናቸው ጉዳይ ብቻ ነው፡፡

ይህ በሊቢያ እና እንደእርሱ ባሉት በሌሎች ሀገሮች የሚገኙት የደንቆሮ ስብስብ ወሮበላ የአሸባሪ ቡድን አባላት ከስቃይ እና መከራ እንዲሁም ከነብዩ ትምህርት በመሸሽ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩትን የመጀመሪያዎችን የእስልምና እምነት ተከታዮች በኢትዮጵያውን ህዝቦች ተደርጎላቸው የነበረውን የአቀባበል መስተንግዶ ሙልጭ አድርጎ ረስቶታል፡፡ በቅርቡ አንድ ግለሰብ በሰጠው ቃለ መጠይቅ መሰረት በኢራቅ ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸው እና ለዕኩይ ምግባራቸው ስኬታማነት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት የአሸባሪ ቡድኑ አባላት የትምህርት ደረጃቸው ከአንደኛ ደረጃ ያልዘለለ መሆኑን ግልጽ አድርገዋል፡፡ እስላም ምንድን ነው ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ እንዲህ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፣ “ሕይወቴ ነው፡፡’ ስለቁራን ወይም ደግሞ ስለቁራን ባህላዊ ስብስቦች ወይም ስለድሮው ነብይ ኦማር እና ኦትማን ምንም የሚያውቁት ነገር የላቸውም፣ ሆኖም ግን ስለእስልምና ከአልቃይዳ እና ከአይሲስ ፕሮፓጋንዳ፣ እንዲሁም ሙስሊም ያልጠራውን እምነት ቀደም ብሎ ያልጠራውን እምነት ካላስተማረ እርሱም የእምነቱ ተከታዮች እንዳልሆኑት ሰዎች ሁሉ መወገድ እንዳለባቸው እና ዒላማ ውስጥ እንደሚወድቁ አሳምረው ያውቃሉ፡፡“ እነዚህ የአሸባሪ ቡድን አባላት እንዲህ በማለት ተናግረዋል፣ “ሳዳም ሁሴን ከወደቀ በኋላ በገሀነም ዓይነት የማያቋርጥ የሽምቅ ውጊያ ያደጉ፣ ቤተሰቦቻቸው የሞቱባቸው እና የተበታተኑባቸው እንዲሁም ከቤቶቻቸው መውጣት የማይችሉ ወይም ደግሞ እስከ ወሩ መጨረሻ ምንም ዓይነት መጠለያ የሌላቸው መሆናቸው ታውቋል፡፡“

ሌሎች የአሸባሪ ቡድን አባላትም ከዚህ የተለዬ የተሻለ ስብዕና የላቸውም፡፡ በአብዛኛው በህይወታቸው በሽግግር ላይ ያሉ ወጣቶች ማለትም ተማሪዎች፣ ስደተኞች፣ ስራ ለመስራት የማይፈልጉ አውደልዳዮች፣ ቤተሰቦቻቸውን የተው ወይም ደግሞ ለመተው የተዘጋጁ እና አንድ ዓይነት ጥቅም ሊያስገኝላቸው የሚችል ሌላ ዓይነት የጓደኝነት ቤተሰብ ለመመስረት ሲሉ ጥረት የሚያደርጉ ናቸው፡፡ አብዛኞቹ የተለመደው የኃይማኖት ትምህርት እውቀት የላቸውም፣ እናም ጥብቅ በሆነ እና በጠባብ የማህበራዊ ፍልስፍና እምነት የታሰሩ ናቸው፣ ሆኖም ግን እነዚህ የአሸባሪ ቡድን አባላት ዓለምን ሊገምድ በሚችል የኃይማኖት ተልዕኮ ስሜት የተሞሉ ናቸው፡፡

እነዚህ በድንቁርና ተቀፍድደው የተያዙት አሸባሪዎች እና ከነባራዊ ሁኔታው ጋር መራመድ የማይችሉ ጉዶች ኢትዮጵያ ለነብዩ መሐመድ እምነት ተከታዮች የመጀመሪያው የእስልምና ኃይማኖት እምነት ስደተኞች ተቀባይ ገነት ስለመሆኗ ምንም ዓይነት ፍንጭ የላቸውም፡፡ ነብዩ መሐመድ በዚያ የመከራ ስደት ወቅት ለተከታዮቻቸው እንዲህ ብለው ተናግረው ነበር፣ “መካን መልቀቅ እና በዚያን ጊዜ በክርስቲያን ንጉስ ትተዳደር በነበረች እና ንጉሷም ፈሪሀ እግዚአብሔር ያደረበት እና ፍትህን የሚከተል ስለሆነ በአቢሲኒያ ሀገር (ኢትዮጵያ) በጥገኝነት መቆየት አለባችሁ፡፡“ የአክሱሙ ንጉስ እና የሐበሻ ህዝብ (ኢትዮጵያውያን) ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ615 ዓ.ም መጀመሪያ አካባቢ በስቃይ እና በመከራ ሸሽተው የመጡትን ሙስሊሞች ተቀብለው በመልካም ሁኔታ አስተናገዱ፡፡ እናም ታላቅ የሆነ መስተንግዶ አደረጉላቸው፣ እንዲሁም አባራሪዎቻቸው እና ጠላቶቻቸው ተመልሰው ወደ ሀገራቸው እንዲላኩላቸው ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ተንከባክበው እና ደግፈው አስተማማኝ መጠለያ በመስጠት ሊሰነዘርባቸው ከሚችለው አስከፊ አደጋ አድነዋቸዋል፡፡ እነዚህ ወሮበላ የአሸባሪ ቡድን አባላት ነብዩ መሐመድ የሀበሻን (አቢሲኒያ) ህዝብ ማመስገናቸውን እና እንዲህ የሚለውን ንግግራቸውን ፍጹም በሆነ መልኩ ረስተውታል፣ “እርምጃ እስካልወሰዱባችሁ ድረስ ሐበሻዎችን አትንኳቸው!“ ከዚህም በተጨማሪ ነብዩ መሐመድ እንዲህ በማለት አስተምረዋል፣ “አምላክ ለሌሎች ምህረትን ለማያደርጉ ምህረትን አይሰጥም፡፡“

በሊቢያ አሸባሪዎች አንገታቸውን የተቀሉት ኢትዮጵያውያን በማንም ዘንድ ጥቃትን አላደረሱም ነበር፡፡ እነዚህ ወጣቶች ሁሉም ድሆች እና ምንም ዓይነት ተስፋ የሌላቸው ሊቢያን እንደመሸጋገሪያ አድርገው መድረሻቸውን ወደ አውሮፓ ሀገሮች ያደረጉ ስደተኞች ነበሩ፡፡ ምህረትን፣ መጠለያን ማግኘት እና አንገታቸው እንዳይቀላ ይፈልጉ ነበር፡፡ እነዚህ እምነቱን ያዋረዱ አሸባሪዎች የኢትዮጵያውያንን አንገት መቅላት ሲጀምሩ ነብዩ መሐመድ ሲያስተምሩ የነበሩትን ትምህርት ወደ ጎን አሽቀንጥረው ጣሉት፡፡ ለእነዚህ የሽብር እና የነውጥ ተዋንያን አላህ ምህረቱን አይሰጣቸውም! እነዚህን ምስኪን እና ጨዋ ኢትዮጵያውያን የአላህ ዓይን ይጎበኛቸዋል! አላህ አክብር ሞት ለአሸባሪዎች እና ለግፈኞች!

መለስ እና እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እ.ኤ.አ በ2005 የተደረገውን ሀገር አቀፍ ምደርጫ ውዝግብ ተከትሎ በተፈጠረው ሁከት ሰላማዊዎቹን ኢትዮጵያውያን አንገታቸውን አልቀሉም፣ ሆኖም ግን በአልሞ ተኳሾች እያነጣጠሩ ጭንቅላቶቻቸውን በጥይት ነበር የደበደቡ እንጅ አንገት አልቀሉም ነበር፡፡ በአንድ በቪዲዮ በተቀረጸ ቃለ መጠይቅ መለስ በዚያን ጊዜ ለፈጸመው እልቂት ምክንያት ለመስጠት እስከ 194 ሰዎች ላለቁበት እኩይ ምግባር እንዲህ የሚል ማሳመኛ ለመስጠት ሞክሮ ነበር፣ “በኢትዮጵያ ህገመንግስታዊ ትዕዛዝን ለመፈጸም ህገመንግስታዊ ተግዳሮት ነበር፣ እናም ያ ተግዳሮት አጋጥሞን ነበር፡፡“ በሌላ አባባል ሰላማዊ ሰዎች እልቂት እንዲፈጸምባቸው አድርጓል ምክንያቱም የእርሱን ህግ ተገዳድረዋልና፡፡ አምባገነኑ መለስ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ያ ዕልቂት የዓለም መሪዎችን አስተያየት በመቀየር ወደ እርሱ የሚያደላ መሆኑን ተጠራጥሮ ነበር፡፡ ሆኖም ግን በግልጽ የኢትዮጵያን ገጽታ ጥላሸት ቀብቶ ነው የሄደው፡፡“

በእራሱ በመለስ ዜናዊ የተሾሙት እና የአጣሪ ኮሚሽኑ ሊቀመንበር የነበሩት የዳኛ ፍሬህይወት ዘገባ ፍጹም በሆነ መልኩ ሰላማዊ አመጸኞችን ነጻ በማድረግ አጠቃላይ ኃላፊነቱን እንዲህ በማለት በመለስ አገዛዝ ላይ ደፍድፎታል፡

የጦር መሳሪያ ጠብመንጃ ያነገበ ወይም ደግሞ የእጅ ቦምብ የታጠቀ አንድም ሰው አልነበረም፣ (የመንግስት መገናኛ ብዙሀን እንደገለጹት ጥቂት ሰላማዊ አመጸኞች ጠብመንጃ እና ቦምብ ታጥቀው ነበር፡፡) የአጣሪ ኮሚሽኑ አባላት በመንግስት ኃይሎች የተተኮሱት ጥይቶች ሰላማዊ አመጸኞችን ለመበተን አልነበረም፡፡ ሆኖም ግን የሰላማዊ ሰልፈኞችንጭንቅላት እና ደረት በአልሞ ተኳሾች እያነጣጠሩ በመምታት ለመግደል የተደረገ ድርጊት ነበር፡፡ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

እ.ኤ.አ በ2005 የተካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ በተፈጠረው ውዝግብ እና ሁከት በሰላማዊ ዜጎች ላይ እልቂት የፈጸሙት ወሮበላ ነብሰገዳይ ፖሊሶች እና የጸጥታ ኃይሎች ማንነት በትክክል ታውቆ እና ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ “በኢትዮጵያ የውስጥ የደህንነት ጥበቃን ማዘመን” በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ዘገባ ላይ የጸረ ሽብር ባለሙያ የሆኑት እና የእግሊዝ ወታደራዊ ኃይል አባል የሆኑት ኮሎኔል ሚካኤል ደዋር የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወርቅነህ ገበየሁ እንዲህ በማለት የገለጹላቸውን በመጥቀስ ተናግረዋል፣ “እ.ኤ.አ በ2005 በተካሄደው አመጽ 237 ፖሊስ አባላትን ከመደበኛ ስራቸው አባረዋል፡፡“ ምንም ዓይነት መሳሪያ ባልታጠቁ በኢትዮጵያ ንጹሀን ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ያሳስበናል! እ.ኤ.አ በ2005 የተካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ተፈጥሮ በነበረው ውዝግብ በርካታ ሰላማዊ ወገኖቻችንን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በጥይት እየደበደቡ እልቂት ሲፈጥሩ የነበሩት ወሮበላ ቅጥር ነብሰገዳዮች በአሁኑ ጊዜ ደረታቸውን ነፍተው በዋና ዋና መንገዶች ላይ ሲንገዳወሉ ይውላሉ፡፡ ያንን የመሰለ ዘግናኝ እልቂት የፈጸሙት ወይም ደግሞ እልቂቱ እንዲፈጸም ትዕዛዝ የሰጡት አንዳቸውም ወንጀለኞች እስከ አሁን ድረስ ለፍትህ አካል አልቀረቡም፡፡

በዚህ በያዝነው ሳምንት ከአንድ ዓመት በፊት እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው የወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ በኩል በ80 ማይሎች ርቀት ላይ በምትገኘው የአምቦ ከተማ ቢያንስ በ47 የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እና በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላይ እልቂት ፈጽሟል፡፡ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አገዛዝ ይህንን አሰቃቂ እልቂት ሙልጭ አድርጎ በመካድ ዓይኑን በጨው በመታጠብ “ጥቂት ጸረ ሰላም ኃይሎች የለኮሱት እና ያቀነባበሩት አመጽ ነው” ብሎታል፡፡ በዚያን ጊዜ እንዲህ በማለት ተቃውሞዬን አሰምቸ ነበር፣ “በቃላት ልገልጸው ከምችለው በላይ አዝኛለሁ፡፡ እነዚህ እምቦቃቅላ ሰላማዊ ወጣት ተማሪዎች በጥይት እየተደበደቡ በእንደዚህ ያለ አሰቃቂ ሁኔታ እልቂት የተፈጸመባቸው በመሆኑ በጣም አዝኛለሁ፡፡ በእነዚህ ለኢትዮጵያ ባለብሩህ ተስፋ ባለለቤቶች ላይ በተፈጸመው እልቂት ላይ እጅግ በጣም አዝናለሁ፡፡ ለእነዚህ የእኩይ ምግባር ሰለባ ለሆኑት ወጣቶች ቤተሰቦች እና ጓደኞቻቸው ሁሉ የማይሳነው አምላክ መጽናናቱን እንዲሰጣቸው እመኛለሁ፡፡“ የኢትዮጵያ ወጣቶች ህይወት ያሳስበናል!

በአምቦ ከተማ በንጹሀን ወገኖቻችን ላይ በጠራራ ጸሐይ ጥይት ያርከፈከፉት እነዚህ አረመኔ ቅጥር ነብሰ ገዳዮች በአሁኑ ጊዜ ያለምንም ተጠያቂነት በዋና ዋና መንገዶች ላይ ደረቶቻቸውን ገልብጠው በነጻነት ከወዲያ ወዲህ እያሉ ሲንገዳወሉ ይውላሉ፡፡ ይህንን ሰይጣናዊ የእልቂት ምግባር የፈጸሙት እና እልቂቱም እንዲፈጸም ትዕዛዝ የሰጡት ወሮበላ ባለስልጣኖች ለሕግ ሳይቀርቡ ያለምንም ተጠያቂነት እጆቻቸው በሰው ልጆች ደም ተጨማልቀው ይገኛሉ፡፡

እ.ኤ.አ በ2013 በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ሰራተኞች እና ስደተኞች ላይ የሽብር እና የእልቂት ዘመቻ ተከፈተባቸው፡፡ የሳውዲ ፖሊስ፣ የደህንነት ኃይል ባለስልጣኖች፣ ዱርዬዎች እና ወሮበሎች ለአንድ ሙሉ ቀን ያህል በየመንገዶች ኢትዮጵያውያንን እያደኑ እና እየያዙ ሲደበድቡ፣ ሲያሰቃዩ እና ሲገድሉ ነበር፡፡ በዩቱቤ ቪዲዮ የተለቀቀው ምስል እንደሚያሳየው የሳውዲ አረቢያ ፖሊስ በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ ሲፈጽም የነበረው ዘግናኝ ድርጊት እጅግ በጣም አስደንጋጭ፣ ለህሊናም የሚዘገንን እንዲሁም ምንም ዓይነት ማብራሪያ የማያስፈልገው የፈሪዎች እኩይ ምግባር ነበር፡፡ እንደዚህም ሆኖ ጥቂት የኢትዮጵያ ዜጎች በመንፈሰ ጠንካራነት በጽናት በመቆም የኢትዮጵያን ባንዲራ በራሳቸው ላይ ጠምጥመው እስከመጨረሻው በመታገል በሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ የጥንት የትውልድ ዘሮቻቸውም እንደዚሁ በኩራት የተወጠሩ እና ለነጻነታቸው ቀናኢ የሆኑ ጀግኖች ነበሩ፡፡!

የወባ ትንኝ ተመራማሪው እና በብርህን ፍጥነት ከጤና ጥበቃ ሚኒስትርነት ወደ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት የተተኮሰው ቴዎድሮስ አድኃኖም በዚያን ጊዜ እንዲህ የሚል ንግግር አድርጎ ነበር፣ “የወገኖቻችን መጋዝ እና መሞት እጅግ በጣም አሳስቦኛል፡፡“ አድኃኖም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ለሳውዲ አረቢያው አምባሳደር እንዲህ የሚል የተማጽዕኖ ጥሪ አስተላልፎ ነበር፣ “ኢትዮጵያ የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣኖች ህገወጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ ሀገርለመመለስ እያደረገችያለችውን የማጋዝ እቅስቃሴ መሰረት በማድረግ ላስተላለፈቻቸው ውሳኔዎች የተሰማትን አድናቆት ትገልጻለች፡፡ በዚህ አጋጣሚ በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመውን ግድያ እና በዜጎቻቸው ላይ እየተተገበረ ያለውን ተገቢ ያልሆነ አያያዝ እናወግዛለን፡፡“ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

ለአድኃኖም እና ለእርሱ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቡድን ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ ወሮበሎች ስለሚደርስባቸው የስብዕና እጦት፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ግድያ ጉዳያቸው አይደለም፡፡ ይኸ ጉዳይ ለእነርሱ ምንም ዓይነት የሚያናድዳቸው ነገር አይደለም፡፡ በዚያን ጊዜ “የሰው የዝውውር መጨናነቅ የታየበት ዋና ጊዜ” በሚል ርዕስ እጅግ በጣም በመናደድ ጽሑፍ አውጥቸ ነበር፡፡ የቤት ስራዎቻቸውን ሳይሰሩ ወደ ክፍል የሚመጡ ተማሪዎች እጅግ በጣም ያናድዱኛል፡፡ ደሜን እንዲፈላ ያደርጉታል፡፡ የሳውዲን ፖሊስ በሰው ልጆች ላይ የሚያደርገውን የሰብአዊ መብት ረገጣ፣ ኃላቀርነት እና አረመኔነት በተመለከትኩበት ጊዜ ግን እንደ እሳት ተቀጣጥዬ ነበር፡፡ የሳውዲ ወሮበሎች እና ዱርየዎች ሲያከናውኗቸው በነበሩት ድርጊቶች ላይ ከብስጭት ብዛት ከቁጥጥር ውጭ ሆኘ ነበር፡፡ የሳውዲ አገዛዝ በኢትዮጵያውያን ስደተኛ ወገኖቻችን ላይ ሲፈጽም የነበረው መጠነሰፊ ወንጀል እና የሰብአዊ መብት ረገጣ ላይ እጅግ በጣም ደንግጨ እና ተበሳጭቸ ነበር፡፡ በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው የሰብአዊ መብት ረገጣ አድሃኖምን ብዙም ያላሳሰበው እና ያላበሳጨው መሆኑ በንዴት ላይ ንዴት ተጨምሮብኝ የበለጠ እንድበሳጭ አድርጎኛል፡፡

እ.ኤ.አ ከ2013 ጀምሮ ስለኢትዮጵያውያን ጉዳይ ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከደቡብ አፍሪካ የሚወጡ ዜናዎች አሳዛኝ እና ተመሳሳይነት ያላቸው ናቸው፡፡ (በደቡብ አፍሪካ ወሮበሎች እና ዘራፊዎች በኢትዮጵያውያን እና በሌሎች አፍሪካውያን ወገኖቻችን ዘንድ እየፈጸሙ ያሉትን ህገወጥ ወንጀል ወደፊት የማቀርበው ይሆናል፡፡) አሁን በቅርቡ ከሳምንት ባልበለጠ ጊዜ በመካከለኛው ምስራቅ አሰሪዋ በኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ ላይ የተፈጸመውን ህገወጥ ድርጊት በመቃወም እራሷን ያጠፋችውን ወይም ደግሞ ሌላ እራስን የሚያሰቃይ ድርጊት ወይም ክብርን የሚነካ ድርጊት የፈጸመችውን ኢትዮጵያዊት ስንመለከት እንደ ኢትዮጵያዊነታችን የሚሰማን መንፈስን የሚሰብር ድርጊት አለ፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት የ23 ዓመት እድሜ ያላት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ በቤይሩት ሊባኖስ እራሷን ሰቅላ ተገኝታለች፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ በንጹሀን ኢትዮጵያውያት የቤት ሰራተኛ ወገኖቻችን ህይወት ላይየሚደረገው አስፈሪ እናአስደንጋጭ ሁኔታ ያሳስበናል!
Saudicry
በአሁኑ ጊዜ በሳውዲ አረቢያ እና በሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ ኢሰብአዊነት ድርጊት እየፈጸሙ ያለምንም ተጠያቂነት ደረታቸውን ገልብጠው በዋና ዋና መንገዶች ላይ ሲንገዳወሉ ይታያሉ፡፡ በዚህ ሁሉ የሰብአዊ መብት ረገጣ ማለትም ድብደባ፣ ማሰቃየት እና ግድያ ሲፈጽሙ በነበሩት የዕኩይ ምግባር አራማጅ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ወደ ህግ ሳይቀርቡ እና ምንም ዓይነት ተጠያቂነት ሳይኖርባቸው ነጻ ሆነው ይኖራሉ፡፡

እ.ኤ.አ ጥቅምት 2007 መለስ ዜናዊ እና የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኦጋዴን የሽምቅ ውጊያ ሲያካሂዱ በነበሩት ዜጎች ላይ መጠነሰፊ የሆነ ጥቃት በመሰንዘር ወዲያውኑ ብዙም ሳይቆይ የጥቃት አድማሱን በማስፋት በሲቪሉ ህዝብ ላይ የጅምላ ጥቃት ፕሮግራም ተግባራዊ እንዲሆን ተደረገ፡፡ የመለስ ተዋጊ ጦር የኦጋዴንን መንደሮች በሙሉ አወደመ፣ የአስገድዶ መድፈር ተግባራትን ፈጸመ፣ ግድያ እና አጠቃላይ ዘረፋዎችን ፈጸመ፡፡ ህዝቡን ለማስፈራራት እና ለማሸማቀቅ በሚል እኩይ ሀሳብ ዜጎችን በማነቅ እና አንገታቸውን በመቅላት በአደባባይ እንዲጣሉ ተደረጉ፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅት ለዩኤስ አሜሪካ የአፍሪካ የውጭ ጉዳዮች እና ለዓለም ጤና ጥበቃ ንኡስ ኮሚቴ የሚከተለውን ተናግሮ ነበር፣ “ኦጋዴን ዳርፉር አይደለችም፡፡ ሆኖም ግን በኦጋዴን ያለው ሁኔታ አስደንጋጭ የሆነ ተመሳሳይ የሆነ አስፈሪ ነገርን ያመላክታል፡፡“ በኦጋዴን ያሉወገኖቻችን ህይወትም ያሳስበናል፡፡!

በምስራቅ ኢትዮጵያ በኦጋዴን አካባቢ በሰው ልጆች ላይ እልቂትን፣ የዘር ማጥፋት ወንጀልን የፈጸሙ እና ወንጀሉ እንዲፈጸምም ትዕዛዙን የሰጡት ኃላፊዎች ምንም ዓይነት እርምጃ ሳይወሰድባቸው እና አንዳቸውም ለህግ ሳይቀርቡ እስከ አሁንም ድረስ በነጻነት በየመንገዶች ደረቶቻቸውን ነፍተው በመንገዋለል ላይ ይገኛሉ፡፡

እ.ኤአ. ታህሳስ 2003 መለስ ዜናዊ እና የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በምዕራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላ ህዝቦች ላይ መጠነ ሰፊ የሆነ ጦርነት እንዲካሄድባቸው የጦር ኃይላቸውን በማዘዝ 400 የአኟክ ህዝቦች እንዲገደሉ ሲደረግ ከ1,000 በላይ የሚሆኑ ቤቶች ደግሞ እንዲወድሙ ተደርገዋል፡፡ በቀጣይነትም የመለስ አገዛዝ እንዲህ የሚል መግለጫ አውጥቶ ነበር፣ “በዚህ ጉዳይ ላይ ፈጣን የሆነ እርምጃ ባለመወሰዱ ይቅርታ እየጠየቅን ወደፊት ግን የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት ወገኖች ጎን በጽናት በመቆም አጥፊዎቹ ለህግ እንዲቀርቡ እናደርጋለን፡፡“ በዚያን ጊዜ አገዛዙ በአኟክ እልቂት ላይ ተዋንያን የነበሩ እና እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ በደርዘኖች የሚቆጠሩ ተጠርጣሪዎች ተለይተው ነበር፡፡ እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ ማናቸውም ቢሆኑ ለህግ አልቀረቡም፡፡ በጋምቤላ ያሉ ወገኖቻችን ህይወትም ያሳስበናል፡፡! በምዕራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላ አካባቢ በሰው ልጆች ላይ እልቂትን፣ የዘር ማጥፋት ወንጀልን የፈጸሙ እና ወንጀሉ እንዲፈጸምም ትዕዛዙን የሰጡት ኃላፊዎች ምንም ዓይነት እርምጃ ሳይወሰድባቸው እና አንዳቸውም ለህግ ሳይቀርቡ እስከ አሁንም ድረስ በነጻነት በየመንገዶች ደረቶቻቸውን ገልበጠው በመንገዋለል ላይ ይገኛሉ፡፡

በአሁኑ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን በማገልገል ላይ የሚገኝ ምንም ዓይነት ወታደር፣ ፖሊስ፣ የደህንነት ኃላፊ እና ሌላ የሲቪል ባለስልጣን በህግ ፊት እንዲቀርብ ተደርጎ የተቀጣ፣ ላጠፋው ጥፋት ተጠያቂ የሆነ ወይም ደግሞ ለፈጸማቸው ግድያዎች፣ ወንጀሎች እና የዘር ማጥፋት ወንጀሎች፣ የጦር ወንጀሎች ወይም ጦrኝነት ተጠያቂ ሆኖ አያውቅም፡፡

በኢትዮጵያውያን/ት እና በኢትዮጵያዊ/ያት ስደተኛ ላይ እየተካሄደ ያለው ነጻ የሰው አደን መቆም አለበት!

የንዴት ሞት እና በኢትዮጵያውያን መሞት ላይ ያለው ንዴት፣

ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ምንም ዓይነት ርህራሄ በሌለው አሸባሪ ቡድን እንደ በግ የመታረዳቸው ሁኔታ በዓለም ህዝብ ዘንድ ታላቅ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡ ጳጳስ ፍራንሲስ እንዲህ ብለዋል፣ “ሰላማዊ በሆኑ የክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ በሊቢያ በጨካኝ ሸፍጠኞች የተደረገው እልቂት በጣም አስደንጋጭ እና አሳዛኝ ነገር ነው፡፡“ በመቀጠልም እንዲህ በማለት ሀሳባቸውን ቋጭተዋል፣ “በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በጥቂት የኤስያ ሀገሮች በዚህ ዓይነት ቀጣይነት ባለው እንደዚህ ባለ ጭካኔ በተመላበት የክርስቲያኖች መስዋዕትነት ከልብ የሆነ መንፈሳዊ ትብብር አስፈላጊ ነው፡፡“ ጳጳሱ እነዚህ አሸባሪ ቡድኖች ከሰይጣን ጎን የቆሙ ናቸው በማለት እንዲህ ብለዋል፡፡ “የእኛ የክርስቲያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ደም በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ገብቶ በመጮህ በደግ ነገር እና በሰይጣናዊ ድርጊት መካከል ያለውን ልዩነት ለማወቅ የሚሰማ ምስክርነት ነው፡፡“

የኦባማ አሰተዳደር በአይኤስአይኤል/ISIL እና ተባባሪዎቹ በሊቢያ በኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ላይ የተፈጸመውን ጭካኔነት የተሞላበት የሽብር የግድያ እልቂት ጠንካራ በሆነ መልኩ አውግዘዋል፡፡ እነዚህ አሸባሪዎች የጥቃት ሰለባዎቹ በአሸባሪዎች ላይ ባላቸው እምነት፣ ጦረኝነት፣ እደገኛነት እና ጨካኝነት ምክንያት ብቻ እነዚህን ወንዶች ገድለዋቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት እየተባለ የሚጠራው የአምባገነን ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በመጀመሪያ ይህንን አሸባሪዎች የጥቃት ሰለባዎችን አንገት እየቀሉ አሰቃቂ በሆነ መልኩ የገደሏቸውን ዜጎች ኢትዮጵያውያን ናቸው ብሎ ለመቀበል እና ዕውቅና ለመስጠት ተቃውሞውን አሰምቶ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ የሆነው ሬድዋን ሁሴን የእርሱ መንግስት የጥቃቱ ሰለባ የኢትዮጵያ ዜጎች መሆናቸውን ገና ማረጋገጥ ሳይችል የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ድርጊት ያወግዛል ብሏል፡፡

አንገታቸውን እየተቀሉ የተገደሉት የጥቃቱ ሰለባዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው የሚለውን ዘገባ ሲኤንኤን/CNN የተባለው ዓለም አቀፍ የዜና ወኪል ቢዘግብም እንኳ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጉዳዩ አይደለም፡፡ አልጃዚራ/Al Jazeera የተባለው ዓለም አቀፍ የዜና ወኪል አንገታቸውን እየተቀሉ እንዲገደሉ የተደረጉት ዜጎች ኢትዮጵያውያን ናቸው የሚል ዘገባ ቢያቀርብም ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምኑም አይደለም፡፡ ሬውተርስ/Reuters፣ ኤጀንስ ፍራንስ ፕሬስ/Agence France Press ቢቢሲ/BBC፣ ቪኦኤ/VOA እንደ ኒዮርክ ታይምስ ያሉ የዜና ወኪሎች በሙሉ በአሸባሪዎች ዕኩይ ምግባር የጥቃቱ ሰለባ ለሆኑት ኢትዮጵያውያን ዕውቅና በመስጠት ሀዘናቸውን የገለጹ ሲሆን የእኛዎቹ ፈጣጣዎች ግን እውነታውን በመቀበል ዕውቅና ለመስጠት ባለመፈለግ አሻፈረኝ ብለዋል፡፡ ለመሆኑ እነዚህ ደንታቢሶች ስለምን ጉዳይ ነው ሊያሳስባቸው የሚችል? አንገታቸውን እየተቀሉ የተገደሉ የሌላ ሀገር ዜጎች መሆናቸውን በስህተት የገለጹ በመሆናቸው ምክንያት ቀደም ሲል ስለዚህ ጉዳይ መረጃው ነበራቸውን? በዓለም ላይ በየትኛውም ቦታ ቢሆን የማንም ጨዋ ሀገር መንግስት በዓለም አቀፍ የዜና ወኪሎች በተደጋጋሚ የተገለጸን እውነታ በጥሬው እንዳለ እውነት ነው ብሎ መውሰድ እና ቁጣውን እና የሚያሳስበው መሆኑን መግለጽ የለበትምን!?

እውነታው ግን፡ ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ምንም ዓይነት ደንታ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም፡፡ ደም በጠማቸውአሸባሪ ዘራፊዎች ስለጠፋውይህ የወጣት ኢትዮጵያውያን ዕልቂት ለወያኔ ምኑም አይደለም!!!

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እነዚህ የጥቃቱ ሰለባዎች አንድ ጊዜ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን ካረጋገጠ በኋላ የአዞ እንባ በማንባት እንዲህ የሚል መግለጫ አወጣ፣ “ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ምንም ነገር በሌላቸው በንጹሀን ዜጎቻችን ላይ በተፈጸመው እኩይ ድርጊት ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል፡፡”

ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በሊቢያ አሸባሪዎች በግፍ ያለቁት የጥቃቱ ሰለባ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ከታወቀ በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት የሶስት ቀናትየሀዘን ቀን በማለት አውጇል፡፡

አድኃኖም እና የእርሱ የወረቀት አለቃው እና የኢትዮጵያ የይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በሊቢያ ለቀሩት ኢትዮጵያውያን ወገኖች አስተማማኝ ደህንነት ሲባል ምንም ዲፕሎማሲያዊ እርምጃ ሳይወስድ ለይስሙላ እንኳ ለታዕይታ ያህል ምንም ነገር ሳይደርግ ዝም በማለት አልፎታል፡፡ ምንም ዓይነት ዲፕሎማሲያዊ ተቃውሞ እንኳ አልተደረገም፡፡ አስገዳጅ በሆነው የዲፕሎማሲ አካሄድ መንገድ እንኳ ለመንቀሳቀስ አልተሞከረም፡፡ በሊቢያ ለቀሩት ኢትዮጵያውያን ደህንነት ሲባል ለተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር መጠለያ በመስጠት እርዳታ እንዲደረግላቸው እንኳ አስቸኳይ የሆነ ጥያቄ አላቀረበም፡፡ ኃይለማርያም እና አድኃኖም የእነርሱ ቃል አቀባይ ሁሉንም ንግግር እንዲናገር በመተው በቤተክርስቲያን ውስጥ እንዳሉ አይጦች ጸጥ በማለት አልፈውታል፡፡ ይኸ ጉዳይ የሚያስደንቅ አይደለም ምክንያቱም የኢትዮጵያ ስደተኞች የትም ሀገር እንዲሄዱ አይፈልጉም!

ለታሪክ ምዝገባ ያህል አድኃኖም እና የእርሱ የወረቀት አለቃው ኃይለማርያም ደሳለኝ እ.ኤ.አ ጥቅምት 2013 በአፍሪካ ህብረት የስብሰባ አዳራሽ በመገኘት የእነርሱ የምግባር ጓደኛ የሆነው ኡሁሩ ኬንያታ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በመከሰሱ ምክንያት ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት ድርጅቱ ሰው ገዳይ እና ዘር አዳኝ እንደሆነ አድርገው ቡራ ከረዩ ሲሉ የነበሩትን ሁኔታ ለመግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ በዚያ ስብሰባ ወቅት ሁሉም ሀገሮች የሮምን ስምምነት በመጠቀም ስብሰባውን ረግጠው ከድርጅቱም እንዲወጡ ለማድረግ ግንባር ቀደም የመድረክ ላይ ተዋናይ ሆነው ታይተዋል፡፡

ዛሬ ወገኖቻቸው በሊቢያ እና በመካከለኛው ምስራቅ የተለያዩ ቦታዎች እንደ አውሬ እየታደኑ ሲገደሉ እና በየቀጣሪዎቻቸው መኖሪያ ቤቶች እንደላውንድሪ ልብስ ሲሰቀሉ እና ሲሰጡ እያዩ እና እየተመለከቱ ምላሳቸው ታሽጓል፣ አንደበታቸው ተሸብቧል፡፡ የአፍሪካ ህብረት በእነዚህ አሸባሪዎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ የመድረክ ላይ ትወና ያላደረጉት ወይም ደግሞ ቁጣቸውን ለመግለጽ ድፍረቱን ያጡት ለምንድን ነው? ለአድኃኖም፣ ለኃይለማርያም እና ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እ.ኤ.አ በ2013 በሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እንደተፈጸመው፣ እ.ኤ.አ በ2005 በኢትዮጵያ የድሀረ ምርጫውን ውዝግብ ተከትሎ ተፈጥሮ እንደነበረው…ሁሉ ተመሳሳይ እንደሆነ አድርገው ነው የሚመለከቱት፡፡ ጉዳዩ ለአንድ ሳምንት ወይም ለሁለት ሳምንታት ያህል የሚያነጋግር ይሆን እና ከዚያ በኋላ እልም ሙልጭ ብሎ በመጥፋት ያው የተለመደው አካሄድ ይቀጥላል፡፡

በዚህ ባሳለፍነው የካቲት ወር ከ21 በላይ የግብጽ ጳጳሳት በጭራቃዊ አሸባሪ ቡድን አባላት በታረዱበት ጊዜም እንደዚሁ ምንም ነገር ሳይደረግ ነው የቀረው፡፡ በሊቢያ አንገታቸውን እንደተቀሉት ኢትዮጵያውያን ሁሉ የግብጽ ጳጳሳትም ብርቱካናማ ልብስ እንዲለብሱ ተደርገው እና እጃቸውን ወደ ጀርባቸው አድርገው በማሰር እልቂቱ እንዲፈጸምባቸው ተደርጓል፡፡ የግብጽ ወንዶች እንደ ኢትዮጵያ ወንዶች ሁሉ አንገታቸው ከመቀላቱ በፊት እንዲንበረከኩ ተደርገዋል፡፡

ፕሬዚዳንት አብደል ኤል ሲሲ የግብጽ ጳጳሳት አንገት መቀላቱን በሰሙ ጊዜ እንደ እብድ ሆነው ነበር፡፡ በቴሌቪዥን የዘለቀ ንግግር በማድረግ ለዚህ ዕኩይ ድርጊት ግብጽ ወዲያውኑ የአጻፋ እርምጃ እንዳትወስድ እና የመቆጠብ መብት እንዳላት አሳስበው ነበር፡፡ ጥልቅ የሆነ ሀዘናቸውን እንዲህ በማለት ገልጸው ነብር፣ “በሊቢያ የሞራል ስብዕና በጎደለው መልኩ ያለቁትን የግብጽ የጥቃት ሰለባዎች የዓለም ህዝብ እንዲገነዘበው እና በዚህ አሰቃቂ ዕልቂት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እና የግብጽ ህዝብ የተጎዳውን ጉዳት ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡“ በሰዓታት ጊዜ ውስጥ ኤል ሲሲ በሊቢያ ከመከላከያ ምክር ቤታቸው ጋር በመምከር የአሸባሪዎች መቀመጫ ከተማ በሆነችው ዴርና ተብላ በምትጠራው የሊቢያ ከተማ ላይ የግብጽን ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ለማሰማራት ስምምነት አደረጉ፡፡ በአሰቃቂ ሁኔታ በግፍ ለተገደሉት 21 የግብጽክርስቲያኖች ሰማአታት ክብር ሲባል ግብጽ የሰባት ቀናት የሀዘን ቀናት አድርጋ አወጀች! በጣም የሚያበሳጨው እውነታ ደግሞ በሊቢያ የሚገኙት ቀሪዎቹ የኢትዮጵያ ስደተኞች እና በሊቢያ ከወያኔ አገዛዝ አምባሳደር የስልክ ቁጥር ተስጥቷቸው ግንኙነት እንዲያደርጉ ቢነገራቸውም ምንም ዓይነት የማቴሪያል እና የሞራል ድጋፍ ያለመደረጉ ጉዳይ ነው፡፡ እርዳታ ለማግኘት ሲያደርጓቸው የነበሩት ጥረቶች ሁሉ በግዴለሽነት ምክንያት ስኬታማ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ አሁን በቅርቡ ከአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ፕሮግራም ጋር ከኢትዮጵያ ስደተኞች ጋር ከተደረገ ቃለ መጠይቅ በተገኘ ዘገባ መሰረት ስደተኞቹ እርዳታ ከማግኘት ይልቅ ቸልተኝነትን እና ግድየለሽነትን አሳይተዋቸዋል፡፡ አንድ ቃለመጠይቅ አድራጊ እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቦ ነበር፡

“በግብጽ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር ለመገናኘት እና ድጋፍ ለማግኘት የኤምባሲውን ስልክ ቁጥር አግኘተን ነበር፡፡ ሆኖም ግን ከኢትዮጵያ መንግስት ምንም ዓይነት እርዳታ አላገኘንም፡፡ ይልቁንም በገዛናት ትንሽ የስልክ ጥሪ ካርድ በመጠቀም በግብጽ ካለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር ለመገናኘት የተቻለንን ያህል ጥረት በማድረግ ስንደውል ነበር፡፡ በምንደውልበት ጊዜ ስልኩን ያነሱ እና ያሾፉብን ነበር፡፡ ከእኛ ጋር ንግግር አያደርጉም ነበር፡፡ ስልኩን ያነሱ እና ከእኛ ጋር ባለመነጋገር ስልኩ የጥሪ ካርዱን ያለምንም ፋይዳ እንዲጨርስ ያደርጉብን ነበር፡፡ ከዚያም ሌላ ካርድ እንገዛ እና እንይዛለን፡፡ አንዳንድ ጊዜ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ምንም ዓይነት ምላሽ አይሰጡም…”

ሌላ በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ፕሮግራም ቃለ መጠይቅ የተደረገለት ሰው ደግሞ እንዲህ የሚል ተመሳሳይነት ተሞክሮ ያለው ዘገባ አቅርቧል፡

“በእርግጥ አድኃኖም፣ ኃይለማርያም እና ወያኔ ለእነርሱ ምን እንደሚናገሩ ሁላችንም እናውቃለን፡ ምንም ነገር አይተውም፡፡ እድሉን አግኝተው ነበር ነገር ግን አልተጠቀሙበትም፡፡ ስለዚህም ቀደም ሲል ነግረናቸዋ፡፡ ከዚያም ትምህርት ይቀስማሉ ብለን እናስባለን…ዘበት! ዘበት! ዘበት! …“

ግን የኢትዮጵያ ወጣቶች እግሮቻቸው ወደመሯቸው የሚሄዱት ለምንድን ነው?

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ወጣቶች ሀገራቸውን በመልቀቅ እንደዚህ ላለ አደገኛ የሆነ ችግር ውስጥ የሚገቡት ለምንድን ነው?

ወተት እና ማር የሚፈስባትን እና ባለሁለት አሀዝ የምጣኔ ሀብት ዕድገት እያስመዘገበች ነው እየተባለ የሚደሰኮርላትን ሀገራቸውን እየለቀቁ ለመሰደድ የሚመርጡት በምን ምክንያት ነው?

ዕድለቢሶቹ ኢትዮጵያውያን አሰቃቂ የሆነውን የዕልቂት ዕጣ ፈንታ ለመገናኘት ወደ ሊቢያ የሚጓዙት ለምንድን ነው?

ለእነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች መልሱ ቀላል እና አጭር ነው፡፡ እነዚህ ወጣቶች ኢትዮጵያን ጥለው የሚሄዱት በትምህርት እና በሥራ ዕድል በተንበሸበሸ ስርዓት ውስጥ ስለኖሩ ነው? እነዚህ ወጣቶች ኢትዮጵያን ጥለው የሚሄዱት የምጣኔ ሀብት ነጻነትን ተጎናጽፈው ስለኖሩ ነው? እነዚህ ወጣቶች ኢትዮጵያን ኢትዮጵያን ጥለው የሚሄዱት በሰሜን አፍሪካ ባሉ በረሀዎች ላይ ጀብዶችን ለመስራት ስለሚፈልጉ ነው? እነዚህ ወጣቶች ለሁሉም ነገር አደጋን ህይወታቸውን ጨምሮ የመጋፈጥ ድፍረቱ አላቸው ምክንያቱም ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚያገኙት የኑሮ ሁኔታ የበለጠ ወደ ውጭ በመሰደድ የተሻለ የኑሮ ሁኔታ ማግኘት ስለሚችሉ ነው፡፡ ህይወታቸውን ለማሻሻል ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖሩ ነበር፣ ሆኖም ግን በድህነት አረንቋ ውስጥ ተዘፍቀው የሚገኙትን ደኃ ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት ሲሉ በተቃጠለው የአፍሪካ በረሀ በመጓዝ የመሞት አደጋን ይጋፈጣሉ፣ ወይም ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅ ለሚገኙ ጨካኝ ለሆነ ወይም ለሆነች የቤተሰብ ኃላፊ አገልጋዮች ይሆናሉ፡፡

በአሁኑ ጊዜ ወጣት ኢትዮጵያውያን በወያኔ አምባገነን ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቁጥጥር ስር በድህነት እና በነጻነት እጦት ተዋርደው ከሚኖሩ ይልቅ እግራቸው ወደመራቸው በበረሀ እና በጫካ ውስጥ ሄደው ለመሞት ፈቃደኞች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች ወደ ሊቢያ በመሄድ እንዲህ የሚለውን ታዋቂ የነጻነት መፈክር በማሰማት የሞት ጽዋቸውን ተጎንጭተዋል፡ “ሞቴን ስጠኝ ወይም ደግሞ ነጻነቴን ስጠኝ!“ እነዚህ ወጣቶች ከወሮበላ አምባገነኖች የግፍ አገዛዝ ነጻ ሆነው ለመኖር ሲሉ በሌሎች ወሮበሎች እጅ ወድቀው ህይወታቸውን አጥተዋል! ሆኖም ግን በነጻነት ለመኖር ሙከራ ሲያደርጉ በመስዋዕትነት አልፈዋል!
eth cry
ኢትዮጵያውያን/ት ሀገራቸውን ከልብ ይወዳሉ፡፡ ሀገራቸው በዲኤንኤ ዘረመላቸው ውስጥ ተቀብሮ የሚኖር ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን የመጨረሻዎቹ ወንድ እና ሴት እስከሚቀሩ ድረስ የምጣኔ ሀብት ፍላጎታቸውን ለማሻሻል ሲሉ ብቻ ሀገራቸውን ትተው እና በከፍተኛ አደጋ ውስጥ ገብተው በፈቃደኝነትም ሆነ በሌላ መልክ ከሀገር በመውጣት ስደተኛ አይሆኑም ወይም ደግሞ በረሀውን እና ጫካውን እያቋረጡ የአውሬ እና የአሞራ እራት አይሆኑም፡፡ ወጣቶች ሀገራቸውን ባለመውደዳቸው ምክንያት አይደለም እየተሰደዱ ያሉት ሆኖም ግን የፍቅር እና የሰላም የነበረችው መሬት ወደ ጥላቻ መሬትነት በመሸጋገሯ ምክንያት ነው፡፡ የ13 ወራት የጸሐይ ብርሀን ባለቤት የሆነችው ሀገራቸው አስከፊ በሆነ የአምባገነንነት የጨለማ መጋረጃ ለሩብ ምዕተ ዓመት ያህል በመሸፈኗ ብቻ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ትተው ከሚሰደዱ ይልቅ ለሀገራቸው ያላቸው ፍቅር የበለጠ ነው፡፡

እንደ ጣሴ አብይ ዘገባ የኢትዮጵያውያን/ት ወደ ውጭ ሀገር የሚደረግ ፍልሰት እንደማዕበል ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል፡፡ እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ የተካሄደው የመጀመሪያው ማዕበል በጣም ጥቂት በሆኑ ምሁራን እና በጊዚያዊነት ብቻ አብዛኛውን ጊዜ ወደ ምዕራቡ ዓለም በዋናነት በትምህርት እና በስልጠና ስም ከሀገር የሚወጡ እና ወደ እናት ሀገራቸው የመመለስ ዓላማን ያነገቡ ነበሩ፡፡ ያ አዝማሚያ እ.ኤ.አ ከ1974 – 1982 ባሉት ዓመታት ውስጥ የተከናወነው ሁለተኛው የስደት ማዕበል ነው፡፡ በዚህ ጊዜ አምባገነኑ እና አረመኔው የወታደራዊ መንግስት እ.ኤ.አ ከ1974 ጀምሮ ማንኛውም ዜጋ ሀገሩን ትቶ መሰደድ እንዳይችል ከፍተኛ የሆነ ችግር ፈጥሮበት ነበር፡፡ እናም በተለያየ ሁኔታ ከሀገር ሾልከው ለመኮብለል ሲሞክሩ የተገኙ ዜጎች ላይ አደገኛ የሆነ ቅጣት ይጣል ነበር፡፡ የደርግ ወታደራዊ ጭቆና የኢትዮጵያውያንን የስደተኞች የጎርፍ በር ብርግድ አድርጎ ከፈተው፡፡

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት የኑሮ መሰረታቸውን በሰሜን አሜሪካ ለማድረግ ሀገራቸውን ትተው ይሰደዳሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ1965 የዩኤስ አሜሪካ የስደተኞች እና የዜግነት ድንጋጌ ሕግ ሀኖ ከወጣ በኋላ ኢትዮጵያውያን/ት ወደ ዩኤስ አሜሪካ ለመሰደድ ከአፍሪካ ሶስተኛ በመሆን ትልቅ ደረጃ ላይ ሆና ተገኝታለች፡፡

አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን/ት ወደ አሜሪካ የደረሱት ዩናይትድ ስቴትስ እ.ኤ.አ በ1980 በምክር ቤቱ ህግ ሆኖ ከወጣ በኋላ ሶማሌዎች እ.ኤ.አ በ1994 በመቅደም የመሪነቱን ቦታ እስከሚይዙት ድረስ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ታላቁ የስደተኞች ቡድን ሆና ቆይታለች፡፡

እንደ ጣሴ ዘገባ እ.ኤ.አ በ1991 የኮሎኔል መንግስቱ አገዛዝ ከወደቀ በኋላ አራተኛው የስደተኛ የጎርፍ ማዕበል አብዛኛውን ጊዜ የጎሳ ግጭትን ለማምለጥ እና የፖለቲካ ጭቆናን ለማስወገድ ሲባል የጎሳ ባለሙያዎች በገፍ ከሀገር መሰደድ ጀመሩ፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ለመኖር በጣም አስቸጋሪ የሆነበት እና ሀገርን ጥሎ ለመሰደድ የተቻለበት ጊዜ አምስተኛው ማዕበል እየተባለ የሚጠራው የስደተኞች ጊዜ ነው፡፡ “ከዓለም አቀፍ የባሪያ ንግድ ወደ ዓለም አቀፍ የቤት ሰራተኛ ንግድ“ በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ ጥር 2012 ባቀረብኩት ትችት መሰረት ወደ ውጭ ለሚደረግ ስደት ዋናው ምክንያት የኢትዮጵያ ውስጣዊ የፖለቲካ ሁኔታ ነው፡፡

በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አገዛዝ ዘመናዊ የባሪያ በንግድ አስፈጻሚዎች ትስስር እና ፈቃድ አውጥተው እየሰሩ ያሉ የግል ቀጣሪ ኤጀንሲዎች በመካከለኛው ምስራቅ በኢትዮጵያውያን ሴቶች ላይ ታላቅ ችግርን ፈጥሯል፡፡ እነዚህ የሰው ንግድ የሚያካሂዱ ድርጅቶች የኮንትራት ባርነትን በመፍጠር በድብቅ በባለስልጣኖች የሚሰጥ ድጋፍ እና ምንም ዓይነት የክትትል ስራ ሳይሰራ የሰራተኞችን ደህንነት እና የኑሮ ሁኔታ በሄዱበት ሀገር የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የኢትዮጵያ የቤት ሰራተኞች በቢና ፌርናንድዝ ጥናት በ7ኛው ምዕራፍ ላይ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ እ.ኤ.አ በ2009 በየመን አድርገው ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመሸጋገር 74 ሺህ ህዝብ በአደጋ ውስጥ ወድቆ የነበረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 42 ሺህ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን/ት ናቸው፡፡ በመንግስት መረጃ መሰረት በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙት ኢትዮጵያዊ የቤት ሰራተኞች ውስጥ 91 በመቶ የሚሆኑት ብቻቸውን ያሉ ሴቶች ሲሆኑ 83 በመቶ የሚሆኑት ከ20- 30 ባሉት የእድሜ ጣሪያ ውስጥ የሚገኙት ናቸው፡፡ ወደ 63 በመቶ የሚሆኑት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያላቸው ሲሆኑ 26 በመቶ የሚሆኑት ምንም ዓይነት ማንበብ እና መጻፍ የማይችሉ ማይሞች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 71 በመቶ የሚሆኑት ሙስሊሞች ሲሆኑ 93 በመቶ የሚሆኑት በየወሩ ከ100 – 150 ዶላር የኪስ ግንዘብ ይሰጣል፡፡ እነዚህ ጥቂት ሴቶች ከመንግስት ጋር በስደተኛ ሰራተኝነት በመንግስት ምዝገባ ያደርጋል፡፡ ሌሎቹ ህገወጥ ደላላዎች እና ላባቸውን ያላፈሰሱበትን መውሰድ የሚፈልጉ በዝባዦች ደግሞ የሴቶችን ገንዘብ ቀምተው ይወስዱ እና ሶማሌ እንኳ ሳይደርሱ በበረሀ ላይ ጥለዋቸው ይሄዳሉ፡፡

ህወሀት እና ህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣

እ.ኤ.አ ከ1998 ጀምሮ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በአዋጅ ቁጥር 104/1998 የግል ስራ ቀጣሪ ኤጀንሲን በማቋቋም ለግል ስራ ቀጣሪ ኤጀንሲዎች እና ህገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎችን እና ደላላዎችን በህግ ሊያስጠይቅ የሚችል አዋጅ አወጣ፡፡ እ.ኤ.አ በ2009 ይኸ አዋጅ ተሻረ እና “የስራ አገልግሎት አዋጅ ቁጥር 632/2009“ በሚል ሌላ አዋጅ ተተካ፡፡ ይህ አዲሱ አዋጅ የግል የስራ ቀጣሪ ኤጀንሲዎች እድሚያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎችን መቅጠር እንደማይቻል፣ ከተቀጣሪው ሰው ጋር በጽሁፍ ስምምነት እስካልተደረሰ በስተቀር ማንንም ሰራተኛ ተነስቶ ከስራው ማባረር እንደማይቻል፣ ስራ ለመቀጠር እና አዲስ ስምምነት ለመፈራረም ወይም የቆዬ ስምምነትን ለማደስ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጽ/ቤት ፈቃድ ማግኘት እንደሚያስፈልግ፣ ወደ ውጭ ሀገር የሄደ ስራ ፈላጊ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጽ/ቤት ቀርቦ መመዝገብ እንዳለበት በግልጽ አስቀምጧል፡፡
Amhara Women Cry
ስራ ፈላጊዎችን ወደ ውጭ ሀገር የሚልክ የግል ስራ ቀጣሪ ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ዜጎች ለስራ ፍለጋ የሄዱበት ሀገር የስራ ሁኔታ የሌሎች ሀገሮች ስራ ፈላጊዎች ሄደው ከሚሰሩት የስራ ሁኔታ እና ያነሰ ጥቀም እንዳይኖረው የማረጋገጥ ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ የውጭ ሀገር ቀጣሪ ሰራተኛው ለተንቀሳቀሰበት ሀገር የቪዛ ክፍያ፣ የደርሶ መልስ ቲኬት፣ የኗሪነት፣ የስራ ፈቃድ እና የኢንሹራንስ ክፍያዎችን ለሰራተኛው እንዲከፍል ይጠበቅበታል፡፡ ከዚህም በላይ ስራ ፈላጊዎችን ወደ ውጭ ሀገር ልኮ ስራ ለማስቀጠር ፈቃድ የተሰጠው ማንኛውም የግል ስራ ቀጣሪ ኤጅንሲ የሰራተኛውን መብት ለማስጠበቅ እና በመብቱ ሊያገኛቸው የሚፈለጉትን ጥቅሞች ተግባራዊ ለማስደረግ እስከ 500 ለሚሆኑ ሰራተኞች ቢያንስ 30,000 ዶላር በባንክ ሂሳብ ማስቀመጥ ወይም ደግሞ ቦንድ መግዛት እንዳለበት ግዴታ ተጥሎበታል፡፡

አዋጅ ቁጥር 632ን ተላልፎ የተገኘ ማንኛውም የግል ስራ ቀጣሪ ኤጀንሲ ስራው ለተወሰነ ጊዜ እዲቋረጥ፣ ህገወጥ ስለሆነ ወደ ተግባር መሸጋገር እንደማይችል ወይም ደግሞ የስራ ፈቃዱ እንደሚሰረዝ በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ በዚያ አዋጅ በአንቀጽ 40 ስር በርካታ የሆኑ አሳሪ የወንጀለኛነት ቅጣቶች ተዘርዝረው የተቀመጡ ቢሆንም ቅሉ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር አስፈጻሚዎችን ወደ ህግ ሊያቀርብ የሚያስችል ተግባራዊ እንቅስቃሴ ግን በጣም አናሳ መሆኑን ሊያስረዱ የሚችሉ ማስረጃዎች አሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 የወጣው የዩኤስ የመንግስት መምሪያ ዘገባ ከሆነ እ.ኤ.አ በመጋቢት እና ጥቅምት 2009 መካከል የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 11ኛ የወንጀል ችሎት ስለድንበር ተሻጋሪ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር የተያያዙ 15 ጉዳዮች ቀርበውለት ከእነዚህ ውስጥ 5ቱ የጥፋተኝነት ብይን የተሰጠባቸው፣ 9ኙ ጥፋተኝነት የሌለባቸው እና አንዱ ደግሞ ምስክር ባለመገኘቱ ምክንያት እንዲቋረጥ የተደረገ ሆኗል፡፡ 5ቱ የጥፋተኝነት ብይን ከተሰጠባቸው መካከል 3ቱ ተከላካዮች የ5 ዓመት እስራት በመጣል ስራቸውም እንዲቆም ሲደረግ፣ ሁለቱ ተከላካዮች ደግሞ በገንዘብ እንዲቀጡ የተደረገ ሲሆን አንዱ ተከላካይ ደግሞ የ5 ዓመት እስራት ተበይኖበታል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን/United Nations Higher Commission for Refugees (UNHCR) እ.ኤ.አ በ2011 እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቷል፣ “የኢትዮጵያ መንግስት የእራሱ ዜጎች ለስራ ጉዳይ ከሚሄዱባቸው ሀገሮች መንግስታት ጋር የኢትዮጵያ ሰራተኞችን የስራ ሁኔታ ለማሻሻል እና የጥቃት ሰለባ የሚሆኑትን ዜጎቹን ደህንነት ለመጠበቅ ሲል ብዙ ርቀት ያልተጓዘ እና ገና በጅምር ላይ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ፈቃድ ያላቸው የሰራተኛ ቀጣሪ ኤጀንሲዎች የሰራተኞች የውል/ኮንትራት ስምምነት ቢቋረጥ ለመያዣነት በሚል ከሰራተኞች እየተቆረጠ ገንዘብ በባንክ እንዲቀመጥ የሚደረግ ቢሆንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህንን የተከማቸውን ገንዘብ የጥቃት ሰለባ ሆነው ወደ ሀገራቸው ወደ ኢትዮጵያ በሚመለሱበት ጊዜ ለእነዚህ የጥቃት ሰለባ ለሆኑት ሰራተኞች ምንም ዓይነት የትራንስፖርት መጓጓዣ አይከፍልም፡፡“

ሆኖም ግን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ሌሎች የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባዎችን ከአደጋ ለመከላከል ሲታትር ይታያል፡፡ ለምሳሌ ያህልም እንዲህ የሚለውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽንን ዘገባ ማየቱ ለዚህ ታላቅ ማስረጃ ነው፣ “እ.ኤ.አ በ2010 ኢትዮጵያ በሲናይ በረሀ በራሻዳ የኮንትሮባንድ ህገወጦች የሚዘረፉትን፣ የሚሰቃዩትን፣ በግዴታ በግንባታ ስራ ላይ እየተመደቡ ጉልበታቸውን የሚበዘበዙትን እንደዚሁም ደግሞ ከብሄራዊ ውትድርና አገልግሎት ፕሮግራም ጋር በተያያዘ መልኩ ከኤርትራ እየኮበለሉ ወደ ጎረቤት ሀገር የሚሰደዱትን የኤርትራ ዜጎች እና ከግብጽ ለተጋዙት 1,383 የኤርትራ ስደተኞች ጥገኝነት ሰጥታለች፡፡“ እንደዚህ ዓይነቱ ከህገወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ መልኩ የጥቃት ሰለባ ለሚሆኑት እና የሰብአዊ መብታቸውን ተነፍገው ለሚሰቃዩት ዜጎች ከለላ መሆን እና መጠለያ መስጠት ከመልካም ስራ እና ከሞራል ስብዕና አንጻር በጎ ምግባር ቢሆንም ቅሉ ደግነት ከቤት መጀመር እንዳለበትም እውነት ነው፡፡

ለችግሩ መፍትሄ ለመፈለግ ቃል የተገባው እ.ኤ.አ በ2013 ነበር፡፡

እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2013 የኢትዮጵያ የቤት ሰራተኞች እና ጥገኝነት የጠየቁ ወገኖች በሳውዲ አረቢያ ስቃይ እና መከራን እየተቀበሉ በነበረበት ወቅት አድኃኖም እንዲህ ብሎ ነበር፡ “በእርግጥ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ችግር ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ እና መፍትሄ ለመስጠት የአጭር እና የረዥም ጊዜ ዕቅድ በመንደፍ ያላሰለሰ ጥረት ስናደርግ ቆይተናል፡፡ እናም እንደምታውቁት ሁሉ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ መሻሻል እያሳየች እና ባለሁለት አሀዝ ዕድገት (ይህንን ባለሁለት አሀዝ የምጣኔ ሀብት ዕድገት እየተባለ በየዕለቱ የሚደሰኮርለትን ተራ ፕሮፓጋንዳ ተጨባጭ መረጃ በማቅረብ በማጋለጥ ከምንም ጥርጣሬ በላይ ቅጥፈት፣ ነጭ ውሸት እና የቁጥር ጨዋታ ነው በማለት ቀደም ሲል ማስተባበሌን ልብ ይሏል) እያስመዘገበች ነው፡፡ ከዋሻው መጨረሻ ብርሀን ይታያል፣ እናም ማድረግ እንደምንችል እናውቃለን፡፡ ድህነትን ማጥፋት እንደምንችል እናውቃለን፡፡ ጉዟችን በትክክለኛው ጎዳና ላይ ነው፡፡ ሆኖም ግን እስከ አሁንም ድረስ በዓለም አቀፋዊ ትብብር ማመን አለብን፡፡ ቢሆንም ግን እንደዚህ ያለ ሁኔታ ይፈጸማል ብለን አልጠረጠርንም፡፡“ አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

አድኃኖም ከተናገራቸው ንግግሮች ውስጥ በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ በሳውዲ አረቢያ “እንደዚህ ያለ ሁኔታ ይፈጸማል ብለን አልጠረጠርንም ነበር” ወይም ደግሞ ለእርሱ ሁሉም ነገር “ፍጹም አስገራሚ ነበር“ በሚሉት አባባሎች ላይ ለማመን እስከ አሁንም ድረስ ይከብደኛል፡፡ በእርግጥ በዚያን ወቅት አዘጋጅቸው በነበረው ትችቴ ላይ በግልጽ እንዳስቀመጥኩት ሁሉም ነገር “ፍጹም አስገራሚ ነበር“ የሚለው አባባል ለሁሉም አስገራሚ ሊሆን እንደማይችል አስገንዝቤ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ጥቅምት 2013 ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ እንደዚያ ያለ የሰብአዊ ቀውስ አደጋ ይድረስባቸዋል በማለት አድኃኖም የወደፊቱን በትክክል ይተነብያል ለማለት የሚያስደፍር ምንም ዓይነት ተጨባጭ ሁኔታ የለም፡፡

ያም ሆነ ይህ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን እየተው በገፍ ወደ ሌሎች ሀገሮች የሚጎርፉበትን ጉዳይ እና እንደ ጥገኝነት ጠያቂነታቻው በሄዱባቸው ሀገሮች ሁሉ መብቶቻቸው ተጠብቀው እና የሰራተኞች የውል/ኮንትራት ስምምነትም በተለይም ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅ በሚደረጉት ላይ መፍትሄ ለማምጣት አድኃኖም “ለብዙ ጊዜ ስንሰራው የቆየነው የአጭር እና የረዥም ጊዜ ዕቅድ መፍትሄ” እያለ የሚጠራው ምን እንደሆነ ለማወቅ በመጠባበቅ ላይ ነኝ፡፡

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2015 ሆነን የተባለውን እና ቃል የተገባለትን ነገር ሁሉ ስንቃኘው ምንም የተለወጠ ነገር የለም፡፡ ወጣት ኢትዮጵያውያን/ት ወንዶች እና ሴቶች እግሮቻቸው ወደመሯቸው በመጓዝ ላይ ናቸው (በእጆቻቸው ሊመሩ ባለመቻላቸው፡፡) በመካከለኛው ምስራቅ ለመናገር በሚያዳግት ሁኔታ የጥቃት ሰለባ የመሆናቸው ጉዳይ ቀጥሎ ይገኛል፡፡ እነዚህ ወገኖቻችን ድብደባ ይፈጸምባቸዋል፣ ይሰቃያሉ፣ በረሀብ እንዲጠቁ ይደረጋሉ፣ ይሰቀላሉ፣ አሁን ደግሞ አንገታቸውን ይቀላሉ፡፡

እነዚህ ወንጀሎች አድኃኖም “ለብዙ ጊዜ ስንሰራው የቆየነው የአጭር እና የረዥም ጊዜ ዕቅድ መፍትሄ” በአገዛዙ በኩል በመደረግ ላይ ነው ብሎ በድፍረት ከተናገረ ከሁለት ድፍን ዓመታት በኋላም ሁኔታዎች ሁሉ ይዘታቸውን፣ የመፈጸም የጊዜ ፍጥነታቸውን እና መጠናቸውን በመጨመር በተጠናከረ መልኩ በመፈጸም ላይ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም የአድኃኖምን እና የኃይለማርያምን ተወዳጅ ሀረጎች በመዋስ በመካከለኛው ምስራቅ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ “የዘር አደን/race hunted” እና “የኃይማኖት አደን/religious hunted” ይፈጸማል ልበል ይሆን! እነዚህን ወገኖቻችንን ለመርዳት እና ለመናገር ከሚዘገንኑ ወንጀሎች ለመጠበቅ እስከ አሁን ድረስ ምንም ዓይነት ነገር አልተሰራም!

እንደ አካደሚክ፣ የህግ እና የሰብአዊ መብት ጥበቃ ወትዋች ባለሙያ ኢትዮጵያውያን/ት በአሸባሪዎች፣ በወሮበሎች፣ በዘራፊዎች እና ሰብአዊ መብታቸውን በሚደፈጥጡ የሰራተኛ ቀጣሪዎች የጥቃት ሰለባ መሆናቸው ብቻ ላይ አይደለም ብዙ መሰራት ያለበት፡፡ ሆኖም ግን በህግ ጥላ ከለላ ስም ህጉን እየጣሱ እና እየደረመሱ ከህግ ውጭ እየተራመዱ በወገኖቻችን መብቶች እና ህይወት ላይ ቁማር በሚጫወቱ ኃላፊ ተብዬዎች ላይ ነው ብዙ ነገር መሰራት ያለበት፡፡ ለምንድን ነው በአሁኑ ጊዜ ለኢትዮጵያውያን/ት ጥገኝነት ጠያቂዎች እና በሀገር ውስጥ መብታቸውን ለሚያጡ ሰራተኞች መፍትሄ ሊፈልግ የሚችል ቋሚ እና ልዩ ግብረ ኃይል የማይቋቋመው? ለምንድን ነው የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖች ዜጎች ወደ ውጭ እንዳይሰደዱ የማይከላከሉት እና ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚመለሱት ስደተኛ እና ጥገኝነት ጠያቂ ወገኖቻችን በሀገራቸው ላይ ስራ አግኝተው በሰላም እንዲኖሩ የማያግዙት? ለመሆኑ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ስለኢትዮጵያውያን/ት ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ የኮንትራት ሰራተኞች እና ሌሎች ምንም ዓይነት ጥሩ አያያዝ ለማይደረግላቸው፣ ሰብአዊ መብቶቻቸው ለሚደፈጠጡባቸው እና ለሚሰቃዩት ወገኖቻችን ደንታ አለውን? እንዴት ሆኖ! (በእርግጥ ይኸ የድስኩር እንጅ የተግባር ጥያቄ አይደለም፡፡)

ኢትዮጵያውያንን/ትን በሳውዲ አረቢያው እንደደረሰው ያለ ቀውስ በሚያጋጥምበት ጊዜ ለዜጎቹ የሚያስብ ማንም አገዛዝ ቢሆን የአስቸኳይ ጊዜ ግብረ ኃይል በማቋቋም በተቀነባበረ መልኩ እገዛ እያደረገ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን እየቀረበ እርዳታ እና ድጋፍ ማሰባሰብ ይኖርበታል፡፡ (ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን እየቀረበ ስል ከእነርሱ ገንዘብን እየለመነ ወደ ኪሱ ያጭቅ ማለቴ እንዳልሆነ ልብ ይባልልኝ፡፡) አድኃኖም እና አገዛዙ በመካከለኛው ምስራቅ እና በሌሎች ሀገሮች በኢትዮጵያውያን/ት የቤት ሰራተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ የደረሰው የአደጋ ሁኔታ ሲያልፍ የትርፍ ስሌታቸውን በመስራት እንደተለመደው የንግድ ጥባ ጥቤ የቁማር ጨዋታቸውን ይቀጥላሉ፡፡

ስለሆነም እነዚህን ሊመለሱ የማይችሉ ጥያቄዎችን ለእራሴ በመጠየቅ እንዲህ የሚሉትን የብቸኝነት የግጥም ስንኞችን እነሆ…

ምንድን ነው ነገሩ?

ምንድን ነው ነገሩ እስቲ ተናገሩ፣

ከቶ ምንድን ይሆን ይህ ሁሉ እሽሩሩ፣

ዕልቂት ዕጣ ፈንታ የሆነ ተግባሩ፣

ሰው መኖር አይችልም በገዛ ሀገሩ?

የኢትዮጵያውያን ነብስ እንዴት ረከሰ፣

በሊቢያ በሳውዲ ደም እየታፈሰ፣

በሲናይ በረሀ አሸዋ እየላሰ፣

ባሸባሪ ቡድን ሰው እየታመሰ፣

ደሙ ተግተልትሎ እንባውም ፈሰሰ፡፡

በሰይጣን ምግባራት ወገን ተላቀሰ፡፡

ጉልበቴን መንዝሬ ልኑር ልስራ ባለ፣

ለሌላው ሰው ድሎት ጉልበቱን ባዋለ፣

ከሀገር ተሰዶ በተንቀዋለለ ነብሱን ባቃጠለ፣

ከሰማይ ጠቀስ ፎቅ ተገፍቶ ተጣለ?

በጥይት እሩምታ በግፍ ተገደለ?

ስራ ልስራ ብሎ ካገር በነጎደ፣

ለህይወት መሻሻል ሀሳብ ባራመደ፣

እንደ ፋሲካ በግ በካራ ታረደ?

ለመስራት አቅዶ ከሄደ በኋላ፣

ለደኃ ወገኑ ሊሆን ጋሻ ባላ፣

ችጋርን በማጥፋት በጥረት በመላ፣

ሊመለስ ላገሩ ነገሩ ሲብላላ፣

እንደ ሀገር ጠላት በጥይት ተቆላ?

ሀገር እንደሌለው እንደ ባዕዳ ሰው፣

ከሀገር ተገፍቶ ሀገር እያለው፣

መኖር አልችል ያለ መብት የሌለው፣

በበረሀ ቀልጦ ጫካ የቀረው፣

የአራዊት መፈንጫ ነብሱ የሆነው፣

በባዕድ ሀገር ባከኖ ውኃ የበላው፣

እሱን ማን ልበለው ኢትዮጵያዊ ነው፡፡

አንች የሀገር ቆንጆ ተስፋው የራቀሽ፣

በሀገርሽ መኖር ፍጹም ተስኖሽ፣

በባዕድ ሀገር ሆነሽ ኑሮን የቀመስሽ፣

ከስብዕና በታች ሆኖ ህይወትሽ፣

ያልፍልኛል ብለሽ ውጥንቅጥ ኑሮሽ፣

ዘመድ ወገኖችሽ እንደናፈቁሽ፣

በሰው ሀገር ሄደሽ ባክነሽ የቀረሽ፣

ሀዘናችን ከፍቷል እስቲ ተመለሽ፡፡

አዕምሮ የሰጠን ለማመዛዘን ነው፣

ደግ እና ክፉውን ለማነጻጸር ነው፣

ግና ምን ያደርጋል ሁሉ አይተገብረው፣

ወያኔ ያዋለው ተንኮል ለማድራት ነው፣

ህዝብን ከህዝብ ጋር ለማተራመስ ነው፡፡

የኢትዮጵያውያን ደም ቢፈስ ቢንዠቀዠቅ፣

በጥይት ቢቆላ በገመድ ቢታነቅ፣

ቢጣል በውቅያኖስ በወንዝ እና በሐይቅ፣

ወያኔ ከጥቅሙ መች ይል እና ንቅንቅ፡፡

ምንድን ነው ነገሩ እስቲ ተናገሩ?

ማንንም ሳትፈሩ ሳትደናገሩ፣

አንድም ነገር የለ በባህር ባየሩ፣

በየብስ በጫካው ባፈሩ በዱሩ፣

የኢትዮጵያ ደም ነው ዶፉ ውሽንፍሩ ፡፡

ምንም የሚያሳስብ የለም አንድ ነገር፣

በባህር በወንዙ ባየሩም በምድር፣

በሰማይ በጫካ በሐይቁ በባህር፡፡

በመሬት ቢዞሩ ባየር ላይ ቢበሩ፣

የማያሳስበው ምንድን ነው ነገሩ?

የኢትዮጵያ ደም ነው ጎርፉ ስንክሳሩ?

የወጣቶቸ ደም ነው ዘዋሪው አኪሩ?

ያሳስባል እንጅ በውንም በህልምም፣

በግፈኞች ድርጊት ህይወት ስትጨልም፣

ራዕይ ሲኮላሽ ሃሳቦች ሲመክኑም፣

ጭራቃዊ ድርጊት ባለም ሲለመልም፡፡

ምንድን ያሳስባል በዚህች ምድር ላይ?

ደኃውን ሀብታሙን ሁሉንም ስናይ፣

ሀቀኛ ሲያዳምጥ ሲናገር አባይ፣

ዓለም ስትናውዝ በሌት በጸሐይ፡፡

የኢትየጵያውያን ህይወት ያሳስባል፣

ሁሉም የሰው ልጆች ህይወት ያሳስባል!

እውነት ተናገሩ ምንድን ነው ነገሩ?

እስቲማ ንገሩኝ ምንድን ነው ነገሩ?

ወገኖቼ አኩርፈው ጠፍተዋል ካገሩ፣

የእውነትን መድኃኒት ሄደው ሊቀምሩ፣

ተመልሰው መጥተው ሀገርን ሊያኮሩ፡፡

ወያኔ ጨካኝ ነው የሞራል ኪሳራ፣

እሱ በመደንገጥ ህዝብን የሚያስፈራ፣

ቀኙን ያዘው ሲሉት የሚመርጥ ግራ፣

ብዕርን ሲያሳዩት የሚመዝ ካራ፣

ጣፋጩን ሲያሳዩት የሚመኝ መራራ፣

የጽድቅ በር ትቶ ጋነም የሚያጓራ፡፡

አሸባሪ አውሬነት ስብዕና የሌለው፣

ኃላፊነት የለሽ ምግባር የጎደለው፣

የደቡብ አፍሪካው ወሮበላው ሌባው፣

የሊቢያው አጋንንት በደም ላይ የዋኘው

የሳውዲው መናጢ ውቃቢ የራቀው፣

እንዴት ሆኖ ይሆን ከህሊና እሚያድረው?

የዲያስፖራው አቅምየለሽነት፣

በኢትዮጵያዊነት ትብበር እጦት፣

በሰው ልጆች ጭራቅነት፣

በሰው ልጆች ኢሰብአዊነት፣

ይንጸባረቃል በዋናነት፣

ሁሌም ያሳስባል የኢትዮጵያዊ ህይወት፡፡

ወያኔ ወገኑን ኬሬዳሽ ብሎታል፣

ቢፈለጥ ቢቆረጥ ዓይኑን ሸፍኖታል፣

ቢሰደድ ቢሰቀል አላይም ብሎታል፣

የኢትዮጵያውያን ህይወት አልሰምር ብሎታል፡፡

ለምንወዳት ሀገራችን ለኢትዮጵያችን እጮሃለሁ፣ “ሆኖም ግን ከዋሻው መጨረሻ ብርሀን አለ”

የኢትዮጵያ የቤት ሰራተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በሳውዲ አረቢያ ስቃይ እና መከራ እየደረሰባቸው በነበረበት ጊዜ አድኃኖም እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ከዋሻው መጨረሻ ብርሀን አለ፣ እናም ድህነትን ማጥፋት እንደምንችል እንደምናጠፋ እናውቃለን፡፡“

እኔም እንደዚሁ በኢትዮጵያ በስልጣን እርካብ ላይ ከህዝብ ፈቃድ ውጭ ተፈናጥጠው ከሚገኙት ጨካኞች እና አምባገነኖች መጨረሻ ብርሀን አለ እላለሁ፡፡ ከአድማሱ ባሻገር አዲስ ቀን አለ፡፡ አንድ መሆን አለብን፣ ክርስቲያን እና ሙስሊም ሳንል ሁላችንም በሀገሪቱ ውስጥ ያለን ሁላችንም ኢትዮጵያውያን/ት ሁሉ እጅ ለእጅ ተያይዘን በአንድነት መጓዝ አለብን፡፡ እጅ ለእጅ ተያይዘን በዋሻው ውስጥ በቀጥታ በመጓዝ ለሁለት አስርት ዓመታት እና ከዚያ በላይ በጭቆና እና መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶችን ተነጥቀን ከቆየንበት ዋሻ ውስጥ በጥሰን እና በጣጥሰን በድል አድራጊነት ብርሀን ከሚታይበት ጫፍ ብቅ ማለት አለብን፡፡

እውነታውን መናገር አለብኝ፡፡ በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ተስፋ እቆርጣለሁ፣ እናም ለምንወዳት ኢትዮጵያችን አለቅሳለሁ፡፡ ይህንን በጽናት አደርጋለሁ፡፡ ምን ያህል እንደማደርግ ብታውቁልኝ? እ.ኤ.አ. በ1948 በዚያው ዓመት አፓርታይድ በደቡብ አፍሪካ እራሱ ህግ መሆኑን በማስመልከት አላን ፓቶን እንዲህ በማለት ጻፉ፣ “ለውዲቷ ሀገራችን እንጩህ“ በማለት በደቡብ አፍሪካ ዕጣ ፈንታ ላይ ጥልቅ የሆነ የተስፋ ማጣት ስሜታቸውን ገልጸው ነበር፡፡ የእኔ የግሌ በኢትዮጵያ ላይ ተስፋ የማጣት ስሜቴ ከፓቶን ስሜት ጋር ጎን ለጎን በመሄድ እንዲህ በማለት ያስተጋባል፡

…የኮሶ መታሪ እንደገባው የኮሶ ትል ስለተበጣጠሰው የጎሳ ክፍፍል፣ መቅኖውን ስላጣው የህግ ስርዓት እና እንደ አሮጌ ቁና ወደ ጎን ስለተሽቀነጠረው ብርቅዬ ባህላችን እና ልማዳችን እጮሀለሁ፡፡ አዎ፣ ስለሞተው ወንድ፣ ስለሞተችዋ ሴት እና በሞት ስለተነጠቁት ልጆች እጮሀለሁ፡፡ ስለውዲቱ ሀገሬ እጮሃለሁ፡፡ እነዚህ ነገሮች ሁሉ በመጨረሻው የውድቀት ምዕራፍ ላይ አይደሉም፡፡ ጸሐይ ሁሉም ሰው ተደስቶ ሊኖርባት ባልቻለባት በመሬት ላይ መሀለቋን ላይ ትጥላለች፡፡ ሰው የሚያውቀው የልቡን ፍርሀት ብቻ ነው፡፡

እኔም እንደ ፓቶን ሁሉ በኢትዮጵያ የጎሳ ክልል እየተባሉ ተበጣጥሰው ላሉት ጎሳዎች እጮሀለሁ፡፡

ለዚህ መቅኖውን አጥቶ ለበከተው እና ለተዋረደው የፍትህ ስርዓት እና እንደ አሮጌ ቁና ለተሽቀነጠረው አኩሪ ባህላችን እና ልማዳችን ድምጼን ከፍ አድርጌ እጮሀለሁ፡፡ ጨርቅ ነው እያሉ በአደባባይ ላዋረዱት ለኢትዮጵያ ባንዲራ ድምጼን ከፍ አድርጌ እጮሀለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ ዓመት እድሜ ብቻ ነው በማለት በድንቁርናቸው ለገደቡት እና በህዝብ በተሳለቁት ደምጼን ጮክ አድርጌ እጮሀለሁ፡፡ ኢትዮጵያ የ100 ዓመት ገደማ ያህል ህልውና ያላት ሀገር ናት ብለው ለተዘባበቱት ድምጼን ከፍ አድርጌ እጮሀላሁ፡፡

ለወንዞች እና ድምጻቸው ለተገደበው ድምጽ የለሾች ድምጼን ከፍ በማድረግ እጮሀለሁ፡፡ ለተራሮች፣ ለሸለቆዎች እና ለበረሀዎች ድምጼን ከፍ በማድረግ እጮሀለሁ፡፡ ወርቋን እና የከርሰ ምድር ማዕድኗን ተነጥቃ ለምትደማው ሀገሬ ድምጼን ከፍ በማድረግ እጮሀለሁ፡፡

በጭራቃዊ አሸባሪ ቡድን አንገታቸውን እየተቀሉ በግፍ እንዲያልቁ ለተደረጉት ለ30 የኢትዮጵያ ወጣት ክርስቲያን ወንዶች ወገኖቼ ድምጼን ከፍ በማድረግ እጮሀለሁ፡፡ ለእነዚህ ወጣቶች አባቶች እናቶች፣ ለእህቶቻቸው እና ለወንድሞቻቸው ለአጎቶቻቸው እና ለአክስቶቻቸው እንዲሁም ለአያቶቻቸው ድምጼን ከፍ በማድረግ እጮሀለሁ፡፡ ለጓደኞቻቸው እና ለጎረቤቶቻቸው፣ ለከተሞቻቸው እና ለመናገሻ መዲናቸው ድምጼን ከፍ በማድረግ እጨሀለሁ፡፡ ለውዲቱ ሀገራቸው እና ለኢትዮጵያ አለቅሳለሁ፡፡ እነዚህ ነገሮች እስከመጨረሻው ለመውደም በመጨረሻው እረድፍ ላይ አይደሉም፡፡ ጸሐይ በአሁኑ ጊዜ በጣም ጥቂቶች ብቻ እየተደሰቱ በሚኖሩባት መሬት ላይ ለ13 ወራት ያህል የሚዘልቀውን መሀለቋን በኢትዮጵያ ምድር ላይ ትጥላለች፡፡ ፍርሀታቸውን በልባቸው ውስጥ ብቻ ለሚያውቁት ወገኖቼ ድምጼን ከፍ በማድረግ እጮሀለሁ፡፡ የወገኖቼን ስቃይ እና መከራ እንዲሁም የሚደርስባቸውን መንገላታት እና መሪር ሀዘን ሁሉ እጋራለሁ፡፡

እንደ በግ ጠቦት ጸጥ ያሉትን እና በሊቢያ አረመኔ ጨካኝ እና ገዳይ ወሮበሎች ለታረዱት ወጣት ወንድሞቼ ድምጼን ከፍ በማድረግ እጮሀለሁ፡፡ ከእግዚአብሔር በቀር ምንም ዓይነት ሊረዳቸው የሚችል ኃይል በሌለበት በሊቢያ ምድር ላይ በወጥመድ ውስጥ ተይዘው በመቁለጭለጭ ላይ ላሉት ወገኖቼ ድምጼን ከፍ በማድረግ እጮሀለሁ፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ አስገድዶ መድፈር በሚፈጸምባቸው፣ በሚደበደቡት እና ከታላቅ ህንጻ ላይ በመስኮት እየተወረወሩ ለሚሞቱት፣ ከጣራ እና ከዛፍ ላይ ለሚሰቀሉት፣ የፈላ ውኃ በላያቸው ላይ ለሚደፋባቸው ወጣት እህቶቻችን ድምጻችንን ከፍ አድርገን እንጮሀለን፡፡ ተወልደው ያደጉበትን እና እትብታቸው የተቀበረበትን ሀገራቸውን በግዳጅ እንዲለቁ እና ለስደት በመዳረግ ነጻነት እንዳይሰማቸው፣ መብት ያላቸው ለመሆናቸው ምንም ዓይነት ስሜት እንዳይኖራቸው በገዛ ሀገራቸው ምንም ዓይነት የሰብአዊ ፍጡር ስሜትነት እንዳይሰማቸው በማድረግ ለከፍተኛ አደጋ እንዲጋለጡ ለሚደረጉ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች ድምጼን ከፍ በማድረግ እጮሀለሁ፡፡ በገዛ ሀገራቸው 3ኛ እና 4ኛ ደረጃ ዜግነት እንዳለ ያውቃሉ፡፡ ኑሯቸውን እና ህይወታቸውን ለማሻሻል በማሰብ የየመንን፣ የሊቢያን እና የሳውዲ አረቢያን በረሀዎች ሲያቋርጡ በሞት ለተነጠቁት እና አሁንም በመሞት ላይ ለሚገኙት ኢትዮጵያውያን/ት ወገኖች ድምጻችንን ከፍ በማድረግ እንጮሀለን፡፡ እ.ኤ.አ የ2005 ሀገር አቀፍ ምርጫ ከተጠናቀቀ በኋላ በመለስ ዜናዊ እና በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጭካኔ እና አረመኒያዊነትን በተላበሰ መልኩ በአዲስ አበባ መንገዶች በጠራራ ጸሐይ በአደባባይ ህይወታቸውን ላጡ ወጣት ወንዶች፣ ወጣት ሴቶች፣ አባቶች እና አባቶች ድምጼን ከፍ በማድረግ እጮሀለሁ፡፡

ለእህቴ ለርዕዮት ዓለሙ፣ ለወንድሞቼ ለእስክንድር ነጋ፣ ለአንዷለም አራጌ፣ ለውብሸት ታዬ፣ ለበቀለ ገርባ፣ ለአቡባከር አህመድ እና ለሌሎችም በሺዎች ለሚቆጠሩት ለኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች ሁሉ ድምጼን ከፍ በማድረግ እጮሀለሁ፡፡ ለኢትዮጵያውያን እና ለኢትዮጵያ ድምጼን ከፍ በማድረግ እጮለሁ፡፡

ተስፋ በማጣት በማሰማው ጩኸት እንዲህ የሚሉትን የሸክስፒርን የግጥም ስንኞች አረፍ በማለት አንጸባርቃለሁ፡

ዕድል እጣ ፈንታ በጨለመ ጊዜ፣

አላንቀሳቅስ ሲል የያዘን አባዜ፣

ከወንዶች ዓይን ላይ በተነነ ጊዜ፣

ሁሉም አይሳካም አይኖርም ኑዛዜ፡፡

በተተፋው መንግስት ሁልጊዜ እጮሀለሁ፣

ግራ ተጋብቼ ቀኙን አጥቻለሁ፣

ወደላይ ከመሄድ ቁልቁል እወርዳለሁ፣

አንድነቱን ትቼ ነጠላ ሆኛለሁ፣

ፍቅርን በመተው ጥላቻን ይዣለሁ፣

በህይወት ከመኖር ሞትን መርጫለሁ፣

በሀገር ከመኖር ባድን አምልኪያለሁ፣

ዘረኛን ከማጥፋት ሀሜት ለምጃለሁ፣

በዚሁ ከቀጠልኩ ጋነም እገባለሁ፡፡

የጻዲቁን መንገድ ተረተሩን ስቼ፣

እውነትን በመፍራት ለሀሰት ሞግቼ፣

ቀረሁ ባደባባይ ለፍቼ ለፍቼ፣

ባልተሳካው ጩኸት ከጋነም ገብቼ፡፡

ጆሮው በማይሰማ በዲያብሎሱ ቤት፣

በጠራራ ጸሐይ ስመላለስበት፣

እዩኝ ተመልከቱኝ ለዚህ ብኩንነት፣

ወገን አንድ በሉ ወገን ላለቀበት፡፡

ቃል ኪዳን ግቡልኝ ለመልካም ዕድል፣

ፈዋሽ አቅርቡልኝ አምጡልኝ ጸበል፣

አማልዱኝ ካምላኬ ከኃያሉ ገድል፣

ተስፋዬ ለምልሞ እንድኖር በድል…

አዎ፣ ደግሜ ደጋግሜ በመጮህ ይህንን የማይሰማ መንግስተ ሰማያት ስኬታማ ባልሆኑት ጩኸቶቼ መግቢያ ቀዳዳ በማሳጣት አስቸግረዋለሁ፡፡ አዎ፣ በእኔ ተስፋ መቁረጥ አንድ ተጨማሪ ተስፋ እቋጥራለሁ፡፡ ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከወሮበሎች አገዛዝ ነጻ ትሆናለች፡፡ ህዝቧ የእነዚህን የአጭበርባሪዎች እና ሸፍጠኞችን ተንኮል በመገንዘብ በአንድ ላይ እጅ ለእጅ በመያያዝ አንድ ላይ ሆኖ በመቻቻል፣ በስምምነት እና በፍቅር ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያን እንደሚገነባ ሙሉ ተስፋ አለኝ፡፡ ተስፋ አደርጋለሁ ምክንያቱም ተስፋየለሽነትን አስወግጃለሁ፡፡

ለውዲቷ ሀገራችን እጮሃለሁ፡፡ በደስታ እና በተስፋ እጮሀለሁ፡፡ ጩኸታችን ይሰማል የሚል ቃል ኪዳን እገባለሁ፡፡ ደቡብ አፍሪካ ከአፓርታይድ የጭካኔ አምባገነናዊ የዘረኝነት አገዛዝ ዋሻ ውስጥ አልወጣችምን? ማንዴላ እንዲህ ሲሉ አንድ ሌላ ተጨማሪ ተስፋን አልሰነቁምን?፡ “በፍጹም በፍጹም ከእንግዲህ ወዲያ በዚህ ቆንጆ መሬት አንዱ በአንዱ ላይ የሚጨቆንበት እና የሚሰቃይበት የተዋረደች ዓለም አትኖርም፡፡“

በፍጹም አትጠራጠሩ፡፡ እኔ የበለጠ በተስፋ የተሞላሁ፣ ከምንጊዜውም በላይ በደስታ የፈነጠዝሁ እንደሆንኩ እዘልቃለሁ፡፡ ኢትዮጵያውያን/ት በቅርብ ጊዜ ውስጥ የነበራቸውን ክብር እና ሞገስ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ እንደገና እንደሚቀዳጁ ምንም ዓይነት ጥርጥር የለኝም፡፡

ኢትዮጵያውያን/ት በክልል አገዛዝ እንደ ደቡብ አፍሪካውያን የአፓርታይድ የዘረኝነት አገዛዝ የዓለም የውርደት ቋት ውስጥ በፍጹም አትገባም፣ እናም ይህንን ከልብ በሆነ መልኩ አምናለሁ፡፡ ኢትዮጵያ እጆቿን በቅርብ ጊዜ ውሰጥ ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች፣ እናም በደስታ ምንም ዓይነት ጩኸት እና ጫጫታ ሳይኖር በደስታ እና በፈንጠዝያ እንኖራለን የሚል እምነት አለኝ!

የማየሳነው እና ዘላለማዊው አምላክ እግዚአብሔር በሊቢያ የወደቁትን የወንድሞቻችንን እና የልጆቻችንን ነብስ ይማርልን፣ በገነት ያኑርልን!

አላህ ምህረት ሰጭው እና መልካም አድራጊው ለእኛ ወንድሞች እና ልጆች ምንም ዓይነት ምህረት ላላደረጉት ወገኖች ምህረቱን እና ጽናቱን ስጣቸው!

ተከብረሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም
እናት ኢትዮጵያያ ያስደፈረሽ ይውደም!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ሚያዝያ 26 ቀን 2007 ዓ.ም

The post ኢትዮጵያ፡ የምንወድሽ ሀገራችን ደግመሽ አልቅሽ! appeared first on Zehabesha Amharic.

ፕሮፍ. መስፍን ወልደማርያም፡- አማራ የሌለው የት ሄዶ ነው?

$
0
0

ከመለክ ሐራ

እኔ ልናገረዎ የማይገባ ብላቴና ነኝ፡፡ በብዙ ነገር አድናቂዎ እና ብዙዎችን ጽሁፎችዎን ያነበብኩ ነኝ፡፡ አሁን ለያዝኩት ማንነትም የእርስዎ አስተዋጽኦ አለበት፡፡ ይሁንና በአማራ ጉዳይ ላይ ባለዎት አቋም ላይ ከረር ያለ ልዩነት አለኝ፡፡ ሰው መሆን አቅቶኝ እና የጎሰኝነት ስሜት አጥቅቶኝ ሳይሆን ይህ የለም እየተባለ መከራ የሚወርድበት ህዝብ ረፍት ስላጣና ዜግነቱን ስለተነጠቀ እንዲሁም አለሁልህ የሚለው ስላጣ አቅሜ በፈቀደው ሁሉ ልሟገትለት ራሴን ስላዘጋጀሁ እርስዎንም አሻቅቤ ለመናገር ተገድጃለሁ፡፡ ስለራሴ ስል የእርስዎ እምነትና ፍልስፍና ነው ያለኝ፡፡ ስለህዝቤ ስል ግን ከዚህ ሸሽቻለሁ፡፡ እንዳይቀየሙኝ፡፡

የክህደት ቁልቁልት በተባለው መጽሀፍዎ ምእራፍ 11 ላይ ያተቱት የአማራ አለመኖር

አማራ ማለት ሀይማኖት ነው ስላሉ በአለም ላይ ያሉ ትናንሽና ትላልቅ እምነቶች ውስጥ ዝርዝሩን ለማግኘት ብዙ ደክሜ ሳላገኘው ቀረሁ፡፡ አማራ ማለት ክርስቲያን ከሆነ አገው ለምን አማራ እንዳልተባለ እንዲያብራሩልኝ እጠይቃለሁ፡፡ ሁለቱም ቅዱስ ላሊበላ የምትሄዱ አልጋ ባልጋ ነው መንገዱ እያሉ ለዘመናት በአንድ የክርስትና ማእድ ሲሳተፉ ኖረዋል፡፡ አንዱ አገው አንዱ አማራ ሆነው፡፡ አማራው ታዲያ ለምን ሁለት የክርስትና ስም አስፈለገው–አማራ እና ክርስቲያን የሚል? ከተለያዩ ጸሀፍት እንደጠቃቀሱትም አማራ ማለት ነጻ የወጣ ህዝብ (ከአረማዊነት የተመለሰ) ማለት ነው፡፡ ታዲያ አገው ነጻ አልወጣም ማለት ነው? ትግሬ ነጻ አልወጣም ማለት ነው? ወይስ የተለያየ አይነት ክርስትና ነው ያለው–አንዱን ነጻ የሚያወጣ ሌውን ነጻ የማያወጣ? እንደገና በአማራ መሀል የሚኖሩት አርጎባዎች እስላም ናቸው፡፡ ከሌላው እስላም ተለይተው ለምንድን አርጎባ የሚል ስም የያዙት? እነሱ የአርጎባ ጎሳ እስላሞች ሲሆኑ ከአርጎባ ውጭ ያለው ምን ሊሆን ነው?
Pro Mesfin
የጠቀሷቸው ጸሀፍት ወደሀይማኖታቸው የሚያደሉ እንጅ ቁሳዊ ምሁራን እንዳልሆኑ እርስዎ ያውቃሉ፡፡ ከዛም የተነሳ ለእምነታቸው ያደላሉ፡፡ አማራ የሚለውንም የእምነታቸው ዘብ አደረጉት፡፡ ይሁንና አማራ ነጻ ህዝብ የሚለው ራሱ ከጠቀሷቸው ጽሁፎች መረዳት እንደሚቻለው ሀይማኖታዊ ይዘት ብቻ አይደለም ያለው፡፡ ሁለት አንድምታ ነው ያለው፡፡ ወደክርስትና የገባ እና ጦረኛ ሆኖ በነጻነት የሚኖር የሚል፡፡ እርስዎ ግን ጦረኛነቱን ሊያተኩሩበት አልፈለጉም፡፡ ለምን ቢባል ጦረኛነት ክርስትና ከሚለው ትርክትዎ ሊየስወጣዎ ስለሚችል፡፡ እንደሚታወቀው ሰው ወደክርስትና ሲገባ የጎሳ ጦረኝነቱ ይቀንሳል፡፡ እርስዎ የጠቀሷቸው ምንጮች የሚሉት ግን ጦረኛ የሆነና ራሱን ከሌላ ጎሳ ይሁን ከምንም ነገር አስከብሮ የሚኖር ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ ጥያቄው ታዲያ ይህ ህዝብ እርስዎ እንደጠቀሱት ከየነገዱ ጦረኛው ተሰብስቦ አማራ ተባለ ወይስ መጀመሪያውንም አማራ የተባለ ጦረኛ ነገድ ነበር የሚለው ነው፡፡ የእርስዎን ትርክት ብንቀበል እንኳ ቤተ አምሐራ የሚለው ነገር ያፈርሰዋል፡፡ ለምን ላስቴዎች ናቸው ይህን የተሰባሰበ ህዝብ አምሐራ ያሉት፡፡ እናም ይህንን አምሐራ ላስታ በቤተምንግስታቸው ዙሪያ አሰፈሩት ወይስ ራቅ አድርገው ቤተ አምሐራ የተባለ ቦታ ውስጥ ወስደው አሰፈሩት የሚለውን ጥያቄ በግድ መመለስ አለብዎት፡፡ ለምን ቢሉ ሁለቱ የሰማይና የምድር ያህል የሚራራቁ ተቃራኒ አስተሳሰቦች ስለሆኑ፡፡

ከአለቃ አስሜ የጠቀሱት “ያልተማረ ጨካኝ ጭፍራ” የሚለው አረፍተ ነገር መላ አማራን ክርስቲያን የማድረግ ክርክርዎን አፈር የሚያበላ ነው፡፡ ለምን ቢሉ ክርስቲያን ሆነ ማለት ጭካኔው አበቃ ማለት ነው፡፡ ክርስቲያን ሆነ ማለት ተማረ ማለት ነው፡፡ የዛ ጊዜ ትምህርት ሀይማኖትን ከማወቅ የዘለለ ሚና ስለሌለው በተለምዶ ክርስትያን ሆነ ማለት የተማረ ማለት ነው፡፡ የሚማረውም የክርስትና ስነምግባርን ነው፡፡ እርሱም ዋናው ትምህርት የአረማዊ ጸባይ የሆነውን ጭካኔን ማስወገድ ነው፡፡ እና እዚህ ላይ ራስዎን ተዋግተው ወድቀዋል፡፡

አንድ የትግርኛ መዝገበ ቃላት አምሐራ የሚለውን የኢትዮጵያ ህዝብ ብሎ ቅልብጭ አድርጎ አስቀመጠው ብለዋል፡፡ ይህ ደራሲ ከራሱ ያመነጨውን ሀሳብ ነው የጻፈው ወይስ ከሌላ ምንጭ ያገኘውን ነው ብለው መጠየቅ ነበረብዎት፡፡ ጸሀፊው እንዳለው አማራ ማለት የኢትዮጵያ ህዝብ ማለት ከሆነ ለምን የትግራይ ሰዎች አማራ አልተባሉም? ወይስ የትግራይ ሰዎች ኢትዮጵያዊ አይደሉም ማለቱ ነው? ቀጥለውም የንቡረ እድን አምሐራ ማለት ከየነገዱ ተሰበስቦ ክርስቲያን የሆነው የእግዚአብሔር ህዝብ እና ፍጹም ሙሉ አንድ አይነት ለሆነው ለኢትዮጵያ ዘር የተሰጠ የሚል የባህታዊ ሀተታ ተቀብለዋል፡፡ እንግዲህ አማራ ማለት የኢትዮጵያ ከእግዜር በጥምቀት የተሰጠ መለኮታዊ ዘር ሀነ ማለት ከባድ ነገር ነው፡፡ አንድ እርስዎ መኖሩን የሚያምኑትን ኦሮሞና ሌላውን ከጨዋታ ውጭ የሚደርግ ነው፡፡ ሲቀጥል ኢትዮጵያዊ ማለት ክርስቲያን ማለት ስለሆነ እስላሞች ኢትዮጵያዊ አይደሉም ማለት ሊሆን ነው፡፡ በዚህም ኢትዮጵያዊ ፍጹም አንድ ዘር የሚለው ሙግት ኢትዮጵያዊነት የማይመለከታቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ስለፈጠረ እዛው ላይ አፈር በላ ማት ነው፡፡ የሆነ ሆኖ አምሐራ ማለት ፍጹም ኢትዮጵያዊ ዘር የሚለው ራሱ ስለዘርና ጎሳ ያለዎትን አረዳድ ፈተና ላይ የሚጥል ነው፡፡ በዘርማ ከሄዱ ብዙ ጣጣ ሊመጣ ነው፡፡ የሰው ዘር ሁሉ አንድ ስለሆነ፡፡ ኢትዮጵያዊ ዘር የሚባል ራሱ የለም በዚህ መንገድማ፡፡ የአማራን አለማዊ ህልውና ለመጻፍ ተነስተው ስለሰማያዊ ህልውናው የሚያትቱ ጽሁፎችን ዋቢ ማድረግ በራሱ መልካም አይመስልም፡፡

ማተብ የሚል ሌላ ሃሳብም ተውሰዋል፡፡ ማተብ ማሰር ክርስትና ነው ከተባለ ማተብ ማሰር የተለየ ክስተትን ተከትሎ እንደመጣ መጠርጠር ያሻል፡፡ ከመጀመሪያው የክርስትና ደንብ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ክርስትናና አማራ ከማተብ ጋር ተያይዘው መገለጽ የጀመሩት ከማተቡ ክስተት በፊት ነው ወይስ በኋላ የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ይህ ጥያቄ ደግሞ ከማተብ በፊት ይህ ህዝብ ማን ይባል ነበር የሚል ሌላ ተቀጣይ ጥያቄ ይወልዳል፡፡ አማራ የለም ብሎ ለመደምደም ይህንን ሁሉ መመለስ ያስፈልጋል፡፡

ሌላው ትልቁ ስህተት አማራ ማለት ሰፊ ነው፤ ማጥበብ አያስፈልግም፤ ጎሳዎች ዝግ ናቸው፤ ማንም ሰው ወደነሱ ገብቶ የነሱን ማንነት ሊያገኝ አይችልም ያሉት ነው፡፡ ይህም ማለት አማራ ጎሳ ስላልሆነ ማንም ቋንቋውን የቻለና ባህሉን የተቀበለ አማራ መሆን ይችላል፡፡ በተጻራሪው ግን ጎሳዎች ዝግ ናቸው ብለዋል፡፡ ይተው እንጅ ፕሮፌሰር፡፡ መቸም ከአይሁድ በላይ ዝግ ነገድ ወይም ጎሳ እንደሌለ ያውቃሉ፡፡ ነገር ግን መጽሀፍ ቅዱስ ወደይሁዲነት የገባ እያለ የሚጠቅሳቸው አይሁዳዊያን ያልሆኑ ህዝቦች የትየለሌ ናቸው፡፡ በዚህ ብቻ ሳይሆን አማራ በደረሰበት የማህበረሰብ የእድገት ደረጃ ያሉ ነገዶች ወይም ጎሳዎች የእነሱን ባህል ለተቀበለ ሁሉ በራቸው ክፍት መሆኑ ያለና የነበረ ነው፡፡ እዚህ ላይ የአማራ ብቻ ተለይቶ እንደ ተአምር የሚቆጠርበት ምክንያት አይታየኝም፡፡

በምእራፍዎ መጨረሻ ላይ የአማራ ወደጎሳዊ ማንነት መለወጥ የወያኔ ሴራ እንደሆነ፤ አንዳንድ አማሮች እንዳስተጋቡት እና ኢትዮጵያዊነትን አደጋ ላይ የሚጥል ብለው ስጋትዎን አስቀምጠዋል፡፡ ጥሩ፡፡ ጎሰኛነት የአገር አንድነትን ይጎዳል፡፡ ከሰውነት ደረጃ መውረድ እንደሆነም አምናለሁ-አውቃለሁ፤ እቀበላሁ፡፡ ከዚህ ፍልስፍናዎ ጋር አንዳች ልዩነት አይኖረኝም፡፡ ይሁንና ሁሉም ወደየጎሳው ከረጢት ሲከት እያዩት፤ ሁሉም የራሱን የጎሳ ማንነት የሚቀርጸው አማራን ከመጥላት እንደሆነ እያወቁ፤ ኢትዮጵያዊነት በጎሳ ተመንዝሮ የሁሉም ጠላት በተባለ ነገር ግን እርስዎ የለም በሚሉት ጎሳ ላይ ቢላ እየሳለ፤ እያረደም እያዩ፤ ሽንጥዎን ገትረው አማራ የለም ማለትዎ ለማን አተርፍ ብለው ነው? እውን ይህ ህዝብ አውላላ ሜዳ ላይ የማንም ጥቃት ሰለባ መሆኑ እንዴት ሳይታይዎ ቀረ? አማራ ለኢትዮጵያዊነት ሲባል አፈር ደቸ ይብላ የሚል ፍልስፍና የሚያራምዱ ነው የሚመስሉት፡፡ ይህ ማለት ደግሞ አማራ የሚጠፋባት ኢትዮጵያ ለሌሎች ጎሳዎች አገር እንድትሆን አንጅ ለአማራ እንዳትበጀው ያውቃሉ፡፡ እና ጠፍቶ በጥፋቱ ላይ አገር የሚገነባበት እንዴት ያለ ህዝብ ነው? እና በጠቅላላው በዚህ ጽሁፍዎ አማራን አንዴ ከሀይማኖት፤ ሌላ ጊዜ ከዜግነት፤ አለፍ ሲልም ከጦረኝነት ሲቀጥልም ከኢትዮጵያዊነት ጋር እያምታቱ ጻፉ፡፡

የጠቀሷቸው ጽሁፎች ሁሉ ሀይማኖታዊ ይዘት ያላቸውና በይሆናል የተባሉ፤ ሀቅነት የጎደለቻው የግልሰብ አስተያዮቶች ናቸው፡፡ የእምነት ሰዎችን መጥቀስ ተገቢ ቢሆን እንኳ እርስዎ ከጠቀሷቸው በእጅጉ የሚልቀውን የነገረ ሀይማኖት አዋቂ ፈላስፋ ዘርአ ያዕቆብን ይጠቅሱ ነበር፡፡ ከአራት መቶ አመታት በፊት ጀምሮ የኖረው ይህ ሰው ከአክሱም ወጥቶ ተከዜን ተሻሯል፡፡ ከተከዜ ተሻግሮም የኖረባቸውን ሰዎች “የአማራ ሰዎች” እያለ ነበር የጠቀሳቸው፡፡ ከዚህ ሰው የሀይማኖት እውቀት አንጻር እና ከጊዜውም ርቀት ዋጋ የተነሳ የእርሱን ዘገባ መቀበል የግድ ነው፡፡

በጣም የሚገርመው ነገር እዚሁ ጽሁፍ ላይ አንድ የጎጃም ሰው እንዲህ አለኝ ብለው የዛን ሰው ቃል እንደመደምደሚያ ተጠቀሙበት፡፡ ከዛም የወሎ ሰፋሪዎች ብለው አከሉበት፡፡ በእውነቱ ይህ ትልቅ ጉድለት ነው፡፡ አንድ ሳይንሳዊ ጥናት ቢያንስ መረጃው ሞልቶ ድግግሞሽ ደረጃ ላይ እስኪደርስ ድረስ አዋቂ ሰዎችን እየፈለገ ማናገር እንዳለበት ያሰምርበታል፡፡ መጀሪያ ብዙ አዋቂ ሰዎችን አፈላልጎ ማግኘት፤ እነሱን በተለያየ አንግል እያመሳከሩ መጠየቅ፤ የታሪክ ድርሳናትን ማገላበጥ፤ እና ያንን የተገኘውን መረጃ በጥንቃቄ አመሳክሮ መተርጎም፤ መተንተንና ድመዳሜ ላይ የሚደርስ ነገር ከሆነ መደምደም ካልሆነ ግን ጥያቀውን ለሌላ ሰው ክፍት አድርጎ መተው የሚሉት ናቸው ዋነኛ ሳይንሳዊ የጥናት ሂደቶች፡፡ እርስዎ ግን ከቃለ ምልልሱም ሆነ ከጽሁፍዎ እንደተረዳሁት ወደጥናት የገቡት መጀመሪያ ደምድመው ነው የሚመስለው፡፡ የለም ብሎ ድምዳሜ ለመድረስ ብዙ ድካም የሚጠይቅ ነው፡፡ የለም የሚል ውጤት ላይ ቢደርሱ እንኳ ከእርስዎ የተለዩ በርካታ አጥኝዎች እስኪያረጋግጡት እና ተመሳሳይ ግኝት ላይ እስኪደርሱ ከመናገር መቆጠብ ተገቢ ነበር፡፡ ምናልባት እንደደንቡ ይመስለኛል ቢሉ ትንሽ የሚመስል ነገር ይሆን ነበር፡፡ ግን ከስሁት ዘዴ ተነስተው የደረሱበት ስሁት ድምዳሜ ነው፡፡

እርስዎ መቸም የአማራ ጉዳየይ ምሁር አይደሉም፡፡ ብዙ ጽሁፎችዎን እንዳነበብኩት ፖለቲከኛ ነዎት፡፡ የፖለቲካ ፍልስፍናወ ደግሞ ሁለንተናዊ ሰውነት ዝቅ ሲልም አንድ ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ ይህ በራሱ ክፋት የለውም፡፡ ችግሩ በዚህ ሚዛን እየለኩ አማራን አለና የለም ማለትዎ ነው፡፡ እንደኔ እይታ የእርስዎ አማራ የለም ድምዳሜ ተቀባይነት ያገኘው በአማራ ላይ ባደረጉት ልዩና ረጅም ጊዜ የወሰደ ምርምር ሳይሆን በሌላው ዘርፍ ባለዎት እውቅናና ተሰሚነት ተጠቅመው ነው፡፡ በእርስዎ የስም ክብደት ነው አማራ የለም የሚለውን አስተሳሰብ ማስረጽ የቻሉት፡፡ ዋናው ቁም ነገር የእርስዎ አለና የለም የሚል ድምዳሜ አልነበረም፡፡ ግን እርስዎ ትልቅ ስም ስላሎዎት አማራን ለመካድና ለመጉዳት ለሚደረገው ርብርቦሸ የእርስዎ ቃል በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠቀሰ ጥቅም ላይ መዋሉ ነው፡፡ ይህም አማራ የለም የሚለው ትርክትዎ በአንድ ወገን አማራው በአማራ ዙሪያ መሰባሰብን እንደነውር እንዲቆጥር አደረገ፡፡ በሌላ ወገን አማራ አለ በማለት ጉዳት የሚያደርሱብት ቡድኖችና ድርጂቶች የእርስዎን ቃል እንደ ይለፍ ይጠቀሙበታል፡፡ አማርኛ ተናጋሪ በሚል ድንግርግርም የሚናገርለትና ብሶቱን የሚረዳለት አጣ፡፡ የእርስዎ ሀሳብ ተከታይ የሆኑትም ለአማራ መመቻ እንጅ መመከቻ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ ወያኔ በእነርሱ ንዴት አማራን ይመታል፡፡ እነሱ ግን አማራ የለም የሚሉ ናቸውና ይህ አማራ ላይ የሚያርፍ ዱላ የማይሰማቸው ሆነ፡፡

ከመአዛ ብሩ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ

እንደተለመደው ሁሉ በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ አማራ የለም አሉ፡፡ ደመደሙ፡፡ በጣም የሚገርመው ጥናት አጥንተው ነው የደመደሙት–እንደተናገሩት፡፡ ግን የጥናትዎ ውጤት ስለ አማራ ህልውና ሳይሆን ስለኢትዮጵያ ህልውና መሰለኝ፡፡ እንዳሉት ያገኙት ገኝት ሶስት ሀይሎች አሉ፡-እነርሱም አካባቢ፡ ሀይማኖት እና ቋንቋ ናቸው፡፡ አንዱ ሲላላ እንዱ እየወጠረ ኢትዮጵያን ጠብቆ ኖረ ነው፡፡ እግዜር ይይልዎትና ይሄ ከአማራ መኖርና አለመኖር ጋር እንዴት እንደሚገናኝ አላውቅልወትም፡፡ አማራ የሚባል ነገር የለም አሉ፡፡ ከማስረጃዎችዎ አንዱ ወሎና ጎንደር፡ ወሎና ጎጃም ምን ያገናኛቸዋል ነው፡፡ ሁለተኛው ሀረር ውስጥ አማራ የሚባሉት ክርስቲያኖች ናቸው ነው፡፡ ሶስተኛው ጎንደር ውስጥ የእስላም መንደር ምናምን የሚባል አይቻለሁ ነው፡፡ አንድ በአንድ እንያቸው፡፡

ወሎና ጎንደር እንዲሁም ወሎና ጎጃም ምን ዝምድና አላቸው ሲሉ የምርዎትን ነው? አንድ ኢትዮጵያ አንድ ነው ብለዋል እዛው ቃለ መጠይቅ ላይ፡፡ ሰው አሁንም እየተጋባ እየተዋለደ ነውና አንድ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ አንድ ሆና ሳለ እንዴት ጎጃምና ወሎ፡ ወሎና ጎንደር ዝምድና ሳይኖራቸው ቀረ? በጣም ያስተዛዝባል፡፡ እዚህ ላይ ከቃልዎ ባሻገር የንግግርዎ ድምጸት ራሱ የሚናገረው አሉታዊ ነገር አለ፡፡ በሞቴ ዝምድና ስንት አይነት ነው በመጀመሪያ? በየትኛውስ የዝምድና መስፈርት እነዚህ ህዝቦች ሳይዛመዱ ቀሩ? ሀቁ ይህ አይደለም፡፡ ምናልባት ወሎ ውስጥ የአገውና የኦሮሞ መኖር ይሆን አማራ የለም ያስባለዎት? እንደዛ ከሆነ ደግሞ ሁለት አካባቢዎች ብቻ ናቸው ድብልቅ ማንነት ያላቸው፡፡

ንግግርዎ የሳይንስ ጉዳይ ቢሆን ኖሮ እውነታው እንዲህ ነበር መቀመጥ የነበረበት፡-“ወሎ ውስጥ ውስን አካባቢዎች ድብልቅ ቋንቋና የዘር ሀረግ ያላቸው አካባቢዎች አሉ፤ የተቀረው ግን አማራ ነው፡፡” እውን እርስዎ እንደሚሉት የሁለቱ አካባቢዎች ህዝብ ቁጥር ከአማራው በልጦ አማራ የለም የሚያሰኝ አልነበረም፡፡ የዘነጉት ነገር ወሎም ሆነ ጎንደር ወይም ሸዋ ወይም ጎጃም ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ብሄረሰቦች በጣም አንድ አይነቱ ነው፡፡ ምናልባት አካባቢያዊ ዘይቤዎችና ልማዶች ከመኖራቸው በቀር በዋና ዋና መስፈርቶች አማራ ከጫፍ እስከጫፍ አንድ ነው፡፡ በቋንቋ፡ በሙዚቃ፡ በስነቃልና በስነኪን፡ በመልክ፡ በባህርይ፡ በልማድ፡ በታሪክ፡ በመሬትና የአየር ንብረት ጸባይ፡ በምርትና አመራረት፡ በስነልቡና፡ በጠቅላላ እይታ-አለም (worldview): ለረጅም ዘመናት እንደአንድ የፖለቲካና ሚሊታሪ ማህበረሰብ መኖሩና በመሳሰሉት ዋና ዋና አሃዶች ልዩነት የለውም፡፡ እርስዎ ምኑን እንደሆነ አይዛመድም ያሉት ለሰሚው ግራ ነው፡፡ እስኪ በምን በምን አሃዶች የማይዛመድ ሆኖ እንዳገኙት ያስቡና ያብራሩ፡፡ ይሄ የለም ያሉት ዝምድናስ አብሮ መኖርን ሲከለክል፤ ጋብቻን ሲከለክል አዩት? በሀሳብ ተለያይተው ቁርቁስ ውስጥ ሲገቡ አዩ? በቋንቋ ሲለያዩና ሳይግባቡ ሲቀሩ አዩ? በባህርይና በተክለቁመና ሳይመሳሰሉ ሲቀሩ አዩ? እንዴው ምን ልዩነት አዩ?

እዚህ ላይ የእምነት ጉዳይ ጠቅሰዋል፡፡ የአንጾኪያ ሰዎች አማሮች አይባሉም፤ እስላሞች ናቸው የሚባሉት ብለዋል፡፡ እንዴ ፐሮፍ.? አንድ ህዝብ ሲጠራ እኮ ከአንጻራዊ ስፍራ ነው፡፡ ማለትም ለምሳሌ እርስዎ የአዲስ አበባ ሰው ነዎት፡፡ ከኢትዮጵያ አንጻር የጉምዝ ወይም የጋምቤላ ኢትዮጵያዊያንን አይመስሉም፡፡ መልክዎ ከወደ ሰሜን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ እርስዎን የሰሜን ሰው ነው የሚልዎት፡፡ ከቆሙበት ቦታ አንጻር ፈካ ያለ ገጽታ ያለው የሰሜን ሰው ነዎት፡፡ ወደ ዩጋንዳ ቢሄዱ አንድ ዩጋንዳዊ ኢትዮጵያዊ ብቻ ነው የሚልዎት፡፡ እርስዎ፡ ዶር. ነጋሶ ጊዳዳ እና ሽፈራው ሽጉጤ ጉምዝ ውስጥ ብትሄዱ ሶስታችሁም አማራ ናችሁ፡፡ ደቡብ ኦሞ ውስጥ ብተሄዱ ሁላችሁም አማራ ናችሁ፡፡ ሱማሌ ብትሄዱ ሁላችሁም አማራ ናችሁ፡፡ አፋርም ብትሄዱም እንደዛው ነው፡፡ እና የአንጾኪያ ሰዎች እስላም ናቸው መባሉ ምንድን ነው ግርታው? ሁሉም አማሮች ስለሆኑ እስላም አማራና ክርስቲያን አማራ ናቸው፡፡ ነገር ግን በዚህ አይጠራሩበትም፡፡ ምክንያቱም አማራ ዋናው ማንነት ስለሆነ በዛ መጠራራት አይቻልም፡፡ ክርስቲያኖቹ በተለምዶ አማራ ነን ይላሉ፡፡ ያ ማለት ግን እስላሞቹ አማራ አይደሉም ማለት አይደለም፡፡ ምናልባት ከግራኝ ጦርነት ጋር ተያይዞ የሰለሙትን አማሮች ከአማራነት ወጡ የማለት አዝማሚያ የያዘ አጠራር ሊሆን ይችላል፡፡ ታዲያ አማራ ማለት ክርስቲያን ማለት ከሆነ እስላም ማለት ምን ሊሆን ነው? ነው ወይስ ክርስቲያን እና እስላም የሚባሉ ብሄረሰቦች ናቸው ሊሉ ፈልገው ነው? አማራ አማርኛ ቋንቋ የሚናገር ህዝብ ነው ብለው ስለሚምኑ እንደዛ ካሰቡ እንኳ እነዚህ የገጠር መንደሮች ዋና ከተማ ሆነው አያውቁምና እንዴት ሆነው ከማን ር ተቀላለቀሉ? እንደሚታወቀው የአንጾኪያና አካባቢው ህዝብ ለዘመናት ራሱን ከአጎራባች ብሄረሰቦች ወረራ ሲከላከል የኖረ ነው፡፡ ይህም ድብልቅነቱን እና የቋንቋ ብቻ ማንነቱን የሚያመለከት ሳይሆን ወጥነቱን ነው የሚያመለክተው፡፡

እሽ የሸዋን አማራ አለመሆን ለማረጋገጥ የአንጾኪያ ቀበሌ እስላም መባል በቂ ሆነልዎት፡፡ ምናለበት መላውን ሸዋ ወስደው አንጾኪያን ቢለኳት፡፡ ቢባል ቢባል እንኳ የአንዲት ቀበሌ ህልውና ነው የአብዛኛውን አንድ ክፍለ ሀገር ህዝብ አለመኖር ለማረጋገጥ መዋል ያለበት ወይስ ናሙና መወሰድ የነበረበት ከትልቁ ነው፡፡ የሳይንሱ የአጠናን ዘዴ ግን ከአብዛኛውም ከአነስተኛውም ወካየይ ናሙና መውሰድ እንደሚገባ ነው፡፡ ከመቶው የመላው ሸዋ አስር ድምጽ ቢወስዱ፡ ከአስሩ አንጾኪያ አንድ ይወስዳሉ ማለት ነው፡፡ ይህ የሳይንሱ ህግ ነው፡፡ በሁለተኛ ይሄም አላስኬድ ሲልዎት ወደሀረር ሄዱ፡፡ የወሎና ጎንደርን፡ የወሎና ጎጃምን አለመዛመድ ለማስረዳት ሀረር ሄዱ፡፡ ይሄን ጎንደር ሊሄዱ ጠዳ ተሸኙ እንለዋለን፡፡ ሀረር ውስጥ ያሉት ድብልቆች ናቸው፡፡ ስለዚህ ሁሉንም አማራ ከማለት ምናልባት ክርስቲያኖች ብሎ መጥራት ተገቢ ሆኖ ይሆናል፡፡ አማራው በታሪክ አጋጣሚ ባህሉ የሁሉም ስለሆነ የአማራውን ዋነኛ መገለጫ ክርስትና ቢሰጡአቸው ምኑ ያስገርማል? ደግሞስ የዚህ አካባቢ ልዩ ተጨባጭ ሁኔታ እንጅ የወሎ፡ ጎንደርና ጎጃምን አማራ አለመሆን እንዴት ብሎ ለማረጋገጫ ይቀርባል? ሌላው ክፍተት ደግሞ ከአንድ ወገን ብቻ የሚሰበሰብ መረጃ ተአማኒ አይደለም፡፡ ክርስቲያኖቹ እነዛ እስላሞች ናቸው አሉ ብለዋል፡፡ በጀ፡፡ እስላሞቹስ ራሳቸውን ምን ብለው እንደሚረዱና ምን ብለው እንደሚጠሩ ጠይቀዋል? ክርስቲያኖች አማሮችን ምን ብለው እንደሚጠሯቸውስ መጠየቅ አልነበረብዎትም? በእርግጥ ከሁለቱም ወገን መረጃ መሰብሰብ ነበረብዎት፡፡ የሁለቱንም ወገን እርስዎ እንደሶስተኛ ወገን ሆነው ተርጉመውና አጣጥመው መደምደም ነበረብዎት፡፡ ግን መረጃዎ ሚዛናዊ ስላልሆነ ድምዳሜዎም ሚዛናዊ አይደለም፡፡ ስለዚህ የተናገሩት ነገር አይረባም፡፡ ለምን ቢሉ የጥናቱ ዘዴ ካልረባ መደምደሚያውም አይረባም፡፡

ሶስተኛው ደግሞ የአማራ አለመኖርን ያረጋገጡበት መንገድ በጣም የሚገርም ነው፡፡ ጎንደር ውስጥ የእስላም መንደር ምናን የሚባል አይቻለሁ አሉ፡፡ ምነው ፕሮፍ. ምናምን አይቸ ተብሎ የህዝብን ህልውና የሚመለከት ከባድ ነገር ድምዳሜ ላይ ይደረሳል እንዴ? የጤና አልመሰለኝም፡፡ የእስላም መንደር ምናምን የሚባል አይቸ አማራ አለመኖሩን አረጋገጥኩ ብለው መናገርዎ በእውነቱ ለትልቅነትዎ የሚመጥን አይደለም፡፡ እውነቱ ጎንደር ዋና ከተማ በነበረች ጊዜ አከፋፈልዋ እንዲህ ነበር፡- ሸዋ ሜዳ–የሸዋ ሰዎች የሚያርፉበት፤ ትግሬ መጮሂያ–የትግሬ ሰዎች የሚያርፉበት፤ እስላምጌ–እስላሞች የሚኖሩበት፤ አዲስጌ–ፈላሾች የሚኖሩበት፤ ወለቃ–ፈላሾች የሚኖሩበት፤ አቡን ቤት–የካህናት አካባቢ፤ መሀል ላይ የነገስታቱ መቀመጫ ወዘተርፈ ተብላ የተከፋፈለች ነበረች፡፡ ከዚህ ሁሉ የአሰፋፈር ስምሪት የእስላም መንደር መኖሩ ብቻውን የአማራን አለመኖር ማረጋገጫ ሆነልዎት፡፡ ይህ በእውነቱ ያሳዝናል፡፡ ሀይማኖት ራሱ የነገድ ወይም ጎሳ መለኪያ ሆኖ አያውቅም–በጭራሽ፡፡ በእርስዎ አረዳድ እስላም ስላልሆኑ ብቻ የአሌክሳንድሪያ ግብጾች ግብጻዊያን አይደሉም ማለት ነው፡፡ ካቶሊክ ኖርዲኮች ፕሮቴስታትንት ስላልሆኑ ኖርዲክ አይደሉም ማለት ነው፡፡ ብዙም መጥቀስ ይቻላል፡፡ ግን ነገር ያረዝማል፡፡

በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ ሁለት ጊዜ ስሜት የሚለውን ቃል አነሱ፡፡ አንዱ አማራ የሚባል አንድ አይነት ስሜት ያለው ህዝብ የለም ብሏል ብለው የዶናልድ ሌቪኒን ድምዳሜ ያለምንም ማንገራገር አምነው የተቀበሉበት ነው፡፡ ስሜት ብቻ ነው እንዴ የአንድ ህዝብ አንድነት መለኪያው? አንድ አይነት ስሜት የለውም ለማለት ስንት አይነት መለኪያዎች ተወስደው ነው እዚህ ድምዳሜ ላይ የተደረሰው? አንድ አይነት ስሜት ማለት ምን ማለት ነው? እንዴያው በሞቴ የአንድ እናትና አባት ልጆች እንኳ በስሜት ደረጃ አንድ አይነት ናቸው? በእርግጥ እርስዎ አማራ ላይ የፈለጉት የስሜትም ይሁን የምንም ነገር አንድነት በአንድ ሰው ብቻ የሚገኝ እንጅ በ35 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ የሚገኝ አይደለም፡፡ እርስዎ የፈለጉትን አይነት ስሜት ማግኘት የሚቻለው አንድ ሰው ላይ ብቻ ነው፡፡ ለዛውም የአንድ ሰው ስሜት ራሱ በየጊዜው ተለዋዋጭ ስለሆነ ረዘም ላለ ጊዜ ከተከታተሉት አንድ አይነት ስሜትና ባህርይ አይደለም ያለው፡፡

ሌላው ስሜት የሚለውን ቃል የተጠቀሙት አማራ አለመኖሩን ያረጋገጡት በስሜት አለመሆኑ ለማጤን ነው፡፡ እዚህ ላይ መክሽፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ በሚባለው መጽሀፍዎ የስሜትን ጠቀሜታ አትተዋል፡፡ ራስዎ እንደጻፉት ስቬን ሮቢንሰን የተባለው የኢትዮጵያ ታሪክ አዋቂ ነኝ የሚል ብለው የወረፉት የባህር ማዶ ዜጋ አለ፡፡ እርሱም አንድ ቀን ታሪክ ስትጽፍ ስሜትህ ይንጸባረቅበታል አይነት ነገር ተናገረዎ፡፡ እርስዎም እርሱ ስለኢትዮጵያ ሲጽፍ ስሜት የሌለው ኢትዮጵያዊ ስላልሆ፤ እርስዎ ግን የራስወን አገር ሲጽፉ ስሜት እንደሚኖርና ተገቢ እንደሆነ ጠቅሰው “ልኩን” ነገሩት፡፡ እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ችግሩ፡፡ ለኢትዮጵያ ሲሆን ስሜት አለዎት፡፡ ለአማራ ሲሆን ደግሞ ምንም ስሜት የለዎትም፡፡ ለኢትዮጵያ ስሜት ስላለዎ በስሜትም በእውቀትም ተከራከሩላት፡፡ ለአማራ ደግሞ ስሜት ስለሌለዎ “ከስሜት በጸዳ” ምክንያታዊነት ካዱት፡፡ አንዱን ፈረንጅ አማራ አንድ አይነት ስሜት የለም ሲል ለምን እና እንዴት ሳይሉ ተቀበሉ፡፡ ስለኢትዮጵያ ሲጽፍ አላግባብ ተይቧል ያሉትን ፈረንጅ ግን ቁም ስቅሉን አሳዩት፡፡ ከዚህ ተነስቸ እንዲህ እደመድማለሁ፡፡ አማራን ሲክዱት የኖሩት ለአማራ ስሜት ስለሌለዎ ነው፡፡ ለአማራ ስሜት እንዳይኖረዎ ያደረገ ደግሞ አንዳች ነገር አለ፡፡ በስሜት ስለማይጋሩት ህዝብ መጻፍዎ ታዲያ የማይመለከተዎትን ነገር ልወክል ማለት አስመሰለብዎ፡፡ ሲጀመር ይህን አታጥና ይሄን አጥና ተብሎ ሰው ገደብ አይጣልበትም፡፡ አማራን ማጥናት መብትዎ ነበር፡፡ ግን በወጉ አላጠኑትም፡፡ ቢያጠኑ እንኳ ለህዝቡ ያለዎ የስሜት ቀረቤታ የጥናትዎ ውጤት ላይ ያጠላበታል፡፡ እዚህ ላይ የእርስዎ ቦታ በ19ኛው መቶ ክፍለዘመን ለቅኝ ገዥዎች የማህበረሰቡን ባህልና ስነልቡና እያጠኑ የሚሰጡ ጸሀፍትን ይመስላል፡፡

እዚሁ ቃለ ምልልስ ላይ በኦሮሞ ዘር ቋንቋ ነው፤ በወለጋ ዘር ቋንቋ አይደለም አሉ፡፡ ይህ ማለት ኦሮሞ ማለት ኦሮምኛ የሚናገር፤ ቋንቋውን እንደዘር ማንነት መገለጫ የሚጠቀም ማለት ነው የሚል ይዘት ያለው ነው–እንደተረዳሁት፡፡ በዚህ አረዳድ በእርግጥ ለአማራ ቋንቋ ማለት አማርኛ ማለት አይደለም፡፡ ለአማራ አማራ ማለት አማራ ብቻ ነው፡፡ ለምን ቢባል አማርኛን አማራ ያልሆኑ ሌሎችም ስለሚገሩት ቋንቋው የአማራነቱ መገለጫ ሊሆን አይችልም፡፡ ምናልባት አማራነቱ የሚታወቀው በቋንቋው ቢሆን እንኳ አማራ ብቻ የሚናገራቸው አካባቢያዊ የአማርኛ ዘይቤዎች ነው የሚሆነው፡፡ እዚህ ላይ ነው እግዲህ የእርስዎ “አማርኛ ተናጋሪ” እና የእኛ አማራነት ልዩነቱ፡፡ አማራ ያልሆኑ አማርኛ ተናጋሪዎችም ስላሉ አማራው ራሱን በቋንቋው ተመስርቶ ትርጉም ሊሰጥ አይችልም፡፡ ልክ አሜሪካዊያን እንግሊዝኛ በመናገራቸው ብቻ የኢንግላንድ ተወላጆች ሊሆኑ እንደማይችሉት ሁሉ፡፡

እና ቃለ ምልልሱ ላይ እንደተረዳሁት ሀረር የተገደሉት አማሮች ሳይሆኑ የሰላሌ ኦሮሞዎች ናቸው አሉ፡፡ አማራ አለመሆናቸውን እንዴት አወቁ ታዲያ? አማራ ከሌለ ሀረር የተገደሉት እንዴት ሆነው ነው አማራ ያልሆኑት? ምናልባት ኦነግ እነዛን ሰዎች ሲገድል የሸዋ ኦሮሞ ኦሮሞ አይደለም ብሎ ነው የገደላቸው ወይስ አማራና ኦሮሞ መለየት አቅቶት ነው? እዚሁም ላይ የሰላሌን ሰው ኦሮሞነት ሳያቅማሙ ተቀብለው ሲያበቁ አማራን ግን አማራ ለማለት ተናነቀዎት፡፡ እዚህ ላይ የኢሰመጉ መሪ ስለነበሩ አማራ አይደሉም የተገደሉት አልኩ አይነት ነገር ብለዋል፡፡ ምናልባት እዚህ ላይ ሀጢአት ሰርተዋል ብየ አስባለሁ፡፡ በወቅቱ አማራ እየተገደለ ነው ብለው ተናግረው ቢሆን ኖሮ ከዛ ወዲህ እስካሁን የሚገደሉት አማሮች ቁጥር ይቀንስ ነበር ብሎ ማሰብ ይቻላል፡፡ በቀጥታ አማራ ተገደለ ብለው ቢሆን ኖሮ አገዛዙም ከዛ ወዲህ የሌላውን አማራ ተቃውሞ በመገንዘብ ጠበቃ ሊያደርግ ይችል ነበር ብየ አስባለሁ፡፡ ግን የኢሰመጉ ሀላፊ ሆነው የተገደለው አማራ አይደለም ማለትዎ መቸም አሉታዊ ተጽእኖ አልፈጠረም ብሎ ማሰብ አይቻልም፡፡ ኦሮሞ የሆነው ኦነግ አማራ ብሎ ገደላቸው፡፡ እርስዎ ደግሞ አማራ አይደሉም አሉ፡፡ በግርግሩ ምናልባት ከለላ ሊሆናቸው የነበረ አካል ከነበር እጅና እግሩን አሰሩት ብየ እገምታለሁ፡፡ ለኦሮሞ የሚታገል ኦነግ አማራና ኦሮሞ መለየት አቅቶት ኦሮሞ ገደለ ማለትዎ መቸም ማንን እደሚያሳምን አላውቅም፡፡ ኢሳት ላይ የቀረበ የአንድ ከዛ ፍጅት የተረፈ መነኩሴ ቃለመጠይቅ አለልዎት እና ይዩት፡፡ ያ መነኩሴ ስለማን እንደሚያወራ እና እርሱም ማን እንደሆነ እርስዎ በደምሳሳው ከሚክዱት የበለጠ ተአማኒነት አለው፡፡ ከእርስዎ ይልቅ ትክክለኛውን የታሪክ ተሳታፊ ለማመን እገደዳለሁ፡፡

እንደ መደምደሚያ

አንድ ህዝብ ጎሳ የሚሆነው በውስጣዊ እምነቱና ስሜቱ ብቻ አይደለም፡፡ የውጫዊ ግፊቶችም አንድን ህዝብ ቅርጽ የመስጠት አቅም አላቸው፡፡ በዚህ አንግል ካዩት አማራ ከኦሮሞ መስፈፋፋት ጋር ሲፋሎም የኖረ ነው፡፡ ይህም ውጫዊ ግፊት የውስጥ አንድነት እንዲፈጥር አስገድዶታል ማለት፡፡ ይህንን ውጫዊ ገግፊት የተከሰተበትን ጊዜ ብንወስድ እንኳ አራት መቶ አመት ይሆነዋል፡፡ አንድን ጎሳ ለመፍጠር ደግሞ ይህ ክስተት ብቻውን ከበቂ በላይ ነው፡፡ ችግሩ ብዙዎች ስለአማራ ሲናገሩ ከአለም ህዝብ በተለየ ሁኔታ አማራ እስከ አዳምና ሄዋን የደም ሀረግ እንዲመዝ መፈለጋቸው ነው፡፡ ይህ ግን አንድን ጎሳ ሊፈጥሩ የሚችሉት ሁለት አመክንዮዎችን የጣሰ ነው፡፡ አንዱ እኔ በደሜ አማራ ነኝ ብሎ ማመን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የጠቀስኩት ውጫዊ ግፊትና ይህንን ግፊት ተከትሎ የሚመጣው ፖለቲካዊ ቅርጽ ነው፡፡ አማራ በትውልድም አማራነቱን ያምናል፡፡ እርስዎ አዲስ አበባ በመወለድና ማደግዎ ብዙ የማያውቁት ነገር እንዳለ እገነዘባለሁ፡፡ እኔ ደግሞ ከመሀሉ ስለተወለድኩ አውቀዋለሁ፡፡ አማራ ሲጋባ እስከሰባት ቤት ይቆጥራል–ወደኋላ፡፡ ወደጎን ደግሞ “አጥንተ ሰባራ” እና “ጨዋ” የሚሉትን የማንነት መገለጫዎች ያጣራል፡፡ የዚህ እሳቤ ጥንካሬው እርስዎ ከሚገምቱት በላይ ነው፡፡ ዝርዝሩን አልናገረውም፡፡ ካወቁት ያውቁታል፤ ካላወቁትም ሩቅ ነዎት ማለት ነው፡፡ ወሎ፤ ጎጃም፤ሸዋ፤ ጎንደር ዝምድና የላቸውም ያሉት ትርክት በጣም የማይረባ ነው፡፡ ለዘመናት ሲደጋገሙ የኖሩ የወታደራዊ፤ የንግስና ሽኩቻና መሳፍንታዊ ዝውውሮች ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው፡፡ ሁሉም የአማራ ክፍለ ሀገሮች ተራ በተራ አንዱ አንዱን ሲወረው፤ አንዱ አመጸኛ ሰራዊቱን ይዞ ወደሌላው ሲሸሽ፤ እና የመሳፍንቱም ጦር በየጊዜው ኡደታዊ ሰፈራ ሲያደርግ ነው የኖረው፡፡ ይህ ሁሉ ተደማምሮ አማራ ሊገለጽ የማይችል የእምነት፤ የባህርይ፤ የታሪካዊ ውርስ፤ የስነልቡና፤ የአኗኗር ዘዴ፤ የልማድ፤ የስነጥበብና ቋንቋ ወዘተርፈ አንድነት እንዲኖረው አስቻለ፡፡

በመጨረሻም አማራ የለም ባሉበት አንደበትና ብእርስ ምነው ትግሬ ወይም ኦሮሞ አለመኖሩን ሳይጽፉ ቀሩ? ምናልባት የአማራን አለመኖር ለማነጻጸር አጎራባች ጎሳዎችን መዳሰስ አልነበረብዎትም? በእርግጥ አማራ የለም የሚለው ትርክት ምን ጥቅም ያመጣል ብለው አስበው ነው? አሁንስ የጥናትዎን ዘዴ ደካማነት ለመፈተሸና ድምዳሜዎን እንደገና ለማየት ወኔው አለዎት ወይ?

The post ፕሮፍ. መስፍን ወልደማርያም፡- አማራ የሌለው የት ሄዶ ነው? appeared first on Zehabesha Amharic.

ችግሩን ሁሉ በአቶ ኃይለማርያም ላይ በማሳበብ በስልጣን መዝለቅ አይቻልም; የኢትዮጵያ የችግሮቿ ምንጭ እራሱ ኢህአዴግ/ወያኔ ነው

$
0
0

(ጉዳያችን) አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በፓርቲያቸው ሰዎች አንድ ቀን በፈጀ ግምገማ ክፉኛ መነቀፋቸውን እና እንባ እየተናነቃቸው ምላሽ መስጠታቸው እንዲሁም አቦይ ስብሃትን በተለይ ”ይጮሃል እንደ አሞራ ይዞረኛል” እስከማለት መድረሳቸውን ኢሳት ራድዮ እና ቴሌቭዥን ግንቦት 5/2007 ዓም ባሰራጨው ዘገባ ገልጧል።

ጎሳን መሰረት ያደረገ ፖሊሲውን፣በሙስና የታሹ የባለስልጣናቱን ነውር ሥራ እና የምጣኔ ሀብት ውድቀቱን ምክንያት ሁሉ በአቶ ኃይለማርያም ላይ አሳቦ ሕዝብን ማታለል አይችልም።አቶ ኃይለማርያም የአቅም ችግር እንዳለባቸው ዛሬ ነው እንዴ የታወቀው? አቶ ኃይለማርያምን ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት የመረጡት አቶ መለስስ አይደሉም እንዴ? የእዚህን ያህል የአቅም ችግር እንዳለባቸው እየታወቀ አቶ መለስ ለምን አቶ ኃይለማርያምን ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት መረጡ? መልሱ አቶ መለስ እራሳቸው የመምረጥ የአቅም ችግር ተጠቂ ነበሩ ወይንም እራሳቸው ጎልተው እንዲታዩ ሲሉ ሆን ብለው ከአቅም በታች የሆነ ሰው መርጠዋል የሚል ካልሆነ ሌላ ሊሆን አይችልም።
Pupet hailemariam
ኢህአዴግ/ወያኔ የአቶ ኃይለ ማርያምን ግምገማ በተለይ አሁን ለምን እንደ አዲስ ለመተረክ ፈለገ? መልሱ ቀላል ነው።ኢህአዲግ/ወያኔ ከገጠር እሰከ ከተማ ባለው ኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ከመቸውም ጊዜ በላይ ‘አይንህን ላፈር’ መባሉ ነው። በተለይ በሊብያ የወገኖቻችን መሰዋት እና እርሱን ተከትሎ በስርዓቱ የተወሰደው የቸልተኝነት ሂደት ይብሱን አዲሱን ትውልድ ሙሉ በሙሉ በኢህአዴግ/ወያኔ ተስፋ እንዲቆርጥ አደረገው። ለእዚህም ነው ከአስር አመታት ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ከፍተኛ ተቃውሞ በአዲስ አበባ ወጣቶች የተሰማው።ይህ የህዝብ ቁጣ ማየል ስጋት ላይ የጣለው ስርዓት ታድያ አንድ አይነት መውጫ ይፈልግ ገባ።ለመውጫው ብቸኛ መንገድ ያደረገው ”ለችግሮች ሁሉ ምክንያቱ ኢህአዴግ/ወያኔ ሳይሆን አቶ ኃይለ ማርያም ነው” የሚል ተረታ ተረት ይዞ ቀረበ።ምናልባት ከምርጫው በፊትም ኢህአዴግ ባደረገው ግምገማ አቶ ኃይለ ማርያም ከስልጣን ወረዱ የሚል ዜና በመልቀቅ የህዝብ ጆሮ በማቆም እና ቁጣውን ወደ ሌላ ትኩረት ለማዞር ይሞከር ይሆናል።ይህ ሁሉ ግን ከንቱ ሙከራ ከመሆን አያልፍም።

ኢህአዴግ/ወያኔስ እንደ ድርጅት አቶ ኃይለማርያምን ሊቀመንበሩ እንዲሆኑ ሲመርጥ ገና ድርጅቱ የአቅም ችግር ያጥለቀለቀው መሆኑን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሚስጥር አይደለም። ኢትዮጵያን በዕውር ድንብር ሲመራ የኖረው ድርጅት ዛሬ የሀገሪቱ ሀብት ተሟጦ ከሄደ በኃላ፣ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት እንደቀረበው ሪፖርት ከ11 ቢልዮን ዶላር (ከ200 ቢልዮን ብር) በላይ በሕገ ወጥ መንገድ ለማጣቷ፣ዜጎች በመላው ዓለም በተለይ በአረብ እና ጎረቤት ሃገራት እጅግ በተዋረደ መልክ ሕይወት መግፋት ለመጀመራቸው፣ኑሮ ውድነቱ ጣርያ ደርሶ ቤተሰብ የተባለ የሕብረተሰቡ አንዱ እና ዋናው አካል የፈረሰው፣ሙስና ቅጡን አጥቶ የሶስት ሺ ብር ደሞዝተኛ ባለስልጣን የአስር ሚልዮን ብር ቤት የሚሰራው፣ፍትህ መድረሻ አጥታ ዜጎች እንደ ከብት በእየእስር ቤቱ የሚታጎሩት እና ሌሎች ማለቅያ የሌላቸው የሀገሪቱ ችግሮች የተከሰቱት ድርጅቱ ኢህአዲግ/ወያኔ በአቅም ችግር የተወረረ በመሆኑ እና በሥርዓት አልበኛ ባለስልጣናት ስለሚዘወር መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠንቅቆ ያውቃል።አቶ ኃይለ ማርያም እራሳቸው የማን ውጤት ናቸው? አሁን በአስራ አንደኛው ሰዓት ላይ ቆማችሁ የኢትዮጵያን ሕዝብ አታታልሉትም።ባጭሩ ስልጣኑን ለሕዝብ መልቀቅ ከመሰለ ብቸኛ አማራጭ ሌላ ለኢህአዲግ/ወያኔ ወርቅ የሆነ መንገድ ፈፅሞ አይገኝም።

በሌላ በኩል ግን አቶ ኃይለ ማርያምም ወደ ስልጣን እንደ መጡ አንስተውት የነበረው የሙስና ጉዳይ ተዳፍኖ ለምን ቀረ? ብሎ የመጠየቅ መብት የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው።የሙስና ኮሚሽን ደብዛው እንዲጠፋ የተደረገው በህወሓት ባለስልጣናት አይደለም እንዴ? አቶ ኃይለ ማርያም ይህንን ሁሉ ጉዳይ የሚነግሩን ወቅት ይኖር ይሆናል አልያም እራሳቸው ጣፋጭ ቀምሼ ነው ብለው ግለ ሂስ አድርግ ተብለው ይገደዱ ይሆናል።አቶ ኃይለ ማርያም በቀረቻቸው ሁለት ሳምንታት ውስጥ ማድረግ የሚችሉት በሙስና የተዘፈቁ ባለስልጣናትን በሙሉ ለፍርድ ማቅረብ አንዱ መሆን ይችላል።ከቤተ መንግስት አትክልተኛ ጀምሮ በአንድ ጎሳ እና በሙስና የተዘፈቀ ስርዓት ውስጥ ይህንን ማድረግ እንደማይችሉ የታወቀ ነው።አቶ ኃይለ ማርያም የጦር ኃይሎች አዛዥ የሚል ማዕረግም ባለቤትም ናቸው ለካ!።እና ጦሩን ይዘዙት እንዴ? ማን ሰምቷቸው?

አንድ ሰሞን አቶ ኃይለ ማርያም ”ሙስና አጠፋለሁ” ብለው ጮክ ብለው በሚናገሩባቸው እነኛ ወርቃማ ወራት ውስጥ (የዛሬ ሁለት ዓመት) ዋናው ኦዲተር በሀገሪቱ ያለውን የመንግስት ባለስልጣናት የአንድ ዓመት ብቻ የሙስና ንቅዘት እንዲህ አስቀምጦት ነበር።

‘- 1.4 ቢሊዮን ብር ያልተወራረደ ሒሳብ አለ፡፡
– 313.6 ሚሊዮን ብር ዕዳ ሳይመልሱ የተሸጡ ድርጅቶች አሉ፡፡
– 897.5 ሚሊዮን ብር ሕጋዊ ያልሆነ ክፍያና ወጪ ተደርጓል፡፡
– ያልተወራረደው 1.4 ቢሊዮን ብር በ57 የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የታየ ነው፡፡
– 15 ድርጅቶች ወይም መሥሪያ ቤቶች ከልዩ ልዩ ገቢ ማስገኛ ምንጮች ገቢ የሚሰበስቡ ቢሆኑም፣ የገቢ ሪፖርት የማያደርጉ በመሆኑ ኦዲት ማድረግ አለተቻለም፡፡
– በ13 ናሙና መሥሪያ ቤቶች የተሟላ ማስረጃ ሳይቀርብ 132.364 ሚሊዮን ብር በወጪ ተመዝግቧል፡፡
– 22 መሥሪያ ቤቶች 13.8 ሚሊዮን ብር ማስረጃ የሌለው ወጪ አድርገዋል፡፡
– 30 መሥሪያ ቤቶች ደንብና መመርያ በመጣስ 353.568 ብር የሚያወጣ ግዥ ፈጽመዋል፡፡
– በውሎ አበልና በትርፍ ሰዓት ተመን 11 መሥሪያ ቤቶች 1.4 ሚሊዮን ብር አባክነዋል፡፡
– በኤርፖርት ተርሚናል የተሰማራ አንድ የግል ድርጅት ገንዘብ በውጭ ምንዛሪ ለመቀበል ፈቃድ ሳይኖረው ከአሥር ዓመታት በላይ እየሠራ እንደሚገኝና ተቆጣጣሪ አካላት ያደረጉት ምንም ነገር የለም፡፡
– 134.7 ሚሊዮን ብር ብድር ያልመለሱ የመንግሥት ድርጅቶች ሲኖሩ፣ የመንግሥት ትርፍ ድርሻ የሆነ 18.549 ሚሊዮን ብር ሳይከፍሉ የተሸጡ ድርጅቶች አሉ፡፡ 44.254 ሚሊዮን ብድር ያለባቸው ሲሸጡም የገዛው አካል ለመንግሥት መከፈል የነበረበትን ያልከፈለ መሆኑን ያስረዳ ነበር።

ይህ ሁሉ ተረሳና ዛሬ ሙሰኞቹ እራሳቸው አንድ አቅመ ቢስ ላይ ከበው አናት አናቱን ይሉ ገቡ።ባጭሩ የአቅም ማነስ ችግሩ የአቶ ኃይለ ማርያም ብቻ ሳይሆን የእራሱ ጎሳው ድርጅትም ጭምር ነው።ኢህአዲግ/ወያኔ ኢትዮጵያን የምታክል ታላቅ ሀገር የመምራት አቅም የለውም።ችግሩን ሁሉ በአቶ ኃይለማርያም ላይ በማሳበብ በስልጣን መዝለቅ አይቻልም።

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

The post ችግሩን ሁሉ በአቶ ኃይለማርያም ላይ በማሳበብ በስልጣን መዝለቅ አይቻልም; የኢትዮጵያ የችግሮቿ ምንጭ እራሱ ኢህአዴግ/ወያኔ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

“አይሲስን ስንቃወም ህወሓትን አለመርሳት”–አርበኞች ግንቦት 7

$
0
0

በአይሲስ በግፍ በታረዱብን ወገኖቻችን የተሰማን ሀዘንና ቁጭት ከፍተኛ ቢሆንም እንኳን ከአዕምሮዓችን መውጣት የሌለበት ሀቅ አለ። ይህ ሀቅ “ያስጠቃን፣ ያሳረደን ወያኔ ነው” ከሚለውም ያለፈ ነው። መረሳት የሌለበት ሀቅ፣ ከአይሲስ የከፋ ጨካኝ በአገራችን የመንግሥት ሥልጣን የተቆጣጠረ መሆኑ ነው።

የህወሓት ፋሽስት ጦር በበደኖ፣ በአዋሳ፣ በሀረር፣ በጋምቤላ፣ በጎንደር፣ በኦጋዴን፣ በአዲስ አበባ፣ በሸካና መዠንገር፤ እንዲሁም በሚታወቁም በማይታወቁም የማሰቃያ እስር ቤቶች አይሲስ እየፈፀመ ካለው የባሱ ወንጀሎች በወገኖቻችን ላይ ፈጽሟል፤ አሁንም እየፈፀመ ነው። ባሳለፍነው ሣምንት እንኳን በሁመራ ወገኖቻችን የራሳቸውን መቀበሪያ ጉድጓድ ቆፍረው በጅምላ ተገድለዋል። በአይሲስና በህወሓት መካከል ያለው ልዩነት አይሲስ ነውረኛና አረመኔዓዊ ተግባሩን በቪዲዮ እየቀረፀ ለዓለም ሲበትን ህወሓት ግን እነዚሁኑ ነውረኛና አረመኔዓዊ ተግባሮችን እየፈፀመ መረጃዎች አፍኖ መያዙ ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ግን ህወሓት ሰዎችን ከነሕይወታቸው ጉድጓድ ውስጥ የቀበረ አረመኔ፣ እኩይ ድርጅት ነው።
ስለሆነም ለዓለም ሰላም ስጋት የሆነውን አይሲስን ስንቃወም የራሳችንን አይሲስ – ህወሓትን – አለመርሳት እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው።
ginbot 7
በሌላ በኩል ደግሞ ህወሓት፣ የአይሲስን እኩይ ተግባራት ከኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጋር እና ከዲሞክራሲያዊያዊ ፓለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ጋር ለማገናኘት እያደረገ ያለው ጥረት ምን ያህል አደገኛ ተግባር እንደሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲረዳው ያስፈልጋል። ዓይን አውጣ ሌባ ንፁሁን ሰው “ሌባ” እንደሚለው ሁሉ የኛው አይሲስ ራሱን ንፁህ አስመስሎ ሌሎችን “አይሲስ” ማለቱ ሊነቃበት ይገባል።

ሌላው ተያያዥ ጉዳይ ደግሞ ስለስደተኝነት የሚሰጠው ገለፃ ነው። ህወሓት ለስደተኝነት ምክንያቱ ደላሎች እንደሆኑ ይናገራል። ይህ የጉዳዩን ግንድ ትቶ ቅርንጫፎች ላይ ማትኮር ነው። ህገወጥ ደላሎች ራሳቸው ሊኖሩ የቻሉት ገንዘብ ከፍለውና የሕይወት ሪስክ ወስደው ለመሰደድ የሚፈልጉ ዜጎች በመኖራቸው ነው። ችግሩን በቅንነት ለመመርመር የሚፈልግ “ይህን ያህል ሰው የሕይወት ሪስክ እየወሰደ ከአገር ለመሰደድ ምን አነሳሳው?” ብሎ መጠየቅ እና ምላሽ ማግኘት ይኖርበታል። በሀገር ውስጥ በነፃነት ተረጋግቶ መኖር፣ ሠርቶ የማደግ ተስፋ ቢኖር ኖሮ ይኸን ያህል ሰው የአደጋውን ከፍተኛነት እያየ ለመሰደድ ይነሳሳ ነበርን? ኢትዮጵያዊው ከስደት ሊያገኝ የሚሻው ምንድነው? እንደ ወያኔ ካድሬዎች ገለፃ ከሆነ ከስደት ሊያገኝ የሚችለው አገሩ ውስጥ እያለለት ነው ኢትዮጵያዊ የሚሰደደው። ይህ ምን ዓይነት አመክኖ ነው? ከዚህ የባሰው ደግሞ ስደትንም የእድገት ውጤት አድርጎ የማቅረብ በሽታ ነው። ይህ እውነት ከሆነ፤ ህወሓት ለኢትዮጵያ አመጣሁላት የሚለው እድገት ውጤት ረሀብ፣ ስደት፣ መርዶ፣ እስር፣ ስቃይ፣ ሞት ከሆነ እንዴት “እድገት” ብለን እንጠራዋለን። ለስደተኝነት መብዛት ህገወጥ ደላሎችን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ፤ “እኔ ከደሙ ንፁህ ነኝ” የማለት ያህል ነው። በህጋዊዎቹም በህገወጦቹም ደላሎች ውስጥ የወያኔ ሰዎች በቀጥታም በተዘዋዋሪም እንዳሉበት መረጃዎች ያመለክታሉ። ገንዘብ ባላበት ሁሉ የወያኔ እጅ መኖሩ ፀሐይ የሞቀው ሀቅ ነው። የሰዎች ዝውውር የህወሓት አንዱ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ መሆኑ የማይታበል፤ በቀላሉ ማረጋገጥ የሚቻል ሀቅ ነው።

አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ በዓለም አቀፉ አይሲስ አረመኔያዊ ተግባሮች በደረሰብን የመጠቃት ስሜት ተውጠን የራሳችንን አይሲስ – አረመኔውን ህወሓት – እንዳንረሳ ያሳስባል። መቆሚያው ለማይታየው የዜጎቻችን መሰደድ መንስኤዎች የነፃነት እጦት እና የኑሮ እድሎች መጥበብ መሆናቸው እንዳንዘነጋ ይጠይቃል። ንቅናቂያችን እነዚህ ተያያዥ ችግሮች ሁሉ የሚቃለሉት ህወሓትን አስወግደን በምትኩ ፍትህ፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሰፈኑባት ኢትዮጵያን ስንመሰረት ብቻ ነው ይላል። ለዚህም ደግሞ ሁላችንም በያለንበት የበኩላችንን ተሳትፎ ማድረግ ይገባናል። ሁለገብ ትግል ማለት፤ እያንዳንዱ ከሚመስለው ጋር እየተደራጀ በያለበት ወያኔ ማስጨነቅ፣ ማዋከብና ማዳከም፤ በመጨረሻም በጋራ ትግል ማስወገድ ማለት እንደሆነ ልብ እንበል። በሁለገብ ትግል ለውጥ የሚመጣው ሁሉም እንደ አቅሙ በሚያደርገው ተሳትፎ በመሆኑ፣ የሚቻለንን በማድረግ የለውጥ ጠባቂ ሳንሆን፣ የለውጥ አምጭ አካል እንሁን ይላል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

The post “አይሲስን ስንቃወም ህወሓትን አለመርሳት” – አርበኞች ግንቦት 7 appeared first on Zehabesha Amharic.


የዓረና_መድረክ የቅስቀሳ በራሪ ወረቀቶች በውቅሮ ተዘረፈ

$
0
0

Zehabesha News
አምዶም ገብረሥላሴ እንደዘገበው

የዓረና_መድረክ ኣማራጭ ፖሊሲዎች የታተመበት የውቅሮ ክልተ ኣውላዕሎ, ኣፅቢ ወንበርታ, ሓወዜን, ሳዕሲዕ ፃዕዳ እምባ ምርጫ ክልሎች ለህዝብ የሚታደል ከ12 ሺ በራሪ ወረቀቶች ባልታወቁ ሰዎች የኣቶ ቴድሮስ ሞገስ የኪራይ ቤት ቁልፍ በመስበር በጠራራ ፀሃይ ሊዘርፉት ችለዋል::

ዘረፋው የተፈፀመው በ04/ 09/ 2007 ዓ/ም ከቀኑ 9: 30 ሰዓት ሲሆን ኣቶ ቴድሮስ ከቤቱ ሲወጣ ወድያውኑ ነው:: የኣቶ ቴድሮስ የፓርቲ ኣባልነት መታወቅያ ሳይቀርና የተለያዩ የመድረክ ሰነዶችም ተዘርፈዋል::

የከተማዋ ካድሩዎች ለኣካራዩ ኣቶ ቴድሮስን ከቤቱ እንድያስወጣው በተደጋጋሚ ግዜ ከፍተኛ ማስፈራርያ ዛቻዎች ሲደርሱባቸው ነበር::
የከተማው ፖሊስ ስለ ወንጀሉ ኣብዮቱታ በቀረበበት ወቅት ጉዳዩ ለመመዝገብና ለማጣራት ከፍተኛ ዳተኝነት በማሳየት ጉዳዩ ተድበስብሶ እንዲቀር ያለው ፍላጎት ኣመላክተዋል::
ዝርፍያው የፖሊስ ወይም ድህንነት እጅ እንዳለው የሚያመላክቱ ነገሮች ለፖሊስ ኣሳውቀናል::

ጎበዝ ህወሓት የመድረክ በራሪ ወረቀት መዝረፍ ያልተወች የምርጫ ካርድ ትተዋለች ብላቹ ትጠብቃላቹ? ለነገሩ መስረቅ የለመደ ኣምባሻ ይልሳል ነው የሚባለው::
በተያያዘ ዜና በውቅሮ ክልተ ኣውላዕሎ ምርጫ ክልል የክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ የሆነው ኣቶ ሃይለኪሮስ ታፈረ በኣይናለም ቀበሌ ዓዲ ወረማ በተባለ የነበረ ገለባ በእሳት እንዲያያዝ በመደረጉ ሙሉ በሙሉ እንደወደመና ገለባው የተቀመጠበት ቤቶችም ወደ ኣመድ እንደተቀየሩ ታውቀዋል:: የእሳት መያያዝ ወንጀሉ በህወሓት ኣመራሮች የታዘዘና የተቀነባበረ ሴራ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው::

ህወሓት በዓረና_መድረክ ፓርቲና ኣባላቱ እያደረሰች ያለው ዓፈናዎች ለማመን የሚዳግቱ ናቸው::

The post የዓረና_መድረክ የቅስቀሳ በራሪ ወረቀቶች በውቅሮ ተዘረፈ appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: ለብሄራዊ ቡድናችን የቀድሞዎቹ የጊዮርጊስ ተጫዋች ፋሲል ተካልኝ ም/ል አሰልጣኝ; የቡናው አሊ ረዲ የበረኞች አሰልጣኝ ሆነው ተመረጡ

$
0
0

ali redi
የብሔራዊ ቡድኑ አዲሱ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በረዳት አሰልጣኝነት የቅ.ጊዮርጊሱን እና የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን ምክትል ፋሲል ተካልኝ እና ለግብ ጠባቂዎች የቀድሞ የኢትዮ ቡናውን አሊ ረዲ መርጠዋል ሲል ኢትዮ ኪክ ዘግበ:: ኢትዮ ኪክ ፌዴሬሽኑን ጠቅሶ እንደዘገበው የተመረጡት ረዳት አሰልጣኞች አስተዳደራዊ ጉዳዮችን እንደተጣናቀቁ ሰሞኑን የቅጥር ውሉ ስምምነት ከተፈፀመ በኃላ ስራ ይጀምራሉ ።

ይህ በ እንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለሌሴቶ ጨዋታ 44 ተጨዋቾች ተጠርተው ዝግጅት ሊጀምሩ ነው!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እ.ኤ.አ በ2017 ጋቦን ለምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ እና ለ2016 የቻን ሻምፒዮና የማጣሪያ ጨዋታዎችን ዝግጅት ለመጀመር ግንቦት 24 ሆቴል እንደሚገቡ የፌደሬሽኑ መረጃ ያመለክተል።
የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ፣ የኢ.እ.ፌ የስራ አስፈፃሚ አባላት እና የቡድን መሪ አቶ ዮሴፍ ተስፋዪ ሰብሳቢነት ዛሬ ስለ ብሔራዊ ቡድኑ ጠቅላላ ዝግጅት ዙሪያ ስብሰባ አድርገዋል።

በዛሬው ስብሰባ እንደተገለፀው በመጀመሪያው ዙር 44 ተጨዋቾች ግንቦት 24 ሆቴል እንዲገቡ ጥሪ የሚደረግ ሲሆን የነዚህ ተጨዋቾች ስም ዝርዝር ልምምዱ ከመጀመሩ አንድ ሳምንት በፊት ይፋ ከተደረገ በኃላ ዝግጅቱን ከጀመሩት ውስጥ 19 ተጨዋቾች ተቀንስው 25 ተጨዋቾች እና በውጭ አገር የሚገኙን 5 ተጨዋቾች ተካተው ለሌሴቶ ወሳኝ ጨዋታ ልምምዱ ዝግጅት እና የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚደረግ በዛሬው ስብሰባ ተልፇል።

The post Sport: ለብሄራዊ ቡድናችን የቀድሞዎቹ የጊዮርጊስ ተጫዋች ፋሲል ተካልኝ ም/ል አሰልጣኝ; የቡናው አሊ ረዲ የበረኞች አሰልጣኝ ሆነው ተመረጡ appeared first on Zehabesha Amharic.

መድረክ በጃንሜዳ የፊታችን ግንቦት 8 ሕዝባዊ ስብሰባ ጠራ (የፈቃዱን ወረቀት ይዘናል)

$
0
0

ከመድረክ የተላለፈ ጥሪ:-
መድረክ በአዲስ አበባ ከተማ ለግንቦት 8 ህጋዊ እውቅና ያገኘ ህዝባዊ ስብሰባ ጠራ፡፡ የውይይቱ ዓላማ የ2007 ምርጫ አስመልክቶ ከአዲስ አበባ ህዝብ ጋር ለመወያየት ነው፡፡ ህዝባዊ ውይይቲ ከጥዋቱ 3፡00 ጀምሮ እስከ ከቀኑ 8፡00 ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም መልእክቱ ለመላው ህብረተሰብ እንዲዳረስ እናድርግ…ውይይቱ የተሳካ እንዲሆን የበኩላችንን ሚና እንጫወት፡፡
mederek

The post መድረክ በጃንሜዳ የፊታችን ግንቦት 8 ሕዝባዊ ስብሰባ ጠራ (የፈቃዱን ወረቀት ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.

ምርጫ ለይስሙላ –አክሎግ ቢራራ (ዶር)

$
0
0

አክሎግ ቢራራ (ዶር)

electionበቅርቡ ኢትዮጵያዊያንን ብቻ ሳይሆን የዓለምን ሕዝብ በሚዘገንን ሁኔታ የቀሰቀሰው፤ ያስለቀሰውና ያስቆጣው የኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖች በሊቢያ በሚገኙ የአይሲስ ሽብርተኞች መታረድና በጥይት መርገፍ፤ ወደ አውሮፓ ሲጓዙ በጀልባ መሞት፤ በደቡብ አፍሪካ በሰላም ሲኖሩ በቤንዚን ተቃጥለው መሞት፤ በየመን የርስ በርስ ጦርነት በሳውዶዎች አየር ኃይል ተባራሪ ጥይት መሞት ወዘተ ብቻ አይደለም። በአወንታዊውም፤ የግብፅ መንግሥት ለሞት አደጋ የተዳረጉ ወገኖቻችን ከአደጋ ማትረፉ ሌላው ያልተጠበቀና የሚያበረታታ ዜና ነው። ኢትዮጵያዊያን በያሉበት ጎሳና ኃይማኖት፤ ሃብትና ሞያ፤ ጾታና እድሜ ሳይለዩ በሰብእነታቸውና በኢትዮጵያዊነታቸው ተባብረው ድምጻቸውን ማሰማታቸውም የሚያበረታታ ክስተት ነው። አሁንም ተባብረን ከጩኸት ወደ ድርጊት እንድንራመድ አሳስባለሁ።

የኢትዮጵያዊያን የስደት ኑሮ አስከፊ ገፅታ ዲሞክራሳዊ በሆነችው ኢስራኤልም ሲካሄድ ቆይቶ ሰላማዊ ሰልፍና ግጭት አስከትሏል። የኢስራኤል መንግሥት ለሌሎች ኢስራኤላዊያን የሚያደርገውን እንክብካቤና የዜግነት መብት ለኢትዮ-ኢስራኤላዊያንም በማያሻማ ደረጃ መስጠትና ሰብአዊ መብታቸውን ማስከበር አለበት። ኢትዮጵያዊያን ጥቁሮች በመሆናቸው ራሱ ጋብዞና አባብሎ ካመጣ በኋላ ልክ እንደ አፓርታይድ ደቡብ አፍሪካ ሁለተኛ ዜጋ ሊያደርጋቸው አይገባም። በሃገር ቤትም እንኑር በውጭ ተቃውሟችን በየቦታው ማሰማት ግዴታችን ነው። ይኼን በሚመለከት እኔንና ሌሎችን ተመልካቾች ያስገረመን የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በኢስራኤል የሚገኙ፤ የሃገሪቱ ዜግነት ያላቸውን ትውልዳቸው ኢትዮጵያ፤ ዜግነታቸው ኢስራኤሊ የሆኑ ወገኖቻችን አስመልክቶ ለኢስራኤል መንግሥት ያቅረበው “አቤቱታ” ነው። ለመሆኑ፤ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችን ያፈነውና ለስደተኛነት ዋና ተጠያቂ የሆነው ገዢው ፓርቲ ከመቸ ወዲህ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሰብአዊ መብት ጠበቃ ሆነ?

ኢትዮጵያዊያን በገፍ ከሃገራቸው የሚሰደዱበት ምክንያቶች ሶስት ናቸው። አንድ፤ ሰብአዊ፤ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መብቶቻቸው ሙሉ በሙሉ ስለታፈኑና መፈናፈኛና አቤቱታ የሚያቀርቡለት፤ ፍትህ የሚሰጥ፤ ከፖለቲካ ቁጥጥር ነጻ የሆነ የሚዳኝና ፍርድ የሚሰጥ ተቋም ስለሌላቸው ነው። ሁለት፤ የተማረ ሆነ ያልተማረ፤ የስራ ልምድ ያለው ሆነ ገና ልምድ የሌለው የስራ እድልና የግል ተቋም ለመመስረት ሁኔታው ጨለማ ስለሆነበት ነው። ሶስት፤ በአንዳንድ ክልሎች የርስ በርስ ግጭት፤ በዜግነት መብት ተማምኖ ለመኖርና ለመስራት አለመቻልና ሌሎች እርጋታ የሌለባቸው ሁኔታዎች እየተስፋፉ በመሄዳቸው ነው። ኢትዮጵያዊያን በገፍ ከሃገር ሲበረግጉ ምን አይነት የኢኮኖሚ መርህ አስበረገጋቸው ብሎ መመራመር አግባብ አለው። ሑሉን አሳታፊ፤ ሕዝብን ማእከል ያደረግና ለሕዝብ አገልጋይ የሆነ የእድገት መርህ ለአብዛኛው ሕዝብ እድል እንደሚከፍት የሌሎች ሃገሮች የእድገት ታሪክ ያስተምረናል።

ዛሬ ወጣት ሴትና ወንድ፤ ገጠሬና ከተሜ፤ መሃንዲስ፤ አውሮፕላን ነጅ፤ ሃኪም፤ መሃንዲስ፤ አስተማሪ፤ ኃብታም፤ ድሃ፤ የተለያዩ የኃይማንት መሪዎችና ተከታዮች፤ ኦሮሞ፤ አማራ፤ ትግሬ፤ ጉራጌ፤ ሶማሌ፤ ወላይታ፤ አኟክ ወዘተ ሳይለዩ በገፍ ይሰደዳሉ። ገዢው ፓርቲ ራሱ “የሰው ነጋዴ ነው”፤ የስራ እድል አለመኖርንና የፖለቲካ ተቃውሞን ችግሮች የሚፈታው በስደት ነው የሚሉ ታዛቢዎች ብዙ ናቸው። ከአራት መቶ በላይ ፈቃድ ተሰጥቷቸው ወገኖቻቸውን ለትርፍ የሚያስተናግዱ የሰው ነጋዴዎች (Human Traffickers) አሉ። ፈቃዱን የሰጠው መንግሥት መሆኑ ሊካድ አይችልም። ሊያቆመውም የሚችል መንግሥት ነው። አግባብ ያለው ጥያቄ ይኼን እንደ ዓባይ ወንዝ ጎርፍ የሆነ የሰው አስበርጋጊ ሁኔታ ምን አይነት የኢኮኖሚና የፖለቲካ ስርዓት ፈጠረው? የሚለው ነው። “የሃገር አንበሳ” የሆነው አገዛዝ ለዚህ ግዙፍ መበርገግ (Exodus) መልስ የለውም። የኢትዮጵያ ችግሮች ሊቀረፉ የሚችሉት በሁሉም የፖለቲካ፤ የማህበረሰብና የኃይማኖት ተከታዮች ተባባሪነትና ተሳታፊነት ብቻ ነው። መበርገጉን ያመጡት ተቃዋሚ ፓርቲዎች አይደሉም። እርጋታ እንዳይኖር ያደረጉት “በሕገ መንግሥቱ መሰረት እንወዳደር” የሚሉት፤ ወይንም በእስር ቤት የታጎሩት፤ ወይንም ከሃገር የተሰደዱት ኢትዮጵያዊያን አይደሉም። ተቃዋሚው ኃይል የሚታገለው ለፍትህ፤ ለእኩልነት፤ አግባብ ላለው የእድል ክፍተት፤ ለዲሞክራሳዊ አገዛዝና ለሕግ የበላይነት ነው።

ነጻ፤ ፍትሃዊ፤ ክፍትና አግባብ ያለው ምርጫ አብሮና ተባብሮ ብሄራዊ ችግሮችን ለመፍታት ያስችል ነበር። የዚህ ትንተና ዋና መከራከሪያ ነጥብ ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት እንደሆነው አሁንም መንግሥትን በሕዝብ ድምጽ የመለወጥ እድሉ አይሳካም የሚል ነው። ምክንያቱም፤ ህወሓት/ኢህአዴግ እውነተኛ የሆነ፤ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች የሚሳተፉበት የፖለቲካ ምህዳር ከልክሏል። ለሕዝብ አገልጋይና ጠበቃ የሆኑ የመገናኛ ብዙሃንንና የማህበረሰብ ድርጅቶችን አውድሟል። አግባብ ያላቸው የአገርና የውጭ ታዛቢዎች የሚሳተፉበት ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲካሄድ አልፈቀደም። የአውሮፓ የጋራ ማህበር በምርጫው አልሳተፍም ያለበት ዋና ምክንያት ገዢው ፓርቲ በተከታታይ ያሳየው ማጭበርበርና አፈና የሚደገም መሆኑን ስላመነበት ነው። ገዢው ፓርቲ በተደጋጋሚ ያሳየው ልምድ፤ ምንም አፈና ለሌለበት የፖለቲካ ውድድርና የመንግሥት ለውጥ ተገዢ እንደማይሆን ነው። ይኼን ያልኩበትን ምክንያቶች ባጭሩ ላስቀምጥ።

በ1995 ዓም የጸደቀው ሕገ መንግሥት መግቢያ ዜግነትን መሰረት ያደረገ፤ ለመላው ሕዝብ ተጠሪነትና ሃላፊነት ያለው ሁኖ አልተቀረፀም። አገልጋይነቱ ለጎሳ ልሂቃንና ለአንድ ፓርቲ ስብስብ በሚሆን ብልሃት የተዋቀረ ነው። መግቢያውና አንቀፅ ስምንት “እኛ የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሄረሰቦች፤ ሕዝቦች የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤቶች” ነን ይላል። የትግራይ፤ የኦሮሞ፤ የጉራጌ፤ የአማራ ወዘተ ሰፊ ሕዝብ ቀጥታ የሆነ “ሉዓላዊ ሥልጣን” ያለው ኃይል ነው የሚል፤ ወይንም ሕዝብ የሥልጣን መነሻና መድረሻ መሆኑን ህጋዊ መልክ ለመስጠት ነው። ሕዝብ የፖለቲካ ሥልጣን ባለቤት ለመሆን አልቻለም። ቢሆን ኑሮ ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሰረት ሰብአዊ መብቶች ይከበራሉ፤ ቀጥተኛ የሆነ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ተሳትፎና ውድድር ይኖራል። ሕገ መንግሥቱ ያጠናከረው የአንድ ፓርቲን ፍፁም የሆነ ተከታታይነትና የጎሳ ልሂቃንን የበላይነት መሆኑን በጥቂት ምሳሌዎች ለማሳየት ይቻላል። አንቀጽ አስር (i) “ሰብዓዊ መብቶችና ነጻነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ የማይሰጡና የማይገፈፉ ናቸው” ይላል። በስራ ሲተረጎም፤ ማንኛውም ግለሰብ ወይንም ስብስብ መብቱን ተጠቅሞ ገዢውን ፓርቲ ለመተቸት፤ አማራጮችን ለማቅረብና ሰላማዊ ሰልፎችን ለማካሄድ መብቶቹ የተከበሩ ናቸው ማለት ነው። ይኼ በኢትዮጵያ አይታሰብም። Washington Post Editorial Comment, “In Ethiopia, a Chilling Message,” እንዲህ ሲል ደምድሟል። “Over the past decade, the Ethiopian government, which controls the country’s main media outlets, has displayed varying degrees of appetite for free political discourse” and mentions the 2005 contested election at which Ethiopians were massacred and that the ruling party annulled when it saw ominous signs of losing. ከአስር ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ የፖለቲካ፤ የኃይማኖትና የማህበረሰብ ሁኔታዎች ተባብሰዋል። የጋዜጠኞችንና የብሎገሮቹን አሰቃቂ ሁኔታ አስመልክቶ የፖስቱ ትችት እንዲህ ይላል። “The Ethiopian government has rejected criticism from Western governments and human rights groups about its handling of the case. It asserts the bloggers are on trial for attempting to sabotage the state.” ገዢው ፓርቲ ለሰብአዊ መብቶችና ለነጻነቶች መገፈፍ የሚሰጠው ምክንያት ተመሳሳይ ነው፤ “አመፀኛ፤ ሽብርተኛ፤ ፀረ-እርጋታ፤ ጸረ-ሰላምና ፀረ ልማት” የሚሉ።

የሰብአዊ ድርጅቶች የሚሉት ገዢው ፓርቲ ከሚለው የተለየ ነው። ለምሳሌ፤ ፍሪደም ሃውስ “ኢትዮጵያ ነጻ ካልሆኑ ሃገሮች መካከል አንዷ ናት” ይላል። The Committee to Protect Journalists (CPJ) በተደጋጋሚ ያወጣው ዘገባ “ኢትዮጵያና ኤርትራ በአፍሪካ ጋዜጠኞችን ከሚያስሩና ከሚያሳድዱ መንግሥታት መካከል አንደኛና ሁለተኛ” መሆናቸውን አስምሮበታል። Human Rights Watch የኢትዮጵያ መንግሥት እርዳታን ለጎሳና ለፖለቲካ አድልወ፤ ለአፈናና ለሙስና እንደሚጠቀምና በፖሊሲ ደረጃ የኢትዮጵያ ልማት በማህበረሰብ አገልግሎት በዜጎች የኑሮ መሻሻል ያልተመሰረተ መሆኑን በማስረጃ አቅርቧል። The World Economic Forum ኢትዮጵያ በሕግ የበላይነት እንደማትተዳደር፤ የሕጉ አካል የገዢው ፓርቲ መቆጣጠሪይ በትር መሆኑን አመልክቷል “The independence of the judicial system was rated 2.9 out of a possible score of 7 in a recent report by the World Economic Forum.” በእነዚህና በሌሎች መስፈርቶች ሲገመገም፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚታወቀው በክህደቷን በስ ብአዊ መብቶች ገፈፋው እንጅ በሃቀኛነቱ፤ በግልፅነቱ፤ በፍትሃዊነቱና በሃላፊነቱ አይደለም።

በሊብያ መስዋእት የሆኑትን ወገኖቻችን በሚመለከት “ከጩኸት ባሻገር” በሚል ርእስ የሰጠሁትን ትችት እንደገና ላቅርብ። የግብጽ መንግሥት የሃገሩ ክርስቲያኖች በሊብያ አንገታቸው እንደ በግ ታርዶ ሲሞቱ ምንም ሳያመናታ በሽብርተኞች ላይ ዘምቷል። በቅርቡም ብዙ ኢትዮጵያዊያንን በጦር አውሮፕላኖች ተደግፎ ከሊቢይ መንጥቆ ከአደጋ አውጥቷቸዋል። እነዚህን ወገኖቻችን ፕሬዝደነት ሲሲ በካይሮ የአውሮፕላን ማረፊያ ሲቀበል ያየ ኢትዮጵያዊ “የእኛስ መንግሥት የት አለ” ብሎ ቢጠይቅና ለግብፅ መንግሥት አክብሮቱን ቢገልፅ አግባብ አለው። የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካይ ነኝ ባዩ ግለሰብ የወገኖቻችን አንገት እንደ በግ ሲቆረጥና በጥይት ተደብድበው ሲሞቱ “ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ገና በማጣራት ላይ ነን” ያለው ትውልድ የማይረሳው ከሃዲነት ነው። አንቀጽ ሰላሳ ሰባት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ “ፍትህ የማግኘት መብት” አለው የሚለው ለፖለቲካ ጥቅም አገልጋይ እንጅ በሃገርም ሆነ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መብት አስከባሪ አይደለም።

ገዢው ፓርቲና ደጋፊዎቹ ቢወዱም ባይወዱም፤ በሕገ መንግሥቱ ላይ የሰፈረው አንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ የኢትዮጵያ አፍራሽ መሳሪያ ሁኗል። ዛሬ ማንም ሃገር ወዳድ መንግሥት የሚገዛውን ሃገር ለፖለቲካና ለኢኮኖሚ የበላይነት ትኩረት ሰጥቶ “የመገንጠል መብትን” አይደግፍም። ኢትዮጵያዊያንን ከሚያኮሩ እሴቶች መካከል የኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ፤ ነጻነትና ሉዓላዊነት መከበር አንዱና ዋናው ነው። የእንግሊዙ ጋዤጠኛና ደራሲ ሪቻርድ ዳውደን እንዲህ ሲል አስቀምጦታል። “Ethiopia has one rich asset that much of Sub-Saharan has lost or never developed. It has been a state for a very long time, longer than Britain and most of Europe…Ethiopian connections to the Semitic world go back thousands of years, through migration and trade. Its Coptic Christianity and ceremonies were established in the third Century, AD.” ይኼን የማይገኝና የማይተካ ጥሪት ነው ገዢው ፓርቲ ሆነ ብሎ ያፈረሰውና የሚያፈራርሰው። ዛሬ የሚታየው ክስተት የአዲስ ታሪክ ፈጠራ፤ የጎሳዎች መለያየት፤ የክልሎች አዲስ መሳፍንት አመራርና የወጣቱ ትውልድ በጎሪጥ እየተያዩ መተላለፍ ለሃገሪቱ ህልውናና ዳይቨርስ ለሆነው ሕዝቧ ጠንቅ የፈጠረ መሆኑ ነው። አንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ (አንድ) እንዲህ ይላል። “ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር፤ ብሔረሰብ፤ ሕዝብ የራሱን እድል በራሱ የመወሰን እስከ መገንጠል ያለው መብት በማናቸውም መልክ የተጠበቀ ነው።” ራሱን በራሱ ለመበታተን ፈቅዶ በሕገ መንግሥቱ ያስገባ ገዢ ፓርቲ ህወሓት/ኢህአዴግ ብቻ ነው። ከጎሳ ልሂቃን ውጭ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይኼን አንቀፅ አይቀበልም። ኢትዮጵያዊያን መስዋእት ሲሆኑ፤ የሃገሪቱ ዜጎች በገፍና በአንድ ላይ ያለቀሱትና የጮኹት፤ ገዢውን ፓርቲ የወቀሱትና የተቹት ኢትዮጵያን እንደ ሃገር፤ ኢትዮጵያዊነትን እንደ ዜግነት መታወቂያና መለያቸው አድርገው ስለመረጡ ነው።

ገዢው ፓርቲ በልማትና በእድገት የሚከተለው መርህ ከፖለቲካው አይለይም።  አንቀጽ አርባ ሶስት (አንድ ሁለትና አራት) እንዲህ ይላል። “የኢትዮጵያ ሕዝቦች፤ በአጠቃላይም ሆነ በኢትዮጵያ ያሉ ብሄሮች፤ ብሄረሰቦች፤ ሕዝቦች በተናጠል የኑሮ ሁኔታዎችን የማሻሻልና የማያቋርጥ እድገት የማግኘት እድላቸው የተጠበቀ ነው (ንኡስ አንድ)። ዜጎች በብሄራዊ ልማት የመሳተፍ በተለይ አባል የሆኑበትን ማህበረሰብ የሚመለከቱ ፖሊሲዎችና ፕሮጀክቶች ላይ ሃሳባቸውን እንዲሰጡ የመጠየቅ መብት  አላቸው” (ንኡስ ሁለት)። ጠንካራና ተጠቃሚ የሆኑ የጎሳ ፖለቲካ መሪዎች ያሏቸው ክልሎች የተሻለ እድል ይኖራቸዋል ማለት ነው። እንደ ጋምቤላ፤ አዋሽ ሸለቆ፤ አፋር ወዘተ ያሉት ማን ይሟገትላቸዋል? የተዛባ የክልል ልማት ወይንም የተዛባ ገቢና ሃብት ቢከሰት ማን ይዳኛል፤ ማን ያስተካክላል? የተፈጥሮ ኃብት ባለባቸው፤ ለምሳሌ ለም መሬት፤ ወንዝ፤ መአድን ወዘተ ኋላ ቀር ክልሎች ሕዝብ መብትና ጥቅም ማን ይከራከራል? ንኡስ አራት እንዲህ ይላል። “የልማት እንቅስቃሤ ዋና ዓላማ የዜጎችን እድገትና መሰረታዊ ፍላጎቶች ማሟላት ይሆናል።” ይኼ መርህ በስራ አልተተረጎመም። ለምሳሌ፤ የስራ እድል ከሌለ ገቢ ሊኖር አይችልም። የፍላጎት ምርት እያደገ ካልሄደ የኑሮ ውድነት የማይቀር ነው። ጉቦ፤ ጎሳዊ አድልው፤ ሙስና ተቋማዊ ከሆኑ ሃብት ከሃገር ማሸሽ የማይቀር ነው። ይኼን ሁኔታ ያባባሰው እያንዳንዱ የጎሳ አለቃ ወይንም አዲስ መሳፍንት የሚሰራው ለመላው የሃገሪቱ ሕዝብ አለመሆኑ ጭምር ነው። ሁሉም ለግሉና ለራሱ ቡድን ከሆነ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያገለግል ኢኮኖሚ አልተመሰረተም ማለት ነው። ለልማት የሚውለው ካፒታል ለግዙፍ ስለላ ፈሰስ ከሆነ፤ ከተሰረቀና ለፖለቲካ ስልጣን ከዋለ ካፒታሉ ባከነ ማለት ነው። “የዜጎች እድገትንና መሰረታዊ ፍላጎቶች” ለማሟላት ቃል የገባና ቆርጦ የተነሳ መንግሥት የጥቂቶች አገልጋይ ሁኗል የምለው ለዚህ ነው።

ሕገ መንግሥቱ ለተዛባ ገቢ፤ ሃብትና እድገት የተቆራኙ የአገዛዝ መርሆዎችን ያስተጋባል። የተዛባውን የሚያስተካክል ከመንግሥት ቁጥጥር ነጻ የሆነ ወይንም  የመንግሥት ሁኖ በሞያው ጥራትና በነጻነት የሚሰራ አካል የለም (The Constitution does not provide an independent oversight to ensure checks and balances in governance). አንቀጽ አምሳ (አንድ) እንዲህ ይላል። “የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሳዊ ሪፐብሊክ በፌደራል መንግሥትና በክልሎች የተዋቀረ ነው።” ልክ እንደ ኮሙኒስት ፓርቲዎች አንዱ ሌላውን የሚደግፍ ማእከላዊ የሆነ የአንድ ፓርቲን የበላይነትና የሚመሩትን ግለሰቦች የሚጠቅም አገዛዝ መሆኑ ነው። ምርጫውን ስንመለከት ሂደቱ ከላይ የቀረቡትን የአንድ ፓርቲ የበላይነት የሚያጠናክር ሁኖ እናገኘዋለን። አንቀጽ አምሳ ስድስት እንዲህ ይላል። “በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይንም ጣምራ ድርጅቶች የፌደራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል ያደራጃል/ያደራጃሉ/ይመጥጣል/ይመርጣሉ።” ይኼን በበለጠ የሚያጠናክረው አንቀጽ ሰባ ሁለት እንዲህ ይላል። “የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የአስፈጻሚነት ሥልጣን የተሰጠው ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ነው” ይላል። ስለዚህ፤ ከዲሞክራሳዊ ባህሪው ይበልጥ ህገ መንግሥቱ የሚያደላው ጠንካራ፤ አንድ ወጥ ለሆነ፤ በመንግሥት ባጀት ለተደገፈ ፓርቲ ነው። በአሁኑ ምርጫ ከአርባ በላይ ከሆኑት “ተወዳዳሪ ፓርቲዎች መካከል ተቃዋሚ ሊባሉ የሚችሉት መድረክና ሰማያዊ” ናቸው። አብዛኛዎቹ ለህወሓት/ኢህአዴግ ታማኝ የሆኑ ተቀጥላዎች ወይንም ሕገ መንግሥቱ “ጣምራ ድርጅቶች” ናቸው። ይኼ የሆነበት ፈሊጥ “በምክር ቤቱ አብላጭ መቀመጫ” ለማግኘት ነው። ስለሆነም፤ ህወሓት/ኢህአዴግ አብላጭ መቀመጫ እንዲያገኝ ቀደም ብሎ ታስቦበት በስራ ላይ የዋለ የተለመደ ዘዴ ነው። ይኼ ሲሆን ከላይ የቀረቡትን የፖሊሲና የመዋቅር ችግሮች ለሕዝብ አቅርቦ ለመወያየት አይቻልም ማለት ነው። ምርጫው የሚካሄደው የገዢን ፓርቲ ስልጣን ለማራዘም ነው።

አደጋው ሰላምና እርጋታ እንዲኖር ሲባል ያለውን እንቀበል የሚለው ምክርና ሽምግልናም አብሮ የሚካካሄድ መሆኑ ነው። ፍትሃዊ የሆነ ለውጥ ከሌለ ችግሩ ይባባሳል፤ ወጣቱ ትውልድ ልክ አንበሳ እንዳየ የእንስሳ መንጋ እንደ ከብት እየበረገገ ከሃገሩ ይሰደዳል። “የነቃ ተሳትፎ ማድረግ” ይገባል የሚለው ምክር የሳታቸው ብዙ የፖሊሲ ጥያቄዎች አሉ፤ የኑሮ ውድነት፤ ሙስና፤ ከሃገር የሚሸሺ ሃብት፤ የወጣቱ ትውልድ ተስፋ መቁረጥ፤ የጎሳ ጥላቻ ወዘተ። “አዲስ አበባ ግንቦት 4/2007 መጪው ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ ኅብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ የአገር ሽማግሌዎች ጠየቁ። የአገር ሽማግሌዎቹ ምርጫው ሠላማዊና ፍትሃዊ ሆኖ በሚጠናቀቅበት ሁኔታ ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ተወያይተዋል። የአገር ሽማግሌዎቹ ምክትል ሰብሳቢ ፓስተር ዳንኤል ገብረስላሴ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ዜጎች የፈቀዱትን የፖለቲካ ፓርቲ በሠላም መርጠው እንዲገቡ ሽማግሌዎቹ የበኩላቸውን ያደርጋሉ።” ተናጋሪው “የፈቀዱትን የፖለቲካ ፓርቲ በሰላም መርጠው እንዲገቡ” ሲሉ ያልተናገሩት ከተናገሩት ይበልጣል፤ አንድነትና መኢአድ መፈራረሳቸው፤ ብዙ መቶ የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብቶች ጠበቃዎች አሁንም አለመፈታታቸው፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በሃገር ቤትና በውጭ ለሚደርሰው የሰብ አዊ መብቶች መገፈፍ ሃላፊነትና ተጠያቂነት እንዳለበት አለማመኑ ወዘተ። “በሕዝብ የተመረጠው አካል ሥልጣኑን እንዲይዝና የተሳካ ምርጫ እንዲሆን የድርሻቸውን እንደሚወጡም ገልጸዋል። የአገር ሽማግሌዎቹ በፖለቲካ ፓርቲዎች የውይይትና የክርክር መድረኮች ላይ በመገኘት የሠላም ኃሳባቸውን እየገለጹ መሆኑን ነው የተናገሩት።የአገር ሽማግሌዎቹ ከተለያዩ የኃይማኖት ተቋማት፣ የሲቪክ ማኅበራትና ከተለያዩ የሙያ መስኮች የተውጣጡ መሆናቸውንና ለኅብረተሰቡ ባላቸው ቅርበት ምርጫው በሠላም እንዲጠናቀቅ በማስተማር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ገልጸዋል።

ከአገር ሽማግሌዎቹ መካከል ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም በአገሪቱ በርካታ ለውጦች እየመጡ መሆኑን በመግለጽ ይህንኑ ለማስቀጠል መጪው ምርጫ በሠላም ሊጠናቀቅ ይገባል ብለዋል።

ወጣቱ ሠላምን በማረጋገጥ የአገሩን ልማት ለማስቀጠል የሚረዳውን ምርጫ በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ ያለውን ሚና ተገንዝቦ በኃላፊነት ሊንቀሳቀስ እንደሚገባም አስገነዝበዋል።” ኢትዮጵያ የአባቶች ምክር እንደሚያስፈልጋት አምናለሁ። ምክር አቅራቢዎች ለህሊናቸው ብቻ የመገዛት ሃላፊነት አለባቸው። ምክሩ ጠቃሚና ሚዛናዊ የሚሆነው በገዢው ፓርቲ የሚካሄደው የሰብአዊ መብቶች ረገጣ እንዲቆም፤ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፤ የሰላምና የእርቅ ድርድር በአስቸኳ እንዲካሄድና ሁሉን አሳታፊ የሆነ ብሄራዊ የሆነ የአንድነት መንግሥት ተቋቁሞ እውነተኛ ዲሞክራሳዊ ምርጭ እንዲካሄድ ቢጨመርበት የሕዝብ ተስፋን ይቀሰቅስ ነበር። በጎሳ ይሁን በጥቅም ወይንም ሌላ ምክንያት ምክሩ አድሏዊ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ይኼን ምክር ሲሰማ ለምርጫው ብቻ ሳይሆን በአሁኑ ወቅት በሽምግልና ስም ገዢውን ፓርቲ ደግፈው ድምፃቸውን ለሚያሰሙ አባቶችም ያላቸው አክብሮት ዝቅ እንደሚል መገመት አያስቸግርም። ወጣቱ ትውልድ ይኼን ሰምቶ “ነገ ስራ አገኛለሁ፤ ተስፋየ የጠነከረ ይሆናል” የሚል አይመስለኝም። በሌሎች ሃገሮች ዘጠና በመቶ የሚሆነውን የስራ እድል የሚፈጥረው የግል ክፍሉ ነው። በኢትዮጵያ የመቅጠር የበላይነት የያዘው ህወሓት፤ የሚቆጣጠረው መንግሥትና የፈጠራቸው ተቋሞች ናቸው።

ነጻ፤ ፍትሃዊና አግባብ ያለው ምርጫ እንዳይካሄድ ሆነ ተብሎ የሚደረገው ተንኮለኛነት መሠረታዊ ምክንያት አለው።  የግል ጥያቄየ ህወሓት/ኢህ አዴግ ለምን ራሱን ለአደጋና ለውርደት ያጋልጣል? የሚል ነው። የምርጫ ቦርዱን ለፖለቲካ የኳስ ጨዋታው የተጠቀመበት ምክንያት ግልጽ ነው። ህወሓት/ኢህአዴግ የውጭና የውስጥ ተመልካቾችን ለመሸንገል ሲል ያመቻቸውና የፈቀደው ለራሱ አጎብዳጅና ተገዢ ለሆኑ፤ በተለይ፤ በውስጣቸው ገብቶ፤ አባብሎ ወይንም አስፈራርቶ በኢትዮጵያ ሕዝብ ባጀት “ለገዛቸው” ተለጣፊ ቡድኖች፤ ተቀናቃኝ የሆኑትን አፍርሶ ላቋቋማቸው ታማኝ ድርጅቶች፤ ለፖሊሲ ለውጥ ሳይሆን ለወንበር ለተሰለፉትና፤ በአብዛኛው ለብሄር/ብሄረሰብና ሕዝቦች ፓርቲዎችን ተሳትፎ ነው። ማስፈራሪይ ዱላው ተተኪው መንግሥት “ያጠቃሃል፤ ያሳድድሃል፤ ያስርሃል፤ የዱሮ ጠላቶችህን ይመልስብሃል” የሚል የተለመደ ፕሮፓጋንዳ ነው። በሰማያዊ ፓርቲ አመራርና አባላት ላይ የሚደረገው ማሳደድ፤ መደብደብ ማሰርና “ተራ ወንጀል” ለዚህ ዋቢ ነው። የብሄር ሆኑ የህብረ ብሄር ድርጅቶች–

በምርጫው የሚሳተፉ ፓርቲዎች–የመሳተፍ መብት እንዳላቸው አምናልሁ። በከፊልም ቢሆን፤ ቢያንስ ከገዢው ፓርቲ የሚለዩበትን መሰረታዊ ጉዳይ ለሕዝብ ለማቅረብ እየሞከሩ ነው። በቅርቡ የሚካሄደውን የቴሌቪዢን ውይይት ሳይ ልዩነቶቹ ከባድ መሆናቸውን እገነዘባለሁ። ለምሳሌ፤ አንድ ለአምሥት የሚለው የገዢው ፓርቲ የስለላ መረብ ማንን ለመቆጣጠር እንደተቋቋመ ለውይይት መቅረቡ። ምርጫው ዲሞክራሳዊ ነው አይደለም? የሚል ውይይት መካሄዱ። ይኼ እናዳለ ሁኖ፤ ውይይቱ ሕዝብ የሚፈልገውንና የሚመኘውን የፖሊሲ ለውጥ ለማምጣት አይችልም። በገፍ ለሚሰደዱ ወጣቶች አጥጋቢ እድል ከፋች መልስ አያመጣም። በኑሮ ውድነት ለሚሰቃየው ድሃና መካከለኛ ስርቶ አደር ሕዝብ በቀን ሶስት ምግብ አያቀርብም። ሙስናው እንዲቆምና በገፍ የተዘረርፈው ወደ ሃገር እንዲመለስ አያደርግም።

ፈልጎም ወይንም ተገዶ ሕዝብ ድምፁን ያሰማል። ሆኖም፤ ብሄራዊ ምርጫ አንድ ሶስተኛ፤ ወይንም ከዚያ በላይ በሆነ የሕዝብ ተሳትፎና በማስፈራራት ሊካሄድ አይችልም። አገሪቱ “ሰሜንና ደቡብ” በሚል የምርጫ ሂደት ብትጓዝ ተከታዩ በጣም አደገኛ ነው። ለመምረጥ አልፈልግም የሚለው ሕዝብ መብትስ ምን ሆነ፤ ለምን ታፈነ፤ ብለን መጠየቅ ይኖርብናል። የማይመርጡና በፍርሃት የሚመርጡ ቢኖሩም ህወሓት/ኢህአዴግ “በከፍተኛ የሕዝብ ድምፅ አሸነፍኩ” ለሚለው ስልት ይጠቅመዋል። ምን አልባት በ99.6 በመቶ ከማሸነፍ 90 በመቶ ወይንም ከዚህ በታች ቢያሸንፍ የፖሊሲ ለውጥ የማይታሰብ ነው።

ለዚህ የምርጫ ማጭበርበር ስልት የተካነበት የአደረጃጀት ዘዴ እንዳለው እናውቃለን። አስቀድሞ መገምገምና ታማኝና ታዛዢ የሆኑ ስብስቦችን ማደረጀትና አቅጣጫ ማስያዝ አገዛዙን ለማራዘም የተፈተነ ዘዴ ነው። ብዙ ማስረጃዎች የሚያመለክቱት፤ ህወሓት በውጭም ሆነ በውስጥ፤ በማንኛውም የኢትዮጵያ “ድርጅት ወይንም ስብስብ” ሰርስሮ ገብቷል። በኢትዮጵያ ሕዝብ ባጀት የፖለቲካ ደጋፊዎች በገፍ ሰብስቧል። በተለይ በወጣቶች ዙሪያ። አንድ ለአምስት ማለት ቁጥጥሩ ወደ ቤተሰብ ገብቷል ማለት ነው።፡ከምርጫ ዘጠና ሰባት በኋላ አንድ የዓለም ባንክ ጥናት ያሳየው የምርጫ ዘጠና ሰባት አይነት ጥቃትና ውርደት እንዳይከሰት፤ ህወሓት ሆነ ብሎ እቅድ አውጥቶ ብዙ ሚሊዮን ደጋፊዎችን ለኢህአዴግ አባልነት መልምሏል። በፈቃድ ሳይሆን በማባበል። በራሱ ወጭ ሳይሆን በሃገሪቱ ባጀት። ዛሬ ከክልል አንድ ውጭ የበላይነቱን የሚያካሂደው በክልሉ በተወለዱ፤ ባህሉን፤ ቋንቋውን ወዘተ በሚያውቁ፤ በተለይ ባለፉት ሃያ አምስትና ሰላሳ ዓመታት በተወለዱ፤ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በቅጡ በማያውቁና እንዳያውቁ በተገደዱ ወጣቶች ተባባሪነትና ደሞዝተኛነት ነው።

የታፈነ ምርጫ ሙስናን ያንፀባርቃል

በጎሳዊ አድልዎ፤ በጉቦና በሙስና የተበከለ አገዛዝ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ሊፈቅድ አይችልም። እንዴት ራሱን ለአደጋ ያጋልጣል? የምርጫ ማጭበርበር ሙስና የተለያዩ ገጾች አሉት፤ የገንዘብ፤ የፍርሃት፤ የፖለቲካ፤ የስም ማጥፋትና ሌላ። በማባበል፤ ድጎማ በመስጠት፤ “ይኼን ካደረግህ ይኼን እስጥሃለሁ” በማለት። ለምሳሌ ብድር፤ ማዳበሪያ፤ መሬት፤ ፈቃድና ሌሎች ግብዓቶች በመስጠት አባላት መሰብሰብ የማጭበርበር ገፅታ ነው። (Fraud, deception and manipulation are forms of electoral corruption at a state level). “የመንግሥት ባጀት” ለፖለቲካ የበላይነት ውሏል። ሰርጎ ገብነት፤ ከፓርቲው ቁጥጥር ውጭ የሆኑ ህብረ ብሄር ድርጅቶችን ማፈራረስ፤ እንዲካሰሱ ማድረግ፤ የግለሰቦችን ስም ማጥፋት፤ ፈቃዳቸውን መከልከል፤ ንብረታቸውን መቀማት ሙስና ነው። በጎጃም ገበሬዎች ላይ እንደሆነው “ምርጫው እስከሚያልቅ ድረስ የመሬት ጥቅም ይዞታ ፈቃዳችሁ ለጊዜው ተከልክሏል” ብሎ የፖለቲካ ውሳኔ ማዳረግ የማይረሳ ጭካኔና የስልጣን ብልግና ነው። በህብረ ብሄር ድርጅቶች ምትክ ጥገኛና ተለጣፊ ድርጅቶችን ፈጥሮ የሕግ እውቅና መስጠት ወዘተ “የሙስና አካል” ነው። እነዚህ አይነቶቹ ጫናዎች የተለመዱ የፖለቲካ የበላይነት መሳሪያዎች ሁነዋል። ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት አገልግለዋል። በዚህ አይነቱ የፖለቲካ ሁኔታ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ይካሄዳል ብሎ ማመን ራስን ማታለል ነው። የአሜሪካ የውጭ መስሪያ ቤት የፖለቲካ ክፍል ምክትል ሃላፌ ዌንዲ ሸርማን “ነጻ፤ ፍትሃዊ፤ ክፍትና አግባብ ያለው ምርጫ ይካሄዳል፤ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ናት” ብላ የተናገረችውን ሌላው ቀርቶ ብዙ የኢህአዴግ አባላት አይቀበሉትም። የኢትዮጵያን ሕዝብ አይቀበለውም፤ አንድም ተቃዋሚ ፓርቲ አላነጋገረችም። የኢትዮጵያንና የራሷን ሃገር ዘላቂ ጥቅም ጎድታለች።

ከፍተኛ ተስፋ የሚሰጠው የኢትዮጵያ ሕዝብ የፖለቲካ ብስለት ያለው መሆኑ ነው። የፖለቲካ ጨዋታውን እየሳቀ ያልፈዋል። ማን ለምን እንደሚወዳደር ያውቃል። አንዳንድ ታዛቢዎች በምርጫው መሳተፍ የዲሞክራሲ ቀዳዳ ይከፍታል የሚል አመለካከት ይሰነዝራሉ። ይኼ አመለካከት ቢያንስ ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት ሲነገር ቆይቷል። ጥቂት ወንበሮች መያዝ ይቻላል። ፖሊሲ ለመለወጥና ሙስናን ከስሩና ከጭንቅላቱ ነቅሎ ለመቅረፍ አይቻልም። በየትኛውም ዲሞክራሳዊ አገር የፓርላማ ውሳኔዎች የሚደረጉት በድምፅ ብልጫ ነው። ጥቂት ወንበሮች የድምፅ ብልጫ ሊያመጡ አይችሉም። ብቸኛ ተቃዋሚ የፓርላማ አባል ከመጮህ ውጭ ምንም ለማድረግ አይችልም/አትችልም። ችግሩ እንዳለ ለዓምስት አመታት፤ ለአስር አመታት ወዘተ ሊቆይ ይችላል። ገዢው ፓርቲ የሚፈልገው ይኼን ነው። የሰላሙ ትግል ዘዴዎች መቀየር አለባቸው የምለው ለዚህ ነው።

የመሳተፍ መብታቸው እንዳለ ሁኖ እውነተኛ በሆነ መንገድ ለሕዝብ መብቶች፤ ለፍትህና ለዲሞክራሳዊ ለውጥ የቆሙ ፓርቲዎች ይኼን “ምርጫ” ይካሄዳል የሚል የፖለቲካ ኪሳራ የሚያስከትል ፕሮፓጋንዳ መሸመትና መቀበል ያለባቸው አይመስለኝም። አስቀድሞ፤ “አናሸንፍም፤ ሆኖም የመሳተፍ መብታችን እንጠቀማለን” የሚል መልእክት ለሕዝብ ቢቀርብ ይጠቅም ይመሰለኛል።

ከለይ ያቀርብኩት የምከራከርብት ሃሳብ አንድ ነው። ይኼውም የፖለቲካ ለውጥ፤ ማለትም የመንግሥት አመራና የፖሊሲ ለውጥ ካስፈለገ “እምቢ፤ የገዢውን ፓርቲ ተንኮል ከአሁን በኋላ አንቀበልም” ብሎ ሕዝቡን ለመብቱ እንዲነሳ የማድረግ ግዴታ እንደሚታይ ነው። ይኼን ደጋግሜ የማመለክተው የምርጫው ውጤት አስቀድሞ የታወቀ ስለሆነ ነው። ያለፉት አራት ምርጫዎች የሚያሳዩት ልምድ፤ የምርጫው አሸናፊ ሁል ጊዜ ህወሓት/ኢህአዴግ እንደሚሆን ነው። የሚያሸንፍበት ምክንያት የፖለቲካ ለውጥ እንዳይመጣና ያካበተው ጥቅም እንዳይናጋ ጭምር ነው።

ታዲያ ምን ይደረግ?

ቢያንስ፤ ተወዳዳሪዎችን ዓለም የሚያከብራቸው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚቀበላቸው፤ ሊያቀርቧቸው የሚገባቸው ዲሞክራሳዊ ጥያቄዎች አሉ። “የህወሓት ገመና” በሚል፤ ከዚህ በፊት በድህረገጾች የቀረበ  በማስረጃ የተደገፈ ሃተታ የኢትዮጵያዊያን ሕዝብ ሰብአዊ መብቶች ፍፁም በሆነ ደረጃ እንደታፈኑ፤ ይኼ አፈና ለሃገሪቱ ህልውናና ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ህይወት አደጋዎችን እንደፈጠረ፤ የምእራብ ሃገሮች፤ በተለይ አሜሪካና እንግሊዝ ለህወሓት የሚሰጡት ግዙፍ እርዳታ፤ የመረጃና የዲፕሎማሲ ድጋፍ ለአደጋው መጋቢ እንደሆነና መለወጥ እንዳለበት አሳስባለሁ። ተቃዋሚ ፓርቲዎች በመተባበርና በመናበብ በጉዳዩ ሊረባረቡበት ይችላሉ፤ አዳማጭ ይኖራቸዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ የማህበረሰብ ክፍሎች፤ ልሂቃን፤ ለጋስ ድርጅቶችና መንግሥታት ደፍረው ማስተናገድ ያለባቸው አስኳል ጉዳዮች አሉ። ለምሳሌ፤ ሰላምና እርጋታ እየደፈረሰ መሄዱና የእርቅና ሰላም ድርድር አስፈላጊ መሆኑን በግልፅ መናገር፤ ሕዝቡ በኑሮ ውድነት መሰቃየቱ አደገኛ የማህበረሰብ ቀውስ (Social Crisis) እንደሚያስከትል ማሳሰብ፤ የምእራብ ሃገሮች ዘላቂ ጥቅም ዋስትና የሚኖረው ግፍ፤ በደል፤ ሙስና ወዘተ ሲጠፉ መሆኑን ማስረዳት። ወጣቱ ትውልድ በሃገሩ አማራጮች እንዲኖሩት ያልተቆጠበ ግፊትና ድጋፍ መስጠት። ተቃዋሚ ፓርቲዎች እነዚህን በግልፅ የሚታዩ ችግሮች መፍትሄዎች ችላ ካሏቸው አስፈላጊ የሆነውን የዲሞክራሲ ስርዓት ምስረታ ለብዙ አስርት ዓመታት ይገቱታል። የአሁኑን ጨቋኝ አገዛዝ ዲሞክራሳዊ በሆነ አገዛዝ ለመተካት ካልተቻለ ከፍተኛ ቀውስ መፈጠሩ አይቀርም።

አንዳንድ ተመልካቾች የሚሉት፤ ህወሓት የኢትዮጵያ የመፈራረስ አደጋ ከታየው ጠቅልሎ ወደ ምሽጉ ወደ ትግራይ ይገባል፤ የፈለገውን “ታላቋን ትግራይ” ይመሰርታል ነው። እንዲያውም፤ በቤኒ ሻንጉል የሚገኘውን የተሃድሶ ግድብ የሚገድበው ለራሱ ለህወሓት ጥቅም እንጅ ለነዋሪዎቹና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተቆርቁሮ አይደለም የሚሉም አሉ። አንድ፤ ቢሆንስ፤ “ታላቋ ትግራይ” ታላቅ ኢትዮጵያ አትሆንም የሚል ግምት አለኝ። ህወሓት ኢትዮጵያዊያንን አናክሶ በሰላም ለመኖር አይቻልም። ሁለት፤ የትግራይ ሕዝብ አገር ወዳድ ስለሆነ እንዴት ይኼን ውጤት ይቀበላል፤ ራሱ መልሶ አንፈልጋችሁም የሚል ድምፅ አያሰማም ብለን ለመቀበል የምንችልበት ምን መረጃ አለ? መረጃ የለም እላለሁ። የጎንደር ሕዝብ፤ በሌላው ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ተደግፎ፤ የተነጠቀውን መሬትና በአዲስ ለፖለቲካ የበላይነት የተመቻቹን ንዑስ ክልሎች ስኬታማ እንዳይሆኑ አድርጎ፤  የታወቀ ድንበሩን እስከ ተከዜ ወንዝ ሳያስመልስና ህወሓት በምስጢር ለሱዳን የሰጠውን መሬት ሳያስመልስ “ለታላቋ” የህወሓት ትግራይ ሰላም የሚሰጥ አይመስለኝም። “የተኛ” የሚመስል ሕዝብ ጉዳቱ እየበዛበት ሲሄድ መነሳቱ የማይቀር ነው። ቢያንስ ለራሱ ህልውና ይታገላል የሚል ግምት አለኝ። የጎንደርም ሆነ የሌላው ሕዝቡ ትእግስት ማለቁን የሚያሳዩ ብዙ ምልክቶች አሉ። በመከላከያ ኃይሉ ውስጥ ልዩነቶች መነሳታቸው አይቀርም። የኃይማናት አባቶች በቅርቡ ያወጧቸው መግለጫዎችና አደራዎች የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል መወከል ያለበት አምባገነኑን አገዛዝ መሆን የለበትም የሚል ነው። የሕዝቡን አደራ አክብሮና ተቀብሎ ፊቱን ወደ ራሱ ሕዝብ መብትና ክብር እንዲያዞር አደራ ብለዋል። ትግል በተናጠል ስኬታማ አይሆንም። ኢትዮጵያዊያን ተባብረውና ቆርጠው በአንድ ድምጽ ከተነሱ አዲስ ታሪክ የመስራት ብቃትና አቅም አላቸው።

በውጭም ሆነ በሃገር ቤት የምንኖር አገር ወዳዶች ማጤን ያለብን በግልጽ የሚታዩ ሁለት አደጋዎች አሉ። አንድ የኢትዮጵያ ሉዐላዊነት መበረዙና ሃገሪቱ በየቦታው እየተናጋች መሆኗ፤ ሁለት ገዢው ፓርቲ ሆነ ብሎ የቀረፀው የጎሳ ልዩነት ሊቆም የማይችል የሚመስል የጎሳ ጥላቻ  መፍጠሩ። ቀውስ የማይቀር ነው የሚሉ የሃገር ውስጥ ታዛቢዎች ብዙ ናቸው። እኔ የምከራከረው ሁለቱንም አደጋዎች ለመከላከል መተባበር አስፈላጊ ሁኗል በሚል ነው። ትእቢተኛውና ጠባብ ጎሰኛው ህወሓት አላወቀበትም እንጅ፤ ቀውስ ለማንም አይበጅም። አስከፊ የሆነ የርስ በርስ ጦርነት ሊነሳ ይችላል። የቀረችው ኢትዮጵያ የመከፋፈል እድሏ የተባባሰ እንደሚሆን አስቀድሞ መገመት አስፈላጊ ነው። አንዳንድ ታዛቢዎች የሚሉት በትጥቅ ትግል ለመገንጠል የሚታገል ኃይል ለህወሓት ህልውናና የበላይነት አደገኛ ከሆነና በፖለቲካውና በዲፕሎማሲው የሚያዋጣው ከሆነ የህወሓት አመራር አንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝን ተጠቅሞ ኤርትራን እንዳስገነጠለ ሁሉ፤ ሌላ ክልል እንዲገነጠል ቢያደርግ አያስገርምም። ኢትዮጵያን ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ወዳለው የእድገት ጎዳና ለማመቻቸት የሚቻለው ለሁሉም አሳታፊ የሆነ በሕግ የበላይነት የተመሰረተ እውነተኛ ዲሞክራሳዊ አገዛዝ ሲመሰረት ብቻ ነው። ገዢው ፓርቲ በራሱ አቅምና ብርታት ዘላቂና ፍትሃዊ እድገት ለማራመድ አይችልም። እስካሁን የቆየው ተቃዋሚው ኃይልና ሌሎቻችን ተከፋፍለን ደካማና ፈሪ መሆናችንን ስለተረዳውና በውጭና በሃገር ቤት ያለው “ተቃዋሚ” ጥበበኛ አመራር ስለሌለው ነው። ይኼ ሁሉ እናዳይደጋገም ከተፈለገ አፋኙን አገዛዝ የሚተካ፤ ሁሉን የሚያስተናግድ ዲሞክራሳዊ አማራጭ አስፈላጊ ነው። ለዚህ መደራጀትና አብሮ መስራት ወሳኝ መሆኑን በተደጋጋሚ አሳስቢያለሁ።

የዲሞክራሲ መንግሥት አማራጭ እንዲሁ በምኞት አይገነባም። ሕዝቡ፤ በተለይ ወጣቱ ትውልድ ለራሱ ህይወት መሻሻል ሲል እውቀቱንና አቅሙን ማጎልመስ፤ እንደ እንሰሳ ከመበርገግ ይልቅ ሳይሰለች መታገል፤ ለፍትህ መስዋእት ለመሆን መድፈር፤ አቤቱታውን በተባበር ድምፅ ማሰማት ወዘተ ግዴታው ነው። በሊብያ አንገትን ተቆርጥና በጥይት ተደብድቦ ከመሞት፤ በየመንና በደቡብ አፊሪካ ተሰዶ ከመዋረድ በሃገር ውስጥ ሁኖ ለመብቶች መታገል ዘላቂ ፍትህ ያመጣል። ይኼን ማንም የውጭ ኃይል ሊያደርግልን አይችልም። ከሁሉም በላይ በየደረጃውና በየአካባቢው ድርጅት ማቋቋም፤ አዲስ መሪዎች እንዲወጡ ማበረታታት፤ በሰሰከነ አእምሮ ብልሃት ያለው ብሄራዊ የፖለቲካ አመራር እንዲኖር መጎትጎት፤ አብሮና ተባብሮ የመስራት የፖለቲክና የማህበረሰብ አደረጃጀት ልምድ እንዲስፋፋና ጥልቀት እንዲኖረው ጠንክሮ መስራት፤ ወጣቱ ትውልድ ከህወሓት/ኢህአዴግ የጎሳ ጥላቻ መርዝና መንጋጋ ነጻ እንዲወጣ ያልተቆጠበ ጥረት ማድረግ፤ በውጭ የሚኖረው ስደተኛ አፋኙን መንግሥት እንዳይደግፍ፤ ማንኛውንም ዓይነት እገባ እንዲያደርግ ጥሪ ማድረግና ለጋስ ድርጅቶች፤ መንግሥታትና ኢንቬስተሮች ለሰብአዊ መብቶች መከበር ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጡ ሳይሰለቹ መጎትጎት  ይገኙበታል። ልዩ በሆነ መንገድ መደራጀትና ማደረጀት ተቀዳሚነት አለው። እኛ ካልደፈርንና አብረን ለመስራት ከፍተኛ ጥረት ካላደረግን ማንም መንግሥት አይደግፈንም። እንዲያውም እንደ ተናቅ እንቆያለን። መቃወም ብቻ አማራጭ አይደለም።

ይኼን የተቀነባበረ ትግል ለማካሄድ ለአብዛኛው ሕዝብ ህይወት አለመሻሻል ማነቆ የሆኑ ስርዓት ወለድ ማነቆዎች እንዳሉ መገንዘብና መፍትሄ መፈለግ ተገቢ ነው። የፖለቲካው ምህዳር ፍፁም በሆነ ደረጃ መዘጋቱ፤ የሰብአዊ መብቶች በሚያሰቅቅ ደረጅ መገፈፋቸው ከችግሮቹ መካከል የመጀመሪያውን ደረጃ ይዘዋል። ይኼን ችግር ነጥለን ብናየው (መነጠል ባይቻልም)፤ በሃገር ቤት የተቃዋሚ ፓርቶዎች ድርጅታዊ ህልውና ጠፍቷል። ጥሩው ነገር መሪዎቹና አባላቱ አሉ። አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይደግፋቸዋል። ሊያንሰራሩ ይችላሉ። በውጭ ያለው ግዙፍ ኃይል በጋራ ራእይና የዓላማ አንድነት ተስማምቶ የተበታተነውን ተቃዋሚ ለማስተባበር ያልተቆጠበ ጥረት ማድረግ ግዴታው ነው። ወገኖቻችን ሲሞቱ ማልቀሱና መቅበሩ ዘላቂ መፍትሄ አያመጣም። አንዱ በሌላው ማመካኘቱ መቆም አለበት። በሃገርና በውጭ ያለው አለመግባባትና አብሮ ለመስራት አለመድፈር የሕብረተሰቡን አሰቃቂ የኑሮ ሁኔታ እንዳባባሰው ስለምናውቅ ከመወቃቀስ ባህል ወደ መተባበርና መስማማት ባህል እንሸጋገር።

ወደ ተሻሻለ ዲሞክራሳዊ አገዛዝ አማራጭ ሊይወስድ የሚያስችል፤ የተዋሃደም ባይሆን የተባበረ፤ በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን፤ የማህበረሰብ ክፍሎችንና ግለሰቦችን ያካተተ አማራጭ መስርቶ በእውቀትና በጥበብ የተቀናጀ፤ የማይበገርና የሃገሪቱን የሕዝብ ስርጭት የሚያንፀባርቅ ድርጅትና አመራር መፍጠር የወቅቱ ታሪካዊ ጥያቄና ግዴታ ሁኗል። ኢትዮጵያን እንደ ሃገር፤ ኢትዮጵያዊያንን እንደ ሕዝብ የምንቀበልና የምናከብር ሁሉ ደፍረንና ተባብረን ከተነሳን የሚያቆመን ኃይል አይኖርም። ለአንድ ለሚያልፍ ህይወት፤ ለሚያልፍ ዝናና ጥቅም ከመረባረብ ይልቅ ተከታታይ ትውልድ ለሚጠቅሰው ቁም ነገር የራሳችን የግል አስተዋፅኦ ብናደርግ ራሳችን አስከብረን ሃገራችንም እናስከብራለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

The post ምርጫ ለይስሙላ – አክሎግ ቢራራ (ዶር) appeared first on Zehabesha Amharic.

የሁለት አመት አስተማሪ ደሞዝ ለአንድ ቀን ፌሽታ በዲሲ (የሳሞራ የኑስ የሆቴል ወጪ በአንድ ቀን)

$
0
0

samora
ከግርማ ካሳ
ጀነራል ሳሞራ የኑስ፣ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኤታ ማጆር ሹም ናቸው። አንዳንዶች እንደዉም አገሪቷን የሚመሩት አቶ ኃይለማሪያም ሳይሆኑ እኝሁ ጀነራል ናቸው የሚሉም አሉ። ጀነራሉ በዋሽንግተን ዲሲ Mandarine Oriental Hotel እንዳረፉ ዘገባዎች ይጠቁማሉ። ጀነራሉ ለምን ወደ አሜሪካ እንደመጡ የታወቀ ነገር የለም። በዋሺንገትን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ድህረ ገጽ ስለ ጀነራሉ ጉብኘት በድህረ ገጹ ላይ ምንም ነገር አላሰፈረም። ምናልባትም የጀነራሉን ጉብኘት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላያውቀዉም ይችላል። ጀነራል በግላቸው ለግል ጉዳይ መጥተዉም ይሆናል። በምርጫው ወቅት አዲስ አበባ አለመገኘታቸው ፣ ምናልባት የሕክምና ችግርም አጋጥሟቸው ሊሆን ይችላል የሚል ግምትም በአንዳንዶች ዘንድ አለ።

ሆኖም አንድ ትኩረታችንን ሊሰብ የሚገባ ትልቅ ነጥብ አለ። ጀነራሉ ያረፉበት ሆቴል እጅግ ዘመናዊና በጣም ዉድ ሆቴል ነው። ለምሳሌ ማንዳሪን ሱት የሚባለው በቀን 1295 ዶላር ( 28 ሺህ ብር ) ነው የሚከፈለው። አምባሳደር ሱት 1495 ዶላር ( 31 ሺህ ብር ) ሲሆን ኦሪየንታል ሱት ደግሞ 2500 ዶላር ( 53 ሺህ ብር) ነው።

እንደዉ አንድ ኢትዮጵያ ያለ አስተማሪ በደንብ ተከፍሎት የወር ደሞዙ 2000 ብር ቢሆን፣ ጀነራል ሳሞራ ለአንድ ቀን ዲስ ፌሽታ የሚያወጡት ቢያንስ ለሁለት አመታት የአንድ አስተማሪን ደሞዝ የሚከፍል ነው ማለት ነው።

የጀነራሉን ወጭ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍሎ ከሆነ፣ ኤምባሲው አወቆት፣ እንግዲህ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ምን ደረጃ ላይ እንዳለች በገሃድ በድጋሚ የሚያሳየን ነው የሚሆነው።

በግላቸው ከሆነ ደግሞ ጄነራል ሳሞራ የመጡት፣ ከሁለት አመታት በላይ የአንድ አስተማሪ ደሞዝን ሊሸፍን የሚችል ገንዘብ፣ ለአንድ ቀን ሆቴል የመክፈል አቅም እንዴት ሊኖራቸው ቻለ የሚል ጥያቄ ይነሳል። ይሄም አሁን የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ለጥቂቶች ሲኦል እንደ ጀነራል ሳሞራ ላሉ በሙስና ለተጨማለቁ ዘራፊ ባለስልጣናትና መኮንኖች ግን ገነት መሆኗንም የሚያሳይ ነው።

The post የሁለት አመት አስተማሪ ደሞዝ ለአንድ ቀን ፌሽታ በዲሲ (የሳሞራ የኑስ የሆቴል ወጪ በአንድ ቀን) appeared first on Zehabesha Amharic.

በፍርሃት ውስጥ ያለው የኢሕአዴግ ሥርዓት የማዕከላዊ ዕዝ ወታደሮች ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መመሪያ አወረደ

$
0
0

የኢህአዴግ ስርአት የማእከላዊ እዝ ወታደሮች ከቦታ ወደ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መምሪያ እንዳወረዱላቸው ምንጮቻችን ገለፁ ሲል የደህሚት ድምጽ ዘገበ::
clash
በአዲ-ኮኮብ የሰፈሩት የማእከላዊ እዝ የበታች አመራር ወታደሮችና ተራ ወታደሮች ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር እንዳይገናኙና ወደ አዲ-ዳዕሮና ሸራሮ እንዳይንቀሳቀሱ ተከልክለው እንደሚገኙ የገለጸው የደህሚት ድምጽ እነዚህ የበላይ አመራሮች ሰራዊቱን በመሰብሰብ በአዲ-ዳዕሮ፤ አዲ ነብሪ ኢድ፤ አዲ-ሃገራይ፤ ሸራሮና አካባቢው በአጠቃላይ በአካባቢው የሚገኝ ህብረተሰብ የትህዴን አባል ሰለሆነ የምናጣራው ነገር አለን መንቀሳቀስ ክልክል ነው በማለት ትእዛዝ እንዳወረዱላቸው ለማወቅ ተችሏል።

በተጨምሪም- ወታደሮቹ በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ ጥላቻ እንዲያሳድሩና ከሱ ጋር እንዳይወግኑ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ቅስቀሳ ሲሰጥ የሰነበተ ሲሆን ስርአቱ ከህዝብ ተነጥሎ በጠምንጃ ሃይል ብቻ የቆመ እንደሆነ በሚገባ ሰለሚያውቅ ወታደሮቹ ደግሞ ስርአቱን በመተው ከህዝባቸው ጋር እንዳይወግኑ በመስጋት የመነጨ መሆኑን ወታደሮቹ በሚገባ እንደተረዱት ለመረጃ ምንጩ የደረሰው መረጃ አስረድቷል።

The post በፍርሃት ውስጥ ያለው የኢሕአዴግ ሥርዓት የማዕከላዊ ዕዝ ወታደሮች ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መመሪያ አወረደ appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: ሰውየው!! –የጆዜ ሞውሪንሆ ልዩ ገፅታ

$
0
0

jose-mourinho
‹‹አንድ ችግር አለብኝ›› ይላሉ ጆዜ ሞውሪንሆ፡፡ ‹‹እሱም በሥራዬ ሁሉ መሻሻሌን መቀጠሌ ነው፡፡ በሁሉም ነገሬ ለውጥ አለኝ፡፡ ጨዋታን የማነብበት መንገድ፣ ለጨዋታ የምዘጋጅበት ሁኔታ እንዲሁም ቡድኔን የማዘጋጅበት ዘዴ ሁሉ በብዙ ተሻሽያለሁ፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመልካም ሁኔታ ላይ እገኛለሁ፡፡ ያልተለወጥኩበት አንድ ነገር ግን አለ፡፡ ሚዲያውን የምጋፈጥበት መንገድ ያው ነው፡፡ አስመሳይ አይደለሁምና››

ቁጥሮችን መሰረት ባደረገ መመዘኛ ሰውየው በዓለም እግር ኳስ እጅግ ስኬታማው የክለብ አሰልጣኝ ናቸው፡፡ በአሰልጣኝነት በሰሩባቸው አራት ሀገሮ (ፖርቹጋል፣ ጣልያን፣ ስፔን እና እንግሊዝ) ሁሉ የሊግ አሸናፊ ሆነዋል፡፡ የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ሁለት ጊዜ አንስተዋል፡፡ የጆዜ መገለጫ ግን ይህ ብቻ አይደለም፡፡ በእግርኳሱ ዓለም እንደ እርሳቸው ብቻውን ሰዎችን በጉራ ለይቶ በክርክር የሚጠምድ አወዛጋቢ አሰልጣኝ አይገኝም፡፡ እንደ ሞውሪንሆ በተደጋጋሚ የባላጋራ ደጋፊዎችን በቁጣ እንዲነዱ በማድረግ የተካነ አሰልጣኝ አልታየም፡፡ ከዳኞች ጋር ይጨቃጨቃሉ፡፡ የእግርኳስ ማህበሩን በነገር ይወጋሉ፡፡ ጋዜጣዊ መግለጫዎቻቸውን ባልተጠበቀ መልኩ ይዘጋሉ፡፡ በሜዳ ጠርዝ ላይ ቆመው ግርግር ይፈጥራሉ፡፡ ከእግርኳሱ ሌላ የሞውሪንሆ ሁኔታዎች በራሳቸው ብዙ ትኩረት ይስባሉ፡፡

ባለፈው ሳምንት የቼልሲው አሰልጣኝ ለንደን ውስጥ በሚገኝ አንድ ስቱዲዮ ለሁለት ሰዓታት ፎቶግራፎችን መነሳት ነበረባቸው፡፡ ቀለል ያሉ ልብሶችን እየለዋወጡ በተደጋጋሚ ጃጓር የስፖርት መኪናቸው ውስጥ ገባ ወጣ እንዲሉ ሲጠየቁ ታዛዥ ነበሩ፡፡ ጆዜ በአለባበሳቸው ዘናጭ የሚባሉ አይነት ቢሆኑም ለልብሶች ብዙ ግድ እንደሌላቸው ይናገራሉ፡፡ ትኩረታቸው ከፋሽን ይልቅ ምኞታቸው ላይ ያመዝናል፡፡ በፎቶግራፎቻቸው ላይ የሚያሳዩት ገፅታ ምንም አይናገርም፡፡ እንደ ሁልጊዜው ሞውሪንሆአዊ ፊታቸው አይለወጥም፡፡ ሌላው ቀርቶ በአቅራቢያቸው በነበረ አንድ ስቱዲዮ ለራሱ የማስታወቂያ ፎቶግራፎችን ሲነሳ የቆየው ዲዲዬ ድሮግባ ድንገት ዘልሎ ገብቶ የእርሳቸውን ቀረፃ ያስተጓጎለ ሲመስል እንኳን ገፅታቸው ብዙ አልተቀየረም፡፡

የፎቶግራፍ ስነ ስርዓቱ አልቆ ሁሉም ሰው ለመመልከት በኮምፒዩተሩ ዙሪያ ተሰበሰበ፡፡ የሁሉም አይኖች ግን ከፎቶግራፎቹ ይልቅ ወደ ጆዜ እየተመለከቱ ሰውዬው የሚሉትን ለመስማት ይጠብቁ ነበር፡፡ ‹‹መጥፎ ነው?›› ምናልባት በእርግጥም እንደተጠቀሟቸው ቃላት ‹‹መጥፎ አይደለም›› ማለት ይሆን? ይህንን እርግጠኛ ሆኖ መናገር ያስቸግራል፡፡
የሞውሪንሆ ጠዋት የሚጀምረው በቼልሲ የልምምድ ማዕከል ኮብሃም ነው፡፡ ይህ ጊዜ አጠባበቃቸው አይዛባም፡፡ ሁልጊዜም ጠዋት 1፡30 ሰዓት ማዕከሉ ከደረሱ በኋላ በቀጥታ ወደ ቢሯቸው ገብተው ከውስጥ ይቆልፉታል፡፡ በዚያው ለሁለት ሰዓታት ያህል ይቆያሉ፡፡ ‹‹ብቻዬን የምሆንበት ጊዜ ያስፈልገኛል›› ይላሉ ሞውሪንሆ፡፡ ‹‹እንደምታውቁት በእግር ኳስ እኔ አዛውንት የሚያስብል ዕድሌ የለኝም፡፡ አሁን በ52 ዓመቴ ገና ለማሰልጠን ከፊቴ 20 ዓመታት ሊኖሩኝ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ራሴን ከወዲሁ ‹‹ነባር›› አድርጌ እመለከታለሁ፡፡ ምንም አያስፈራኝም፡፡ ብዙ የሚያስጨንቀኝ ነገርም የለም፡፡ ምንም አዲስ ነገር የሚፈጠርብኝ አይመስልም፡፡ አሁን በእጅጉ ሰክኛለሁ፡፡ ስሜቶቼን መቆጣጠር እችላለሁ፡፡ በድንገት በውድቅት ሌሊት እየባነንኩ ስለ አንደኛው ተጫዋቼ ጉዳት ወይም ስለ አንደኛው ጨዋታ ታክቲክ አልጨነቅም፡፡ ይልቅ የራሴ የሆነ የማሰቢያ ጊዜ ያስፈልገኛል፡፡ ሁኔታዎችን ከተለያየ አቅጣጫ መመዘን እና ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ቀድሜ መገመት ይኖርብኛል፡፡ ስለዚህ የግል ጊዜ ያሻኛል››

የሞውሪንሆ ወላጅ አባት ጆዜ ግብ ጠባቂ ነበሩ፡፡ እንዲያውም ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን በአንድ ጨዋታ የመሰለፍ ዕድል አግኝተዋል፡፡ የኋላ ኋላ እርሳቸው አሰልጣኝ ሲሆኑ ልጃቸው አልፎ አልፎም ቢሆን ያጅባቸው ነበር፡፡ አባት የሚያሰለጥኑት ቡድን ጨዋታ ሲኖረው እና ሰውየው በግጥሚያ መካከል ለተጨዋቾቻቸው መልዕክት ሲኖራቸው ወጣቱ ሞወሪንሆ በሜዳው ጠርዝ እየሮጠ መመሪያቸውን ያደርስላቸው ነበር፡፡ ልጁ በፖርቹጋል ሁለተኛ ዲቪዚዮን በሚሳተፍ ክለብ በተከላካይነት ሚና የመጫወት ዕድል ቢያገኝም እዚህ ግባ የሚባል የተጨዋችነት ዘመን ሳያሳልፍ ወደ አሰልጣኝነቱ ሙያ ለመቀላቀል ወሰነ፡፡ ሊዝበን ውስጥ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ ትምህርቱን ተከታትሎ መምህር ሆነ፡፡
የሞውሪንሆ የመጀመሪያ ሥራ ከውልደታቸው አንስቶ አካላዊ እና አዕምሯዊ እክል ያለባቸውን ልጆች ማስተማር ነበር፡፡ ‹‹በጣም ፈታኝ ነበር›› ይላሉ ጆዜ፡፡ ‹‹እነዚያን ልጆች ለማገዝ በቴክኒክ ረገድ ዝግጁ አልነበርኩም፡፡ ነገር ግን ስኬታማ የመሆኔ ምክንያቱ አንድ ነበር፡፡ ከእነርሱ ጋር የፈጠርኩት ከውስጥ የሆነ ትስስር፡፡ ፍቅር፣ ቅርበት እና ስሜትን መጋራት ያገኘኋትን የተአምር ያህል የምትቆጠር፣ አነስተኛ ስኬት አምጥቶልኛል፡፡ አንድ ዕድሜ ልኩን ወደ ህንፃ አናት ለመውጣት ፈቃደኛ ያልነበረ ልጅ አስታውሳለሁ፡፡ ሌላው ደግሞ እጅግ ቀላል የሚባሉ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን በአንድነት ማከናወን የተሳነው ነበር፡፡ ልጆቹ የተለያየ ችግር የሳባቸው ነበሩ፡፡ ከሁሉም ጋር የነበረኝ የውስጥ ትስስር ግን በብዙዎቹ ላይ መልካም ለውጥ እንድናመጣ አግዞኛል፡፡

‹‹ከዚያ በኋላ ከ16 ዓመት በታች ታዳጊዎችን ማሰልጠን ጀመርኩ፡፡ አሁን ደግሞ የዓለም ምርጥ ተጨዋቾችን አሰለጥናለሁ፡፡ በሥራዬ ትልቁ ነገር በቴክኒክ ራሴን ማዘጋጀቱ ሳይሆን ከተጨዋቾቼ ጋር የምፈጥረው ከውስጥ የሆነ ቁርኝት ነው፡፡ በእርግጥ እውነት እና ነገሮችን በጥልቀት የምትመለከትበት አቅም ያስፈልግሃል፡፡ ነገር ግን የእነዚህ ሁሉ ቁልፉ የምትፈጥረው ጠንካራ ግንኙነት ነው፡፡ ቁርኝትህ በግለሰብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን ከቡድኑ ጋርም ሊሆን ይገባል፡፡ ምክንያቱም የሚያሸንፍልህ ቡድን ነው››
‹‹ቡድን›› የሚለው ቃል በጆዜ ቃለ ምልልሶች ውስጥ በብዛት ይደመጣል፡፡ አሰልጣኙ ባለተሰጥኦ ተጨዋቾችን ወደ ቡድን ተጨዋችነት የሚለውጡት እንዴት ነው? ዕድሜያቸው 21 ዓመት እንኳን ሳይሞላ ለከፍተኛ ደመወዝ ባለቤት የሚበቁትንስ ከዋክብት የሚያስተዳድሩት በምን መልኩ ይሆን? ‹‹ትክክል ነው›› ይላሉ ጆዜ ድምጻቸው ከፍ እያደረጉ፡፡ ‹‹ቀደም ባለው ጊዜ ተጨዋቾች ወደ እግርኳስ ዓለም ሲመጡ ሃሳባቸው ጫማቸውን ሲሰቅሉ ሀብታም መሆን ነበር፡፡ የአሁኖቹ ደግሞ ባለሁበት መሆን የሚፈልጉት ገና የመጀመሪያ ጨዋታቸውን እንኳን ሳያደርጉ ነው››

እግርኳስ እንደ ሌሎቹ የጥበብ ዘርፎ ሁሉ የራሱን ዝነኞች ይፈጥራል፡፡ ለፊልም ተዋናዮች ከሚሰጠው ትልቅ የእውቅና ሽልማት አካዳሚ አዋርድ ጋር የሚነፃፀረው ባሎንዶር በእግርኳስ ግለሰቦች የሚገዝፉበት ነው፡፡

ሞውሪንሆ ራሳቸው እንደሚመሰክሩት ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ከአርሰናሉ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር ጋር የሚያስማማቸው ብዙ ነጥብ የላቸውም፡፡ ‹‹ነገር ግን ቬንገር ንድ ጥሩ ነገር ተናግሯል፡፡ በባሎንዶር አስፈላጊነት አይስማማም፡፡ ትክክል ነው፡፡ አሁን በእግር ኳስ የሰዎች ትኩረት ከቡድን ይልቅ ግለሰቦች ላይ እየሆነ ነው፡፡ ሁልጊዜም ትኩረታችን የአንድ ተጨዋች ብቃት እና ስታስቲስቲክ ላይ ሆኗል፡፡ የትኛው ተጫዋች ብዙ እንደሚሮጥ መነጋገር እናበዛለን፡፡ በአንድ ጨዋታ አንተ 11 ኪሎ ሜትር እኔ ዘጠኝ ኪሎ ሜትር ከሮጥን አንተ ከእኔ የተሻልክ ነህ ማለት ነው? ላይሆን ይችላል፡፡ ምናልባት ከ11ዱ ኪሎ ሜትር ይልቅ ዘጠኙ ይበልጥ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል›› ብለው ይስቃሉ አሰልጣኙ፡፡
‹‹ለእኔ እግርኳስ በጋራ የምትወዳደርበት ነው፡፡ ለግለሰብ ቦታ አለን በተለይ ቡድናችንን የሚያበረታ ከሆነ፡፡ ነገር ግን ግለሰቡ ለቡድኑ መስራት አለበት እንጂ ቡድኑ ለእርሱ ሊለፋለት አይገባም፡፡ ትልቅ ተጨዋች ሲመጣ ቡድኑ ቀደም ብሎም አለ፡፡ ኮሎምቦስ አሜሪካንን እንዳገኘው አንድ ተጨዋች ቡድኑን ሊያገኝ አይችልም፡፡ እንደ አሰልጣኝ ለተጨዋቾችህ ይህንን ሁልጊዜ ማስታወስ ይኖርብናል፡፡ በንግግር እና በቃላት ሳይሆን ተጨዋቹ ሃሳብህን እንዲገነዘብ ጥሩ ግንኙነት መፍጠር ያስፈልጋል፡፡ ለተጨዋች መስጠት የማትችለው ተፈጥሯዊ ተሰጥኦን ነው፡፡ ቡድኑ ከተጨዋቹ ምን ይፈልጋል? ተጫዋቹ ብልህ እና እንዲሻሻል ከአንተ የሚደረግለትን እገዛ የሚፈልግ አይነት ነው? ቡድኑ ከእርሱ እንደሚተልቅ ሲነገረው የማይሰማ ራስ ወዳድ እና ረባሽ ነው? እነዚህ ሁሉ አይነት ባህሪያት ያላቸው ተጨዋቾች ገጥመውኛል፡፡ የትም ቦታ እንከን የለሽ የሚባል ስብስብ አይገኝም፡፡ ከተጫዋች እጅግ ወሳኙ ነገሩ ምንድነው? ብላችሁ ከጠየቃችሁኝ ተሰጥኦ ነው፡፡

‹‹ለምሳሌ አንድ ተጨዋች ነበረኝ፡፡ ስሙን አልነግራችሁም፡፡ ለዋናው ቡድኔ እንዲጫወት ዕድል ሰጠሁት፡፡ ለሁለት ሳምንታት እንደተጫወተ አባቱ ምስሪያ ቤታቸውን ለቀቁ፡፡ እናቱም ሥራቸውን ተዉ፡፡ አብረውት መኖር ብቻ ሳይሆን የእርሱን ህይወት መኖር ጀመሩ፡፡ በተጫዋቹ ዙሪያ ትልልቅ ውሳኔዎችን የሚያሳልፉት እነርሱ ሆኑ፡፡ እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡››

ተጫዋቹ ለመጨረሻ ምን ሆነ? ጆዜ ምላሽ ለመስጠት ቃላት አልተጠቀሙም፡፡ ትከሻቸውን ሰበቁ፡፡ የልጁ የእግርኳስ ህይወት የኋሊት ተጓዙ፡፡
‹‹ይህ ልሰጣችሁ ከምችላቸው 1 ሺ ምሳሌዎች አንድ ብቻ ነው፡፡ ተጫዋቾች ጥሩ ወላጆች ካሏቸው ዕድለኞች ናቸው፡፡ መልካም ወኪል ካገኙም እንዲሁ ዕድለኞች ናቸው፡፡ በዚህ ላይ ትምህርትም ያስፈልጋቸዋል፡፡ አንድ ሌላ ተጫዋቼ ትዝ ይለኛል፡፡ አንድ ቀን አዲስ መኪና እያሽከረከረ መጣ፡፡ ደግሞ ሌላ? ለምን? ለመሆኑ መኖሪያ ቤት አለህ? ብዬ ጠየቅኩት፡፡ አልነበረውም፡፡ ይልቁን እንዲህ ሲል መለሰልኝ፡፡ ይህንን መኪና እኔ አልገዛሁትም፡፡ አባቴ በነፃ የሊዝ ዕድል ወሰደልኝ፡፡ እኔም ሰነዱ ላይ ፈረምኩ፡፡ ይሄን ጊዜ ሊሊ ምን እንደሆነ ታውቃለህ? ብዬ ደግሜ ጠየቅኩት፡፡ እርሱም በነፃ መውሰድ ማለት ነው አለኝ፡፡ አይደለም፡፡ እስኪ ተቀመጥ፡፡ ብዬ ስለ ሊዝ አስረዳሁት፡፡ ምንም አላወቀም ነበር፡፡ ምክንያቱም ማንም ሰው አላብራራለትም ነበር››

‹‹እኔ ብዙ ሊባል የሚችል ገንዘብ በእጄ የገባው በ2003 በፖርቶ ለሁለተኛ ጊዜ ኮንትራት ስፈርም ነው፡፡ በወቅቱ ዕድሜዬ 30ዎቹ ውስጥ የነበረ ሲሆን ባለትዳርም ነበርኩ፡፡ ወጣቶቹ ተጫዋቾች ይህንን ሁሉ ገንዘብ ሊያገኙ ዕድሜያቸው 16፣ 17፣ 19 ወይም 20 ዓመት ቢሆን ነው፡፡ በገንዘቡ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንኳን አያውቁም፡፡››
‹‹በቼልሲ ተጨዋቾችን በተለያዩ ሁኔታዎች የሚያግዝ ዲፓርትመንት አለን፡፡ ስለገንዘብ ሁኔታ የሚያስረዷቸው ሰዎች በባንክ አሉ፡፡ ቤት መግዛት ብትፈልግ ውል የምትፈፅመው ከትክክለኛው ሰው ጋር መሆኑን የሚያረጋግጡልህ ይኖራሉ፡፡ ወደ ክለባችን የሚመጡ ወጣቶች መኪና መግዛት አይኖርባቸውም፡፡ ስፖንሰራችን መኪና አምራቹ ኦዲ መኪና ይሰጣቸዋል፡፡ ተጫዋቾች እንዲህ አይነት እንክብካቤ ያሻቸዋል፡፡ ምክንያቱም ያለንበት ዓለም ውስብስብ ነው፡፡

ስለዚህ ጆዜ ራሳቸውን እንደ አባት ኃላፊነት ሲወስዱ እያገኙት ይሆን? ‹‹ይህ ኃላፊነት ነው›› ሲሉ ይመልሳሉ፡፡
ሞውሪንሆ እና የትዳር አጋራቸው ማቲልደ በፍቅር የተቆራኙት ገና ለጋ ወጣቶች ሆነው ሲሆን በፖርቹጋሏ ሴቱባል መኖሪያ ቤታቸውን የሚለየው አንድ ጎዳና ብቻ ነበር፡፡ ለትዳር ለ26 ዓመታት የቆዩት ጥንዶች ሁለቱን የአብራካቸው ክፋዮ ማቱልደ እና ጆዜ ሲሉ ሰይመዋቸዋል፡፡
FOOTBALL/ITALIAN CHAMP/ATALANTA BERGAMASCA v INTER MILANO
ስኬታማው ጆዜ የአሰልጣኝነት ህይወታቸው የጀመረው በ2000 የፖርቹጋሉን ቤንፊካ ሲረከቡ ይሁን እንጂ ቀደም ሲል ከቦቢ ሮብሰን ጋር መጀመሪያ በተርጓሚነት በኋላም በአሰልጣኝ ረዳትነት በስፖርቲንግ ሊዝበን፣ ፖርቶ እና ባርሴሎና ሰርተዋል፡፡ በቤንፊካ ከተሾሙ በኋላ ከሶስት ወራት በላይ አልቆዩም፡፡ ከክለቡ ፕሬዝዳት ጋር በፈጠሩት አለመግባባት ስራቸውን ለቀቁ፡፡ ቀጣዩ ስራቸው በኡናዮ ደ ሌይሪያ ነበር፡፡ ከዚያ ወደ ፖርቶ ሲመጡ የሀገሪቱን ሊግ ሁለት ጊዜ፣ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ዋንጫን እና የቻምፒዮንስ ሊግን አሸነፉ፡፡ ይሄ ስኬታቸው ወደ እንግሊዝ መራቸው፡፡ በቼልሲ በ2004/05 እና 2005/06 በተከታታይ ፕሪሚየር ሊጉን ድል ነሱ፡፡ የኤፍኤ ካፕ እና የሊግ ካፕን ሁለት ጊዜ አሸነፉ፡፡ የኢንተር ሚላን አሰልጣኝ ሆነውም ሴሪአውን ሁለት ጊዜ በተከታታይ ድል አድርገዋል፡፡ በ2010 ወደ ሪያል ማድሪድ አምርተው ኮፓዴል ሬይ እና ላሊጋ በተከታታይ ዓመታት አሸንፈዋል፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ በ2013 በድጋሚ ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ ተመልሰዋል፡፡

ሞውሪንሆ የቅርብ ጓደኛዬ ብለው የሚጠቅሱት ሩይ ፋሪያን ነው፡፡ እኚህ ሰው ከጆዜ ጋር ከቤንፊካ የመጀመሪያ ሥራቸው አንስተው በየክለቡ አብረዋቸው ሲዟዟሩ የቆዩ ናቸው፡፡ ‹‹ሩይ አንድ የሚናገሩት ነገር አለች›› ይላሉ ሞውሪንሆ እየሳቁ፡፡ ‹‹በዚህች ዓለም ምርጥ ህይወት ማለት አሸናፊ አሰልጣኝ የሚኖረው ነው ይላል፡፡ ትክክል ነው፡፡ ሆኖም በዚህ ሀገር ተከታታይ ጨዋታዎች እናደርጋለን፡፡ ስለዚህ በአንዱ ጨዋታ ውጤት ስሜት ውስጥ መቆየትን አትችልም፡፡ 5-3 ተሸንፈን በቀጣዩ ቀን የልምምድ ፕሮግራም አለ፡፡ ከሁለት ወይም ሶስት ቀናት በፆፄላ ደግሞ ሌላ ጨዋታ ይኖረናል፡፡ ከዚህ ስሜቴን ውጬ ሽንፈት እና ድልን መቀበል አለብኝ፡፡

‹‹አሰልጣኝ እጅግ ወሳኙ ሰው አይደለም፡፡ በክለብ ውስጥ እጅግ አስፈላጊው አካል ደጋፊዎች ናቸው፡፡ ባለቤቶቹ ቀጥለው ይቀመጣሉ፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ተጨዋቾች አሉ፡፡ እኔ የምመጣው ከዚህ በኋላ ነው፡፡ ሆኖም ሁሉም ሰው ትኩረቱን ያደረገው አሰልጣኝ ላይ ነው፡፡ ተጨዋቾችም አንተን ይመለከታሉ፣ ይታዘቡሃል፡፡ ለነገሮች ምላሽ የምትሰጥበትን መንገድ ማየት ይፈልጋሉ፡፡ እርጋታህንም እንደዚሁ ይመዝናሉ፡፡ በክለብ የሚሰሩ ሰዎችም እንደዚህ በጥንቃቄ ይከታተሉሃል፡፡ ምላሻቸውም አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ይሆናል፡፡ ደጋፊዎችም አሰልጣኞችን ይከታተላሉ፡፡ ከሽንፈት ማግስት ለቀጣዩ ጨዋታ ዝግጁ መሆንህን ማረጋገጥ ይፈልጋሉ፡፡ እንዲህ አይነቱ ሁኔታ የሚቆጣጠር አቅም አለኝ፡፡ ሰዎች በአሉታዊ እና አዎንታዊ አስተያየታቸውን በሚዛናዊ መልኩ ማስኬድ እችላለሁ፡፡ በቤቴ ጥሩ አይደለሁም፡፡ እነርሱ በሚገባ ያውቁኛል፡፡ ስሜቴን ልደብቅ አልችልም፡፡ ጠንቅቀው ያውቁኛል፡፡››

ጆዜ ከእግርኳስ ወጣ ብሎ በቅርቡ የገጠማቸው ለየት ያለ ነገር ካለ ተብለው ሲጠየቁ በworld food progeramm Ambasador Agminst Hunger ተልዕኮ የጎበኟትን አይቮሪኮስት ይጠቅሳሉ፡፡ ‹‹ከባለቤቴ እና ልጆቼ ጋር ሆኜ የተመለከትኩት ሁሉ ልዩ ተሞክሮ ሆኖልኛል፡፡ ድህነትን እናውቃለን፡፡ ነገር ግን ከእውነታው ጋር ቀጥተኛ ፍጥጫ ውስጥ መግባት ለየት ይላል፡፡ በአዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ጎኑ ይህንን ከመሰለው እውነታ ጋር መጋፈጥ እና ሚና መውሰድ ልዩ የኩራት ስሜት ይፈጥራል፡፡››
አሰልጣኙ እና ባለቤታቸው በሀገራቸው ፖርቹጋልም የካቶሊክን የምግብ ፕሮግራ በሴቱባል ያግዛሉ፡፡ ‹‹ሆኖም ከቤተሰባችን መርህ አለን፡፡ የምናደርገውን ሁሉ የምናደርገው ሰዎች ስለ እኛ ብዙ እንዲያውቁ አይደለም፡፡ ይህንን የምንሰራው ማድረግ ስለምንችል ነው፡፡ ወንድ እና ሴት ልጆቻችን እኛ ወላጆቻቸው ምን አይነት መልካም አጋጣሚዎች የተፈጠሩልን ሰዎች እንደሆንን እንዲያውቁ እንሻለን ሌሎች ብዙ እገዛ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች እንዳሉ እንዲገነዘቡም እንፈልጋለን››

ሞውሪንሆ ሃይማኖተኛ እንደሆኑ ያስባሉ፡፡ ‹‹እምነት አለኝ፡፡ ሁልጊዜም እፀልያለሁ፡፡ ሁልጊዜም ከፈጣሪ ጋር እነጋገራለሁ፡፡ በየዕለቱ ወደ ቤተክርስቲያን አንሄድም፡፡ በየሳምንቱም ቢሆን አይሳካልኝም፡፡ ሆኖም መሄድ እንዳለብኝ ሲሰማኝ እሄዳለሁ፡፡ ፖርቹጋል ውስጥ ከሆነ ግን በየዕለቱ እሄዳለሁ፡፡››
ጆዜ የሚፀልዩት ለማን ይሆን? ‹‹ለቤተሰቤ፣ ለልጆቼ፣ ለባለቤቴ፣ ለወላጆቼ፣ ስለደስተኛነቴ እና መልካም የቤተሰብ ህይወት እፀልያለሁ፡፡ እውነቴን ብነግራችሁ ግን ከፈጣሪዬ ጋር ለመነጋገር ወደ ቤተክርስቲያን ስሄድ ርዕሴ እግርኳስ አይሆንም፡፡ በፍፁም!››

አሰልጣኙ ራሳቸውን መልካም ሰው አድርገው ያስባሉ? ‹‹ይመስለኛል፡፡ እንደዚያ ለመሆን እሞክራለሁ፡፡ ከቤተሰቦቼም ጋርም ሆነ ከጓደኞቼ ጋር ችግር የለብኝም፡፡ ለቤተሰቡ መልካም ሰው ነኝ፡፡ ጥሩ ጓደኛም ነኝ፡፡ የማላውቃቸውን ሰዎች እንኳን ለማገዝ እነሳለሁ፡፡ ስህተቶች እሰራለሁ? አዎን፡፡ የሥራ ባህሪዬ የፉክክር ብቻ አይደለም፡፡ ስሜታዊነትንም ይቸምራል፡፡ በዚህ ምክንያት አንዳንድ ጊዜ ሰዎችን ልትደርስባቸው ትችላለህ፡፡ ሆኖም ፕሮፌሽናል ህይወትህ ከአንተነትህ የሚገለፀው ከፊሉን ነው፡፡ የግለሰብ ስብዕና ከዚያም የላቀ ነው፡፡››

ሰውዬው የፕሮፌሽናል ህይወታቸውን ከቤተሰባቸው አኗኗር ሊለዩት ብዙ ይጥራሉ፡፡ ከባለቤታቸው ጋር ስለ እግርኳስ አያወሩም፡፡ ‹‹የእርሷ ዓለም ሌላ ነው፡፡ በምወደው ክለብ እና በምወደው ቦታ እንድቆይ እንዲሁም ከሚመቹኝ ሰዎች ጋር እንድሰራ ትመክረኛለች፡፡ምክንያቱም በዚህ መልኩ የቤተሰባችን ህይወት መልካም ይሆናል፡፡ ነገር ግን ይህ ቀላል አይሆንም፡፡ የቤተሰቤን ህይወት ከእግር ኳስ ለመነጠል ብሞክርም የማይሳካበት አጋጣሚ ይኖራል፡፡ በወሳኝ ጨዋታ ሽንፈት ከገጠመኝ የፊቴን ገፅታ ቀላል አድርጌ ወደ ቤቴ ለመሄድ እሞክራለሁ፡፡ ነገ ሌላ ቀን ነው፡፡ በቃ ይህ አንድ የእግርኳስ ጨዋታ ብቻ ነው እያልኩ ለራሴ እናገራለሁ፡፡ ነገ ሌላ ቀን ነው፡፡ በቃ ይህ አንድ የእግርኳስ ጨዋታ ብቻ ነው እያልኩ ለራሴ እናገራለሁ፡፡ ሆኖም ቤቴ ስገባ እነርሱ ብሰው አኩርፈው አገኛቸዋለሁ›› ብለው ጆዜ ይስቃሉ፡፡ ‹‹ስለ እኔ እነርሱ ያዝናሉ››

በእንግሊዝ የእግርኳስ ትልልቅ ክለቦች ባሉበት ከተማ የሀብታሞች መኖሪያ ብዙዎቹ የክለቡ ተጨዋቾች እና አሰልጣኞች መኖሪያ ቤቶች አይጠፉም፡፡ በቼሻየር ዳርቻ በምትገኘው አልደርሌይ ኤጅ መረቡን የጣለ አሰልጣኙን ጨምሮ ማንቸስተር ዩናይትድ የቡድን አባላት ብዙዎቹን ይይዛል፡፡ በኮብሀም አካባቢም ያንዣበበ ሁሉ በርከት ያሉ የቼልሲ ተጨዋቾችን ያገኛል፡፡ ሞውሪንሆ ግን እዚህ አታገኟቸውም፡፡ ከቤተሰባቸው ጋር በቤልራቪያ አካባቢ ይኖራሉ፡፡ ቤተሰባቸው ቦታውን እንደሚወደው ይናገራሉ፡፡ ‹‹እኔም እወደዋለሁ›› ከማድሪድ ወይም ሚላን በተለየ ለንደን ትመቻቸዋለች፡፡ ‹‹ጤናማ ህይወት›› መኖር የሚችሉባት ከተማ ነች፡፡

ሞውሪንሆ በመኖሪያቸው አካባቢ ባለ ጎዳና የእግር ጉዞ ያደርጋሉ፡፡ ‹‹በአምስት ደቂቃዎች ውስጥ›› የቼልሲ ደጋፊ፣ የቶተንሃም ደጋፊ፣ የአርሰናል ደጋፊ ያገኛሉ፡፡ ‹‹ሌላው ቀርቶ የሊቨርፑል ወይም የዩናይትድ ደጋፊዎችም አገኛለሁ፡፡ ይህ ያስደስተኛል፡፡ በሰራሁባቸው ሌሎች ከተሞች በእግርህ የምትጓዘው በክለብህ ደጋፊዎች ታጅበህ ነው፡፡ በሚላን 50 በመቶ የኢንተር 50 በመቶ የኤሲ ሚላን ደጋፊዎች ይኖራሉ፡፡ ምናልባት ማድሪድ 70 በመቶ ሪያል 30 በመቶ አትሌቲኮ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በፖርቶ 100 በመቶ ናቸው፡፡ ማንም ሰው ወደ እኔ ቢመጣ ላደምጠው ዝግጁ ነኝ፡፡ ስለ እግር ኳስ ሊያስተምረኝ ቢፈልግ ግን አልሰማውም፡፡››

‹‹የለንደን ነዋሪዎች ሰውን በመረበሽ እና ባለመረበሽ መካከል ያለውን ልዩነት ይገነዘባሉ፡፡ ሰዎች ነፃነት እና ክብር እንደሚፈልጉ ያውቃሉ፡፡ እዚህ እኔ ከተረበሽኩ በእርግጠኝነት ሲያገኙኝ እንድፈርምላቸው እና አብረውኝ ፎቶግራፍ መነሳት ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን ተመግቤ እስክጨርስ ይጠብቁኛል፡፡ መደብሮች ውስጥ ሊያገኙኝም ይጠብቁኛል እንጂ አይረብሹኝም፡፡ በመንገድ ስራመድም እንደዚያው ነው፡፡ በእንግሊዝ በቡድንህ ውጤት የተበሳጨ ደጋፊ ከቤተሰብህ ጋር እየተራመድክ መጥቶ አይጨቃጨቅህም፡፡ ይህ አይታሰብም፡፡ በማድሪድ እና ሚላን ግን ሁልጊዜም እንዲህ አይነት ነገሮች ይገጥሙሃል፡፡››

‹‹ሁሉም ደጋፊ አሰልጣኝም ነው›› ይላሉ ጆዜ በሁኔታው ደስተኛ አለመሆናቸውን በሚያሳጣ የፊት ገፅታ፡፡ ሰዎች እግር ኳስን በተጋነነ መልኩ ይወስዱታል፡፡ ያለጥርጥር እኔ እግር ኳስን እወድዳለሁ፡፡ ሆኖም እኛ ፕሮፌሽናሎቹ እግርኳሱን ሁሉ ነገራችን ካረግነው ችግር ውስጥ ነን ማለት ነው፡፡ ለደጋፊውም ተመሳሳይ ነው፡፡ በፖርቹጋል አንድ ሰው በህይወቱ እናቱን እና የሚደግፈውን ክለብ ሊቀይር እንደማይችል ሲናገር ታደምጣላችሁ፡፡ የእግርኳስን ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ባህላዊ ጉልበት እገነዘባለሁ፡፡ ነገር ግን አንድ የእግር ኳስ ተጨዋች ከዓለም 100 ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ተመዝግ በፎርብስ መፅሔት እንዴት እውቅና እንደሚሰጠው አይገባኝም፡፡ ለዚያውም አንድ ሳይሆን ሁለት ተጨዋቾች ተመሳሳይ ዕድል አግኝተዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዝርዝሩ 360ኛ ደረጃ ላይ ተገኝቷል፡፡ ሊዮኔል ሜሲም 45ኛ ሆኗል፡፡

‹‹ይህ ቀልድ ነው፡፡ እኛ የማንንም ህይወት ከአደጋ አናድንም፡፡ ሰዎች ቡድናቸው ሲሸነፍ ከአምስተኛ ፎቅ ራሳቸው ሊወረውሩ እንደሚችሉ አውቃለሁ፡፡ እንግዲህ የሚያደርገው ሰውዬ ችግር አለበት፡፡ የእግርኳስ ተጨዋች ወይም አሰልጣኝን ከሳይንቲስት ወይም ዶክተር ጋር እንዴት ልታነፃፅር ትችላለህ? አይነፃፀሩም፡፡››

ሞውሪንሆ በእንግሊዝ እግርኳስ የቅርብ ወዳጅ እንደሌላቸው ይናገራሉ፡፡ ‹‹አንዳንዶቻችን እንወደዳለን እንግባባለንም፡፡ ሆኖም ጥብቅ ወዳጆ አይደለንም፡፡ ሆኖም ሞውሪንሆ ያለ ገደብ የሚያደንቋቸው አንድ ሰው አሉ- ሰርአ ሌክስ ፈርጉሰን፡፡ ሁለቱ ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት በ2007 ፖርቶ ማንቸስተር ዩናይትድን ከቻምፒዮንስ ሊግ ሲያሰናብተው ነበር፡፡ ‹‹የዚያን ታላቅ ሰው ሁለት ገጽታ ያስተዋልኩት ያን ጊዜ ነበር›› ይላሉ ሞውሪንሆ፡፡ ‹‹አንደኛው መልካቸው ተፋላሚ ነው፡፡ ሰውዬው ለማሸነፍ ሁሉንም አይነት መንገዶች የሞከሩ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሁልጊዜም በመርህ የሚጓዙ ነበሩ፡፡ ተጋጣሚን ያከብራሉ፡፡ እነዚህ ሁለት መልኮች ለእኔ እጅግ አስፈላጊዎች ነበሩ፡፡
‹‹በእኛ ባህል፣ በፖርቹጋል እና ላቲን ባህል ሁለት መልክ የለንም፡፡ በእግርኳስ አላማችን ማሸነፍ ብቻ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ሌላ መልክ አይኖረንም፡፡ በቻምፒዮንስ ሊግ ዩናይትድን ስናሸንፍ በሰር አሌክስ ፊት ላይ የተመለከትኩት ማራኪ ገፅታ ለእኔ ቢሆን ብዬ የተመኘሁት ነበር፡፡ ይህንን ለማድረግ እሞክራሁ፡፡››

የሞውሪንሆ ጥረት እና ፈተና ሁልጊዜም በሌሎች ዘንድ ቦታ የሚያገኝ አይመስልም፡፡ ብዙዎች ጆዜን ‹‹ቀጣፊው›› ይሏቸዋል፡፡ ‹‹እኔ ራሴን እንዲዚያ ነኝ ብዬ አላምንም›› ይላሉ አሰልጣኙ፡፡ ጆዜ እርሳቸውን በዚህ መልኩ የሚጠቅሱ ፅሑፎችን አንብበው ያውቃሉ? ‹‹አዎን! እንደዚያ እንደሚሉኝ አውቃለሁ፡፡ በእርግ አልፎ አልፎ የምሰጣቸው አስተያየቶች እንደዚያ ሊያስመስሉኝ እንደሚችሉ እረዳለሁ፡፡ ከዚህ ያለፈ ነገር የለም፡፡››

ሁሉም አሰልጣኝ የዳኝነት ውሳኔዎች ላይ ቅሬታውን ያሰማል፡፡ ፍፁም ቅጣት ምት ነበር፤ በፍም አልነበረም፤ ዕድለኞች አልነበርንም የመሳሰሉ ንግግሮች በተደጋጋሚ ይደመጣሉ፡፡ ሞውሪንሆ ግን የቅሬታ አቀራረብን በጥበራ የማድረግን ደረጃ አሳድገዋል፡፡ ዳኞች ብቻ ሳይሆኑ የቀረው ዓለም ሁሉ የሞውሪንሆ ተቃራ መሆኑን ማሳየት ይፈልጋሉ፡፡ በዚህም የቡድናቸውን ስነ ልቦና ከፍ ሲያደርጉ እግረ መንገዳቸውንም ስኬታማ ሳይሆኑ ሊረዷቸው የሚችሉ ሰበቦችንም ያስቀምጣሉ፡፡

ሞውሪንሆ ሁልጊዜም ይበልጥ ሃያል ሆነው በሚቀርቡባቸው የጋዜጣዊ መግለጫ መድረኮች ብንነግራቸው ለተለያዩ ወገኖች ያላቸውን ዝቅ ያለ ግምት ለማንፀባረቅ ይሞክራሉ፡፡ ተጋጣሚዎቻቸውን፣ የእግርኳስ ባለስልጣናትን፣ ሪፖርተሮችን ሁሉ ያጣጥላሉ፡፡ አድናቆታቸው እንኳን በራሳቸው የተሟሉ አይደሉም፡፡
ይህ የፈርጉሰን ባህርይ ነው፡፡ ብዙ የፃፈ ጋዜጠኛ አለ፡፡ ‹‹ጆዜ ለሰዎች መልካም ከሆነ ሰዎቹ ስጋቶቹ አይደሉም ማለት ነው››

ሞውሪንሆን ቃለ ምልልስ ሲያደርግ የነበረው ሰው የዚህን ጋዜጠኛ አስተያየት ሲያስታውሳቸው ጆዜ ክፉኛ መከፋታቸው ያስታውቅባቸው ነበር፡፡ ‹‹በፍፁም! ሰዎች አድናቆት የተገባቸው ሆነው ሲገኙ አደንቃቸዋለሁ፡፡ ለምሳሌ ከሽንፈት በኋላ ድንቅ ዳኛ እያልኩ መናገር እወዳለሁ፡፡››

ጆዜን ሰዎች ሁልጊዜም በተሳሳተ መንገድ ይረዷቸው ይሆን? በቃለ ምልልስ አብሯቸው የቆየው ጋዜጠኛ አሰልጣኙን በዓለም ላይ እውነተኛ ስሜታቸውን ከሚያስነብቡ ኮሜዲያኖች አንዱ ያደርጋቸዋል፡፡ ለዚህም ሃሳቡን እንዲህ ይገልፃል፡፡ ‹‹ሞውሪንሆ በዝምታ ያስተውለኛል፡፡ ከዚያም በፊቱ ገፅታ በዝግታ የደመቀ ፈገግታ ያስነብባል፡፡››

The post Sport: ሰውየው!! – የጆዜ ሞውሪንሆ ልዩ ገፅታ appeared first on Zehabesha Amharic.


አነጋጋሪው የጥላሁን ገሰሰ መጽሐፍና የባለቤቱ ሮማን በዙ ምላሽ

$
0
0

Tilahun and Roman Bezu
በጋዜጠኛ ዘከርያ መሀመድ የተጻፈውና ‹‹ጥላሁን ገሠሠ የሕይወት ታሪክና ምስጢር›› በሚል ርዕስ ለንባብ የበቃውን መጽሐፍ አስመልክቶ የተለያዩ ሀሳቦች እየተነሱ ነው፡፡ ዘከርያ በቁም ነገር መጽሔት 202ኛ እትም ላይ በሰጠው ቃለምልልስ መጽሐፉን ለማዘጋጀት ዋና ምክንያት የሆነው በጥላሁን ገሠሠ ዙሪያ የሚነሱ የተዛቡ ታሪኮችን ማጥራት መሆኑን መግለጹ የሚታወስ ነው፡፡ ይሁንና የጥላሁን ባለቤት ወ/ሮ ሮማን በዙ ‹ከመጽሐፉ መታተም ጀርባ ሌላ ታሪክ አለ› ትላለች፡

ቁም ነገር፡- ጋዜጠኛ ዘከርያ የጻፈው መጽሐፍ ለንባብ ከመብቃቱ በፊት እየተጻፈ እንደሆነ ታውቂ ነበር?
ወ/ሮ ሮማን፡- አንድ ጊዜ በጥላሁን ዙሪያ ኮሚቴውን ለማመስገን አንድ ዝግጅት ቤታችን ውስጥ ተዘጋጅቶ በነበረበት ወቅት ንጉሤ የሃረሩ መጥቶ ነበር፡፡ እሱ ነው መጀመሪያ የነገረኝ፡፡ ‹ዘከርያ የሚባል ሠው እኔን አነጋግሮኛል፤ በጥላሁን ዙሪያ መጽሐፍ እያዘጋጀ ነው ለምን ባለቤቱን አታነጋግራትም ብየው ነበር› አለኝ፡፡ ከዚያ ወዲያው ደወለለትና ከኔ ጋር አገናኘን፡፡ እኔም ‹‹ከበፊቱ መጽሐፍ የተለየ ነገር አለኝ የምትል ከሆነ በአካል እንገናኝና እናውራ፤ ጥላሁን ሠፊ ነው፤ ብዙ የምንልለት ነገር ይኖራል፡፡ የጥላሁን ነገር በአንድ
መጽሐፍ የሚያልቅ አይደለም፤ ስለዚህ አዲስ ነገር ካለህ እንገናኝና አብረን እንሰራለን›› አልኩት፡፡ እሽ ተባብለን ስልኩን ዘጋሁት፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ጠፋ፡፡

የሚሆነው ይመስለኛል፡፡ ንጉሤ በትክክል ጊዜውን ያስታውሰው ይሆናል፡፡ በንጉሴ ስልክ ነው ያወራነው፡፡ ከዚያ በኋላ አንድ ቀን ንጉሤን ‹ያልከኝ ሰውዬ የታለ› አልኩት፡፡ እሱም እኔም ጋ መረጃ ከወሰደ በኋላ ጠፍቷል፡ ከአንች ጋር በስልክካወራችሁ በኋላ ደውሎልኝ አያውቅም አለኝ፡፡ ከዚያ በኋላ መጽሐፍ እየተጻፈ ነው.. ሊያልቅ ነው የሚለውን ወሬ መስማት ጀመርኩ፡፡

ቁም ነገር፡- መጽሐፉን መቼ ነው ያየሽው?
ወ/ሮ ሮማን፡- መጽሐፉ ውስጥ ያነጋገራቸው አንዳንድ የጥላሁን ወዳጆች እየደወሉ ይጠይቁኛል፡፡ አንች ጋር አልመጣም እንዴ? እኛን እኮ መጥቶ አነጋግሮናል፤ እሷ ጋ መሄድ አለብህ ብለነዋል ብለው ሲነግሩኝ እኔ ጋ አልመጣም ብዬ እመልስላቸዋለሁ፡፡ በዚህ ሁኔታ መጽሐፉ ታትሞ ወጣ፡፡
መፅሐፉ ከወጣ በኋላ የእሱ ጓደኞች አንጋፋዎቹ ተናደው ምንድነው አሁን የሞተን ሠው አንስቶ ዋሽቷል እንዲህ ብሏል ማለት፣ እንዴት ዝም ትያለሽ ብለው ይደውሉልኛል፡፡ እኔ ደግሞ መጽሐፉን ገና አላነበብኩትም ነበር፡፡ መጽሐፉን ላንብበውና የምንለውን እንላለን አልኳቸው፡፡

ቁም ነገር፡- እነ ማናቸው ?
ወ/ሮ ሮማን፡- የጥላሁን ወዳጆች ናቸው፤ ጥላሁንን ከስር ከመሠረቱ የሚያውቁ ወዳጆቹ ናቸው፡ ፡ ነይ ብለው ብሔራዊ ቴአትር ቤት ጠርተው ቁም ነገር መጽሔት ላይም ወጥቷል፤ መጽሐፉንም ነይ አንብቢ ብለውኝ እዚያ ሄጄ ነው መጀመርያ ያየሁት፡፡ ከዚያ ወዲያው ነው መጽሐፉን ይዤ ቤቴ ሄጄ ማንበብ
የጀመርኩት፡፡
ቁም ነገር፡- መጽሐፉን ካነበብሽ በኋላ ልክ አይደሉም ያልሻቸው ሃሳቦች የትኞቹ ናቸው?
ወ/ሮ ሮማን፡- ከሀሉም በፊት መነሳት ያለበት ይሄ መጽሐፍ ለምን ተጻፈ የሚለው ነው፡፡ ስለ መጽሐፉ ይዘት ከማውራታችን በፊት ሌላ ማወቅ ያለብን ነገር አለ፡፡ መጽሐፉን ካነበብኩ በኋላ ስደርስበት ከደራሲው በስተጀርባ ያለው ሠው ነው ዋና ምክንያቱ፡፡ መነሻው የአቶ ፈይሣ ልጅ የሆነው ሳምሶን ነው፡፡ በመጽሐፉ ላይ የሳምሶን እጅ እንዳለ ሳውቅ መጽሐፉ በምን ደረጃ እንደሚጻፍ ይገባኛል፡፡ እያንዳንዱን ገጽ እንኳ ማንበብ አይጠበቅብኝም፡፡

አቶ ፈይሳን አውቃቸዋለሁ፡፡ ደብረብርሃን ወስዶ ጥላሁን አስተዋውቆኛል፡፡ የእሳቸው ልጅ ሳምሶን ደግሞ እኛ ቤት ይኖር የነበረ ሠው ነው፡፡ እኔና ጥላሁን በትዳራችን መሃል ለተፈጠረው ግጭት ዋናው መሳሪያ ሳምሶን ነበር፡፡ ለጥላሁን የሆነ ያልሆነ ነገር ይነግረው ነበር፡፡ እንዲህ እያደረገች… እንዲህ ልታስደርግህ…ብዙ ነገር…በቃ እኔ ልናገረው የሚዘገንነኝን ነገር ሁሉ እያለ ጥላሁንን ከቤት እንዲወጣ አደረገው፡፡ ከዚያ ጥላሁን ወጣ፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ እቃዎቼን ስመለከት ብዙ ነገር ጠፍቷል፡፡ በሻንጣ የነበሩ ልብሶቼና ወርቅ ሁሉ ሳይቀር ይጠፋል፡፡ ላንቻ ፓሊስ ጣቢያ አመልክቼ ሰራተኞቹ ሁሉ ሲመረመሩ ሳምሶን ነው የወሰደው ብለው ተናገሩ፡፡ ፖሊስ ጣቢያ ተወሰደ፡፡ እሱ ግን ሊያምን አልቻለም፡፡ ታሪኩ በጣም ረዥም ነው፡፡ በኋላ ፖሊሶቹን ደብረብርሃን እንሂድ አልኳቸውና እዚያ ስንሄድ በሙሉ ከአሜሪካ ሀገር ያመጣኋቸው 7 ሻንጣ ልብስና ወርቆቼ ሳይቀር ተገኙ፡፡

ጥላሁን ይህን ሲያውቅ ፖሊሶቹ ሲነግሩት መሬት ላይ ነው የተደፋው፡፡ ‹‹የልጄ እናት ይቅርታ አድርጊልኝ፣ ለዚህ ያበቃኝ እሱ ነው፤ ብዙ ነገር እየነገረ››
ብሎ አለቀሰ፡፡
በአጭሩ ሳምሶን ማለት ይሄንን ያደረገ ሰው ነው፡፡ ላንቻ ፖሊስ ጣቢያ ብትጠይቁ መረጃውን ታገኛላችሁ፡፡ ፖሊሶች ከሳምሶን ኪስ ውስጥ ብዙ የጥንቆላ ነገሮችን ሁሉ ነው ያገኙት፡፡ ‹‹ጥላሁንን እንዲህ አርግልኝ…ምናምን›› የሚል እንዲሁም ደግሞ ጥላሁን ከተለያየ ሠው እንደተበደረ አስመስሎ ያዘጋጀው ወረቀት ሁሉ ተገኝቶበታል፡፡ ጥላሁንን ትብትብ አድርጎ የተጫወተበት ሰው ነው ሳምሶን ማለት፡፡

ቁም ነገር፡- ከጥላሁን ጋር ምንድነው ዝምድናቸው?
ወ/ሮ ሮማን፡- አቶ ፈይሳ ለጥላሁን እናት አጎት ናቸው፡፡ ሳምሶን ደግሞ የእሳቸው ልጅ ነው፡፡ አቶ ፈይሳ ስለጥላሁን ሊያውቁ የሚችሉት ብቸኛው ነገር ምናልባት የተወለደበትን ቦታ ነው፡ ፡ እሱንም ቢሆን የጻፉትን መረጃ ማየት አለብን፡፡ አቶ ፈይሳ በዚያ ዘመን የረቀቁ ሰው ሆነው ጥላሁን ወደፊት እዚህ ደረጃ እንደሚደርስ ታይቷቸው ነው የጻፉት? ጠንቋይ ናቸው? የወደፊቱ ይታያቸዋል? የጥላሁንን ብቻ ነው ወይስ የልጆቻቸውን ታሪክ ጽፈዋል? ምንድነው? በማስረጃ መረጋገጥ አለበት፡፡

ቁም ነገር፡- መጽሐፉ ለሆነ የተለየ አላማ የወጣ ነው ብለሽ ታምኛለሽ?
ወ/ሮ ሮማን፡- አንደኛ ሳምሶን ምን ያህል ገንዘብ እንደሚወድ አውቃለሁ፡፡ ጥላሁን ገና በህይወት እያለ እንኳ ሊሸጠው ሊለውጠው የፈለገ ሠው ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ መጽሐፍ ጀርባ ከደራሲው ጋር በምን እንደተደራደረ ባላውቅም የተወሰነ ሳንቲም ሊገኝበት ይችላል፡፡ ትልቁ አላማው ሳንቲም ነው፡፡ ሳምሶንን ጠንቅቄ አውቀዋለሁ፡፡ ከዚህ በተረፈ መጽሐፉ ምንድነው ያመጣው አዲስ ነገር? ትንሽ የተለየ አገኘሁ ብል የት ተወለደ የሚለውን ነው፡፡ ሌላው ግን የቃላት ጨዋታ ነው እንጂ ምንም የተለየ ነገር የለውም፡፡ ‹‹አንድን መጽሐፍ ሽፋኑን አይተህ ግምት አትስጥ›› የሚባለው እውነት ነው፡፡ ‹‹ምስጢር›› ይላል ግን ምንም አዲስ ምስጢር የለም፡፡ በእርግጥ ስለሙያው ጥሩ አድርጎ ጽፏል፡፡ እሱም ቢሆን ግን ከዚህ በፊት ያልተባለ ነገር አይደለም፡፡ የትዳሩን ጉዳይ በተመለከተ ግን ዝም ብለህ ቁጭ ብለህ የምትጽፈው አይደለም፡፡ የስሚ ስሚ ልትጽፍ አትችልም፡፡ በትዳር ውስጥ ስላለው ጉዳይ የሚያውቁት ባለቤቶቹ ብቻ ናቸው፡፡ እኔ እንኳን ልናገር ብል እኔን በተመለከተ ያለውን እንጅ ከዚያ በፊት ስለነበረው የትዳር ህይወት ግን ማንም ገብቶ ከሁለቱ ባልና ሚስት ውጭ እውነቱን ሊናገር አይችልም፡፡ ልትጽፍ የምትችለው ባለቤቱ ራሱ የተናገረውን ነው፡፡

ስለእኔ ተጽፏል፡፡ ግን ፀሐፊው እኔ ጋ አልመጣም፡፡ አውቃለሁ፡፡ ሳምሶን ዘከርያ ወደእኔ እንዲመጣ አይፈልግም፡፡ ምክንቱም እኔ ምን እንደምል ያውቃል፡፡ ግን ፀሐፊው መጽሐፉ ውስጥ ስለኔ የሚያወራ ከሆነ መጥቶ ሊያነጋግረኝ ይገባ ነበር፡፡ ስለ አንድ ሰው አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ
ነገር ስትጽፍ ባለቤቱን ማናገር ያስፈልጋል፡፡

ቁም ነገር፡- ያ ችግር ከተፈጠረ በኋላ ሳምሶን ከጥላሁን ወይም ከአንቺ ጋር ተገናኝቶ ያውቃል?
ወ/ሮ ሮማን፡- በፍፁም፡፡ ከጥላሁን ጋር ራሱ አስራ ምናምን አመት ይሆናቸዋል፡፡ ሕይወቱ ካለፈ በኋላም ለቅሶ እንኳ እኔ ጋ መጥቶ
አልደረሰም፡፡
roman bezu

ቁም ነገር፡- የደራሲያን ማህበር በጻፈው መጽሐፍ ላይ ጥላሁን የተወለደው አዲስ አበባ መሆኑን ይገልፃል፤ በአዲሱ መጽሐፍ ደግሞ የጥላሁን የትውልድ ቦታ ወሊሶ መሆኑ ተጽፏል፤ ያሄን እንዴት ነው ማስታረቅ የሚቻለው?

ወ/ሮ ሮማን፡- እኔ አሁን በሁለቱም ጎን ሆኜ ጥላሁን አዲስ አበባ ነው የተወለደው ወይም ወሊሶ ነው የተወለደው ማለት አልችልም፡ ፡ ለምሳሌ አቶ ፈይሳ ለጥላሁን በእናቱ በኩል ባላቸው ዝምድና ስለጥላሁን ማስታወሻ ጽፈው እዚያ ላይ የገለጹት ወሊሶ እንደተወለደ ነው ተብሏል፡፡ ማስረጃ ካለ ላምን እችላለሁ፡፡ ግን ይቅርታ አድርግልኝና እሳቸው ጽፈዋል በሚል ሳምሶን ያን ሊያደርገው አይችልም የሚል እምነት የለኝም፡፡ ሳምሶን ጥላሁንን በቁም እያለ ሊሸጠው የነበረ ሠው ነው፡፡

ዞሮ ዞሮ ወሊሶ ነው የተወለደው ወይም አዲስ አበባ ያንን የሚያውቀው ራሱ ባለቤቱ ነው፡ ፡ በነገራችን ላይ ጥላሁን የውልደት ቦታ ወይም የብሔር ነገር የሚያሳስበው ሰው አልነበረም፡ ፡ በተለያዩ ቦታዎች የሆነ ፎርም ሲሞላ እንኳ ብሔር ሲባል ኢትዮጵያዊ ብሎ ነበር የሚሞላው፡፡ ጥላሁን ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ በዚያ ላይ አዲስ አበባ መወለድም ሆነ ወሊሶ መወለድ የሚያሰፍርም ሆነ የሚያኮራ ነገር የለውም፡፡ ስለዚህ ሊደብቅ የሚችልበት ምክንያት የለም፡፡ የደራሲያን ማህበሩ መጽሐፍ ላይ ጥላሁን አዲስ አበባ ጠመንጃ ያዥ ሠፈር እንደተወለደ ነው የገለጸው፡፡ የተቀረጸና ከሰውዬው አንደበት የተሰማ ነው፡፡ ነገር ግን በማስረጃ እስከተጻፈ ድረስ በዚህኛው መጽሐፍ ላይ የሠፈረውንም ቢሆን አምነዋለሁ፡፡

ቁም ነገር፡- ስለዚህ በአጠቃላይ መጽሐፉ የተጻፈው በሳምሶን ግፊትና ለጥቅም ሲባል ነው ብለሽ ነው የምታምኚው?

ወ/ሮ ሮማን፡- ለጥቅምና ስም ለማጥፋት ተብሎ የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡ እኔ እንዳጋጣሚ በጥላሁን የትዳር ህይወት ውስጥ መጨረሻ ላይ ሆንኩኝ፡፡ ማንም ሠው የህይወቱን አጋጣሚ አያውቅም፡፡ የእኔ ከሱ ጋር የመጨረሻ መሆን የሰሞኑ አጀንዳ ሳምሶንና የሳምሶን አጃቢዎችን ስላናደዳቸው ‹‹ጥላሁን እሷ ጋር በነበረበት ወቅት ተጎድቷል በጥሩ አታስታምመውም ነበር›› ብለዋል፡፡ ይሄ እኮ ስም ማጥፋት ነው፡፡ ይሄ ባይሆን እኔ ጋ መጥቶ ይጠይቀኝ ነበር፡፡ አንድ ሶስቱን የቀድሞ የትዳር ጓደኞቹን መርጦ አነጋግሮ እነሱ ጋ እንክብካቤው ከፍ ያለ እንደነበር አድርጎ፤ እኔ ግን እንደበደልኩት አድርጎ ነው የጻፈው፡፡ እኔን ግን አላናገረኝም፡፡ በተጨማሪ የሞተን ሰው አሁን አንስተህ ዋሽቶ ነበር፤ በህይወቱ ደስተኛ አልነበረም፤ እያሉ መጻፍስ ምን ይጠቅማል፡፡ እሱ ታዋቂ ስለሆነ ማንም ተነስቶ እየዘለፈ መጻፍ ያለበት አይመስለኝም፡፡

ቁም ነገር፡- ጥላሁን ራሱን ለማጥፋት እንደሞከረ በመጽሐፉ ተገልጾዋል፤ በዚህ ጉዳይ ምን ትያለሽ?
እየተባለ ነው የተፃፈው፡፡ የሠው ስምም ተጠቅሶ እከሌም ይጠረጠራል ተብሎ ተጽፏል፡፡ አሁንም በ‹ሆድ ይፍጀው› ዙሪያ ነው እንጅ የተቀመጠው መፍትሔ አልሰጠውም፡፡ መፍትሔ የሚሰጠው ማስረጃ ሲኖረው ነው፡፡ ለጥርጣሬ ለጥርጣሬማ ሠው እቤቱ ቁጭ ብሎ እኮ ‹‹ራሱን ሊያጠፋ ሞክሮ ይሆን እንዴ? ለምንድነው ሆድ ይፍጀው ያለው?›› እያለ ሊነጋገር ይችላል፡፡

ቁም ነገር፡- አቶ ፈይሳ የቤተሰብ ማስታወሻ እንደሚጽፉ ታውቂ ነበር፤ ከጥላሁን ጋር ሲያወሩ ሰምተሸ ይሆን ?
ወ/ሮ ሮማን፡- አንድ ሁለት ጊዜ ነው ደብረብርሃን ሄጄ ያገኘኋቸው፡፡ ምንም የማውቀው ጉዳይ የለም፡፡ በጣም በቅርብ የማውቀው ልጃቸው ሳምሶንን ነው፡፡ እሱ እኛ ቤት ነው ይኖር የነበረው፡፡

ቁምነገር፡- ደራሲያን ማህበር የፃፈው መጽሐፍ ጥላሁንን በበቂ ሁኔታ ገልጾታል ብለሽ ታምኛለሽ?
ወ/ሮ፡- ጥላሁን በህይወት እያለ ነው መጽሐፉ የተጀመረው፡፡ ከትውልዱ አንስቶ ትዳሩ ደረጃ እስኪገባ ድረስ ራሱ የተረከው ነገር ነው፡፡ እርግጥ ህይወቱ ካለፈ በኋላ ያለው ሲጻፍ በጥልቀት ሊኼድበት ይገባ ነበር የሚለውን አስባለሁ፡፡ እንጅ በህይወቱ እያለ ለተጠየቀው ሁሉ ጥላሁን እሱ ያመነበትን መልስ ሰጥቷል፡፡ ስለዚህ እኔ ሁሌ እንደምለው ጥላሁን በእያንዳንዱ ሠው ህይወት ውስጥ የገባ ሠው ነው፡፡ ሁሌም ብትጽፈው አያልቅም፡፡ ይኼኛው መጽሐፍ ግን ሆነ ተብሎ ለተለየ አላማ የተጻፈ ነው፡፡ እንደዚያ ባይሆን ኖሮ የደራሲያን ማህበር በጥላሁን ዙሪያ መረጃ ያላችሁ ስጡን ሲል ነበር፡፡ ለምን ያኔ ሳምሶን የአባቴ ማስታወሻ አለ ብሎ አልመጣም፡፡ ‹‹በህይወት እያለሁ እንዳይወጣብኝ›› ብሏል አይደል የሚሉት፡ ፡ ያ ከሆነ ታዲያ ለምን ከሞተ በኋላ ለደራሲያን ማህበር መረጃውን አልሠጡም፡፡

ቁምነገር፡- በመጨረሻ ከጥላሁን ገሠሠ አደባባይ ጋር በተያያዘ ምን አዲስ ነገር አለ?
ወ/ሮ፡- የአደባባዩ ጉዳይ ሁሉም የሚያነሳውም ነገር ነው፡፡ በመንገዱ ስራ ምክንያት ነው እንደዚያ የሆነው፡፡ ባለፈው ጊዜ ከኢንጅነር ፈቃደ ሃይሌ ጋር ተገናኝተን ተነጋግረናል፡፡ ሌላ ቦታ፣ የማይነካ ቦታ ላይ አደባባይ ለመሰየም ታስቧል፡ ፡ ሐውልቱን ለማቆም ከቀራጺያን ጋር መነጋገር ጀምረን ሁሉ ነበር፡፡ አሁን ተለዋጭ አደባባይ ለማግኘት በሂደት ላይ እንገኛለን፡፡
ቁምነገር፡- አመሰግናለሁ፡፡

The post አነጋጋሪው የጥላሁን ገሰሰ መጽሐፍና የባለቤቱ ሮማን በዙ ምላሽ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢትዮጵያዊ ማንነታችን የሚፈተንበት ቁጥር ፫ –የሰማዕቱ ኢያሱ ባለቤት ሮዛ ገ/ፃዲቅ

$
0
0

ከዘመድኩን በቀለ

” እህት ያላችሁ ፣ ሴት ልጅም የወለዳችሁ ፣ እናታችሁን የምትወዱ ሚስታችሁን የምታፈቅሩ በአግባቡ ከልብ ሆናችሁ በደንብ አንብቡት ። ”
[ይህን ጽሑፍ አንብቦ የማይጨረስ አይጀመረው]

roza gebrestadik
ሰሞኑን አዋሬና ገርጂ ድረስ በመሄድ የ ” ሰማዕት ብርሃኑን ” የሚያሳዝኑ ልጆችና ገርጂ ጊዮርጊስ ባጃጅ ማዞሪያ ድረስ በመሄድ ” የአያልቅበትን እናት እማማ አለሚቱን ስናፅናና መቆየታችን ይታወሳል ። እጅግ በጣም ደስስ ይላል ። የሃይማኖት ልዩነት ሳናደርግ ሁላችን ከመላው ዓለም ተረባርበን በሰብአዊነት ሁለቱንም የተጎጂ ቤተሰቦች ለመርዳት ያሳየነው መነሳሳት እጅግ የሚያስደስት ነው ። የብርሃኑም ባለቤት ከነልጆቿ የአያልቅበትም እናት በሚገርም ሁኔታ አሁን በህዝብ እየተጎበኙም እየተረዱም ነው ።
ዛሬ ደግሞ እንደሰሞኑ ሁሉ አንድ ስርቻ ውስጥ ብቻዋን ኩርምት ብላ በጭንቀት ከምትሰቃይ በሊብያ በረሃ የተሰዋ ” ሰማዕት ” ህጋዊ ሚስት ከሆነች ታዳጊ ወጣት ቤት እወስዳችዃለሁ ።

ውድ ጓደኞቹ እስካሁን የነገርኳችሁን በማመን እና በወሰድኩዋችሁ ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር በዓይነ ሕሊናቸሁ እየተከተላችሁኝ በመሄድ ባስለቀሰኝ ጉዳይ ላይ እያለቀሳችሁ ባሳዘነኝ ጉዳይ ላይም እንዲሁ እያዘናችሁ እንደቆያችሁ ይታወቃል ። ዛሬ ደግሞ በጀመርኩት ርእስ ላይ የመጨረሻዬ የሆነውን አሳዛኝ ታሪክ ወደ ዓየሁበት ቤት ልወስዳችሁ ነውና እባካችሁ ተከተሉኝ ።

እኔን ወደዚህ አሳዛኝ ታሪክ ወደአላት ሴት ቤት እባክህ ዘመዴ እንሂድ ብሎ በመጎትጎት የወሰደኝ የማኅበረ ወይንዬው ደረጀ ነጋሽ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜም የሄድነው እኔ ፣ ዘማሪ ዲያቆን ልዑልሰገድ ጌታቸው ፣ ዶክተር ህንፃዊት እና ዘማሪት ትእግስት ነበርን ።

ቤቱን ቀደም ብሎ ደረጀ ነጋሽ ያውቀው ስለነበር ለማግኘት አልተቸገርንም ። በአንድ የጥንት ግቢ ውስጥ በእኔ ዕይታ ያየሁትን ቤት ብዬ አፌን ሞልቼ የማልናገርላት 2×3 በምትሆን ቤት ውስጥ ፣ አንዲት ለግላጋ ልጅ እግር ወጣት ፣ ነገር ግን ሐዘን ያደቀቃት ሴት ከላይ እስከታች ጥቁር በጥቁር ልብሷን እንደለበሰች በቤት መሳይዋና ከሦስት ሰዎች በላይ በማትይዘው ቤቷ ውስጥ ተቀምጣ አገኘናት ።

በዚያች ቤት ውስጥ ከተዘረጋው ትንሽዬ አልጋ ፣ አንድ ወንበርና የልብስ ሻንጣ በቀር ሌላ ምንም አይነት ንብረትና ቁሳቁስ አይታይም ። ቤቷ ከመጥበቧም በተጨማሪ ለደቂቃዎች የማያስቀምጥ መጥፎ ጠረን ይገጥሞታል ።ይህ መጥፎ ጠረን ደግሞ መምጫው በአልጋው በኩል ከመጋረጃ መሳይ ነገር በተሸፈነ ከኮምፐርሳቶ ከተሠራ ግድግዳ በኩል ነው ። ለካ ይሄ ቤት መሳይ ቤት የተሠራው በሽንት ቤት ላይ ነው ። እኔ ለደቂቃ መቀመጥ ባቃተኝ ቤት ውስጥ ግን አልጋ ዘርግታ የምትኖር ሴት አለች ። ዛሬ ከዚህች ምስኪን የሰማዕት ሚስት ጋር ነው ቆይታ የምናደርገው ። ተከተሉኝ ።

ይህች ሴት ደረጀ እንደነገረኝ የዚህ ሰማዕት ሕጋዊ ሚስት ከሆነች ለምን አንድም እንኳን አስተዛዛኝ ይጠፋል በሚል ጥያቄ አዕምሮዬን ወጥሬ የቤቱንም መጥፎ የሽንት ቤት ጠረን ተቋቁሜ በትእግስት ተቀመጥኩኝ ። በገርጂ በእማማ አለሚቱ ቤት 2 ሰው በአዋሬ በብርሃኑ ቤት ጥቂት ሰዎችም እንኳን ቢሆኑም አስተዛዛኝ አይቻለሁ ። በዚህ ቤት ግን አንድም ሰው የለም ።
Rosa Gebretsadik
ቢያንስ የሚያፅናና ጎረቤት እንኳን ለምን አይኖርም የሚለው ጥያቄዬን በአዕምሮዬ እንደያዝኩ እንደምንም ታሪኳን እንድታጫውተኝ በጠየኳት መሠረት ያጫወተችን፣ በብዙ ዝምታዎችና ልቅሶ የታጀበው ታሪኳን እነሆ በአጭሩ እንዲህ አድርጌ አቅርቤላችዃለሁ እና ተከታተሉት።

ይህች ሴት ሮዚና ገብረ ጻድቅ ትባላለች ። አሁን 24ተኛ አመቷን ጨርሳ 25ተኛ ዓመቷን በመጀመር ላይም ትገኛለች ። ሮዚና ሁለት ወንድሞች ያሏት ሲሆን አሷ ለቤተሰቦቿ ሁለተኛ ልጅ ናት ። እነ ሮዛ ወላጅ እናትና እና አባታቸውን ገና ፍቅራቸውን በቅጡ ሳይጠግቡ ነው በልጅነታቸው በሞት የተነጠቁት ። ወገን ዘመድና የሚረዳቸው ባለመኖሩም የግድ ሕይወታቸውን ለማቆየት ሲሉ ታዳጊዎቹ በየፊናቸው ሥራ ፍለጋ በለጋ ዕድሜያቸው ተበታተኑ ። አያድርስ ነው ። እንዲህ አይነት ታሪክ ያለቻው በሚልየን የሚቆጠሩ ሰዎች ይኖራሉ ። ማን ያውቃል ምናልባትም ይህን ጽሑፍ ከምታነቡ ሰዎች መሃልም ትኖሩ ይሆናል ።

እሷ ለቤተሰቡ ሴትና ሁለተኛ ልጅ ስትሆን በትምህርት በኩልም 10ኛ ክፍል ላይ ነው ያቆመችው ። ይህ ሆኖም ዕድሜዋም አስራዎቹ መጨረሻ ላይ ቢገኝም ህይወትን ለማቆየት ሲባል በሰዎች እርዳታ ጭምር ወደ ኳታር ዶሃ ከተማ ትጓዛለች ። በዚያም ሳለች በልጅ አቅሟ የምትሰራውን እየሠራች ለወንድሞቿም እየላከች መኖር እንደጀመረች ነው የእህል ውሃ ነገር ሆኖ በቅርቡ በሊብያ በረሃ ውስጥ ” ሰማዕት ” ከሆነው የህግ ባለቤቷ ኢያሱ ይኩኖ አምላክ ጋር የተገናኘችው ።

ኢያሱ በሾፌርነት እሷም የልብስ መሸጫ ሱቅ ውስጥ እየሠራች ብዙም ሳይቆዩ እሱም እሷም በዚያ በረሃ የቋጠሯትን እና የያዟትን ጥሪት ቋጥረው በመመለስ በሃገራቸው ለመኖር በመወሰን አዲስ አበባ ይገባሉ ። አዲስ አበባ ከመግባታቸው በፊት ግን ኢያሱ በኳታር እንደታሰና ንብረቱንም እንደተቀማ ሮዛ በቁጭት ታስታውሰዋለች ።

የሆነው ሁሉ ሆኖ ያለፈውም ሁሉ አልፎ የሁለቱ የፍቅር ግኑኝነታቸው በማደጉ እነሱም ሁኔታውን መልክ በማስያዝ ህጋዊ ጋብቻን ቤተሰቦቻቸው እና ጓደኞቻቸው በተገኙበት የሠርግ ስርዓታቸውን በመፈጸም አሁን ሮዛ ተቀምጣ ያለችበትን ቤት ማድቤት እና ሽንት ቤት ሆና ተገለግል የነበረችውን የቀበሌ ቤት አልጋ ዘርግተውባት መኖር ይጀምራሉ ።
ኋላ ላይ የአዲስ አበባው ኑሮ እየከበዳቸው የመጣው የሟች ባለቤት በዚህ አይነት ሁኔታ መቀጠል ስለሌብን እኔ ዳግመኛ ወደ ስደት መሄድ አለብኝ ብሎ ይወስናል ። ኳታር ከመሄዱ በፊት ተመዝግቦ ከጋብቻ በፊት የደረሰውን የኮንዶሚኒየም ቤት ሸጦ እሷ ጋር የነበረውንም ጥቂት ሳንቲም ጨምሮ አይሆንም እባክህን ብትለውም እንደምንም አሳምኗት ከጓደኛው ጋር በመሆን ጎዞአቸውን በሱዳን በኩል ወደ ሊቢያ እንዳደረጉ ሮዛ ትናገራለች ።

ኢያሱ ድምጹን እስካጠፋበት ጊዜ ድረስ የሟች ታላቅ ወንድም ባለቤቷ ገንዘብ ላኩልኝ ባለ ጊዜ ሁሉ ብር እየላከለት መቆየቱን ትናገራለች ። ኢያሱም ለእሷም በየደረሰበት ቦታ ሁሉ ስልክ እየደወለ አይዞሽ ሮዚ በቅርቡ ያልፍልናል እያለ ያጽናናት እንደነበር ሮዛ በእንባ እየታጠበች ስትናገር አንጀት ትበላለች ።

በኋላ ላይ የቀን ክፉ የቀን ጎዶሎ ብላ በምትጠራው እለት ኢንተርኔት በመጠቀም ላይ የነበሩ ጓደኞቿ ባለቤቷን በሊብያ በረሃ በሜዲትራንያን ባሕር አጠገብ ጥቁር ቱታ ለብሶ እጁን የዃሊት የፊጥኝ ታሥሮ በእንብርክክ ለእርድ ከተዘጋጁት መሃል የአራጆቹ መሪ ከጀርባው ቆሞ ዲስኩሩን ሲያሰማ ባሏ በዝምታ አንገቱን ደፍቶ በማቀርቀር ሲያደምጠው ከዚያም አረመኔያዊ ድርጊት ሲፈፀምበት የሚያሳየውን ዘግናኝና አሰቃቂ ፊልም ተመልክተው ለእሷም በመንገር እንድታረጋግጥ ይነግሯታል ። ሮዛም እውነት መሆኑን ቪድዮውን በማየት አረጋገጠች ።

ሮዛ ከዚያ በኋላ የሆነውን ማስታወስና ማውራት አትፈልግም ። ዕድለቢስነት ይሰማታል ። ሞት እየተከታተለ በመጀመሪያ በ13 ዓመቷ ወላጅ እናቷን ፣ በመቀጠል በ19 ዓመቷ የምትመካበት አባቷን አሁን ደግሞ ተስፋዋን የጣለችበትና የወላጆቿን መርሻ ያደረገችውን ውድ ባሏን ነጥቋታል ። ኢያሱ የሄደበት መንገድ አደጋ እንዳለው ባውቅም እንዲህ አይነት አደጋ ይደርስበታል ብዬ በፍጹም አላሰብኩም ትላለች ሮዛ ። እኔ ብዙ ሰው የሚያልቅበትን የባህሩን የጀልባ ላይ ጉዞና በየበረሃው መንገላታት ይገጥመው ይሆናል ብዬ ነበር የፈራሁት እንጂ እንዲህ አይነት ዘግናኝ አረመኔያዊ ድርጊት ይፈጸምበታል ብዬ በህልሜም በውኔም መች አስቤው ።
እሱም ያለኝ ይሄንኑ ነው ። በኳታር ቆይታው አረብኛ መናገር በደንብ ስለሚችል መንገድ ላይ ክፉ እንደማይገጥመው ነበር የነገረኝ ። ግን መናገሩም ቋንቋን መቻሉም አላዳነውም ። ልቅሶ ……

አሁን በምን አይነት ሁኔታ ላይ ነው ያለሽው ?
ምንም ይኸው የማደርገው ግራ ገብቶኝ መረጋጋት አቅቶኝ ቁጭ ብያለሁ ። ” አንድ ኮንዲሚንየም ቤት ነበረን እሱንም ሽጦ ለመንገዱ ከፍሎ ነው የሄደው ። አብረን እያለን ከመሄዱ በፊት እዚህች ቤት ውስጥ የነበረንን ንብረት በሙሉ ቴሌቪዥንና ሻንጣዎቻችንን ሳይቀር በሌባ ተዘርፈናል ። ሌቦቹ ትተውልን የሄዱት ይህን አልጋ ብቻ ነው ። እኔ ጋርም የነበረችውን ሳንቲም ለስንቁ ሰጥቼዋለሁ ። ቶሎ አውሮፓ ገብቶ ያወጣውን ወጪ ሁሉ እንደሚመልስ እና ኑሮአችንን እንደሚለውጥ ነበር ተስፋ አድርገን የተቀመጥነው ።
ግን ሁሉም እንዳሰብነው ሳይሆን በስደት በበረሃ ያገኘሁትን ፍቅሬንና ባሌን በበረሃ በግፍ ብቻውን አስቀሩብኝ ።

እያሱ ለእናቱ ልዩ ፍቅር አለው ። እናቱን ስለሚያማቸው አብዛኛውን ጊዜ እሳቸውም ጋር እየሄደ በማደር ይንከባከባቸውም ነበር ። አብዛኛውን ገንዘቡን በእሳቸው ህክምና ላይ ያውለው ነበር ። እናቱን ያከብራል ፣ ይወዳል ፣ ዝምተኛ ነው ፣ ያሰበውን ካላሳካ ብቻ ነው ሲናደድ የማውቀው ። በተለይ ከእኔ ውጪ አብሮት የተሰዋው ለአብሮአደግ ጓደኛው ለባልቻም ከአክብሮት ጋር ልዩ የሆነ መዋደድ አላቸው ። ባልቻ ለኢያሱ ስንጋባም ሚዜው ነበር ።

እኔ አሁን ምን እንደምሆን ምንም እንደማደርግም ግራ ገብቶኛል ። አደጋውን በአይኔ ካየሁበት ዕለት ጀምሮ እንቅልፍ የሚባል የለኝም ። ጨለማ ማየት እፈራለሁ ። ኦሬንጅ ልብስ የለበሰ ሳይ እደነግጣለሁ ። ሌላም የሚቆጨኝ ነገር እግዚአብሔር አልፈቀደውም እንጂ የአራት ወር ፅንስ ይዤም ነበር ። ይኸው ተመልክተው ህክምና የተከታተልኩበትን ። በድንገት ደም ሲፈሰኝ አብሮ አደጉና ሚዜው ከነበረው ባልቻ ጋር ዘውዲቱ ሆስፒታል ወስደውኝ ነው ጽንሱ ተበላሽቶ እኔ ከሞት የተረፍኩት ።
አሁን ምን አማራጭ አለኝ ። እዚህ የሚረዳኝ ዘመድ ወገን የለኝም ። እየበላሁት ያለውን ቆሎና አስቤዛ ለጊዜው አምጥቶ ያረጋጋኝ ደረጄ ዘወይንዬ ነው ። ቤተሰቦቻችን በህይወት ስለሌሉ ሁሉም ሕይወቱን ለማቆየት ከእኔ ጋር የሉም ። ተበታትነናል ። እኔ እድለቦስ ነኝ ። የወንድሞቼን ፍቅር ፣ የወላጆቼን ፍቅር ፣ የባለቤቴን ፍቅር ሳላጣጥም እንድኖር የተፈረደብኝ ሰው ነኝ ። ልቅሶ ልቅሶ ልቅሶ ።

ዶር ሕንፃዊት ልቅሶ ዘማሪዋ ልቅሶ ሉሌም ደረጄ ልቅሶ ማንም ማንንም ሊያጽናና አልወደደም ። እኔ እሷ ይህን እየነገረችኝ ስለራሴ ልጆች ማሰብ ጀመርኩኝ ። ለ3 ወር እነበጋሻው ከሰውኝ ቃሊቲ ብከርም ለልጆቼ ያለሁበትን እናታቸውና ቤተሰብ ባይነግሯቸውም በትምህርት ቤት ይሰሙት ስለነበር እንዴት መማር እንዳቃታቸው ፣ መብላት ፣ መጠጣት ፣ እንቅልፍ መተኛት እንዳቃታቸው አሰብኩ ። ተፈትቼ እቤት የመጣሁ ቀን እንዴት ተጠምጥመውብኝ እንዳለቀሱ አስታወስኩት ። ቆይ እንዲህ ለጥቂት ጊዜ የተለየኋቸው ሞቼስ ቢሆን ኖሮ ብዬ ሳስበው ያሳዝኑኛል ።

እኔም እንዲህ አልኳት ። ሮዛ አይዞሽ አንቺም እኮ እድለኛ ነሽ ። የባልሽ የሰማዕቱ ኢያሱ ስም በተነሳ ቁጥር የአንቺም ስም አብሮ ይነሳል ። ገድሉም ቢጻፍ ፣ ስንክሳርም ቢጻፍ አንቺም በዚያ አለሽ ። የታሪኩም አንድ አካል ነሽ ። ደግሞም ባልሽ ታማኝነቱን እስከሞት ያስመሰከረ ግሩም ሰው መሆኑን አይተናል ። ስለትና ጥይት ከአምላኩ ፍቅር አልለየውም ። እስከ ሞት ድረስ የታመነ የሰማዕቱ የቅዱስ ቂርቆስ ፍሬ ነው ። እናም ልትረጋጊ ያስፈልጋል ።
እኔ አንቺ የምትረጂበትን መንገድ አመቻቻለሁ ። ደግሞ ለልመና ማን ብሎኝ ። አንቺም ቃል ግቢልኝ እንድትረጋጊ ። እግዚአብሔር ከረዳኝ ለመንግሥትም ለህዝብም በመላው ዓለም ላሉ ኢትዮጵያውያንም ችግርሽን አሰማለሁ ። እመኚኝ ችግርሽ ይፈታል ብቻ ጥቂት ቀን ታገሺኝ ብዬ ሌሎቹም እንዲሁ የሚያፅናና ቃል አካፍለዋት እያለቀስን ተለይተናት ሄድን ።
Rosa Gebretsadik  2
የብርሃኑን ልጆችና የአያልቅበትን እናት ጉዳይ ከዳር አድርሼ ለህዝብ ይፋ ሳደርግ ቆየሁና በዚያም ከመላው ዓለም የተገኘው ነገር ደስስስስ ስላሰኘኝ የመጨረሻዬ የሆነውን የሮዛን ጉዳይ ለመጀመር ስደውልላት ሌሊት ሌሊት የባሏ አሟሟት እየመጣባት እየተቸገረች እንደሆነች ስለነገረችኝ እኔም ዛሬ ከወንድሜ አብርሃም እንዳሻውና ከአባ ወልደ ኢየሱስ ጋር በመሄድ አባ ጸሎት አድርገው ቤቷንም ጸበል ረጭተው አረጋግተው ፣ መክረው አጽናንተዋታል ።
ሮዛ እንደነገረችኝ የሚበላ የላትም የታክሲ ቤሳቤስቲን የላትም ። አሁን ወደምታውቀው ስደት ለመሄድ እንደተዘጋጀችም ነገረችኝ ። በሁኔታው ሁላችንም ደነገጥን ። እኔም አይሆንም አይደረግም አልኳትና ። ተነሽ ልብስሽን ልበሽ ብዬ ምንም እንኳን ሰዓቱ ቢመሽም ፒያሳ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመምጣት በመሐል አራዳ ቅርንጫፍ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በባንኩ ሥራ አስኪያጅ በአቶ ወንድራድ ይሁኔ ቀና ትብብር የባንክ ሂሳብ ደብተር አውጥተንላታል ።
መክፈቻውንም አልማዝ እርገጤ የተባለች እህት በአቶ ወንደሰን ውቤ በኩል በላከችው 100 የአሜሪካን ዶላር ዘርዝረን በሁለት ሺህ አርባ ብር ጀምረናል ። ይቀጥላል ። እማምላክ ምስክሬ ናት እውነት እውነት እላችኋለሁ የዚህችን ወጣት ሕይወት እንደሚለወጥ ቅንጣት ታህል ጥርጥር የለኝም ።
ከማን ምን ይጠበቃል ?

መንግሥት ፦ ብትስማማም ባትሰማም መናገሬን እቀጥላለሁ ። ለሮዛ አንዲት የቀበሌ ቤት እንኳን የምታጣ አይመስለኝምና የመኖሪያዋን ጉዳይ እንዲያው ከተቻለ ብትይዝልኝ ።
ቤተክህነት ፦ እስካሁን የዚህችንም ልጅ ፣ የብርሃኑንም ልጆች ጉዳይ እንዳልሰማችሁ ልቁጠረውና እኒህን የእምነቱን ተከታይ ልጆች ባዶ ቤት አይጠፋምና እንደው ብትጸድቁባቸው ። ካልተቻለ ደግሞ ጥቂት የገንዘብ ድጋፍ ብታደርጉላቸው ።

የሴቶች ጉዳይ ፦ አለ ወይስ የለም ? ካለ ስለነዚህ የግፍ ሰለባ የሆኑ ሴቶች ምን ትላላችሁ ? ምነው ዝምታ አበዛችሁ ።
ባለሐብቶች ፦ ይቅርታ የእናንተን ስም በስህተት ነው የጠቀስኩት ። ስም ያለው አትሌት ፣ ዘፋኝ ፣ እግርኳስ ተጫዋች ካልሆነ እንደማትረዱ ያልተጻፈ ህግ አውጥታችኋል ለካ ። ይቅር በሉኝ ተሳስቼ ነው ።
እኛ ኢትዮጵያውያን ፦ በቃ ከኛ በቀር ለእኛ የሚደርስ ማንም የለም ። እናም በያላችሁበት ሐገር ያላችሁ ሁላችሁ አነሰ በዛ ሳትሉ የእርዳታ እጃችሁን ዘርጉ ።
ዮሴፍ ገብሬ /ጄሲ/ ያው እንደተለመደው ለምነህም ሆነ አስለምነህ ለሰማዕቱ ኢያሱ ባለቤትም ስለ እግዚአብሔር ብለህ ድረስላት ። ከተቻለ እግረመንገድህን ውላ የምትገባበት ሥራ የሚያሰሯት ድርጅቶችም ካሉ ፈልግላት ።
እኔም የምስራች አለኝ ፦
★ ለሮዛ አንዲት የገዳማውያን አባቶች መከታ የሆነች መንፈሳዊት እህቴ በሕይወት ዘመኗ ሁሉ ገና ልጅም ስለሆነች ትምህርቷን የፈለገችውን አይነት ዘርፍ መርጣ መማር ብትፈልግ እስከመጨረሻው አስተምራታለሁ ብላለች ።
★ ወሮ ገነት ከጀርመን 50 ዩሮ
★ አብሮ አደግ እህቴ የልጅ አዋቂዋ Helen Negash Mekonnen /ሚጢጢ / 150 ዶላር። እልካለሁ ያለች ሲሆን ። እህቴ ሚሚ ነጋሽም ሰምተሻልና ቶሎ ቃልሽን ስጪ ።
★አበባ ለገሰ ከአሜሪካ 500 ዶላር እልካለሁ ብላለች ። እንጠብቃለን ። ሌሎቻችሁም ፍጠኑ እና ድረሱላት ። የሰማዕት ሚስት ናትና እንንከባከባት ።
ሮዛ ገብረ ጻድቅ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
መሃል ከተማ ቅርንጫፍ
ሂሳብ ቁጥር 1000127035184
የእጅ ስልኳ +251946399795 ነው ። ደውሉና አጽኗኗት ። አይዞሽ ፣ በርቺም በሏት ።
እኔም እስከ ቅዳሜ ድረስ አዲስ አበባ ነኝ ። እስከዚያው የሮዛ ባንክም ምን እንደደረሰ እነግራችኋለሁ ።
ማንኛውንም አስተያየት በእጅ ስልኬ +251911608054 ላይ አስተናግዳለሁ ። እንደተለመደው ይህም ጽሑፍ ሼር ይፈልጋል ። ይቆየን ።
በነገራችን ላይ ሰማዕት እያሱን የገደለው ነፍሰ በላ ዛሬ የመገደሉ ዜና ተሰምቷል ። ” በቀል የእግዚአብሔር ነው ” አይደል የሚባለው ።
ዘመድኩን በቀለ ነኝ
ግንቦት 6/9/2007 ዓም
አዲስ አበባ — ኢትዮጵያ

The post ኢትዮጵያዊ ማንነታችን የሚፈተንበት ቁጥር ፫ – የሰማዕቱ ኢያሱ ባለቤት ሮዛ ገ/ፃዲቅ appeared first on Zehabesha Amharic.

ጀርመን አሻፍንቡርግ ከተማ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሰላማዊ ፡ ሰልፍ ፡ ጥሪና ፡ የሀዘን ፡ ጉዞ

$
0
0

Saudicryሁላችሁም ፡ እንደምታውቁት ፡ ሚያዝያ ፡ 20 ቀን ፡ 2015 ዓ.ም ፡ 28 ኢትዮጵያውያን ፡ ወንድሞቻችን ፡ በእስልምና ፡ ስም ፡ በሚነግደው ፡ ኣሽባሪ ቡድን ፡ ISIS (የእስልምና ፡ መንግስት ፡ በኢራቅና ፡ ሲሪያ) በኣሰቃቂና ፡ በዘግናኝ ፡ ሁኔታ ፡ መሰዋታቸውን ፤

በደቡብ ፡ ኣፍሪካ ፡ በሕይወታቸው ፡ የተቃጠሉና ፡ ንብረታቸውን ፡ የተዘረፉትን ፤

በየመን ፡ በተቀሰቀሰው ፡ የሀገር ፡ ውስጥ ፡ የእርስ ፡ በእርስ ፡ ጦርነት ፡ መጠጊያ ፡ ኣጥተው ፡ የተገደሉ ፤ የቆሰሉ ፤ አሁንም ፡ በርሀብና ፡ በጥማት ፡ የሚሰቃዩትን ፡

በተለያየ ፡ ምክንያት ፡ ከኣገራቸው ፡ ኢትዮጵያ ፡ ወጥተው ፡ በየበረሐው ፡ የኣውሬ ፡ እራት ፡ በየባሕሩ ፡ የሰመጡትን ፡ እህቶችችንና ፡ወንድሞቻችንን ፡ ታስታውሳላችሁ!!

በተከታታይ ፡ እየደረሰብን ፡ ያለውን ፡ መከራ ፡ በጋራ ፡ ለማዘንና ፡ ችግራችንንም ፡ ለየምንኖርበት ፡ ኣካባቢ ፡ ለማሳወቅ ፡ በአሻፈንቦርግና ፡ ኣካባቢ ፡ የኢትዮጵያን ፡ ማህበር ፡ e.V. ለግንቦት(MAY) 21 2015 . 1400 ሰዓት እስከ 1700 ሰዓት ፡ በኣሻፈንቦርግ ፡ ከተማ ፡ ሰላማዊ ፡ ሰልፍ ፡ የጠራ ፡ ስለሆነ ፡ እርስዎም ፡ የሰላማዊ ፡ ሰልፉ ፡ ተካፋይ ፡ እንዲሆኑ ፡ በኣክብርት ፡ ጥሪ ፡ ቀርቦልዎታል ።

ወደ ፡ ቦታው ፡ ለመምጣት ፡ የሚከተሉትን ፡ ኣማራጮች ፡ መጠቀም ፡ ይችላሉ ።

በባቡር ለምትመጡ፤

ከደቡብ (ሙኒክ ፤ ኑርንበርግ ፤ ቩርዝቦርግ …) የምትመጡ ፡ ከባቡር ፡ እንደወረዳችሁ ፡ ወደ ፡ ግራ ፡ በመታጠፍ ፡ ወደ ፡ ከተማው ፡ ይውጡ ፤

 

ከሰሜንና ፡ ከምዕራብ ፡ ከዳርምስታት ፤ ከፍራንክፎርት ፡ ኣቅጣጫ ፡ የምትመጡ ፡ ከባቡር ፡ እንደወረዳችሁ ፡ ወደ ፡ ቀኝ ፡ በመታጠፍ ፡ ወደ ፡ ከተማው ፡ ይውጡ ፤

 

በመኪና ፡ ለምትመጡ፤

 

ከደቡብ (ሙኒክ ፤ ኑርንበርግ ፤ ቩርዝቦርግ …) የምትመጡ ፡ A3 – Ausfahrt Aschaffenburg Ost – Schönbornstraße –  Auhofstraße -Glattbacher Überfahrt – Elisenstraße

ከምዕራብ ፡ ከዳርምስታት ፡ ኣቅጣጫ ፡ የምትመጡ ፡ B26 – Darmstädter Straße – Westring – Friedrich Ebertsbrücke – B 26  Hanauerstraße – Kolpingstraße – Ludwigstraße

ከሰሜን ፡ ፤ ከፍራንክፎርት ፡ ኣቅጣጫ ፡ የምትመጡ ፡ A3 – Ausfahrt Aschaffenburg West – B 8 – Hanauerstraße – Kolpingstraße – Ludwigstraße

የኣሻፈንቦርግና ፡ ኣካባቢ ፡ የኢትዮጵያን ፡ ማህበር  e.V.

The post ጀርመን አሻፍንቡርግ ከተማ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሰላማዊ ፡ ሰልፍ ፡ ጥሪና ፡ የሀዘን ፡ ጉዞ appeared first on Zehabesha Amharic.

በስቶክሆልም በሊቢያ ሕይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያውያን በደመቀ ሁኔታ ታስበው ዋሉ

$
0
0

ethiopians in sweden

ethiopians in sweden 2

ethiopians in sweden 3

ዳንኤል ሐረር ለዘ-ሐበሻ ከስዊድን እንደዘገበው:-

ትላንት ሐሙስ ግንቦት 6/2007 በምስራቅ አፍሪካ እና አውሮፓ አህጉረ ስብከት የመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ እስቶኮልም ሆተርየት ባዘጋጀው የ21ኛው ክፍለ ዘመን ድንቅ የእግዚአብሔር ምስክሮች ለሆኑት 30 (ሰላሳ ) የኦርቶዶክስ ልጆች መታሰቢያ ፕሮግራም በዕለቱ ከተገኙ የግብፅ የሶርያ ብጹአን አባቶች ጋር በደማቅ ሁኔታ ታሥቦ ውሏል፡፡ በዕለቱ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ካህንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ካህናት ተገኝተዋል።

እንዲሁም በስቶኮልም ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ስንበት ት/ቤት ተማሪዎች የህብረት መዝሙረና በወቅቱ የነበረውን የሰማዕታቱን ጽናት የሚያሳይ ትዕይንት ፤የአበባ ማስቀመጥ እና የጧፍ ማብራት ፕሮግራሞ ተካሂዷል።

The post በስቶክሆልም በሊቢያ ሕይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያውያን በደመቀ ሁኔታ ታስበው ዋሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

5 በሃይል አማራጭ የሚያምኑ ድርጅቶች በጋራ ለመታገል ውይይት ጀመሩ

$
0
0

Ethsatበስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ በማንኛውም አማራጭ ለማስወገድ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ የተቃዋሚ ሃይሎች በጋራ ለመታገል የሚያስችላቸውን ውይይት መጀመራቸውን ለኢሳት በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል።

ውይይቱን የጀመሩት የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ትህዴን)፣ የጋምቤላ ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፣ የቤንሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፣ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄና አርበኞች ግንቦት7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ናቸው።

ድርጅቶቹ ” በሂደት ወደ አንድ የምንመጣበትን ሁኔታ እያመቻቸን፣ አሁን ግን አገርና ህዝብን የማዳኑን ስራ እንጀምር በሚል ውይይት እያደረግን መሆናችንን ለኢትዮጵያ ህዝብ መግለጽ እንወዳለን” ብለዋል።

የኢህአዴግን አገዛዝ በሃይል እናስወግዳለን በማለት የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ድርጅቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ በሰው ሃይልና በሎጂስቲክ እየተጠናከሩ መምጣታቸውን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ስርዓቱ በአገር ውስጥ በሚገኙ ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው አፈና ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመር፣ ወጣቶች የትጥቅ ትግል አማራጭን የሚደግፉ ሃይሎችን እንዲቀላቀሉ እያደረጋቸው ነው።

Source:: Ethsat

The post 5 በሃይል አማራጭ የሚያምኑ ድርጅቶች በጋራ ለመታገል ውይይት ጀመሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live