Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የወቅቱ የኢትዮጵያ ጠላቶች –በገ/ክርስቶስ ዓባይ

$
0
0

በገ/ክርስቶስ ዓባይ  ሚያዝያ 6 ቀን 2005 ዓ/ም

አንድን  ታላቅ ሀገራዊ እንቅስቃሴ ከአጥናፍ  እስከ አጥናፍ ማለትም ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ፤  ወጥ በሆነ መልኩ እንዲዳረስ የሚገፋፋና የሚያስገድድ፤ አሁን እንዳለንበት ወቅት ያለ ፈታኝ ሁኔታ ሲከሰት፤ በቅድሚያ መታወቅ ያለባቸውንና ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች ለይቶና አበጥሮ ደረጃ በደረጃ ማስቀመጥ ግድ ይላል ።

ስለሆነም ከጸጸት ለመዳን የሚያስችለንን ሐቀኛና ፍትሐዊ የሆነ መመዘኛ ጊዜ ወስደን  አስበንና አሰላስለን ማስቀመጥ ይኖርብናል። በዚህ አጋጣሚ ለሰላም፤ ለፍትሕ፤ ለዲሞክራሲና ለዕኩልነት እንዲሁም ሐሳብን በነፃነት የመጻፍና የመግለጽ መብት፤ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ተዘዋውሮ የመሥራት፤ ሀብት የማፍራትና በመረጠው የአገሪቱ ክፍል የመኖር መብት ሊኖረው ይገባል በማለት የሚያምን፤ ፍትሐዊ አስተሳሰብ ያለው ዜጋ ሁሉ፤ በሃይማኖት፤ በቋንቋ፤ በጎሣ፤ በክልልም ሆነ በጎጥ እንዲሁም በድርጅትም ቢሆን ሳንከፋፈል፤ በዚህ መርህ እስማማለሁ፤ ለዚህም መከበር እታገላለሁ፤ የሚል አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ለዚህ የጋራ ዓላማችን  እውን መሆን፤ የምንኖርበት የቦታ ርቀትም ቢሆን ሳይበግረን በየአለንበት  በአንድ ላይ ሆነን መቆም አለብን።

እንዴት ?ብሎ መጠየቅ ይቻላል።

eprdfከሁሉም በፊት ቅድሚያ ልንሰጠው የሚገባን ነገር የአገራችን ጉዳይ መሆን ይኖርበታል። አገር ማለት ደግሞ ወገን ማለት ነው። እዚህ ላይ ግልጽ ማድረግ የሚገባን ጉዳይ ይኖራል። በተለይ ሀገርና አገር የተለያዩ መሆናቸውን ልናስተውል ይገባል። ሀገር ማለት በተደረሰበት የጋራ ስምምነት ወይም በኃይል የተሰመረ ድንበር፤ ወይም ለግዛት እንዲያመች የተዘጋጀ (Political Boundary)ራሱን የቻለ መጠሪያ ያለው የፖለቲካ ክልል ሲሆን፤ ይህም በአብዛኛው የሚያተኩረው በዱር በገደሉ ፤ በጫካውና በሸለቆው፤ እንዲሁም በተራራውና በሜዳው ላይ ነው። ከዚህም የተነሣ በተለይ አምባገነኖች ሁሉንም ነገር ትተው አገር የሚለውን ሳይሆን ሀገር የሚለውን አጉልተው ለማሣየትና አገር የሚለውን ጽንሰ ሐሳብ አሳንሰውና አኰስሰው ለማሳየት ያላደረጉት ጥረት የለም። ለምሳሌም ብናነሳ የወያኔው ዋና ጠርናፊ የነበሩት በቅድሚያ ሁሉን ሲጠቀልሉ ቆይተው አሁን የተጠቀለሉት መለስ ዜናዊ የአዲስ አበባን ዩኒቨርስቲ ምሁራንን አስመልክቶ እነዚህ ምሁራን ያለአግባብ ከሥራ ሲባረሩ ማን ሊያስተምር ነው ሲባሉ “መንገዱን ጨርቅ ያድርግላቸው” ማለታቸው አይዘነጋም።  በተጨማሪም ለሱዳን ወደ 65 ኪሎሜትር እርዝመት ያለው በአገር(በወገን) ያልተመከረበት መሬት ከልለው፤ የሱዳን መንግሥት በትግል ጊዜ ላደረገላቸው እገዛ እንደ ካሣ መስጠታቸው ይታወቃል። ሌላም መጨመር ይቻላል።

 

የትግራይን ክልል ለማስፋት እና የአማራውን ክልል ለማሳነስ ሲባል ራያን ከወሎ ፤ ጠለምትንና፤ ቆላ ወገራንና፤ ወልቃይት ጠገዴን ከጎንደር እንደ ዳቦ በመቁረስ ወደ ትግራይ አድርገዋል፤ ቤንሻንጉልን ግማሹን ከወለጋ ግማሹን ከጎጃም በውሰድ አዲስ ከልል ፈጥረዋል። ድቡብንም እንዲሁ ከሸዋ፤ ከሲዳሞ ከጋሞ ጎፋ እና ከከፋን ከጂማ በመቀናነስ ፈጥረዋል። በአጠቃላይ ይህ ዓይነቱ አከላለል ለሕዝብ እንዲጠቅም ታስቦ ሳይሆን ቀደም ሲል የነበረውን ሥር የሰደደ የማንነት ጥንካሬና በራሥ የመተማመን  አንድነት በመሸርሸር ፍጹም ያልነበረና ከቶ በኢትዮጵያዊ አእምሮ ሊታሰብ የማይችል የመከነና የያንዳንዱን ዜጋ ህልውና የሚፈታተን ሰይጣናዊ የሆነ እርምጃ ነው። በእነርሱ አባባል ለሌላው ኢትዮጵያዊ “የመቶ ዓመት የቤት ሥራ” በመስጠት በዚህ ግርግር ውስጥ ግን እነርሱ ያሻቸውን እንዲያደርጉና እንደፈለጉ የአገርን ሐብትና ንብረት እንዲዘርፉ መንገዳቸውን አስተካክለው ጨርሰው የአስፓልት ንጣፍ ሊያነጥፉ በተዘጋጁበት ወቅት ሕዝቡ ያለፉትን የሃያ ሁለት ዓመታት ቆይታውን እንደገና መረምር ሲጀምር ነው፤ በተለይ የነፃ ሚዲያ የሆነው ተወዳጁ ኢሳት አገልግሎቱን በማስፋፋት አስተማማኝ መረጃዎችን ማሰራጨት ከጀመረ በኋላ ነው ሕዝቡ ከዕንቅልፉ እንደነቃ ሁሉ መባነን የጀመረው።  በተለይ ወያኔ መራሹ የትግሬ ባንዳዎች ስብስብ  ዘራፊ ሥርዓት ብዙ የዋሃንን አጭበርብሮ በትረ መንግሥቱን ሲቆናጠጥ የወሰዳቸውን በማር የተሸፈኑ አንዳንድ እርምጃዎች ማስታወሱ ተገቢ ይሆናል።

ለምሳሌም ያህል የኦሮሞ ሕዝብ ታላቅ እንደመሆኑ መጠን ለዚህ ሕዝብ የሚሆን የቤት ሥራ ወዲያውኑ ነበር የተሰጠው።  ይኸውም ለሥልጣንና ለገንዘብ ጥቅም ያጎበደዱ አንዳንድ ከሐዲ የኦሮሞ ተወላጆችን አቶ ሐሰን አሊን ጨምሮ የተወሰኑ ሰዎችን በማሰልጠን የኦሮሞን የተከበረውን ባህልና የገዳ ሥርዓት ከፊት ለፊት በማስቀደም እየሰበኩ፤ የግዕዝ ፊደል ለኦሮምኛ ቋንቋ አይሆንም ከእንግዲህ በኋላ ኦሮምኛ የሚጻፈው በላቲን ነው በማለት ማስተማር መጀመራቸውን በቁጭት የምናስታውሰው ነው።፤

በወቅቱ አንድ የማውቀው የቅርብ ጓደኛየ ኦሮሞ በመሆኑ በሚሠራበት መ/ቤት ይህንኑ “ቁቤ” ብለው የሰየሙትን የላቲን ፊደል አጠቃቀም እንዲሠለጥን የደረሰውን ትዕዛዝ ቀመስ  ግብዣ ተቀብሎ ሄዶ ነበር፤ ነገር ግን ሥልጠናውን ሳይጨርስ እሳት ለብሦ እሳት ጎርሦ እየተናደደ  አቋርጦ በመመልሱ፤ ምነው የከፋህ ትመስላለህሳ ? ብለው ጓደኞቹ ሲጠይቁት የመለሰው መልስ የሚረሳ አይደለም።

እነዚህ ሰዎች ዓላማቸው ምን እንደሆነ አልገባኝም፤ የሚሠሩትንም የሚያውቁ አይደሉም። የኦሮሞ ሕዝብ የሚፈልገው የሥርዓት ለውጥ እንጂ የፊደል ለውጥ አይደለም ደግሞስ ቢሆን የተለያዩ ድምፅን በመወከል የላቲን ፊደል እንደ የኛው የግዕዝ ፊደል የበለጸገ አይደለም።ለምሳሌም እንደ ቀ፤ ቸ፤ ኘ፤ ዠ፤ ጠ፤ ጨ፤ ጸ፤ ጰ የመሳሰሉ ፊደላት እንኳ የሉትም ታዲያ በምን መስፈርት ነው የላቲን ፊደል አጠቃቀም ተማሩ ተብሎ የኦሮሞ ሕዝብ የተወሰነበት ?በማለት ጠይቋል።

አየይዞም በሦስት መስመር በግዕዝ ፊደል የሚጻፈው ኦሮምኛ በላቲን ከሆነ ሲቸከችኩ መዋል ነው፤ አንድ ገጽ ገደማ ይፈጃል ስለዚህ አጠቃላይ ሁኔታው የኦሮሞን ሕዝብ ዕድገት ሆነ ተብሎ ለመግታት፤ ወይም ደግሞ ምስጢሩ ያልታወቀ የቤት ሥራ ሳይሆን አይቀርም  እኔ ግን በዚህ በማይረባ ጉዳይ ጊዜየን አላጠፋም፤ ሌላውም  የኦሮሞ ሕዝብ ቢሆን በዚህ ተታሎ ጊዜውንና ገንዘቡን ማጥፋት የለበትም፤ በማለት በመናገሩ የት እንደደረሰ አይታወቅም።

 

ለማንኛውም አገር ግን ከዚህም በላይ ታላቅ ትርጉም ያለው ጉዳይ ነው። ቀደም ሲል እንዳየነው ሀገር ሕዝብን አይጨምርም። አገር ስንል ግን ቅድሚያ የሚመጣው ሕዝቡ፤ ቀጥሎም ያ ሕዝብ የሚኖርበት መሬት (ሀገር) እና የአኗኗሩ ሁኔታ፤ የአስተዳደሩ ፤የባህሉ ፤የኢኮኖሚው፤ የሃይማኖቱ፤ የፖለቲካውና የጤናውን ሁኔታ ሁሉ ያጠቅልላል።

እንግዲህ እስከዚህ ድረስ በተደረገው ማብራሪያ የምንግባባ ከሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ላለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት በቀጥታም ሆን በተዘዋዋሪ ትግራይ በቀል በሆኑ ጥቂት ደቂቀ ባንዳ ስብስቦች ከዘር ባገኙት አስነዋሪ የአገር ክህደት ውርስ የደረሰባቸውን የበታችነት ስሜት ተንተርሰው በጀግኖች አባቶቻችን መስዋዕትነት ዳር ድንበሯ ተከብሮ ለብዙ ሺህ ዓምታት ታፍራና ተክብራ የቆየችውን ኢትዮጵያን ለማፈራረስና ለመበታተን ያልፈነቀሉት ድንጋይና ያልሸረቡት ሤራ የለም።

እዚህ ላይ የወያኔን አንዱን የማስመሰያ መሠሪ ተንኰል የሆነውን የብሄር ተዋጸዖን የተመለከትን እንደሆነ ዓላማው  ለሀገርና ለወገን የሚጠቅም ሊመስለን ይችላል። ሐቁ ግን በብሄር ተዋጽዖ ሲባል የችሎታ መለኪያ ዋጋውን ያጣል። ያም የሚወከል ሰው ቢማር ባይማር ግድ የለም ቢቻል እንዲያውም ባይማር ይሻላል። ምክንያቱም የቀረበለትን ሁሉ ያለምንም ጥያቄ የተጻፈውን ይፈርማል፡ የታዘዘውን እንዳለ ተቀብሎ ይፈጽማል ያስፈጽማል። ሌላው ቀርቶ ወንድሙን ግደል ቢባል ይገድላል። አውቀው ደግሞ በተለያዬ የጥቅም መረብ ውስጥ እንዲገባ ያደርጉትና ከዚያ በኋላ በሰው አእምሮ ሊታሰብ የማይችል ነገር እንኳ ቢሆን እንዲሠራ ይገደዳል። ለምሳሌ ም/ጠ/ሚ/ርና የትምህርት ሚ/ር ደመቀ መኰንን የኢትዮጵያን ግዛት ለሱዳን ለማስረክብ ኢትዮጵያን ወክለው የፈረሙ መሆናቸው በስፋት ይወራል።  ይህ ጉዳይ እውነት ከሆነ ግለሰቡ ቢታሠሩ፤ አለበለዚያም ከነ ክብራቸው ቢሞቱ ይሻላቸው ነበር ። ግን ወያኔ እርሳቸውን በጊዜያዊ መቅቡጥ አታሎ እንደሮቦት ወይም እንደ ለማዳ ውሻ ተጠቅሞባቸዋል።

የ97 ዓ/ም ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረው የምርጫ ውጤት አይደግ (ኢሕአዴግ) በዝረራ መሸነፉ አይዘነጋም። ይሁን እንጂ አይደግ በጠመንጃ ያገኘሁትን ሥልጣን በካርድ ልነጠቅ አልችልም በማለት የሕዝቡን ድምጽ ዋጋ አሳጥቶታል ። ይህንኑ ተከትሎ በተፈጠረው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ አሁንም አይደግ ሆዬ በዚህ አጋጣሚ ሕዝቡን ለመበቀል በድብቅ የነፃ እርምጃ ትዕዛዝ አስተላልፎ ኖሮ ይህንኑ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አነጣጥሮ ተኳሾችን አሠማርቶ እንደነበር ይነገራል።

ታዲያ ነፍሰ ገዳዮች ተብለው የተመደቡት የመጀመሪያውን ዙር ትዕዛዝ አከናውነው እንደተመለሱ በተደረገ ግምገማ፤ አንዳንዶቹ ባደረጉት ገለጻ “እኔ ይህን ያህል ጥይት ተኩሼ ይህን ያህል ሰው ገድያለሁ፤ እገሌ ግን እንኳን ሰው ሊገድል  አንዲት ጥይትም አልተኰሰም” በማለት እነዚሁ ሮቦቶች ድርጊታቸውን እንደጀግንነት ሲያቀርቡ ሌሎች ግን “በማን ላይ ነው ጥይት የምተኩሰው? ጠላት ላይ ቢሆን እሺ፤ ያ ሌላ ጉዳይ ነው ግን በሰላማዊ ሕዝብ ላይ ያውም በወገን ላይ እንዴት ተደርጎ”  ይላሉ። ጥይት የተኮሱት ወደ ሌላ ክፍል እንዲሄዱ ይደረጋል ።ከዚያም ጥይት ያልተኮሳችሁ እዚሁ ቆዩ ተጨማሪ ገለጻ ይደረግላችኋል ይባሉና እንግዲህ ተጨማሪ ዙር ስላለ በዚያን ጊዜ ትታያላችሁ ይህ የመንግሥት ተዕዛዝ እስከሆነ ድረስ ግዳጃችሁን መፈጸም ይጠበቅባችኋል ተብለው ይሰናበታሉ።

ጥይት ተኩሰናል እያሉ ለተገመገሙት ነፍሰ ገዳዮች የተሰጣቸው መመሪያ ደግሞ የተለዬ ነበር። እናንተ ለመንግሥት ያላችሁን ታማኝነት በግልጽ አስመስክራችኋል፤ አይደግም ለእናንተ ያለው ክብር ከፍተኛ መሆኑን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።

ይሁን እንጂ እነዚህ ከሐዲዎች የተሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት አልተወጡም ስለሆነም ከዛሬ ጀምሮ ለድርጅታችን ብቻ ሳይሆን ለእናንተም ጠላቶች ስለሆኑ መወገድ አለባቸው።

አሁን ለሁለትኛው ዙር ስትወጡ ከኋላቸው በመሆን ጭንቅላት ጭንቅላታቸውን እንድትሏቸው፤ የሚል ቀጭን ትዕዛዝ መሰጠቱና በኋላም ተፈጻሚ እንደሆነ ይነገራል። ይህም እንደገና ለአይደጎች እንደ መከራከሪያ ነጥብ ሆኖ መቅረቡ ይታወቃል። ይኸውም ከሰላማዊው ሕዝብ በተተኮሰ ጥይት የመንግሥት ወታደሮች ተገድለውብናል የሚል ነው ። እንግዲህ እንደዚህ ያለ ጅብ የሆነን መንግሥት በዘርና በጥቅማ ጥቅም እየተሸነገሉ ሕሊናን በመሸጥ መደገፍ የሞት ሞት ነው።

 

እዚህ ላይ ርዓዬ ቢሱ፤ ሟቹ ጠ/ሚር በአንድ ወቅት የተናገሩትን ለመጥቀስ እገደዳለሁ። እኛ የምንፈልገው ታማኝነት ብቻ ነው እንጂ ባይማርም  ታማኝ እስከሆነ ድረስ ጄኔራልም መሆን ይችላል ማለታችውን ሐቀኛ ኢትዮጵያውያን በቁጭት የምናስታውሰው ነው። እዚህ ላይ ዋናው ጉዳይ ያዘዝነውን ብቻ ሳይሆን ያስብነውን የሚሠራ ማለታቸው እንደሆነ ግልጽ ነው።  ይህንን የመሰለውን ግልጽ የሆነ የዘቀጠና፤ በትዕቢት የተወጠረ አነጋገር ሲጠቀሙ የነበሩትን ሰው የ… ራዕይ እናስቀጥላለን እያሉ ሲደሰኩሩ ዝም ብለን እያዳመጥናቸው ነው። እነርሱማ መያዣው መጨበጫው ቅጥ አምባሩ ስለጠፋባቸው ቢሉም አይደንቅም ፤ ምክንያቱም ካፈሩና ከደነገጡ ውለው አድረዋል።

እኛ ግን ከነርሱ የባሰ የህሊና ስብራት ደርሶብናል። ምክንያቱም ስለ እነርሱ  መጥፎነት ብቻ ስናወራ ይኸው ድፍን ሃያ ሁለት ዓመት ሆነን። ወገናችንም አቅጣጫና መሥመር አስይዞ የሚመራው ቁርጠኛ ድርጅት እስኪመጣ ድረስ በተጠንቀቅ እየተጠባበቀ ይገኛል።

ስለሆነም በአሁኑ ወቅት መቅደም ያለበት ምን እንደሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠንቅቆ አውቆታል። ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ለአገር ዕድገትና ብልጽግና እንዲሁም ለዲሞክራሲና ስብዓዊ መብት መከበር የተቋቋሙ እንደመሆናቸው መጠን ከሁለት ጥቃቅን ጉዳዮች በስተቀር ሊታረቁ በሚችሉ መርህ ላይ የተመሠረቱ እንደሆነ ይታወቃል።

እነርሱም አንደኛው ያቋቋሙት ፓርቲ መጠሪያና፤ ለሥልጣን ያላቸው የጉጉት መጠን ናቸው። መቼም ቢሆን በዲሞክራሲ እናምናለን የሚሉና ለዚህም መከበር እንታገላለን የሚሉ ከሆነ ለሥልጣን ያላቸው ፍላጎት በሕዝብ ዘንድ ባላቸው ታማኝነትና ክብር ላይ የተመሠረተ እንዲሁም በሕዝበ ውሳኔ የሚረጋገጥ በመሆኑ የሥልጣን ጉጉት እዚህ ላይ ያከትማል። የድርጅታቸውን መጠሪያ ግን ከፈለጉ እንደያዙ በዚያው በጀመሩት የዕዝ ስንሠለት መቀጠል ይችላሉ ግን ማየት የሚገባቸው ጉዳይ አለ።

 

በተናጥል ብዙ ቢደክሙም ለውጥ ማምጣት ያለመቻላቸውን የተገነዘቡ ስለሆነ ከሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ተቀናጅቶ መሥራትና ይህን ራሡ ላወጣው ሕግ እንኳ የማይገዛ አምባገነን ሥርዓት ከሕዝብ ጫንቃ ላይ አውርዶ በመቅበር በምትኩም በሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘንድ የሚናፈቀውን ሰብአዊ መብት የሚከበርበት፤ ሕግና ፍትህ የሠፈነበት መንግሥት እውን እንዲሆን ሌት ተቀን መሥራትን ይጠይቃል። ከዚያ በኋላ ችሎታውና ፍላጎቱ እስካለ ድረስ ሥልጣኑም በአስተማማኝነት ሊመጣ ይችላል። ምክንያቱም የሕዝብ ድምፅ ተቀባይነት ስለሚኖረው ተወዳድረው ካሸነፉ ሥልጣንም ሊይዙና ለወገን የሚጠቅም ራዕያቸውን ተግባራዊ ከማድረግ የሚያግዳቸው አንዳችም መሰናክል አይኖርም።

ነገር ግን ቁምነገርኛ መዥገር ቆርበት  ነክሶ ይሞታል እንዲሉ በዚያው ባለሁበት እቀጥላለሁ ቢሉ ሕዝብ ከጎናቸው ከሌለ ብቻቸውን እንደሚቀሩ ከአሁኑ ማወቅ አለባቸው። የሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና ዓባላት መነጋገርና መወያየት ያለባቸው የወቅቱ ሁኔታ ከየትኛው ፓርቲ ጋር ብንቀናጅ ተስማምተንና ተግባብተን፤ በመረዳዳት ሥራችንን አንድ እርምጃ ወደፊት ማስኬድ እንችላለን በሚለው ላይ ጊዜና ትኩረት ሰጥተው  መነጋገር ይጠበቅባቸዋል። አስፈላጊ ከሆነም ከተለያዩ ፓርቲዎች የተለያዩ ሰዎችን በመጋበዝ ስለእነርሱ ፓርቲ ገለጻ እንዲያደርጉላቸው ማድረጉ ተገቢ ነው።

ያሉትን የተቃዋሚ ፓርቲዎች በማሰባሰብ ወደ አንድ የሚመጡበትን ዘዴ መቀየስ ካልሆነ በስተቀር ከእንግዲህ ወዲህ ሌላ አዲስ ድርጅት ወይም ፓርቲ ማቋቋም ማለት፤ የጠላትን ዕድሜ ለማሳጠር ሳይሆን ለማስረዘም ብሎም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ መቀለድ ስለሚሆን ከቶ መታሰብ እንኳ የለበትም እላለሁ።

አሁን የሚያስፈልገው ሁሉም ተቀራርቦ መሥራትና፤ ለዚህ ችግሩና ኑሮው  ላንገፈገፈውና በተጠንቀቅ ለሚገኘው ወገናችን አቅጣጫ በማስያዝ መንገዱን መምራት ብቻ ነው። ነገር ግን የተባና ወጥ የሆነ አመራር ለመስጠት የግድ ማዕከል መፈጠር አለበት።

ለምሳሌም ክርስቲያኑ ሕዝብ በወያኔ ጣልቃ ገብነት ለተመረጠው ፓትሪያርክ ያለውን፡ተቃውሞ ለመግለጽ ሁኔታዎች እስከሚስተካከሉ ድረስ ሙዳዬ ምጽዋት የሚባል ነገር ለቤተክርስቲያን መስጠቱን እንዲያቆም መቀስቀስ፤ ትልቅ ሚሳይል እንደመትኰስ ይቆጠራል። በአንፃሩ ግን መለመን ለአፈሩ ችግረኛ ሰዎችና በቤተ ክርስትያን ዙሪያ ወድቀው ለሚለምኑ ወገኖች እንዲመጸውቱ  ማስተማር። ጠንከር ያለ አቅም ያላቸውን ደግሞ ድርጅቶን እንዲረዱ ማበረታት።

 

በተለይ ወጣቱ ክፍል በአብዛኛው፤ አይደግ ሥልጣን ሲይዝ የ10 እና የ8 ዓመት የነበሩ ሁሉ በአሁኑ ሰዓት የ30 ዓመት ዕድሜና ከዚያም በላይ በመሆናቸው እነርሱን በከፍተኛ ደረጃ እየተጠቀመባቸው ይገኛል። ስለሆነም ይህ ወጣት ትውልድ አገሩ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ በትክክል እንዲያውቅና ዘመኑ ያመጣቸውን የመገናኛ ዘዴዎች ማለትም ኢንተርኔት፤ ዩቲዩብ፤ ኢሜይል፤ ፌስ ቡክ፤ ትዊተር፤ ስካይፕና ቫይበር የመሳሰሉ የመገናኛ ዘዴዎችን እንዲጠቀም በማስተማር በመርዳትና በማደፋፈር መረጃዎችን የመቀበል፤ የመዘገብ፤ የማስተላለፍና የማሠራጨት ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ማስተማር ይጠበቅባቸዋል።

ከዚያም በተጨማሪ ከልባቸው አምነውበት ሳይሆን ለዕለት ጉሮሮአቸው ማለትም ቤተሰባቸውን ችግር ላይ ላለመጣል ብለው በሥርዓቱ ታቅፈው ያሉትን በዘዴ በመቅረብና በማግባባት አይደግ በቀጣይ ሊተገብራቸው ያሉትን ምስጢራዊ ዕቅዶች በማወቅ ለመገናኛ ብዙኃን እንዲደርሱና በወቅቱ ለሕዝብ ይፋ የሚሆኑበትን መንገድ ማመቻቸት። ነገር ግን በዚህ ሁኔታ የማይተባበሩትን የአገር ከሐዲ ባንዳዎች ከየትኛው ቅርንጫፍ ማለትም፤ ከብአዴን፤ ከኦሕዴድ፤ ወይንም ከደሕዴግ መሆናቸውን ለይቶ፤ ዕድሉም የተሰጣቸውን ዕለትና ቀን  ጭምር፤በጥንቃቄ በልዩ ሠነድ መዝግቦ መያዝ።

እንደሚታወቀው የመጀመሪያው የቅርብ ጠላታችን ከላይ በተጠቀሱት የአይደግ ቅርንጫፎች ውስጥ ተሰግስገው ለጊዜያዊ ጥቅም ሲሉ ወገናቸውን የሚያሰቃዩ የመጀመሪያ ጠላት መሆናቸው መታወቅ አለበት። ምንም እንኳ ትዕዛዙንና መመሪያውን የሚያወጣው ወያኔ ቢሆንም ይህንን መመሪያ የሚፈጽመውና በወገኑ ላይ አሰቃቂ ሥቃይ፤ ዘረፋና ግድያ የሚፈጸመው፤ በኦሮሞው ላይ ኦሕዴድ፤ በአማራው ላይ ብአዴን፤ በደቡብ ሕዝብ ላይ ደሕዴን እንዲሁም በቀሩት ኢትዮጵያውያን ላይ የአጋር ድርጅቶች ዓባላት ስለሆኑ ባለፈው ሥራቸው ተጸጽተው ስማቸውን ለማደስ ከወገናቸው ጎን ካልተሰለፉ በስተቀር፤ እነዚህ አካላት ከወያኔ በከፋ መልኩ ከሞራል አኳያ የእኛነት ስሜት የሌላቸው ጨካኝና አረመኔዎች ስለሆኑ ምንም ዓይነት ይቅርታ ሊደረግላቸው ከቶ አይገባም።

ስለዚህ እነዚህ የወያኔ ፍርፋሪ ለቃሚ ውሾች በአንደኛ ደረጃ በጠላትነት መታየት አለባቸው። ምክንያቱም ወያኔ የወጣው ከትግራይ እንደመሆኑ መጠን እነዚህን ጥቂት አገር ከሐዲዎች በመርዳት የሥርዓቱ ደጋፊና አስፈጻሚ ባይሆኑ ኖሮ እንኳን ሃያ ሁለት ዓመት አንድ ዓመትም ሊቆዩ ባልቻሉም ነበር።

ጠላትማ ሁልጊዜም ጠላት ነው፤

አስቀድሞ መግደል አሾክሿኪውን ነው።

ብለው አባቶቻችን ከልምዳቸው ያገኙትን ተሞክሮ እንደ መመሪያ እንድንጠቀምበት ትተውልን አልፈዋል። በዚህ ፈታኝና ወሳኝ ወቅት ከተራ አገልጋይ እስከ ከፍተኛ የአሻንጉሊሊትነት ሥልጣን ደረጃ ላይ ያለ ፍርፋሪ ለቃሚ ሁሉ በክብር ወደ ወገኑ ወደ ሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ መመለስ አለበት።

ይህን የማያደርግ ግን በቅርቡ የነበረው እንዳልነበረ ሲሆን መድረሻው የት ይሆን?

አዎ ቢያንስ ከሁለት አንዱ መሆኑ አይቀርም፤ አንድም ንጹሃን አገር ወዳዶች ያለአግባብ በሚሰቃዩበት በቃሊቲ ወይም ወደ ጠርናፊያቸው መቀላቀል በፍጹም አይቀርም።

ባንዳን ጊዜ ከዳው! ድል ለሠፊው ሕዝብ!

ኢትዮጵያ እንደ ቀድሞ አባቶቻችን ሁሉ በሐቀኛ ልጆቿ አንድነቷ ጸንቶ ይቀጥላል!


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>