Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ኃይሌ ሩትስ በሚኒያፖሊስ ቀለበት አሠረ

$
0
0

hailie roots

(ዘ-ሐበሻ) በሬጌ የሙዚቃ ስልት የሚታወቀው ድምጻዊ ኃይሌ ሩትስ በሚኒሶታ ትናንት ሴፕቴምበር 15 ቀን 2013 ዓ.ም ቀለበት አሰረ። ድምፃዊ ኃይለሚካኤል ጌትነት (ኃይሌ ሩትስ) ቀለበት ያሠረው ነዋሪነቷ ሚኒሶታ ውስጥ ከሆነችው ከወይዘሪት ነዋል ስምዖን ጋር መሆኑን ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለከታል።
በዳውንታውን ሚኒያፖሊስ በተለምዶ “SEVEN Steakhouse” እየተባለ በሚጠራው ቦታ ቀለበቱን ያሠረው ድምፃዊ ሃይሌ ሩትስ ሠርጉን ኢትዮጵያ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

በዚህ የሠርግ ሥነ- ሥርዓት ላይ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ለመገኘት ሄደው የነበረ ቢሆንም ከበሩ ጀምሮ ፎቶ ግራፍ ማንሳት ክልክል ነው የሚሉ ፖስተሮች በመለጠፋቸው አንዳችም ፎቶ ግራፍ ለማንሳስት አልቻልንም። በተጨማሪም በቀለበቱ ላይ የታደሙት ወገኖችም በስልካቸው ጭምር ፎቶ ግራፍ ማንሳት እንዳልቻሉም ለማወቅ ተችሏል። “ቺጌ” በሚል አልበሙ ታዋቂነትን ያተረፈው ኃይሌ ሩትስ በአንድ ወቅት በዘ-ሐበሻ ላይ በታተመው ቃለ ምልልሱ ላይ “እኔ ብዙ ግርግር አልፈልግም፤ ብዙ መታየትም አልወድም” ሲል መናገሩን ያስታወሱት ወገኖች ምናልባትም የቀለበቱ ፎቶ ግራፍ እንዳይነሳ የከለከለው በሚዲያዎች በኩል ስሙ እንዳይነሳ ይሆናል የሚሉ አስተየት ይሰጣሉ።

ሃይሌ ሩትስ በዘ-ሐበሻ ላይ በታተመው ቃለ ምልልሱ ላይ፡ “ጥያቄ፡- የቤተሰቦችህ ሁኔታ ምን ይመስላል? የት ተወለድክ? የት አደግክ? የት ተማርክ? ከቤተሰብ ያንተን ፈለግ የተከተለ አለ?” የሚል ጥያቄ ቀርቦለት “ዘጠኝ ወንድማማቾች ነን፡፡ ሁለት እህቶች አሉኝ፡፡ ከመጨረሻ ሁለተኛ ልጅ ነኝ፡፡ እናቴ በህይወት የለችም፡፡ አባቴ አለ፡፡ አባታችን ነው ያሳደገን፡፡ ያደግሁት እንግሊዝ ኤምባሲ አካባቢ ነው፡፡ አንደኛ ደረጃን ስላሴ ካቴድራል፤ ሁለተኛ ደረጃን ደግሞ ዳግማዊ ምኒልክ ነው የተማርኩት፡፡ ከዚያ በኋላ ትምህርት አልሆነኝም (ሳቅ)፡፡ እግርኳስ ተጨዋች ነበርኩ፤ እግርኳስ በጣም ነበር የምጫወተው፤ ከዚያ እርሱን ተውኩና ወደ ሙዚቃው ገባሁ፡፡
ሙዚቀኛ በዘሬም የለም፤ እኔ ብቻ ነኝ በድፍረት የወጣሁት፡፡ ለዚያ ነው በወቅቱ ሙዚቃ ስጀምር ተቸግሬ የነበረው፡፡ መግባባት አልነበረም፤ ቤተሰብ የሚፈልገው የሃይማኖት እና ሌላ ሌላውን ሙያ ስለነበር ይህን አይደግፉትም ነበር፡፡ እና በወቅቱ ችግር ነበር፡፡” ሲል መመለሱ ይታወሳል።

ከዚህ ቀደም በዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ ላይ የታተመውን ቃለ ምልልስ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>