(ዘ-ሐበሻ) ዘ-ሐበሻ ጋዜጣና ድረገጽ በየዓመቱ አንባቢዎቻቸውን በማሳተፍ “የዓመቱ ምርጥ ሰው” በማለት ይሰይማሉ። ከ2 ዓመት በፊት መምህር የኔሰው ገብሬ በዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ምርጥ ሰው ተብሎ የተሰየመ ሲሆን ባለፈው ዓመት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አሸንፎ እንደነበር ይታወሳል። በዚህ ዓመት ዘ-ሐበሻ ለአንባቢዎቿ ባቀረበችው ጥያቄ መሠረት 598 ሰዎች በዓመቱ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ያሉትን ምርጥ ሰው ጠቁመዋል። በተለይ አንባቢዎች እስር ቤት የሚገኙ ወገኖችን አንዱን ከአንዱ ማበላለጥ እንዳይሆን የሚል ፍራቻቸውን እየገለጹ የነበረ ቢሆንም በምርጫው ሕዝቡ እስር ቤት ያሉትን ሰዎች አስታውሶ መምረጡ በራሱ የታሰሩት ወገኖች እንዳልተረሱ ያሳያል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች በሌላ በኩል ነበሩ።
የዘ-ሐበሻ 598 መራጮች ባደረጉት ምርጫ የዘ-ሐበሻ የዓመቱ ምርጦች የሚከተሉት ናቸው። (ይህ ማለት ግን ሌሎቹ ምርጥ አይደሉም ማለት ሳይሆን ብዙ ድምጽ ያገኙ ለማለት ነው)
የዓመቱ ምርጥ ሰው፦ አንዷዓለም አራጌ
የዓመቱ ምርጥ ሰላማዊ ትግል፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች
የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ (ከወንዶች)፡ ፡ ተመስገን ደሳለኝ
የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ (ከሴቶች) ፡ ርዕዮት ዓለሙ
የዓመቱ ምርጥ አክቲቪስት ታማኝ በየነ
የዓመቱ ምርጥ ስፖርተኛ መሐመድ አማን