Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Health: ተፈጥሯዊ –ብጉር ማጥፊያዎች

$
0
0

ከሊሊ ሞገስ
እዚህ ሚኒሶታ አንዳንድ ሴቶች የሞንግ ወይም የቻይና ገበያ በመሄድ የፊት ሳሙናዎችን እና ቅባቶችን በመግዛት ቡግራችንን እናጠፋለን፤ መልካችንን እናቀላለን በሚል ካለ ሃኪም ትዕዛዝ ይህን ሳሙናና ቅባት በመጠቀም ፊታቸውን ሲያበላሹ አስተውለናል። አንዳንድ ሴቶችም ወደ ዘ-ሐበሻ በመደወል “ሳሙናውና ቅባቱ ፊታችንን አበላሸው፣ አዥጎረጎረን፣ ቡግር አወጣብን” ሲሉ በ እኛ የደረሰው እንዳይደርስ ምክራችንን አስተላልፉልን ብለውናል። የዘ-ሐበሻ የጤና አምድ ሁልጊዜም ሰዎች ሳሙናም ሆነ ፊት የሚያጠራ ቅባት ከመቀባት በፊት ከቆዳ ሃኪም ጋር መነጋገር እንደሚያስፈልግ ስትመክር ቆይታለች። የኤሲያኖች ቆዳ እና የሃበሾች ቆዳ አንድ አይነት አይደለም። እነርሱን ስለጠቀማቸው ሃበሾችን ይጠቅማል ማለት አይደለም። በመሆኑም የዚህ ችግር ስለባዎች ወደ ሃኪም እንዲሄዱ በመምከር ተፈጥሯዊ የቡግር ማጥፊያዎችን እንጠቁማለን። ይህንን ያዘጋጀነውም ለግንዛቤዎ እንዲጠቅም እንጂ ሁልጊዜም ቢሆን አንድ ነገር ከማድረግ በፊት ሃኪምዎን ማማከርዎን አይርሱ።
health
ቅባታማ ምርቶችን ያስወግዱ፡- ከፍተኛ የቅባትነት ይዘት ያላቸውን የፀጉር ቅባቶች ጨምሮ የፊት ማውዣዎች (moisturizers) እና ዘይታማ ማጽጃዎችን አይጠቀሙ፡፡
የፊትዎን ንፅህና ይጠብቁ፡- ፊትዎን የእጅዎ መዳፍ ላይ በፍፁም ማሳረፍ አሊያም በተደጋጋሚ ፊትዎን መዳሰስ አይኖርብዎትም፡፡ ፀጉርዎን አዘውትረው በሻምፖ ይታጠቡ፣ ነገር ግን ፊትዎን መንካት የለቦትም፡፡
የአካል እንቅስቃሴ ያዘውትሩ፡- በመካከለኛ ደረጃ የአካል እንቅስቃሴ ማዘውተርዎ የደም ዝውውርን ከማቀለጣጠፉም በላይ መርዛማ ንጥረ ነገሮች ከሰውነትዎ እንዲወገዱ ለማድረግ ይረዳል፡፡
ከጭንቀት ነፃ ይሁኑ፡- በርካታ ጥናቶች ጭንቀት ብጉርን ከማባባሱም በላይ የቆዳ ጤንነት ችግር ላይ እንዲወድቅ ያደርጋል ይላሉ፡፡ ጭንቀት ሲያድርብዎ ከወዳጆችዎ ጋር ይማከሩ፣ የሚወዱትን ሙዚቃ ያዳምጡ፣ አሊያም ዘና ለማለት ይሞክሩ፡፡ የእግር ጉዞ ማድረግዎ ዘና እንዲሉ ያደርጋል፡፡ እነዚህን ጨምሮ ሌሎች ከጭንቀት ነፃ እንዲሆኑ የሚረዱም ነገሮችንም ይከውኑ፡፡
በቂ የፀሐይ ብርሃንና ኦክስጅን፡- የሐይ ብርሃን ቫይታሚን ዲን ለሰውነታችን ይሰጣል፡፡ ይህ ቫይታሚን ለቆዳ ጤንነት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ንፁህ አየርና የፀሐይ ሙቀት ጭንቀትን በመቀነስ በቆዳ ውስጥ የኦክስጅን መጠን እንዲጨምር ያደርጋሉ፡፡ ይሁን እንጂ ፀሐይ ላይ ለረጅም ጊዜ በመቆየት ቆዳዎ እንዲቆጣ ማድረግ አይኖርብዎትም፡፡
ብጉርን ለመቀነስና ለማጥፋት ይረዳሉ ተብለው የሚመረቱ ዘመናዊ ባህላዊ ቅባቶችና ዘይቶች በርካታ ናቸው፡፡ ብዙዎቹ ለጊዜው ችግሩን ያጠፉ ቢመስሉም ቅባቱ ካለቀ በኋላ ግን ብጉሩ ተባብሶ ሊቀጥል የሚችልበት ዕድል ሰፊ ነው፡፡ ከባህላዊም ሆነ ዘመናዊ ህክምናዎች ባልተናነሰ ተፈጥሯዊ የሚባሉት ዘዴዎች ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታ ይሰጣሉ፡፡ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
ብጉሮችን በጣትዎ አይነካኩ፡- ፊትዎ ላይ የሚታዩትን ብጉሮች በጣትዎችዎ መጫን ወይም ማሸት አይገባም፡፡ እንዲህ በሚያደርጉበት ጊዜ የፈሳሹን (sebum ይሰኛል) መጠን እንዲጨምር ከማድረግዎም በላይ ከቆዳዎ ስር ያለው አካል (membrane) እንዲቀደድ ያደርጋሉ፡፡ ኢንፌክሽኑና ፈሳሹ በቆዳዎ ስር በመዛመት ሌሎች ብጉሮች እንዲፈጠሩም ምክንያት ይሆናል፡፡ ከሁሉም በላይ በፊትዎ ላይ የማይጠፉ ጠባሳዎች የመከሰት ዕድልን እንዲጨምር ሊያደርጉ ስለሚችሉ ፊትዎን በጣትዎችዎ ማሸትን ያስወግዱ፡፡
ፊትዎን በቀን ሁለት ጊዜ በሳሙና ይታጠቡ፡- ፊታቸው ላይ ብጉር የሚታይባቸው ሰዎች ከሰልፈር (sulfur) የተሰሩ ሳሙናዎችን እንዲጠቀሙ ይመከራል፡፡ ቆዳዎ በተፈጥሮው ባለ ወዝ (oily) ከሆነ benzoyl peroxide የተካተተበት ሳሙና ይጠቀሙ፡፡ ፊትዎን በስፖንጅና በሌሎችም ሻካራ ጨርቆችና ብሩሾች እየሞዠቁ እንዳያጥቡ፡፡
- ብጉሩን ያብሰዋል እንጂ አያጠፋውም፡፡
ፊትዎን ከሁለት ጊዜ በላይ ደጋግመው በማጠብ እንዳያደርቁት መጠንቀቅ ይኖርብዎታል፡፡ የቆዳ ዕጢዎች ፊትዎ የደረቀ ከመሰላቸው ብዙ sebum እንዲመረት በማድረግ ብጉሩ እንዲስፋፋ ምክንያት ይሆናሉ፡፡
ምግብና ብጉር፡- ለበርካታ ሰዎች የምግብ አለርጂ ለረጅም ጊዜ የማይጠፋ ብጉር እንዲፈጠርባቸው ሊያደርግ ይችላል፡፡ ብጉር ፊታቸው ላይ የሚታይባቸው ሰዎች ቅባትና ቅመማ ቅመም የበዛባቸው ምግቦች አብዝተው እንዲወስዱ ይመከራል፡፡ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች በወተት ውስጥ የሚገኙ ሆርሞኖችና በባህር ምግቦች ውስጥ የሚገኘው ከፍተኛ የአዮዲን መጠን ብጉርን እንደሚያባብሱ ተደርሶበታል ይላሉ፡፡ ከተቻለ እነዚህ ምግቦች አይወሰዱ፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ ስኳር፣ የወተት ተዋፅኦዎች፣ ለረጅም ሰዓት ሲጠበሱ የቆዩ ምግቦች፣ ስጋ፣ የኦቾሎኒ ቅቤ እና የመሳሰሉት ቅባታማና ዘይታማ ምግቦችን ያስወግዱ፡፡ ከዚህ በተቃራኒው አረንጓዴ ተክሎች፣ የአትክልት ጭማቂና በዚንክ የበለፀጉ ምግቦች ብጉርን ለመቀነስ ይረዳሉ፡፡
ውሃ ይጠጡ፡- ሲባል በመጠኑ በርከት ያለ መሆን ይኖርበታል፡፡ ጄኒፈር ቶደን የተባሉ የብጉር ኤክስፐርት በቀን ስምንት ብርጭቆ ውሃ በመጠጣት ብጉርን መከላከል እንደሚቻል ይመክራሉ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ውሃ ቆሻሻን ከሰውነታችን ሲስተም ማስወገድ ስለሚችል ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሰውነታችን ብጉርን እንዲከላከልና እንዲያድን ይረዳዋል፡፡
ሜክአፖችን አይጠቀሙ፡- የተለያዩ የሜክአፕ ምርቶች ብጉርን ሊያስከትሉ ስለሚችሉ በተቻለ መጠን ባይጠቀሟቸው ይመከራል፡፡ እነዚህ መኳኳያዎች ብጉር እንዲስፋፋ ያደርጋሉ፡፡ የግድ መጠቀም አለብኝ ካሉ ደግሞ መሰረታቸው ውሃ የሆነ (water based) ሜክአፖችን ምርጫዎ ያድርጉ፡፡ የሜክአፕ ብሩሾችዎን በቋሚነት ያጽዱ፤ እንዲሁም ወደ መኝታዎ ከመሄድዎ በፊት ፊትዎንና ሜክአፕ የነካውን አካል ይታጠቡ፡፡
የወይራ ዘይት
- የጓሮ አትክልት መንከባከቢያ ቁሳቁሶችን በቀላሉ ለማጽዳት ያስችላል፡፡
- የቤትና የቢሮ ፈርኒቸር ያሳምራል፡፡
- በቀላሉ ከዓይን ላይ ሜክአፕ ለማስለቀቅ ይረዳል፡፡
- ከማይዝግ ብረት የተሰሩ (stainless steel) ቁሶች እንዲያንፀባርቁ ያደርጋል፡፡
- የካጄት አሊያም የሱሪዎ ዚፕ ተቀርቅሮ አልንቀሳቀስ ካለ የወይራ ዘይት ጠብ ያድርጉበት፡፡
- የቆዳዎን ልስላሴ ይጠብቃል፡፡
- ማንኳራፋትን ያስወግዳል፡፡
- የኩራዝ መብራት ሆኖ ማገልግል ይችላል፡፡
- አንዳንድ ስቲከሮች የተዉትን ማጣበቂያ ያስወግዳል፡፡
- ለጉሮሮ ህመም ፈውስ ይሰጣል፡፡
- የጆሮ ህመምን ያስታግሳል፡፡
- ጺምዎን ከተላጩት በኋላ ጥቂት የወይራ ዘይት ይቀቡት፡፡ ልስላሴው ያስደስትዎታል፡፡
- ጫማዎን ቢጠርጉበት ያሳምርልዎታል፡፡
- ጥሩ የፀጉር ቶኒክ ነው፡፡
- ገላዎን ገንዳ ውስጥ የሚለቃለቁ ከሆነ የወይራ ዘይት ጠብ ያድርጉበት፡፡ S


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>