ከታሪኩ ደሳለኝ
የጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚ ችሎት ለዛሬ የተመስገን ፍርድ ላይ የህግ ሰህተት አለበት የለበትም የሚለው ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል። ሆኖም ዛሬ አዲስ የተቀየሩት ደኞች የሰበር ውሳኔውን ለመወሰን የስር ፍርድ ቤቱ ለህገ መንግስት አጣሪ ኮሚሽን መቅረብ የለበትም ብሎ ብይን የሰጠበትን ሰነድ አቅርቡና ወሳኔውን ለሐምሌ 30/2007 ዓም ከሰዓት በ8:00 ሰዓት እንሰጣለን በማለት ፍርድቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተል።