Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በረከት ስምዖን ደክመዋል

$
0
0
በረከት ስም ዖን እና ባለቤታቸው ወ/ሮ አሰፉ

በረከት ስም ዖን እና ባለቤታቸው ወ/ሮ አሰፉ

* በጥቂት ቀናት በ እንግሊዝ; በጀርመን እና በሳዑዲ አረቢያ ህክምና ውስጥ ነበሩ
* በልብ በሽታ የተነሳ ከመጠጥ ከብስጭት እና ከአልኮል መጠጦች እንዲርቁ ተመክረው ነበር
* ሳዑዲ አረቢያው ብግሻን ሆስፒታል በሕይወት ብዙም እንደማይቆዩ ተነግሯቸዋል
* በረከት ለወ/ሮ አሰፉ “ከዚህ በኋላ የምተርፍም አይመስለኝም” ብለዋቸዋል

 

(ዘ-ሐበሻ) ለኢትዮጵያ ውድቀት ተጠያቂ ከሆኑት ሆዳም የብአዴን መስራች አባላት ውስጥ አንዱ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን የጤና ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ:: ለአቶ በረከት ህክምናም ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ እየፈሰሰ ነው::

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን በሳዑዲ አረቢያ ሲደረግላቸው የቆየው ህክምና ምንም ሳይረዳቸው በመቅረቱ በቅርብ ቀናት ውስጥ ህመማቸው ተባብሶ ወደ እንግሊዝ ሃገር ተጉዘው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ እዚያው እየተላከ ሲታከሙ ቢቆይም ከህመማቸው ሊድኑ አለመቻላቸው ተገልጿል::

የ እንግሊዝ ሃገር ህክምናውም ያልረዳቸው አቶ በረከት ወደ ጀርመን ሃገር ለተሻለ ህክምና ሄደው የነበረ ቢሆንም ያም ቢሆን ውጤት አልባ እንደሆነባቸው የቅርብ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ አስታውቀዋል:: ለአቶ በረከት ስምዖን ህክምና በሳዑዲ አረቢያና በደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ወጪ እየወጣ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ በ እንግሊዝ ሃገር እና በጀርመን ከፍተኛ ገንዘብ እየወጣ ቢታከሙም ውጤት እንደጠፋ የገለጹት ምንጮች አቶ በረከት ለባለቤታቸው ወ/ሮ አሰፉ “ካሁን በኋላ ዋጋ የለኝም:: በሕይወት የምቆይም አይመስለኝም:: ወደ ሃገሬ መልሱኝና እዚያው እንደሆንኩ ልሁን” እንዳሉ አስታውቀዋል::

በረከት ለንደን ለህክምና ሲሄዱ የተነሱት ፎቶ

በረከት ለንደን ለህክምና ሲሄዱ የተነሱት ፎቶ


በጤናቸው ከፍተኛውን ተስፋ የቆረጡት አቶ በረከት ሕይወታቸው በአስጊ ሁኔታ ላይ እንዳለ የቅርብ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::

በሌላ በኩል ጅዳ የሚገኘው ኢትዮጵያ ሃገሬ አቶ በረከት ከጀርመን ህክምና መልስ ሳዑዲ አረቢያ እንደነበሩ ዘግቧል::

እንደዘገባው ከሆነ በልብ በሽታ የሚሰቃዩት አቶ በረከት ለህክምና ጅዳ ሳውዲ አረቢያ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ህክምናቸውን ተከታትለው ወደ ሃገር ከተመለሱ ወዲህ የጤንነታቸው ሁኔታ እንብዛም ባለመስተካከሉ አመት ባልሞላ ግዜ ውስጥ ለሁለተኛ ዙር ወደ ሳውዲ አረቢያ « ብግሻን» ሪፈራል ሆስፒታል ማቅናታቸው የታወሳል::

አቶ በረከት ስሞኦን ከብስጭት ከተለያዩ የአልኮል መጠጦችና ከአይምሮ አደንዛዥ እጽ እንዲርቁ ተመክረው ጤንነታቸው አሰተማማኝ ደረጃ እስኪ ደርስ የዶክተሮች ቅርብ ክትትል እንደሚያሻው ተነግሯቸው በቀጠሮ ቢሸኙም የቀጠሮ ግዜያቸውን አክብረው ዶክተሮቻቸው ጋር መቀረብ አለመቻላቸውን የሚገልጹ የሆስፒታሉ ምንጮች ባለስልጣኑ በህይወት መኖራቸውን ይጠራጠራሉ። ጅዳ « ብግሻን» ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የልብ ቧንቧ ማስፋት ህክምና የተደረገላቸው የኢ.ህ.አ.ዴ.ጉ ሹም የጤነነት ሁኔታ የሚጠበቀውን ያህል ለወጥ አስይቶ እንዳል ነበር ሙያዊ ትንታኔ የሚሰጡ ምስጢራዊ የሆስፒታሉ ምንጮች በሽታው የልብ እንደ መሆኑ መጠን ባልታሰበ ግዜ ባለስልጣኑን ለሞት ሊዳርጋቸው እንደሚችል ከአቶ በረከት ጋር ለመጣ አስታማሚ ገልጸው እንደ ነበር ያስታውሳሉ። በዚህም መስረት አቶ በረከት ስሞዖን ለሶስተኛ ግዜ ልባቸውን መታየት እንዳለባቸው ተነግሮቸው ቢሰናበቱም በቀጠሮ ቀን ተገኝተው ህክምናቸውን መከታተል ባለመቻላቸው በጤናቸው ላይ ሊያደርስ የሚችለው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን የሚያሳየው የምርመራ ውጤት በረከት ሌላ ሃገር ለህክምና ሄዶ ካልሆነ በቀር አሁን ባሉበት ሁኔታ የልብ በሽታው አደጋ ሊጥላቸው እንደሚችል ተገልጿል:: ። በአቶ በረከት ስሞን ጤንነት ዙሪያ ከጅዳ «ብግሻን» ሆስፒታል ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት እናደርጋለን ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>