Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Sport: ሰርጂዮራሞስ ወደ ኦልድትራፎርድ?

$
0
0

ማንችስተር ዩናይትድ በ2009 ፕሪ ሲዝን ፖርቹጋላዊው ኢንተርናሽናል ክርስቲያኖ ሮናልዶን ከሪያል ማድሪድ ከሸጠ ወዲህ በሁለቱ የዓለማችን ታላላቅ ክለቦች መካከል በግዙፍነቱ አቻ የማይገኝለት የዝውውር ውል ሊፈርም ተቃርቧል፡፡ ውሉ የሚያመለክታቸው ተጨዋቾች የስፔን ኢንተርናሽናሎቹ ዳቪድ ዳሂኦና ሰርጂዮ ራምስ ናቸው፡፡ ሪያል ማድሪድ ከወዲሁ ዳሂአን ለማንችስተር ዩናይትድ ለመግዛት ያቀደ መሆኑ ይታወቃል፡፡

Sergio Ramos Wallpapers (2)አሁን ደግሞ የማንቸስተር ዩናይትድ ኃላፊዎች ከዳሂአ የዝውውር ውል ስፔናዊው የተከላካይ መስመር ተጨዋች የዳሂአ የዝውውር አካል ሆኖ በልዋጩ ወደ ክለቡ የሚመጣበት ሃሳብን አቅርቧል፡፡ ሪያል ማድሪድ በ2005 ከሲቪያ ያስፈረመው ዋጋ 65 ሚሊዮን ዩሮስ ቢሆንም በሁለቱ የዓለማችን ሀብታም ክለቦች መካከል በሚደረገው ስምምነት ግን ይህ ዋጋው ዳቪድ ዳሂአን ከኦልድትራፎርድ ወደ ሳንቲያጎ በርናባ የሚሸኝ በመሆኑ የማውረድ ጥረት ይደረግበታል፡፡

የ29 ዓመቱ ስፔናዊ ተከላካይ ከወዲሁም ባለፈው ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ የሪያል ማድሪዱ ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ጣሊያናዊው አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲ ከሥራቸው በሸኙበት ተግባራቸው ቅር እንዳሰኘው መናገሩ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ባሻገር የክለቡ ኃላፊዎች የገቡለት ቃልን በማክበር የኮንትራት ማራዘሚያ ውል ሳይፈቅዱለት መቅረታቸው አስገራሚ ሆኖበታል፡፡

ከዚህ በፊት ሪያል ማድሪድ ለራምስ የገባለት ቃል የዓመት ደመወዙን ወደ 10 ሚሊዮን ዩሮስ ከፍ የሚያደርግበት የኮንትራት ማራዘሚያ ውል ይፈቅዱለታል የሚል ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ከሪያል ማድሪድ ጋር ያለው እስከ ጁን 2017 ድረስ የሚዘልቀው የኮንትራት ውሉ ግን በዓት የሚያስገኝለት 6 ሚሊዮን ዩሮስ ነው፡፡ ከመሀል ተከላካይ ሚና ባሻገር በሁሉም የተከላካይ መስመር ቦታዎች ላይ ለመሰለፍ የሚችልበት ሁለገብ ብቃትን የተላበሰውን የራምስን ቅሬታን ይበልጥ ያባባሰው ባለፉት 12 ወራት ውስጥ የሌሎቹ የሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች ኮንትራት ውል ሲታደስ የእሱ ግን ችላ ተብሎ መዝለቁ ነው፡፡

በተለይም በክለቡ ደጋፊዎች የተጣለው ዌልሳዊው ኢንተርናሽናል ጋሬዝ ቤል የዓት ደመወዙን ከ9 ሚሊየን ዩሮስ ወደ 10 ሚሊየን ዩሮስ ከፍ ያደረገለት የኮንትራት ማራዘሚያ የዛሬ ዓመት ተፈቅዶለታል፡፡ በሌሎች ታላላቅ ክለቦች የሚገኙ የመሃል ተከላካይ ሚና ባለቤቶች ዓመታዊ ደመወዝም ከራምስ በላይ ነው፡፡ በተለይ ብራዚላዊያኖቹ ቲያጎ ሲልቫና ዳቪድ ዳሂአ በፒኤስጂ የሚፈላቸው ዓመታዊ ደመወዝ 12 ሚሊየንና 11 ሚሊየን ዩሮስ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ጆን ቴሪና ዤራርድ ፒኬን የመሳሰሉት የመሀል ተከላካይ ሚና ባለቤቶችም ከራምስ በላይ የደመወዝ ክፍያን በማግኘት ላይ ናቸው፡፡ በዚህ መልኩ ራምስ ለድፍን 10 ዓመታት የዘለቀበት ሪያል ማድሪድን የመልቀቅ ሃሳብን መያዙን ከግንዛቤ በማስገባትም ለባርሴሎና ፕሬዝዳንትነት ምርጫ እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ጆርዲ ማጅ ራምስና ከሪያል ማድሪድ የመግዛት እቅድን ይዘዋል፡፡

ሆኖም ግን የ20 ዓመቱ ስፔናዊ ኢንተርናሽናል ከዚህ በፊት በሰጣቸው መግለጫዎች ሪያል ማድሪድን ለመልቀቅ የሚገደድ ከሆነ የመጀመሪያው ምርጫው ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በማምራት መጫወት እንደሚሆን መናገሩ የተለመደ ነው፡፡ ለበርካታ ወራቶች ስማቸው ከማንቸስተር ዩናይትድ ዝውውር ጋር በስፋት ሲያያዝ የዘለቀው የሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች ጋሬዝ ቤልና ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ቢሆንም አሁን ግን ሆላንዳዊው አሰልጣኝ ሉዊ ቫንሃል ዳቬድ ዳሂአን በሪያል ማድሪድ የሚነጠቁ ከሆነ አጠቃላዩ የቡድኑ የተከላካይ መስመር እንደሚጎዳ ከግንዛቤ በማስገባት ራምስን ማግኘትን የመጀመሪያው ምርጫቸው አድርገውታል፡፡ በሪያል ማድሪድ ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ እስካሁን ድረስ የራምስን ኮንትራትን የማራዘም ምንም አይነት ፍላጎት የሌላቸው መሆኑም ስፔናዊው የተከላካይ መስመር ተጨዋች ኦልድትራፎርድ የመድረሱ ተስፋን የበለጠ እያሰፋው የመጣ ጉዳይ ሆኗል፡፡

ከ2009 እስከ 2013 ድረስ ለአትሌቲኮ ማድሪድ የተሰለፈው ዳቪድ ዳሂም ማንቸስተር ዩናይትድን በመልቀቅ ወደ ሪያል ማድሪድ የማምራቱ ተስፋ ሰፊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በርካታዎቹ የእንግሊዝ ጋዜጦች ሰሞኑን ባቀረቡት ዘገባ ዳሂኦ ለማንቸስተር ዩናይትድ አንዳንድ ተጨዋቾች ወደ ማድሪድ ከተማ ተመልሶ ለመጫወት መወሰኑን እንደነገራቸው ጠቁመዋል፡፡ ዳሂአ ከማንቸስተር ዩናይትድ የቀረበለት 200 ሺ ፓውንድ የሳምንት ደመወዝን የሚያገኝበት የኮንትራት ማራዘሚያ ጥሪን ከወዲሁ ያልተቀበለው መሆኑ ይታወቃል፡፡
የስፔን ብሔራዊ ቡድን ጓደኛው ሁዋን ማታ በጉዳዩ ዙሪያ በትናንትናው ዕለት በሰጠው መግለጫው የ2014-15 ሲዝን የክለባቸው ኮከብ ተጨዋች ሆኖ የተመረጠው ዳሂአ ለተጨማሪ ዓመታት በማንቸስተር ዩናይትድ እንዲቆይ ከፍተኛ ጉጉትን ማሳደሩን አረጋግጦ የዳሂኦ ፍላጎት ግን ወደ ሪያል ማድሪድ ማምራት ከሆነ ውሳኔውን ልናከብርለት ይገባል ብሏል፡፡

ማታ በመቀጠልም በሰነዘረው አስተያየት ‹‹በርካታ ጉዳይ በዳሂአ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ ጥያቄን ያቀርቡልኛል፡፡ የእኔ የቅርብ ጓደኛ እንደመሆኑ ከክለባችን እንዲለይ በጭራሽ አልመኝም፡፡ በአሁኑ ወቅት በዓለም ፉትቦል እጅግ ወሳኙ ግብ ጠባቂ በመሆኑም እኔ በግሌ በማንቸስተር ዩናይድ ለተጨማሪ ዓመታት እንዲቆይ ያለኝ ፍላጎት እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ሆኖም ግን ውሳኔው ከዚህ የተለየ ከሆነ በሄደበት መልካም ነገሮች እንዲገጥሙት በመመኘት ከመሸኘት በስተቀር ሌላ አማራጭ ሊኖረን አይችልም›› ብሏል፡፡
የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሉዊ ቫንሃል የሪያል ማድሪድ ተከላካይ ሰርጂዮ ራምስን የዳሂአ ዝውውር አካል አድርገው ለማግኘት እቅዳቸው ባሻገር የ24 ዓመቱ ስፔናዊ ግብ ጠባቂን ለመተካት የሚችልላቸው አስተማማኝ ብቃት ያለው ግብ ጠባቂ የመግዛት ሃሳብ አላቸው፡፡ ለዚህ ተግባራዊነት የቅድሚያ ሙሉ ትኩረታቸው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ቁጥር አንድ የሆነው ሁጎ ሎሪስን ከቶተንሃም ሆትስበርስ መግዛት ነው፡፡ ሆኖም ግን የቶተንሃም ኃላፊዎች በሁጎ ሎሪስ ላይ ያወጡት 35 ሚሊዮን ፓውንድ ዋጋ ለቫንሃል የሚዋጥላቸው አልሆነም፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>