Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ተገልብጦ 21 ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ * 39 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

$
0
0

tigray
(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የሚደርሱ የመኪና አደጋዎች ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ነው:: በዚህ ዓመት እንኳ በዘሐበሻ ላይ በርከት ያሉ የመኪና አደጋዎችንና ካስከተለው የሰው ሕይወት መጥፋት ጋር ዘግበናል:: ከሃገር ቤት የመጣ ዜና እንደሚያስረዳው ትናንት በትግራይ ክልል የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ተገልብጦ 21 ሰዎች ሕይወታቸው መጥፋቱን ነው::

በትግራይ ክልል በክልተአውላዕሎ ወረዳ ነጋሽ በተባለ ቀበሌ አደጋው የደረሰው ከአክሱም ወደ አዲስ አበባ 63 መንገደኞች አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥሩ 51672 ኢትዮጵያ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ነጋሽ በተባለ ቀበሌ አቅጣጫ ስቶ 300 ሜትር ጥልቀት ባለው ገደል በመግባቱ ነው ሲል የአካባቢው ፖሊስ ገልጿል::

በዚህ አሰቃቂ የመኪና አደጋ 39 ሰዎች በከባድ የቆሰሉ ሲሆን ሶስት ሰዎች ብቻ ናቸው ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሲል ፖሊስ አስታውቋል::


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>