ሐምሌ 2 /2004 ለሊት ሰባት ሰዓት ማዕከላዊ የደረሰው ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት የደረሰበትን አሰቃቂ ድርጊት አስረድቷል፡፡ በዚህ የተበሳጩት የማዕከላዊ ቢሮ ቁጥር 49 መርማሪዎች ኢንስፔክተር አለማየሁ፣ዘመድኩንና ጸጋዬ የተባሉ የሱፍን ከፍርድ ቤት መልስ ቢሯቸው ድረስ በማስመጣት ‹‹ፍርድ ቤት ሄደህ መጥሪያ ይዘህልን መጣህ አሉ ባክህ?›› ‹‹የደረሰብኝን ከመናገር ውጪ ምን አጠፋሁ?›› ባገኙት ነገር ሁሉ ወረዱበት ጾሙን ለመፍታት እየተዘጋጀ የነበረው የሱፍ ዱላውን መቋቋም ተስኖት ተዝለፍልፎ ወደቀ ፡፡
መርማሪዎቹ ቂም ቋጥረው በየቀኑ ከባድ ስፖርቶችን በማሰራት ይደበድቡት ነበር፡፡በመጨረሻም ባላነበበውና ቃሉን ባልተቀበሉት ሁኔታ መርማሪዎቹ ባዘጋጁለት የቃል መቀበያ ወረቀት ላይ እንዲፈርም አደረጉት፡፡
ኢንስፔክተር አለማየሁ –ሱሪህን አውልቅ አለኝ
የሱፍ — አላወልቅም አልኩት፡፡
መርማሪው– ለምን ?
የሱፍ — እኔ ወንድ ነኝ የወንድን ገላም ለማየት
አልናፍቅም፡፡ከፈለግክ አንተ መጥተህ አውልቀው አልኩት፡፡
እናም መሬት ላይ አስተኝተው ደበደቡኝ ።
↧
ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት የደረሰበትን አሰቃቂ ድርጊት
↧