Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ጆን ዶ የተሰኘው ኢትዮጵያዊ አማሪካዊና እና የኢትዮጵያ መንግስት በዲሲ ፍርድ ቤት

$
0
0

ቢላል አበጋዝ

ጁላይ 13፡2015

justiceዛሬ በዲትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ በዋለው ችሎት ጆን ዶ የተሰኘው ኢትዮጵያዊ አማሪካዊና እና የኢትዮጵያ መንግስት ጠበቆች ቀርበው ሁለቱም ወገኖች ዳኛው ፊት ቃላቸውን ሰጥተዋል።ጆን ዶ የተሰኘው ኢትዮጵያዊ አማሪካዊ የተሰጠው ስም (ጆን ዶ)  ይህ ስያሜ ስማቸው በግልጽ መገለጥ ለሌለባቸው ሰዎች በጅምላ የሚሰጥ ነው።ጆን ዶ ተብሎ መቅረቡ የክሱ መስራች የኢትዮጵያ መንግስት ወይም ወኪሎቹ ይህን ዜጋ ለይተው እንዳያጠቁት በሚል ወይም ስሜ ቢጠቀስ ጉዳት ያገኘኛል ከሚለው ስጋት ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት  ያቆማቸው ጠበቃ ግሪንበርግ ቱሪግ (Greenberg Traurig LLP)ለተባለ እዚህ ዋሽግቶን ዲሲ ለሚገኝ የጥብቅና ተቋም ሰራተኛ ናቸው።ኢትዮጵያዊ አማሪካዊውን ግለሰብ የወከሉት ኤሌክትሮኒ ፍሮንቲር ፋውዴሽ ከተሰኘ ድርጅት የቀረቡ ጠበቆች ነበሩ (Electronic Frontier Foundation) ዋና ድሬክተርዋ ሲንዲ ኮህን የተባሉ ሲሆኑ “ነጻነትና የሰው መብት ሲደፈር ፈጥነው የሚክላከሉ” በማለት ብሄራዊ የአማሪካ ጠበቆች መጻሄት( National Law Journal)ያደነቃቸው ናቸው።በእለቱ የኢትዮጵያዊ አማሪካዊውን ጉዳይ ያቀረበው ናታን ካርዶዞ የተባለው የዚሁ ድርጅት ጠበቃ ነበር።

ክሱ የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያዊ አማሪካዊው ላይ ያደረገው ህገወጥ ድርጊት የኮምፑተር ቫይረስ በመላክ ሰርስሮ በድብቅ ተኮምፑተር ገብቶ ቫይረሱ በኮምፑተሩ ይቀበርና ስለላን ለማካሄድ የሚያስችል የተንል መሳሪያ በተግባር ላይ ማዋል ነው።ይህን ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት የተለያዩ ኩባንያዎችን ተጠቅሟል። ወያኔ ዳቪድ ቪንቼንዜቲ በተባለ ጣሊያናዊ የሚመራ ሰርሳሪ ቡድን (The Hacking Team) የተባለ ኩባንያንም ተጠቅሟል።ኩባንያው ሚላኖ ኢጣሊያ የሚገኝ ነው።አገልግሎቱን ለሱዳን ሞሮኮ ግብጽ ከኢትዮጵያ ሌላ የሰጠ ሲሆን ስለ ኢትዮጵያ ሲጠየቅ ክዷል። ጋርዲያ የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው።

በአማሪካን አገር ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የግለሰቡ መብት በመንግስት አካላት አይደፈርም። ያገሩ መንግስት ያልደፈረውን ህወሃት መሩ መንግስት ተዳፍሯል በማለት የከሳሽ ጠበቃ ሲናገር የተከሳሽ ጠበቃ ድርጊቱ እዚህ አማሪካ አልተፈጸመም የሚል ክርክር ዳጋግሞ አቅርቧል። ቀድሞ ባአማሪካ ዜጎች ላይ ተደርገው ነበር የሚላቸውን ክሶች አጣቅሷል። የከሳሽ ጠበቃ ህገ መንግስታዊ መርሆዎችን፡ስለላ የማካሄድን (መንግስት ከፍርድ ቤት አስፈቅዶ) ስለላው እዲደረግ ገፊ ምክንያቶችን ሁሉ የሚነካ ጉዳይ መሆኑን አስዘግቧል። ፍርድ ቤቱ የሚደርስበት ውሳኔ የህወሃት መሩ መንግስትን ተረቺ ካደረገ ይላል ጠበቃው የአሜሪካንን የስለላ ተቋማትን ሳያሳስብ አይቀርም። ለአጃዚራ እንደሰጠው ቃል።

እንደሚታወሰው ህወሃት መሩ መንግስት ይህኑ የስለላ ተግባር በሚሊዮኖች የሚቆጠር ንዋይ አፍስሶ እነ እስክንድር ነጋ ላይ “መረጃ” አቀረብሁ ማለቱ ይታወሳል።መእራባውያን መንግስታት አይቶ እንዳላየ የሚሆኑት ዛሬ ህወሃት መሩ መንግስት በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ምእራቡን የሚያሳስበውን ሽብርተኝነት ለመዋጋት እንዳአጋር በመወሰዱ ነው።

ህወሃት መሩ መንግስት ልማት ሊያራምድ የሚችሉትን የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በተግባር ለማዋል ቀርቶ ለስለላው መሽቀዳደሙ የመንግስቱ እኩይ ባህሪ ግፊት መሆኑን ከፍርድ ቤቱ መጥተው የታዘቡ ተናግረዋል።

በፍርድ ቤቱ የዲሲ ሜትሮ ነዋሪዎች፡የኢሳትና የቪኦኤ ጋዜጠኛች፡የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተገኝተው ነበር።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>