ሰኔ 26/2007
ኢሳት በኣምስት ዓመታት በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭ የኢትዮጵያውያን ከፍተኛ የመረጃ ምንጭ ሆኖ አገለግሏል፥ለሀገራቸው በጎን የሚመኙና የነጻነት ርሃብ ያለባቸው ኢሳትን ማየት እና መስማት በቻ ሳይሆን በአቅማቸው እየደገፉ ኢሳትን የነጻነት ብርሃን አድርገው ይመለከቱታል::
ያለ ክፍያ ኢሳትን የሚያዩና የሚያደምጡ፣ ነገር ግን ለኢሳት መቃብር የሚቆፍሩ ገዢዎች እና ደጋፊዎቻቸው ከቁጥራቸው ይልቅ አቅማቸው ከባድ ቢሆንም ዕውነት እና ሕዝባዊ ዓላማ ሰንቆ ኢትዮጵያዊ አርማ የሚያውለበልበው ኢሳት በኢትዮጵያውያን ድጋፍ መሰናክሉን እየሰበረ ቀጥሏል፣ኢሳት የተደቀኑበትን ዘርፈ-ብዙ ጋሬጣዎችን ሁሉ እየተሻገረ ተሰሚነቱ እየጨመረ እና አቅሙ እየጎለበተ ሄዷል።
ኢሳት በኢትዮጵያ ምድር እንዳይታይ ከሳተላይት ለማውረድ አምስት ኦመታት ሙሉ በተደረገው የመንግስት ርብርብ 15 ያህል ሳተላይት ለመቀየር ብንገደድም፣ለሳተላይት አቅራቢ ኩባንያዎች የተማጽኖ ደብዳቤ በመጻፍ እና መደለያ በማቅረብ እንዲሁም ዋሺንግተን ፖስትን የመሳሰሉ ታዋቂ የምዕራብ ሚዲያዎች ጭምር እንደዘገቡት ኢሳት ላይ የሳይበር ጥቃት ቢሰነዘርም ሁሉንም ተቋቁመን ለ 5ኛው ዓመት ደርሰናል፥ ግባችን ዓመታት መቁጠር ሳይሆን ነጻነት በመሆኑ የእሮሮ ድምጾች በደስታና ድል ሲመነዘሩ ማየትና መስማት ይህንንም ማድረስ ተስፋችን ነው።
የኢሳት አስተዳደር እና የቴኪኒክ ባለሙያዎች ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ኢሳት የአየር ላይ ጥቃቱን ተቋቁሞ ሁለት አመታት ያህል ያለምቋርጥ በኢትዮጵያ ምድር በአሸናፊነት ሲታይ ቆይቶ ከወር በፊት የባዕዳን ድጋፍ ታክሎበት ከአየር ላይ ለመውረድ የተገደደ ቢሆንም፣ መሰናክሎችን ለማለፍ በተደረገ ጥረት የ24 ሰዓት የሳተላይት ሬዲዮያችን ወዲያውኑ ተመልሷል፣ 24 ሰዓታት በመደመጥ ላይ ይገኛል። ቴሌቪዥኑን ለመመለስ የተደረገው ጥረትም ከሃሙስ ሰኔ 25/2007 (ጁላይ 2/2015) ጀምሮ ፍጻሜ በማግኘቱ ኢሳት ወደ አየር ተመልሶ የሙከራ ስርጭት ቀጥሏል። ለማፈን የሚንቀሳቀሰው ሃይል ለማፈን ካለው እልህ በላይ ቆርጠን የምንሰራ በመሆናችን ፈተናው ቢቀጥልም በማናቸውም ሁኔታ ኢሳት ወደኋላ እንደማይመለስ ማረጋገጥ እንሻለን።
ይህንን ሁሉ ፈተና እየተጋፈጥን እንድንቀጥል ጉልበት የሆነን በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እና በሃገር ቤት ያለው ወገናችን የነጻነት እና የፍትህ ርሃብ በመሆኑ አሁንም ድጋፋችሁ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ እያቀረብን አዲሱ ሳተላይት የሚከተለው መሆኑን እንገልጻለን።
Satellite: AM 4411 Degrees West
Frequency: 11040, 9320
Symbol Rate: 2200
Frequency: 3/4 Vertical
የኢሳት አስተዳደር
The post ኢሳት ወደ አየር ተመለሰ – appeared first on Zehabesha Amharic.