Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የቴዲ አፍሮ ባለቤት አምለሰት ሙጩ የሆስፒታሎች አምባሳደር ልትሆን ነው

$
0
0

teddy afro and ameslet
ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሆስፒታሎችን ንፁህና ፅዱ /Clean and save Hospital- CASH/ በማድረግ
ለታካሚዎች፤ለጤና ባለሙያዎችና ለተገልጋዩ ህብረተሰብ የተሻለ የጤና አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል የጤና ተቋማትን ምቹ የማድረግ ዘመቻ የጀመረ ሲሆን ለዚሁ ዘመቻ በሙያዋ ቅስቀሳ እንድታካሂድ የዝነኛው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ባለቢኤት አርቲስትና ሞዴል አምለሰት ሙጩን አምባሳደር አድርጎ መርጧል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ይህንን ትግበራ ከጀመረባቸው ሆስፒታሎች መሀከል አንዱ የሆነው በራስ ደስታ ሆስፒታል ሲሆን የአዲስ አባባ ጤና ቢሮ ከአብት አሶስየት ፕሮጀክት Abt project Associate-HSFR/HFG project ጋር በጥምረት የሚያካሂደው ዘመቻ ሆስፒታሎችን ንፅህና ፅዱ በማድረግ ምቹ አካባቢን የመፍጠር ዓላማ አለው፡፡ አዳዲስና ዘመናዊ ሆስፒታሎች እስከሚገነቡ ድረስ ያሉትን ሆስፒታሎች ለአገልግሎት ንፁህና ምቹ በማድረግ የተሻለ የጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ የመስጠት እቅድም ተይዟል፡፡
ባለፈው ግንቦት 9 ቀን 2007 ዓ.ም የራስ ደስታ ሆስፒታል ማኔጅመንት አባላትና የአብት አሶስየት ፕሮጀክት ሃላፊዎች እንዲሁም አርቲስት አምለሰት ሙጩ በተገኘችበት የጉብኝት ፕሮግራም ተካሂዷል፡ ፡ የራስ ደስታ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ምትኩ ጨመዳ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር አርቲስት አምለሰት ሙጩ በራስ ደስታ ሆስፒታል የተጀመረውን የህክምና አካባቢን ንፁህና ምቹ የማደርግ ዘመቻ ላይ ለመሳተፍና በአምባሳደርነት ሀላፊነቷን ለመወጣት ፍቃደኛ መሆኗን አድንቀው ሆስፒታሉ ንፅህና ምቹ መሆኑ ሆስፒታሉ የእናቶችንና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ እያደረገ ላለው እንቅስቃሴ አጋዥ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ameleset
የአብት አሶስየት ፕሮጀክት ዋና ዳይሬክትር አቶ ሉዑልሰገድ አገዘ እንደተናገሩት ግንቦት 23 ቀን 2007 ዓ.ም የራስ ደስታ ዳምጠው ቤተሰቦች፤የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና የአዲስ አበባ የጤና ቢሮ የስራ ሀላፊዎች፤ የራስ ደስታ ሆስፒታል ማኔጅመንትና የአስተዳደር ሰራተኞች በሚገኙበት ሥነ ሥርዓት ላይ አምለሰት አምባሳደር ሆና እንድትሰራ ሃላፊነቱ እንደሚሰጣትና ይኸውም ለህዝቡ በይፋ እንደሚገለፅ ተናግረዋል፡፡ አርቲስትና ሞዴል አምለሰት ሙጩ በበኩሏ ይህንን ሀላሀፊነት ከፍ ባለ አክብሮት እንደምትቀበል ገልፃ ከዚህ ቀደምም በተለያዩ አጋጣሚዎች ወደየሆስፒታሎች ስትንቀሳቀስ ከንፅህና ጋር ተያያዞ ጉድለቶችን በማየቷ በዚሁ ዘመቻ ላይ የተቻላትን ያህል እንደምትሰራ ተናግራለች፡፡

አምለሰት ቀደም ሲል በአካባቢ ጥበቃ ላይ የራሷን እንቅስቃሴ ማድረጓና በውበት ኢንዱስትሪ ውስጥ ባላት ተሳትፎ ሳቢያ ለዚህ ሀላፊነት መመረጧ ታውቋል፡፡

ምንጭ – ቁምነገር መጽሔት ከአዲስ አበባ

The post የቴዲ አፍሮ ባለቤት አምለሰት ሙጩ የሆስፒታሎች አምባሳደር ልትሆን ነው appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>