(ዘ-ሐበሻ) በዘፋኝነት; በሙዚቃ አቀናባሪነትና በሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋችነት የሚታወቁት ታዋቂው አርቲስት ሻምበል መኮንን መርሻ አረፉ::
በፖሊስ ኦርኬስትራ ውስጥ የትራንፔት ሙዚቃ ተጫዋች የነበሩትና “አደሉላ (የዘማች እናት)” በሚለው ታዋቂ ዘፈናቸው የሚታወቁት ሻምበል ወደ ሙዚቃው ዓለም ከመግባታቸው በፊት የወርቅ ሰራተኛ ነበሩ:: ሻምበሉ በአንድ ወቅት ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢ እንደገለጹት ወርቅ ሰሪነት የተቀጠሩት በወቅቱ 15 ብር ነበር::
ድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ዛሬ የተለዩት እኚሁ ባለጥምር የሙዚቃ ክህሎት ባለሙያ ሻምበል መኮንን ለሂሩት በቀለና ለተለያዩ የሙዚቃ ሰዎች ሙዚቃ አቀናብረዋል:: ለ50 ዓመታት በሙዚቃ ዓለም ቆይታቸውም በርከት ያሉ ሥራዎችን ሰርተዋል:: ሃመልማል አባተ ከሃረር መጥታ በአዲስ አበባ የሙዚቃ ሥራ እንድትሰራ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ትልቅ ሲሆን የቴዲ አፍሮ አባት አቶ ካሳሁን ገርማሞ የቴዲ አፍሮን እናት ባገባ ጊዜ ሚዜም ነበሩ::
የእኚሁ ታዋቂ አርቲስት የቀብር ስነስርዓት በኖሩበት ኮልፌ አካባቢ በሚገኝ ቤተክርስቲያን ነገ ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል::
ቭዲዮውን ይመልከቱ::
The post ለ50 ዓመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ትልቅ ሥፍራ የነበራቸው አርቲስት ሻምበል መኮንን መርሻ አረፉ appeared first on Zehabesha Amharic.