በአዲስ አበባ አቃቂ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የአረቄ ፋብሪካ የኢህአዴግ ባለስልጣኖች መሆኑን ያወቁ ሰዎች እንዳቃጠሉት ታወቀ።በአዲስ አበባ አቃቂ ክፍለ ከተማ የሚገኘው አረቄ ፋብሪካ ንብረትነቱ የከፍተኞች የኢህአዴግ አመራሮች የኩማ ደመቅሳና አዲሱ ለገሰ መሆኑን የተገነዘቡ ወገኖች ይህ ፋብሪካ በሃገርና በህዝብ ገንዘብ ተሰርቶ ለባለስልጣኖች ጥቅም ብቻ መዋል የለበትም በማለት ግንቦት 11/2007 ዓ.ም እንዳቃጠሉት የሚስጥሩ አዋቂ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ።
ፋብሪካው እየተቃጠለ በነበረበት ወቅት ሲመለከት የነበረው ነዋሪው ማህበረስብ፣ እሳቱን ለማጥፋት ምንም አይነት እገዛ ማድረግ ያለመቻሉን የተመለከቱት የስርዓቱ ካድሬዎች ወሮበላ ተከታዮቻቸውን በማሰባሰብ ነዋሪውን ህዝብ ማን አቃጠለው ከእናንተ አልፎ ሌላ የሚያውቅ የለም ተናገሩ እያሉ ላይና ታች ቢሉም እንኳን ነዋሪው ህዝብ ግን እኛ የምናወቀው የለንም የምታውቁት ካለ ደግሞ እናንተ ንገሩን በማለት ለጥያቄአቸው በጥያቄ መልክ በመመለስ ምንም አይነት መረጃ ከመስጠት እንደተቆጠበ ለማወቅ ተችሏል።
The post በአ.አ. አቃቂ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የተቃጠለው የአረቄ ፋብሪካ የኩማ ደመቅሳና አዲሱ ለገሰ ንብረት መሆኑ ታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.